ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
*እናት ሀገሬ *

ባለሟት የምትለማ በዘሯት የምትዘራ
በሰጧት የምትለገስ ባኮሯት የምትኮራ
በእምነት ቃልኪዳን ያላት
በታሪክ ገድል የፃፈች
በእድሜዋ ጎህ የቀደደች
ከምዕት ምዕት ያለፈች
በጠላት ባትንበረከክ
ለ አንዴ እንኳን እጅ ባትሰጥም
እናቴን ሀገሬ አትበሏት
ሀገሬ ከ እናቴ አትበልጥም።

#አስታውሰኝ_ረጋሳ (አስቱ)

@getem
@getem
@gebriel_19
የጣፋጭ ግጥሞች ቅኝት!!!
Written by ደረጀ በላይነህ


ግጥም፤ ዜማ የተነከረ ቃል፣ የተመረጠ ሀሳብና ከፍታ ስለሆነ፣ በዝርው
ከሚጻፉት ይልቅ ለልብ ይቀርባል። እኛ አገር ሁሉም እጁን እየሰደደበት ዝቅ
አለ እንጂ በእጅጉ ዘውድ የደፋ ጥበብ ነው:: እረኛ አጥቶ ባከነ እንጂ የጥበብ
ዕንቁ ነው፡፡ ያለ ልክ አደባባይ ላይ እየወጣ ግን ስንዴውን እንክርዳዱ ውጦት፣
ቀልሎ ታየ፡፡
ቀደም ካሉት አመታት፣ የግጥም መጻሕፍት ህትመት ያነሰው በ2010 ዓ.ም
ነበር፡፡ በሚገርም ሁኔታ የታተሙት ከአስራ አምስት በታች መሆናቸው፣
ምክንያቱን ለማወቅ የሚያጓጓ ነው፡፡ ጉጉቱን ለአጥኚዎች ትቼ፣ ከነዚያ ጥቂት
ህትመቶች ውስጥ የተሻለ ውበትና እውነት ያየሁበትን የገጣሚ መዘክር
ግርማን ‹‹ወደ መንገድ ሰዎች›› የተሰኘ መድበል ለመዳሰስ እሞክራለሁ።
ዳሰሳዬ ከሌሎች አላባዎች ፍተሻ ይልቅ ሀሳብ ላይ የተቃኘ ይሆናል፡፡ ‹‹ጅብ
ድሮና ዘንድሮ›› በሚለው ልጀምር፡-

የድሮ ጅብ ትህትናው
ከማያውቁት ሄዶ ‹‹ቁርበት አንጥፉልኝ››
ነበረ ልመናው።
የዛሬ ጅብ ድፍረቱ
ባለቤቱ እያየው፣ ባይኑ በብረቱ
ይሰለቅጥና፣ ላሚቱን ዘርግፎ
እብረቱ ያድራል፣ ቁርበቷን አንጥፎ፡፡
የዚህን ግጥም ፍካሬያዊ ፍቺ ይዞ መነሳት፣ ለግጥሙ ሀሳብ ጥሩ መንደርደሪያ
ይሆናል የሚል ምርጫ አለኝ፡፡ ‹‹ጅብ›› የሚለውን ባለ አራት እግር ሳይሆን
ባለ ሁለት እግር ጅብ መውሰድ ያዋጣል፡፡ ከርሳም፣ ሆዳም፣ ዘራፊ፣ ቀማኛ
ብንለው ለዘመናችን አውድ ትክክለኛውን መልክ ይሰጠናል፡፡ የኛ ዘመኑ፤ ጅብ
ዐይን ያወጣ በአደባባይ የሚዘርፍ፣ ዘርፎ እዚያው አጠገባችን ፎቅ የሚሰራ
ነበር፡፡ የድሮ ጅብ የዘረፈውን ዘርፎ፣ ፊት ለፊታችን ፎቅ አይገትርም፤ ውድ
ሸቀጦች አንጠልጥሎ፣ በውድ መኪና ጡሩንባ እየነፋ አያደነቁርም። ባይሆን
ወደ ሌላ ቦታ ዞር ብሎ፣ ሰርቶ ያገኘው እንዲመስል፣ ብዙ መላ ይፈጥራል፡፡
አሁን ግን ነገሩ ሁሉ የግሪንቢጥ ሆኖ፣ ከኛው በልቶ እኛው ላይ ያገሳል፡፡
መጽሐፉ ውስጥ በርካታ የፍቅር ግጥሞች አሉ:: በአጠቃላይ ፍቅር ፍቅር
የሚሸተቱ ስንኞች ብዙ ናቸው፡፡ አጫጭርም ረዣዥምም አሉ፡፡ ጥቂቱን ማየት
ያዝናናል፡፡ ‹‹የአፍቃሪ ስንብት›› የሚለውን እነሆ፡-

