ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#አንድነት
:
:
አንድነት የሚባል የጥንት አብሮ አደጌ
ሰው መሀል አጣሁት ዛሬ ላይ ፈልጌ።
በሉ እስኪ እንቁረጠው እንውጣና ካፋፍ
አንድነት እንዳይታይ የከለለውን ዛፍ።


#አሜን
@getem
@getem
አስተያየት ካሎት @Henokbirhanu
#ከፍቅር_በላይ
:
:
አፍቅሮኛል እያልሽ ያወጋሽው ወሬ
ስንት ጆሮ አልፎ ከኔም ደርሷል ዛሬ።
በኔ መውደድ ታስሮ መላወስ ከብዶታል
ያልሺውም ንግግር ከጆሮዬ ገብቷል።
ከራሴው ሳትሰሚ ሳታውቂው እርግጡን
የብብትሽን ጣልሽ ስታልሚ ቆጡን።
ሁሉን ሰምቻለው ማን ምንስ እንዳለኝ
አንቺ አፍ እንዳለሽ እኔም ጆሮ አለኝ።
:
:
ምንም ይሁን ምንም
ስሜን ስላጠፋሽ አላዘንኩብሽም
እውነቱ ግን ይህ ነው እኔ አላፈቅርሽም
እኔስ አልወድሽም።
:
:
እርግጥ ነው አልክድም...
ከቤትሽ ፊት ለፊት ከዋርካው ጥላ ስር ሁሌ እቀመጣለው
ዕድል ያልቀናኝ ለት ያላየውሽ እንደው ጭንቄን አምጣለው
ያየውሽም ከሆን እንደ ረጋ ወተት በደስታ እናጣለው።
:
:
እርግጥ ነው አልክድም...
ያ የሰፈራችን ጠብደሉ ጎረምሳ በጨዋታ መሀል ሲሰድብሽ ስሰማ
በጣም ተናድጄ ፈንክቼው ሮጬያለው ጠብቄ ጨለማ።
ደግሞም የሆነ ጊዜ በመንገድ እያለፍሽ አንዱ ጓደኛችን የለከፈሽ ለታ
ደም ፋላቴ መቶ አዝንቤበታለው የቡጢ ጋጋታ።
:
:
እርግጥ ነው አልክድም...
ሳገኝሽ ስቄያለው ሳጣሽም ከፍቶኛል
አንቺን ብቻ እያየው በመንገድ ሳቀናም ስልክ እንጨት ገጭቶኛል
ትረፍ ሲለኝ ከላይ መኪናም ስቶኛል።
:
:
እርግጥ ነው አልክድም...
ጎኔና ፍራሼ የገጠሙ ጊዜም በህልሜ አይሻለው
ስምሽን ሲጠሩት የጠሩኝም መስሎኝ ስንቴ አቤት ብያለው
አዝነሽ ያየው ቀንም ደም እንባ አልቅሻለው።
:
:
ይህንም አልክድም...
ምንም ቢሆን ምንም
እኔ አንቺን አልወድም።
:
:
አፍቅሮኛል ብለሽ ስሜን ስላጠፋሽ አላዘንኩብሽም
እውነት እውነት ስሚኝ አላፈቀርኩሽም።
:
:
ይህ ፍቅር አይደለም
ይህ መውደድ አይደለም
ለጓደኞችሽም ዳግም ስታወጊ
ከዚህ የተሻለ ሌላ ቃል ፈልጊ።
አፍቅሮኛል ብለሽ ፍቅሬን አትግደዪ
ከፍቅር በላይ ነው ያፈቀረኝ በዪ
ከመውደድ በላይ ነው የወደደኝ በዪ።

#አሜን
@getem
@getem
@getem
አስተያየት ካሎት @Henokbirhanu
#ሆናለች_ሞልቃቃ
:
:
አንድ ቀን በማታ ከፍቅሬ ጋር ሆኜ
ሽቅብ ሽቅቡን ሳይ በአሳብ መንኜ
አንድ እውነት ተረዳሁ በልቤም ገነነ
ቀን በመሽ ጊዜ የሰማይ ውበቱ ኮከብ እንደሆነ።
:
:
ልክ ይሄ እንደገባኝ ወዲያው በሹክሹክታ
ለምወዳት ፍቅሬ እንዲ ብዬ አልኳታ።
:
:
ያለ ከዋክብት እንደማይደምቅ ሰማይ
እኔም ደንጋዛ ነኝ ካንቺ ውጪ ስታይ።
አንቺው ነሽ ኮከቤ ለህይወቴ ድምቀት
ሰማዩ እኔነቴን እንዳይወርሰው ፅልመት።
:
:
ይህን ካልኳት ወዲ...
የሚገርመው ነገር ኮከቤ ያልኳትን ቃል በአምሮዋ ታጥቃ
ያለሷ እንደማልደምቅ በተጠንቀቅ አውቃ
ከዛን ቀን ጀምሮ ሆናለች ሞልቃቃ።

