ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
መልካም ልደት ለንጉሳችን
ዶክተር ኤሊያስ ገብሩ

@getem
@getem
@getem
ቡሄ በዪ(ልዑል ሃይሌ)
ሙልሙል ዳቦ ስጪኝ
ችቦ እኔ አበራለሁ፤
አንቺ ጅራፍ ሁኚ እኔ አጮህሻለሁ፤
እየተረዳዳን ቡሄ እናስመስለው፤

@getem
@getem
##### ምኒሊክ !!!!!!!!!!!!!!!!!! ####
ምኒሊክ ተወልዶ ፤
ባይተኩስ ናስማሰር ፤ ባያነሳ ሞይዘር ፤
ጎበና አድዋ ላይ ፤
ባልቻ አምባላጌ ላይ ፤
አትንኳት ሃገሬን አትንኳት እያለ ባይነቀንቅ ዘገር ፤
ይህን ጊዜ ባንዳ ፤
""አፋንኩሎ!!!"" እያለ ፓስታ እያስቀቀለ፤ ተጫውቶብን ነበር ።
ምኒሊክ ተወልዶ ባይባል ነፍጠኛ ፤
ኧረ ጎራው ብሎ ፤
ጥሻ ባይመነጥር የአባ ዳኘው አሽከር የእቴጌ መልከኛ፤
አወይ ይህን ጊዜ፤
አሰሱን ገሰሱን ተሸከም እያለ ተጫውቶብን ነበር ባንዳና ጎጠኛ ።
ምኒሊክ ተወልዶ እዝነት ሞልቶ ተርፎት ባይባል እምዬ ፤
አባ ዳኘው ሲዘልቅ፤
ገበየሁ ባይመጣ ሰላቶ እየወቃ ጦር እያበራየ ፤
መይሳው ጃሎ ሲል እሳት እየተፋ ባይመጣ ገብርዬ ፤
አቤት በዚህ ሰሞን አገር ሞታ ነበር ኧረ እናንተ ሆዬ ።
ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሳ ሰንደቅ ባይጠምድ ዲሞፍተር፤
በጣይቱ ወኔ ፤
እንሂድ ተብሎ መሃል ወረኢሉ ማርያምን ተብሎ አዋጅ ባይነገር፤
መቼም ይህን ጊዜ፤
ሹምባሻና ባንዳ፤እንደዝክር ቂጣ፤ ቁርስርስ አድርጎ ተጫውቶብን ነበር ።
በጦቢያ ምድር ላይ፤ በአበሾች ሰማይ፤
ነሃሴ ውሃ አዝሎ ፤ ሲያዘንብ ሲሳይ፤
ምኒሊክ ተወልዶ ፤ ጥቁር ሰው ባናይ፤
ጭጋጉን ገንድሳ፤
ደመናውን ሰብራ ፤ ባትወጣ ጠሃይ ፤
ጦቢያን ያህል ሃገር ፤ ይገኝ ነበር ወይ? ???

