#ሰማያዊት_ቅኔ
፡
በመለኮት ፈትል
ሸማኔ ፈጣሪ ጥበብሽን ቋጭቶ
በሰማይ ሸራ ላይ
ጥለት ሰንደቅሽን እንዲታይ ዘርግቶ
ከህያው መንበሩ
በገዘፈ ክብር ደርሶ ቢያነግስሽም
ባ'ለም ቋንቋ ፍቺ
ከኀላ ተቀምጠሽ ማንም አላየሽም፡፡
፡
ነገሩ እውነት ነው፡፡
፡
የገዛ ልጆችሽ
ውበታም ፊትሽ ላይ ምራቅ እየተፋን
እኛው ጭርታም አርገን
ጭርታም ናት እያልን ስናማሽ ካልከፋን
ሌላው እየናቀሽ
ክብርሽን ቢያወርደው ከቶ ምን ይገርማል
ቢገባን እውነቱ
ትልቅ ሆነው መቅለል ከሞት በላይ ያማል፡፡
፡
አይገርምሽም አይደል?
፡
በባዶ ማንነት
የኛ መዘላበድ እንዲህ መተናነስ
ባልተጨበጠ ውል
በገዛ ግብራችን ከስመን መፈራረስ?
፡
ለምን ይገርምሻል!!
፡
አንቺ እንደው አንቺ ነሽ
በዘመን መለወጥ የማትለወጪ የፈጣሪ ዙፋን
እኛ ነን ሞኞቹ
ያ ሰፊው ጎዳናሽ ጠቦን የሚያጋፋን፡፡
ምናለ በደፋን!!!
#ልብ_አልባው_ገጣሚ
@getem
@getem
፡
በመለኮት ፈትል
ሸማኔ ፈጣሪ ጥበብሽን ቋጭቶ
በሰማይ ሸራ ላይ
ጥለት ሰንደቅሽን እንዲታይ ዘርግቶ
ከህያው መንበሩ
በገዘፈ ክብር ደርሶ ቢያነግስሽም
ባ'ለም ቋንቋ ፍቺ
ከኀላ ተቀምጠሽ ማንም አላየሽም፡፡
፡
ነገሩ እውነት ነው፡፡
፡
የገዛ ልጆችሽ
ውበታም ፊትሽ ላይ ምራቅ እየተፋን
እኛው ጭርታም አርገን
ጭርታም ናት እያልን ስናማሽ ካልከፋን
ሌላው እየናቀሽ
ክብርሽን ቢያወርደው ከቶ ምን ይገርማል
ቢገባን እውነቱ
ትልቅ ሆነው መቅለል ከሞት በላይ ያማል፡፡
፡
አይገርምሽም አይደል?
፡
በባዶ ማንነት
የኛ መዘላበድ እንዲህ መተናነስ
ባልተጨበጠ ውል
በገዛ ግብራችን ከስመን መፈራረስ?
፡
ለምን ይገርምሻል!!
፡
አንቺ እንደው አንቺ ነሽ
በዘመን መለወጥ የማትለወጪ የፈጣሪ ዙፋን
እኛ ነን ሞኞቹ
ያ ሰፊው ጎዳናሽ ጠቦን የሚያጋፋን፡፡
ምናለ በደፋን!!!
#ልብ_አልባው_ገጣሚ
@getem
@getem
❤1
#ምንማም~ምንሞች
በምንም ማንነት
ምንሞች ለምንም
ምን ሆነሀል ሲሉኝ በምንም አልቄ
ምንም የምላቸው
ከምንም ጓዳዬ ምንሜን ደብቄ
ወድጄ አይምሰልህ
እንዳይነጥቁኝ እንጂ
በምንም እጃቸው ምንም እኔነቴን
ምንም ናቸውና
ምንሜን ላይምሉት
ለኚህ ምንማሞች አላሳይም ቤቴን፡፡
#ልብ_አልባው_ገጣሚ
@getem
@getem
በምንም ማንነት
ምንሞች ለምንም
ምን ሆነሀል ሲሉኝ በምንም አልቄ
ምንም የምላቸው
ከምንም ጓዳዬ ምንሜን ደብቄ
ወድጄ አይምሰልህ
እንዳይነጥቁኝ እንጂ
በምንም እጃቸው ምንም እኔነቴን
ምንም ናቸውና
ምንሜን ላይምሉት
ለኚህ ምንማሞች አላሳይም ቤቴን፡፡
#ልብ_አልባው_ገጣሚ
@getem
@getem
❤1
#ልብ_አልባው_ገጣሚ
.
.
