ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
አላማጣ ውየ መልሼ አላማጣ
በበሽታየ ላይ በሽታ ላመጣ።
ራያ ሜዳ ላይ፥
ጀምዓ ቀበሌ ሰደቃ አይታጣም
ላንቺ ይብላኝ እንጂ እኔስ ሸጋ አላጣም።
ላንቺ ይብላኝ እንጂ
ግባ ብሎ ለማኝ ዋጃ ላይ አላጣም።
ወሎ-ነገረ-ብዙ!!

@getem
@getem
@balmbaras
ዝምታ እና ጨኸት኿኿

በዝምታ ውስጥ ሆነህ፤
ጩኸት እንዳለ፣ ለጉያህ መስክር፤
ዝምታ በራሱ…
ጩኸት እንደሆነ፣ በአፅኖት አስተውል፡፡
የዝምን ትርጉም፤
የጪጭን ሚስጥር፤
የረጭን ቅኔ፤
ከሌላው ነጥሎ ፣አሻቅቦ ላየ፤
እውነትን አጢኖ፣ በልክ ላስተዋለ፤
ዝምታ ይደመጣል!
ዝምታ ይሰማል!
ዝምታ ያወራል!
ዝምታ ያነባል!
ዝምታ ዝም ይላል!
ዝምታ ይጮሀል!
ከጩኸት ያለፈ ፣እሩቅ ያስተጋባል፤

ከዛ ከላይ ማዶ፣ ከአቀበቱ ግርጌ፤
…….ሁለት ቤቶች አሉ
በደራሲው ምናብ፣ ብዕር የተሳሉ፤
አንድ ደራሲ መትሮ፣ እሱ ያፀናቸው፤
ሁለት ቤቶች አሉ፣ ቀለም ሚለያቸው፤
እናም አንደኛው ቤት….
ሄድኩ መጣው በሚል፣ መብራት አሸብርቋል፤
የሙዚቃው ድምፀት፣ ሰላምን ይነሳል፤
እናም በዚች ቤት፤
ሰላማቸው ጠፍቶ፣ ሰላም ሚፈልጉ፤
ደስታን የተሳኑ ፣ፈገግታ ሚናፍቁ፤
ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ሁሉም ተሰብስበዋል፤
አንደኛው ብርጭቆውን፣ ከሌላው ያጋጫል፤
ልክ በሌለው አፍ ፣ላንቃውን ይከፍታል፤
ከሙዚቃው ቅኝት ፣በሚወጣው ዜማ፤
ይነጉዳል ብዙ ሰው፣ ልቡን እየሰማ፤
ዘላዩ ብዙ ነው፣ ወንበር ሰባሪ፤
ለራሱ ሚኖር ፣የጩኸት አዝማሪ፡፡

እናም በዚች ቤት…
የጨርቅ ብጣሽ ፣አገልድመው ካሉ፤
እርቃን ገላቸውን፣ ደምቀው ከሚታዩ፤
ከዉብ እንስቶች፣ ይሰማል ጫጫታ ፤
ቅምጥ ካበጃጁ፣ ይወጣል ሁካታ፤
እናም በዚች ቤት….
ጩኸት ከፍ ብሎ፣ ወሰን አልባ ሆኗል፤
ሰላም እየነሳ፣ ሰላምንም ሰቷል፡፡
ሁለተኛው ቤት ፣ደራሲው የሳለው፤
ቀለሙን ነክሮበተ፣ እራሱ የሰራው፤
ሁለተኛይቷ ይህች፣ ትንሽ ቤት፤
ዝምታ ዉጧታል ፤
ደጀን መሰሶዋን ፣ፀጥታ ረቧታል፡፡
በቤቱ ጥጋት፣ በመስኮቱ ትይዩ፤
ብዙ ሰዎች አሉ፤
ዝም ዝም ያሉ፡፡

