ይህቺ ዘንባባ እና የፍቅር ማኅልይ የተሰኘች አጭር የልቦለድ እና የግጥም መጽሃፍ ወደ ራሳችን የምትመልሰን መንገድ እንዳላት አምናለሁ፡፡ አምኜም ይህን እመሰክራለሁ፡፡ እያንዳንዱ ጥሩ መፅሐፍ ከልባችን ጋር ያገናኘናል፡፡ በስራ ጫና፣ በሌሎች ወሬና አሉባልታ፣ በፖለቲካ እንካ ሰላንቲያ፣ በድብርት እና በመሳሰሉት ከራሳችን ተፋተን ከሆነ፤ ይህቺ መጽሃፍ ወደ ልባችን መመለሻ አቋራጭ ናትና… ከጥሩ መጽሃፎች ተርታ እመድባታለሁ፡፡
ቢንያም ገብሩ
@getem
@getem
@Gebriel_19
ቢንያም ገብሩ
@getem
@getem
@Gebriel_19
ላቻም የለሽ
አንቺን.
እንደመስከረም አስውቦ
ባደይ በፅጌ ከቦ.
እንዲያመጣልኝ.
ለቅዱስ ሚካኤል ሥለት አለብኝ፡፡
እናማ ቅዱሱ.
አይቀርምና መንገሱ
ጥላ ይዤ ላስጠልለው.
ዘቢብ ዕጣን ላቀብለው
በግርማ ድባብ ከብቤ.
በጧፍ ጠሎት ጠብሼ
ስባሄ መዝሙር ላበላው.
የፊታችን ህዳር ባመትሽ
ሚኪያል ከኔ ቀጠሮ አለው፡፡
ደረሰልሽ፡፡
ህዳር ጠባ.
ኦና ልቤ ውበት ገባ፡፡
አንቺ መጣሽ.
(ጠጠር መጣያ እስከሚጠፋ)
ነፍሴን ሞላሽ፡፡
ታድያ በማግስቱ…
የመቅሰፍት መአት ሆነ፡፡
ሚካኤል ተቆጣ፡፡
ከሰጠሁት ከርቤ.
ከሰጠሁት ሽቱ.
ከሰጠሁት ዘቢብ.
ካስጠለልኩት ድባብ
የሚስተካከልሽ. አንድ እንኳ ቢያጣ
እሷን ስጠኝ አለኝ
አንቺን ስላመጣ፡፡
(ወላሂ!! ቢሳልሽም አልሰጠው፡፡)
።ዘንባባ ከተሰኘችው መፅሀፍ የተወሰደ።
(ምግባር ሲራጅ)
@getem
@getem
@getem
አንቺን.
እንደመስከረም አስውቦ
ባደይ በፅጌ ከቦ.
እንዲያመጣልኝ.
ለቅዱስ ሚካኤል ሥለት አለብኝ፡፡
እናማ ቅዱሱ.
አይቀርምና መንገሱ
ጥላ ይዤ ላስጠልለው.
ዘቢብ ዕጣን ላቀብለው
በግርማ ድባብ ከብቤ.
በጧፍ ጠሎት ጠብሼ
ስባሄ መዝሙር ላበላው.
የፊታችን ህዳር ባመትሽ
ሚኪያል ከኔ ቀጠሮ አለው፡፡
ደረሰልሽ፡፡
ህዳር ጠባ.
ኦና ልቤ ውበት ገባ፡፡
አንቺ መጣሽ.
(ጠጠር መጣያ እስከሚጠፋ)
ነፍሴን ሞላሽ፡፡
ታድያ በማግስቱ…
የመቅሰፍት መአት ሆነ፡፡
ሚካኤል ተቆጣ፡፡
ከሰጠሁት ከርቤ.
ከሰጠሁት ሽቱ.
ከሰጠሁት ዘቢብ.
ካስጠለልኩት ድባብ
የሚስተካከልሽ. አንድ እንኳ ቢያጣ
እሷን ስጠኝ አለኝ
አንቺን ስላመጣ፡፡
(ወላሂ!! ቢሳልሽም አልሰጠው፡፡)
።ዘንባባ ከተሰኘችው መፅሀፍ የተወሰደ።
(ምግባር ሲራጅ)
@getem
@getem
@getem
የጀግና ሀገር ግጥም
*
ሁሉ ነገር ደም ነው~ የጀግና ሀገር ውሎ
ውበት እንኳ ሲያደንቅ~ የደም ገንቦ ብሎ
ደሙ ነው ሚታየው ~ከ አካሏ ነጥሎ።
*
የፍቅር ጥልቀቱን
ለሀገሩ የዋለውን ~ለሚወዳት ሲገልጽ
ደሜን አፍስሼ ነው ~ ከልብሽ የምሰርጽ።
*
እያለ ስኬቱን ~ በደም እየሳለ
ጥርጣሬ እንዳይኖር ~በደም እየማለ
*
አመታት ሲነጉዱ ~እለታት ሲርቁ
ደምን የሚሰጡት ~ምንጮቹ ሲደርቁ
ድል መንሳት ሲያቅተው~ ሽንፈቱን ሲያጣጥም
ደመ ከልብ ይሆናል ~ የጀግና ሀገር ግጥም።
*
*
እሱባለው Ethiopian
@getem
@getem
@getem
*
ሁሉ ነገር ደም ነው~ የጀግና ሀገር ውሎ
ውበት እንኳ ሲያደንቅ~ የደም ገንቦ ብሎ
ደሙ ነው ሚታየው ~ከ አካሏ ነጥሎ።
*
የፍቅር ጥልቀቱን
ለሀገሩ የዋለውን ~ለሚወዳት ሲገልጽ
ደሜን አፍስሼ ነው ~ ከልብሽ የምሰርጽ።
*
እያለ ስኬቱን ~ በደም እየሳለ
ጥርጣሬ እንዳይኖር ~በደም እየማለ
*
አመታት ሲነጉዱ ~እለታት ሲርቁ
ደምን የሚሰጡት ~ምንጮቹ ሲደርቁ
ድል መንሳት ሲያቅተው~ ሽንፈቱን ሲያጣጥም
ደመ ከልብ ይሆናል ~ የጀግና ሀገር ግጥም።
*
*
እሱባለው Ethiopian
@getem
@getem
@getem
👍1
#አላምንም!
እስኪ ተጠየቁ...!
-
የዝንጀሮ መልኳ አስቀያሚ እንደሆን
በልሳን ብ'ነግራት ትደነግጥ ይሆን?
-
ስናወራ ሰምታ - ወፍ እንደምታምር
ፉጨቷን አቋርጣ - ትለን ይሆን "የምር??"
-
እህሳ?!.....
ታድያ የት ተለከፍን? ምን ነክቶን ነው እኛ?
ስለ አቋም መልካችን ...
እንዴት ባለው ልኬት - ሆንን እርግጠኛ??
.
የቱ ቡዳ በላን?
ምን ቀን ሰፈረብን? ተያዝን በመንፈስ
ለምን ተጠመድን?
ስለራስ በማዜም - ስለራስ በማልቀስ።
.
ቢያማልል ....
ቢያባብል...
ማር ቢሆን ቢጣፍጥ - ነገር በምሳሌ
ባለማመን የማምን -
ተጠራጣሪ ነኝ - እኔ በበኩሌ።
-
-
"ሔዋን እንደዚ ነች!"
"አዳም እንደዚ ነው!"
የሚል ጥቅስ ቢናኝ - አየሩን ቢሞላ
ማንንም አላምንም - ከእንግዲህ በኋላ!!
