ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ድህረ_በላ

የሰውልጅ ለመንቆር የባተለ ቁራ
ቆጥ ስሩልኝ የሚል ዱር አዳሪ ጅግራ
ጥፍሩን የነቀለ ንስር አባወራ
ከተራማጅ አለም ጎጆ የሚሰራ
ዶሮ የሚጋልብ የዘመን ጋላቢ
ጣራ የሚነድል ስውር አንደርቢ
በገሀድ ሲገለፅ ስጋ ለብሶ ሊያድር
መስጂድ እና ደብር
በያሬዳይ ዜማ ለእርኩስ የሚዘምር
ታቦት የማይፈራ አሊም የሚደፍር
ምንቸገረኝ ትውልድ ከመቅፅበት ፈልቆ
ገሞራ ፈንድቆ
መዋኘት ያሻውን እንብርቱ ረፍቆ
እህል እንደ ፀበል ለመድሀኒት ፈልቆ
ውጉዝ!!!.ከም አርዮስ.....ሆድ ተገብሮለት
የማይሆነው ያሉት ደርሶ የሆነበት
የሲኦልን ጠረፍ ባህር
ሳጥናኤልም እንደ ሙሴ ዘመዶቹን እንዲያሻግር
የሚከፍል ግሩም ግዜ.... የሚመትር ድንቅ በትር
እባብ ወቅት ሰብሮ ቅርፊቱን ሲበጣ
ገፊ ከንቱ ዘመን እርካቡን ሲወጣ
በበግ ንክሻ ነው እብደት የሚመጣ።

#አብርሀም_ተክሉ

@getem
@getem