ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ግፍ ይሆን

አንቺን ባ`ንድ ጣምራ በሾርኔ ያየሁሽ
በስላቅ ፈገግታ በአይን ያወራሁሽ
የመለኮት ቁጣ እስኪወርድ ያቀፍኩሽ
በምናቤ ይሁን ወይስ ውሸት ነበርሽ?

ልጠይቅሽ ውዴ
በእፉዬ ገላ ይዞ በለቀቋት
ንፋስ በሚያባራት
አባረን ላንይዛት ይዘን ላናስቀራት
የተሯሯጥንላት የተወናበድነው
እስከዚች ወይ ነበረ ፍቅርን ያፈቀርነው
ላንጨርሰው ነገር መንገድ የጀመርነው?

ልጠይቅሽ ሆዴ

ወልደን ከብረን ነጥቀን ብለን ያልነው ያኔ
ነገ የለም ብለን ወይስ ላይሆኑ ተስፋ ነው
ልቡን ለመጠበቅ በሚል ብሂል ታስረሽ
ሳትወጂኝ ነበር ወይ ስወድህ ማለትሽ?

እማ ምትፈቅጂልኝ ከሆን
አንዴ ልጠይቅሽ
ሺ ንጉስ ደርድረሽ ሺ ንጉስ ምትመርጪ
ምን ላይ ልታነግሺ
አላያ ተዋድቀው ግምት ልታወጪ?
ዛዲያ ደሞ ከርሞ ጦርነቱን ፍልሚያ
ንግስቷን የመውስድ የንጉሶች ግጥሚያ
ሰውነት አቁስሎ ግን ስንቱን ንጉስ ጥሎ
ወዳንቺ የመጣ አካሉን አጉድሎ
ንጉስ ይሆናል ወይ ባንቺ መንበር ከብሮ
ወይስ መዝናሽ ነው እንዲህ አይነት ኑሮ
የሰው ሀዘን ሲቃ ሚያረካሽ እሮሮ!

ፍቅር አለም ልጠይቅሽ እስቲ
ባትመልሺም እንኳ ስለኔ ግድ የለም።
አንቺን እሚያስገድድ ደፋር ንጉስ የለም
ቀረርቶ ሽለላ ፉከራ ሚያውድሽ
ልብሽ ጀግና ሚወድ ግራ ግብ መሻትሽ

አንቺጋ ሲደረሱ የፊትዮሽ ኋላ
ኋልዮሽ ፊትዮሽ እሚሆነው ሌላ
ግራ ገብ ባህሪሽ ተጠናውቷቸው
ወይስ ማስመሰል ነው?

ደጀን ነው ስቲይኝ ቀርቤ ያየሁት
ጅማተ ቆራጣ ዝል ክንደ ፋድያት
ድጋፌ እሚያሻው ስለ ልቡ ጡዘት
መሆኑን አልደብቅ የህጣን ልጅ ቅንጣት

#ኤሽታ
@getem
@getem
@gebriel_19
የሞተ ተጎዳ
"""""""""""""""

በብዙ አውርተን
በብዙ እንረሳለን
ለድንገት ገላልጠን እንሸፍነዋለን
እንደ ተልባ ስፍር
እንሰፈርና ወዲያው እንፈርሳለን።

ህይወታችን ሆኖ

ጊዜያዊ ጭብጨባ ጊዚያዊ ሆሆታ
እንባ ቢዘረገፍ ደረትም ቢመታ
እንዲያው ለጊዜያዊ ለጥቂት ለአፍታ
አንዳንዱም ለይምሰል አንዳንዱ ለታይታ

እንደው ለጊዜያዊ

ሀዘን ቢሰቅሰን ሆዳችን ቢባባ
ልባችን ቢሰበር
አይን እንባ ቢያዝል ለለቅሶ ቢዳዳ
ያለፈው አለፈ
የቀረው ቀረ እንጂ የሞተው ተጎዳ
እናውቅበታለን
እየሳቁ ማልቀስ ለተስካር ፍሪዳ!!!

