ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ጠላቴ
፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣

ጠላቴን ስፈልግ፣ ከጎሮቤቶቼ
ጠላቴን ስፈልግ፣ ከባልደረቦቼ
ጠላቴን ስፈልግ፣ ከሩቅ፣ ከቅርቦቼ
ለካስ ክፉ ጠላት ደመኛዬ ያለው
ከገዛ እኔነቴ ከራሴ ውስጥ ነው።

@getem
@getem
@paappii

#solomon moges
ግጥም በSAM:
#የሴት_ልጅ
(በስሜነህ አማረ- SAM)
በወንድነት ልኬት~ ሴትነት ካነሰ
የሰው ልጅ ለራሱ~ ራሱን አሳነሰ።
እኔን ግን...
ሁለት ሶስት ጊዜ
ድጋሚ ደጋግመህ~ ና 'የሴት ልጅ' በለኝ
እናቴን ስትጠራት
በክብሯ ስትነግስ~ ልጇን ደስ ይበለኝ
ስሟን ልታሳንስ
መጥራትህ ከሆነ~ እንዲህ ብለህ ያልከኝ
ይግረምህ ሞተሃል
እኔ ግን እንዳልከው~ አዎ የሴት ልጅ ነኝ።
ገበሬ ዘር ይዞ
መዝሪያ ቦታ ካጣ~ ምን ላይ ነው ግብርናው?
ዘሩ ፍሬ ሆኖ
አፍሰህ የምትቅመው~ በልስልስ ማሳ ነው
ስለዚህ...
እናትህ አፈር ነች
ለስላሳዋ ማሳ~ ያንተነት መብቀያ
እናትህ ውሃ ነች
ያለሷ ድርቅ ነው~ ህይወት የ'ልም ቋያ
እናትህ አየር ነች
እስትንፋስ 'ምትለግስ~ የሷ ትንፋሽ ሲያጥራት
እናትህ እሳት ነች
ለራሷ ተቃጥላ~ ላንተ ስትል 'ምትሞት
ያንተን የት መጤነት
ሰው የመሆን ምስጢር~ ልክህን ብታውቀው
ሁሉም ማንነትህ
አፈርና ውሃ~ ነፋስና 'ሳት ነው።
:
:
ማነው...?
ሴት ያላረገዘው
ሴት ያላማጠችው~ ሴት ያልወለደችው
ሴት ያላቀፈችው
ሴት ያላጠባችው~ ሴት ያላዘለችው
ወንድ ነኝ ባይ ሁላ~ ክፍት አፉን ሲከፍተው
የውስጡ ባዶነት~ ጎልቶ የሚታየው
ከሴት ያልተገኘ~ እርሱ ራሱ ማነው???
:
:
እኔን ግን...
ሁለት ሶስት ጊዜ
ድጋሚ ደጋግመህ~ ና 'የሴት ልጅ' በለኝ
እናቴን ስትጠራት
በክብሯ ስትነግስ~ ልጇን ደስ ይበለኝ::


የሴት ልጅ ነኝ።
:
:
@SAM

@getem
@getem
@getem
PERM University Russia ( For Medical students)
It is not scholarship, but the tution fee is cheap and reasonable compared to another universities abroad even compared to Ethiopian Private medical schools.
1. Medicine , Dentistry and Pharmacy tution fee is 1800 USD per year.
2. Very low living cost 300 USD( For Dormitory and Meal) Per month.
 The students who apply now will start the class on December. So the university representative  Mr Neil is here in Ethiopia to facilitate the visa and application process for students with in short time. Students who would like to pay 1,800 USD( very cheap for Medical study) tuition per year for medicine can come to our office and begin application process with Mr. Neil. For more information read the below PDF.
Office location: kera Sophia mall Room number 315.
Also dial: 0968494912 for more information
To see the update join @EthiopiaEducation
ሕብረ ሙሾ

ለዕርቅ የማይዳኝ ፈራጅ ስለ በዛ
ቆሞ ስለሚከስ ይሄን ታሪክ በ'ዛ
እከሌ ሚሉት ነው እንደዚህ ያረገኝ
በሚለው ሐረግ ውስጥ
እግዜር ጥፋተኛ ሆኖ እንዳይገኝ፤
ፈራሁ!
ግድ የለም ግድ የለም
ጥፋተኛስ ይሁን ሸንጎ እናቅርበው
ከጎልጎታ ሌላ ወዴት እንስቀለው?
ልበ -ቢስ ከሆንን ከትናንት 'ማንማር
እኛስ አንታረቅ እግዜሩን እንማር፡፡

@getem
@getem

#stupid world 1
ኑሯችን
፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣

አበ መቃብር ቤት፣ በመቃብሩ ላይ
መንኩሰው ሲኖሩ ይገረማል የሚያይ
በቀን፣ በጨለማ ገፍተን ወዲያ ጥለን
ሌሎች መቃብር ላይ የቆምነው ስንት ነን??

