🇪🇹 ወገን ለወገን የክተት ጥሪ 🇪🇹
📯ዓዋጅ❗️ 📯ዓዋጅ❗️ 📯ዓዋጅ❗️
✔ በጉጉት ስንጠብቀው የነበረ ነውና ሁላችሁም #SHARE በማድረግ ለወገን ጥሪ የበኩላችሁን ተወጡ።
✔ይሄ የክተት ዓዋጅ ቤተ ክርስቲያንና መስጊድ ከመገንባት በላይ ነው ። እኔ መቼም በጓደኞቼ አላፍርም። በጭራሽ።
✔ ኢትዮጵያን እወዳለሁና ኢትዮጵያዊ ነኝ የምትል ኢትዮጵያዊ የሆንክ በሙሉ። ከወደ አዲስ አበባ የምሥራች የሆነ ዜና መጥቷልና #ሀሀሀ ብለህ ስማ ተብለሃል። በደቡብ ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ ረሃብ ለሚሰቃዩት ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን እንደርስላቸው ዘንድ በጉዞ ዓደዋዎቹ #ያሬድ_ሹመቴና በጓደኛው #መሐመድ_ካሳ አማካኝነት የቁሳቁስና የእህል እርዳታ ለተጎጂዎቹ ለማድረስ ተወስኗል እና ተዘጋጁ ተብላችኋል።
✔ካለሁበት ከራየን ወንዝ ዳር ሆኜ በዛሬው ዕለት ከወንድሜ ያሬድ ሹመቴ ጋር በእርዳታ አሰባሰቡና አሰጣጡ ላይ በሰፊው ተነጋግረናል። ከያሬዶና ከመሐመድ ጋር በሊቢያ ለታረዱት ክርስቲያኖች እርዳታ በማሰባሰብ ተጎጂዎችን በማጽናናት የቆየ ልምድም አለን። እናም ወገን ከእነ ያሬዶ ጋር የተነጋገርንበትንም ጉዳይ ለእኔ የፌስ ቡክ ጓደኞቼ ለሆናችሁ ለእናንተ እነግር ዘንድም ከወንድሜ መሐመድ ጋርም ወስነናል። ዝግጁ ናችሁ?
✔ወደህ ነው ዝግጁ የምትሆነው። በግድህ ነው እንጂ። አሁን ሁሉም ሰው ባለበት ይዘጋጅ። እርዳታው የሚሰበሰበው ከመጋቢት 16 እስከ መጋቢት 21 በመሐል አዲስ አበባ በሚገኝ ሥፍራ ነው። ቦታው አሁን #የማይገለጸው ሰዉ ከነገ ጀምሮ እርዳታውን ይዞ እንዳይመጣ ነው። እርዳታው ከሚጠበቀው በላይ ከሆነ ደግሞም ይሆናል ለሁሉም በኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ ተፈናቃይ ወገኖቻችን ህይወት ማቆያ ይሆናል ማለት ነው። አስቸኳይ እርዳታ ታላቅ ዘመቻ። ተዘጋጁ።
✔መንግሥት መኪና በማቅረብ፣ የእርዳታ መሰብሰቢያውን ቦታ በማዘጋጀት ፣ የተሰበሰበውንም ዕርዳታ አጅቦ ተጎጂዎቹ ያሉበት ቦታ ድረስ ለማድረስ ፈቃደኝነቱን ብቻ ሳይሆን ቁርጠኝነቱንም አሳውቋል። ወዶ ነው።
✔አሁን ከእናንተ ገንዘብ አይፈለግም። በገንዘብ የሚታማም፣ የሚነካካም አይኖርም። የባንክ አካውንትም አይከፈትም። የሚፈለገው ዕቃ ብቻ ነው። ምግቦች፣ የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶች፣ አልባሳት ከእናንተ ይጠበቃል።
🥞የማይበላሹ_ምግቦች
•ስንዴ
•ምስር
•ፓስታ
•መኮረኒ
•ሩዝ
•ፉርኖ ዱቄት
•ዘይት
•ሴሪፋም /ፋፋ/
•ብስኩት /ጋቤጣ/
🗑የንጽህና_ቁሳቁሶች
•ሳሙና
•ኦሞ
•ሳኒታይዘር
•የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ /ሞዴስ/
👖አልባሳት
•ብርድ ልብስ
•ነጠላ ጫማ (ብቻ)
•የተለያዩ አልባሳት (ያገለገሉም ቢሆን) አዘጋጁ ተብላችኋል።
✔አስተባባሪዎቹ የጊዞ ዓደዋ መስራቾቹ ቅድሚያ ለሰብዓዊት ቡድን ጊዜያዊ አስተባባሪዎችና የቡድኑ ተወካዮች የሆኑት ያሬድ ሹመቴና መሐመድ ካሳ።
⚠️ማስታወሻ ⚠️
