ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
(#ፋሲል_ስዩም )
...................
(እናት አለም ከወደዚህ)
በደም ቅብ ጌጥ ደምቃ፣
በሚስጢሯ ግምደት ከቁንጅና ረቃ፣
ከብናኝ አፈር ዑደት ርቃ፣
ባቋቋሟ ፀንታ፣
ብርሀን በፀነሰ
የጨለማ ንጥ ውጊያ ታግላ
በልቤ ፅላ ላይ...
በታሪክ ቅጥል-ጥሎሽ ሀረግ ግምጃ
ታትማ ተቀምጣ...፣
እስከ ዛሬ አለች...
(እኔ ከባሻገር)
ለምወዳት እንስት...ለጠዋቴ ጀምበር፣
ላልከዳት
ላልተዋት
ላፈቅራት
ምዬላት
በጡቷ እሽታ....
ፍቅሯን ስምገው፣ክንዷን ተንተርሻት፣
(በሕልም አለም ሳለሁ)
(በሙት ምሳል ጊዜ)
(ደምቄ በደሟ)
(በወዟ በወዜ)
አንዴ በፍጋግ ቅኝት
ደግሞ በትካዜ፣

ኩኩሉን ሳልሰማ...
ጭራፍ የብርሃን ምዛዥ
ከልፍኜ ሳይጠባ...
ድብዙዝ ገፄ ሳይጠራ
ጭላም ቤቴ ሳያበራ...
የኔ ገላ እንደጋለ...
የር'ሷም ገላ እንደቀላ፣
ጩኸት ሰማን የሚያስፈራ፣
አፈር ካ'ፈር ሲቀናና፡፡

(አሁን)

በ'ስር በግልቢያ የመጣው፣
የስሜቴ ፋኖስ፣
ባንዳፍታ ጨለመ፣
በእምባ እርግዛት፣
ዝናብ ላያመጣ፣
ሰማዬም ደመነ፣
በግን-ጥል-ጣይ ዘመን
እላፍ የታሪክ ገፅ፣
የአንድነት ማሰሪያ
ገመዱ ሲበጠስ፣
ያመኑት ሲከዳ፣
ተስፋ እንደጉም ሲበን
(ሲበተን)
የፍቅር ቃል ንዳዱ ሲዳፈን፣
የሀሰት መውደድ ቃል ሲሰፋ፣
ከግቷ የጠባሁትን ፍቅር ስተፋ፣
በስሜት እቅፋት...ውበቴን ሳጠፋ፣
(እቴ ከወደዚያ)
አይኗ በስለት ተኳለ፣
በኔ ግብር ትኩሳት ፊቷ ተቃጠለ፣
የ"ቅር-ፍቅር" ቅኔ...
የ"ቅር ፍቅር" ዜማ፣
ገና ሳይወለድ ፀንሳ አኑራው፣
ሽል ሆኖ በሞተው ልጇ ተዘመረ፡፡
(አንድም ተፈፀመ፣)
(አንድም ተጀመረ፣)
...///....
04;04:2011
ዲላ

@getem
@getem
@lula_al_greeko
(#ፋሲል_ስዩም )
.........በድምፅ..........
(እናት አለም ከወደዚህ)



@getem
@getem
@getem
ቄሳር አፈረሰ !!!!!


የቄሳር ለቄሳር ፤
የእግዚሃርን ለእግዜር ፤
ነበር ኪዳናችን ፤
ቄሳር አፈረሰ ፤
ይኸው ቃሉን በላ ፤
ልቀድስ እያለ ገባ መቅደሳችን ፤
ካህን ባገር ጠፍቶ ፤
ፍቱን ፍቱን ማለት ሆኗል ጸሎታችን ።

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

ሸጋ ጁምኣ!💚

@balmbaras
@getem
@getem
😁1
እግዜሩ ፍፁም ነው!
ሰው የግዜር ስራ ነው።
የሰው ልጅ አመሉ ÷ ከጌታው ቃል መውጣት
የፈጣሪም ፍርዱ ÷ ሰውን በሞት መቅጣት።
.
.
ሞት መቀጫ ሲሆን
ፍፁም የተባለው÷ እግዜር አጎደለ
አንድም መሳሳትን
ሁለትም መሞትን÷ ለሰዎች አደለ።

