ለአረፋችን
❤️❤️❤️
የመዲናን ጎራ፤የመካን መሬት!!!!
መካ መዲና ላይ ከፈረፈሪቱ፤
ይናፍቅ የለም ወይ አፈሩ መሬቱ፤
አላህ በወፈቀኝ ፤
ሙቼ በተገኘሁ እንደግመሊቱ።
ምነው ባደረገኝ፤ ክንፍ ያላት አሞራ፤
ዘይሬው በመጣሁ፤
የመካን ዛውያ ፤ የመዲናን ጎራ።
እድሜ ይስጠኝና ፤
ሂጄ አይቼው ልምጣ፤
የመዲናን ጎራ፤ የመካን በረሃ፤
ጠጥቼ እሽራለሁ፤
ኢማን የሞላውን፤ የዘምዘሙን ውሃ።
እንኳን በውሃና ቢታጠር በእሳት፤
መዘየሬን አልተው መዲና መሬት።
ባህሩን ማን ባሻገረኝ፤
በረሃውን ማን ባሻገረኝ፤
መዲና ጉዳይ ነበረኝ፤
መካ ላይ ሃጃ ነበረኝ።
ከሸህ ሚስባህ ሃገር፤ የጁ ተፈጥሬ፤
ዳና ከጎራው ላይ፤
ነቢ ዘይኔ እያልኩኝ፤
ባገሬ መንዙማ መደድ ተሞሽሬ፤
ዋሪዳው ሲያዘንበው፤
የመካን ዛውያ፤
ቁባውን አየሁት ከሩቅ አሻግሬ።
የጀሊሉ ባሪያ ኸይረኛው መለይካ፤
ጉዳይ ነበረብኝ መዲናና መካ ፤
ክንፍህን አውሰኝ ፤
ዘግኜው ልመለስ የዘምዘሙን ጅረት የአፈሩን በረካ ።
-
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
እያሉ እነዚያ ቀደምት የኢትዮጵያ ሃበሾች ለሃጅና ኡምራ በባዶ እግራቸው የተጓዙበት ዘመን
በታሪክ ድርሳናት ተመዝግቦ ይገኛል። በዚሁ ዘመን ከኢትዮጵያ ወደ ጅዳ ይጓዙ የነበሩ
አባቶቻችን የእንጀራ ድርቆሽ፣ ቋንጣና የተለያዩ ደረቅ ምግቦችን በመውሰድ እዚያ ለሚገኙ
ምስኪን ዜጎች ሰደቃ ይሰጡ ነበር። ሳውዲ እንዲህ እንደዛሬው ሃብታም ሀገር
አልነበረችም። ከታች ምስሉ ላይ የሚታዩት ሰወች እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1902
ከወሎ ወደ መካ ሃጂ ያደረጉ ወገኖቻችን ናቸው።
-
ሁላችሁም ሙስሊም ወገኖቻችን ለዚህ የሃጅ በረካ ያብቃችሁ!
በደስታ የተጥለቀለ፤እዝነትና በረካ የሞላበት የአረፋ በአል ይሁንልን!!!
ሸጋ በዓል❤️❤️!!
@getem
@getem
@balmbaras
❤️❤️❤️
የመዲናን ጎራ፤የመካን መሬት!!!!