.
በቃ አላምንም ከቶ፣
ግርምቱን - ትዝብቱን ሳይጨምር - ሳያስቀር
"ሰው እንዲህ ነው!" ብሎ -
ሰው ያልሆነ ፍጥረት - ካልነገረኝ በቀር።
============//==========
(በርናባስ ከበደ)
@getem
@getem
@gebriel_19
እስኪ ተጠየቁ...!
-
የዝንጀሮ መልኳ አስቀያሚ እንደሆን
በልሳን ብ'ነግራት ትደነግጥ ይሆን?
-
ስናወራ ሰምታ - ወፍ እንደምታምር
ፉጨቷን አቋርጣ - ትለን ይሆን "የምር??"
-
እህሳ?!.....
ታድያ የት ተለከፍን? ምን ነክቶን ነው እኛ?
ስለ አቋም መልካችን ...
እንዴት ባለው ልኬት - ሆንን እርግጠኛ??
.
የቱ ቡዳ በላን?
ምን ቀን ሰፈረብን? ተያዝን በመንፈስ
ለምን ተጠመድን?
ስለራስ በማዜም - ስለራስ በማልቀስ።
.
ቢያማልል ....
ቢያባብል...
ማር ቢሆን ቢጣፍጥ - ነገር በምሳሌ
ባለማመን የማምን -
ተጠራጣሪ ነኝ - እኔ በበኩሌ።
-
-
"ሔዋን እንደዚ ነች!"
"አዳም እንደዚ ነው!"
የሚል ጥቅስ ቢናኝ - አየሩን ቢሞላ
ማንንም አላምንም - ከእንግዲህ በኋላ!!
.
በቃ አላምንም ከቶ፣
ግርምቱን - ትዝብቱን ሳይጨምር - ሳያስቀር
"ሰው እንዲህ ነው!" ብሎ -
ሰው ያልሆነ ፍጥረት - ካልነገረኝ በቀር።
============//==========
(በርናባስ ከበደ)
@getem
@getem
@gebriel_19
👍3❤1
😔😔😔😔😔😔😔😔😔😔😔😔
ተማሪ ፂዮን አበበ ነሐሴ16ቀን 2011ዓ.ም ከምሽቱ 3:00 አካባቢ እንደወጣች አልተመለሰችም ። ፅዮን አበበ ለመጨረሻ ጊዜ የታየችው አዲስ አበባ ቀበና መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን አካባቢ ሲሆን የለበሰችዉ ልብስ ሰማያዊ ሱሪ እና ከላይ ኮፍያ ያለው ሹራብ ነበር ። በ እለቱ እናትዋ ስለሞተችባት በመሪር ሀዘን እራስዋን እራስዋን ማረጋጋት ስላቃታት እንደወጣች አልተመለሰችም። ፅዮን ምንም አይነት የአዕምሮ ህመም የሌለባት ሲሆን ያለችበትን የሚያውቅ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ደውለው ቢያሳውቁን ወሮታዉን በእግዚአብሔር ስም እንከፍላለን ቤተሰቦቹዋ።
0911815050
0920856595
ተማሪ ፂዮን አበበ ነሐሴ16ቀን 2011ዓ.ም ከምሽቱ 3:00 አካባቢ እንደወጣች አልተመለሰችም ። ፅዮን አበበ ለመጨረሻ ጊዜ የታየችው አዲስ አበባ ቀበና መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን አካባቢ ሲሆን የለበሰችዉ ልብስ ሰማያዊ ሱሪ እና ከላይ ኮፍያ ያለው ሹራብ ነበር ። በ እለቱ እናትዋ ስለሞተችባት በመሪር ሀዘን እራስዋን እራስዋን ማረጋጋት ስላቃታት እንደወጣች አልተመለሰችም። ፅዮን ምንም አይነት የአዕምሮ ህመም የሌለባት ሲሆን ያለችበትን የሚያውቅ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ደውለው ቢያሳውቁን ወሮታዉን በእግዚአብሔር ስም እንከፍላለን ቤተሰቦቹዋ።
0911815050
0920856595
ወድጄ ነው እንዴ??
(መንግስቱ መርሃፅዮን)
'ርቄ ስሸሸው
ጎዳና አሳብሮ ቀድሞ እየጠበቀኝ
ዋኝቼ ሳመልጠው
ቁልቁል እየሳበ መልሶ ሲደፍቀኝ
ከስርሽ መንግዬ-ነቅዬ ስጥልሽ
እንዳፈሉት ችግኝ-በውስጤ እየበዛሽ
ከቶም ፈውስሽ ላልሆን - ስትሆኚኝ ህመሜ
ስንጥቅ ልቤን ስጠቅም
በትዝታ መርፌ-በናፍቆት ቀምቅሜ
ስወድሽ......ስወድሽ.....ስወድሽ......ስ..................ወድሽ
አፍላነቴ ከስሞ-አጎበጠኝ እድሜ!
*
*
*
እንደኩፍኝ ድውይ "ወጣሽልኝ" ብዬ
ስለቴን ሳገባ
የአብሮነት ውሏችን "አከተመ!" እያልኩ
ከፍቺሽ ስጋባ
መች ለቀቀኝ ፍቅርሽ-መች ተፋታኝና
እንደቅል አበባ ሰርክ እየታደሰ
ይህው ሊያንገላታኝ -እንዳምና ካቻምና
ሽምጥ ጋልቦ ደርሶ ያዘኝ እንደገና!
*
*
*
ፍቅርሽን....
.........
በተመሳቀለ
እርጥብ እንጨት መስቀል
ጠርቄ ብሰቅለው
በድን እሱነቱን ከሲዖል ጉድጔድ ውስጥ
አርቄ ባኖረው
ልክ እንደመሲሁ
መቃብር ፈንቅሎ-ገልብጦ ወጣና
ይህው .....
ምስኪን ልቤን ጎበኘው እንደገና!
*
*
*
እኔ 'ምልሽ ውዴ?
ምን ያ'ረግልሻል 'ሳልወድሽ ብወድሽ'
እንደ ንጉስ ት'ዛዝ እዳ ሆነሽ ባዝልሽ
ምን ሊረባሽ ከቶ
ሰቀቀን ቢገርፈኝ "ርግማኔ" ሆነሽ?
*
*
*
ንገሪኛ ውዴ??
ፍላጎቴን ነጥቆ
ሎሌሽ ባደረገኝ-ዕኩይ ሆኖኝ ፍቅርሽ
እንደ ድል አድራጊ
ሃሴት ሊሆንልሽ ተወደድኩኝ ብለሽ??
*
*
*
እን.........ዴ....................!
እረ አትኩራሪበት- እረ ሀፍረት ይግባሽ??
ፈርዶብኝ ነው እንጂ
ወድጄ ነው እንዴ እኔ አንቺን ስወድሽ???
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
ቲሽ!
@getem
@getem
@gebriel_19
(መንግስቱ መርሃፅዮን)
'ርቄ ስሸሸው
ጎዳና አሳብሮ ቀድሞ እየጠበቀኝ
ዋኝቼ ሳመልጠው
ቁልቁል እየሳበ መልሶ ሲደፍቀኝ
ከስርሽ መንግዬ-ነቅዬ ስጥልሽ
እንዳፈሉት ችግኝ-በውስጤ እየበዛሽ
ከቶም ፈውስሽ ላልሆን - ስትሆኚኝ ህመሜ
ስንጥቅ ልቤን ስጠቅም
በትዝታ መርፌ-በናፍቆት ቀምቅሜ
ስወድሽ......ስወድሽ.....ስወድሽ......ስ..................ወድሽ
አፍላነቴ ከስሞ-አጎበጠኝ እድሜ!
