ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
አያ ዘመድ ሁላ ሴት ልጅህን አክብር። ሴት ልጅህን ውደድ። Senedu Abebe መሃመድን
የመሰለች የፍቅርና የሰው መሆን ብእር ካዳሚ ባትገለጥልን ኖሮ የሙሉጌታ ተስፋየን ብእር
አናገኘውም ነበር።
ስንዱ መሃመድ፤
የሸህ ሙሌ አውገረድ፤
አንች ባትስቂ ፤
አንች ባትካድሚን፤
ይመጣ ነበር ወይ አውራድና መደድ???
ከጉባርጃ ማርያም፤
ከታች ቆላ አዳሜ፤
የቆለኛ ዛቱን ይዞ ለሄደ ሰው፤
መሃል አዲስአባ፤
ስንዱ ባትካድም፤
እንደምን አርጎ ነው ቅኔ የሚፈሰው።
አሁን የየጁ ሰው፤
አሁን የቃሉ ሰው፤
የስንዱን ነገር ቢሰማው በጀማ፤
እነየ ስንዱን፤
ያለብሳት አልነበር፤
የእህትነት ቦፌ የእናትነት ሸማ።
ልቅሶውን፤
ኩርፊያውን፤
ግፊያውን፤
እፊያውን፤
ገራገርነቱን፤
ፅናቱን፤
ስንፈቱን፤
ብክንክን ህይወቱን ፤
ከደፋበት መንደር ሂዳ እየለቀመች፤
ገጥመው ከዘረፉት ገጥማ እየነጠቀች፤
ድፍርስማ መልኩን ማቅናት የተካነች፤
ነፍስያና ልቧ ፤
ሃቂቃውን ከፍሏል ልክ እንደመይሳው እቴጌ ተዋበች።
ሙሌ ባይጨነቁር፤
ስንዱ ባትቆም ሁና መሻገሪያ፤
ሙሌም ጠፍቶ ነበር እንኳንስ ወልዲያ።
ባለውለታህን በአዋጅ ተቀበላት፤
ከጨው ሪጋ ሃውልት፤
የአያ ሙሌ ብእር ፤ ቀልቧን የሞሸራት፤
አደራ ጠባቂ ፤
የሰው መሆን ስንቁ ስንዱ አበበ ናት።
እንደናት፤
እንደእህት፤
እንደ ዳባሽ አጉራሽ ባትሆን ቀኝ ክንዱ፤
የት ይገኝ ቆየ፤
የአያ ሙሌ ትንፋሽ ቅኔና መደዱ፤
አቦ ሆድ ይመርቅ፤
አቦ በረካ ሁኝ ፤
የአቤ መሃመድ ልጅ ፤ አውገረድ ስንዱ።
በእውነት የ Senedu Abebe ውለታ በጣም ሆኖ ጠልቆ የገባኝ እጅግ ዘግይቶ ነው ።

(( ጃ ኖ ))💚💛

@getem
@getem
@balmbaras
የደከሙ ገጾች
__
(እዮብ ዘ ማርያም)
______
ልክ እንደ ለሊት ወፍ፣
ሲነጋ ይጨንቀኛል ሲነጋ አልወድም
ጨለማ ነው ሱሴ፣
ፍጡር ይከብደኛል ሰው አልላመድም

ከሰማዩ ምስራቅ ብረሀን ብቅ አለ
ከሙታን ጎዳና፣
ወደ ንቃት ጉዞ አለም ኮበለለ

እኔ ግን ከፍቶኛል
እኔ ግን ጨንቆኛል
የፀሀዩዋ መውጣት ሰላም ይነሳኛል

ሰው ወጋገን አይቶ
ዕንቅልፉን ሰውቶ~ማለዳ ሲነሳ
የኔ ቤት ምስኪኑ፣
በብርሀን ጨረር ጣሪያውን ተበሳ

ምስኪን በሆነ ቤት በተበሳ ጣራ
ካለቆች የሚዘንብ ሲገባ መከራ
ደም ስታስለቅሰኝ የዕድሌ ወፍ በራ

ማነው በምድሬ ላይ ብሶት ያመረተ
እንዳይወጣ አድርጎ ችግር የከተተ
ብዬ ብጠይቅም
ከጥያቄው በቀር መልሱ አይታወቅም

ምስኪን የሆነ ህዝብ ያልታደለ ሀገር
ድልድዩን ተነጥቆ በሞት የሚሻገር

አንዱ ያንዱ ገዳይ ምቀኛ ሸረኛ
ነገር ሲያብሰለስል በሌት የማይተኛ

በፈጣሪ ፀጋ፣
ባህር ላይ ስራመድ የሚያዩ ሁሉ
ከመገረም ይልቅ፣
ዋና አይችልም ብለው ለሰው ያወራሉ

አለም የጥል ቦታ አለም የጥል መሬት
መኖር ሲሰለችህ ሲመርህ እንደ'ሬት

ዙሪያህን በሙሉ
የነበረህ ሁሉ
ባይን ጥቅሻ ፍጥነት ሲሆንብህ ኦና
ምንስ ቀረኝ ብለህ በምንህ ትፅናና?

የግፈኞች ኮቴ፣
ከትቢያ ላይ ጥሎህ ሲረግጥህ እንደ ትል
አይንህ ዕንባ አቅርሮ፣
አንገትህን ደፍተህ ሀሳብ ስትፈትል
አለም ፎቶ ቤት ናት፣
ሀዘንህን ትተህ ፈገግ በል የምትል

