ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
።።።። ዋ! ።።።።
(በረከት በላይነህ)

አይኔ ወደደሽ ስልሽ፣
አይኑን አጥፋው ብለሽ ገባሽ አሉ ስለት
ምኞትሽ ሰመረ
አይኖቼ ጠፉልሽ ይኸው አንደዘበት።

ግን መች ተውሻለው
በልቤ ብሩህ አይን ዛሬም አይሻለው።

ደሞ አንደዚ ስልሽ አትወጅኝምና
ልቡንም አጥፋልኝ ብለሽ ትሳይና
ፀሎት ያልቅብሻል እሞትብሽና።



@lula_al_greeko
@getem
@getem
ቆሎነት እና ብልሐት
(ልዑል ሀይሌ)

ቆሎ ነው ጥሬ ነው የአንዳንድ ሰው እውነት፤
ቆርጣሚን መማጠን የተዘገኑ ዕለት፤
ዘጋኝ እጅ ከገቡ ምን ምን ሊያ'ረግ መማጠን፤
ፈጣሪ ሆይ ስማን
ከመዘገን በፊት
ከሰፌድ ማምለጫ አንዳች ብልሐት ስጠን፤
፬-፰-፳፻፲፩ ዓ.ም.

@getem
@getem
@gebriel_19
የፈረሶዎቹን ጋጣ

ለአህያዎች አትስጡ

ኤፍሬም ስዩም የአንድ አባት በኦሮምኛ የተቀኙትን ቅኔ ተርጉሞ ካቀረበው የተቀነጨበች ነች!

ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም " ጥበብ አዲስ " በሚል ርዕስ
ዛሬ በጀመረው የጥበብ ምሸት አስገራሚ አሳቦች እና
ቅኔዎች ተዘረፈዋል አበበ ባልቻ ከዚህ በፊት ተሰምተው የማያውቁ የሎሬት ፀጋዬን ግጥሞች በሚያምር ለዛ አቅርቦታል ፣ ደምሰው መርሻ መድረኩን ከሚያምር ግጥም ጋር ተገማሽሮበታል ፣ ሰለሞን ሳህለ እንደዛው ፣ ምዕልቲ ኪሮስ ፈገግ አለ እሱ በሚል ቅኔ አዘል ግጥሟ ፈገግ አስደርጋናለች ፣ ዛሬ ከቀረቡት ግን ለኔ የመድረኩ ከባድ ሚዛን የነበረው የመጀመሪያው የመድረክ "ትዝብት አዲስን" ( ስለ ቋንቋችን ውድቀት) ያቀረበው ጥላሁን ለኔ የዛሬው ምርጥ ነበር!!👑👑👑

በቀጣይም ዘወትር አርብ ማለትም
ወር በገባ የመጀመሪያ አርብ ኤፍሬም በአዳዲስ አሳቦች
ይመጣል ማለት ነው
በዛሬው የግጥም ምሽት ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬም ነበሩ ለሁለቱም የሚሆን ምክር ቢጤ የግጥም ስንኝ እንካቹ ተብለዋል


የመጣቹ ተደስታቹ አትርፋቹ እንደሄዳቹ ተስፋ አደርጋለሁ !!

የወር ሰው ይበለን !!!❤️ሰላም እደሩልኝ!!

@getem
@balmbaras
ሳይፈለግ በቅሎ

ትከል ያንን ችግኝ
ንቀል ያንን ኩፍኝ
የሀገሬን ነቀርሳ
ቅበረው ያን ሬሳ
ጎጠኛውን አውድም
ዛፉን ግን አለምልም
ይሰጠሀል ሠላም
ሸንጎ መዋያ ነው
ለእርቅህ ትከለው
ጥላቻን ግደለው
ፍቅርህን አብቅለው
ይቃጠል ያ ጓሳ
ሳይፈለግ በቅሎ አሳየን አበሳ።

ከንጉስ አማኑኤል ብርሃኑ

@getem
@getem
👍1
መሀል ሸዋ ላይ ዛሬ ራስ ሆቴል እንገናኝና የሸዋን ቀበሌ መረባ
እንበልበት! !!!