*
*
*
እንደኩፍኝ ድውይ "ወጣሽልኝ" ብዬ
ስለቴን ሳገባ
የአብሮነት ውሏችን "አከተመ!" እያልኩ
ከፍቺሽ ስጋባ
መች ለቀቀኝ ፍቅርሽ-መች ተፋታኝና
እንደቅል አበባ ሰርክ እየታደሰ
ይህው ሊያንገላታኝ -እንዳምና ካቻምና
ሽምጥ ጋልቦ ደርሶ ያዘኝ እንደገና!
*
*
*
ፍቅርሽን....
.........
በተመሳቀለ
እርጥብ እንጨት መስቀል
ጠርቄ ብሰቅለው
በድን እሱነቱን ከሲዖል ጉድጔድ ውስጥ
አርቄ ባኖረው
ልክ እንደመሲሁ
መቃብር ፈንቅሎ-ገልብጦ ወጣና
ይህው .....
ምስኪን ልቤን ጎበኘው እንደገና!
*
*
*
እኔ 'ምልሽ ውዴ?
ምን ያ'ረግልሻል 'ሳልወድሽ ብወድሽ'
እንደ ንጉስ ት'ዛዝ እዳ ሆነሽ ባዝልሽ
ምን ሊረባሽ ከቶ
ሰቀቀን ቢገርፈኝ "ርግማኔ" ሆነሽ?
*
*
*
ንገሪኛ ውዴ??
ፍላጎቴን ነጥቆ
ሎሌሽ ባደረገኝ-ዕኩይ ሆኖኝ ፍቅርሽ
እንደ ድል አድራጊ
ሃሴት ሊሆንልሽ ተወደድኩኝ ብለሽ??
*
*
*
እን.........ዴ....................!
እረ አትኩራሪበት- እረ ሀፍረት ይግባሽ??
ፈርዶብኝ ነው እንጂ
ወድጄ ነው እንዴ እኔ አንቺን ስወድሽ???
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
ቲሽ!
@getem
@getem
@gebriel_19
ዋኔ! ሀኖሴ!!
።።።።።።።።፡፡
ነይ ትጥቄ!!
ነይ ስንቄ!!
ጎልያድ ጥላቴን፡ ዳዊት ሁነሽ ግደይ፣
በወንጭፍሽ መዳፍ፡ ጠጠር ሁኘ ልታይ፣
ነይ ዋኔ ሀኖሴ፣
ነይ ፋና ፋኖሴ፣
በፈገግታሽ ፀዳል፡ ኑሮ ቤቴ ይድመቅ፣
ባፍቅሮትሽ ብርታት፡ ጥላቻ ቃል ይድቀቅ፣
ወዶ ዘማች ልቤ፡ የልቡ ይሳካ፣
በብርታትሽ ይፅና፡ በግብርሽ ይመካ፣
ውበት ነሽ።
ኪነት ነሽ።
ከቅፍሽ ልጋመድ፣
ከልብሽ ልጣመድ፣
ከጉያሽ ልዛመድ፣
ነይ ቀኔ ንጋቴ!!
ነይ ሳቄ ንቃቴ!!
እንደንስር ጥልቅ አይቸ፡ የህይወትን ሚስጥር ልፍታ፣
እንደትንኝ ቅንጣት ሁኘ፡ ዝሆን ግዝፈትን ልርታ፣
የበደል ቃር ሳይሰንገኝ፡ በፍትሕ ቃልሽ ልቀጣ፣
ባደባባይ በሸንጎ ፊት፡ በፈገግታሽ ሽልም ልውጣ፣
ነይ ጉልበት ብርታቴ፣
ነይ ህይወት እውነቴ፣
እኛም ህዝብ እንሁን፡
እንደወርቅ እንቅለጥ፡ በ'ሳት እንፈተን፣
ሲቀጥፉን ሲገድሉን፡
ሺ ምንተ ሺ ሁነን፡ እንድንገኝ በዝተን፣
ነይ ሳቄ!!
ነይ ሐቄ!!
ወንጌል ፍቅርሽ ነድፎኝ፡ ከልሳኔ ታስረሽ፡
የህይወት ቃል ልስበክ፡ ልጓዝ በጎዳናሽ፡
ነይልኝ እምነቴ!!
ነይልኝ ህብስቴ!!
በወደድኩሽ መውደድ፡ የገረረው ይግራ፣
ባፈቀርኩሽ ፍቅር፡ ድፍርስ ዘመን ይጥራ፣
ዓለም ባንቺ ትዋብ፡ ምድር ባንቺ ትድመቅ፣
የመረረው ይጣፍጥ፡ እፎይታ ይደለቅ፣
ነይልኝ ንጋቴ፣
ነይልኝ ድምቀቴ!!
የኔ ቀን መች ነጋ፡
ከሚል ክፉ ውጋት፡ በብርሃን ስውሪኝ፣
አቋሜን ዘንግቸ፡
በነፈሰ እንዳልነፍስ፡ በቅፍሽ ደግፊኝ፣
ነይ ጌጤ...
ነይ ድምጤ...
ቀና ልበል በቅን፡
ፍክት እንደፀደይ፡ ኮምተር እንደኮሶ፣
መራር ቀኔ ያክትም፡
እኔም ቀን ይንጋልኝ፡ ፅልመት ተገርስሶ፣
ነይ ገዴ ዘመዴ!!
ነይ ጓዴ ጥማዴ!!
ያመመሽ ይመመኝ፡ ቁስልሽ ይሁን ቁስሌ፣
የሳቅሽውን ልሳቅ፡ ድልሽ ይሁን ድሌ፣
ነይ ወኔ ሀሞቴ!!
ነይ ቅኔ ቅኝቴ!!
ቀራንዬ ፍቅርሽ፡ መስቀል ሸክም ሁኖኝ፣
ጎለጎልታ ፍቅርሽ፡ በሰሌን ጠቅልሎኝ፣
ሞትን ድል አድርጌ፡ በህይወት እንድገኝ፣
ነይ...!!
።።።።።።
............
ይህ የእብዱ እስትንፋሰ ብእር ነው!!
ሸጌ ማግሰተ ሰኝት!!💚💛❤️
@getem
@getem
@balmbaras
።።።።።።።።፡፡
ነይ ትጥቄ!!
ነይ ስንቄ!!
ጎልያድ ጥላቴን፡ ዳዊት ሁነሽ ግደይ፣
በወንጭፍሽ መዳፍ፡ ጠጠር ሁኘ ልታይ፣
ነይ ዋኔ ሀኖሴ፣
ነይ ፋና ፋኖሴ፣
በፈገግታሽ ፀዳል፡ ኑሮ ቤቴ ይድመቅ፣
ባፍቅሮትሽ ብርታት፡ ጥላቻ ቃል ይድቀቅ፣
ወዶ ዘማች ልቤ፡ የልቡ ይሳካ፣
በብርታትሽ ይፅና፡ በግብርሽ ይመካ፣
ውበት ነሽ።
ኪነት ነሽ።
ከቅፍሽ ልጋመድ፣
ከልብሽ ልጣመድ፣
ከጉያሽ ልዛመድ፣
ነይ ቀኔ ንጋቴ!!
ነይ ሳቄ ንቃቴ!!
