ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
?

“ጊዜ ብሎ ነገር
ጅማሬ የሌለው ፥ የማናየው አልቆ
ነባራዊ አይደለም
የፈበረከው ነው ፥ የሰው ልጅ ተጨንቆ
አለ የሚባለው
ይህ ቅፅበት ብቻ ነው ፥ እድሜ ለዘንድሮ
ነቅቼ ነው እንጂ
ጊዜ እውነት መስሎኝ ፥ አምን ነበር ድሮ፡፡”
ቢለኝ አዳመጥኩት
ሃሳቡን ግን ጣልኩት፥ ሳያሻኝ ማስረጃ
እስከዛሬ ድረስ
አልነቃሁም ካለ ፥ የከርሞንም እንጃ፡፡
ድሮና ዘንድሮን
ለማንፀሪያው ጠቅሶ ፥ ወድቆ ከጊዜ እቅፍ
ከአሁን ቅፅበት ሌላ
ጊዜ የለም ማለት ፥ መንቃት ወይስ እንቅልፍ?

@getem
@paappii

#Haileleul Aph
እኔ ለተከፋሁ ፥ እኔን ሆድ ለባሰኝ
መኖር ምናባቱ ፥ ህይወት ከንቱ ሚያሰኝ
በሽታ ከያዘኝ....
ሆድ ካገር ይሰፋል? እኔን ይተልቃል?
መኖሬ ቢያከትም ፥ ህላዌ ያበቃል?
.
ዛፉ ክንፍ አብቅሎ ፥ መጥረቢያ ካልሸሸ
ፀሃይ ፅልመት ፈርታ ፥ በጠዋት ካልመሸ
ውልደት ሞትን ጠልቶ ፥ ካልቀረ ጨንግፎ
ስለምን ያቅታል
አንድ ቀን ማሳለፍ ፥ ቅሬታን ታቅፎ?
.
ውሃ ጥም ከውሃ ፥ ጦርሜዳ ሳይወርዱ
ረሃብም እንጀራን ፥ ሳይደቃው በክንዱ
ሳር መረገጥ መሮት ፥ ሳያበቅል ተንኮል
መጀመሪያ ሞት ነው ፥ ለመሞት መቸኮል፡፡
.
ና ልሰርህ ልቤ
ሲሞላ አትብረር ፥ ሲጎል አትሰበር
ሸክሙን እንልመደው ፥ የመኖርን ቀንበር
በውልደት የገባን
በሞት እስክንወጣው ፥ ማሳለፊያውን በር፡፡
.
(መነሻ ሃሳብ- ሩሚ)

@getem
@getem
@paappii

#haileleul_aph
እግዜሩ ፍፁም ነው!
ሰው የግዜር ስራ ነው።
የሰው ልጅ አመሉ ÷ ከጌታው ቃል መውጣት
የፈጣሪም ፍርዱ ÷ ሰውን በሞት መቅጣት።
.
.
ሞት መቀጫ ሲሆን
ፍፁም የተባለው÷ እግዜር አጎደለ
አንድም መሳሳትን
ሁለትም መሞትን÷ ለሰዎች አደለ።

ታመው፣ ታመው፣ ታመው
ደክመው፣ ደክመው፣ ደክመው
ሽማግሌው ሞቱ ÷ (ወይስ አረፉ እንበል?)
በቅርብና በሩቅ
ይለያያል መሰል ÷ የሞት አቀባበል።

የሚያውቁት ሰው ቢሞት
ያለቅሳል ቀባሪ ÷ ውሎ ተሰብስቦ
ለማያውቁት ሞት ግን
እንባ መራጨቱ ÷ አይን ምን አስቦ?
ከሞት ተፈጥሮ ነው?
የመተላለፉ÷ እንባ እንደ ተስቦ?
.
.
መቃብር ቆፋሪው
ሞተና ቆፍረን ÷ አፈር አለበስነው
ሳጥን ሻጩም ሞተ
አስከሬን ገናዡ ÷ በሳጥን ከደነው።
ገናዡ ሲገነዝ
ፍትሃት የቆሙት ÷ ተጋድመው ተፈቱ
አልቃሽ አስለቃሾች
ተራ እስኪደርሳቸው ÷ ደረት የሚመቱ።