ታመው፣ ታመው፣ ታመው
ደክመው፣ ደክመው፣ ደክመው
ሽማግሌው ሞቱ ÷ (ወይስ አረፉ እንበል?)
በቅርብና በሩቅ
ይለያያል መሰል ÷ የሞት አቀባበል።

የሚያውቁት ሰው ቢሞት
ያለቅሳል ቀባሪ ÷ ውሎ ተሰብስቦ
ለማያውቁት ሞት ግን
እንባ መራጨቱ ÷ አይን ምን አስቦ?
ከሞት ተፈጥሮ ነው?
የመተላለፉ÷ እንባ እንደ ተስቦ?
.
.
መቃብር ቆፋሪው
ሞተና ቆፍረን ÷ አፈር አለበስነው
ሳጥን ሻጩም ሞተ
አስከሬን ገናዡ ÷ በሳጥን ከደነው።
ገናዡ ሲገነዝ
ፍትሃት የቆሙት ÷ ተጋድመው ተፈቱ
አልቃሽ አስለቃሾች
ተራ እስኪደርሳቸው ÷ ደረት የሚመቱ።

ህይወት በምን ያምራል?
ህፃን ፈገግ ቢል ÷ ያየው ፈገግ ይላል
ከእንባና ከሳቅ
ለማስተላለፉ ÷ የትኛው ይቀላል?
ሞት ለምትናፍቅ ልብ
መኖር በቃኝ ላለች ÷ ምላ ተገዝታ
አስሮ ለማሰንበት
አቅም ያለው ማነው ÷ ተስፋ ነው ትዝታ?

@getem
@getem
@paappii

#Haileleul Aph
ጤና ይስጥልኝ 🙏 ሚኪያስ ልየው እባላለሁ (Street photographer ) ነኝ ። አዲስ አበባን እና ማህበረሰብዋን እጄ ላይ በሚገኘው የሞባይል ቀፎ ፎቶግራፍ እያነሳሁ ለማስተዋወቅ እሞክራለሁ። ቻናሌን ተቀላቅላቹ ስራዎቼን እንድትመለከቱ እጋብዛችኋለሁ።
@Mykeyonthestreet
@Mykeyonthestreet
@Mykeyonthestreet
@Mykeyonthestreet
ከዳርቻው ሳንደርስ!!!!!!!!


ቀኑ እየረዘመ ፤
ጎጆ እየዘመመ፤
ቃል እየታመመ ነውና ሁኖ እንጅ መረሳሳታችን ፤
የተማማልንበት ፤
እስከዳር ዳርቻ ነበር ትንፋሻችን፤
እስከ ያሬድ ድጓ እስከ ፑሽኪን ቅኔ ነበር ምህላችን፤
ምነው ከመሃል ላይ እንደ ፈሪ ዘማች ቆሟል መንገዳችን???
ያንን መንቻካ እድሜ ፤
ያንን ግራዋ ቀን ፤
በፊደል ቀረርቶ ፤በሆሄ ሽለላ አልፈን ስናበቃ፤
ምነው ዳር ሳንደርስ ፤
መሃል ላይ ጋረደን የርእያችን አዚም የህልማችን ሲቃ፤??
ምን እስከዳር ቢሆን እስከ አድማስ ቢሰግር የገጣሚ ህልሙ፤
ምን ሩቅ ቢሆንም የልቡናው ቁና የምናብ አለሙ፤
መሄድ ያማረው ቀን ፤
ይበቃኛል ብሎ ከመሃል መንገድ ላይ ይጎድላል ቀለሙ ።
በዚች የቅኔ አገር ፤
ምስኪን ባለቅኔ ፍታት እያጠኑት ቢሄድ ወደአፈሩ በአልጋ በወሳንሳ ፤
መች ይረሳል ከቶ አሁንም አሁንም በጣፈው ቅኔ ስር ስሙ እየተነሳ ።
ኑሮ እያስገጠመው፤
ንጉስ እያገመው፤
ሽፍታ እየገጠመው፤
እየተጋጠመ ፤
ደግሞ እየገጠመ፤
በሚኖር ሃበሻ ፤
ስምህ እንደ ቋጥኝ እንዲያስከነዳቸው ደርሰው ሲሸከሙት፤
ከኑሮአቸው መሃል፤
ቅኔና ህልምህን ፤
በዘፈን ሙሿቸው ሰም ወርቅ እያበጁ እየዘራረፉ ቃልህን እንዲሰሙት፤
እንደ ባልቻ ሰፎ፤
ወይ እንደ ፀጋየ፤
ወይ በጦር ወይ በቃል ገጣሚ ሁነህ ሙት !!!