አሁንስ አቃተን፣
ቅስማችንን ሰብሮ ኑሮ አንገዳገደን
ፈጣሪ ሆይ ባክህ፣
ወይ አንተ ቶሎ ና ወይ እኛን ውሰደን፡፡

For any comment

@getem
@getem
@eyob567
#4
ለመንግስት የተፃፈ ደብዳቤ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
መልእክት እንዳናደርስ ፣ በስልክህ አፍ በኩል
ወይ ሜሴጅ እንዳንልክ ፣ ወይ እንዳንመሰኩል
ቁጥርን አናውቅም ፣ እንዳንደውልልህ
ገዳይ ጉዳይ ሲሆን
መልእክት እንዳንተው ፣ የለንም ኢሜልህ
ቢጠበን ቢጨንቀን
ተገቢ ባይሆንም
በኢንተርኔት ዘመን ፣ ደብዳቤ ፃፍንልህ።
።።።
እንደምነህ መንግስት እኛ አለን በደህና
ባመቻቸህልን የለውጥ ጎዳና
የቀን ጅቦች ሲያልፉ
ከቀን ጅሎች ጋራ ፣ ለሞት ተሰልፈን
"ወያኔ ሌባ" እያልን ፣
እየተገፋፋን ፣ ኪሳችን ተዘርፈን
እኛ አለን በተድላ
በቀን ሶስት ጊዜ
ቁርስ ፣ ምሳና ራት ፣ስጋት ስንበላ
ያንተ ደህንነት ነዉ እኛን ሚያስጨንቀን
ተደመሩ ብለህ ፣ ምታስጨፈልቀን
ትእግስት እያበዛህ ፣ ምታሸማቅቀን
ቀልድ ቁም ነገርህ ፣አመት የሚያስቀን
እንደምነህ አንተ ፣
በፍቅር ስብከትህ ፣ የምታቀልጠው ልብ
ትእግስትህ ረቂቅ ፣ ቁርጠኛነትህ ግልብ
ከንብ መንጋ ወጥተህ ፣ የማትናደፍ ንብ
ጧት ማታ ማትሰለች
ሰላም ፍቅር ብለህ ፣ ፀበኞችን መምከር
ከልምጥምጥች ጋር
ከምትለማመጥ ፣
ከአሸባሪዎች ጋር ፣ ከምትከራከር
ለምን አትቆርጥም?
መቼም ደም ለጠማው ፣ ውሃ አይሰጥም
ጳጳሶች አልቅሰው
ሼሆች እንባ ለብሰው ፣ ህዝብ አይገለፍጥም
አቦ አስፈጀኸን
ሚቀለጥሙንን ፣ ቀልጥም ወይ አስቀልጥም።
።።።።

እንደ ምነህ መንግስት እኛ አለን በደህና
ባመቻቸህልኝ የለውጥ ጎዳና
እየተጠቀምን
እንደ ባህር እንቁ ፣ ሟች እየለቀምን
አለንልህ ሰግተን ፣ አለን ለሞት ታጭተን
እንደምነህ አንተ
ፍቅር ፍቅር እያልክ ፣ ምታስፈነክተን
ትእግሰት እያበዛህ
የህዝብህን ትግስት ፣የምትፈታተን
ፍትህ ስንጠይቅ ፣ መግለጫ ምትሰጠን
አንጥረኛን ለቀህ
እኛን እንደብረት ፣ ምታስቀጠቅጠን
አንተ እንደምን አለህ ፣ እኛ አለን ያለ አድሎ
አንድ ሰው ሲከበብ ፣
ሺህ በመንጋው ሞቶ ፣ ሺህ በመንጋው ቆስሎ
አለን ተደምረን
በሰጠህኸን እድል ፣ ኢትዮጵያን አፍቅረን
የማይመጣን ፍትህ
የማይመጣን ሰላም
የማትመጣ ለውጥን ፣በአንድ ላይ ቀጥረን
"ይመጣሉ" እያልን ፣ እንጠብቃለን
አንተ ግን እንዴት ነህ?
አንተ ደህና ከሆንክ ፣ እኛ ስንሰጋ አለን።

እንደምነህ መንግስት እኛ አለን በደህና
ባመቻቸህልኝ የለውጥ ጎዳና
እየተሰበርን "ሰበር" በሚል ዜና
በዘር በዘር ሆነን ፣ እየተደራጀን
የማይተገበር ፣ ህግ እያዘጋጀን
መንገድ ሲዘጋብን...
እግረ መንገዳችን ፣ ህግጋት ተላልፈን
ከደብዳቢ ጋራ
ደብዳቤ እስክንልክ፣ በደማችን ፅፈን
እየተደበደብን ፣ እኛ አለን በተድላ
እንደምነህልን?
እንደምነህልን ካልንህስ በኋላ?!
እኛ አለን በድሎት
ከገዳያችን ጋር ፣ ቀብር ስናስፈጥም
ስንኖር ኢትዮጵያዊ
ስንሞት ምን እንደሆንን ፣ ባናረጋግጥም
እኛ የምንልህ
"ጥላቻ የጠማው
ፍቅርን ቢግቱት ፣ ጥሙ ከቶ አይቆርጥም
አቦ አስፈጀኸን
ሚቀለጥሙንን ፣ ቀልጥም ወይ አስቀልጥም!
።።።።
እንደምነህ መንግስት
እኛ አለን በስጋት ፥ አንተን ስንነቅፍ ፣አንተኑ ስንደግፍ
ባይቀርልን እንኳ ፣ ይቀራል ያልነው ግፍ
አለን ተደምረን ፣ አለን ተደናብረን
ሀገር ክንፍ አውጥታ
መብረር እንድትችል ፣ እግራችንን ሰብረን
የአንዲት ኢትዮጵያን
ትንሳኤዋን ልናይ ፣ ነፍሳችን ገብረን
አለን ስናነክስ
አለን ስናለቅስ ፣ መኖር እያማረን ።
።።።
እናም የምንልህ
ለውጥ ነውጥ ይዞ ፣ ከመጣ በኋላ
ጥላቻ እንደ ጥላ
ብለን ነበር ያልፋል
ነገር ግን እያደር ፣ጭራሹን ይገዝፋል።
እርግጥ ነው
እውነት ነው
ካምናና ካቻምና ፣ ስናነፃፅረው
በገፍ እና በግፍ ፣ ግፈኛ ያሰረው
ብዙ ሰው ተፈቷል ፣
ኢትዮጵያ ሚለው ስም ፣ ሺህ ጊዜ ተጠርቷል
በጥቂቱም ቢሆን ፣ ተቀርፏል ጭቆና
የማይሆነው ሳይሆን ፣ የሆነው ሆነና
ለውጥ ነውጥ ሆኖ
ከመጣ በኋላ ፣ ስጋት ተባብሷል
የምናውቀው አይጥ ፣ የአንበሳ ለምድ ለብሷል
ሀገር ሀገር ቢሉም ፣ ዘረኝነት ነግሷል
በዝቷል ማፈናቀል
በዝቷል የመንጋ ፍርድ ፣ ተበራክቷል በቀል
ይቻላል ቀላል ነው
በጠራራ ፀሀይ
ሰው በድንጋይ መውገር ፣ ሰው ዘቅዝቆ መሥቀል።
።።
የለም አስታራቂ ፣ የለንም ይቅር ባይ
ዛሬም ሰው ይሞታል ፣ በቀን ባደባባይ
ዛሬም ቁጭት አለ ፣ በነጠላ ጫፍ ላይ።
።።
አገገምን ስንል
አልተገላገልንም ፣ ህመሙ መርቅዟል
በሶ አትብሉ ብሎ ፣ አበበ አውግዟል
ጫላ ጩቤ ጥሎ ፣ ስናይፐር ይዟል።