#አሜን
@getem
@getem
@getem
አስተያየት ካሎት @henokbirhanu
#ነይ
:
:
ማብሰሉን ተዪና ወጥን በስልቻ
ላንቺም እንዲስማማሽ እንዲሆንሽ ሀቻ
ነይ ከኔ ውሰጂ ድስትና ጉልቻ።

#አሜን
@getem
@getem
@getem
አስተያየቶን @Henokbirhanu
#አይገኝም
:
:
በህይወት ጎዳና
ሳንል ጎንበስ ቀና
ያለ እንቅፋት ያለ እሾ
አይገኝም የድል እርሾ።

#አሜን
@getem
@getem
@getem
ለአስተያየቶ @Henokbirhanu
Henok Birhanu:
#ብቸኝነቴ
:
:
የብቸኝነት ዶፍ በላዬ ዘነበ
አንቺን ካጣ ወዲ መንፈሴም ተራበ
ሰው መግባባት ጠፋቶት ምላሴም ለዘበ
ገላዬ አዘን ጎዳው ፅልመትን ደረበ
ልቤ አላምን ብሎ እውነት ነው እያለ ዐይኔ ዘንድ ቀረበ
ዐይኔም አዎ እውነት ነው ለልቤም ነገረው በእምባ እየታጠበ።
:
:
ይሄኔ ነው እንግዲ አንቺን ለማጣቴ እርግጠኛ የሆንኩት
አብረን እንደማንኖር ውስጤን ያሳመንኩት።
:
:
አብረን እንደማንሄድ ከጎኔ ሸሽጌሽ
አቅፌሽ አቅፈሺኝ ባደባባይ ይዤሽ
እንደማይሆን ገባኝ ካሁን ቧላ በቅቷል
መለያየታችንን ሀገር ሁሉ ሰምቷል
አምላክ እስካልሻረው በማህተም ተመቷል።
:
:
ይሄኔ ነው በቃ
ብቸኝነቴ ዘልቆ ከደምስሬ
ብቸኝነቴ ከእግር እስከ ፀጉሬ
እያወዛወዘኝ ልክ እንደ ባህር ዛፍ
እያመነመነኝ ሲያቀልጠኝ እንደ ጧፍ
እያብረከረከኝ ጉልበት እንዳነሰው
ችግር እንደበላ ሆዴን እያመሰው
እንደ ሁዳድ ቆጥሮ ልቤን እያረሰው
ሽቅብ አስመልክቶ ዐይኔን ያስለቀሰው።
:
:
ታዲያ
ምን ይሆንስ መፍቴ ምን ይሆንስ መላ
ባተሌነት ደርሶ ላባከነው ገላ።
ምን ይሆን ማርከሻ ምን ይሆን መድሀኒት
የትካዜ ሾተል ለሚሸነቁረው ቀንም ሆነ ሌሊት።
:
:
ምንም ነው መልሱ የለም አማራጪ
በትዝታ አለንጋ ከመሸንቆጥ ውጪ።
:
:
በስተመጨረሻም
በዚች አጭር መንገድ በዚች የህይወት ጉዞ
እኔነቴ በፍቅር እልፍ ተወዝውዞ
ብዙ ነገር ታዘብኩ ብዙ ነገር ቃኘው
መለያየት ከሞት እንደሚበልጥ አየው።

#አሜን
@getem
@getem
@getem
አስተያየት ካሎት @henokbirhanu
#እኔ እንደው
:
:
በሀዘን ሌት ተቀን ብናኝ
በደስታ ውቅያኖስ ውስጥ ብዋኝ
በችግር ሰውነቴ ቢደቅ
በተድላ ምን ብንደላቀቅ
ቢበርደኝ ቁሩ በርትቶ
ቢሞቀኝ ኑሮ ተስማምቶ
ቢጥለኝ የዚህ ዓለም ፍዳ
ቢደላኝ ያለ አንዳች ዕዳ
ብታለቅስ ህይወቴ ታማ
ብትስቅ ደግሞ አገግማ
ብሸነፍ ካንዴም ሁለቴ
ቢበልጥ ከሰው ብርታቴ
ቢኖረኝ ብዙ ቀማኛ
አልያም ብሆን ዝነኛ
ቢነሳ ስሜ በክፉ
ቢስሙኝ እየደገፉ
ብከበር ባገር መንደሬ
ቢረሳም ከነ መኖሬ
እኔ እንደው እኔ እራሴው ነኝ
ሁኔታን ሁሉን ረግጬ
የምኖር አንቺን መርጬ።
እኔ እንደው እኔ እራሴው ነኝ
እንዳሻው ቢፈጠር ታምር
የምሞት አንቺን ሳፈቅር።
እኔ እንደው እኔ እራሴው ነኝ
እኔ እንደው እኔ እራሴው ነኝ