እንደንስር ጥልቅ አይቸ፡ የህይወትን ሚስጥር ልፍታ፣
እንደትንኝ ቅንጣት ሁኘ፡ ዝሆን ግዝፈትን ልርታ፣
የበደል ቃር ሳይሰንገኝ፡ በፍትሕ ቃልሽ ልቀጣ፣
ባደባባይ በሸንጎ ፊት፡ በፈገግታሽ ሽልም ልውጣ፣
ነይ ጉልበት ብርታቴ፣
ነይ ህይወት እውነቴ፣
እኛም ህዝብ እንሁን፡
እንደወርቅ እንቅለጥ፡ በ'ሳት እንፈተን፣
ሲቀጥፉን ሲገድሉን፡
ሺ ምንተ ሺ ሁነን፡ እንድንገኝ በዝተን፣
ነይ ሳቄ!!
ነይ ሐቄ!!
ወንጌል ፍቅርሽ ነድፎኝ፡ ከልሳኔ ታስረሽ፡
የህይወት ቃል ልስበክ፡ ልጓዝ በጎዳናሽ፡
ነይልኝ እምነቴ!!
ነይልኝ ህብስቴ!!
በወደድኩሽ መውደድ፡ የገረረው ይግራ፣
ባፈቀርኩሽ ፍቅር፡ ድፍርስ ዘመን ይጥራ፣
ዓለም ባንቺ ትዋብ፡ ምድር ባንቺ ትድመቅ፣
የመረረው ይጣፍጥ፡ እፎይታ ይደለቅ፣
ነይልኝ ንጋቴ፣
ነይልኝ ድምቀቴ!!
የኔ ቀን መች ነጋ፡
ከሚል ክፉ ውጋት፡ በብርሃን ስውሪኝ፣
አቋሜን ዘንግቸ፡
በነፈሰ እንዳልነፍስ፡ በቅፍሽ ደግፊኝ፣
ነይ ጌጤ...
ነይ ድምጤ...
ቀና ልበል በቅን፡
ፍክት እንደፀደይ፡ ኮምተር እንደኮሶ፣
መራር ቀኔ ያክትም፡
እኔም ቀን ይንጋልኝ፡ ፅልመት ተገርስሶ፣
ነይ ገዴ ዘመዴ!!
ነይ ጓዴ ጥማዴ!!
ያመመሽ ይመመኝ፡ ቁስልሽ ይሁን ቁስሌ፣
የሳቅሽውን ልሳቅ፡ ድልሽ ይሁን ድሌ፣
ነይ ወኔ ሀሞቴ!!
ነይ ቅኔ ቅኝቴ!!
ቀራንዬ ፍቅርሽ፡ መስቀል ሸክም ሁኖኝ፣
ጎለጎልታ ፍቅርሽ፡ በሰሌን ጠቅልሎኝ፣
ሞትን ድል አድርጌ፡ በህይወት እንድገኝ፣
ነይ...!!
።።።።።።
............
ይህ የእብዱ እስትንፋሰ ብእር ነው!!
ሸጌ ማግሰተ ሰኝት!!💚💛❤️
@getem
@getem
@balmbaras
👍1
#ድህረ_በላ
የሰውልጅ ለመንቆር የባተለ ቁራ
ቆጥ ስሩልኝ የሚል ዱር አዳሪ ጅግራ
ጥፍሩን የነቀለ ንስር አባወራ
ከተራማጅ አለም ጎጆ የሚሰራ
ዶሮ የሚጋልብ የዘመን ጋላቢ
ጣራ የሚነድል ስውር አንደርቢ
በገሀድ ሲገለፅ ስጋ ለብሶ ሊያድር
መስጂድ እና ደብር
በያሬዳይ ዜማ ለእርኩስ የሚዘምር
ታቦት የማይፈራ አሊም የሚደፍር
ምንቸገረኝ ትውልድ ከመቅፅበት ፈልቆ
ገሞራ ፈንድቆ
መዋኘት ያሻውን እንብርቱ ረፍቆ
እህል እንደ ፀበል ለመድሀኒት ፈልቆ
ውጉዝ!!!.ከም አርዮስ.....ሆድ ተገብሮለት
የማይሆነው ያሉት ደርሶ የሆነበት
የሲኦልን ጠረፍ ባህር
ሳጥናኤልም እንደ ሙሴ ዘመዶቹን እንዲያሻግር
የሚከፍል ግሩም ግዜ.... የሚመትር ድንቅ በትር
እባብ ወቅት ሰብሮ ቅርፊቱን ሲበጣ
ገፊ ከንቱ ዘመን እርካቡን ሲወጣ
በበግ ንክሻ ነው እብደት የሚመጣ።
✍ #አብርሀም_ተክሉ
@getem
@getem
የሰውልጅ ለመንቆር የባተለ ቁራ
ቆጥ ስሩልኝ የሚል ዱር አዳሪ ጅግራ
ጥፍሩን የነቀለ ንስር አባወራ
ከተራማጅ አለም ጎጆ የሚሰራ
ዶሮ የሚጋልብ የዘመን ጋላቢ
ጣራ የሚነድል ስውር አንደርቢ
በገሀድ ሲገለፅ ስጋ ለብሶ ሊያድር
መስጂድ እና ደብር
በያሬዳይ ዜማ ለእርኩስ የሚዘምር
ታቦት የማይፈራ አሊም የሚደፍር
ምንቸገረኝ ትውልድ ከመቅፅበት ፈልቆ
ገሞራ ፈንድቆ
መዋኘት ያሻውን እንብርቱ ረፍቆ
እህል እንደ ፀበል ለመድሀኒት ፈልቆ
ውጉዝ!!!.ከም አርዮስ.....ሆድ ተገብሮለት
የማይሆነው ያሉት ደርሶ የሆነበት
የሲኦልን ጠረፍ ባህር
ሳጥናኤልም እንደ ሙሴ ዘመዶቹን እንዲያሻግር
የሚከፍል ግሩም ግዜ.... የሚመትር ድንቅ በትር
እባብ ወቅት ሰብሮ ቅርፊቱን ሲበጣ
ገፊ ከንቱ ዘመን እርካቡን ሲወጣ
በበግ ንክሻ ነው እብደት የሚመጣ።
✍ #አብርሀም_ተክሉ
@getem
@getem
*ህመምህ አሞኛል*****
(አሌክስ አብርሃም)
የጥበብን ቀኝ እጅበቀኙ የዘየረ፣
ነብዩ ሰለሞን “ያማል” ይል ነበረ፡፡
ቆሞ ሲጠብቃት ቀርታበት ወዳጁ፣
አንድ እሷ የምትሞላው፣
ኦና ቢሆን ደጁ፣
ግትልትል መኪናው፣
ታክሲው አውቶብሱ፣
የሰው ግሳንግሱ፣
የሰው አጋሰሱ፣
ላይኑ አልሞላ ብሎት፣
ለተራበች ነፍሱ፣
“ያማል” ይል ነበረ፡፡
በአይኖቹ አንቀልባ በእንባ መቀነቻ፣
ተስፋ እንደቋጠረ፣
ማዶ ማዶ እያየ በተሰበረ ቅስም “ያማል”ይል ነበረ!
እኔ መች ተሰማኝ የጓዴ ህመሙ፣
የታባቴ ገብቶኝ የጥበቃ ጥሙ፣
ዛሬ ግን አወቅኩት...ብቻዬን ባወራው እብድ ይሉኛል ብዬ፣
ህመምን ላለፍካት ህመሜን ላኩልህ ʻባረቄʼ ጠቅልዬ፡፡
እየውልህ ጓዴ...