እኛ የምንልህ
በተገዳዮች ፊት ፣ ገዳይ ካስታመሙ
በተበዳዮች ላይ ፣ በዳይን ከሾሙ
ምንድነው ይቅርታ
ምንድነው ምህረት
የመደመር ሀሳብ ፣ ምንድነው ትርጉሙ ?
ምንድነው እዚ እዛ ፣ ሰው ሚፈናቀለው
ምንድነው እዛ እዚህ ፣ ሰው የሚገደለው
ሚንዲኖ ፀጢታው ፣ ሚንዲኖ ሁካታው
ምን አይነት ፂድቅ ነው
ቀኝ ጉንጪን መስጠት ፣ ግራ ለሚማታው
ፍቅር ለማይገባው
ስለ ፍቅር ብሎ ፣ መታገስ ምንድነው?
ጊራ ጉንጪን ላለ
ግንባር ቀደሙ መልስ ፣ ጊምባሩን ማለት ነው።
እውነታችንን ነው!!!
።።።።።።።።
እንደምነህ መንግስት ፣ እኛ አለን በደህና
ባመቻቸህልን ፣ የፍቅር ጎዳና
ሞት እየደገስን
ተገነቡ ሲባል ፣ እየፈራረስን
ተደመርን ስንል ፣እየተቀነስን
እየተጓተትን ፣ በዘር ጅኒ ጃንካ
ዛሬ አለን በስጋት
ነገ ሚሆነውን ፣ ዋቀዮ ሲቤካ።
።።።
እኛ የምንልህ
ከካቻምና በፊት
የነበረን ገዢ ፣ ካቻምና ወቀስን
አምና ስልጣን ያዝን
የካቻምናዎችን ፣ ደም እያፈሰስን
ዘንድሮ በብልሀት ፣
ስልጣን ሀክ አድርገን ፣ ዙፋኑን ወረስን።
ሰይጣኑ ሳይጠፋ
ስልጣኑን ቢይዙት ፣ መች እኛን ፈወሰን
ደም የጠማው ወንበር
በመደመር ማግስት ፣ ደንብሮ ጨረሰን።
እናም የምንልህ
በፍቅር ሲጠመቅ
አልለቅም ያለውን ፣ ፀብ መጥመቅ ያዋጣል
አንዳንዴም አጋንንት
አጋንንቱን ስቦ ፣ በአጋንንት ይወጣል ።
።።።።።
እንደምነህ መንግስት ፣ ስልጣንህ እንዴት ነው
ፍቂርና ምህረት፣ በእርግጥ ጥሩ ነው
ግን ደሞ ግን ደሞ
ሲበዛ ዪመራል ፣ ኣይደለም ተገቢ
ኢንኳንስ የሀገር ገዢ
ግፍን ለሚያበዛ ፣ አዪራራም ረቢ።
።።
እናም የምንልህ
ተገነባን ሲንል ፣ የሚንደን ቶሎ
ተደመርን ስንል ፣ የሚያጎድለን ጎድሎ
አልጠግብ ላለ አካል
እንባ ደማችንን ፣ ላባችንን መጦ
ለሱ ሰላም ሲባል ፣ ህዝቡን አበጣብጦ
ለመኖር ለሚጥር ፣ ሀገሩን በታትኖ
ሆዱን ለሚያሰፋ ፣ ጥላቻን በትኖ
ፍርድ ካልተሰጠው ፣ ምህረት ምንድኖ
ይቅርታ ምንድኖ
የመደመር ሀሳብ ቲርጉሙ ምንድኖ?
።።።
እናም የምንልህ
እሾህ በእሾህ እንጂ ፣ በእሹሩሩ አይወጣም
ፍቅር ያልገባውን
በሚገባው ቋንቋ ፣ ለምን አትቀጣም?
ከእንግዲህ በኋላ
የጨለመበት ህዝብ
ፀሐይ ለሰረቀው ፣ ሻማ አያዋጣም!!!

በመጨረሻም #ሼር በማድረግ ደብዳቤውን ለመንግስት አድርሱ😁


@getem
@getem
@getem
1
የየጁ ዝየራ!!!!


በቅኔ ሙሃባ፤
በሰማይ ዋሪዳ፤
ተቀብተን ነበር፤
ከዳና እስከ ሾንኬ ቅኔና ዝየራ፤
ከጅለን ነበረ፤
ደረቅ ብእር ይዘን ህይወትን ፍጀራ፤
አዳ ምን ዋጋ አለው፤
ወደ ዃላ ሳበን ፤የማይረባ እንጀራ።


እንደሙሉጌታ፤
ተሰጥተን ነበር፤
የቅኔ ብርሃን ጨለማ የሚያነጋ፤
አስሮ ያዘን እንጅ፥
በየጉራንጉሩ እንጀራ ፍለጋ።
ሸጋው አያ ሙሌ፤
ይሰማችሁ እንደሁ፤
ጠይቁልኝማ አደራ እባካችሁ፤
ስጋ እየጨቆኑ፤
ለነፍስያ ማደር እንዴት ነው ብላችሁ።
ለስጋ ገበያ አልጠፋም እንጀራ፤
ለነፍስ መቃተት፤
ቀረ እንጅ ያን ጊዜ በነሙሌ ጎራ።
አንች ጨው ሪጋ ሙጋድ ረግረጉ፤
ሙሌ ምን ብሎሻል፤
ስለ ነፍስያ ስንቅ ያኔ ስታወጉ???
ለነፍስ ነው እንጅ ጥማትና ራቡ፤
ስጋማ ሞኝ ነው፤
ቆሎ የበላ ቀን ጋብ ይላል ራቡ።
መገን መነካት!!!!

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

@getem
@getem
@balmbaras
ስንኖር

በተቀደደ ነው ለሸማ ፀሎቴ
በተሰበረ ነው ምኞቷ ጎረቤቴ
እሷም መርፌ ሻጭ ነች እኔም ልብስ አሰፊ
ማሰበር ነው ትርፏ ማስቀደድ ነው ትርፌ

@getem
@getem

#Rebika sisay
…ኢሪስ ጤፋ…
[አብርሃም የሙሉ]

ሰላም ሲናፍቀኝ፤ ሰላምን አቅፌ
ሰላም የሚል ግጥም፤ ተሸብሬ ፅፌ
የአንገቴን ሜንጫ፤ የግንባሬን ጥይት
በአይኔ እያየሁ፤
ሰላም ነኝ እላለሁ፤ ሰላሜን በግምት።