እሄዳለሁ ብለሽ ሻንጣሽን ካነሳሽ
ትናንትናችንን በዛሬ ከረሳሽ
አላስገድድሽም መሄድ ካሻሽ ሂጂ
ባይሆን ተከትዬሽ እመጣለሁ እንጂ፡፡
‹‹ካልሄድኩ›› ብላ እግሯን ያነሳች ተፈቃሪ አለች:: ይህች ሴት ዛሬ የበቀለች
አይደለችም፤ ትዝታ ቋጥራለች፣ ፍቅርን ጎርሳለች፡፡ ግን ያ ምስል፣ ያ ጥፍጥና
የጠፋት ይመስላል፡፡ ሌላ ቦታ አምሯታል:: ግጥሙ ውስጥ የሚናገረው ገፀ
ሰብ ደግሞ ‹‹ቅሪ!›› ብሎ ሊያስገድዳት አልወደደም፡፡ ‹‹ትሂድ!›› ብሎ
ሊያሰናብታትም አልሆነለትም፡፡ ስለዚህ ‹‹ ትሂድ›› ብሎ እርሱም ተከትሏት
ሊሄድ አስቧል፡፡ ከራሱ ጋር እየተጓተተ፣ ከነፍሱ ጋር እየተሟገተ የተሸነፈ
ይመስላል። ግማሽ ትዝታ፣ ግማሽ ተስፋ! ይህ ደግሞ ያጋጥማል፡፡ ‹‹Poetry
comes to us bringing life›› የሚባለውም ለዚህ ነው፡፡ ሕይወት ይዞ
ይመጣል፡፡ ሕይወት ውስጥ የሳቅ ብርሃን፣ የእንባ ነጠብጣቦች አሉ፡፡ ግና
ገጣሚ አይሰብክም፣ ገጣሚ አያስተምርም!... የነፍሱን ዘንግ
በሚያወዛውዘው ወጀብ ውስጥ ሆኖ ቀለሙን ይረጫል።
ገጣሚው ስለ ፍቅር በተለይ ስለ ማራኪነት የፃፉት አንድ ግጥም፤ ሙዚቃው
ሳይቀር ነፍስ ያስደንሳል፡፡ አድናቆቱ እንደ ፊልም አንዲቷን - ቀዘብ - ውልብ
ያደርጋል፡፡


