ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ሰማያዊት_ቅኔ

በመለኮት ፈትል
ሸማኔ ፈጣሪ ጥበብሽን ቋጭቶ
በሰማይ ሸራ ላይ
ጥለት ሰንደቅሽን እንዲታይ ዘርግቶ
ከህያው መንበሩ
በገዘፈ ክብር ደርሶ ቢያነግስሽም
ባ'ለም ቋንቋ ፍቺ
ከኀላ ተቀምጠሽ ማንም አላየሽም፡፡

ነገሩ እውነት ነው፡፡

የገዛ ልጆችሽ
ውበታም ፊትሽ ላይ ምራቅ እየተፋን
እኛው ጭርታም አርገን
ጭርታም ናት እያልን ስናማሽ ካልከፋን
ሌላው እየናቀሽ
ክብርሽን ቢያወርደው ከቶ ምን ይገርማል
ቢገባን እውነቱ
ትልቅ ሆነው መቅለል ከሞት በላይ ያማል፡፡

አይገርምሽም አይደል?

በባዶ ማንነት
የኛ መዘላበድ እንዲህ መተናነስ
ባልተጨበጠ ውል
በገዛ ግብራችን ከስመን መፈራረስ?

ለምን ይገርምሻል!!

አንቺ እንደው አንቺ ነሽ
በዘመን መለወጥ የማትለወጪ የፈጣሪ ዙፋን
እኛ ነን ሞኞቹ
ያ ሰፊው ጎዳናሽ ጠቦን የሚያጋፋን፡፡
ምናለ በደፋን!!!

#ልብ_አልባው_ገጣሚ

@getem
@getem
1