📍 የእርዳታ መሰብሰቢያውን ቦታ ከመጋቢት 16 ሁለት ቀን በፊት መጋቢት 14 በይፋ እናሳውቃለን። እስከዚያው ድረስ ግን ሁላችንም በዕድር፣ በመሥሪያ ቤት፣ በቤተሰብ፣ በመኅበር፣ በየሠፈራችሁ እያሰባሰባችሁ። በማዳበሪያ፣ በማዳበሪያ እየከተታችሁ ጠብቁ። በውጭ የምትኖሩም ኢትዮጵያውያን በቤተሰብ በኩል ገንዘብ እያስላካችሁ የፈለጋችሁትን ዕቃ እየገዛችሁ አዘጋጅታችሁ ጠብቁ። ከእኛ በላይ ለእኛ የሚደርስልን የለም።
📍በረሃብ ለተጠቁት ለጌዲኦ ህዝብ የምንደርስበት ዕድል ተዘጋጅቷልና ወገኔ በያለህበት ተዘጋጅተህ ጠብቅ። ተመስገን አምላኬ ሆይ ይህን የምሥራች ያሰማኸኝ አምላክ ክበር ተመስገንልኝ።
መጋቢት 6/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ዳር።
#ምንጭ:- Zemedkun Bekele Facebook Page
📍 ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ፁፉን እንዳነበባችሁት ነው፡፡ ወገኖቻችን እጅግ ያሳዝናሉ፡፡ አብዛኞቻችን ምናልባት የምንበላው ፣ የምንለብሰው አላጣን ይሆናል፤ ነገር ግን እዚህ እኛ ባይሞላልን እንኳን ሳይጎልብን ውለን እናድራለን፡፡ በሌላ በኩል ግን የገዛ እህት ወንድሞቻችን በዚህ ዘመን በእራብ እያለቁ ነው፡፡ ህፃናት መቦረቅ ቀርቶ አፋቸውን መክፈት እያቃታቸው ነው፡፡ አረጋዊያን በርሀብ ደርቀው እየሞቱ ነው፡፡
📍እናም እላችኀለው ቢያንስ ቢያንስ የአንድ ቀን ሻይ ፣ ካርድ ፣ ቢራ ፣ ጫት ይቅርብንና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡ የግድ ማዳበሪያ ሙሉ አዋጡ አይደለም። ኤኔ 1 ኪሎ ፍርኖ ዱቄት ባዋጣ አንተ አንድ እሽግ ፓስታ ብታመጣ አንቺ ደሞ አንድ ኪሎ ምስር ብታመጪ ሁለት ወይም ሶስት ሰውን ለአነድ ቀን በህይወት ማቆየት ይቻላል፡፡ ስንበዛ ደሞ አስቡት፡፡ ስለዚህ ትንሽ ነው ብላችሁ ሳትጨናነቁ ከ10 ብር ሳሙና ጀምራችሁ እናዋጣ፡፡
ከጎናችን የሆናቹ ኢትዮጵያኖች ✅
🙏ሰው ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ ይበቃል🙏

#ዝክረ ሙሉ ጌታ ተስፋዬ❤️❤️...!!!
የወፍዬ ግጥም ደራሲ ነው ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ ...ወፍዬን ከሁለት ልጆቹ ቀጥላ 3ተኛ ልጄ ናት ይላል አያ ሙሌ። ማንም አማርኛ ተናጋሪ ፍጡር በህይወት ዘመኑ ወፍዬን ቢያንስ አንድ ግዜ ሊሰማ ግድ አለበት ይል ነበር አያ ሙሌ። አያ ሙሌ በተለይም የባለቅኔ ምህላ በሚል ስራው በጣም ይታወቃል። ወፍዬ ከሙዚቃም በላይ ነው...ይህ ግጥም በህይወት ተክለሰውነት ላይ ያለን የፍትህ መጓደል በስንኞቹ መነፅር ያሳያል...ስለህይወት ውጣውረድና እንግልት ይተርካል.....ተመስገን ብሎ ስለማደር ሰማያዊ ህይወትን ስለመሻት ያትታል...ስለ ሰው ከንቱነት ይፈላሰፋል....አንዲትን ከመንጋው የተገፋች ሴት እውነት....ፍትህ ስላጣች ሴት ያወጋል በሰውኛና ተምሳሌታዊ ዘይቤም ተቀንብቧል ይህን ሁሉ በውስጡ ያዘለው ይህ ያያ ሙሌ ግጥም ዜማ ታክሎበት በአበበ ተካ ሲንጎራጎር ደግሞ በስንጥቅ ገላችን ላይ ሰርጎ የመቅረት የሆነ አንዳች የህይወትን ስንክሳር በመንገር ጥምን የማርካት ባህሪ አለው እስቲ እናንተስ ምን ትላላችሁ? ይችትላችሁ ሙሉ የሙዚቃዋ ስንኝ።
(ወፍዬ)
ከአበበ ተካ ዘፈን
......