#አሜን
@getem
@getem
@getem
አስተያየት ካሎት @henokbirhanu
#ከፍቅር_በላይ
:
:
አፍቅሮኛል እያልሽ ያወጋሽው ወሬ
ስንት ጆሮ አልፎ ከኔም ደርሷል ዛሬ።
በኔ መውደድ ታስሮ መላወስ ከብዶታል
ያልሺውም ንግግር ከጆሮዬ ገብቷል።
ከራሴው ሳትሰሚ ሳታውቂው እርግጡን
የብብትሽን ጣልሽ ስታልሚ ቆጡን።
ሁሉን ሰምቻለው ማን ምንስ እንዳለኝ
አንቺ አፍ እንዳለሽ እኔም ጆሮ አለኝ።
:
:
ምንም ይሁን ምንም
ስሜን ስላጠፋሽ አላዘንኩብሽም
እውነቱ ግን ይህ ነው እኔ አላፈቅርሽም
እኔስ አልወድሽም።
:
:
እርግጥ ነው አልክድም...
ከቤትሽ ፊት ለፊት ከዋርካው ጥላ ስር ሁሌ እቀመጣለው
ዕድል ያልቀናኝ ለት ያላየውሽ እንደው ጭንቄን አምጣለው
ያየውሽም ከሆን እንደ ረጋ ወተት በደስታ እናጣለው።
:
:
እርግጥ ነው አልክድም...
ያ የሰፈራችን ጠብደሉ ጎረምሳ በጨዋታ መሀል ሲሰድብሽ ስሰማ
በጣም ተናድጄ ፈንክቼው ሮጬያለው ጠብቄ ጨለማ።
ደግሞም የሆነ ጊዜ በመንገድ እያለፍሽ አንዱ ጓደኛችን የለከፈሽ ለታ
ደም ፋላቴ መቶ አዝንቤበታለው የቡጢ ጋጋታ።
:
:
እርግጥ ነው አልክድም...
ሳገኝሽ ስቄያለው ሳጣሽም ከፍቶኛል
አንቺን ብቻ እያየው በመንገድ ሳቀናም ስልክ እንጨት ገጭቶኛል
ትረፍ ሲለኝ ከላይ መኪናም ስቶኛል።
:
:
እርግጥ ነው አልክድም...
ጎኔና ፍራሼ የገጠሙ ጊዜም በህልሜ አይሻለው
ስምሽን ሲጠሩት የጠሩኝም መስሎኝ ስንቴ አቤት ብያለው
አዝነሽ ያየው ቀንም ደም እንባ አልቅሻለው።
:
:
ይህንም አልክድም...
ምንም ቢሆን ምንም
እኔ አንቺን አልወድም።
:
:
አፍቅሮኛል ብለሽ ስሜን ስላጠፋሽ አላዘንኩብሽም
እውነት እውነት ስሚኝ አላፈቀርኩሽም።
:
:
ይህ ፍቅር አይደለም
ይህ መውደድ አይደለም
ለጓደኞችሽም ዳግም ስታወጊ
ከዚህ የተሻለ ሌላ ቃል ፈልጊ።
አፍቅሮኛል ብለሽ ፍቅሬን አትግደዪ
ከፍቅር በላይ ነው ያፈቀረኝ በዪ
ከመውደድ በላይ ነው የወደደኝ በዪ።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
#አሜን
@getem
@getem
@getem
ዱአና ፀሎት
""""""""""""""
በክርስቲያኑ ዘንድ
የአብይ ፆም አልቆ እንደተቃለለ
አሁን በሙስሊሙ
የረመዳን ፆም ወቅት መልሶ ቀጠለ
በዱአና ፀሎት
ሰይጣን መሄጃ አጣ ሲደበደብ ዋለ
በሰንሰለት ታስሮ
በብረቶች ታጥሮ በሩቁ ተጣለ።

አለም ነጃ ትውጣ
አለም ነፃ ትውጣ
ከመጣባት ደዌ ከያዛት በሽታ
በቃ በለን ይብቃ
ከሰቆቃ ወጥተን እንኑር በደስታ!

ነጃ በለን ነጃ
ነፃነት አድለን ሰላም ለዱንያ
ሞቶብን አይለቅ
የሰው ክቡር ህይወት ልክ እንደ ክፍያ!

ነፃ በለን ነፃ
ነፃነት አድለን ሰላም ለምድሩ
ጤና ሁኖ ይደር
ጤና ሁኖ ይዋል አውጋርና አድባሩ!
#አሜን

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@getem
@getem
@getem