ሰላም ናቹ?😭
።።።።።።።
እምነት ማህተቤን
ባህል ማንነቴን
እንድኖር ቀይሬ፤
ሀገሬን ስጠየቅ፤ በገንዛ ሀገሬ
ጓዜን ጠቀለልኩኝ፤
ሀገሬን ልፈልግ፤ ከሀገሬ ወጣሁኝ😭
።።።።።።።።።
ሁለት መሪ ያላት፤ ነበረኝ አንድ ሀገር
ያንዱ አመል መጣላት፤ ያንዱ እውነት መፋቀር
ያንዱ ግራ መርዶ፤ ያንዱ ቀኝ ተስፋ
ህዝብ ሀገር ተጣቦ፤ አንዱ ብሄር ሰፋ።
።።።።።።።።።
ታሪክ በሬሳ ላይ፤ እየተራመደ
አንዱ እንዲከበር፤ ሺ እየተዋረደ
ሰላም ይሰበካል፤ በመሪ መቃዠት
ቀን ይወጣል ሲባል፤ በቀን፣ በቀን መሞት።
።።።።።።።።
ለማውራት ያክል ነው፤ እኔ እንኳን ደህና ነኝ
አብይ ሲያደማምረኝ፤ ጃ-ዋር ካልቀነሰኝ
i mean
የዘንድሮ ድምር፤ መቀነስ መሰለኝ🤔

@getem
@getem
@yemulu_lij
1
ሀገር
ስንኖር እምትኖር ስንሞት እምትኖር
ነበር እኔ ሳቃት ያች ቆራጥ ሀገር
ከፊሉ ሲያጠፍ ከፊሉ ሲመክር
ከፊሉ ሲሰራ ከፊሉ ሲዘክር
ነበር እኔ ሳቃት ያች ጀግና ሀገር

የፊቱን በታሪክ ኣልፈነው መተናል
ግጭት ኣቀጭጮን እንዲሁ ከስተናል
መድሀኒት እንዳንል ምን ይበጅልናል
በመፋቀር ፈንታ ጠቡ ጌጥ ሁኖናል
ታሪክ እያወራን ስራን ረስተናል
በማይበጀው ደሞ ዘርጎሳ መርጠናል
አንድ ሀገር ይዘን ዘሩ በዝቶብናል

ዘር መብዛት ካልሆነን ጉልበት
ይቅር የታባቱ ኣንዱስ ጠፍቶብናል
ግን ግን
ሀይማኖትስ የታል ቃሉ ያስተሳሰረን
ያንዱ ስራ ላንዱ መች ኣቀባበረን
ሙስሊም ኣዛን ሲያረግ ቄሱ ሲያመሰግን
ሰላም ላሳደርከኝ ብሎ ሳይጨርሰው
ከመስጅድ ይመጣል እንድ ከይረኛ ሰው
እንዴት እደሩ ኣባ ብሎ ሳይጨርሰው
ሰላም ለኩሉ ይላሉ መልሰው

የት ገባ ያትውልድ እማያንቀላፋው
ሀገሩን ሚጠብቅ ዘሩ ማይሸውደው
የት ገባ ያ ትውልድ ማይንበረከከው


የትስ ነው መገኛው ያ ሀገሩን ወዳጅ
ገና በመጠርያው የጠላት ልብ ኣንጓጅ


ከድር

@getem
@getem
#ቀንዲል የጥበብ ምሽት ምርጥ ገጣሚያንን...ከድንቅ የተውኔት ባለሙያዎች እና ልዩ እንግዳ ጋር አዋህዶ እሮብ ጥቅምት 19 ጉርድ ሾላ በሚገኘው ቶፕ 10 ሆቴል እያዝናና ቁምነገር ሊያስጨብጣችሁ ዝግጅቱን ጨርሷል ።

መግቢያ ፦ 50 ብር

አዘጋጆች ፦ ሚካኤል አስጨናቂ ከአብርሀም ታደሰ ፕሮሞሽን ጋር በመተባበር
እምነት!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።
ከእልፍ የቀለም ቀንድ ፥ መጥሀፍ አዋቂ
አንደበተ ርቱዕ ፥ ቃላትን አርቃቂ
ወጎች ተነጥላ.. .
ሽሙጥ ቧልታቸው ጫንቃዋ ላይ አዝላ
መሬት የወደቀች ...
በእንባዋ ተማፅኖ ፥ ይቅር በለኝ ብላ
የእየሱስን እግር በጠጉሯ ያበሰች
አንዲት እንስት አለች!
።።።።
ወዲያ ማዶ ግድም.. .
መጎተት አዝሎት ፥ ሰንፎ የማይለግም
አንድ አባት ይጮሀል ፥ ድምፁን አሰምቶ
ልጄን ማራት ይላል ፥ መሲሁን ተጣርቶ
።።።።
ደግሞ ሌላ እናት.. .
የመንጋው ሁካታ ፥ ግርግር የረታት
ደዌዋን ልታሽር ፥ በአማኑኤል ሸማ
እጇን ዘርግታለች ፥ ከጠርዝ ዳር ቆማ
።።።።።።።
ኢየሱስ ዞር አለ !
በዛች በቀድሞ ሴት ፥ ሀፍረት ተሸብበው
ሀጥያተኛ ሳለች ፥ ዝም ያላት ለምን ነው?
ብለው ለመጠየቅ እያጉረመረሙ
በእምነቷ መዳኗን ተናግሯቸው ሰሙ።
።።።።።።።።።።
ደግሞም ወዲያ ግድም
ልጅህ ስለሞተች መምህሩን አታድክም
ብለው የሚመክሩ አዋቂዎች ቆመው
ሙት ልጁ ተነስታ ጉንጮቹን ብትስመው
እነርሱ አፈሩ ፥ ከእምነት ተናንሰው ።
።።።
ያቺም አንዲት እናት.. .
መጮህ ባትችልም ፥ ማረኝ ማረኝ ብላ
ፊቱ ባትቆምም ፥ በግፊያ ተሽላ
ሸማውን ስትነካ ፥ ምህረቱን ዘርግቶ
ደዌዋን ሽሮታል ፥ ስር እምነቷን አይቶ ።
።።።።
ኢየሱስ ዞር አለ !
ከስቅለቱ በፊት ፥ ከስሩ የማይርቅ
ህጉን እያፀና ፥ ምግባሩን የሚያርቅ
የእግሩ ስር ተማሪ ቶማስ ተጠራጥሯል
መዳፉን ሊዳስስ እጆቹን ዘርግቷል
ዳሰሰ መዳፉን!
እሳት አነፈረው የዘረጋው እጁን...
ቶማስ ማረኝ አለ ፥ ዳግም ምህረት ሽቶ
ጌታችን አነፃው ፥ ይቅርታውን ሰጥቶ
ደግሞም ለማስረጃ ፥ አንድ ሀቅታ ሊተው
ገፄን ያልዳሰሱኝ ፥ እኔን ተጠራጥረው
በቃሌ የሚያድሩ ፥ መፈተንን ትተው
ሳያዩ የሚያምኑ ፥ ብፁአኖች ናቸው
ብሎ ተናገረው !

@getem
@getem
@getem
ሁሉ በእርሱ ሆነ?

