ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
175 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ገብረክርስቶስ ደስታ
(8)ከሞተች ቆይቷል
-----------------*
ከሞተች ቀይቷል
ብዙ ዘመን ሆኗል
ብዙ ነበር ጊዜው
ግን ፎቶግራፏ አለ
ደብዳቤዋም አለ
በጠጉሯ ጉንጉን የጠቀለለችው
ምን ቀን ቀጠሮ ነው
ቀን የቀን ጎደሎ
የቀን ጥቁር መጥፎ
አበባ ሄድኩ ይዤ
እዛ አበባ አልጠፋም
በመቃብሯ ውስጥ አበባ ተኝቷል፡፡
ስሜቴ ፈነዳ ገላዬን በተነው
ነፍሴን ነቀነቃት ገላዬን በተነው፡፡
ነፍሴን ነቀነቃት
እንባዬ ወረደ ጉንጬን አረጠበው
ለተረሳ ነገር እንዴት ያለቅሳል ሰው!
ለተረሳ ነገር
ምን ጊዜው ቢረዝም
የዚህ ዓለም ጣጣ እያንከራተተኝ
የዚህ ዓለም ስቃይ እየቦረቦረኝ
ሲጨንቀኝ ሰውነት
ፍቅሬ ይሁን ያንቺ የኔ መቃብር ቤት
ህይወት ነዶ ጠፍቶ
ሞት ፍሙን ሲያዳፍን
ያን ጨለማ ጓዳ ሄጄ ልተኛበት
ይመስላል ዘላለም
ሰው ሰውን ሲወዱት
አይኑን አይኑን ሲያዩት
ይመስላል ዘላለም
አድማስ አልፎ አድማስ
ምጥቀት አልፎ ምጥቀት
ጠፈር አልፎ ጠፈር
ይመስላል ዘላለም
ሰው ባካል የሚኖር
ድሮ አውቀዋለው
ተረድቼዋለው
ፀሀይ ጥቁር ስትሆን
ቀን ቀንን ሲያጠላው
ሌት ሌትን ሲሸፍን
እረስቸው እንደሁ፡፡
እንዴት አንቺን ልርሳ
ነፍሴ አብሯት የሚኖር
የፍቅርሽ ጠባሳ፡፡
˝ፍቅርሽና ፍቅሬ የተወሳሰበው
አልበጠስ አለኝ ብስበው ባስበው˝
ማን ነበር ማ ነበር
ማ ነበር እንደዚህ ብሎ የገጠመው?
ይመስላል ዘላለም
አንቺ የኔ እመቤት ብያት የነበረ
አንተ የኔ ጌታ
አንተ የኔ ጌታ ብላኝ የነበረ
አንቺ የኔ እመቤት
ይመስላል ዘላለም፡፡
እንባዬ ወረደ ልቤን አቃጠለው
ልቤ ተነደለ
የሰቀቀን እሳት አካሌን ሲያነደው
ደሜ ገነፈለ
የደም ጥቁር እንባ
ቆዳ የሚያሳስር መንፈስ የሚያባባ
አለቀሰቅሳትም
ቡዳ እሷን አይበላም
ቢስ አሷን አያይም
አልቀሰቅሳትም በነብሴ ተጉዤ እጠይቃታለው
አውቃለው አውቃለው
በመቃብሯ ውስጥ
ጢስ እንጨት ይጨሳል
ከርቤ ብርጉድ እጣን
መቃብሯ ሽቱ
ጣፋጭ መኣዛ አለው አጥንቷ ታቦቱ
መቅደስ ቤተልሄም ቅኔ ማህሌቷ
እጣኑ ይጨሳል ይታጠናል ቤቷ
ፍቅሬ ሙሽራዬ
እመቤቴ ፍቅሬ ያለም አለኝታዬ
አቴቴዋ ይታጠናል
ልዩ መዓዛ አላት
በመቃብሯ ውስጥ ጢስ እንጨት ይጨሳል
በመቃብሯ ውስጥ አበባ ተኝቷል፡፡
ፍቅሬ ፍቅሬ ፍቅሬ፤
ፍቅሬ ፍቅሬ ፍቅሬ
እመቤቴ ፍቅሬ እመቤቴ ፍቅሬ፤
እመቤቴ ፍቅሬ እመቤቴ ፍቅሬ
ፍቅሬ አለኝታዬ ፍቅሬ አለኝታዬ፤
ፍቅሬ አለኝታዬፍቅሬ አለኝታዬ
እንባዬ ወረደ…………………..
እንግዲህ ይበቃል ይቅር ይቅር ይብቃ
በድካም መድከም ባሳብ ሀሳብ አለ
ባዘን………….. ሃዘን……….ሃዘን