((( ጃ ኖ )))💚💛❤️

👑👑👑👑መልካም ልደት👑👑👑👑

@balmbaras
@getem
@getem
ቡሄ በሉ…

ሀብል መልቲሚዲያና ማስታወቂያ "ቡሄ በሉ…" የተሰኘ አመታዊ የቡሄ በአል ክቡረ በአል
ባህላዊ፣ ሀይማኖታዊ እና ኪነጥበባዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ በየአመቱ የቡሄን በዓል
ለማዘጋጀት አቅዷል።
በዚህም መሰረት ዘንድሮ የመጀመሪያው "ቡሄ በሉ…፩" አመታዊ የቡሄ ክብረ በዓል
"ዱላችን ለጭፈራችን፤ ጭፈራችን ለሰላማችን!" በሚል መሪ ቃል ልዩ ኪነ-ጥበባዊ ምሽት
በዕለተ ቡሄ ነሀሴ 13 ቀን 2011 ዓ.ም አመሻሽ 11:30 ጀምሮ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል
ተሰናድቷል።
በዚህ ዝግጅት ላይ የኢትዮጵያ የጃዝ ሙዚቃ አባት ዶ/ርሙላቱ አስታጥቄ በክብር
እንግድነት ሲገኙ:-
ቅኔ:- በደራሲ አበረ አዳሙ
የደብረ ታቦር ዝማሬ:- በማህበረ ቅዱሳን
ዲስኩር:- በመጋቢ ብሉይ አይነኩሉ ጌታነህ፣ በደራሲና ጋዜጠኛ ዘነበ ወላ እና በስነ-ጥበብ
መምህሩ ዮናስ ሀይሉ
ግጥም:- በነብይ መኮንን፣ ኤፍሬም ስዩም፣ ሰለሞን ሳህለ፣ ፍሬዘር አድማሱ እና በላይ
በቀለ ወያ
ወግ:- በጋዜጠኛና ገጣሚ ተፈሪ አለሙ፣ አርቲስት አለማየሁ ታደሰ እና በተጓዡ ጋዜጠኛ
ሔኖክ ስዩም
ትውፊታዊ ድራማ:- በዋ ያቺ አድዋ ተጓዥ የትያትር ቡድን በመድረኩ የሚቀርቡ ይሆናሉ።
መድረኩን ጋዜጠኛ ሚካኤል አለማየሁ (የእናኑ ልጅ) ይመራዋል።
አዘጋጅ ሀብል መልቲሚዲያና ማስታወቂያ
የመግቢያ ዋጋ:- 100 ብር
ለበለጠ መረጃ 092253 64 69 ይደውሉ።

@getem
@getem
ሰፈሯ አዲሱ ሰፈር ነው ስሟ ሄዋን ተሻለ ነው ቀይ አይኗ ተለቅ ተለቅ ያለ ናት ዛሬ12 ቀን ሆናት ሀምሌ 30 ጠዋት ኪዳነምህረት ፀበል ልትጠመቅ የወጣች እስካሁን አልመጣችም ያያት ወይም ያለችበትን የሚያውቅ
+251910047874
+251972101536
+251913005544
contact ያርገን
👍1
፨፨፨፨የይቅርታ መሐልይ፨፨፨

ማነዉ የፈለገኝ?
በማይነጋ ሌሊት
በማይመሽ ቀን መሀል
ተዘርሬ ስገኝ።
ከተዉሽኝ በኀላ 'ርቃን ቀርታ ነፍሴ
እንኳን ከሰው ዐዉድ ተነጠልኩ ከራሴ፡፡
፨ ፨ ፨
ተመልሼ ልምጣ ተመልሰሽ ነዪ
ልጣል ምሰሶዬን ማገርሽን ጣዪ
አዲስ ቤት መገንባት ዛሬ መች ይደላል
ለምደዉ ወደተዉት መመለስ ይቀላል፡፡
፨ ፨ ፨
ካሳ ባልክልሽ ቁና ጤፍ ሰፍሬ
ባዶ እጄን አልቆምም ከደጅሽ ደፍሬ
ጵንፍ የለሽ ይቅርታን ውሰጅ ከከንፈሬ፡፡
★★★በእውቀቱ ስዩም★★★

@getem
@getem
@gebriel_19
1👍1
ለውብ ቀን
💚


ያኔ እንዲህ ነበር ጥንዶች ፍቅራቸውን ሲገልፁ


ማሚቴ ማሚቴ ባለቤቴ

ከበደ ከበደ ከብዬ ጎምላላዬ

እኔና አንቺ ሁነን ኧረ ስንቱን አለፍን


ማሚቴ ማሚቴ ባለቤቴ


ከበቡሽን ስንድር
ባቡር አዲስ ነበር


ከበደ ከበደ ከብዬ ጎምላላዬ

አይሮፕላን ሲመጣ
ሞገሴ ግግ ሲያወጣ
ታስታውሻለሽ ወይ


ማሜቴ ማሚቴ ባለቤቴ


አልተረሳኝም ኧረ እስተዚህ ጃጄሁ ወይ
የሞገሴ እድሜ እንዴት እረሳለሁ ወይ
አርባ ሦስት አመቱ ህዳር ሚካኤል
ምምሬ አልታየ ከበቅሎ ሲወድቁ
ጊዜው ስንት አመት ነው ይሄንን እወቁ