(( ጃ ኖ ))

ነብስሽን በገነት ያኑረው እህቴ

@getem
@getem
@balmbaras
Audio
ግጥም ፦ እንዳለጌታ ከበደ
አቅራቢ ፦ መብረቁ ጥቁር ሰው (መባ)
@getem
@getem
@Bookfor
# አብዮታዊ # ፍቅር
የሥራ እግር ጥሎኝ — ወረዳ ተዋውቀን
ስለምድሽ ስትለምጂኝ — አለፍን ብዙ ቀን
* * *
የምግባር ወሰንሽ — ከድንበርሽ ላቀ
ወረዳ ጀምሮ — ከዞንም ተለቀ
* * *
ገዝፌያለሁ ብለሽ — ክልል ባትጠይቂም
ካልተሰጠኝ ብለሽ — አመፅን ባታውቂም
ለጎጆአችን አድባር _ ለአብሮነት ከራማ
ለመውደድ አጀንዳ _ ለፍቅር አላማ
ክልል አድርጎሻል _ የልቤ ፓርላማ
* * *
ፓርላማ አስወስኜ — ግዛትሽን ተመኘሁ
ለአፈፃፀም ብዬ — አልጋሽ ላይ ተገኘሁ
ከአልጋሽ ተነስቼ — ወራት እንደቆየሁ
ቀን ቀንን ሲገፋ—ሆድሽ ላይ ለውጥ አየሁ
* * *
የፍቅራች‘ን አብዮት — ስር ስላሰደድኩት
እውነቴን ነው ምልሽ—ለውጥሽን ወደድኩት
* * *
ለካስ ለንጋት ነው — አልኩኝ መደንገዜ
ካንቺ ጋር ብሩህ ነው — ውዴ መጪው ጊዜ
* * *
አንቺ የልቤ ክልል — አንቺ የልቤ ግዛት
ሽማግሌ ልኬ — ነገር ከማንዛዛት
ለውጡ ሳይጠነክር — በበረታው ክንዴ
ዛሬ ነገ ሳልል — ልገንጥልሽ እንዴ?
* * * * *

@getem
@getem
@paappii

ከሙሉቀን.ሰ
የቆመውን ሁሉ
ያለፈውን ሁሉ፤
የኔ የኔ ማለት፤
ያሳጣል ልቡና ያስረሳል ቀለበት ።
በእነንትና መንደር፤
አንዱን ድስት ድጠው፤ አንዱን ሲወዝቱ፤
እንኳንስ ሊያገቡ ፤ሳያጩ ተፋቱ ።

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!

@getem
@getem
@balmbaras
ለቅዳሚታችን አንድ ግጥም ብንጨምር ማን ከልካይ አለን? ማንም!!! ቅዳሜም አይደል!

መሃል አዲስአባ፤
በላምባዲና አይኗ ፤
በትርንጎ ባቷ፤ ገምሸርሸር እያለች ፤
ኮለምላማየዋ፤
አራት ኪሎ ሄዳ፤ አራት ሰው ገደለች፤
አዳሪ ሙናዋ፤
አምስት ኪሎ ሂዳ፤ አምስት ሰው ገድላለች፤
የምወድሽዋ፤
ስድስት ኪሎ ሄዳ፤ ስድስት ሰው ገድላለች፤
ደሴ ብትመጣ፤
ገምሻራየዋየ በሸጋ ተስማ እሷው ትሞታለች ።
ያችን አይነ ኩሌ ሰው አትግደይ ብለው እንዴት ይነግሯታል፤
እሷ መንገደኛ ሰዎቹም ያይዋታል፤
እንዳሻት ትውረግረግ አቦ ያምርባታል፤
ምን አስጨነቃችሁ፤
ሸጋ የገደለ እሱም በሸጋ አገር በሸጋ ይሞታል።

((( ጃ ኖ ))💚💛❤️

@getem
@getem
@balmbaras
1
#እህህህ ~ስለኔ!!!