ሁሉ ጨልሞበት፣ በድንግዝግዝ ያለ፤
ብቻውን የሚታይ፣ አንድ ወጣት አለ፤
እናም ይሄ ወጣት…
እናም የዚህ ወጣት፤
ልብሱ ተቀዳዷል
ሰው ሆኖ ፣ሰው አጥቷል፤
ሲጋራውን ይምጋል፤
ከሲጋራው ምገት ፣የሚወጣው ጭስ፤
አንዳች ሹክ ይለዋል፣ ለራሱ በሎሆሳስ፤
የጪሱን ፍኖት፣ እየተከተለ፤
በሀሳብ ዳክሮ፣ ላይ ታች እያለ፤
በቁሙ ያነባል፤
የሁለት እጆቹ ፣የመዳፉ መስመር ፤
ተቋጥሮ ሚፈታው፣ የግንባሩ ሸንተረር፤
ጥያቄ እንዳዘለ፣ ከሩቅ ያሳብቃል፤
እንኳን ለወዳጁ ፣ለባዳም ይታያል፤
የአይኑ መዝዉር ፣ፈጣሪን ይከሳል፤
የከንፈሩ መድረቅ፣ ሄዋንን ይወቅሳል፤
ደረት መደቃቱ ፣ብዙ የጎደለዉ፤
መልስ ያጣ ጥያቄ፣ ነፍሱን የጠፈረዉ፤
የደራሲዉ ዉጤት፤
እናም ይሄ ወጣት፤
ከሰው ተነጥሎ፤
በፊናዉ ዘምኖ፤
ዝም ብሎ ፣ዝም ማለት ተስኖት፤
የራሱ ማንነት ፣ጩኸትን ለግሶት፤
ከራሱ ተጣልቶ፣ ህልዉናዉ በኖ፤
እየጮኸ ይኖራል ፣በዝምታ ዉስጥ ሆኖ፡፡
እናም በዚች ቤት…..
ዝምታ ንጉስ ነዉ፤
ሁሉም ሚቀበለዉ፤
ቤቱ ያነገሰዉ፤
ፉት ፉት እያሉ፣ የሀሳብን መጠጥ፤
ዝምታን ተችረዉ ፣አርገውት ዘውድ እና ጌጥ፤
እኮ በዚች ቤት ፣የሚያወራ የለም፤ መለፈፍ ሚፈልግ፣ ከቶ አይታም፤

ግን…..
የውስጥ ጩኸት አለ፣ ከሁሉ ሚወጣ፤
ዝምታን ሸልሞ፣ ደስታን ያሳጣ፤
እናልህ ዘመዴ….
ዝምታ ይደመጣል፤
ዝምታ ይሰማል፤
ዝምታ ያወራል፤
ዝምታ ያነባል፤
ዝምታ ይጮሀል!
ከጩኸት ያለፈ፣ እሩቅ ያስተጋባል!!


በበዛብህ ብርሃኑ ከ የይሁዳ ገመድ ላይ የተሸመተ²

@getem
@getem
@getem
👍1
ካድሚኝ አለሜ
ከቡና ገበታ
ሥኒ ከሞላው
ጆሮ ማንጠልጠያ
ሎቲ ከቀረው
አልያም በድፍኑ
ማድመጫ አልባው
ጨው ከስኳር ጋራ
በአይነት ቀርበው
የወሎ ጢስ 'ባይነት
በከሠል አፍኖ ጢስ ከሚያሥነባው
ከቡናሽ ማጀት ስር
ዱካ ላይ ቁጭ ብዬ
የፈካ ፈንድሻ
ይዤ በጉያዬ
እግሬ ካረፈበት
ለምለሙ ቄጠማ
እጄ ከሰደደው
የዳቦ አውድማ
በጣቴ ቆንጥሬ
ሥልከው ከአፌ
በድንገት ባነንኩኝ
ጣት ጣቴን ቀርጥፌ
እናማ
እናማ ከአቦሉ
ከቶና በረካ
የጠጣሁት ቡና
ልብን የሚያረካ
ነበርና ውዴ
ጥዑም አፈላልሽ
ይሁን አሚን በይኝ
እኔም ልመርቅሽ
በይ ጀባ ልበልሽ
ው ሠጅ ምርቃቴን
እንደሼሁ ባልችል
ባይመስል የቄሡን
አሜን በይ አለሜ
ልዘይርሽና ይብዛልኝ ሰላሜ
የመካ'ን ዛውያ
ያድርገው እድሜሽን
ኢማን ይሙላሽ ኣቦ
ያድርግሽ በረካ
ወሥዶ ይመልሥሽ
መዲናና መካ
አንቺም በይ መረባ
ከነ ሙሉ ሲኒሽ ከነ ግሳንግሱ
ሀጃ እንዲያወጣ
እንዳይበርድ ድግሱ