‹‹ደማምዬ ልጅ ናት››
ከዘፈን ገላዋ፣ ከለምለም እወዳ
ቀምሞ የሰራት፣ እሪኩም ዘመዳ
ደማምዬ ልጅ ናት… በደማምነቷ
የተከለከለ፣ በተስኪያን መግባቷ፡፡
መድረኩን ቢነሷት፣
ማህሌት ቢገፏት፣ ባይሰጧት ዲቁና
ከንፈሯ ለሃሌ፣ አይኗ ለትወና…
የጻፈችም እንደሁ፣ ጥርሷን አስመስላ
ያወራችም እንደሁ፣ ልብ ጨርቅ አስጥላ
የሳቀችም እንደሁ፣ እርግፍ እንደ ሾላ!
እርግፍ እንደ ሾላ፣ ቁጣዋን ሰምቼ
እሆዷ እንድገባ፣ በጇ ተነስቼ፡፡
ግጥምን ከሙዚቃ ነጥለን ሀሳብ ብቻ ነው ብለን ለምንሞኝ ሰዎች፤ ዜማ ምን
ያህል ምትሀት እንዳለው የምታሳይ ግጥም ናት። ቤት አመታቷ፣ ከአናባቢ
መረጣ ጀምሮ የተሳካላት ናት፡፡ የስነ ግጥም ተመራማሪው ኢ. ኤኒ ግሪዲንግ
ላምቦርን የሚለውንም ማስታወስ ይሄኔ ነው፡፡ ‹‹The first and most
fatal mistake we can make in regard to poetry is to forget
the poetry was born of music››
ይህ ሀሳብ ሁሌ ሊታሰብ የሚገባ ነው፡፡ ከሙዚቃ ጋር የተወለደው የማህጸን
ልጅ፣ ደረቅ ቃልና ሀሳብ ለሚመስለን ሰዎች፣ መዘንጋት የሌለበት መድኃኒት
ይመስለኛል፡፡
ገጣሚው፣ የተቃራኒ ፆታ ፍቅርን ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮ ፍቅርንም በግጥሞቹ
ቃኝቷል፡፡ ብዙ የአገራችንን ገጣሚያንን ያማለለ፣ ብዕር ያስመዘዘው መስከረም
እርሱንም በውበት ጥቅሻ፣ በውበት ጉርሻ፣ ቀልቡን ስቦታል፡፡ ጥቂት ስንኞቹን
እወስዳለሁ፡፡ ‹‹የምስራቺቱ›› የሚል ርዕስ ሰጥቶታል፡፡
መሽቶ ለጠፋ’ቃ፣ ሲነጋ እንፈልገው


ብሎ ለተባለ
የሆነ ፈገግታ ንጋት የመሰለ
ቃል ጠቋሚ ጥቅሻ፣ ሽፋኗ ላይ አለ፡፡
አረንጓዴ ለብሳ
ቢጫ ጽጌ ሆና
ተሸግና ታየች
በቀይ ፀደና፡።
‹‹መፍርህ›› ነሽ እንበላት፣ ‹‹መደንግድ›› ነችና
ታምር ነሽ እንበላት፣ አንች አበባ ለምለም
‹‹የመስቀል ወፍና የአደይ አበባ
‹‹ቀጠሮ እንዳላቸው›› ታውቃለች መስከረም፡፡
አደይ አበባውንና የአዲሱን ዓመት ልምላሜ፣ ቀለም የተነከረ ውበት፣
ከእንቁጣጣሽ ዜማ አዛንቆ፣ እንደ ታምር ከቆጠራት በኋላ፣ የመንግስቱ ለማን
ግጥም፣ በጠቃሽ ዘይቤ ጠቅሶ፣ በዜማ አስዘንጧታል:: ሎውረንስ ፔሪኔ፤
‹‹ግጥም አያስተምርም፣ ግን ይነሽጣል!›› ያሉት ለዚህ ይሆን!
ውበቷን በዘይቤ ዋንጫ አስጨብጦ፣ ሽፋሏን ኩሎ፣ መስከረምን በአዲስ
ዜማ፣ የተስፋ አብሳሪ አድርጓታል፡፡ መስከረም የማትቀሰቅሰው እንቅልፍ -
ዜማ የማትነጥቀው ከያኒ የለም፡፡ የአደይ አበባ - የአመት ናፍቆት፣ የወንዞች
ዜማ፣ የሰማይ ገፅ - ሁሉም ያጓጓል፡፡ ሁሉም ያባባል፣ ሁሉም ይርባል።
ገጣሚውም ይህንን የተፈጥሮ እውነት፤ በጥበብ አድምቆት ብቅ ብሏል፡፡ ዞሮ
ዞፎ ሥራው ይሄው ነዋ!
‹‹Art has nothing to do with absolute truth; it shows truth
colored by the artist mood;.. ››
‹‹አንድ ዘፈን አለ›› በሚል ርዕሰ ከጻፈው ግጥም አንድ አንጓ ወስጄ፣
በሙዚቃው ስልትና በሀሳቡ አሻራ ብንጫወት ብያለሁ፡-
የወደድሽው ዘፈን፣ የመረጥሽው ዜማ
ዓመታት ቢያልፉትም፣ ለሰው ከተሰማ
የድሮ ቢሆንም፣ ብዙ ዓመት የኖረ
በኔና አንቺ ቤት ግን፣ ሁሌ እንደጀመረ፡፡ አየሽ…
አገሬው አላምጦ የጨረሰው፣ ተደንቆ ያበቃው ዘፈን…፣ ተደምሞ የተወው
ስልትና ቃል፣ ለኔና አንቺ እንደ ቀትር ፀሐይ እየሞቀ የሚሄድ፣ እየደመቀ
የሚደንቅ ነው ይላታል፡፡ ዓመታት ቢቆጠሩም ለኔና አንቺ ግን ገና ትኩስ፣
መዐዛው ነፍስን የሚነቀንቅ፣ ቀልብን የሚነጥቅ ነው እያላት ነው፡፡ ይህ ሕግ
የፍቅር ሕግ ነው፡። ጊዜ ነገሮችን ሁሉ የሚያስረጅበትን ሕግ፤ የፍቅር አጥር
አያስገባውም!... ፍቅር ሁልጊዜ አዲስ፣ ሁልጊዜ ብርቅ ነው። ፀሐይ ዘመን
ቆጥራ አትሸብትም፣ ጊዜ ሞልታ አትሞትም፡፡ በመንታ ልቦች ላይ የበቀለ
ፍቅርም እንዲሁ ነው፡፡ ማልዶ አይጠወልግም፣ ማልዶ አይከስምም፡፡
አድማሱ በሳቅ ጥርሶች እየነደደ ይኖራል እንጂ!
ገጣሚው መዘክር፤ ፍቅርን በውበቱ፣ ፍቅርን በትኩሳቱ፣ ሕይወትን በተስፋው፣
ሀዘንን በጭጋጉ በየመልኩ አስቀምጦታል፡፡ የገጣሚ እጣም ይኸ
2👍2
ው ነው፡፡