ትዝታ ክፉ ነው
ለሰባራ ልቦች የማይራራ ከቶ
ይኸው በሰቀቀን
ያንከራትተኛል ውስጤን አደህይቶ፡፡
ግን አልደነቅም
ድሮስ ባንቺ ሚዛን ሴትነት ለክቼ
እንዴት ይቻለኛል
ነገዬን መናፈቅ ትላንትናን ትቼ?
አልችልም አለሜ
የምትመጣው ሁሉ ውስጤን ሳትረዳ
በማንነት ስሌት
ከ'ምነት ልትጣረስ ከዙፋኔ ወረዳ
ሰባራውን ልቤን
እንኳንስ ልጠግን ልታክመው ዳብሳ
ትርፏ ሰቀቀን ነው
በለምን ምክንያት ምትዳርግ ላበሳ፡፡
ለዛ ነው ትዝታሽ
ሰርክ እየታወሰ ኑሮዬን ሚቀማኝ
አረሳሁሽ ብዬ
ባወራሁኝ ማግስት ናፍቆት የሚሰማኝ፡፡
እሺ በምን ልዳን?
ከዘመን ልክፍቴ ጩሆ ከማይወጣው
ውስጤን ሳይረዱት
በቀለኛ እያሉኝ በፀፀት ገረጣው፡፡
እኔኮ ጥሎብኝ
እንኳንስ ልበቀል ልስቅ በሴት እንባ
አመታት አልፈዋል
ለሰባራ ልቤ ነፍሴ ሰው ተርባ፡፡
ታዲያ እንዴት ሆኖ
መሰበርን ያየ ሌላውን ይሰብራል
ድሮም ታውቂው የለ
ልቤ እኮ ደግ ነው
እርሱ ጨልሞበት ለሰዎች ያበራል፡

ብቻ ግን ግድየለም
አንቺን አስረስታ
የምታሸንፈኝ እንስት እስክትመጣ
ለሌላው ቢመስልም
በቀል የለም ልቤ ሴትን የሚቀጣ፡፡


((ልብ አልባው ገጣሚ))
@getem
@getem
@gebriel_19
👍2
🇪🇹🇪🇹🇪ዘጠነኛው የብርሃን ዕለት የመጀመሪያው ማክሠኞ ነሀሴ 7። ይምጡና አብዝተው ያትርፉ እንድቅትዮን በ አዲስ አበባ ትያትር እና ባህል አዳራሽ(ፒያሳ) ።
ልዩ እና እውቅ የጥበብ ሰዎች ግጥም እና ወግ በባህላዊ ሙዚቃ ታጅበው ያቀርባሉ።

እማይቀርበት ልዩ የጥበብ ምሽት!


@getem
@wegoch
@tebeb_mereja
።።።።።።የጠጉር ንቅሳት ።።።።።።
(በብርሃን_ዘኢትዮጵያ)

በእውቀቴ በእድሜዬ ብዛት ብመለጥም
ከጋሜነቴ ግን ዘበት ነው አይልቅም
እድሜ እየተጓዘ ግርማን ቢያላብስም
ከልጅነት ጥበብ ፈጥሞ አይደርስም።

በዘመን ካደፈ የወርቅ ጉልላት
የአልማዝ የዕንቁ ካባ
ይበልጣል ልጅነት በመዳብ ያለው ፈርጥ
የማያውቀው ደባ
በጥቂት ተይዞ በአእላፍ የተጣለው
በደግነት አክሊል ተሸልሞ የቆመው
የእውቀት ሁሉ ጥግ ልጅነት ጥበብ ነው።