አብርሃም

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
ለተገፋ ሁሉ ፍርድ እንዳይታጣ፣
ድመት ሌሊት አይሂድ አይጥ ም ቀን አይምጣ

@getem
@getem
ከታች ባለው አድራሻ የጓደኛ ፣ የወዳጅ ፣ ዘመድ እና የፍቅረኛችሁን #ፎቶ በመላክ በተመጣጣኝ ዋጋ ሦዕል ማሳል ይቻላል።

+251984740577
ወይም @gebriel_19


@seiloch
@seiloch
አረንጓዴ ምድር አረንጓዴ ልማት
በየቦታው ሽታ በየቦታው ግማት
በያካባቢው ድርቅ በየቦታው ማጣት
_
ልማታዊ መስመር ባለራዕይ መሪ
ሳቅ የራቀው አገር የሚራብ ታታሪ
_
ብዙ ዩኒቨርሲቲ መአት አላዋቂ
ተመርቆ ጨዋ እውቀትን ጠባቂ
_
ብዬ ግጥም ልፅፍ ከጀመርኩኝ ወዲያ
ወንበር ስላገኘሁ አድጋለች ኢትዮጵያ
_
ለንደኔ አይነት ከንቱ ለእኔ አይነት መሐይም
ወንበር ላይ ካልወጡ እድገት አይታይም።

@getem
@getem
@paappii

ፍቄ ወንድማችን
............አፍርስ........

በህግ ያልቆመ አጥር ፣ ምድርህን እንዳይወርስ
ትዕዛዝ ይከበር ፣ ህገወጡም ይፍረስ።
በለው!!! ክስ...ክስ
በለው!!! ድር...ምስ
ታዲያ ስትጨርስ...
ህግህን የጣሰ ፣ የህገወጥ መንፈስ
ከሞት አፋፍ ነቅቶ ፣ ዳግም እንዳይነግስ
አንተም ባለ ህጉ ፣ ጭንቅሌህን አፍርስ።

@getem
@getem
@paappii

ሚኮ
ይነጋል
ይነጋል መሽቶ አይቀርም
ይደርሳል ቀኑ አይርቅም
ብትሄጅም አንቺን ባጣ
ትመጣለች የኔ እጣ

4/08/09 ተፃፈ
ራስ ታዲዬስ
@getem
@getem
@gebriel_19
Rediet Aseffa
አርምሞ.

.
.
ፍቅርና
ህብረት፥
አጥሩን ካልጣሰ
.
ንስሃና
ይቅርታ፥
ተበዳይ ካልካሰ
.
ፍርጠማና
ጡንቻ፥
ማዕበል ካልገታ
.
ጥበብና
ብስለት፥
ቋጠሮ ካልፈታ
.
ብትነቃም
ብታውቅም
አቅምህን
ሰብቀህ፥
እንደ ናዝሬት ጌታ
.
ሀቅህን
ባደራ
የምታኖርበት፥
የምትሰጥበት፥ ለጊዜ ይሁንታ
.
ሽንፈት
እንዳይመስልህ
ቀን
ቆጥሮ
እሚያደባይ
አቅም ነው
ሃይል ነው
ጉልበት ነው ዝምታ።