ሸጋ ምሽት!💚

ምንጭ:- አዲስ አድማስ ጋዜጣ ነሀሴ11 ቀን 2011 ከወጣችው

@getem
@getem
@balmbaras
1
#አቢ_ማርዬ

ሆያ ሆዬ ጌታው ደጃፉን ክፈተው
አንተን አደለም ወይ የምንጋተተው?
ሙደ ገድ አትሁን ጀለስካ በርግደው
ጃን ሜዳ ተወልዶ ኤድና ሞል ያደገው
ቾምቤ ከተፍ አለ ሳቢ ቢጎትተው
እና እንደምታዪው ሲስቱካ ማርዬ
አመድ ውረጅልኝ ይልሻል ባርዬ
የቻት ግዜ ማጣት ቀልድ አይደል እሙዬ
ውረጂ.....ውረጂ.....ውረጅ ለባርዬ
ከጠዋት ጀምሬ ስንቱን አባብዬ
ቋጣሪ ፈትቼ ንፉግ አታልዬ
እናት ቀለል አርጉት ፋዘር አይገጅሩ
እንደ እድሜዎት ሳይሆን እንደ ጊዜው ኑሩ
አመድ ጨላ ሆኖ አትደራደሩ
የፀዳ ቅላፄ ያበደ ጉሮሮ
ቢልቦርድ የሚረታ ራንኩን ሰባብሮ
ይዘን ከቻስ አልን በኒሳን ፓጃሮ
በራቫ በቪላ ልባችን ታውሮ