ያች የነገርኩህ ልጅ የፍቅር እትብቴ፣
ለተስፋዬ ደብር ያኖርኳት ፅላቴ፣
በራችንን ዘግተን ሲንቆረቆር ህልሜ ሲንቆረቆር ህልምህትዝ አይልህም ጓዴ፣
እልፍ ʻዝም በልʼ ያልኩህ
(እ.................................................................ሷ!)
የሰው ሁሉ ዳና ʻየሷ ነውʼ እያልኩኝ፣
ከበሬ ሲርቁ ተስፋ እያስወረድኩኝ፣
የጠበቅኳት ፍቅሬ - መቼ ለታ መጣች፣
ጓዴ ሃሌ ሉ.....ያ የኔ ፀሐይ ወጣች፣
ከምዕራብ አድማስ ብርሃኗን ነዛች፡፡
ተዘግቶ የነበር በሬ ተከፈተ፣
ገድሎኝ የነበረው ብቸኝነት ሞተ፡፡
ሊተን የነበረ የመውደዴ ተስፋ፣
ፀጉሬ ጫፍ ላይ ሲደርስ ተመልሶ ፋፋ፡፡
ጥቋቁር ተራሮች ፍቅሬን የጋረዱ፣
የእግሯን ዳና ሰምተው ከፊቴ ተናዱ፡፡
ጓዴ ሃሌሉ.....ያ
አበቦች ደመቁ፣
የመከኑ ምንጮች ኩል ውሃ አፈለቁ፣
በጠራራ ግንቦት አደይ ምድሩን ሞላ፣
ምን ልበልህ ሌላ...ሃሃሃ ሃሃ ሃሃ እኔ እምልህ ጓዴ፣
“የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ...”ነበረ አይደል ያልከው ?
ከመቅረት የባሰ አመጣጥ እንዳለ አንተ መቸ አወቅከው ?!!
እና የነገርኩህ ልጅ...
መኖሬን ረስታ፣
ደብሬን ክፍቱን ትታ፣
እግዜር የሰማውን የእምነት ቃሏን ክዳ፣
ከበዓድ ተዛምዳከባዕድ ተዋልዳ፣
“አ...ንተ እስካሁን አለህ ?”አትለኝ መሰለህ…ል...ሙትልህ ጓዴ !
እንዲህ ነው ያለችኝ፣
ቁልቁል እያየችኝ፡፡
እንዲህ ናት ቅፅበቷ...
እሷ ከፊቴ አለች፡፡
የጎደፈ እምነቷን፣
በቃል እያጠበች፡፡
ውራጅ ፍቅሯን ገዝቶ፣
ደረቱን የነፋ ʻፈረንጅʼ ጎኗ ቆሟል፣
ከሷና እሱ ኋላ፣
ተራራ ሸንተረር ዛፍ ቅጠሉ ታምሟል..
.ደመናውም ደክሟል...ከደመናው በላይ አፉን በእጁ ይዞ፣
እግዜርም ተደምሟል(ወቸ ጉድ እያለ…)
ፈረንጁ....
እጁን ʻመክሊቴʼ ላይ ጣል አድርጎ ያየኛል፣
ያኔ ያልከው ʻህመምʼ ጎኔን ይወጋኛል፡፡
የምትወዳት ልጅ በሌላ መታቀፍ፣
ከዚህ በላይ ስቃይ ከዚህ በላይ መቅፈፍ...ምናለበት
እሱ...ግዴለም ይቀፋት፣
በፈራረሰ ቤትጭቃው በረገፈ፣
በንፁህ ልቦና በቀን ባልጎደፈ፣
አንዲት አግዳሚ ላይ ጎን ለጎን ተቀምጠን፣
አንድ እርሳስ ተካፍለን አንድ መፅሐፍ ገልጠን፣
የአበበን በሶ - የጫላን ስል ጩቤ፣
እኔ እንጅ የማስታውስ - ልቤ ላይ ከትቤ፣
ፈረንጁ ምን እዳው… ከሀዲን ያስከዳው፡፡
የአየለን ብርታት፣
የጫልቱን እንስራ፣
በቀዳዳው ጣራ፣
ጉንጯ ላይ ያረፈች የምተገርም ጮራ...፡፡
ቆዳዋ ላይ ያሉ ገራገር ስስ ፀጉሮች፣
ጥቁር ሰሌዳ ላይ ተስፋ የሚቃርሙ የልጀነት አይኖች፡፡
አርፈው የማይቆሙ፣
ተወዛዋዥ እግሮች፣
እርሱ መቸ አያቸው...
ከአንጎሉ ጥልቀት በትዝታ መረብ መች አጠመዳቸው፡፡
ምቾት ያደለበው ስጋዋን ይቀፈው፣.
እንደመሲህ ካባ በእምነት የምነካው፣
ሰገባ ቀሚሷን በድፍረት ይግፈፈው…
ከሰማይ የራቁኝ - ጡቶቿ መካከል፣
በእፎይታ ይረፍ-በአርያም ይንሳፈፍ…ልሙትልህ ጓዴ፣
እጎኔ ብትኖርʻእናቷን ጨረቃʼ ያስባለህ ህመምህ፣
በጠራራ ፀሃይ ይነሳብህ ነበር፡፡
እኔ ተነሳብኝ ሾይጧን ወሰወሰኝ፣
እከካም ክህደት የምፎክትበት ጥፍርህን አውሰኝ፡፡
የኔና እሷን ነበር ዛሬ ያላወራው፣
ʻእ ና ቱ ንʼ ...ሸለቆው እ ና ቱ ን ተራራው፡፡
እፊቴ የቆመው... እ ና ቱን ፈረንጁ፣
ወገቧን ያቀፈው እ ና ቱ ን ቀኝ እጁ፡፡
ስማኝማ አንተ ሰው..
.የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ አልነበረ ያልከው…
ከመቅረት የባሰ አመጣጥ እንዳለ አንተ መች አወቅከው፡፡
አይዞን ወዳጄ፣
ያው እንዳንተ ደጃፍ ኦና ሆኗል ደጄ፣
አሁን ናፍቀኸኛል...
እጠብቅው የለኝ ትጠብቀው የ ለህ፣
እንገናኝና ʻአረቄʼ እየጠጣን፣
ግጥም እንፃፍለት፣
ለድህነታችን ጥበቃን ላሳጣን
!!እናቱን ድህነት !!
እናቱን ጥበቃ
!!በቃ!!
@getem
@getem
@getem
(አሌክስ አብርሃም)
የጥበብን ቀኝ እጅበቀኙ የዘየረ፣
ነብዩ ሰለሞን “ያማል” ይል ነበረ፡፡
ቆሞ ሲጠብቃት ቀርታበት ወዳጁ፣
አንድ እሷ የምትሞላው፣
ኦና ቢሆን ደጁ፣
ግትልትል መኪናው፣
ታክሲው አውቶብሱ፣
የሰው ግሳንግሱ፣
የሰው አጋሰሱ፣
ላይኑ አልሞላ ብሎት፣
ለተራበች ነፍሱ፣
“ያማል” ይል ነበረ፡፡
በአይኖቹ አንቀልባ በእንባ መቀነቻ፣
ተስፋ እንደቋጠረ፣
ማዶ ማዶ እያየ በተሰበረ ቅስም “ያማል”ይል ነበረ!
እኔ መች ተሰማኝ የጓዴ ህመሙ፣
የታባቴ ገብቶኝ የጥበቃ ጥሙ፣
ዛሬ ግን አወቅኩት...ብቻዬን ባወራው እብድ ይሉኛል ብዬ፣
ህመምን ላለፍካት ህመሜን ላኩልህ ʻባረቄʼ ጠቅልዬ፡፡
እየውልህ ጓዴ...