@gebriel_19
@getem
@getem
👍1
ከአዳም ግራ ፥ አጥንት ወስዶ
ሄዋንን የሰራት...
እርሱ ስርቆትን ፥ ጀመራት። 😊

@getem
@getem
@paappii

Wubishet tadelle
ጥሩ ሰው መርጫ፣ ጓደኛ እሚሆነኝ
ፈልጌ ለማግኛት ፣ በምርመራ ላይ ነኝ።

@getem
@getem
@Gebriel_19
"ነይ እንበስብስ"
.
# _ዳዊት_ንጉሡ
.
ይኸው ደሞ መጣሁ!
.
የዝናም ውስጥ ተጓዥ
መሸሻ የሌለው፥ይጠጋበት ስፍራ
ይራመዳል እንጂ
ጸሐያ እስክት 'ሠርቅ'፥ወጀቡ እስኪያባራ
ኃላ አያፈገፍግም
መጨቅየትን አይሸሽ!..መነከር አይፈራ!
.
ለሙሾ ስጠበቅ
አመስጋኝ ምላሴ፥ቅኔ 'እየተቀኜ'
ይኸው ደሞ መጣሁ!
ከጽልመት ብተዪኝ፥የሌሊት ወፍ ሆኜ
.
ይኸው ደሞ ፈራሁ
ዘር ከአፈር ሲጥሉት፥'ፈርቶ' እንደሚነቃ
በመገፋቴ ይልቅ
ከትናንቱ ይባስ፥ልወድሽ ነው በቃ!
.
ዘራፍ!
.
እስቲ ደሞ ግፊኝ
ልበስብስ..ልዘፈቅ...ልብሽ እስኪቀና
ወድቄ ልነሳ
ተዋግቶ ነው እንጂ
ሸሽቶ አይሞትም ጀግና
.
ዘራፍ..!
.
ተመስገን ነው እኛስ!
የተገኘንበት ላይነሳን አፈር
በሟች ቆሞ መሄድ
ገዳይ ነው 'ሚሸበር
.
ከጭቃ መብቀልን
ሞቶ መነሳትን፥ከፍጡር ተውሼ
ከጣልሺኝ ቦታ ላይ
ከጭላንጭል ብርሃን
ከአፈሩ ርጥበት፥'ፈራሁኝ' በስብሼ
.
ይመስገን ስብራት!
.
ካሰበው እስኪደርስ
ያልተንገዳገደ..ማነው ያልወደቀ?..
በመዶሻም አይደል
በመመታት አይደል፥ምስማር የጠበቀ?
.
ይመስገን አምላክሽ!
.
አፈር ያልነፈገኝ
የተገፋሁ እኔን፥ከጭንጫ ያልጣለ
ከውድቀትም ውድቀት
ከሞትም ሞት አለ
.
ይመስገን!
ይመስገን...ይመስገነው እጅሽ!
ይኸው ደሞ ፈራሁ፥ይመስገነው ጭቃ
ደግሞ እነሳለሁ
ደግሞ እመጣለሁ፥ተስፋዬን ጥበቃ
.
መምጣቴ አይግረምሽ!
ያዝላል መንገዱ፥ካልተደጋገፉ
በብቻነት ጉዞ፥ስንዝር ላትራመጅ
እግር ማድከም ትርፉ
.
ነይልኝ አልልም!
ስሜቴን ተረድተሽ፥ልብሽን ሳታውቂ
መጎዳቴን አይተሽ
ፍቅርሽን መጽውተሽ፥በሃዘንሽ ልጸድቂ
ነይልኝ አልልም!
በአማራጭ እጦት፥ምርጫሽን ልትወጂ
መሰንበቻ ልሆን
ይሻል የመጣ 'ለት፥ጥለሺኝ ልትሄጂ
.
(ይሄዱታል እንጂ
ቆመው ቢጠብቁት..አይጓዝም መንገድ
በእንፉቅቅ ጉዞ ነው
ወድቆ በመነሳት...መሄድ የሚለመድ)
.
.
ነይልኝ በህማም
በጌቴ ሰማኔ.....ነይ በጎልጎታ
ኩራትሽን ሰብረሽ
መስቀሌን ተጋርተሽ.....ወድቀሽ ከከፍታ

@getem
@getem
@paappii
👍2
አፋልጉኝ
።።።።።።
#AbaynehTegegne
ኮፍያዬ ከላይ፣
………………ከታች ከረቫቴ፣
ሱሪና ጫማዬ…
………………ሸሚዝና ኮቴ፣
ቦታቸውን ይዘው፣
………………ደምቆልኝ ውበቴ፣
ሰው የመሆኛዬ፣
………………ጠፋ ጭንቅላቴ።