ከበደ ከበደ ከብዬ ጎምላላዬ

በዚያኑ አመት ነው በግንቦት ወራት
የሙሉውን መሬት ልሸጥ የሄድኩት


ማሚቴ ማሚቴ ባለቤቴ


ኧረ ለመሆኑ ተሆነስ ሆነና
ምን ነበር የሰሩኝ ታች አምና ለገና


ከበደ ከበደ ከብዬ ጎምላላዬ


የታቻምናው ነገር መች ይታወሳኛል
የዱሮውን አምጭ እሱ ይሻለኛል


ማሚቴ ማሚቴ ባለቤቴ
አይ የርሶ ነገር በጣም ይገርማሉ
ከቅርቡ ለሩቁ እንዴት ይፈጥናሉ


ከበደ ከበደ ከብዬ ጎምላላዬ
ማሚቴ
ከበደ
©ሰዓሊው ዳንኤል ጌታሁን

ይቺን ሙዚቃ ብዙ ሰው ያውቃታል ብዬ አስባለሁ ግጥሟን እና ሙዚቃዎን አዋህዶ ማዜም ነው እንግዲህ..

@getem
@getem
@balmbaras
==ምፅውት-ሕመም==(ልዑል ሃይሌ)
.
ሕመም ተ-ው-ሻ-ለ-ሁ
ራስ ከታመመ ሠው፤
ማይማር ገላዬ
ስቃይ እንዲደርሰው፤
በሕመም ያለፈ
ሲሽር ሲጠነክር ዘመናት ታዝቤ፤
ሕመም ተመፀወትኩ
በፈውስ ፍለጋ ብርታትን አስቤ፤
.
(ይኸው ምፅውት ሕመም...)
.
ስቃይን ከስቃይ እየተለካካሁ፤
ሠውነቴን ላውጅ በሕመም ተመካሁ፤
ምንም ብድር ሕመም
ባያም' እንደመፅዋች እንዳበደረው ሰው፤
ላፍታም አያስተኛም
መድኃኒት ፍለጋ እ-የ-ቀ-ሰ-ቀ-ሰ-ው፤
.
(ይኸው ቀሰቀሰኝ...)
.
ከየቅጠሉ ላይ ከየስራስሩ፤
ሕልሞች ይታዩኛል
የኔን ሐኪምነት የሚመሠክሩ፤
.
ልበጥስ ያን ቅጠል
ልንቀለው ያንን ስር፤
ያድነኝ እንደሆን
ከገባሁበት ማጥ ከሠው ሕመም እስር፤
.
ልፈልግ ድኅነቴን
ልፈልግ ድኅነቱን ለመፅዋች ታማሚ፤
ምፅውት ሕመም ያ'ርገኝ መድኃኒት ቀማሚ፤
.
(ይኸው ቅመማዬ...)
.
ሕመም አይጥፋ እንጂ
መድኃኒት አይጠፋም፤
ስቃይ የበዛበት
ፈውስ ያስባል እንጂ ላፍታ አያንቀላፋም፤
.
እኔም የሠው ሕመም
ተመፅውቼ ያደርኩ የጊዜ ታማሚ፤
ፈውሱን ነው 'ምከፍለው
ሕመም ስላ'ረገኝ መድኃኒት ቀማሚ፤

@getem
@getem
ጥቁር_ዕንባ
________________
ከጌታዬ ተመስገን(jalude)