ጭራ ጭራ የምታድረው (2)
ጭራ ለቅማ የምታድረው (2)
እንዴት አስናቀችኝ
ቀድማኝ ጎጆ ወጥታ ጎጆ አስተማረችኝ
ጎጇቤት ጎጆ እኔን ወፍዬ አስቀናችኝ
……..
ምነው ባደረገኝ
የሷ ጋሻ ጃግሬ
እንደምንም ብዬ እኔም ጥሬ ግሬ
ያገዳ ጎጆዬን ባቆምኳት ማግሬ
አጉል በቃኝ ላይል
አይን አይቶ ገምቶ
ወይ ሞልቶ ላይሞላ
ጆሮ አይችሉ ሰምቶ
እንዴት ጎጆ ይቅር
አርሶና ሸምቶ
……..
ገመና ከታቹን የሳር ቤት ያማረሽ
ሚስጥረ መለኮት ማነው ያስተማረሽ (2)
ካፈር ክዳን ጎጆ መሬቱን ፈልፍሎ
ከሰማይ ቤት እጣሽ ማን በሰጠኝ ከፍሎ (2)
………..
እኔን እኔን እኔን ይብላኝ (2)
እኔን አይኔን እኔን ይብላኝ (2)
የቀን ሰው ሌት አፈር
ልቤ እሩቅ አሳቢው
ቅርብ አድሮ ሲደፈር
ምን ነበር ቢቆጨው ጎጆ አጥቶ ከማፈር
………
ፈጣሪዋን አምና ያፏን ጥሬ ሰጥታ
ለጭሮ አዳር ውሎ በዝማሬ ወጥታ
አዳኝ እንዴት ያጥቃት ፍርድና ዳኛ አጥታ
አጣው ነጣው ብላ እንደሰው ባይከፋት
ምፅዋት ባትለምን ትርፉን ባንደግፋት
ጎጆዋ ለቻላት ምን ነበር ባንገፋት
………
ታማ ትንፋሽ አጥሯት ደክማ ስታጣጥር
ማን ያቃናት ይሆን ውለታ ሳይቆጥር (2)
ወልዶ ማሳደጉን ብዙ ሰው ቢያውቅበት
ያፉን ማን ይሰጣል የጁ ሲርቅበት (2)
እህህ ወፊቱ እሁሁ ወፊቱ እህህ ወፍዬ እህህ ወፊቱ እህህ ወፍቱ (8)
#ምንጭ:-ስንታየሁ እንደከተበው
እሱ ወፊቱን❤️የአያ ሙሌን ስራ አስታውሶ ሲዘክርልን ሲከትብልን ነፍሳችን ደስ ደስ አላትና...በሚጎመዝዘው ድምፃችን ተጫወትናት👇👇👇
@balmbaras

አመሉ፡፡
***
እንዲያው ቢሆን እንኳ…
ንጉሱን ብናምነው
የበዙ እባቦችን እንደምን አድርጎ አንድ ርግብ ይመራል
አንድ ሻማ ብቻ የጨለመ ሀገርን እንደምን ያበራል
ቤተ እምነቶች ዱዳ ሽማግሌው ዱጋ ጋዜጠኛው ዱዳ
እንዳልተወለደ እንዳልኖረ ሁሉ ሕዝብሽም እንግዳ፡፡
…ግጥሙ ይቀጥላል፡፡ የዚህ ግጥም ወቀሳ ብዙ እውነት አለው። ፍርሃትና
ጥርጣሬው፣ ነባራዊው እውነትም አሳማኝ ነው፡፡ በተለይ ሁለተኛው አንጓ ላይ
ያለው ሀሳብ በእምነት ተቋማቶቻችን፣ በጋዜጠኞቻችን… በአጠቃላይ
በሽንቁሮቻችን ላይ አተኩሯል፡፡
መጽሐፉ አሁን ባለንበት አገራዊ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ መረር ያለና
የሚያሳዝንም ነው፡፡ አንዳንዱ ደግሞ ሚዛን የሳተ ይመስላል፡፡ ወደ አንድ ጥግ
የሄዱ ግጥሞች አሉ፡፡ ገጣሚ የአገር ወገን፣ የሕዝቦች ተገን መሆኑን ግን
መርሳት የለበትም፡፡ እንደ መጽሐፍ ዘመን ተሻጋሪ እንዲሆን ጭብጦቹ ከአንድ
ድንኳን የተመዘዙ፣ ባለ ተመሳሳይ ጭብጥና ድምጽ መሆን የለባቸውም፡፡
ስሜት የጥበቡን ዋልታዎች እንዳይበትን መጠንቀቅና ምሰሶውን ሁለንታዊ
ማድረግ ያስፈልገዋል፡፡ በተረፈ ገጣሚው ክፍተቶቹን ሞልቶ፣ በግሩም