አረ .....በቃ ......በቃ
ጉሮሮዋችን .....ነቃ
አረ ላሽ አይነፋም...አንድ አመድ አይጠፋም

የሚል ሆዬ ክሩ
የhope entertegnment እህት ኩባንያ
የሳባት እታለም ለዘመኑ ባዳ
የቅዬው ታውሷት... የወዛ አኮፋዳ
እንኩ በሉ ልጆች..ብላ ሙልሙል ብትልክ
የሰፈሩ ውሪ በፈገግታ ሙክክ
...
...
ማዘርዬ... ሼም ነው
ኮይን ይውረዱ እንጂ ፥ ሙድ መያዝ ምንድነው?
ላሽ ይሄን ውሰዱት ፥ የቡቺ ምግብ ነው
ብትባል በግንባር
ዘመን ተገልብጦ...ጊዜው ተለውጦ
ትውፊት አርጅቶ አቡዬ ዘንጦ
በመስጠት አፈረች ባይተዋር እሙዬ
ሆያ ሆዬ የሚል አባቡ ማርዬ
ላጋፋሪ ድግስ ጭሱን ተከተሎ የሚደርስ ኢጆሌ
ጎፈሬው ደመና ቅንድቡ አይነኩሌ
ሽመል ያነገበ ቀምጣላ ኮበሌ
እታለም ናፈቃት ...
ባያት አስተምህሮ በልጅ አቅል ማጣት
ትወቅሰው
ትከሰው
ትነግረው....ቢጠፋት።

#አብርሀም_ተክሉ

@getem
@getem
@getem
1👍1
#ናፍቆት

//ኑረዲን ዒሣ//

ስጋዬን ሲበላኝ በጥርሴ ነከስኩት
ቆዳዬን ሲበላኝ በጥፍሬ ፎከትኩት
እፎይ አስታገስኩት
ፀጥ ረጭ አረኩት።
የውስጥ አጥንቴ ግን ሲበላኝ ነዝንዞ
ሲነክሰኝ ጠዝጥዞ
ምንም አላረኩት
ምንም አላከኩት
ላልችል ችየ ቻልኩት።
አልፎክተው ነገር፣ ቆዳዬን መንቅሬ
አላኝከው ነገር፣ ስጋዬን ሰርስሬ
ይኸው እስከዛሬ፣
አጥንቴ እየበላኝ፣ አለሁልሽ(ህ) ፍቅሬ።

@getem
@getem
@getem
👍21
Forwarded from Joyfull Gifts 🎁 via @like
ካሲዮፒያ የግጥም ምሽት በታላቁ ብሔራዊ ቲያትር .... ቀናቶች እየቆጠሩ ነው ... 14 ቀናት ብቻ ቀርተውታል!

ለኢትዮጵያ መልካም ለማድረግ ተዘጋጃችሁ?

ነሐሴ 28/2011 ዓ.ም
ከምሽቱ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ

ከሰፕራይዝ እንግዶች እና ገጣሚያን ጋር!

የማይቀርበት ታላቅ ምሽት!
@cassiopeiacharity
@cassiopeiamedia

አዘጋጅ፡ ካሲዮፒያ የበጎ አድራጎት ማህበር ከአዲስ አበባ ወጣቶች ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር

ለተጨማሪ መረጃ ይደውሉ
0972102935
.በመውደድ ልሽሽ-ሽ.

ውዴ ስላልገባሽ፤ ላንቺ ያለኝ መውደድ
ድካም ስለሆነሽ፤ የምንሄደው መንገድ
እላፊ'ና አላፊ፤ ክፉ ሳልናገር
እንዳይከፋሽ ብዬ፤
ልተው አንቺን ማፍቀር።

[አብርሃም የሙሉ] |

@getem
@getem
@yemulu_lij
1
ማለቀስ መከፋትህ
በሆነው ነገር ላይ ለውጥ ካላመጣ
ሳቅበት ወዳጄ
ስለ ስጋህ ብለህ ነፍስህን አትቅጣ፡፡
ብዬ የማልመክር
የማጣት ክፋቱ ሰርክ የሚያስለቅሰኝ
ብሶታም ነኝና
ዘመናት አልቀሰው
ለደረቁ አይኖቼ እንባህን አውሰኝ፡፡

@getem
@getem
@getem
1
#ሰማያዊት_ቅኔ

በመለኮት ፈትል
ሸማኔ ፈጣሪ ጥበብሽን ቋጭቶ
በሰማይ ሸራ ላይ
ጥለት ሰንደቅሽን እንዲታይ ዘርግቶ
ከህያው መንበሩ
በገዘፈ ክብር ደርሶ ቢያነግስሽም
ባ'ለም ቋንቋ ፍቺ
ከኀላ ተቀምጠሽ ማንም አላየሽም፡፡