@getem
@getem
@gebriel_19
///ሰማይን///

ሰው አፍቅሬ ሰው ሲከዳኝ
ንፋስ ስከተል ሲሰወርብኝ
የኔ ያልኩት ተራራ የወደድኩት ደን
ሲሰጥ ለቆራጭ የሌላ ሲሆን
ስወድ
ስካድ
ስወድ
ስካድ
ስወድ
ስካድ
የሞትኩለት ገድሎኝ ሲሄድ
ሁሉም ከፍቶ ሁሉም ሲክድ
መካድን ካድኩና አንድ ዘዴ ዘየድኩ
ትቶኝ ማይሸሸውን ሰማይን አፈቀርኩ።

እስጢፋኖስ ተስፋየ
2011 woldia university

@getem
@getem
@gebriel_19
ይቅር በል (ዳኒ ከአርባምንጭ)
--------------

ከቶ እንዳትመጻደቅ!!
ባንተ ሲሆን ድንገት, አንተ ስትጠየቅ
ሊከብድ እንደሚችል ቀድሞዉኑ ጠብቅ
ከከበደህ ደግሞ ምትለዉን አታዉቅ
ስለዚህ ተጠንቀቅ
ማለት ያለብህን አስቀድመህ እወቅ
.
.
.
ወጥነኸዉ ሳይሆን
ሳታስበዉ ጭራሽ
ወይ ተጠያቂ ልትሆን
ወይ ይቅርታህን አድራሽ
ባንዱ ትገኛለህ
ከሆንክ ስጋ ለባሽ!!!
.
.
.
ይቅርባዩ መምህር
እራሱ ሲያስተምር
ሰባት ጊዜ ሳይሆን ሰባሰባቴ እንድንምር
አስቦ ይሆናል እኛ #እንድንማር
.
.
.
ምንም ሆኖ ቢሆን ምንም እንዳልሆነ
ረስቶት ይቅር ብሎ ደግሞ ካልኮነነ
በቃ አዉቆበታል እሱ ነዉ ይቅር-ባይ
አምላክ የሚምረዉ ኃጢአቱ ሚሰረይ
------------------------------

Jul. 6, 2013...

@getem
@getem
@gebriel_19
🎉1
///የማይቻል አንድ ነገር///

እዉነት - ቤት ስትሰራ
ዉሸት - ላግዝ ካለች፣
ምስማር ካቀበለች፣
ቤቱም አልተሰራ
እዉነትም አልኖረች።

#ጌትነት_እንየው

@getem
@getem
@gebriel_19
🇪🇹 ወገን ለወገን የክተት ጥሪ 🇪🇹
📯ዓዋጅ❗️ 📯ዓዋጅ❗️ 📯ዓዋጅ❗️

በጉጉት ስንጠብቀው የነበረ ነውና ሁላችሁም #SHARE በማድረግ ለወገን ጥሪ የበኩላችሁን ተወጡ።

ይሄ የክተት ዓዋጅ ቤተ ክርስቲያንና መስጊድ ከመገንባት በላይ ነው ። እኔ መቼም በጓደኞቼ አላፍርም። በጭራሽ።

ኢትዮጵያን እወዳለሁና ኢትዮጵያዊ ነኝ የምትል ኢትዮጵያዊ የሆንክ በሙሉ። ከወደ አዲስ አበባ የምሥራች የሆነ ዜና መጥቷልና #ሀሀሀ ብለህ ስማ ተብለሃል። በደቡብ ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ ረሃብ ለሚሰቃዩት ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን እንደርስላቸው ዘንድ በጉዞ ዓደዋዎቹ #ያሬድ_ሹመቴና በጓደኛው #መሐመድ_ካሳ አማካኝነት የቁሳቁስና የእህል እርዳታ ለተጎጂዎቹ ለማድረስ ተወስኗል እና ተዘጋጁ ተብላችኋል።