በየወሩ የሚካሄደው ጦቢያ ግጥምን በጃዝ ምሽት

ከቀኑ 11 :00 ሰዓት ጀምሮ

እንደተለመደው በራስ ሆቴል ይካሄዳል።

#መግቢያ 100

ኑና አብረን መረባ እንበል!

መረባ አትይም ወይ ፤
ከምትወዘወዥ እንዳበደ ጥጃ ፤
መረባ አይደለም ወይ ፤
ጀምበር ሳይዘቀዝቅ የሚያወጣው ሃጃ ።


እንጃ! !!!

(( ጃ ኖ )))💚💛❤️


@balmbaras
ጥሬ ጨው!
መስለውኝ ነበረ፣
የበቁ፣ የነቁ፣
ያወቁ የረቀቁ፤
የሰው ፍጡሮች፣
ለካስ እነሱ ናቸው፣
ጥሬ ጨው፣ ጥሬ ጨው፣
ጥሬ ጨዋዎች፣
መፈጨት መሰለቅ፣
መደለዝ መወቀጥ፣
መታሸት መቀየጥ፣
ገና የሚቀራቸው፣
“እኔ የለሁበትም!”
ዘወትር ቋንቋቸው፡፡
(ደበበ ሠይፉ)

@getem
@getem
@paappii
(( አክባሪ አልባ ልደት)))

ዛሬ በውዱ'ዓ እለት ፣ በተወለድኩባት
የዚን አለም ኑሮ ፣ ልቃኝ ይሂን ህይወት
አሀዱ ባልኩባት ፣ በዚች ቀን ምክንያት
ሂሳቡ በእኔ ነው ፤ ጠጡ ባላቹበት
ኬኩን ተደፋፉ ፣ ወይኑን ተራጩበት
አቅማቹ እስከቻለ ፣ ልደቴን አክብሩት
እኔን ግን አትጥሩኝ ፣ ከቤት ልዋልበት
በእኔ እንዲጀመር ፣ አክባሪ አልባ ልደት
1/12/2011 sz
🎂🎂🎂
ዛሬ ልደቴ ነው ሁልሽም ይሂን ግጥም ያነበብሽ ሁላ አንብቦ ዝም የለምና መልካም ምኞት ተመኙልኝ 👉 @samized7

@getem
@getem
@getem
2
አለማምጂኝ(ልዑል ሀይሌ)
.
(አለማምጂኝ!!)
.
በጨበጥኩት ብዕር
ውበትሽን ልገልጠው ቃላት ባማርጥም፤
ቤት መምቻ ቸግሮኝ
አጥር ላይ ቆሚያለሁ ስላንቺ ሳልገጥም፤
.
(አለማምጂኝ!!)
.
ወይ አልገጠምኩልሽ
ቤቱን እየመታሁ፤
ወይ አልተመለስኩኝ
ቅኔዋን ውበቴን አንቺን እየፈታሁ፤
ልፈታሽ ብጥርም
ማሠሪያሽ ቸገረ፤
ቀን በቀን እያደር
ውበትሽ ጨመረ፤
.
እንዴት ላ'ርገው?..
.
(አለማምጂኝ!!)
.
.
እስቲ ነይ ወደኔ
ውብ ገላሽን አምጪው፤
የማይገጥም ጣቴን
ብዕር አስጨብጪው፤
ቅኔሽን ስፈታ አግዢኝ ነይ ፍቺ፤
አጥሩ ላይ ስደርስ
ደርሰሽ ቤቱን ምቺ፤
ተባብረን እንፃፈው
በልብ የታመቀ ያልተፃፈ እውነት፤
ይህ ነው ግጥም ማለት፤

.
(ግን አለማምጂኝ...)
፳፱-፲፩-፳፻፲፩ ዓ.ም.