ደግ ደጉን እንጂ ክፉን መች አረገ
ሰላምን ነው እንጂ ጥልን መች ፈለገ
አብዝቶ ቸረ እንጂ ፍቅሩን መች ነፈገ
ታዲያ ውሉ ምኑ ላይ ነው ሁሉ በእርሱ ሆነ ብሎ መዘመሩ
ስራዉን አርክሶ ስሙን ግን ማግነኑ
ለክፉም ለደጉም ጌታን መኮነኑ።

@getem
@getem
@gebriel_19

ከ yafet
ከጎራው ላይ ቆማ፤
ከዛፉ ላይ ሆና፤
እረ ተዋጉልኝ፤
ኧረ ተናቸፉ፤ አለች አሉ አሞራ፤
እኛ ስንሞትላት እኛ ስንዋደቅ እሷ ልትበላ።
ሞኚሺን ፈልጊ፤
በዱኣ በመደድ፤
ክንፍሽን፤ሰብረን ነው የምናሳድብሽ ከእንግዲህ በዃላ።

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

@getem
@getem
@balmbaras
#ቀንዲል

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።።።

መጣች አሉኝ ደግም !

ቀኔ ላይ ፅልመቷን ፥ እንዳልነበር ጥላ

ላምናው ልምምጤ ፥ 

መልሷን ለማበደር ፥ እንዳላለች ችላ

ንፁህ ነኝ ለማለት እጇን ውሀ ነክራ 

ለመናኙ ልቧ

የደፋችውን ቆብ ፥ ስፌቱን ተርትራ 

በከተማው አጀብ.. .

አሸወይና ልትል ፥ ዳግም ተሞሽራ

መጥታለች ይላሉ.. .

ያቺ ለምዳም ተኩላ ፥ የዋሁ በግ ነኝ ባይ

መጥታለች ይላሉ.. .

ያቺ ቄሳሪያዊ ፥ ባለ ጭንብላም ቄስ ፥ የመሲህ አታላይ

መንታ ጥያቄዋን ልትዘነዝር ቀርባ 

ረጭታ ልትጮህ የአዞንቷን እንባ

በቀል ባጀገነው

ሽንፈት በማያውቀው 

አጥፍቶ ባፈረ ፥ ባደፈ ህሊና

እውነቷን ልትቀብር ፥ እሳቱን አዳፍና

መታለች ይላሉ

እንዲህ ያወራሉ ... 

በበደሏ ቆስሎ ለላላው አንጀቴ ነገር ይፈትላሉ። 

።።።።

እኔም ደግሞ እላለሁ!

መምጣቱንስ ትምጣ

የመሸገችበት ጥሻውን ገላልጣ

ቀርባም ትናገረኝ.. .

በዳይ ነህ ትበለኝ.. .

እንባዋንም ታፍስስ ፥ ደረት እየደቃች ፥  ያለ ስስት ትዝራ

ጨለማ ሲኖር ነው ... 

የቀንዲሌ ፋኖስ ፥ አልነግቶም እያለ መንገድ 'ሚያጠራ

@getem
@getem
@getem

👇

።።።። የቀንዲል የጥበብ ምሽት መዳረሻ ስራ ነች ።።።።።

(ነገ ...ረቡዕ.. .ጉርድ ሾላ top10 ሆቴል ከ11፡00 ጀምሮ ....መግቢያ 50 ብር ነው ጓዶች ...ሼር ይደረግ) 
ለውብ ቀን!
💚




///ህዳር ሆይ///

አደይ አበባዬን...
ከመስቀል ወፍ ጋራ አንድ ላይ ጠቅልዬ
መስከረምን ተውኩት
ለእንቁጣጣሽ ብዬ ለመስቀል ነው ብዬ
ጥቅምትም አበባየማር የእሸት ወዙ
ጸጋውን ተፈጥሮ የሰጠው በብዙ
ህዳር ወር ነው የኔ ህዳር ህዳር ህዳር
የወራቶች ንጉሥ
የኔ ብቻ ፅደይ የኔ ብቻ መኽር
ህዳር ህዳር ህዳር
ከሰው ተሰውረን ካድባር ቅየው ጠፍተን
እኔና እሷ ብቻ እኔና እሷ ሆነን
ዞማ ፅጉሯ መሃል አበባ ሰክቼ
እርብትብት ከንፈሯን ጉንጮቿን ነክቼ
እኔና እሷ ብቻ እኔና እሷ ሆነን
አሁን አሁን አሁን
ህዳር ህዳር ህዳር
ከለምለሙ ሜዳ ከዛፎች ጥላ ስር
ፍቅር ስናወራ ፍቅር ስንዘምር
በጀርባችን ሆነን መሬት ላይ ተኝተን
ጨፌ ተንተርሰን በጤዛ ረስርሰን
በንብ ዜማ ዘመን ቢራቢሮ ይዘን
ህዳር ህዳር ህዳር
አሻግረን እያየን ጽንፍ የለሹን ሰማይ
እጄ ከወገቧ አንገቷ ክንዴ ላይ
ዝንት አለም አንድ ሆነን መቼም ላንለያይ
ከአይኖቻችን መሃል አይኖቻችንን ስናይ
ህዳር ህዳር ህዳር
ደግሞ እንደልጅነትሽ አባሮሽ ጨዋታ
በድንገት ስትሮጥ ከሜዳ ተነስታ
ለስለስ ያለው ንፋስ
ቀሚሷን አንስቶ ሸሚዟን ከፋፍቶ
ገላ ስር መአዛ ያንገቷ ስር ሽቶ
እኔነቴን ሲያውድ ከንፋስ ተጋብቶ
ልይዛት ስነሳ ላባርራት ስሮጥ
ሳር ሃረጉ ጠልፏት መሬት ላይ ስትቀመጥ
ባየር ተንሳፍፌ ቀዝፌ ስይዛት
መያዙ ሳይበቃኝ ደግሞ አጥብቄ ሳቅፋት
ማቀፍ ሳያጠግበኝ ከንፈሯን ስስማት
ትንፋሽ እያጠራት
ሲቃው እያነቃት ደስታ እያሳበዳት
ዐይኖቿን ጨፍና አንገቴ ስር ገብታ
ያን ቀን ቀኑ ሲመሽ ያን ቀን ወደ ማታ
ብቻዋን የሆነች ጨረቃዋ ቀንታ
ህዳር ህዳር ህዳር
ፍቅር ከሆነች ጋር በፍቅር ስንሰክር
የቀኑ ሳይበቃን በለሊት ስንዞር
ማንም አያክላት ምንም የላት አቻ
ከሷ ጋር ሆኜ ከሷ ጋራ ብቻ
እግዜሩ ደስ ብሎት
አምሳለ መላእክትን እርግቦችን ልኮ
ዜማ እየወረደ ቀድሶና ባርኮ
ደግሞ ሌላ ህይወት ደግሞ ሌላ ዘመን
ደግሞ ሌላ ዓለም ደግሞ ሌላ ሆነን
ምሳሌ እንድንሆን ፍቅር እንዲፅና
ደጋግመህ ደጋግመህ ህዳር ሆይ ቶሎ ና!!!