ሥራዎች እንደሚመለስ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
#ምንጭ አዲስ አድማስ ጋዜጣ
ውብ ቀን!💚
@getem

❤1
ች በትወና ወቅት የሚናገሩት ሲሆን፤ ይህን
Dialogue የተሰኘውን ቃል ወደ አማርኛ አምጥቶት ቃለ-ተውኔት በማለት የተረጐመው
ደበበ ሰይፉ ነው።
ደበበ እነዚህንና ሌሎችንም ሥነ-ጽሑፋዊ ቃላትን በመፈጠር በትውልዶች አንደበት፣
አእምሮ እና ብዕር ውስጥ ለዘላለም እንዲኖር ያደረገ ጥበበኛ ነው።
ደበበ ሰይፉ ለዚሁ ለቴአትር ትምህርት ዘርፍ ካበረከታቸው አስተዋፅኦዎች መካከል
ለትምህርቱ መጐልበት ይረዳ ዘንድ በ1973 ዓ.ም መፅሐፍም አሳትሟል። መፅሐፏ
የቴአትር ጥበብ ከፀሐፌ-ተውኔቱ አንፃር የምትሰኝ ርዕስ የያዘች ሲሆን፤ ለሀገራችን የቴአተር
ሙያተኞች እንዲበራከቱ እና በእውቀት ላይ የተመሠረተ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ሰፊ ድርሻ
አበርክታለች። ደበበ በዚሁ በቴአትር ዘርፍ ውስጥ የተፃፉ የንባብ መፅሐፍት
ያለመኖራቸውን ክፍተት ተገንዝቦ ያንን ክፍተት ለመሙላት ሙያዊ ጥሪውን የተወጣ
ባለሟል ነው።
ደበበ ሰይፉ ፀሐፌ - ተውኔትም ነው። በርካታ ተውኔቶችን ፅፎ ለመድረክ አብቅቷል።
አንዳንዶቹ ደግሞ ለምሳሌ ክፍተት የተሰኘው ተውኔቱ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለበርካታ
ጊዜያት ታይቶለታል። በዚህ
ክፍተት በተሰኘው የደበበ የቴሌቭዥን ድራማው ላይ በመተወን ተፈሪ ዓለሙ፣ አለማየሁ
ታደሰ እና ሙሉአለም ታደሰ ድንቅ የሆነ ብቃታቸውን አሳይተውበታል።
ደበበ ሰይፉ ከፃፋቸውና ከተረጐማቸው ተውኔቶች መካከል የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ
ናቸው፡-
1. ከባህር የወጣ ዓሣ
2. እናትና ልጆቹ
3. እነሱ እነሷ
4. ሳይቋጠር ሲተረተር
5. የህፃን ሽማግሌ
6. ማክቤዝ እና
7. ጋሊሊዮ ጋሊሊ ይገኙበታል።
ከእነዚህ ሌላም በ1973 ዓ.ም ማርክሲዝምና የቋንቋ ችግሮቹ የሚል መፅሐፍ
ከማሳተሙም በላይ በ1960 ዓ.ም ያዘጋጃት የሦስት አጫጭር ልቦለዶች መድብል
የሆነችው ድርሳኑ ትጠቀሳለች።
ደበበ ሰይፉ ከእነዚህ ከረቀቁ እና ከመጠቁ ምሁራዊ አስተዋፅኦው በተጨማሪ በበርካታ
ኪነ-ጥበባዊ ጉዳዮች ላይም አሻራውን ያሳረፈ ነው። ለምሳሌ በቀድሞው ኩራዝ አሳታሚ
ድርጅት ውስጥ በመሳተፍ ለኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ መስፋፋት እገዛው ሰፊ ሆኖ ኖሯል።
በኢትዮጵያ ሬዲዮ ውስጥም የኪነ-ጥበብ ዘርፍ ውስጥ ያሉትን ፕሮግራሞች አማካሪ ሆኖ
ሰርቷል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የቋንቋዎች ተቋም ጆርናል አሳታሚ ኮሚቴ