ነገሩ እውነት ነው፡፡

የገዛ ልጆችሽ
ውበታም ፊትሽ ላይ ምራቅ እየተፋን
እኛው ጭርታም አርገን
ጭርታም ናት እያልን ስናማሽ ካልከፋን
ሌላው እየናቀሽ
ክብርሽን ቢያወርደው ከቶ ምን ይገርማል
ቢገባን እውነቱ
ትልቅ ሆነው መቅለል ከሞት በላይ ያማል፡፡

አይገርምሽም አይደል?

በባዶ ማንነት
የኛ መዘላበድ እንዲህ መተናነስ
ባልተጨበጠ ውል
በገዛ ግብራችን ከስመን መፈራረስ?

ለምን ይገርምሻል!!

አንቺ እንደው አንቺ ነሽ
በዘመን መለወጥ የማትለወጪ የፈጣሪ ዙፋን
እኛ ነን ሞኞቹ
ያ ሰፊው ጎዳናሽ ጠቦን የሚያጋፋን፡፡
ምናለ በደፋን!!!

#ልብ_አልባው_ገጣሚ

@getem
@getem
1
ለምሽታችን
💚

እንደዚህ አይነት ሸጋ ግጥሞች ቢነበቡ ቢነበቡ አይሰለችም እውነት !!!!




የራስ ገፅ!!
።።።።።።።
አምባሰል ፈገግታሽ፣
አንቺ ሆዬ ዐይኖችሽ፣
ባቲ አረማመድሽ፣
ደማቅ ውብ ውበትሽ፣
ምንኩስና አስጥሎ፣
ከግዜር አስኮብልሎ፣
በፍቅር ቢነድፍም፣
ላንቺ ቢያስመንንም፣
.
.
ጡቶችሽ አስግገው፣
እጅግ ተወጥረው፣
ልብ ቢያሸብሩም፣
በሙቀት ቢያፍኑም፣
.
.
ስትስቂ...
ሀገር ብታደምቂ...
ብርሃን ብታፈልቂ...
.
.
ልሳንሽ ቢጥምም፣
እምነትሽ ቢያይልም፣
.
.
ማተብሽ ቢከርም፣
ኪዳንሽ ቢጠብቅም፣
.
.
ሐቅሽ ባይሻርም፣
ክብርሽ ባይፋቅም፣
.
.
በፍፁም...
በፍፁም...
በፍጹም...
በፍጹም...
እንደብብቴ ላብ...
እንደካልሴ ሽታ...
የነዚህን ያክል...
ትኩረቴን አትስቢም...
.
.
.
.
ምክንያቱም!!
እንዳለት የፀና፡ ልቤን ያሸነፈች፣
ላይን የረቀቀ፡ መንፈሴን ያቀፈች፣
የራሴ ሴት አለች።

((( ዘቢደር ))💚💛❤️

@getem
@getem
@balmbaras
👍1
ጤና ይስጥልኝ 🙏 ሚኪያስ ልየው እባላለሁ (Street photographer ) ነኝ ። አዲስ አበባን እና ማህበረሰብዋን እጄ ላይ በሚገኘው የሞባይል ቀፎ ፎቶግራፍ እያነሳሁ ለማስተዋወቅ እሞክራለሁ። ቻናሌን ተቀላቅላቹ ስራዎቼን እንድትመለከቱ እጋብዛችኋለሁ።
@Mykeyonthestreet
@Mykeyonthestreet
@Mykeyonthestreet
@Mykeyonthestreet
2👍1
በእንተ ማርያም!!!!