ያች የነገርኩህ ልጅ የፍቅር እትብቴ፣
ለተስፋዬ ደብር ያኖርኳት ፅላቴ፣
በራችንን ዘግተን ሲንቆረቆር ህልሜ ሲንቆረቆር ህልምህትዝ አይልህም ጓዴ፣
እልፍ ʻዝም በልʼ ያልኩህ
(እ.................................................................ሷ!)
የሰው ሁሉ ዳና ʻየሷ ነውʼ እያልኩኝ፣
ከበሬ ሲርቁ ተስፋ እያስወረድኩኝ፣
የጠበቅኳት ፍቅሬ - መቼ ለታ መጣች፣
ጓዴ ሃሌ ሉ.....ያ የኔ ፀሐይ ወጣች፣
ከምዕራብ አድማስ ብርሃኗን ነዛች፡፡
ተዘግቶ የነበር በሬ ተከፈተ፣
ገድሎኝ የነበረው ብቸኝነት ሞተ፡፡
ሊተን የነበረ የመውደዴ ተስፋ፣
ፀጉሬ ጫፍ ላይ ሲደርስ ተመልሶ ፋፋ፡፡
ጥቋቁር ተራሮች ፍቅሬን የጋረዱ፣
የእግሯን ዳና ሰምተው ከፊቴ ተናዱ፡፡
ጓዴ ሃሌሉ.....ያ
አበቦች ደመቁ፣
የመከኑ ምንጮች ኩል ውሃ አፈለቁ፣
በጠራራ ግንቦት አደይ ምድሩን ሞላ፣
ምን ልበልህ ሌላ...ሃሃሃ ሃሃ ሃሃ እኔ እምልህ ጓዴ፣
“የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ...”ነበረ አይደል ያልከው ?
ከመቅረት የባሰ አመጣጥ እንዳለ አንተ መቸ አወቅከው ?!!
እና የነገርኩህ ልጅ...
መኖሬን ረስታ፣
ደብሬን ክፍቱን ትታ፣
እግዜር የሰማውን የእምነት ቃሏን ክዳ፣
ከበዓድ ተዛምዳከባዕድ ተዋልዳ፣
“አ...ንተ እስካሁን አለህ ?”አትለኝ መሰለህ…ል...ሙትልህ ጓዴ !
እንዲህ ነው ያለችኝ፣
ቁልቁል እያየችኝ፡፡
እንዲህ ናት ቅፅበቷ...
እሷ ከፊቴ አለች፡፡
የጎደፈ እምነቷን፣
በቃል እያጠበች፡፡
ውራጅ ፍቅሯን ገዝቶ፣
ደረቱን የነፋ ʻፈረንጅʼ ጎኗ ቆሟል፣
ከሷና እሱ ኋላ፣
ተራራ ሸንተረር ዛፍ ቅጠሉ ታምሟል..
.ደመናውም ደክሟል...ከደመናው በላይ አፉን በእጁ ይዞ፣
እግዜርም ተደምሟል(ወቸ ጉድ እያለ…)
ፈረንጁ....
እጁን ʻመክሊቴʼ ላይ ጣል አድርጎ ያየኛል፣
ያኔ ያልከው ʻህመምʼ ጎኔን ይወጋኛል፡፡
የምትወዳት ልጅ በሌላ መታቀፍ፣
ከዚህ በላይ ስቃይ ከዚህ በላይ መቅፈፍ...ምናለበት
እሱ...ግዴለም ይቀፋት፣
በፈራረሰ ቤትጭቃው በረገፈ፣
በንፁህ ልቦና በቀን ባልጎደፈ፣
አንዲት አግዳሚ ላይ ጎን ለጎን ተቀምጠን፣
አንድ እርሳስ ተካፍለን አንድ መፅሐፍ ገልጠን፣
የአበበን በሶ - የጫላን ስል ጩቤ፣
እኔ እንጅ የማስታውስ - ልቤ ላይ ከትቤ፣
ፈረንጁ ምን እዳው… ከሀዲን ያስከዳው፡፡
የአየለን ብርታት፣
የጫልቱን እንስራ፣
በቀዳዳው ጣራ፣
ጉንጯ ላይ ያረፈች የምተገርም ጮራ...፡፡
ቆዳዋ ላይ ያሉ ገራገር ስስ ፀጉሮች፣
ጥቁር ሰሌዳ ላይ ተስፋ የሚቃርሙ የልጀነት አይኖች፡፡
አርፈው የማይቆሙ፣
ተወዛዋዥ እግሮች፣
እርሱ መቸ አያቸው...
ከአንጎሉ ጥልቀት በትዝታ መረብ መች አጠመዳቸው፡፡
ምቾት ያደለበው ስጋዋን ይቀፈው፣.
እንደመሲህ ካባ በእምነት የምነካው፣
ሰገባ ቀሚሷን በድፍረት ይግፈፈው…
ከሰማይ የራቁኝ - ጡቶቿ መካከል፣
በእፎይታ ይረፍ-በአርያም ይንሳፈፍ…ልሙትልህ ጓዴ፣
እጎኔ ብትኖርʻእናቷን ጨረቃʼ ያስባለህ ህመምህ፣
በጠራራ ፀሃይ ይነሳብህ ነበር፡፡
እኔ ተነሳብኝ ሾይጧን ወሰወሰኝ፣
እከካም ክህደት የምፎክትበት ጥፍርህን አውሰኝ፡፡
የኔና እሷን ነበር ዛሬ ያላወራው፣
ʻእ ና ቱ ንʼ ...ሸለቆው እ ና ቱ ን ተራራው፡፡
እፊቴ የቆመው... እ ና ቱን ፈረንጁ፣
ወገቧን ያቀፈው እ ና ቱ ን ቀኝ እጁ፡፡
ስማኝማ አንተ ሰው..
.የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ አልነበረ ያልከው…
ከመቅረት የባሰ አመጣጥ እንዳለ አንተ መች አወቅከው፡፡
አይዞን ወዳጄ፣
ያው እንዳንተ ደጃፍ ኦና ሆኗል ደጄ፣
አሁን ናፍቀኸኛል...
እጠብቅው የለኝ ትጠብቀው የ ለህ፣
እንገናኝና ʻአረቄʼ እየጠጣን፣
ግጥም እንፃፍለት፣
ለድህነታችን ጥበቃን ላሳጣን
!!እናቱን ድህነት !!
እናቱን ጥበቃ
!!በቃ!!
@getem
@getem
@getem
👍5
የፀሎት ቋጠሮ
------------------------
"ሀ" ማለት "ለ"ሁኗል ሲዳሩ እንደማልቀስ
ለአቀበት ገደል ሳሌቡ ቢታወስ
አሜን ያልነው ነቅዞ
ያልፀለይነው ፀሎት ለእይታችን ፈዞ
ዝም ያልነው ተሰምቷል አንደበት ቢቀየር
የፀሎት መሰሚያው የት ይሆን ያ ሀገር?
ብለን ለፍፈናል ሰሚ እንዳጣ ሁሉ
ሚዛን የደፋብን ሜዳው ከገደሉ
ውሎአችን ሆነና የጅብ ፍቅር ኑሮ
ስንት እርግማን ሳተን የመታንም ሽሮ
የቂል ዘመን ትውልድ ሁሉን እያመነ
የሌት ፀሎታችን በጉም ተጠራቅሞ ንፋስ ሊያቅፈው ቢሮጥ ፈርቶ ተበተነ
ያነሳ ሚጥለን
የካደ ሚወደን
የፀሎት ቋጠሮ መልሱ የጠፋብን
ሰምተን ይሆን እንዴ ፀሎት በትርጁማን ?