በፀባዖት 12/12/2011

@getem
@getem
@getem
👍1
አንቺ ጋር ስጣላ
( በላይ በቀለ ወያ )

መንግስትን ተሳደብ ፣ ተሳደብ ይለኛል
ከሰደብኩት ደሞ ፣ አስሮ ይገርፈኛል
ከገረፈኝ ደሞ...
ለጊዜውም ቢሆን ፣ አንቺን ያስረሳኛል!
ከረሳሁሽ ደሞ...
እንደተጣላሁሽ ፣ አላስብም ቅንጣት
ተሳድቦ መገረፍ....
ሳይሻል አይቀርም፣ አፍቅሮ ከማጣት፡፡

@getem
@getem
@getem
1
አረዳድ 18+(ልዑል ሃይሌ)

ስለፍቅር ሲባል 'ሄዳለሁ ያለበት፤
ደከመኝ አልልም
አንቺን ለማስረዳት የለም ማልገባበት፤
ብቻ ምን አለፋሽ
ይሆናል ያሰብሽው፤
አስታውሠዋለሁ
አንቺም እንዳትረሽው፤
.
ይኸው ላንቺ ስል ነው...
ፍቅሬ ለመሆንሽ ምስክር ፍለጋ፤
ሄጄ ልመጣ ነው ሌላዋ ሚስቴ ጋ፤
ድንገት እንደው ድንገት
አልጋ ላይ ሌላ ሴት አቅፌ ብታይኝ፤
ሌላ ነገር መስሎሽ እንዳትጠረጥሪኝ፤
ይልቅ እስክጨርስ ዝም ብለሽ እዪኝ፤
እዪኝ!
.
እዪኝ!
.
እዪኝ!
.
አየሽው አይደለ
የምትጠረጥሪው እንዳልተፈጠረ፤
ፍቅር ዕውር ሆኖ ባንቺ እንዳላደረ፤
እሱን ላሳይሽ ነው ይህ ሁሉ ድካሜ፤
ካልገባሽ ንገሪኝ ላሳይሽ ደግሜ፤
እንዳንቺ አይነት ሰዎች
ዓይናማውን ፍቅር እውር እያደረጉ፤
እኛን ለምሳሌ
እያደከሙን ነው ከሌላ እያስጠጉ፤
ይኸው አንቺም ደግሞ...
ፍቅር ይጋርዳል እውር ነው ብለሺኝ፤
ሌላ ሴት ጋ ስሄድ ታዲያ እንዴት አየሽኝ?፤
.
ኩኩሉ!
.
18-12-2011 ዓ.ም.


@getem
@getem
@getem
1
*የቃልሽ ፍሬ*

ልበ ስውር ነበርኩ
ውስጤ የታጠረ ባለማመን ክምር
ቀልቤ የሸፈተ
አካሌ ደንዳና የማይበላው አፈር
ብቻ ሆድ ይፍጀው
መንፈሴን በትኜ ከዚ አለም የጠፋው
ስውር ነበርኩ ያኔ
ውስጤ ማይፈታ እንደ ጌታው ቅኔ
እና ዛሬ እና ዛሬ
እህል ተዘርቶብኝ ማላፈራ ፍሬ
አሁን ለማው መሰል
አሁን ሳሳው መሰል
በከንፈርሽ ውሃ
በከንፈርሽ ዝና ረጠብኩኝ መሰል
እናም እናም
ካፍሽ የሚወጣው ያ መልካሙ ፍሬ
ካካሌ ላይ ወድቆ አፈራሁኝ ዛሬ

ይስሐቅ አሰፋ ( izak)