@getem
@getem
@gebriel_19
#ሶስተኛ_ወገን

በእግዜር የተጋባ
በሰው ላይፋታ
እንለይ !! ቢመስለን
ሽርደዳ በረታ
የኔና አንቺ ፍቅር ፥ ለመቆራፈዱ
ሶስተኛ ወገን ነው ፥ አመኬላ ጉዱ
ትያለሽ...
እላለው...
ሆድ ሲያውቅ ሽወዳ
ታውቂያለሽ ...
አውቃለው...
ለገዛ ቤታችን
የትዳር ጦርነት ፥ የፍቅር ሽኩቻ
መተማመን ሳለ
የጠብን ዳውላ ፥ ጥሎ መበለቻ
ዱላና ወሬውን ፥ ያቀበለሽ ማን ነው?
ሚስትህን ግደላት !!
ብሎ ያስታጠቀህ ፥ ያዘመተህ ማን ነው?
በሚል ማተራመስ !!
ሀገር ምድሩን ማመስ
ጣት እየቀሰሩ ፥ ነገሩ ማድበስበስ
ለጫርነው ጠባሳ ፥ ሶስተኛ አካል መውቀስ
አይጠቅመኝ
አይጠቅምሽ
አፉ በይኝ አንቺ ፥ እኔ ይቅር ስልሽ
እንጂማ ....ትዳሬ
አድሮ መወቃቀስ ፥ እየፈጩ ጥሬ
ምን ሊረባኝ ለኔ ?
ላንቺስ ምን ሊበጅሽ ?
እረፍት የሚነሳን ፥ ከደጄ ፣ ከደጅሽ
የሚደቃሽ ክንዴ ፥ የደቆሰኝ እጅሽ ።

#አብርሀም_ተክሉ

@getem
@getem
@getem
👍1
ገብረክርስቶስ ደስታ
(9)እጠብቃታለው
---------------*
አይን የማያየውን ሀሳብ ያያል ሄዶ
እጅ የማይነካውን ልብ ያንቃል አሳዶ
ተመለሽ አልልም ሞት ለያይቶን እንደው
ያባት ያያት እርስት
የመጨረሻው ቤት
ለፀጥታው አለም
እንግዳ አይደለንም
መለየት እንደሆን
ለይቶ ያስቀረን
ሃሳብ ይላላካል
ሃሳብ ይገናኛል
አይን የማያየውን ሀሳብ ያያል ሄዶ
ጆሮ የማይሰማውን
በፀጥታው ቦታ ልብ ያንቃል አሳዶ
ማን ያውቃል ለሞትም
ይኖራል መቃብር
ጉዞ አይቋረጥም
አለም እያረጀ አለም ይፈጠራል
አበባ በፍሬው ህይወትን ያድሳል
የፅጌረዳ እሾህ ያበባው ጠባቂ
ሳቂ የለም ሳቂ
እሾህ እሆናለው
የምወዳትን ልጅ እጠብቃታለው
በቁም ያሰረኝን የሃሳብ ሰንሰለት
ሰብሬ በጥሼ እኮበልላለሁ፡፡
እስከ ዓለም ዳርቻ እከተላታለሁ
ሳላያት አልቀርም አለ ስጦታዋ
አለ ትዝታዋ እሷን የሚያስታውስ
ስበላ ስጠጣ
ስተኛ ስነቃ ሳስብ ስተነፍስ
እሷን መርሳት አልችል
ፍቅር እምነት ህይወት
አብረን ተደስተን አብረን ተቸግረን
አበባ ለቅመናል ከወንዝ ዳር ሄደን
እሸት ፈልፍለናል መስክ ላይ በልተናል
ልብሳችን በስብሶ በዝናብ ሄደናል
እሳት አንድደናል
ፍሙን ተርኩሰናል
በርዷት ተኮራምታ ህፃኗ ጨረቃ
ፊቷ ደም ሲመስል ፀሀይ ተዘቅዝቃ
ሁሉንም አይተናል
በሁሉም ስቀናል
ህይወት እንደዚህ ነው
ዓለም ነው ብለናል
እርሷን መርሳት አልችል
እፈልጋታለው
እከተላታለው
እጠብቃታለው፡፡