@getem
@getem
@gebriel_19
👍3
​የአባው ውብ ብሂል
ከችግር አላቆ መፍትሄን ቢጠራም
እሾህን በእሾህ ለችግር አይሰራም።

እናም

መንገዱን ለውጦ 
ሌላ ሀሳብ ለማዝመር
ልብህ ካልቆረጠ ከሆነ ስስታም
በችግር አምጪ ሀሳብ፣
ችግሩ አይፈታም።

@getem
@getem
@paappii

#ድራእዝ( ዶ/ር አብይ አህመድ) ከእርካብና መንበር
🇪🇹🇪🇹🇪ዘጠነኛው የብርሃን ዕለት የመጀመሪያው ማክሠኞ ነሀሴ 7። ይምጡና አብዝተው ያትርፉ እንድቅትዮን በ አዲስ አበባ ትያትር እና ባህል አዳራሽ(ፒያሳ) ።
ልዩ እና እውቅ የጥበብ ሰዎች ግጥም እና ወግ በባህላዊ ሙዚቃ ታጅበው ያቀርባሉ።

እማይቀርበት ልዩ የጥበብ ምሽት!


@getem
@wegoch
@tebeb_mereja
አንዳንዴ በጥዋት ሀሳቦች ብልጭ ይሉና ያጋጠሙህን ወይ በሰው ላይ የደረሱትን
በማሰላሰል ትጠመዳለህ በመሀል "ነገሩ ገብቶኛል " የሚለው ግጥም ከሀሳብ ጋር
ተገጣጠመ የግጥሙም ሀሳብ ይወዳታል ግን አኩርፏታል እሷን ትቷት ውጭ አደረ
እስከትመጣ አላስቻለውም በማለዳ ሩጦ ቤቷ ሄደ ካዛ በኋላ ያለውን ከግጥሙ እናገኛለን


……
ነገሩ ገብቶኛል
ጠዋት ቤትሽ መጣሁ
አንቺ ግን የለሽም፤ በተስኪያን ሄደሻል::
ያዉ፤ የገላገልሽዉ
የጉደሩ ጠርሙስ ባዶዉን ተኝቷል::
ስትንፈራገጪ ድንገት የረገጥሺዉ
ብርጭቆ ተሰብሮ፣ ወለሉን ሞልቶታል::
ብርድልብስሽ የለም -
እንደአድፋጭ - ዉሽማ፣ አልጋሽ ሥር መሽጓል::
አንሶላሽ ከፍቶታል -
በሌሊቱ አበሳ ሽንሽን ቀሚስ መስሏል::
ግድየለሽም ፍቅሬ ነገሩ ገብቶኛል
በህልምሽ ከኔ ጋር፣ ተቃቅፈሽ አድረሻል::
እኔ አኩርፌሽ ብዬ፣ ጅሉ ልቤ ወልቋል::



አይ የልብሽ ጉዱ !
ዕምነትን መሻሩ፣ ልማድን መካዱ
ለብቻ እንዳደረ፣ ደሞ እንደጨዋ ልብ፣ በተስክያን መሄዱ::
አይ የልብሽ ጉዱ !