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
#የጨካኝ_ሰው_ጥበብ
-
ለለስላሳው እግሬ ፥ አለት አፍራሽ ጫማ
ለወስዋሳው ልቤ ፥ አፅናኝ ፋጨት ዜማ፣
ስበት ህጉን ሽሬ ፥ ባየር እስክንሳፈፍ
ሸ..ከ..ተ..ፍ! ....... ሸ..ከ..ተ..ፍ!!...
-
እንዲያ ሁኜ ስነጉድ ፥ ከራስ ጋ ውድድር
ከሩቅ ሲሮጥ ታየኝ ፥ አንዱ በባዶ እግር!
..... ወ.ይ.ኔ ... ሲ..ያ..ሳ..ዝ..ን!!
-
ወየው! .... ኧረ ወየው!
መከራን በመፍራት ፥ መከራ ገበየሁ
. እኔ እሱን እያየሁ!!
-
ካሁን አሁን እያልኩ ፥ ስሳቀቅ ስሰጋው
ድንጋይ እንዳይልጠው ፥ እሾህ እንዳይወጋው፣ ...
... ምፅ!
ለሟች ከንፈር መጣጭ ፥ ወዮልኝ ለራሴ
ከጉድጓድ ወድቄ ፥ ተ..ለ..ቀ..መ ጥርሴ!!!
-
-
ያኔ ነው የገባኝ
ምስጢር የተረዳኝ!
-
ከሩህሩሁ ይልቅ ፥ ጨካኝ መሰንበቱ
አለመራመጃው ፥ ሌላ አለማየቱ ፨
----------------//---------------
(በርናባስ ከበደ)

@getem
@getem
@getem
👍1
Audio
አቅራቢ: መብረቁ ጥቁር ሰው (መባ)
join us
👇👇👇
@Bookfor
@getem
@getem
ሲያምሽ አይመመኝ
በማለቴ ውዴ ለምን ይከፋሻል
ለራስሽ ብዬ ነው
ሲያምሽ ከታመምኩኝ ማን ያስታምምሻል?

((ልብ አልባው ገጣሚ))

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
#ይብቃሽ~እታለሜ

ሀገር እያላቸው ኑሮን ለማሸነፍ በሰው ሀገር
ከሰው በታች ሆነው ለሚኖሩ እህቶቻችን መታሰቢያነት የተፃፈ፡፡ ይሄ ከላይ ያለው ፎቶ የኑሯቸውን መራርነት ስለሚያሳኝ ሁሌም ባየሁት ቁጥር ልቤን እያደማ ግጥም ያፅፈኛል፡፡ እንሆ ዛሬም ይህን ቋጠርኩ፡፡

ድህነትን ሽሽት
ለባዕድ ግርድና ማንነት ሲበተን
ከ'ናት ጎጆ ርቆ
በሰቀቀን ድካም ሴትነት ሲፈተን
ከባህሩ ማዶ
አድማሱን ተሻግሮ ባንቺ እየታየኝ
ኑሮሽን ሳስበው
በማይድን ስብራት ህመም አሰቃየኝ፡፡

ህልም አለሽ አውቃለሁ
ከባርነት አልጋ ተኝተሽ ያለምሽው
ለዚህ ነው እህቴ
ኑሮሽን ለመጣል ቆመሽ የተኛሽው፡፡
እንጂማ ሳይታክት
የማዳምን ቁጣ ገላሽ ተሸክሞ
ከ'ናት ቤት የራቀ
መከረኛ ልብሽ ባ'ገር ናቆት ታሞ
ሰርክ እያሰቀቀ
በባዕዳን አለም እንባሽን ሲያፈሰው
ለምን ትይው ነበር
ሀገር አለሽና አንቺም ልክ እንደሰው፡፡

ግና ጊዜ ጥሎሽ
እንደ እድሜ እኩዮችሽ ለመኖር ሳትጓጊ
ላ'ፈር ገፊ አባትሽ
ለእናትሽ ሀዘን ደስታን ልትፈልጊ
የኸው በሰው ሀገር
ስትንከራተቺ በጊዜ ሀዲድ ላይ ሰርክ እየከነፉ
ከመከራሽ ጋራ
መታገል ሳይበቃሽ አመታት አለፉ፡፡

ነይልን አለሜ
ይብቃሽ መታገሉ
ክንድሽ እየዛለ እኛን አታበርቺን
አልቅሰሽ አንስቅም
ለደሀ ጎጆአችን
ማግኘት ምን ያደርጋል እያሳጣን አንቺን?