@getem
@getem
@gebriel_19
ልንገርሽ
#####

ልንገርሽ አንቺዬ
ትንሽ ካሰብኩበት ነገር በኔ ይብሳል፤
ገጣሚ ደንቡ ነው
ከአንገቱ ጎንብሶ ስንኝ ይቀልሳል።

ስንኝ ሌላ አይደለም
አንቺው ነሽ ስንኟ በኔ ድርሰት ዓለም፥
እሩቅ አታስቢ
ይኸው ካንቺ ውጪ ሌላ ማንም የለም።

ልንገርሽ አንቺዬ
ልብ ብለሽ ስሚኝ ብትሰሚ ይበጅሻል፣
አንቺ ካነሽበት
ብዕሬ ክፉ ነው አሳንሶ ያይሻል፤
ከስንኝ ወደ ሀረግ
ከሀረግ ወደ ቃል
ከቃል ወደ ፊደል ቁልቁል ያ




ል።

@getem
@getem
@paappii

#አብርሃም
ገብረ ክርስቶስ ደስታ
(10)የፍቅር ቃጠሎ
-----------------*
ጉንጭሽ ፅጌረዳ ሞቆት የፈነዳ
አይንሽ የጠዋት ጨረር
የበራ ማለዳ፡፡
የማትጠገቢ የሥንዴ ራስ ዛላ
አገዳ ጥንቅሽ
ጠብ አትይ አንጀቴ ባኝክ ብመጥሽ፡፡
ቆንጀ ነሽ አንቺዬ
እሳት ነበልባል ነሽ ንዳድ ባከላቴ
ሆነሻል ሙቀቴ
ሆነሻል ህይወቴ፡፡
የጋለው ትንፋሽሽ
የሞቀው ምላስሽ
ማርኮኝ በከንፈርሽ
እጄን ሰጥቻለው
እስረኛ ሆኛለው፡፡
ያንቀጠቅጠኛል ወባ ቅናት ገብቶ
ልቤን አስፈራርቶ
ትኩሳት አምጥቶ፡፡
ፍቅርሽ አቃጠለኝ በመልክሽ ልተክዝ
እቀፊኝ ልቀዝቅዝ
ንከሺኝ ልደንዝዝ፡፡
............//............
©ገብረ ክርስቶስ ደስታ

አናመሰግናለን!!!

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
"ሲመሽ ሰው ፈጥሬ"
(ሁለት የወለደ አባት)
መዝን ወርቁ
**
ለጉልበቴ ክፋይ ለዘሬ መተኪያ አምሳያ ዘርቼ
ለልጄ ወንድሞች ሁለት ልጅ ወልጄ
አንዱ አንዱን መሣይ እንዳንዱ ያማረ
ታላቁ ጠይሞ ታናሹ የወፈረ
በመልክ 'ማይለዩ ደማቸው አንድ ቃል
አንድ ማእድ ቆራሽ ያንድ ደብር ብ'ቅል
አንድ ላይ አዳሪ
አንድቤት ተማሪ
በየኔታ ቅኔ በያሬድ ቅላፄ አንድ ፃፍ ዘማሪ
በአንድ ቀንጃ አራሽ አንድ ማሳ ሰሪ
ሁለት አንድ የሆኑ
ሺ አንድ የሆኑ ሁለት ልጅ አኑሬ
ጭልምልም አለብኝ ሲመሽ ሰው ፈጥሬ
እሄው
ለሁለቱ ልጆቼ ሁለት ዳስ ጣልኩና
አንዱን ኩዬ ዳርኩት አንዱን ቀበርኩና
@getem
@getem
@getem
በሃገሩ ባዳ!
_________________________