መካ መዲና ላይ ከፈረፈሪቱ፤
ይናፍቅ የለም ወይ አፈሩ መሬቱ፤
አላህ በወፈቀኝ ፤
ሙቼ በተገኘሁ እንደግመሊቱ።
ምነው ባደረገኝ፤ ክንፍ ያላት አሞራ፤
ዘይሬው በመጣሁ፤
የመካን ዛውያ ፤ የመዲናን ጎራ።
እድሜ ይስጠኝና ፤
ሂጄ አይቼው ልምጣ፤
የመዲናን ጎራ፤ የመካን በረሃ፤
ጠጥቼ እሽራለሁ፤
ኢማን የሞላውን፤ የዘምዘሙን ውሃ።
እንኳን በውሃና ቢታጠር በእሳት፤
መዘየሬን አልተው መዲና መሬት።
ባህሩን ማን ባሻገረኝ፤
በረሃውን ማን ባሻገረኝ፤
መዲና ጉዳይ ነበረኝ፤
መካ ላይ ሃጃ ነበረኝ።
ከሸህ ሚስባህ ሃገር፤ የጁ ተፈጥሬ፤
ዳና ከጎራው ላይ፤
ነቢ ዘይኔ እያልኩኝ፤
ባገሬ መንዙማ መደድ ተሞሽሬ፤
ዋሪዳው ሲያዘንበው፤
የመካን ዛውያ፤
ቁባውን አየሁት ከሩቅ አሻግሬ።
የጀሊሉ ባሪያ ኸይረኛው መለይካ፤
ጉዳይ ነበረብኝ መዲናና መካ ፤
ክንፍህን አውሰኝ ፤
ዘግኜው ልመለስ የዘምዘሙን ጅረት የአፈሩን በረካ ።
-
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
እያሉ እነዚያ ቀደምት የኢትዮጵያ ሃበሾች ለሃጅና ኡምራ በባዶ እግራቸው የተጓዙበት ዘመን
በታሪክ ድርሳናት ተመዝግቦ ይገኛል። በዚሁ ዘመን ከኢትዮጵያ ወደ ጅዳ ይጓዙ የነበሩ
አባቶቻችን የእንጀራ ድርቆሽ፣ ቋንጣና የተለያዩ ደረቅ ምግቦችን በመውሰድ እዚያ ለሚገኙ
ምስኪን ዜጎች ሰደቃ ይሰጡ ነበር። ሳውዲ እንዲህ እንደዛሬው ሃብታም ሀገር
አልነበረችም። ከታች ምስሉ ላይ የሚታዩት ሰወች እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1902
ከወሎ ወደ መካ ሃጂ ያደረጉ ወገኖቻችን ናቸው።
-
ሁላችሁም ሙስሊም ወገኖቻችን ለዚህ የሃጅ በረካ ያብቃችሁ!
በደስታ የተጥለቀለ፤እዝነትና በረካ የሞላበት የአረፋ በአል ይሁንልን!!!
ሸጋ በዓል❤️❤️!!
@getem
@getem
@balmbaras
…ግራ ይገባኛል…
[አብርሃም የሙሉ]
መውደዴን ስታውቂ እንደምትቀብጪ
ቃላትሽን ሁላ እንደ ምትለጥጪ
እንደዛ አይነት ነገር
እገምትሽ ነበር
ግራ ይገባኛል
በጠራራ ፀሀይ አይኑ እንደፈጠጠ
እንደ ሙሰኛ ሰው እንደተጋለጠ
እንደዛ አይነት እዳ
ሀገር እንደ ከዳ
ግራ ይገባኛል
ይለኛል ከውስጤ ባለህ ገመድ ግዛ
መኖርህን ተወው ባለመኖር ውዛ
አይነት መጥፎ ምክር
ከክፉ ሰይጣን ጋ' እንደሚያከራክር
ግራ ይገባኛል
ከትዛዛት አንዱ አትዘሙት ተረስቶ
ለቅፅበታት ስሜት አመታትን ሙቶ
ልክ እንደመቀንዘር
ከቅንዝራም ጋራ እንደመቀናዘር
ግራ ይገባኛል
በእባብ ተመክሮ
ከሰይጣን ውል አድሮ
ክፉኛ እንደማልቀስ
ከተካዱም ሌላ ልክ እንደመወቀስ
ግራ ይገባኛል
ክፉ ሀሳብ ፀንሶ
ደሞ ለምን ምክንያት ከ'ራስ ጋ' ተዋቅሶ
ፍርድን እንደቀጣ
ምንም አንዳልገባው እራሱን እንዳጣ
ግራ ይገባኛል
የሰው ሞት ዘገባ
የውልድ ልጅ እንባ
…እንደሚቻል ሁሉ
"ባልፈጠርስ"