ሊቀመንበር ሆኖ አገልግሏል። ደበበ ሰይፉ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር ፕሬዚደንት ሆኖ
ሰፊ ድርሻ አበርክቷል። ደበበ ሰይፉ በኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ዓለም ውስጥ ትልቅ ድርሻውን
አበርክቶ ያለፈ የትውልድ ምሳሌ ነው።
ግን ሁሉም ነገር እንዳማረበት እስከ መጨረሻው አይሄድም፤ እናም ደበበ በዙሪያው ባሉ
ሰዎች በሚያውቃቸው ሰዎች ተበሳጨ። ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ ከቤት ዋለ። ታመመ።
መናገርም አቆመ። ለኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ በአጠቃላይ ለኪነ-ጥበቧ እድገት የአንበሳውን
ድርሻ ያበረከተው ደበበ ሰይፉ ሚያዚያ 16 ቀን 1992 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
ቀብሩም ቅዱስ ዮሴፍ ቤተ-ክርስትያን ተፈፀመ።
ስለ ደበበ ሰይፉ ምን ተፃፈ?
“ደበበ ሰይፉ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር ፕሬዝዳንት ሆኖ ከ1978 እስከ 1983 ዓ.ም
ድረስ ሰርቷል። ከዚህም በላይ በወቅቱ አያሌ የሙያው ባለቤቶች እንዲሰባሰቡ አድርጓል።
ከውጭ ሀገር በተለይም ከሶቭዬት ኅብረት ጋር ሙያዊ ድጋፍና ትብብር እንዲደረግ
አድርጓል። አንጋፋው ደራሲና ሃያሲ አቶ አስፋው ዳምጤ በአንድ ወቅት ስለ ደበበ የህይወት
ታሪክ ለሚያጠናው ተማሪ፣ ለተክቶ ታደሰ በሰጡት ቃለ-ምልልስ እንዲህ ብለዋል።
“ደበበ ስራ ይወዳል ስራው ጥንቅቅ ያለ ነው። ግን ሰዎችን ለመጋፈጥ ድፍረት ያንሰዋል።
ለቴአትር ዲፓርትመንት ከመከፈቱ ጀምሮ መጽሐፍ ጽፎላቸዋል። ፅንሰ ሃሳቡን እንዲረዱት
አድርጓል። ስለ ደበበ ካስደነቁኝ አንዱ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታው ነው። የደራሲያን
ማኅበር ሊቀመንበር ሆኖ እኔ ስራ አስፈፃሚ ሆነን ሠርተናል። ቀድሞ ከነበረው የማኅበሩ
የሥራ ዘመን ያልታየ እንቅስቃሴ ደረገ” የሚሉት አቶ አስፋው “እነሆ” የምትሰኘው
የአጫጭር ልቦለዶች መድብልና “ብሌን” የተሰኘችው መጽሔትም መታተሟን ያስረዳሉ።
“የጽጌረዳ ብዕር” የሚል የግጥም መድብል መታተሙንም አስረድተው የደበበን ጥንካሬ
ገልፀዋል።
ታዋቂው የወግ ፀሐፊ መስፍን ኃ/ማርያም ደግሞ ለአጥኚው እንዲህ ብሎ ነግሮታል።
“ደበበ በጣም ጠንካራ፣ ትጉህ ሠራተኛ፣ ለተሰለፈበት ዓላማ ወደኋላ የማይል፣ በማስተማር
ደበበ innovator /ፈጣሪ/ አይነት ነበር። የምናስተምረውን ኮርስ እንዲህ ብናደርገው፣
እንዲህ ብንለው እያለ ከጊዜ ወደ ጊዜ እንድናሻሽል በማድረግ በኩል ፈር ቀዳጅ ነበር።….