ዩኒቨርስቲ የላኩት ልጄ... ሃገሩን አምኜ፥
ምንም አይቸገርም.. ወገኑ ነው ብዬ...
"ተደበደበ!" አሉኝ እንዲያው እንደዋዛ!
"ሊሞትብሽ ነው፡፡" የሚል - መርዶ አርጂ በዛ።
...............................................
ምነው ሆዴም ባባ... አንጀቴ ሳሳብኝ
ያጠባሁት ጡቴን ክፉ ጦር ወጋብኝ፥
የምሰማው ነገር ገዳይ መርዝ ሆነብኝ፤
ፍርሃት ... ፍርሃት አለኝ..
ሊማር እንደወጣ - ልጄ እንዳይቀርብኝ፤
…………………………………………………………….
በላቤ ነው ያደገው - በጭስ ውስጥ አልቅሼ - ባነባሁት እንባ
እንጀራ ጋግሬ - ቆጮውን ጠፍጥፌ - ጡቶቼን ሳጠባ፥
ነበር መፅናኛዬ - የአይኔ ማረፊያ
አይኑ እስኪቀላ - በኩራዝ አንብቦ - ግቢ እስኪገባ፤

ታዲያ ዛሬ...
ያለኝን ቋጥሬ - ከሌለኝ ቆጥሬ፥
ስሜ የሸኘሁት ልጄ - ድግሪ ይጭናል ብዬ!
ሃገሩን አምኜ!
ወገኑ ነው ብዬ!
"ተደበደበ!" አሉኝ እንዲያው እንደዋዛ፥
"ሊሞት ነው" የሚል ባለመርዶ በዛ!
…እኔን ይደብድቡኝ - ይሁን ለናትህ!
…እኔን ከርታታዬ... እኔ ልሙትልህ!
ልጄ ላንተስ አይሁን!
እኮ እንዴት ተደርጎ?
ምንስ አጠፋና...
ምስኪን ድሃው ልጄ - ወዶ ባልመረጠው - በብሔሩ ይቀጣ?
ምን አይነት ጭካኔ - ጊዜ ያመጣው ጣጣ፤
ለትምህርት የሄደ - ህይወቱን የሚያጣ?!
እኔስ አልችለውም - የሃዘኑን ነገር፥
ሌላ ባዕድ ሲሆን
በወገኑ ሲገፋ - ሰው በራሱ ሐገር!
__( አንድ ሃገር/ቢያ ቶኮ/ ገጽ 33-34 ... በዶ/ር ኤልያስ ገብሩ/ ህይወታቸውን ለመለወጥ ዩኒቨርሲቲ ሄደው በጎሣቸው ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን በሙሉ መታሰቢያ የተፃፈ፤) @eliasgebru

...
@getem
@getem
ጥያቄ??!!!!!!


ሰው ባይሆን ለሰዉ መሰላል ፤

ማን ከፍ ማን ዝቅ ይላል???

((( ምስራቅ ተረፈ )))