ካለሁበት ከራየን ወንዝ ዳር ሆኜ በዛሬው ዕለት ከወንድሜ ያሬድ ሹመቴ ጋር በእርዳታ አሰባሰቡና አሰጣጡ ላይ በሰፊው ተነጋግረናል። ከያሬዶና ከመሐመድ ጋር በሊቢያ ለታረዱት ክርስቲያኖች እርዳታ በማሰባሰብ ተጎጂዎችን በማጽናናት የቆየ ልምድም አለን። እናም ወገን ከእነ ያሬዶ ጋር የተነጋገርንበትንም ጉዳይ ለእኔ የፌስ ቡክ ጓደኞቼ ለሆናችሁ ለእናንተ እነግር ዘንድም ከወንድሜ መሐመድ ጋርም ወስነናል። ዝግጁ ናችሁ?

ወደህ ነው ዝግጁ የምትሆነው። በግድህ ነው እንጂ። አሁን ሁሉም ሰው ባለበት ይዘጋጅ። እርዳታው የሚሰበሰበው ከመጋቢት 16 እስከ መጋቢት 21 በመሐል አዲስ አበባ በሚገኝ ሥፍራ ነው። ቦታው አሁን #የማይገለጸው ሰዉ ከነገ ጀምሮ እርዳታውን ይዞ እንዳይመጣ ነው። እርዳታው ከሚጠበቀው በላይ ከሆነ ደግሞም ይሆናል ለሁሉም በኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ ተፈናቃይ ወገኖቻችን ህይወት ማቆያ ይሆናል ማለት ነው። አስቸኳይ እርዳታ ታላቅ ዘመቻ። ተዘጋጁ።

መንግሥት መኪና በማቅረብ፣ የእርዳታ መሰብሰቢያውን ቦታ በማዘጋጀት ፣ የተሰበሰበውንም ዕርዳታ አጅቦ ተጎጂዎቹ ያሉበት ቦታ ድረስ ለማድረስ ፈቃደኝነቱን ብቻ ሳይሆን ቁርጠኝነቱንም አሳውቋል። ወዶ ነው።

አሁን ከእናንተ ገንዘብ አይፈለግም። በገንዘብ የሚታማም፣ የሚነካካም አይኖርም። የባንክ አካውንትም አይከፈትም። የሚፈለገው ዕቃ ብቻ ነው። ምግቦች፣ የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶች፣ አልባሳት ከእናንተ ይጠበቃል።

🥞የማይበላሹ_ምግቦች
•ስንዴ
•ምስር
•ፓስታ
•መኮረኒ
•ሩዝ
•ፉርኖ ዱቄት
•ዘይት
•ሴሪፋም /ፋፋ/
•ብስኩት /ጋቤጣ/

🗑የንጽህና_ቁሳቁሶች
•ሳሙና
•ኦሞ
•ሳኒታይዘር
•የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ /ሞዴስ/

👖አልባሳት
•ብርድ ልብስ
•ነጠላ ጫማ (ብቻ)
•የተለያዩ አልባሳት (ያገለገሉም ቢሆን) አዘጋጁ ተብላችኋል።

አስተባባሪዎቹ የጊዞ ዓደዋ መስራቾቹ ቅድሚያ ለሰብዓዊት ቡድን ጊዜያዊ አስተባባሪዎችና የቡድኑ ተወካዮች የሆኑት ያሬድ ሹመቴና መሐመድ ካሳ።

⚠️ማስታወሻ ⚠️

📍 የእርዳታ መሰብሰቢያውን ቦታ ከመጋቢት 16 ሁለት ቀን በፊት መጋቢት 14 በይፋ እናሳውቃለን። እስከዚያው ድረስ ግን ሁላችንም በዕድር፣ በመሥሪያ ቤት፣ በቤተሰብ፣ በመኅበር፣ በየሠፈራችሁ እያሰባሰባችሁ። በማዳበሪያ፣ በማዳበሪያ እየከተታችሁ ጠብቁ። በውጭ የምትኖሩም ኢትዮጵያውያን በቤተሰብ በኩል ገንዘብ እያስላካችሁ የፈለጋችሁትን ዕቃ እየገዛችሁ አዘጋጅታችሁ ጠብቁ። ከእኛ በላይ ለእኛ የሚደርስልን የለም።