@getem
@getem
@paappii

#solomon moges
#BREAKING


👉 ሰላም የግጥም ብቻ ቤተሰቦች እንዴት ናቹ፣ ዛሬ ሽልማት ሚየስገኝ ጥያቄ ማታ #3:30_ሰዓት ላይ ይዘንላቹ እንቀርባለን፣ ሽልማቱን ላሸነፉ ተሳታፊዎችም፣ ጥቅምት 17 ቀን በሀገር ፍቅር ቲያትር በሚዘጋጀው፣

#ወገግታ_ወ_ስዕል_ወ_ወግጥም በተሰኘው የስነፁፍ ምሽት መግቢያ #አስር_የ100 ብር ቲኬቶችን 😳 ለሽልማት አቅርበናል፣ እድሎን ይሞክሩ 👍

@getem
@getem
@getem

#share
👍1
* #በላይ_በቀለ_ወያ *

ሰው ሀገር ሆናችሁ
ሞቴን ባገሬ አርገው ፣
ምናምን ብላችሁ ፣ አታውሩልኝ ወሬ
ሬሳ ሰብሳቢ..
ጥንባንሳ አይደለችም ፣ ኢትዮጵያ ሀገሬ፡፡

ህይወታቹ እንጂ
እውቀታችሁ እንጂ ፣ የሚበጀው ላገር
ሞትማ ያው ሞት ነው!
የትም ቀባሪ አለ ፣ የትም አለ አፈር፡፡

@getem
@getem
@getem
እንዳያመልጣቹ 3:30 ሰዓት ላይ ለግጥም ብቻ ተከታዮች 10 የመቶ ብር መግቢያ ትኬቶች
.
.
.
.
loading


@getem
#BREAKING

Guys i got a big suprise for you የትኬቱን መጠን ከ10 ወደ 20 አሳድገነዋል
.
.
.
@getem
@getem
@getem
ሞቼ ተቀብሬ
ተበልቶ ተዝካሬ
በ አለም ተረስቼ
ሞቼ ተዘንግቼ
ከመቃብሬ ላይ አንድ ቀን ብቅ ብለሽ
በፈካ ጨረቃ ውብ አበባ ይዘሽ
"አዎድሀለውኝ " ብትይኝ ጮክ ብለሽ
አፈር አራግፌ መቃብር ፈንቅዬ
እነሳልሽ ነበር ጠራሽን ወይ? ብዬ።
#የመጀመሪያ ጥያቄ አሁን የለቀቅነው ግጥም፣ የገጣሚው ስምና የግጥሙስ ርዕስ ምንድነው ?

መልሱን ለመለሱ 3 መላሾች ለእያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት የመቶ ብር መግቢያ ትኬት እንሸልማለን

መልሳቹንም ከአሁን ጀምሮ @paappii በመላክ መወዳደር ትችላላቹ

መልካም እድል

@getem
@getem
@getem
#BREAKING

እስካሁን ማንም ሙሉ ለሙሉ መልሱን የመለሰ ሰው #የለም.......አሁንም ሞክሩ .........ካልሆነ ግን የተሻለ ለሞከሩት እንሸልማለን

@getem
@getem
@paappii
ሰዓት አልቋል

#መልስ ቁጥር አንድ

ገጣሚ: ሰለሞን ሞገስ(ፋሲል)
የግጥሙ ርዕስ "ዳግማዊ አላዛር

@getem
@getem
@paappii
የጥያቄ ቁጥር አንድ መላሾች

1. @olan_yzo
2. @brook_m
3. @Henokbirhanu

አሸናፊዎቹ እነዚ ናቸው #ኮንግራ

በውስጥ መስመር አናግሩኝ @paappii

@getem
@getem
@getem
ጥያቄ ቁጥር #ሁለት 4:25 ጠብቁን ቀላል ጥያቄ በዛ ካለ ሽልማት ጋር

@getem
@getem
@getem
ሁለተኛ ጥያቄ እየመጣ ነው
ባንቺ የተነሳ
በእጥፍ ጨመረ የውበት ሚዛኑ፣
የፈኩት አበቦች አፍረው ተሸፈኑ፣
ዕንቡጦች ከምንጩ ደንግጠው መከኑ

ድሮስ!
ይሄ ሁሉ ውበት!
ለጨረቃ ሰግዶ ፣ ፀሃይን ተማፅኖ ለምኖ ሚፈካ፣
በምን ጉልበቱ ነው ካንቺ የሚለካካ?
እኮ በምን ጥበብ እኮ በምን ዘዴ
እንኳን የአበቦቹ፣
የፀሃይቱ ምንጭ አንቺ አይደለሽ እንዴ?
#ሁለተኛ ጥያቄ አሁን የለቀቅነው ግጥም፣ የገጣሚው ስምና የግጥሙስ ርዕስ ምንድነው ?

መልሱን ለመለሱ #5 መላሾች ለእያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት የመቶ ብር ትኬት እንሸልማለን

መልሳቹንም ከአሁን ጀምሮ @paappii በመላክ መወዳደር ትችላላቹ

መልካም እድል

@getem
@getem
@getem