አዬ... ጎጆዬ!
እኔ ሆኜ-ህመምተኛ፣
ተኝቼልሽ-በቁራኛ፤
እዚህ...
ሀዘን ካጨገገው-ሞት ካደራበት ቤት - የሞት አምባ፣
ድማ'ን ሳቆች-ከሸመኑት ጥቁር ዕንባ፤

መልከ-ጠይም ባጥሽ-በሀዘን ፅላሎት...
ሽማን ድር አቅልሞ-ጠቀራውን ለብሷል፣
ከመቃ-አንገትሽ ላይ-ውዝ-ጠገብ ወጋግራሽ...
በክታብ ተነቅሶ-'ርቃኑን ተሰቅሏል፤
እኔ እንደሆንኩ ህመምተኛ፣
የሺህ አሳባት ዋናተኛ፣
ያልጋ አዳሪ የቁራኛ፣
ቁሜ ማልሄድ መፃተኛ፤
የስትንፋሴ ላቦት ዝሪያ !ኡሁ'ታዬን የሚያሰማ፣
እንደ ክራር የሚገርፈኝ-የሚንጠኝ ቀጭን ዜማ፤
'ለቅሶ አይሆን-ወይ ሙዚቃ፣
የዕሪታ አይሉት-ወይ የሲቃ፣
ከሞት እንቅልፍ-የሚያባንን የሚያነቃ፣
ንዴት! አለ'!!
የሚያነደኝ የ'ሳት ንባ'ል-የ'ሳት ላንቃ::

እዚያ ከማዠትሽ...
የነተበች የወየበች-ብጣይ ቡትት፣
ከመግቢያሽ ላይ-ጣል ያረግሻት እንደዘበት፤
'የኔን እድሜ-የምትቆጥር፣
የሞቴን ቀን-የምትሰፍር፤
ዛሬ ያንቺ-የገመና መሸፈኛ፣
ነገ የኔ-የበድኔ መከፈኛ፤
(ክፉ ምልኪ!...)' እያልኩ አስባለሁ፡፡

እናም ከማዠትሽ...
የወጠንኩት አሳብ-ትብትብ መቀነትሽን...
በልስልስ ጣቶችሽ-አጥብቆ የያዘ፣
ከውብ ፊት ገፅሽ ላይ-ከብሌንሽ ግርጌ...
ባይኖችሽ ሽፋሎት-ዕንባን ያረገዘ፤
የሞት አዚምሽን-ፅንሱን የገደለ
ጅምር አሳብ አለ
በዕንባ የተኳለ፡፡
ዕንባ ቢሉት...
ዕንባ የ'ሳት-'ሳት የዕንባ!
ከትናንትሽ-የተራባ፣
የነገሽን-ያስተጋባ፤
ከነፋስ የሳሳ ብን...ትን... የሚል ጢስ፣
ከአልጋዬ መጦ-አይኖቼን ሚዳብስ፤
ሙጣጭ ጭላጭ-ብናኝ ተስፋ!!
ወይ ያልሞቀ ወይ ያልጠፋ!!
--------------------------

@getem
@getem
ናፍቆት ይህ ነው እንዴ...

ድብን ባለው ሙቀት ድብን ባለው ቀትር
ገላዬ ቅርብ ነው ለብርድ ለውሽንፍር
ደግሞ
በጨለማ በሌሊት መዓልት ላይ
ያይን ብሌኔ ስር
ፀሃይ ተንቀልቅላ ደምቃ ነው ምትታይ
አንዳንዴም ወደ ምስራቅ ስዞር በጧት ተነስቼ
ግራ ይገባኛል
ከፀሃይ መውጣት ጋር ምስልሽን አይቼ
ኧረ ትላንትማ....
በገነፈለ ብዕር ጎልታ የተሳለች
ትንሽ ፅጌረዳ
በትንሽ ሸራ ላይ ጎልታ ትታያለች
ያቺን ያየ ቀልቤም ግድግዳ ላይ ወጥቶ
ሊስልሽ አሰበ በውጥር ሸራ ላይ ውጥር ውበት አይቶ
===========
እኔ ምለው ውዴ
ናፍቆት ስሩ እንዴት ነው?
እንዴት ነው ሚያደርገው?
=============
ይሄ የኔው ነገር
በመዓልት በሌሊት ሚመጣው አንዳንዴ
ናፍቆት ይሆን እንዴ??????
እባክሽ ንገሪኝ!!!!