ደበበ ደራሲ ብቻ አይደለም። ጥሩ የማስተማር ችሎታ ነበረው” ብሏል።
ደራሲ ታደለ ገድሌም ሚያዚያ 29 ቀን 1992 ዓ.ም በወጣው “አዲስ ዘመን” ጋዜጣ ላይ
“ደበበ ሰይፉና ስራዎቹ ሲታወሱ” በሚለ ርዕስ ስለዚሁ ታላቅ ሰው አስነብቦናል።
ይህች ከተማ ነሐሴ 5 ቀን 1942 ዓ.ም ደበበን ያህል ታላቅ የኪነ-ጥበብ ሰው አፍርታለች።
አባቱ በጅሮንድ ሰይፉ አንተን ይስጠኝ እና እናቱ ወ/ሮ የማርያምወርቅ አስፋው የኢትዮጵያ
የኪነ-ጥበብ ዋልታ ያቆሙት በዚህች ምድር ነው። ደበበ ሰይፉን! ይርጋለም ከተማ ውስጥ።
“ይርጋለም
ዋ… ይርጋለም
የልጅነቴ ህልም ቀለም
ዓይኔን የከፈትሽው ጨረር
ወርቃማይቱ ጀንበር” ብሎ ደበበ ፅፎታል።
ዛሬ በህይወት የሌለው የስነ-ጽሁፍ መምህሩ ብርሃኑ ገበየሁ ትዝ አለኝ። ስለ ደበበ ሰይፉ
በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ሲፅፍ እንዲህ ብሏል። “የደበበ አቀራረቡ ቀላልና የማያሻማ
ነው። ድምፀቱ ደግሞ ሐዘን ከሰበረው ልብ የሚፈልቅ እንጉርጉሮ። የአቀራረብ ቀላልነት
ውበቱ ነው። ይርጋለምና ልጅነቱ በተናጋሪው ህሊና አንድም ሁለትም ናቸው፤ የማይፈቱ”
ብሏል። እናም ይርጋለም ደበበ ሰይፉ ናት!
ሌላኛው የስነ-ጽሁፍ መምህር የሆነው ወዳጄ ገዛኸኝ ጌታቸው፣ ደበበ ሰይፉ እንዳረፈ
በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ እንዲህ ብሎ ነበር። “ዛሬ የኢትዮጵያ ስነ-ጽሁፍ አንድ ለጋ ብዕር
አጣ፤ ነጥፎ አይደለም ታጥፎ ነው። ዛሬ የኢትዮጵያ ስነ-ጽሁፍ የዋህ ሃሳብ አጣ። ከፍቶ
አይደለም በኖ ተኖ እንጂ። ዛሬ ብዙዎቻችን ካወቅነው ብዙ ነገር አጣን። ካላወቅንም
እሰየው፤ ከእንጉርጉሮና ከፀፀት ተረፍን” ብሏል።
ጋዜጠኛ መሠረት አታላይ በፈርጥ መጽሔት ላይ “ለኪነ-ጥበብ ተፈጥሮ ለኪነ-ጥበብ
የሞተ” በሚል ርዕስ የደበበን ጓደኞች ዶ/ር ፍቃደ አዘዘን፤ መስፍን ኃ/ማርያምን እና
አስፋው ዳምጤን ቃለ መጠይቅ አድርጐ ጽፏል። ሁሉም የኪነ-ጥበብ ጋዜጠኞች ማለት
ይቻላል ስለ ደበበ ጽፈዋል። በ1995 ዓ.ም ደግሞ በጀርመን የባህል ተቋም ውስጥ በወ/ሮ
ተናኘ ታደሰ አስተባባሪነት ዶ/ር ፈቃደ አዘዘ፣ ዶ/ር ዮናስ አድማሱ እና ገዛኸኝ ጌታቸው
“የደበበ ሰይፉ ምሽት” ብለው እጅግ የደመቀ ዝግጅት አድርገዋል። ነብይ መኮንን፣ አበራ
ለማ እና አብርሃም ረታ ቅኔዎች ዘርፈውለታል። የወንዙ ልጅ አብርሃም ረታ እንዲህ
ገጥሞለታል፡-
ብናቀጣጥለው ኪነትክን እንደጧፍ
ስምህ ርችት ነበር
ላውዳመት እሚተኮስ
ሰማይ ላይ የሚጣፍ
ሰማይ ላይ የሚጦፍ
ሰማይ ላይ የሚጥፍ።
#ምንጭ ጥበቡ በለጠ