(በሰለሞን ሣህለ)

#እስቲ ግጥሟ ደስ ስለምትል በድምፅ እንሞክራት

@getem
@getem
@balmbaras
Hello hello dear Visual artist & art lover(families)it's Utopia visual arts club first motivational Program with guest speaker our member & passionated street photographer kidus abera (@KidusA16).

At  4 kilo kidus plaza Addis Ababa culture & tourism bureau hall.(in front of wow burger)

 🗓 Friday Nov.1 (hidar 21)
🕥11:30(local time)

Entrance free

For more info.
+251984871096 (Natnael fikru)


ART FOR CHANGE!


@UTOPIAVISUALARTS
\\_ለምን ሞተ? (ሞት ማንን ገደለ?)_//
በታሪኩ ገላሼ(ዘሩባቤል ዘወርቅያንጥፉ)

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡☜☞፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ንሰሃ ከመግቢያ - ቤተ-እምነት በአፋ፡
እርቃኑን ተሰቅሎ - እራሱን ያጠፋ፡
አንድ የሆነ ምስኪን - ድሃ አደግ ወጣት፡
በለተ ሰንበቱ - ሊያውም ደግሞ በጥዋት፡
ማን አበሳጭቶት ነው - በማንስ ቢቆጣ?
ምን አነሳስቶት ነው - ነፍሱን የሚያወጣ?
ለማን ተናዞ ነው - እራሱን የሚቀጣ?
ለኑዛዜው መቁነን - ራሱን እንዲሰዋ፡
ማነው ያስጎነጨው - መሪር የሞት ፅዋ?
ሊያውም ቤተስኪያን ፊት - ካልጠበበ ስፍራ፡
ካላጣው ዛፍ ሁሉ - ሊያውም መርጦ ወይራ፡
ምን አይነት ቅኔ ነው - ውስጡ ጥምዝዝ ነገር የስርየት ግራ?

ለኪዳን ያልመጣ - ለቅዳሴ ያልወጣ
ወሬ ሊቀላውጥ - የግዜር ደጅ የመጣ
ቀላዋጭ ምዕመን - አማኝ ኢአማኙ አስክሬኑን ከቦ፡
ሀጥያቱን በሀጥያት - ስተቱን በስተት መተንተን አስቦ፡
እንዲ ሲል ይሰማል!
ልክ እንደ ይሁዳ ትላንትና ማታ
ስሞ ሰው ሸጦ ነው፡
ለቀባሪ ስራ ለማቃለል ብሎ ቅርበቱን መርጦ ነው፡
ሌላ ጋ ገድለውት ራሱ ነው ለማስባል
እዚ ሰቅለውት ነው፡
እንዲህ ነው እንዲያ ነው፡
እያሉ ሲያወሩ እርግጠኞች ሆነው፡
እልፍ መላምቶች - ሽቅብ ሲያናፍሱ፡
ከሞተው ሰው በላይ - ገረሙኝ እነሱ፡፡

ይህ በንዲህ እንዳለ፡
አንቀፅ እያወሱ - ገፅ እያጣቀሱ፡
ህግጋትን ሁሉ - ሟች ስለመጣሱ፡
ያድራጎቱን ነገር - ሀጥያት ለማድረግ ሲጣደፉ ገርሞኝ፡
ከመሞቱ በላይ
ከአሟሟቱ ይልቅ - የሞቱ መንስኤ ማስገረሙ ገርሞኝ፡
መሃላቸው ሆኜ እፈላሰማለሁ እኔም ልክ እንደሞኝ፡፡

ለምን ብሎ ሞተ?
ለማን ብሎ ሞተ?
በ ፫ ብር የአይጥ መርዝ ቅንጡ አሟሟት መሞት እየቻለ፡
በ ፳ ብር ገመድ ለምን አስከፊ ሞት መጎንጨት ከጀለ?

እንደው ከመጣ አይቀር
ቤተስኪያን ደጃፍ - ባደረሰው እግር፡
ምናል በምላሱ - የበደሉን ነገር ላምላኩ ቢነግር፡
እላለሁ ቢቸግር፡፡
ሰው ራሱ በራሱ - መጨከን ከቻለ፡
ጠንከር ያለ ነገር - በስተኀላው አለ፡
እላለሁ በውስጤ - ሞቱ እያቃጨለ፡

ምናልባት ይህ ምስኪን - ይህ ደሃ ሰውዬ፡
ፍትህ አልባ በሆነች - በዚች በኛ ቀዬ፡
ምን አይነት ኑሮ ውስጥ እንዴት እንደቆዬ፡
ተከትቦ ያለ በድህረ ታሪኩ የመጨረሻ ቃል፡
እንዲ ሚል ይሆናል
ነፃነት በነፃ ማግኘት ለናፈቀ ሆዱ ለባሰው ሰው፡
የ፳ብር ገመድ መግዛት ለማይችል ሰው፡
የ፫ብር ያይጥ መርዝ - መግዛት እጁ ለሚያጥር - የደሃ ደሃ ሰው፡
በተውሶ ገመድ
በተውሶ ሰፈር
በተውሶ አድባር
ራሱን እያፅናና "ሞት ማንን ገደ" በሚሉት ስነ-ቃል፡
እራሱን መግደሉ ለምን ያስደንቃል?
ለምን ሞተ ተብሎስ ለምን ይጠየቃል?
እንዴት ሞተ ተብሎስ እንዴት ይጠየቃል?
እንዴትም ይፈፀም አበቃ ሲልኮ የዛኔ ያበቃል፡፡
እንኳንስ የነፍስን የስጋን ጥያቄ መመለስ ላልቻለ፡
ለቆመው ነውዪ ሞት መፍትሄ ማይሆነው ፅዋው ላልጎደለ፡
ለተከፋውማ
ለተገፋውማ
ጥያቄውም መልሱም ሞት ማንን ገደለ?
በሌላ አገላለፅ!
በመኖር ውጥንቅጥ
ጥያቄ ሲያነሳ እየጠፋው መልሱ
ጥያቄ ሲረሳ ሲመጣለት መልሱ
የህይወት ድብልቅልቋ ብቻ ለሚተርፈው፡
ላለመኖር ሰንፎ ለሞተ ሰውኮ
መሞቱ በራሱ የሁሉም መልስ ነው፡፡