ስዉር-ስፌት ነብይ መኮንን

ለመረዳት ሞክሩና የተሰማችሁን ለመግለፅ ሞክሩ እስኪ

እግረመንገዳቹን ደግሞ አንድ ጠዋት ነሸጥ ሲያደርገኝ እያዜምኩኝ የሞከርኩትን ተጋበዙልኝ

ሸጋ ቀን!💚

@getem
@getem
@balmbaras
👍1
*በድጋሜ የቀረበ*

////ጎዳናው ይገርማል////
#በረከት_በላይነህ

ይገርማል መንገዱ
እግረኛው ይገርማል

ሸራ ጫማ ባ'ይነት
በነጫጭ ካልሲ
በሲኪኒ ሱሪ
ከመምህሩ ጋራ
አይስክሬም ሚልስ
የሀይስኩል ተማሪ
.
ፀባይኛ ወጣት
ጃንቦ ተከልሎ
በምርቃና ሆኖ
ሀሳብ የሚፈትል
አንዲት ሙ......ደኛ እናት
በ'ድሜ ከልጆቼ አንሳለው የምትል
ፒዛውን የሚገምጥ
ጭማቂ የሚመጥ
አራዳ አባወራ
በሚስቱ ትከሻ
በልጆቹ ምላስ
ቅምጥ የሚጣራ
.
አንድ ፍሬ ሴቶች
በተገዛ ቅንድብ
በተገዛ ፀጉር በተገዛ ጥፍር
በውሰት ወዘና የተብለጨለጩ
ማኪያቶ ከበው
ለውስኪ ሚንጫጩ
ጅናም ጅንሳም ወንዶች በሴቶች ጫጫታ የሚቁለጨለጩ
.
ይገርማል ጎዳናው ይገርማል መንገዱ....
.
ድንቡሽቡሽ ህፃናት
በቶም ኤንድ ጄሪ ሱስ
ቀልባቸው የከሳ
በአይፎኑ አጮልቆ
ያንጀሊናን ከንፈር የሚስም ጎረምሳ
.
ቀውጢ ዳያስፖራ
.
የሎቲው የቁምጣው የቲሸርቱ ጥለት የተንዘረፈፈው
አማርኛ ሲሸሽ "what's happen" የጠለፈው
.
ነቄ ብላቴና
.
ከዮፍታዬ ቀዬ
ካ'ዲስ አለማየሁ
ከመዝገቡ መንደር
የአዲስ አ'ባ ጥሪ
በቁምጣ ያበረረው
ከቅኔ ተጣልቶ
ከግዕዝ ተኳርፎ ሎተሪ ሚያዞረው
.
ፀዴ ብላቴና
.
ከባላገር ዘመን
ከጨለማ ዘመን
ወደ ብርሃን ጥግ ተሸጋገርኩ ብሎ
በሸንኮራ ምርኩዝ ከተማ ሚያካልል መቋሚያውን ጥሎ
ነብሱ እየሰለለች
በከተሜነት ወግ ባ'ራዳነት ልምሻ
ሲያዘግም የሚውል
ሊስትሮውን ጭኖ በታቦት ትከሻ
.
ፎቆቹ
.
በመስታወት ቁመት በቆርቆሮ ገፆች
ባ'ልሙኒየም ጥራዝ የተብረቀረቁ
የጌቶቻቸውን እድሜ ሚያሳብቁ
ሁሉም........ ሁሉም......ሁሉም ጥግ ናቸው
ለወደቀ ወገን ይራራል ልባቸው
.
ሁሉም
...... ሁሉም
.
ከዘለለት ጥድፊያ
ከሰርክ ውጣ ውረድ በተረፈች አንጀት
ለወደቀ ወገን ምርኩዝ ማበጃጀት
ሁሉም...... ሁሉም ይችላሉ
ስለ'ግዚአር ላለ ይመፀውታሉ
.
እኔ ግን........ እኔ ግን .........ቆጥራለው
የ'ድሜ ክቡር ጀንበር
በጎዳና ፅልመት ሲዋጥ አስተውላለው
ጡረታ መንገድ ዳር ሲከፈን አያለው
.
ቆጥራለው.....ቆጥራለው
.
ቆጥራለው አዛውንት
በየአቀበቱ በየቁልቁለቱ
ማረፊያ ፍለጋ የሚንከራተቱ
ቆጥራለው አዛውንት ከልጆቻቸው ፊት
የልመና መዝገብ የገለጡ አሮጊት
ቆጥራለው በየመንገዱ ዳር
እርጅና ሙሽራው ለምፅዋት ሲዳር
ቆጥራለው በየሸንተረሩ በየተፋሰሱ
አቀርቅሮ ሲያዘግም እርጅና ሞገሱ
ቆጥራለው በ'ያደባባዩ
የሽማግሌ አይኖች የልጅ ፊት እያዩ
ቆጥራለው በየሰርጣሰርጡ
በልመና ጉልበት ከሞት ሲፋጠጡ
የ'ርጅና መዳፎች እሾህ ሲጨብጡ
.
ቆጥሬ..... ቆጥሬ.......ቆጥሬ
በለማኝ አዛውንት ብዛት ተሳክሬ
የማሰንበቻ ስንቅ ከኪሴ ቆንጥሬ