°°°°°°°°°°°#ሲራክ°°°°°°°°°
ነሀሴ ፪፼፲፩ ዓ.ም
ሚዛን ተፈሪ
ኢትዮጵያ
@getem
@getem
@getem
------------------------
"ሀ" ማለት "ለ"ሁኗል ሲዳሩ እንደማልቀስ
ለአቀበት ገደል ሳሌቡ ቢታወስ
አሜን ያልነው ነቅዞ
ያልፀለይነው ፀሎት ለእይታችን ፈዞ
ዝም ያልነው ተሰምቷል አንደበት ቢቀየር
የፀሎት መሰሚያው የት ይሆን ያ ሀገር?
ብለን ለፍፈናል ሰሚ እንዳጣ ሁሉ
ሚዛን የደፋብን ሜዳው ከገደሉ
ውሎአችን ሆነና የጅብ ፍቅር ኑሮ
ስንት እርግማን ሳተን የመታንም ሽሮ
የቂል ዘመን ትውልድ ሁሉን እያመነ
የሌት ፀሎታችን በጉም ተጠራቅሞ ንፋስ ሊያቅፈው ቢሮጥ ፈርቶ ተበተነ
ያነሳ ሚጥለን
የካደ ሚወደን
የፀሎት ቋጠሮ መልሱ የጠፋብን
ሰምተን ይሆን እንዴ ፀሎት በትርጁማን ?
°°°°°°°°°°°#ሲራክ°°°°°°°°°
ነሀሴ ፪፼፲፩ ዓ.ም
ሚዛን ተፈሪ
ኢትዮጵያ
@getem
@getem
@getem
እንዴት ታደርገኝ ይሆን?
(የብሶተኘው ግጥም)
(ቡሩክ ካሳሁን)
በካቻምና ክረምት
በአንዲት ሽንቁር መሀል ጣራዬ ላይ ባለች
የዝናብ ዘለላ አልፋ ገብታ ኖሮ ጠብ ጠብ እያለች
ማስታጠቢያ መደቀኑ ቢታክተኝ
አማርሬካለው እኔኮ ደፋር ነኝ!
በዘንድሮ ክረምት;
በዘንድሮ ክረምት ከአምና ከካኣምና ትምህርት ወስጃለው
ለሽንቁር ሳማርር ቤቴ ተነድሎ በአይኔ አይቻለው
ዝናብ የመጣ እንደሁ ውጪ እጠለላለሁ
ተመስገን እላለሁ፡፡
ከአመታት በፊት
ባለቤቴ እያመሸች በር መክፈት ቢሰለቸኝ
ህልውናህን ተጠራጥሬ ቀና ብዬ እንዲህ አልኩኝ
“ፈጣሪ አለሁ ብቻ እንዳትለኝ”
አሁን ሚስቴ አታመሽም ምስጋናው ይነበብ ከአትሮንሱ
አንዴ ከቤት አትውጣ እንጂ አድራ ነው ምትመለሰው ምን ይሳነዋል ለሱ;!
በቀደም ዕለት ማልጄ ስሄድ ወደ ስራ
ባትልክልኝ ታክሲ ረዳት የሚራራ
ስሙኒ ቢጎድለኝ ግማሽ ላይ ወረድኩኝ
አማርርክ ነበር በእግሬ እየዳከርኩኝ፡፡
አሁን ተመስገን ነው ታክሲ ተገላገልኩ
በማርፈዴ ብዛት ከስራ ተባረርኩ!
ከዚህ ሁሉ በኋላ
ከህይወት ማልማር አማራሪ ግልብ ብሆን
እንዴት ታረገኝ ይሆን?!!!
@getem
@getem
@getem
(የብሶተኘው ግጥም)
(ቡሩክ ካሳሁን)
በካቻምና ክረምት
በአንዲት ሽንቁር መሀል ጣራዬ ላይ ባለች
የዝናብ ዘለላ አልፋ ገብታ ኖሮ ጠብ ጠብ እያለች
ማስታጠቢያ መደቀኑ ቢታክተኝ
አማርሬካለው እኔኮ ደፋር ነኝ!
በዘንድሮ ክረምት;
በዘንድሮ ክረምት ከአምና ከካኣምና ትምህርት ወስጃለው
ለሽንቁር ሳማርር ቤቴ ተነድሎ በአይኔ አይቻለው
ዝናብ የመጣ እንደሁ ውጪ እጠለላለሁ
ተመስገን እላለሁ፡፡
ከአመታት በፊት
ባለቤቴ እያመሸች በር መክፈት ቢሰለቸኝ
ህልውናህን ተጠራጥሬ ቀና ብዬ እንዲህ አልኩኝ
“ፈጣሪ አለሁ ብቻ እንዳትለኝ”
አሁን ሚስቴ አታመሽም ምስጋናው ይነበብ ከአትሮንሱ
አንዴ ከቤት አትውጣ እንጂ አድራ ነው ምትመለሰው ምን ይሳነዋል ለሱ;!
በቀደም ዕለት ማልጄ ስሄድ ወደ ስራ
ባትልክልኝ ታክሲ ረዳት የሚራራ
ስሙኒ ቢጎድለኝ ግማሽ ላይ ወረድኩኝ
አማርርክ ነበር በእግሬ እየዳከርኩኝ፡፡
አሁን ተመስገን ነው ታክሲ ተገላገልኩ
በማርፈዴ ብዛት ከስራ ተባረርኩ!
ከዚህ ሁሉ በኋላ
ከህይወት ማልማር አማራሪ ግልብ ብሆን
እንዴት ታረገኝ ይሆን?!!!
@getem
@getem
@getem
የቀጩ መዳኒት
------//------
እንደ መሬት ጅና ፥ እንደ ደቡብ ዋልታ
ባራቱ ነፋሳት ፥ .....ብቻነት ተረድታ
አልጋዬ ላይ በረድ ፣ ግግሯን አምርታ
እንደ መንዝ ጠባሴ፥እንደ ጣርማ ምድር
እንደ ሰላ'ድንጋይ፥ እንደ ሞስካብ ድንበር
ከራሴ አንስቶ ፥ እስከ'ግር ጥፍሬ
ብታርከፈክፈው ፥ የሐምሌውን ኩሬ
የለት ጽንስ ይመስል...
ኩርማን አከልኩልሽ ፥ ...መናኛ ሻድሬ*
=======
እንደው ከወደድሺኝ
ገላዬ በላቦት ፥ ወይባ እንዲመስለኝ
ቆርጣማው አጥንቴ፥ሰላሙን እንዲያገኝ
የቤቴም ምሰሶ ፥ እንዲሞቅ ማገሬ
መጠጥ እንዲልልኝ ፥ ያ ጤዛው አዳሬ
እባክሽ ነይና…
የቀጩን መዳኒት ፥ ...ስጪኝ ለከንፈሬ
« ሚኪ እንዳለ »
ማንጸሪያ ፦ ሻድሬ* ማለት ከጥጥና ከጭረት የተሠራ ሽድሬ፣ሳዱሬ፣ሻቡሬ ተብሎ የሚጠራ በቀላል ዋጋ የሚሸጥ ልብስ ማለት ነው፡፡
@getem
@getem
@mmiku
------//------
እንደ መሬት ጅና ፥ እንደ ደቡብ ዋልታ
ባራቱ ነፋሳት ፥ .....ብቻነት ተረድታ
አልጋዬ ላይ በረድ ፣ ግግሯን አምርታ
እንደ መንዝ ጠባሴ፥እንደ ጣርማ ምድር
እንደ ሰላ'ድንጋይ፥ እንደ ሞስካብ ድንበር
ከራሴ አንስቶ ፥ እስከ'ግር ጥፍሬ
ብታርከፈክፈው ፥ የሐምሌውን ኩሬ
የለት ጽንስ ይመስል...