እናም እንኳን ሞትኩኝ!
ከሞትኩም በኀላ ደግሞ አትነካኩኝ፡
ከሞት ለመመለስ ነውና በአርምሞ ጥያቄ እየጫርኩኝ፡
ግን ግን ለምን ሞትኩኝ?"
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ተፃፈ ጥቅምት ፩፯, ፳፻፲፪ ዓ.ም
አዳማ, ኢትዮጵያ
----Edited----
\\_ለምን ሞተ? (ሞት ማንን ገደለ?)_//
በታሪኩ ገላሼ(ዘሩባቤል ዘወርቅያንጥፉ)
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡☜☞፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ንሰሃ ከመግቢያ - ቤተ-እምነት በአፋ፡
እርቃኑን ተሰቅሎ - እራሱን ያጠፋ፡
አንድ የሆነ ምስኪን - ድሃ አደግ ወጣት፡
በለተ ሰንበቱ - ሊያውም ደግሞ በጥዋት፡
ማን አበሳጭቶት ነው - በማንስ ቢቆጣ?
ምን አነሳስቶት ነው - ነፍሱን የሚያወጣ?
ለማን ተናዞ ነው - እራሱን የሚቀጣ?
ለኑዛዜው መቁነን - ራሱን እንዲሰዋ፡
ማነው ያስጎነጨው - መሪር የሞት ፅዋ?
ሊያውም ቤተስኪያን ፊት - ካልጠበበ ስፍራ፡
ካላጣው ዛፍ ሁሉ - ሊያውም መርጦ ወይራ፡
ምን አይነት ቅኔ ነው - ውስጡ ጥምዝዝ ነገር የስርየት ግራ?

ለኪዳን ያልመጣ - ለቅዳሴ ያልወጣ
ወሬ ሊቀላውጥ - የግዜር ደጅ የመጣ
ቀላዋጭ ምዕመን - አማኝ ኢአማኙ አስክሬኑን ከቦ፡
ሀጥያቱን በሀጥያት - ስተቱን በስተት መተንተን አስቦ፡
እንዲ ሲል ይሰማል!
ልክ እንደ ይሁዳ ትላንትና ማታ
ስሞ ሰው ሸጦ ነው፡
ለቀባሪ ስራ ለማቃለል ብሎ ቅርበቱን መርጦ ነው፡
ሌላ ጋ ገድለውት ራሱ ነው ለማስባል
እዚ ሰቅለውት ነው፡
እንዲህ ነው እንዲያ ነው፡
እያሉ ሲያወሩ እርግጠኞች ሆነው፡
እልፍ መላምቶች - ሽቅብ ሲያናፍሱ፡
ከሞተው ሰው በላይ - ገረሙኝ እነሱ፡፡

ይህ በንዲህ እንዳለ፡
አንቀፅ እያወሱ - ገፅ እያጣቀሱ፡
ህግጋትን ሁሉ - ሟች ስለመጣሱ፡
ያድራጎቱን ነገር - ሀጥያት ለማድረግ ሲጣደፉ ገርሞኝ፡
ከመሞቱ በላይ
ከአሟሟቱ ይልቅ - የሞቱ መንስኤ ማስገረሙ ገርሞኝ፡
መሃላቸው ሆኜ እፈላሰማለሁ እኔም ልክ እንደሞኝ፡፡

ለምን ብሎ ሞተ?
ለማን ብሎ ሞተ?
በ ፫ ብር የአይጥ መርዝ ቅንጡ አሟሟት መሞት እየቻለ፡
በ ፳ ብር ገመድ ለምን አስከፊ ሞት መጎንጨት ከጀለ?

እንደው ከመጣ አይቀር - ቤተስኪያን ደጃፍ - ባደረሰው እግር፡
ምናል በምላሱ - የበደሉን ነገር ላምላኩ ቢነግር፡
እላለሁ ቢቸግር፡፡
ሰው ራሱ በራሱ - መጨከን ከቻለ፡
ጠንከር ያለ ነገር - በስተኀላው አለ፡
እላለሁ በውስጤ - ሞቱ እያቃጨለ፡

ምናልባት ይህ ምስኪን - ይህ ደሃ ሰውዬ፡
ፍትህ አልባ በሆነች - በዚች በኛ ቀዬ፡
ምን አይነት ኑሮ ውስጥ እንዴት እንደቆዬ፡
ተከትቦ ያለ በድህረ ታሪኩ የመጨረሻ ቃል፡
እንዲ ሚል ይሆናል
ነፃነት በነፃ ማግኘት ለናፈቀ ሆዱ ለባሰው ሰው፡
የ፳ብር ገመድ መግዛት ለማይችል ሰው፡
የ፫ብር ያይጥ መርዝ - መግዛት እጁ ለሚያጥር - የደሃ ደሃ ሰው፡
በተውሶ ገመድ
በተውሶ ሰፈር
በተውሶ አድባር
ራሱን እያፅናና "ሞት ማንን ገደ" በሚሉት ስነ-ቃል፡
እራሱን መግደሉ ለምን ያስደንቃል?
ለምን ሞተ ተብሎስ ለምን ይጠየቃል?
እንዴት ሞተ ተብሎስ እንዴት ይጠየቃል?
እንዴትም ይፈፀም አበቃ ሲልኮ የዛኔ ያበቃል፡፡
እንኳንስ የነፍስን የስጋን ጥያቄ መመለስ ላልቻለ፡
ለቆመው ነውዪ ሞት መፍትሄ ማይሆነው ፅዋው ላልጎደለ፡
ለተከፋውማ
ለተገፋውማ
ጥያቄውም መልሱም ሞት ማንን ገደለ?
በሌላ አገላለፅ!
በመኖር ውጥንቅጥ
ጥያቄ ሲያነሳ እየጠፋው መልሱ
ጥያቄ ሲረሳ ሲመጣለት መልሱ
የህይወት ድብልቅልቋ ብቻ ለሚተርፈው፡
ላለመኖር ሰንፎ ለሞተ ሰውኮ
መሞቱ በራሱ የሁሉም መልስ ነው፡፡

እናም እንኳን ሞትኩኝ!
ከሞትኩም በኀላ ደግሞ አትነካኩኝ፡
ከሞት ለመመለስ ነውና በአርምሞ ጥያቄ እየጫርኩኝ፡
ግን ግን ለምን ሞትኩኝ?"
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ተፃፈ ጥቅምት ፩፯, ፳፻፲፪ ዓ.ም
አዳማ, ኢትዮጵያ

@getem
@getem
@gebriel_19
#ከፋኝ

ንቄም ከፋኝ ስቄም ከፋኝ
አክብሬ ስናቅ ደስታ ከዳኝ
እውነት አጣኝ
በገባኝ ልክ እየኖርኩ በሰማውት ልክ ሳላወራ
የሌለኝን የለኝ ብዬ በያዝኩትም ሳልኩራራ

ጥርሴን ወገግ
አይኔን ገርበብ
ለሚያወሩት እኔ እያፈርኩ
ጆሮዬን ግን ክፍት እያረኩ
ሳላምንበት እሺ ብዬ ሳልረዳ ብቀበልም
ውስጥ ውስጤ ግን አይገኝም