በጊዜ መሠውር አድጎና ጎልምሶ
የልቡን እሳቤ መርዞ በኮሶ
በእንጭጭነቱ አደኩ ከሚል ደርሶ
የእድሜን ርዝማኔ ከንቱ ያልከወነበት
ማወቅን በትኖ ማግኘት ከማካበት
ካመዳም ምልጥና ይወዛል ልጅነት ።

አበቅቴ ቢያከማች መጥቅዕ ቢደረደር
እንቶፈንቶ ደርቶ ከከረመ አፈር
ከትዕቢት ርምጃ የትሑታን ስንዝር
የሰው ማንነቱ
ከባሕረ ሃሳብ የሚለይበቱ
ዘመንን ከመቁጠር ኖሮበት መሥራት ነው ምስጢሩ ርቀቱ
ምግባረ ቢስ ሆኖ በእድሜ ከመሸበት
ቅንነት የሞላው ክቡርነት ነው ኩተት።

@Berhan_zETHIOPIA
ሰኔ ፳፻፲፩


@getem
@getem
@getem
Qur'ann 75:4
Yes,We are able to put together in perfect order the very tips of his
fingers.

Masha Allah.


አይደለም ጣቶቹን (ፊት እንደነበሩ )
በማስተካከል ላይ ቻዮች ስንኾን
(እንሰበስባቸዋለን)

ሱረቱል አል ቂያማህ ቁጥር 4


ለበይክ አሏሁመ ለበይክ
ለበይከ-ላሸሪከለከ-ለበይክ
ኢነል ሃምደ-
ወኒዕመተ
ለከረል ሙልክ-
ላ ሸሪከ-ለክ!!
-
አረፋ የመስዋዕትነት፣ የመታዘዝና የምህረት በዓል ነው።
ሁሉም ነገር በቦታውና በጊዜው ያምራል።
ለእስልምና እምነት ተከታዮች ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንኳን ለአረፋ በዓል አደረሳችሁ ❤️❤️❤️

@getem
@getem
@balmbaras
ዮዲት መኮንን(ናኒ)

(አይነጋልሽም ወይ)
ሌሊትሽ ረዝሞ ንጋትሽን ሳናይ
በይነጋል ተስፋ ሰማይ ሰማይ ስናይ
ሊነጋ ሲል ይጨልማል እያልን ስንተርት
ወራቶች አልፈውን ስንጠብቅ አመታት

ይኸው እኛም አለን አንቺም እንደጨለምሽ
እንኳንስ ሊነጋ ጠፍተው ክዋክብትሽ
ኩራዝ የሚያበራ ጠፍቶ ከልጆችሽ
ወጠ ሰሪ ሳይሆን አማሳይ በዝቶብሽ
ይኸው እኛም አለን አንቺም እንደጨለምሽ

የቃል ኪዳን ሀገር መሆንሽ ተረስቶን
እኔ እኔ ስንል እኛ ማለት ትተን
አንድ ማዕድ ላይ መቅረቡ ተስኖን
ይኸው ዛሬም አለን እንደተበታተን

ወንዙ ሳይደርቅብን እህሉ ሳይጠፋን
በረሀብ አልቀናል
በጥማት ደርቀናል
ቀድቶ የመጠጣት ብልሀቱ እየጠፋን

ይኸው እኛም አለን አንድ መሆን አቅቶን
የአቤል እና ቃዬል ታሪክ እየደገምን
ወንድም በወንድሙ መሳሪያ እያነሳ
ልጅም በአ'ባቱ ላይ ሽቅብ እየተነሳ
አለን እንላለን
ሀገሬ እጆቿን ለግዜር እስክታነሳ

አለን እንላለን ባምላክ ላይ ተማምነን
ነገ አዲስ ቀን ነው የሚል ተ ፋ ይዘን
ሊነጋ ሲል ይጨልማል የሚል ቅኔ ዘርፈን
ሰምና ወርቅ ስንል ዘመን እያስቆጠርን

ይኸው እኛም አለን አንቺም እንደጨለምሽ
እንደጨለመብን እንደጨለመብሽ

@getem
@getem
@gebriel_19