ቤላ የእናቱ ፍሬ

@getem
@getem
@getem
የሚተኙበትን አልጋ እያፈረሱ፤
እኛን የሰለቹን፤
እንቅልፋችን ጠፋን ብለው የሚያለቅሱ ።

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

@getem
@getem
@balmbaras
👍1
ቅድም ስትደውይ
<unknown>
ገጣሚ ሰለሞን ሳህለ
አንባቢ ታምራት ጀምበሩ

@getem
@getem
@getem
ብረት እና ቁርበት
(ተስፋ ብዙወርቅ)

ማን አለ እንደኔ?
ቀስትና ደጋንን በሮኬቶች አቻ
ቁርበት ሰራሽ ጋሻን ካረር መመከቻ
ብረት ኮንቴነርን ከሌጦ ስልቻ
አላቻ ሚያነጽር
እንደኔ ማን ኖሮ?
አላቻም አንጽሮ
ከሮኬት ካረሩ የብረት ትግግል፣
ለቀስት እና ደጋን ለጋሻ ሚያጋድል
ሮኬት ሚያኮስስ በቁርበቱ ገድል
ማን አለ እንደኔ? የተወላገደ፣
ከሃቅ ብረቱ ቁርበት የወደደ፡

@getem
@getem
@getem
በውይይት አለም
ሚኒባሱን መርጠን ሰልፉ እያጋፋን
ባ'ንበሳው ተዋደን
ለሚኒባስ ህይወት ሀገር ሸጠን ጠፋን፡፡

እስቲ ላዳው ቀርቶ
ካሰብነው ለመድረስ ለባስ እንሰለፍ
እረዥሙን መንገድ
በውይይት ታክሲ ሳናውቀው እንለፍ፡፡

።።።ልብ አልባው ገጣሚ።።።

@getem
@getem
@gebriel_19
#ያምና ናፍቆት !!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።
እሷን አስብና !
የቀድሞዋ ፍቅሬን፦
ያምናዋ ወዳጄን...
እኔ ባጠፋሁት ፥ በበደልሁት በደል
ይቅርታ ማለቷን ፥ ከኔ እንዳትነጠል
ደግሞ አንቺን አይቼ ...
በምትምሽው ገደል ፥ በለኮስሽው እሳት
ሳለ ያንቺው ጥፋት!
እኔው ይቅር ብዬ ...
ደጅሽ ላይ ተጥዬ ...
በተማጥኖ እንባ ፥ ወራት ባስቆጥርም
ፍቅሬን ስትገፊ ፥ ልብሽ እንዲለግም
አገኘሁ እላለሁ!
ያምና ብድራቴን
እሷ ላይ የቆየኝ
የሐጥያት ውርሴን ።
ይኸው ዛሬም ድረስ!
እሷ ባቀናችው ፥ ጎጆ በማይበቁ
ለሷ በቀለድሁት ፥ ቀልድ በማይስቁ
እሷን ባስለቀሳት ፥ መርዶ በማያዝኑ
እሷን በማረካት ፥ ቦታ 'ማይዝናኑ
ከክፍቱ ጎኔ ፥ መሙላት በማይችሉ
አንዴ በሚረዝሙ ፥ አንዴ በሚጎድሉ
በግዑዛን ሴቶች ፥ መንደር ተሰልፌ
አምናን እራባለሁ ፥ ዘንድሮን ታቅፌ።

@getem
@getem
@getem