የማላውቀው ስሜት
ደርሶ እያነዘረኝ ውስጤን እየናጠው
ሶስቱን ቀለማቶች
አይኔ ባየ ቁጥር የምደነግጠው
ዘመን የማይሽረው
የማንነት ክብርሽ ነውና እያዘዘኝ
ለምን ሆነ አልልም
ዝንታለም ልታሰር ፍቅርሽ ይወዝውዘኝ፡፡
፡
ደግሞ ታውቂኛለሽ
ሀበሻዊው ልቤ ለምስኪን ቢራራም
ባንቺ ከመጡብኝ
ከፈጣሪ በታች ማንንም አልፈራም፡፡
@getem
@getem
@getem
.
.
የማላውቀው ስሜት
ደርሶ እያነዘረኝ ውስጤን እየናጠው
ሶስቱን ቀለማቶች
አይኔ ባየ ቁጥር የምደነግጠው
ዘመን የማይሽረው
የማንነት ክብርሽ ነውና እያዘዘኝ
ለምን ሆነ አልልም
ዝንታለም ልታሰር ፍቅርሽ ይወዝውዘኝ፡፡
፡
ደግሞ ታውቂኛለሽ
ሀበሻዊው ልቤ ለምስኪን ቢራራም
ባንቺ ከመጡብኝ
ከፈጣሪ በታች ማንንም አልፈራም፡፡
@getem
@getem
@getem
❤1
ከጎርፍ አለም ገፈት
ከጥልቁ ሊያተርፈኝ ደክሞት የታገለ
የትከሻው ጉልበት
በመከራው ብዛት ስለኔ የዛለ
ሞቶ የሚያኖረኝ
ይህ ነው አባቴ ህልሞቼን ያዘለ፡፡
፡
መልካም የአባቶች ቀን
#ልብ_አልባው_ገጣሚ
@getem
@getem
@getem
ከጥልቁ ሊያተርፈኝ ደክሞት የታገለ
የትከሻው ጉልበት
በመከራው ብዛት ስለኔ የዛለ
ሞቶ የሚያኖረኝ
ይህ ነው አባቴ ህልሞቼን ያዘለ፡፡
፡
መልካም የአባቶች ቀን
#ልብ_አልባው_ገጣሚ
@getem
@getem
@getem
❤1
🌼🌼🌼
#ልብ_አልባው_ገጣሚ
.
ከመጣብን ቁጣ
በፈጣሪ ፀጋ ከመሞት ተሽረን
ተባልተን ሳናልቅ
በምህረት ታንኳ ዘመን ካሻገረን
:
ሚመጣውን ግዜ
ባብሮነት እናብብ በተስፋና በምነት
የሀገሬ ልጆች
ሰላሙን ያብዛልን መልካም አዲስ አመት፡፡
@getem
@getem
#ልብ_አልባው_ገጣሚ
.
ከመጣብን ቁጣ
በፈጣሪ ፀጋ ከመሞት ተሽረን
ተባልተን ሳናልቅ
በምህረት ታንኳ ዘመን ካሻገረን
:
ሚመጣውን ግዜ
ባብሮነት እናብብ በተስፋና በምነት
የሀገሬ ልጆች
ሰላሙን ያብዛልን መልካም አዲስ አመት፡፡
@getem
@getem
#ልብ_አልባው_ገጣሚ
.
.
ሰው በሞተ ቁጥር
መግደል መሸነፍ ነው የሚል ከንቱ ተረት
ሟቹን ላያነሳ
ገዳይ ላይሸነፍ
መልመድ ካስተማረን እየወጡ መቅረት
:
ይቅርብን ስብከቱ
የቃሬዛ ሲሳይ መሆን ይታክታል
በማይሸነፉ
ስሜት አልባ ልቦች እልፍ ሰው ይሞታል።
:
እናም ለገዳዩ
የሽንፈትን ፅዋ ገሎ ለማይቀምሰው
በሟቹ ልትቆምር
በማይረባ ስብከት ድፍረት አታውርሰው
በቅቶናል አንተ ሰው።
@getem
@getem
.
.
ሰው በሞተ ቁጥር
መግደል መሸነፍ ነው የሚል ከንቱ ተረት
ሟቹን ላያነሳ
ገዳይ ላይሸነፍ
መልመድ ካስተማረን እየወጡ መቅረት
:
ይቅርብን ስብከቱ
የቃሬዛ ሲሳይ መሆን ይታክታል
በማይሸነፉ
ስሜት አልባ ልቦች እልፍ ሰው ይሞታል።
:
እናም ለገዳዩ
የሽንፈትን ፅዋ ገሎ ለማይቀምሰው
በሟቹ ልትቆምር
በማይረባ ስብከት ድፍረት አታውርሰው
በቅቶናል አንተ ሰው።
@getem
@getem
👍3