ህይወት በምን ያምራል?
ህፃን ፈገግ ቢል ÷ ያየው ፈገግ ይላል
ከእንባና ከሳቅ
ለማስተላለፉ ÷ የትኛው ይቀላል?
ሞት ለምትናፍቅ ልብ
መኖር በቃኝ ላለች ÷ ምላ ተገዝታ
አስሮ ለማሰንበት
አቅም ያለው ማነው ÷ ተስፋ ነው ትዝታ?

@getem
@getem
@paappii

#Haileleul Aph
#ልጅነትና_እውቀት
.
ይመስለኝ ነበረ
.
.
ከእለታት አንድ ቀን
ጦርነት ሁሉ አልቆ፥ ሰላም የሚሰፍን
ይመስለኝ ነበረ
ትልልቅ ሰው ሁሉ
ሚስጥር የሚደብቅ፥ ገመና የሚሸፍን።
.
ይመስለኝ ነበረ
ቤተስኪያን ሂያጅ ሁሉ፥ እውነት የሚናገር
ሰው የመሬት ዜጋ
መሬትም የሰው ልጅ፥ ሁሉም የራስ ሃገር፡፡
.
ይመስለኝ ነበረ
የታመመ ሁሉ ፥ ታክሞ የሚድን
የተራበ ጠግቦ
የምስጋና ንፋስ፥ ምድርን የሚከድን።
.
ይመስሉኝ ነበረ
አብረው ያየኋቸው፥ ከልብ ሚዋደዱ
‘ሚዋደዱ ሁሉ
የማይለያዩ፥ የማይከዳዱ።
ሰው በሙሉ መልካም
ያጠፋ እንኳን ቢኖር፥ ወዲያው የሚቀጣ
መጥፎው ተወግዶ
ደግ የሚነግስበት፥ ዘመን የሚመጣ።
.
ይመስለኝ ነበረ
.
.
ማደግ ደስ የሚያሰኝ
ለሚራበሽ አለም፥ መድሃኒት የማስገኝ
በመኖሬ ምክንያት
የሌላውን ህይወት፥ ሳሻሽል የምገኝ፡፡
.
.
ይመስለኝ ነበረ....።
.
.
የዋህ ልጅነቴን
አደግሁና አየሁት፥ ትዝብቴ አሳቀቀኝ
ሃሳቤን ቢያውቁብኝ
መሳቂያ መሆኔን፥ ማን አስጠነቀቀኝ?
.
አደግሁና ጀመርኩ
በያደባባዩ፥ መካሰስ መወንጀል
ባከማቸሁት ላይ
ነጥቆ ማከማቸት፥ ያማኜን መከጀል።
በሰው ሰራሽ ድንበር
በሰው ሰራሽ ቀንበር፥ ቡድን እየሰራሁ
እንደ ሰኔ መሬት
እየተሸናሸንኩ፥ መባላት ከዘራሁ
ማነው ያስተማረኝ
ታቦት ሰርቆ መሸጥ፥ ክህነቴን ጥዬ
ማነው የነገረኝ
ሸንግሎ ማሳደር፥ የእግዜር ሰው ነኝ ብዬ?
የሚል ጥያቄ አለኝ
ለዚያ ልጅነቴ፥ ለዛሬው ማደጌ
ማን ያብራራልኛል
በሽታ መፍጠሬን፥ መድሃኒት ፈልጌ?
መሳሪያ ፈልስፌ
ጠብ-መንጃ መሸጤን፥ ለጦር ማስታጠቄን
ማን ይመልስልኝ
የማደግ ክፋቴን፥ የልጅነት ሃቄን?
.
አለም አኬልዳማ
በእድሜዬ እሾህ ማሳ፥ ደማምቼ ባለፍኩ
አደግሁና ገባኝ
ሌላው ምን አገባኝ.. ራሴን ካተረፍኩ?


#Haileleul_Aph
@getem
@getem
@getem
2