📍በረሃብ ለተጠቁት ለጌዲኦ ህዝብ የምንደርስበት ዕድል ተዘጋጅቷልና ወገኔ በያለህበት ተዘጋጅተህ ጠብቅ። ተመስገን አምላኬ ሆይ ይህን የምሥራች ያሰማኸኝ አምላክ ክበር ተመስገንልኝ።

መጋቢት 6/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ዳር።

#ምንጭ:- Zemedkun Bekele Facebook Page

📍 ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ፁፉን እንዳነበባችሁት ነው፡፡ ወገኖቻችን እጅግ ያሳዝናሉ፡፡ አብዛኞቻችን ምናልባት የምንበላው ፣ የምንለብሰው አላጣን ይሆናል፤ ነገር ግን እዚህ እኛ ባይሞላልን እንኳን ሳይጎልብን ውለን እናድራለን፡፡ በሌላ በኩል ግን የገዛ እህት ወንድሞቻችን በዚህ ዘመን በእራብ እያለቁ ነው፡፡ ህፃናት መቦረቅ ቀርቶ አፋቸውን መክፈት እያቃታቸው ነው፡፡ አረጋዊያን በርሀብ ደርቀው እየሞቱ ነው፡፡

📍እናም እላችኀለው ቢያንስ ቢያንስ የአንድ ቀን ሻይ ፣ ካርድ ፣ ቢራ ፣ ጫት ይቅርብንና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡ የግድ ማዳበሪያ ሙሉ አዋጡ አይደለም። ኤኔ 1 ኪሎ ፍርኖ ዱቄት ባዋጣ አንተ አንድ እሽግ ፓስታ ብታመጣ አንቺ ደሞ አንድ ኪሎ ምስር ብታመጪ ሁለት ወይም ሶስት ሰውን ለአነድ ቀን በህይወት ማቆየት ይቻላል፡፡ ስንበዛ ደሞ አስቡት፡፡ ስለዚህ ትንሽ ነው ብላችሁ ሳትጨናነቁ ከ10 ብር ሳሙና ጀምራችሁ እናዋጣ፡፡

ከጎናችን የሆናቹ ኢትዮጵያኖች

🙏ሰው ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ ይበቃል🙏
እኔ ጠላሻለሁ
______
(እዮብ ዘ ማርያም)
.
እኔ ጠላሻለሁ፣
እንደ ጫማ ሽታ
ልክ እንደ በሽታ
ጌታ በባሪያው ላይ እንደ ሚበረታ
እኔ ጠላሻለሁ፣
እንደ ረጅም መንገድ
ላብታም እንደ መስገድ
ከጠጡ በሗላ እንደ መንገዳገድ
እኔ ጠላሻለሁ፣
ገንዘብ እንደ ማጣት
ዳገት እንደ መውጣት
ከያዘ እንደ ማይለቅ እንደ ጨካኝ ቅጣት
እኔ ጠላሻለሁ፣
ልክ እንደ መልከስከስ
እምነት እንደ ማርከስ
ማስቲካ እያኘኩ ምላስ እንደ መንከስ
እኔ ጠላሻለሁ...(ወዘተ)...
አሁን ግኔ ፈራሁኝ ጀመርኩኝ መብሰልሰል
ጠላሁሽ ያበዛው ወድጄሽ ነው መሰል!