ቃል ስጋ ሲነሳ፤
እንደቃልህ ይሁን፤ ይሁን ያልሽለታ፤
የታሰረው አዳም፤
አመክሮው ደርሶ፤ ከወህኒ ተፈታ።


አንች ይሁን ባትይ፤
እንደቃልህ ይሁን፤
ብለሽ ባትቀበይ፤
የገብርኤል ዜና፤
በአማናዊ ልብሽ፤ ቃሉ ባይታተም፤
አውቃለሁ እምየ፤
ከህመም መፈወስ፤ ከሞት መዳን የለም።


እናማ እናቴ ሆይ፤
ቤዛዊተ ኩሉ፤
የጦቢያ ባለቃል፤የመቃተት ደጄ፤
እኔም ልክ እንዳንችው፤
እንደ ቃልህ ይሁን፤የሚል ቃል ለምጄ፤
ሸለቆየ ሞላ፤
እንባየ ታበሰ፤
በእንተ ማርያም እያልኩ፤
በማይጠግብሽ አይኔ፤ በጎደለው እጄ።



((( ጃ ኖ )))💚💛❤️

ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳቹ!

@balmbaras
@getem
@getem
2
እኛ ነን እነሱ

ባንቺ ሆዬ ባቲ፣ መብሰልሰል ባምባሰል፤
እሽሩሩ እያሉ፣ ቤተዘመድ መምሰል፤
ሰንሰለት ሆኖብን፣ ይህው እስከዛሬ፤
የማለዳን ደውል፣ ባልሰማሁም ቅኔ፤
ማታን ተኝተው፣ ጥዋትን ላልተነሱ፤
እንዲህ ፃፍንላቸው፣ በእኛ ቤት ለእነሱ ፡ ፡

እነሱ---
በፀጥታ ሞገድ፣ ዝምታን ሲፈትሉ፤
ተኩላ እያረቡ፣ በጎች ነን ይላሉ።

ይበሉ ግድየለም፤
ድመት አይጥ ሲውጥ የተከፋ የለም።

እረ ሆይ፣
እረ ሆይ፣
ምነው ተኩላ ዝም አልክ፣በግ አይደለንወይ?
እረ ሆይ፣
እረ ሆይ፣
ምነው አፈር ዝም አልሽ፣ አጠሪንም ወይ?

እሽሩሩ ወይኔ፣ እሽሩሩ ወይኔ፤
ዝም አትበል፣ ባለቅኔ፤
የቅኔን ዛር፣ ዝራልኝ ለወገኔ፤

እህህ ትዝታ፣ እህህ አምባሰል፤
ደም አያፈሰሱ፣ በሀዘን መብሰልሰል፤
ወይኔ ወይኔ እያሉ፣ ሀዘንተኛ መምሰል፤

ትብታቡ ሳይፈታን፣ ይህው እስከዛሬ፤
የማለዳን አዛን፣ ባልሰማሁም ቅኔ፤
ኢሻን ተኝተው፣ ሱቢህን ላልተነሱ፤
እንዲህ ፃፍንላቸው፣ በእኛ ቤት ለእነሱ።

እነሱ---
በበገና ቃና፣ ዋሽንት እየነፉ፤
ጭነት ጭነውብን፣ ሸክም ላይ ሲያናፉ፤
አፈር ሰትጠራቸው---
እንደ ዋዛ መተው፣ እንደ ዋዛ አለፉ።

ይለፉ ግድ የለም።
ሁሉም እንግዳ ነው፣ ቤተ-ምድር የለም።

እረ ሆይ፣
እረ ሆይ፣
የካህናት ዜማ፣ መስጂድ አለ ወይ?
እረ ሆይ፣
አረ ሆይ፣
ምነው አፈር ዝም አልሽ፣ አጠሪንም ወይ?

እሽሩሩ ወይኔ፣ እሽሩሩ ወይኔ፤
አንድ በለኝ፣ ባለቅኔ፤
የቅኔን ዘር፣ እጨድልኝ ከወገኔ፤

የታጨደን ቅኔ፣ ጥሰን እንዳንተኛ፤
እኛ በእነሱ ቤት፣ እነሱ ነን እኛ።


©ከድር አሊ

@getem
@getem
@getem
#የፍቅርሽ_ትንታ#

በረቀቀ ጥበብ በረቀቀ ሚስጥር
ያለምንም ስስት ያጎረሺኝ ፍቅር
ጨጓራዬን ትቶ ልቤ ላይ በማረፍ
በፍቅር ትንታ ዘውትር ስንደፋደፍ
ይሻለኛል ብዬ ከዛሬ ከነገ
ጀርባዬን ባስመታም ይባስ እያደገ
ሊለቀኝ አልቻለም የፍቅርሽ ትንታ
ውሀም ብጠጣበት ጠዋትና ማታ።