ያፅድቆቴን ዋጋ በሳንቲም መንዝሬ
ባ'ዛውንት ምርቃት ከሀገር ከቀዬው ትርፌን ሳመሳስል
በጎዳናው ቀለም ፃድቅ መልኬን ስስል
ጎልቶ ሚታየኝ ግን የሚያሳፍር ምስል
በቀላል ጥያቄ የነተበ ምስል
.
ጥያቄ
.
የዲጄ ኳኳታ የደናሽ ጋጋታ
የድራፍት እርካታ ያ'ረቄ ድንፋታ
ባጣበበው መንገድ
እንደምን ይቻካል
ላ'ያት ሳንቲም ሰጥቶ በ'ርካታ መራመድ?
.
ለወጣት ሹክሹክታ ለገደል ዝምታ
ላስመሳይ ጫጫታ ላድርባይ እሪታ
በተሰራ መንገድ
እውነት ቀላል ነው ወይ
ላ'ያት ሳንቲም ሰቶ በ'ርካታ መራመድ?
.
ለቡቲክ ሰልፈኛ ለካፌ 'ድምተኛ
ለውስኪ ጭሰኛ ለበርገር ምርኮኛ
በተሰራ መንገድ
እንደምን ይቻላል
ላ'ያት ሳንቲም ሰቶ በ'ርካታ መራመድ?
.
አያት....አያት...አያትነት ማለት
በደማቅ አሻራ የሸመኑት ጥለት
ለተራኪ እድሜ የተሰጠ አንደበት
ባ'ባት በ'ናት ፅናት የማይደክም ጉልበት
በልጅ ልጅ መነፅር የማያረጅ ውበት
በልጅ ልጆች ጥበብ የሚታደስ እውቀት
.....................................የሚታደስ እውነት
አያት ሆኑ ማለት
ድርብ አባትነት
ድርብ እናትነት
.
በተለይ እዚህማ.......
በዚህች አይነት ሀገር
ጎጆዋን ላቆመች
በተጋድሎ ካስማ
ባርበኝነት ማገር
በዚህች አይነት ሀገር
ጥያቄና መልሷን
ባ'ዛን በቅዳሴ በምትሰራ መንደር
በዱአ በፀሎት
በምናኔ ምርኩዝ በከረመች ሰፈር
የአያትነት ዋጋው በልኩ ቢሰፈር
ለሳንቲም ምርቃት ባልተሻማን ነበር!
.
ታሪክ በመዳፉ ስላደላደለው
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ንጉስ አያት አለው
የልጅ ልጆች ስባት ባያመነምነው
ያያቶቻችን መልክ ሁሌም አንድ አይነት ነው
.
እላለው... እላለው....
.
የልጆች ምፅዋት ያ'ያቶች ልመና
ያ'ባቶች ግርግር በሞላው ጎዳና
መንገዱ አይልቅም
ጎዳናው አያልቅም
ይሰፋል ይረዝማል ይሄዳል ይጓዛል
እግረኛው ሞኝ ነው
ሳንቲሙን ዘርዝሮ
ከወደቁ አዛውንት ምርቃት ይገዛል
.
መንገዱ ያስፈራል
መንገዱ ይጨንቃል
ልጆች ሳቅ ሲያንቃቸው
አያት እምባ ይጨምቃል
መንገዱ ያሰጋል መንገዱ ያረጃል
ከዘናጭ ልጆች ጎን እርዛት ያዘለ አያት ይወለዳል
.
ሰጪ ካለቀሰ ተበዳሪ ስቆ
ጌታ ከለመነ አማኙ 'ግር ወድቆ
ልዑል ከዘመረ ንጉሱ ተዋርዶ
ገፁ ተመሳቅሎ ሽፋኑ ካማረ
ወለሉ ተንቆ ምንጣፍ ከከበረ
ባ'ገርኛ ስሌት ማነው ያልከሰረ?
.
እላለው........እላለው
.
ከየጎዳናው ገፅ ጥያቄ አነሳለው
ጥያቄ እጥላለው
እርጅና ለማምሻው ጎዳናን ካመነ
አያት ከልጅ ልጁ ሳንቲም ከለመነ
ባገርኛ ስሌት ማነው ያልመከነ?
.
በ'ግዚኦታ ዘመን በምዕላ ዘመን
እመንገድ ዳር ወድቆ ትራፊ መለመን
በጥሞና ዘመን የሚያስቡት ማጣት
በማውረሻ እድሜ የሚሰጡት ማጣት
በማልበሻ ዘመን በ'ርዛት መቀጣት
በለጋሽነት ወቅት በማጉረሻ ዘመን
በጥማት መገረፍ በርሀብ መመንመን
ከሆነ እጣችን
ይጠየቅ ትርጉሙ የልጅነታችን
ይፈተሽ መንገዱ የልጅ ልጆቻችን