@getem
@getem
@paappii
👍1
ፈላጊ_ነፍስ

# አሌክስ_ይህ
.
ከግዙፍ ዋርካ ላይ
ነፋስ እንደጣላት ~ ትንሽዬ ቅጠል
ይህ ነው ችግር ማለት
በሰዎች ተከቦ ~ ከሰዎች መነጠል
.
በዚህ በዘመኔ ...
ዝቅ በሚልበት ~ ዝምታ ሚዛኑ
በሚገመትበት ~ "መፅሃፍ በሽፋኑ ..."
.
ከዳንኪረኞች ጋር
መደለቅ እየቻልሽ
እስኪሰማሽ ድረስ ~ የድምፅሽ ማሚቶ
ተክዘሻል ኣሉ
ታስቢያለሽ ኣሉ
የዝምታ ባህር ~ ነፍስሽ ላይ ተኝቶ
...
ታስቢያለሽ ኣሉ !
.
ወዲህ ደግሞ ...
ርሃብሽን ላይቆርጠው ~ የማዕድሽ ዕንጀራ
በሚቀዱልሽ ወይን ~ ጥምሽ ላያባራ
"ምን ጎደለ" እያሉ ~ ሰዎች ያደክሙሻል
ያጣውን የሚያውቀው
ልብሽ ሌላ ይሻል።
.
ሌላ !


@getem
@getem
@paappii
👍1
ሰው መጣ.....ሰው ሄደ


ያይኔ የልቤ ጉጥ የዘላለም ፍቅሬ
ሰው ያየናል እዚህ ፈርቻለሁ ዛሬ
እንዲህ ተሸጉጬ በአንተ ክንድ ላይ
አባዬ ያየኝ እንደሁ አይኖርም ገላጋይ

ብዬ እያካፈልኩት ጭንቀቴን ከሆዴ
ጥላ ባየሁ ቁጥር ከእቅፉ እወጣለሁ
አወይ ልጅነቴ

ሰው መጣ ሰው ሄደ
ምንም ሳናወራ በመጨነቅ ብቻ
አንዴ እጁን ሲሰቅል አንዴ እጁን ሲያወርድ
ሰአቴ ደረሰ የመሰናበቻ
ሳልጠግበው ሳይጠግበኝ ናፍቆቴ ሳይወጣ
ሌላ የቀን ቀጠሮ ላንድ አይነት ቆይታ፡፡

ያኔ በልጅነት ባፍላነት እድሜያችን
ሰው መጣ ሰው ሄደ ነበር ስጋታችን

አመታት አለፉ ጊዜውም ነጎደ
በሰው መጣ ጭንቀት ሀሳብ ተወገደ
በትዳር ትስስር ነፃነት ታወጀ

ነገር ግን

የሰው መጣ ጭንቀት ቆይቶ ቆይቶ...
ጊዜውን ጠብቆ በር ላይ አድብቶ
እንደገና መጣ በራችን አንኳክቶ

ዐይኖችህ ከዐይኖቼ እንዳልተራራቡ
እንዳልተቃቀፍን ጠብቀን ሲዞሩ
መተቃቀፍ ጀመርን ሰው ሲኖር ከበሩ፡፡


ንፁህ ግርማ

@getem
@getem
ንጉስ ይከሰስ(ልዑል ሀይሌ)

ነገሩ ነው እንጂ...
ንጉስ ይከሰሳል
በችሎቱ ፍርጃ
ወንበር ይወረሳል
በውርሻው ክፍፍል
እግሩ ባይሰበር
ለከሳሹ ካሳስ
ወንበር ደግ ነበር
..
.
ነገሩ ነው እንጂ...
ሰማይ ይታረሳል
በገበሬ ዕንባ
በበሬ ልመና
ፈጣሪ ይደርሳል.
.
የታረሰው ሰማይ
ጥሩ ፍሬ አፍርቶ
በዓለም ህዝብ ላይ
ሰላም ፍቅርን ዘርቶ
ሁሉን ሆኖ እንድናይ
ንጉሱ ይከሰስ
ሰማዩም ይታረስ
ለውርስ ከመጋጨት
ተስማምተን እንንገስ
.
ሰላም ፍቅር ጤና
ካሳ ይከፈለን
ለዓለሙ ገዢ
ዛሬም እንጮሃለን
.
ሰላም!
ፍቅር!!


@getem
@getem
@lula_al_greeko
👍1