ሸጋ የሆነ ጁምኣ ይሁንላቹ!!!💚💛❤️

@balmbaras
@getem
@getem
ከ አሜን በስተቀር...
"እዮብ ዘ ማርያም"
-
ላትመጪ ነገር
ላትመለሽ ነገር
ከዕንባዬ ታግዬ..
የውስጤን ትኩሳት ምን ብዬ ልናገር?
ይህ ከንቱ ምኞቴ፣
ከቅዠት ተላቆ ለእውነት ቢበቃ
ደስ ይለኝ ነበረ፣
ከጎኔ ባገኝሽ ከዕንቅልፌ ስነቃ!
ሀዘኔን ላይገታው፣
ዕንባዬን ገድቦ ላይመልሰኝ ምክር
እንደዚህ ይለኛል፣
ከጭንቄ አላቆ ሊያፅናናኝ ሚሞክር!
"ንፋስ እስኪመጣ፣
በዛፍ ቅርንጫፍ ላይ እንዳረፈች ቅጠል
ሰውም እንደዚሁ፣
በግዜ ገላ ላይ ምንም ቢንጠለጠል
ግዜውን ጠብቆ፣
ሁሉም በየ ተራ ይረግፋል እንደ ጠል"
የዘመን ሀያል ክንድ፣
ውስጥን እያደማ እንደዘበት ያልፋል
አለ የተባለ፣
እንደ ጠዋት ጤዛ በ ንዳድ ይጠፋል
ይህ ሁሉ ቢሆንም፣
ከአሜን በስተቀር...
የትኛው ብርቱ ሰው ከግዜ ይጋፋል?
ቅስም እየሰበረ እየነጠቀ አቅም
ልክ እንደ ሱሰኛ፣
አፈር በየተራ የሰው ልጅን ቢቅም
ሁሉም ለበጎ ነው፣
ሀዘን እያበዛው ከ እግዜሩ አርቅም!
እራሴን ላበርታ፣
ሀዘኔን ልቀንስ ልፅናና ግድ የለም
ፍጡር የተባለ፣
ባለተራ እንጂ ማንም ቋሚ አይደለም
እንኳን ሰው ይቅርና፣
ግዜዋን ጠብቃ ሀላፊ ናት አለም!
የዘመን ሀያል ክንድ፣
ውስጥን እያደማ እንደዘበት ያልፋል
አለ የተባለ፣
እንደ ጠዋት ጤዛ በ ንዳድ ይጠፋል
ይህ ሁሉ ቢሆንም፣
ከአሜን በስተቀር...
የትኛው ብርቱ ሰው ከግዜ ይጋፋል?

@getem
@getem
@getem
በታደልሽው ሞያ
የምትሰሪው ምግብ እጅግ ቢጣፍጥም
እውነት እልሻለሁ
ዶሮ ወጥሽ እንኳን ከዳቦሽ አይበልጥም፡፡
😋😋😋

ልብ አልባው ገጣሚ
@getem
@getem
ታሪክማ በግድ እንሰራለን

(ቡሩክ ካሳሁን)

አያቶቻችን ሀገርን ከወራሪ ለመጠበቅ
ከጠላት ጋር ተከሳከሱ
ዘር ብሄር ሳይለዩ ደማቸውንም አፈሰሱ
እኛ ታሪክ መስራት ከብዶን ከአባቶቻችን ስላነስን
ወጉ እንዳይቀርብን በአያቶቻችን አፅም ተጫረስን፡፡


22/06/2011



😉
👕👉 @burukassahunc
👖
@getem
@getem
👍1
ለቅዳሜዋ!


ድሮ መች ነበረ ዘር መርጦ ጎረቤት
በጥዋቱ በጥንቱ በነ አባብዬ ቤት

እድር ማህበሩ ሲያሰባስብዋቸው
መች ይጠየቅ ነበር የዘር ሀረጋቸው


የአዳም ፍጥረቱ አንድ አይደለም ወይ
ለምን አስር ሆነ የሰው ልጅ ፀባይ


እፁብ ይቅር ብለህ በደላችንን
አንድ አምላክ ነህና
እኛንም አንድ አድርገን


እንድ አድርገን ጌታ !!!

አስቴር አወቀ

ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሚት!💚💛
"ናካይታ"💚
@getem
@getem
@balmbaras
።።። እሺ ይበልጣል ከሺ ።።።።።።

ይሄንንም እሺ...........
ያኛውንም እሺ...........
ሁሉን ስለው እሺ........
የኔ ምለው ጠፍቶ ተካፈልኩኝ ለ ሺ
ሀ.ገ.መ