ብሎ እራስ እንደመውቀስ
እንባ እየጠረጉ ደምን እንደማፍሰስ
ግራ ይገባኛል
ግና አልገባሽም
ጭንቀቴ አልታየሽም
ከፍራቴ ሁሉ የፊቱ ይበልጣል
"መውደዴን ስታውቂ እንደምትቀብጪ
ቃላትሽን ሁላ እንደምትለጥጪ"
አውቄው ነበረ…
እውን ቢሆን ግዜ ልቤ ተሸበረ።
፬-፫-፪፻፲፩
@getem
@getem
@getem
[አብርሃም የሙሉ]
መውደዴን ስታውቂ እንደምትቀብጪ
ቃላትሽን ሁላ እንደ ምትለጥጪ
እንደዛ አይነት ነገር
እገምትሽ ነበር
ግራ ይገባኛል
በጠራራ ፀሀይ አይኑ እንደፈጠጠ
እንደ ሙሰኛ ሰው እንደተጋለጠ
እንደዛ አይነት እዳ
ሀገር እንደ ከዳ
ግራ ይገባኛል
ይለኛል ከውስጤ ባለህ ገመድ ግዛ
መኖርህን ተወው ባለመኖር ውዛ
አይነት መጥፎ ምክር
ከክፉ ሰይጣን ጋ' እንደሚያከራክር
ግራ ይገባኛል
ከትዛዛት አንዱ አትዘሙት ተረስቶ
ለቅፅበታት ስሜት አመታትን ሙቶ
ልክ እንደመቀንዘር
ከቅንዝራም ጋራ እንደመቀናዘር
ግራ ይገባኛል
በእባብ ተመክሮ
ከሰይጣን ውል አድሮ
ክፉኛ እንደማልቀስ
ከተካዱም ሌላ ልክ እንደመወቀስ
ግራ ይገባኛል
ክፉ ሀሳብ ፀንሶ
ደሞ ለምን ምክንያት ከ'ራስ ጋ' ተዋቅሶ
ፍርድን እንደቀጣ
ምንም አንዳልገባው እራሱን እንዳጣ
ግራ ይገባኛል
የሰው ሞት ዘገባ
የውልድ ልጅ እንባ
…እንደሚቻል ሁሉ
"ባልፈጠርስ"
ብሎ እራስ እንደመውቀስ
እንባ እየጠረጉ ደምን እንደማፍሰስ
ግራ ይገባኛል
ግና አልገባሽም
ጭንቀቴ አልታየሽም
ከፍራቴ ሁሉ የፊቱ ይበልጣል
"መውደዴን ስታውቂ እንደምትቀብጪ
ቃላትሽን ሁላ እንደምትለጥጪ"
አውቄው ነበረ…
እውን ቢሆን ግዜ ልቤ ተሸበረ።
፬-፫-፪፻፲፩
@getem
@getem
@getem
👍1
ተስፋ የግጥም ስብስብ መፅሀፍ ምረቃ
በ አስታውሰኝ ረጋሳ (አስቱ)
አርብ ነሀሴ 10
ክ 11:00 ጀምሮ
በ አዲስ አበባ ቲያትር እና ባህል አዳራሽ (ማዘጋጃ) ፒያሳ
@getem
@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
በ አስታውሰኝ ረጋሳ (አስቱ)
አርብ ነሀሴ 10
ክ 11:00 ጀምሮ
በ አዲስ አበባ ቲያትር እና ባህል አዳራሽ (ማዘጋጃ) ፒያሳ
@getem
@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
❤1
…የባህታዊ ንግርት…
"ልብ ያለው ልብ ይበል፤የሌለውም ይግዛ
ጊዜው ቁም-ነገር ነው፣አይደለም የዋዛ…
እንፁም እንፀልይ፤ ማንኮራፋት ይብቃ
ጠላት ሳይሰለጥን፤ የተኛን እንንቃ"
ከምዕራፍ በኋላ፤
ጠላት ሰለጠነ፤ ያሉትም ደረሰ
በእዬዬ ሆይታ፤ ሁሉም አለቀሰ
በእንባ ፀሎቱ፤ ሁሉም ሰው ተረፈ
ግና ያልታሰበው፤ አንድ ሰው አረፈ።
በእቅልፍ ልባቸው፤ ሁሉንም ቀስቅሰው
እሳቸው ሳይነቁ፤ ጠላት ደርሶባቸው
የተኮፈሰ እንቅልፍ፤ አባን ገደላቸው።
እዬዬ… እዬዬ፤ አስተማሪው ሞቱ
እስኪ ምን ይባላል?፤
ለነጋለት ሲመሽ፤ ለመሸበት መንጋቱ?!