#ለምን?????
ለምን ላለኝ ለምን ጥሩ
ከፋኝ ያልኩት ከጅምሩ
ማጣት አይደለም ሚስጥሩ
በኔ አይደለም ክፍት ያለኝ
በኔ አይደለም መረበሼ
ይልቅስ እማዝነው ምድሪቱ ላይ ለሰፈረው
ጥዋት ማታ ለሚበክነው
ላሁን ዘመን ላሁን ሰው ነው።

ሀ በል ሲባል ፊደል ትቶ አፉን ሚከፍት
ለ በል ሲባል ሰውን ረግጦ ለኔ ለኔ እሚጋፋ
ለበላዩ አሸርግዶ በታቹ ላይ ሚደነፋ

እኔስ ማዝነው ላሁን ዘመን ለዚህ ሰዎ ነው።

ግና የኔ ማዘን ምን ሊጠቅም
ለዚህ ሁሉ መልስ አይሆንም
እናም በማስበው ባቅሜ ልክ
የገባኝን መፍትሄ ልስጥ.......

ሀ ተብሎ ምን ቢበላ ቢጠገብም
ርሀብን አያስቀርም
ለኔ ለኔ ምን ቢባልም
ከሰው በላይ የራስ ስጋ የራስ ምቾት ቢወደድም
በቀን መሀል ለሚመጣው ለክፉ ቀን ስንቅ አይሆንም
ስለዚህ......
ሀ በሉ ሲባል ከ ሀ እስከ ሆ
ለ በሉ ሲባል ከ ለ እስከ ሎ
እንደያኔው ህፃንነት
ፊደል ጠርተን ተማምረን
እንለፋት እቺን ዘመን
ምህረቱን እስኪያድለን
ቸርነትን እስኪቸረን። 🙏🙏🙏🙏

@getem
@getem

#nata
👍1
ብለሽኝ ነበረ

"ጎስቁሎ ቢያገኘው እዳፊው ደርቶ
ጊዜ ይደግፋል ~ ልብሱ ለቀጨመ ላመዳም ቡትቶ"

እኔም እልሻለሁ
ፀዳድቶ ካገኘው ~ ግንባሩ ወርዝቶ
ጊዜ የሚመቸው ~ ለባለጊዜ ነው ፊቱን እጁን አይቶ

እባክሽ ውዴ ሆይ
የቂል ማጽናኛሽን ~ ካመድ ደባልቂና ወደ ጓሮሽ ጣይው
ፋይዳ ቢስ ተረትሽን ~ በጊዜ መስታወት አገላብጠሽ እይው።

✍️አወቀ ካሳው
.............…
#ሼር

@getem
@getem
@getem
እስቲ የገጣሚ ሶሎሞን ሳህለን "ያማል" ወደ ወቅታዊ ጉዳይ እንከርብታት
(በላይ በቀለ ወያ) #ሼር ይደረግ

እና እንደ ነገርኩሽ
ሀገር አሸባሪን
ወታደሮች ቀጥሮ ፣ልክ እንደማስጠበቅ
በቄሮዎች ዱላ ፣ ተመቶ እንደመውደቅ
ሬሳ ሲጎተት ፣ አይቶ እንደመሳቀቅ
ለውጡ "ውጡ" ብሎ ፣ ጎዳና እንደመውደቅ
ስቃይ በበዛባት ፣ በዚች ቧልተኛ ሀገር
ከዚህ የበለጠ ፣ የለም ሚያም ነገር።
ዘረኝነት ያማል
የመንጋ ፍርድ ያማል
ሜንጫ ዱላው ያማል
ምስኪን መግደል ያማል
ጳጳስ ሲያለቅስ ያማል
መስጂድ ማፍረስ ያማል
ካህን ማረድ ያማል
መንገድ መዝጋት ያማል
የማይጎድል ፣ የዘር ጎርፍ ፣ የደም ማዕበሉ
የዕንባ ቅጥልጥሉ
ቤተስኪያን ማጋየት ፣ ንብረት ማቃጠሉ
በድንጋይ ተወግሮ ፣ ድሀ መገደሉ
ምን ብዬ ልንገርሽ ፣ ያማል ይሄ ሁሉ!
።።።
እና እንደ ነገርኩሽ
ቄሮ ሚወደውን ፣ ሌላው ካልወደደ
ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ፣ ሌላ ሀገር ከሄደ
ነገር ተበላሸ ፣
ሀገር ተረበሸ
ጭካኔና በቀል ፣ በግፍ ተወለደ
መንገዱ ተዘጋ ፣ ምስኪኑ ታረደ
ተርፎ ይህን ያየ ፣ጨጓራው ነደደ
አንጀቱ በገነ
የሚሆነው ሳይሆን የማይሆነው ሆነ
ተከበብኩኝ ብሎ
አንድ ሰው በቃዠው ፣ ከእንቅልፉ ሳይነቃ
ሁሉም ተቀይሮ ፣ ተተካ በሲቃ
ምንብዬ ልንገርሽ? ይሄም ያማል በቃ!
።።
ፈንካች ተፈንካቹ
ገዳዩና ሟቹ
እብሪቱ ጥጋቡ
ያለምንም ምክንያት ፣ የጠፋበት ግቡ
ከመርፌ ቀዳዳ ፣ አእምሮ መጥበቡ
በቆራጭ ሜንጫ ፊት ፣ እልፍ አንገት መቅረቡ
ውል የሌለው ቅዠት ፣የተኛን መክበቡ
እልፍ አእላፍ በደል ፣ መግለጫን ማጀቡ
ደሞ ለሱ ግጥም ፣እናቱን መግለጫ
ምንብዬ ልንገርሽ ፣
ይሄ ሁሉ ነገር ፣ ያማል እንደ ሜንጫ።
።።።
እና እንደ ነገርኩሽ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ
ግራ ወይ ቀኝ እግሩ
የሌላ ሀገር ምድርን ፣ ልክ እንደረገጠ
አንዱ መንገድ ዘጊ ፣ ወደኔ አፈጠጠ
ዱላ የጨበጠ ፣ አንድ እጁን ሰንዝሮ
በአንድ እጁ ደግሞ ፣ ድንጋይ ተወራውሮ
ምን ልታዘዝ ይላል…?? ፣ ደረቱን ወጥሮ!
ምን ልታዘዝ ይላል?
እንዴት መንገደኛ ፣ መንገድ ዘጊን ያዛል?!
ክፍት መንገድ ልዘዝ?
አንዲት ሀገር ልዘዝ?
አንድ ፍቅር ልዘዝ?
አንድ ሰላም ልዘዝ?

@getem
@getem

#getem le hulum