@getem
@getem
የፍቅር ድር (ክፍል አንድ)
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ሊሆኑ ማይችሉ ፣ ግን ደሞ የሆኑ
ለማመን ሚከብዱ ፣ ግን የሚታመኑ
ታሪኮች አሉና
አፈቀርኩሽ ስልሽ ፣ እንዳትገረሚ
ታእምር የሚመስል ፣ ታሪክ ላውጋሽ ስሚ።
።።።።።
የቀደሙ እናቶች ፣ በስራ ተጠምደው
በምድር ያለን ጥጥ ፣ ጠቅላላ አገባደው
ሰማይ ባዶ እስኪቀር ፣ ደመናን ሲፈትሉ
የሚዘንብ ጠፍቶ
በጋራ ደረቀ ፣ ሳር ቅጠል እህሉ።
እናም በዚህ ጊዜ
አንድ የተራበ አባት
ለሚስቱ እንዲህ ሲል ፣ ቅኔ ተቀኘ አሉ።
።።።።።።
"ምትበዪው ሳይኖርሽ ፣ አምሮሽ መከናነብ
ደመናን ፈትለሽው
ከለበሽው ኋላ ፣ ዝናብ ከየት ይዝነብ?!
ሆዴስ እንዴት ይጥገብ
ልብሽና ልቤ በምን ይቀራረብ?
።።።።።
ሆዴ እየተራበ ፣ ልቤ እንዴት ይሙላ
ለብሶም አያጌጥም
ሆድ እየበረደው ፣ አይሞቀውም ገላ።"
።።።።።
ይህንን ስትሰማ
ከቆየች ሚስቱ ፣ ቅኔ ተፈጠረ
እንዲህ ትል ጀመረ
"ሁሉን ቢናገሩት ፣ ሆድ ባዶ ይቀራል
ደመና ቢጠፋ
ጠቢብ ሰው ከ'ሳት ጪስ ፣ ደመናን ይፈጥራል።
።።።።።
ልብህን ከልቤ
ለፈተለው ጠቢብ ፣ አይገኝም ወደር
ለሆድ ልብ አልሰጥም
እንጀራ ይሆናል ፣ ልብስ ሽጦ ማደር።
ፍቅርን የለበሰ
ሆዱን አይበርደውም ፣ ረቂቅ ነው ማፍቀር።"
።።።።
ሊሆኑ ማይችሉ ፣ ግን ደሞ የሆኑ
ለማመን ሚከብዱ ፣ ግን የሚታመኑ
ታሪኮች አሉና
"አፈቀርኩሽ" ስልሽ ፣ ፈፅሞ እንዳይደንቅሽ
ይልቅ ልብ ስጪኝ
በልብሽ አድምጪኝ ፣ ታምር የሚመስል ታሪክ ላሳውቅሽ ።
።።።።።።
አንድ ታላቅ ነብይ
እናትም ድንግልም ፣
ስለምትሆን ሴት ፣ ሲናገር ትንቢቱን
ህዝቡ ባለማመን
አዞሮበት ልቡን ፣ ፊት ነስተውት ፊቱን
ባገሩ ሲንቁት ፣
ለናቁት ልቦች ልብስ ፣ ክብርን ሸመነ
ነብይ ቀድሞ ያውቃል
አለማመን ራሱ ፣ ማመን እንደሆነ።