"ይሄ ያባ ታሪክ፤ የኔም እውነታ ነው
ካስተማርኩት ትምህርት፤ መች ይሆን ምማረው?!"
[አብርሃም የሙሉ] | ፲፪-፱-፳፻፲፩ |
@getem
@getem
@getem
"ልብ ያለው ልብ ይበል፤የሌለውም ይግዛ
ጊዜው ቁም-ነገር ነው፣አይደለም የዋዛ…
እንፁም እንፀልይ፤ ማንኮራፋት ይብቃ
ጠላት ሳይሰለጥን፤ የተኛን እንንቃ"
ከምዕራፍ በኋላ፤
ጠላት ሰለጠነ፤ ያሉትም ደረሰ
በእዬዬ ሆይታ፤ ሁሉም አለቀሰ
በእንባ ፀሎቱ፤ ሁሉም ሰው ተረፈ
ግና ያልታሰበው፤ አንድ ሰው አረፈ።
በእቅልፍ ልባቸው፤ ሁሉንም ቀስቅሰው
እሳቸው ሳይነቁ፤ ጠላት ደርሶባቸው
የተኮፈሰ እንቅልፍ፤ አባን ገደላቸው።
እዬዬ… እዬዬ፤ አስተማሪው ሞቱ
እስኪ ምን ይባላል?፤
ለነጋለት ሲመሽ፤ ለመሸበት መንጋቱ?!
"ይሄ ያባ ታሪክ፤ የኔም እውነታ ነው
ካስተማርኩት ትምህርት፤ መች ይሆን ምማረው?!"
[አብርሃም የሙሉ] | ፲፪-፱-፳፻፲፩ |
@getem
@getem
@getem
ህልምና አላሚ
‹‹ትናንት›› ህልም ነበር
ህልም ዛሬም አለ
ነገም ህልም አይጠፋ፤
አላሚ ብቻ ነው
በወረፋ መጥቶ 'ሚሄድ በወረፋ፤
ዘመን ግን አንዳንዴ የምሩን ሲከፋ፤
የሚታለም በዝቶ የሚያልም ሲጠፋ፤
ያኔ አገር አለቀ ያኔ ህዝብ ጠፋ፡፡
# ፍቅርኤል
@getem
@getem
@kaleab_1888
‹‹ትናንት›› ህልም ነበር
ህልም ዛሬም አለ
ነገም ህልም አይጠፋ፤
አላሚ ብቻ ነው
በወረፋ መጥቶ 'ሚሄድ በወረፋ፤
ዘመን ግን አንዳንዴ የምሩን ሲከፋ፤
የሚታለም በዝቶ የሚያልም ሲጠፋ፤
ያኔ አገር አለቀ ያኔ ህዝብ ጠፋ፡፡
# ፍቅርኤል
@getem
@getem
@kaleab_1888
👍2
ፍቅር ዘ-ዝንት አለም
°°°°°°°°°°°°°°°°°
ቅዱሳን...!
አታስምሩ ፀሎት አትለምኑ ለኛ
እንባ አይቅረራቹ አትማልዱ ስለኛ
አንሞት በነብሳችን አንገባም ከጥልቁ
እግዜርም ሴጣንም ይህንን ይወቁ
የፍርድህ ሰለባ አይደለም ነብሳችን
ስትፈርድ አንገኝም ይቅርታ ጌታችን
አንተም አጠብቀን ደጅህን ጎዝጉዘክ
አንዳች ሐይል የለው ሴጣን ሆይ እሳትክ
ይልቅ ለነብሳችን ለኔና እሷ ስጋ
ካለን ይበቃናል መደብ ወይም አልጋ
በነብሳችን ጡዘት
በስጋችን ኡደት
ባሳባችን ግለት
በልባችን እብደት
አካሏ ካካሌ ድንበሩን ሲዘራ
ነብሷ በነብሴ ላይ ፀዳሉን ሲያበራ
አንድ አይደል ሺ ፈራጅ አዳምን ሲዳኘው
ሚልየን ሌጊዮን ነብሱን ሲሞግተው
ምድር እንደ ሰሌን ብትጠቀለልም
ሰማይ ከባላው ላይ ሽቅብ ቢሰደድም
ፀሐይ ከካስማዋ ብትሽቀነጠርም
ጨረቃ ካውታሯ ብትፈጠፈጥም
እቴ በመደቡ ባልጋችን መሀል ላይ የፈጠርሽው ግለት ከቶ አይቀዘቅዝም
በልቤ መቅረዝ ላይ ገነት ተለኩሶ ስለ እሳት ነበልባል እኔ አልጨነቅም
ስለ እግዚያር መንግስት ሳስብ አልገኝም
ጌታም በመንበርህ ፍርድህን ስትጨርስ
ሴጣን ባርያዎችን ከፍርዱ ስትቀንስ
እኔ በፍቅሯ ላይ እቴ በፍቅሬ ላይ ህይወት ስንቀጥል
እንመሰርታለን አንድ ግዙፍ አለም አንድ ፅኑ ክልል።
∞ Mr. Trump ∞
@getem
@getem
@getem
°°°°°°°°°°°°°°°°°
ቅዱሳን...!