ግድ የለም እንመን

እንመን

በሰውኛ ስሌት ውጤቱ ሲሰራ
ትውልድ ያደኸያል ያያቶች ኪሳራ
በልጅ ልጆች ዓለም
እንደጉድ ቢደለቅ ቢዘመር ቢዘፈን
አባት ይወራጫል ባ'ያቶች መታፈን
.
አባት ሆይ
.
ለልጆችህ ርዕዮት
ትላንቱን የረሳ ተስፋ ሲደራረት
ህልሜ ነው ይልሀል ያ'ያቶቹ ቅዠት
ከልጅህ አንደበት
ቋንቋ እንደዶፍ ቢዘንብ
ትርጉም ቢንፎለፎል ሺ ቃላት ቢጎርፍም
የልጅ ልጅ አግባቢ ግማሽ ገፅ አይፅፍም
ከልጆችህ ባህር
አሳ የሚያጠግቡ ለአሳ ሚስማሙ
እፅዋት ተክሎች
እንደጉድ ቢራቡ እንደጉድ ቢያብቡ
ገበታው አይሞላም ተቀዷል መረቡ
.
ግድ የለም እንመን........እንመን
.
የስኬት ክብደቱ
የምቾት አይነቱ
የነገ ውበቱ ባሻው ቋት ቢለካ
በምንም ቢሰፈር ባሻው ቃል ቢነገር
ጀግና ልጅ አትወልድም
አያቶቿን ገድላ የምትሸልል ሀገር
.
ከፎቆቹ ጥላ....
ከያስፓልቱ ገላ ሲታተም ድምቀቴ
በመስታወት አጀብ ሲጠገን ጉልበቴ
ይኸው አነበብኩት
አያቶቼ ፊት ላይ ተፅፏል ሽንፈቴ
በመኪና ብዛት
በመስታወት አይነት ሲለካ ፍጥነቴ
በግንብ አጥር መአት
በፎቆች ጋጋታ ሲሰላ ስኬቴ
ይኸው ይታየኛል
አያቴ ገፅ ላይ ተስሏል ውድቀቴ
።።።።።።።።።።።።።ተስሏል ሽንፈቴ!

@getem
@getem
@lula_al_greeko
👍1
ለምሽታችን
💚💚💚

የቅኔ ምርቃት ከሩሚ
"You are not a drop in the ocean, You are the entire ocean in a drop."
Rumi
"ጠብታ አይደለህም
ባህር ውስጥ የገባህ፥
ባህሩ አንተ ነህ
በጠብታ የሞላህ"
ሩሚ
ትርጉም - ጫንያለው በቀለች ወ/ጊዮርጊስ

@getem
@getem
@getem
👍1
🇪🇹🇪🇹🇪ዘጠነኛው የብርሃን ዕለት የመጀመሪያው ማክሠኞ ነሀሴ 7። ይምጡና አብዝተው ያትርፉ እንድቅትዮን በ አዲስ አበባ ትያትር እና ባህል አዳራሽ(ፒያሳ) ።
ልዩ እና እውቅ የጥበብ ሰዎች ግጥም እና ወግ በባህላዊ ሙዚቃ ታጅበው ያቀርባሉ።

እማይቀርበት ልዩ የጥበብ ምሽት!


@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
@tebeb_mereja