(((ልብ አልባው ገጣሚ)))
@getem
@getem
@getem
1
ምስጢሩ

አንቺ እየከሳሽ እኔ መፋፋቴ
አንቺ አኅንብሰሽ እኔ መቃናቴ
ተርቦ አንጀትሽ ጠግቤ መብለቴ
ባዶ እግርሽን ሆነሽ እኔ መጫማቴ
አንቺ አፊሽ ደርቆ እኔ መጠጣቴ
አንቺ ሳትማሪ ተምሬ ማወቄ
ልፋትሽ ተረስቶ እኔ መደነቄ
ዕውቀትና ክብሬ ስጦታ ውበቴ
ሽልመት ማዓረጌ መልኬ ደም ግባቴ
የእኔ እኮ አይደለም የአንቺ ነው እማ እናቴ

ልጅ ሙቤ

@getem
@getem
@getem
1
#አዎ ~ባላ'ገር~ነህ!!!

የደመናን እንባ
የናፈቁ አይኖችህ
ሽቅብ ወደ ሰማይ ዘውትር ሲዋትቱ
ከደረቀ መሬት
ትግል የገጠሙ
ሻካራ እጆችህ ሞፈር ሲጎትቱ
ከበሬ ተጣምደህ
አፈር ስትገፋ ቀንበር ስትሸከም
ያኔ ነው የገባኝ
የህይወትህ ምሬት ለኔ ያንተ መድከም፡፡

ግና ከተሜው ሰው
የባላገር ትርጉም ያልገባው ምፃጉ
ለስም አልባ ስሙ
መሆንህን እረስቶ ክብርና ማረጉ
አርሰህ ባጎረስከው
ውለታቢስ ሆዱ ለባእዳን ሰግዶ
ባላገር ይልሀል
በመዘመን ብሂል እርሱ ሀገሩን ክዶ፡፡

አዎ ባላ'ገር ነህ
ሀገር ስላለህ ነው ባላ'ገር ምትባል
እውነትም ይሄ ስም
ከማንም በላቀ ለክብርህ ይገባል፡፡

ስለዚህ ለነሱ
ለከተሜው ጭሶች ባላገር ለናቁ
ሀገር እያላቸው
ሀገር አልባ ሆነው ሀገር ለናፈቁ
ባላ'ገር ነህና
ይበሉህ ባላገር ሀገርን እስኪያውቁ፡፡

((ልብ አልባው ገጣሚ))

@getem
@getem
@getem
1👍1
ለውብ ቀን!
💚

ክቡር ኢትዮጵያውያን
ቂንጥር ይቆርጣሉ
ቂንጥር ይሰፋሉ
ግን ቂንጥር ማለት ያፍራሉ

((( ሠሎሞን ደሬሳ ))💚💛❤️

@getem
@getem
@balmbaras
ዮሃንስ ፬ ፤ ያንተም ቀን ደረሰ!

ያጎረሰውን እጅ የሚናከስ በዝቶ
የቤቱን ምሰሶ የሚጥል ጎትቶ
ባዘለው ጀርባ ላይ የሚዝት በዛና
ሰማዩንም ችሎ ላይጋርድ ደመና
ስንቱ ቂል አዝማሪ በከንቱ ዘፈነ
ስንቱ ግንዱን ትቶ ስንጥር አገነነ።

የተምቤኑ ካሳ ደመ መራራው
አስራስምንት አመት እንቅልፍ ያልተኛው
የቴድሮስን ሀገር ርስቱን ተረክቦ
ያንዲትን ኢትዮጵያ አላማ አንግቦ
ወራሪና ባንዳን ሬት እያቀመሰ
ጎንደር መተማ ላይ ደሙን አፈሰሰ።

ሀገሩን ያልሸጠ ለነጭ ያልዘመረ
የሀበሻን ድንበር ባንገቱ ያጠረ
ዮሃንስ ራብዓይ ንጉሠ ነገስት
የሀገር ጠባቂ ያበሻ አባት።

ምን ትል ነበር ይሆን ብታይ ቀና ብለህ
በእምዬ ውጫሌ ስትሸጥ ርስትህ
የሓማሴን ጌታ ፣ ያካለ ጉዛይ
የምፅዋ አምበሳ የአረብ ገዳይ

አንተ ግብፃ-ግብፁን ካንድም ሁለት ሶስቴ ባትዘርረውማ
አባይና አገሬው ማተቡን ባስቀማ።
አንተ መሃዲስቱን ጀሃዱን ቀልብሰህ ባታረገው ውሻ
ምን ይሆን ነበረ የኛ መጨረሻ?