*ሄኖክ ብርሃኑ***

@getem
@getem
*መራራ ነዉና*

ነገሩም ታከተኝ ወሎ እና አዳሩ
ለማይገባ ነገር የኑሮ ሚስጥሩ
የሚመር ከሆነ እንዲ ህይወት ጎሞርቶ
እና ምን ጎደለዉ ሰዉ ሲያርፍ ሞቶ?

ልጅ ሞሌ

@getem
@getem
#ፍቺ_ምህላ

በኪዳነ ቃሏ በፆመ ሱባኤ
ከበርባሮስ ጋሪ መውረጃ ትንሳኤ
አዘቅት አንደርድሮ የዘመን ሉቃጦ
አረንቋ .. ...ሳይረፍቀኝ
የደፈረሰ ወንዝ ...ሰርኔን ሳይሰንገኝ
ደራሽ ሳያነሳ ...ቋጥኝ ሳይግድለኝ
የሞተ ከብት በልቼ ነብሴን ሳላጎድፍ
የታጠፈ አንጀቴን በሀሜት ሳልገድፍ
የእድሜ ዘመን በደል.... የዝንተ ለት ነውሬን
ለገሞራ ዙፋን ...ለዳቢሎስ ስልጣን
የሚደግፍ ሀሲድ ....ቀንዳንም ሽልም ሰይጣን
ነጋሪት ጎስሞ
ጡሩንባ ለፍፎ
አሳላፊ አበጅቶ
በደም ስሬ ሀጢያት ቀዝፎ
በፅድቅናዬ ወራት... በጥሞና ግዜ
በእግዚዎታ ሰአት ......በንስሀ ግዜ
ገሀነም ሰድሮ ፥ ሊገል የበረታ
የተሳለ ህፀፅ ፥ የተማታ ካርታ
ተደግኖ.....በ'ሬ
የግፍ ቁና ...የሬት ጎሬ
ብኩን ውላድ ከንቱ ፍሬ
ሚዛን ደፍቶ በዝቶ ነውሬ

ይህች ትንፋሽ... አትቅለል!!!
ገነት ሳለች ....ለሲኦል
ውሀ ሳለ .......መቃጠል
እጣ ግታ....አትዋል።
የባከነች ነብሴን..... አድናት!!!
አላፊ በድን .......አይግዛት!!!
አጧጡመኝ ክንዴ.... አብቃኝ ለመሰንበት
የከረፋ ስጋ ነብሴን.... ቀን ያውጣለት
ብዬህም አልነበር!!!
ሀ_ሌ_ሉ_ያ....
ሀሌሉያ....ክበር!!!
ሀሌሉያ ..ትክበር!!!
አዛኝቷ ማርያም ወላጅ እናቲቱ
በፍልሰታሽ ፍቺ..ልክ በእለቱ
ባንቺ ትልቅ ምልጃ በልጅሽ ውህብቱ
................... በዝቶልኝ ምህረቱ
ከሚፀድቁ ልዋል......ልቁም ከሚፈቱ
አሜን!!!

#አብርሀም_ተክሉ

መልካም ፆመ ፍቺ

@getem
@getem
@getem
1
#ምንማም~ምንሞች

በምንም ማንነት
ምንሞች ለምንም
ምን ሆነሀል ሲሉኝ በምንም አልቄ
ምንም የምላቸው
ከምንም ጓዳዬ ምንሜን ደብቄ
ወድጄ አይምሰልህ
እንዳይነጥቁኝ እንጂ
በምንም እጃቸው ምንም እኔነቴን
ምንም ናቸውና
ምንሜን ላይምሉት
ለኚህ ምንማሞች አላሳይም ቤቴን፡፡

#ልብ_አልባው_ገጣሚ
@getem
@getem
1