ኩርማን አከልኩልሽ ፥ ...መናኛ ሻድሬ*
=======
እንደው ከወደድሺኝ
ገላዬ በላቦት ፥ ወይባ እንዲመስለኝ
ቆርጣማው አጥንቴ፥ሰላሙን እንዲያገኝ
የቤቴም ምሰሶ ፥ እንዲሞቅ ማገሬ
መጠጥ እንዲልልኝ ፥ ያ ጤዛው አዳሬ
እባክሽ ነይና…
የቀጩን መዳኒት ፥ ...ስጪኝ ለከንፈሬ
« ሚኪ እንዳለ »
ማንጸሪያ ፦ ሻድሬ* ማለት ከጥጥና ከጭረት የተሠራ ሽድሬ፣ሳዱሬ፣ሻቡሬ ተብሎ የሚጠራ በቀላል ዋጋ የሚሸጥ ልብስ ማለት ነው፡፡
@getem
@getem
@mmiku
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Ermiyas Dejene)
ኑ ትውልድ እንገንባ!
#ሰበታ የምትገኙ 0932540523/ያሬድ ለማ/ ፣ 0921421493/ያብስራ ካሳ/
#አዲስ_አበባ የምትገኙ 0970514616/ዮናስ ገ/መስቀል/፣ 0924140293/መባ/
#መቐለ የምትገኙ 0912178520/ኤርሚያስ ደጀኔ/: 0923602445/ፊራኦል መስፍን/
#ድሬዳዋ የምትገኙ 0915034762/መሃሪ/
#አዳማ የምተገኙ 0949377735/ሰላም/
#ደብረብርሃን የምትገኙ 0941907303/ሄኖክ ዳኜ/
#ሀዋሳ የምትገኙ +251926429534/ተስፋ/፣ +251935932153/ብስራት/
በሁሉም የክልል፣ ዞን እና ወረዳ የሚገኙ አስተባባሪዎችን በየጊዜው ይፋ እናደርጋለን!! እርሶም የዚህ አካል በመሆን ማስተባበር ይችላሉ! @tsegabwolde 0919743630
የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች በትልቁ አሻራችሁን እንደምታሳርፉ ምንም አንጠራጠርም!
✅ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከ ቅንድል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር
@KendelM
@KendelM
#ሰበታ የምትገኙ 0932540523/ያሬድ ለማ/ ፣ 0921421493/ያብስራ ካሳ/
#አዲስ_አበባ የምትገኙ 0970514616/ዮናስ ገ/መስቀል/፣ 0924140293/መባ/
#መቐለ የምትገኙ 0912178520/ኤርሚያስ ደጀኔ/: 0923602445/ፊራኦል መስፍን/
#ድሬዳዋ የምትገኙ 0915034762/መሃሪ/
#አዳማ የምተገኙ 0949377735/ሰላም/
#ደብረብርሃን የምትገኙ 0941907303/ሄኖክ ዳኜ/
#ሀዋሳ የምትገኙ +251926429534/ተስፋ/፣ +251935932153/ብስራት/
በሁሉም የክልል፣ ዞን እና ወረዳ የሚገኙ አስተባባሪዎችን በየጊዜው ይፋ እናደርጋለን!! እርሶም የዚህ አካል በመሆን ማስተባበር ይችላሉ! @tsegabwolde 0919743630
የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች በትልቁ አሻራችሁን እንደምታሳርፉ ምንም አንጠራጠርም!
✅ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከ ቅንድል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር
@KendelM
@KendelM
👍1
የሳቅ ሙሽራ!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።
ማቱሳላን ላልሆን ፥ ያለስፍር ዕድሜ
በሺህ ላላስቆጥር ፥ ከሙት ቀን ቀድሜ
በአጭር ተሰጥቶኝ ፥ ዘመን ተለክቶ
ስለምን ልተክዝ ፥ ለምን ይክፋኝ ከቶ ?
አዎን አላነባም !
እንባዬን አልዘራም
ፊቴም አይጨማደድ ፥ ገፄም አይከፋም
እንዲህ ካልበረቱ
ክፉህ ቀን አይገፋም።
ሀሳብ ሲሰለጥን!
ግዞት በኔ ነግሶ ፥ ሊጥል ሲታገለኝ
መጥፎ ህልም አይሎ ...
ከሰላም መኝታ ፥ ከእንቅልፍ ሲያናጥበኝ
የመከራ ቀንበር ፥
ኸበላዬ ሰፍሮ ፥ ጫንቃዬን ሲያዝለኝ
አልተናነስም ፥ ለድካም ጎብጬ
በሳቄ እቃናለሁ ፥ ከንፈሬን ገልጬ
አዎን እስቃለሁ!
ደስ ብሎኝ አድራላሁ !
ቅንጣት ላልጨምር ፥ ጠጉሬን አስረዝሜ
ሸክላውን ላላስውብ ፥ አፈሩን ቀምሜ
ጭንቀት ባሉት በትር
ለቅሶ ባሉት እሳት
ከዕድሜዬ ቆንጥሬ
አንድ ቀኔን ሽሬ
ድንኳን እየጣልሁኝ ፥ ለሀዘን አልዳርም
ፈገግ ብዬ አልፋለሁ ፥ ከፍቶኝ አልቆዝምም።
@getem
@getem
@getem
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።
ማቱሳላን ላልሆን ፥ ያለስፍር ዕድሜ
በሺህ ላላስቆጥር ፥ ከሙት ቀን ቀድሜ
በአጭር ተሰጥቶኝ ፥ ዘመን ተለክቶ
ስለምን ልተክዝ ፥ ለምን ይክፋኝ ከቶ ?
አዎን አላነባም !
እንባዬን አልዘራም
ፊቴም አይጨማደድ ፥ ገፄም አይከፋም
እንዲህ ካልበረቱ
ክፉህ ቀን አይገፋም።
ሀሳብ ሲሰለጥን!
ግዞት በኔ ነግሶ ፥ ሊጥል ሲታገለኝ
መጥፎ ህልም አይሎ ...
ከሰላም መኝታ ፥ ከእንቅልፍ ሲያናጥበኝ
የመከራ ቀንበር ፥
ኸበላዬ ሰፍሮ ፥ ጫንቃዬን ሲያዝለኝ
አልተናነስም ፥ ለድካም ጎብጬ
በሳቄ እቃናለሁ ፥ ከንፈሬን ገልጬ
አዎን እስቃለሁ!
ደስ ብሎኝ አድራላሁ !
ቅንጣት ላልጨምር ፥ ጠጉሬን አስረዝሜ
ሸክላውን ላላስውብ ፥ አፈሩን ቀምሜ
ጭንቀት ባሉት በትር
ለቅሶ ባሉት እሳት
ከዕድሜዬ ቆንጥሬ
አንድ ቀኔን ሽሬ
ድንኳን እየጣልሁኝ ፥ ለሀዘን አልዳርም
ፈገግ ብዬ አልፋለሁ ፥ ከፍቶኝ አልቆዝምም።
@getem
@getem
@getem