ግጥም ብቻ 📘
67.4K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ግፍ ይሆን

አንቺን ባ`ንድ ጣምራ በሾርኔ ያየሁሽ
በስላቅ ፈገግታ በአይን ያወራሁሽ
የመለኮት ቁጣ እስኪወርድ ያቀፍኩሽ
በምናቤ ይሁን ወይስ ውሸት ነበርሽ?

ልጠይቅሽ ውዴ
በእፉዬ ገላ ይዞ በለቀቋት
ንፋስ በሚያባራት
አባረን ላንይዛት ይዘን ላናስቀራት
የተሯሯጥንላት የተወናበድነው
እስከዚች ወይ ነበረ ፍቅርን ያፈቀርነው
ላንጨርሰው ነገር መንገድ የጀመርነው?

ልጠይቅሽ ሆዴ

ወልደን ከብረን ነጥቀን ብለን ያልነው ያኔ
ነገ የለም ብለን ወይስ ላይሆኑ ተስፋ ነው
ልቡን ለመጠበቅ በሚል ብሂል ታስረሽ
ሳትወጂኝ ነበር ወይ ስወድህ ማለትሽ?

እማ ምትፈቅጂልኝ ከሆን
አንዴ ልጠይቅሽ
ሺ ንጉስ ደርድረሽ ሺ ንጉስ ምትመርጪ
ምን ላይ ልታነግሺ
አላያ ተዋድቀው ግምት ልታወጪ?
ዛዲያ ደሞ ከርሞ ጦርነቱን ፍልሚያ
ንግስቷን የመውስድ የንጉሶች ግጥሚያ
ሰውነት አቁስሎ ግን ስንቱን ንጉስ ጥሎ
ወዳንቺ የመጣ አካሉን አጉድሎ
ንጉስ ይሆናል ወይ ባንቺ መንበር ከብሮ
ወይስ መዝናሽ ነው እንዲህ አይነት ኑሮ
የሰው ሀዘን ሲቃ ሚያረካሽ እሮሮ!

ፍቅር አለም ልጠይቅሽ እስቲ
ባትመልሺም እንኳ ስለኔ ግድ የለም።
አንቺን እሚያስገድድ ደፋር ንጉስ የለም
ቀረርቶ ሽለላ ፉከራ ሚያውድሽ
ልብሽ ጀግና ሚወድ ግራ ግብ መሻትሽ

አንቺጋ ሲደረሱ የፊትዮሽ ኋላ
ኋልዮሽ ፊትዮሽ እሚሆነው ሌላ
ግራ ገብ ባህሪሽ ተጠናውቷቸው
ወይስ ማስመሰል ነው?

ደጀን ነው ስቲይኝ ቀርቤ ያየሁት
ጅማተ ቆራጣ ዝል ክንደ ፋድያት
ድጋፌ እሚያሻው ስለ ልቡ ጡዘት
መሆኑን አልደብቅ የህጣን ልጅ ቅንጣት

#ኤሽታ
@getem
@getem
@gebriel_19