ካሳ ካንተ ኋላ ሀገሬን ከፍቷቷል
ያክሱሙ ሃውልትም ከአዱሊስ ተጣልቷል።
ባገር ምስረታ ስም ብዙ ግፍ ተሰርቷል
ወዲ ጅግና ካሳ ስምህም ተረስቷል።

እውነት ግን ለወትሮው አይጠፋንምና
ከሰማይ ሲገፈፍ ጥቁሩ ደመና
የትግራይ ልጅ ካሳ ስምህ ይነሳሳል
ኢትዮጵያዊ ሁሉ እውነቱን ይረዳል።

ቀይና ቢጫውን አረንጓዴውን
አንተእንደጀመርከው ስንቱ ያውቅ ይሆን?
ለሙስሉሙ ህዝብህ ያልነጃሺን መሬት አራት እጥፍ አርገህ እንደሸላለምከው
አዝማሪዎች ቀጥረህ ምነው ባዘፈንከው።

የመይሳው ካሳ በጠጣው ጥይት
የተምቤኑ ካሳ በሰጠው አንገት
በትግራይ በሸዋ በጎንደር ኤርትራ
በስንቱ ደም አጥንት ፀንታ የምትኮራ
በውቧ ሀገርህ በጥንታዊ ርስትህ
ባንዳና ሰላቶ ባዝማሪ መሰንቆ ሲወደስ ዋለልህ
የሀገሩን መሬት ከህዝቡ ጋር አርጎ
ለጣልያን የሸጠ ለፒዛና ለእርጎ
ዳግም ላያቅራራ ባንተ ስራ ወዝቶ
በእውቀት የታጠቀ ነቄ ትውልድ መጥቶ
ታሪክህ ሊታደስ ቅኔ እየፈሰሰ
የቀይ ባህሩ ጀግና ያንተ ቀን ደረሰ!

ገጣሚ Utopiawi

🌞🌍🌙
🇪🇹🇪🇷

@getem
@getem
@getem
1
#እመጣልሃለሁ !
~
እንዴት ነህ ወዳጄ?
የጭንቅ አማላጄ የበረሃው ሽፍታ
መች እረሳውና እኔ ያንተን ውለታ!
~
ስብሓት ይሁን ላንተ ...
ከጠላትህ ደጃፍ ታስሬ አግኝተኸኝ
በሰላም ሂድ ብለህ ፈተህ ለለቀከኝ።
~
ገፋፊ - ዘራፊ ብትሆን ነብሰ-በላ
ፅዋህ እለት-ተለት በደም ብትመላ፣ ...
ወቃሽ የለም ብዬ
ሙቀት ተከትዬ፣ ...
አልገላበጥም - አልከንፍም በወረት
ታሪክህን ክጄ - አልለውም "ተረት!!"
-
ስምክን ሳላነሳ
ሳላሞጋግስህ መሽቶም አይነጋልኝ
ሞልቶልን ሰልቶልን
ባይን እስክንተያይ አማን ያቆይልኝ።
-
ከለታት አንድ ቀን ...
ዳገት ቁልቁለቱን
ዱር ገደል ጫካውን በጽናት ተጉዤ
ከተፍ እላለሁኝ
የወግ የልማዱን እጅ መንሻ ይዤ።
-
በመሃሪነትህ
በመልካምነትህ
ሀ-ሞቴን ሳልጠጣት ካለፈች ጽዋዬ
ባንተው ፈለግ ሄጄ
እስኪ እኔም ለሌሎች ልዋል በተራዬ!
-
ማ ር ያ ም ን አልቀርም!
ከእናቴ ይነጥለኝ እውነት እልሃለሁ
መግደል ያሳበዳት
ነብስህን ልወስዳት
ስካለብ - ስጣደፍ እ መ ጣ ል ሃ ለ ሁ!!
-
እ መ ጣ ል ሃ ለ ሁ
በባህር ቀዛፊ
ባየር ተንሳፋፊ - ጦር አደራጅቼ
ሽፍታጋ'ማ ታበርኩ
መትረፌ ምን ረባ ከሙት ተለይቼ?
============//=======
( በርናባስ ከበደ )

@getem
@getem
@getem