@getem
@getem
@lula_al_greeko
#ከፍቅር_በላይ
:
:
አፍቅሮኛል እያልሽ ያወጋሽው ወሬ
ስንት ጆሮ አልፎ ከኔም ደርሷል ዛሬ።
በኔ መውደድ ታስሮ መላወስ ከብዶታል
ያልሺውም ንግግር ከጆሮዬ ገብቷል።
ከራሴው ሳትሰሚ ሳታውቂው እርግጡን
የብብትሽን ጣልሽ ስታልሚ ቆጡን።
ሁሉን ሰምቻለው ማን ምንስ እንዳለኝ
አንቺ አፍ እንዳለሽ እኔም ጆሮ አለኝ።
:
:
ምንም ይሁን ምንም
ስሜን ስላጠፋሽ አላዘንኩብሽም
እውነቱ ግን ይህ ነው እኔ አላፈቅርሽም
እኔስ አልወድሽም።
:
:
እርግጥ ነው አልክድም...
ከቤትሽ ፊት ለፊት ከዋርካው ጥላ ስር ሁሌ እቀመጣለው
ዕድል ያልቀናኝ ለት ያላየውሽ እንደው ጭንቄን አምጣለው
ያየውሽም ከሆን እንደ ረጋ ወተት በደስታ እናጣለው።
:
:
እርግጥ ነው አልክድም...
ያ የሰፈራችን ጠብደሉ ጎረምሳ በጨዋታ መሀል ሲሰድብሽ ስሰማ
በጣም ተናድጄ ፈንክቼው ሮጬያለው ጠብቄ ጨለማ።
ደግሞም የሆነ ጊዜ በመንገድ እያለፍሽ አንዱ ጓደኛችን የለከፈሽ ለታ
ደም ፋላቴ መቶ አዝንቤበታለው የቡጢ ጋጋታ።
:
:
እርግጥ ነው አልክድም...
ሳገኝሽ ስቄያለው ሳጣሽም ከፍቶኛል
አንቺን ብቻ እያየው በመንገድ ሳቀናም ስልክ እንጨት ገጭቶኛል
ትረፍ ሲለኝ ከላይ መኪናም ስቶኛል።
:
:
እርግጥ ነው አልክድም...
ጎኔና ፍራሼ የገጠሙ ጊዜም በህልሜ አይሻለው
ስምሽን ሲጠሩት የጠሩኝም መስሎኝ ስንቴ አቤት ብያለው
አዝነሽ ያየው ቀንም ደም እንባ አልቅሻለው።
:
:
ይህንም አልክድም...
ምንም ቢሆን ምንም
እኔ አንቺን አልወድም።
:
:
አፍቅሮኛል ብለሽ ስሜን ስላጠፋሽ አላዘንኩብሽም
እውነት እውነት ስሚኝ አላፈቀርኩሽም።
:
:
ይህ ፍቅር አይደለም
ይህ መውደድ አይደለም
ለጓደኞችሽም ዳግም ስታወጊ
ከዚህ የተሻለ ሌላ ቃል ፈልጊ።
አፍቅሮኛል ብለሽ ፍቅሬን አትግደዪ
ከፍቅር በላይ ነው ያፈቀረኝ በዪ
ከመውደድ በላይ ነው የወደደኝ በዪ።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
#አሜን
@getem
@getem
@getem
feeling የራስሽ
...ጉዳይ!!
---------------------------
ከ'ምነቴ፣ ከ'ውነቴ
ሸሽተሽ ከገነቴ፣

ዓርያም እሚያወጣን
የፍቅርን ቅዳሴ
የዕርገቱን እጣን፣
ብትሄጂም እረግጠሽ
ከወረብ፣ ዝማሜ
ዳንኪራውን መርጠሽ፤
...
ምላሴን ለእርግማን አላንቀሳቅስም
በሃገሬ ባህል ሙት አይወቀስም።

--------------------//------------------
( በርናባስ ከበደ )

@getwm
@getem
@lula_al_greeko
ትቀሪያለሽ ብዬ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
.
ትቀሪያለሽ እያልኩ
ታረፍጃለሽ እያልኩ ፣ ብዙ ጊዜ አለፈ
ገጣሚው በውሉ
ፍቅረኛው ቀርታበት
"ትመጫለሽ የሚል ፣ እልፍ ግጥም ፃፈ።
እኔ ግጥም ጠፋኝ ፣
ቀድመሽ ስትገኚ ፣ ራቀ ከልቤ ሀሴት
ለገጣሚ ደግሞ
ፍቅረኛ አትሆንም ፣ቀጥራ የማትቀር ሴት።
።።
እናም እልሻለሁ
ቅሪብኝ ልቅርብሽ ፣ ልቤ እያፈቀረሽ
ምኑን ገጣሚ ሆንኩ
ትመጣለች ካላልኩ ፣ ቀጥረሽኝ ካልቀረሽ።

@getem
@getem
@lula_al_greeko
ለውብ ቀን!
💚

አለን እንዳንል ኖረን አላወቅንም
የለንም እንዳንል ሞተን አላለቅንም፡፡

ታሪክ ሆኖ ሊጻፍ ጉድ ተብሎ ሊነገር
እንሰሳ ወሮታል የሰዎቹን አገር!!


ገጣሚ Minase

@getem
@getem
👍2