ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
** #ይሰማኛል *

ይሰማኛል ኮቴ ከፈረስ ሽዎና
ወኔ ከጨበጠ ከጋላቢው ጀግና

ይሰማኛል ዜማ ሽለላ ቀረርቶ
ተደፈርኩኝ የሚል ንጉስ ቀንድ አውጥቶ

ይሰማኛል ፀሎት ከፅላቱ እንፋሎት
መስቀልና ጦርን ከያዙ መናኩስት

ብዙ ነገር ዘመንን ተሻግሮ ሲሰማኝ
ቅኔ ተቃኝቶ
ዜማ ዘምሞ
ደም እየመነጨ ነፃ ወጣ ሲለኝ
እኔ ግን አለውኝ ባርነት ናፋቂ
ባህልና ወጌን ከብራናው ፋቂ

አያቴ ነበረ ወንድሙን ወዳጅ
ተደፈርኩኝ ብሎ ጠላቱን አሳዳጅ
አያቴም ነበረች የወንድ ንፅር ጀግና
በጦሩ አውድማ ፀንታ የምታፀና

ታዲያ የእሳት ልጅ አመድ እኔ
ፍራቻዬ ስር ሰዶ ከወንድነት መቅኔ
ባዶ ድንፋታ አዋቂ ነኝ አዋጅ
ጉራ እየነዛውኝ በጠላት ቤት ሰጋጅ
ቁማር ብቻ! ዘራፍ! አሉባልታ
ሀገር አትሸጥም ትከራይ ጨዋታ

ወይ እኔ ወንዱ የሐበሻው ዘር
ጦር የፈራው እጄ ጋሻ ሲደረድር
ለጠላቴ አፈሙዝ ወንድሜን የምድር
እኔ አዲስ ጀግና ታሪኬን የምሰብር
ምናገባኝ ትላንት የግል ኪሴን እማሰምር
 
ይሰማኛል ትዝብት ደሞ ደግሞ
ሀገር ከቁርበት ላይ በጠናውም ታሞ
ጠባብ ልጆች ወልዶ ሰፊ አሳቢ ጠፍቶ
ሀገራዊ ፍቅሩ በመንደር ተሰፍቶ

ይሄን እንዴት ልየው እንዴት ይግባኝ ሀገር
ተሸንሽኜ እያየው በድንበርና ዘር
አርበኝነት ቅኔው ከየትስ ይሰማኝ
የሀገር ቀሚሷስ ደፋሪ እንዴት ይግባኝ
ወንድም ወንድሙን ገደለው እያሉኝ
እህት በእህቷ ላይ ዶለተች እያሉኝ
የሀገር ደሜ ሞቶ ለብሔር ቆሰልኩኝ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
:- #ተክለ_ዮሀንስ

@getem
@getem