ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
የዓለት ጥበብ
፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣

አያቴ ዓለቱን ፈልፍሎ ቤቱን፣
ሀውልቱን አነፀ
ይህም ከዘር ዘር ተላልፎ በደሜ ስላሰረፀ
እኔም የጥንቱን ያዝኩና ዓለት እፈለፍላለው
ሰዋራ ዋሻ ሰርቼ መንገደኞችን እዘርፋለው።

@getem
@getem
@paappii

#solomon moges
ትናንት አመም አርጎኝ
የራስ ምታት ይዞኝ
በአንዲት ቅጠል ብጤ ዳብሰሽው ግንባሬን፣
ሞት፣ ሞት ያሰኘኝን አጣሁት ህመሜን
እኔ ግን ያልገባኝ ነገረ ብሂሉ
በአንቺ ነው የዳንኩት ወይስ በቅጠሉ?

@getem
@getem
@paappii

#solomon moges
ጠላቴ
፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣

ጠላቴን ስፈልግ፣ ከጎሮቤቶቼ
ጠላቴን ስፈልግ፣ ከባልደረቦቼ
ጠላቴን ስፈልግ፣ ከሩቅ፣ ከቅርቦቼ
ለካስ ክፉ ጠላት ደመኛዬ ያለው
ከገዛ እኔነቴ ከራሴ ውስጥ ነው።

@getem
@getem
@paappii

#solomon moges
ኑሯችን
፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣

አበ መቃብር ቤት፣ በመቃብሩ ላይ
መንኩሰው ሲኖሩ ይገረማል የሚያይ
በቀን፣ በጨለማ ገፍተን ወዲያ ጥለን
ሌሎች መቃብር ላይ የቆምነው ስንት ነን??

@getem
@getem
@paappii

#solomon moges
Audio
ሽሽት

አሁን በቀደም ለት
መጣች ተቀበልኳት
አወጋች አመንኳት
ብዙ ብዙ አለችኝ
የትም ከርማ መታ
የሄደችበትን ምክንያት ነገረችኝ።

ትክክል ነሽ አልኳት
ባትሆንም ግድ የለኝ
ከመመለሷ እንጂ፣ ከመሄድ ምን አለኝ።

@getem
@getem
@paappii

#Solomon shiferaw
👍16🔥51