አታስምሩ ፀሎት አትለምኑ ለኛ
እንባ አይቅረራቹ አትማልዱ ስለኛ
አንሞት በነብሳችን አንገባም ከጥልቁ
እግዜርም ሴጣንም ይህንን ይወቁ
የፍርድህ ሰለባ አይደለም ነብሳችን
ስትፈርድ አንገኝም ይቅርታ ጌታችን
አንተም አጠብቀን ደጅህን ጎዝጉዘክ
አንዳች ሐይል የለው ሴጣን ሆይ እሳትክ
ይልቅ ለነብሳችን ለኔና እሷ ስጋ
ካለን ይበቃናል መደብ ወይም አልጋ
በነብሳችን ጡዘት
በስጋችን ኡደት
ባሳባችን ግለት
በልባችን እብደት
አካሏ ካካሌ ድንበሩን ሲዘራ
ነብሷ በነብሴ ላይ ፀዳሉን ሲያበራ
አንድ አይደል ሺ ፈራጅ አዳምን ሲዳኘው
ሚልየን ሌጊዮን ነብሱን ሲሞግተው
ምድር እንደ ሰሌን ብትጠቀለልም
ሰማይ ከባላው ላይ ሽቅብ ቢሰደድም
ፀሐይ ከካስማዋ ብትሽቀነጠርም
ጨረቃ ካውታሯ ብትፈጠፈጥም
እቴ በመደቡ ባልጋችን መሀል ላይ የፈጠርሽው ግለት ከቶ አይቀዘቅዝም
በልቤ መቅረዝ ላይ ገነት ተለኩሶ ስለ እሳት ነበልባል እኔ አልጨነቅም
ስለ እግዚያር መንግስት ሳስብ አልገኝም
ጌታም በመንበርህ ፍርድህን ስትጨርስ
ሴጣን ባርያዎችን ከፍርዱ ስትቀንስ
እኔ በፍቅሯ ላይ እቴ በፍቅሬ ላይ ህይወት ስንቀጥል
እንመሰርታለን አንድ ግዙፍ አለም አንድ ፅኑ ክልል።
∞ Mr. Trump ∞
@getem
@getem
@getem
#ማስታወሻ
ውዴ ከ'ኔ ከራቅሽ መሄድሽ ካልቀረ፣
ልቤ ባንቺ እጦት ደርሶ ከከሰረ፣
ከውስጤ እንዳትወጪ እስከመጨረሻ ፣
የወርቅ ሃብልሽን ስጭኝ ማስታወሻ።😜😍
©fb
@getem
@getem
@kaleab_1888
ውዴ ከ'ኔ ከራቅሽ መሄድሽ ካልቀረ፣
ልቤ ባንቺ እጦት ደርሶ ከከሰረ፣
ከውስጤ እንዳትወጪ እስከመጨረሻ ፣
የወርቅ ሃብልሽን ስጭኝ ማስታወሻ።😜😍
©fb
@getem
@getem
@kaleab_1888
👍1
......
ደሞ ስለፍቅር፤ ይቺ ማናት እሷ
በሙዚቃ ቃና፤ ምትፅናና ነፍሷ
ይቺ ማናት አሉ፤ ቤትህን ናፋቂ
ምን ብዬ ምጠራት፤ እየከፋት ሳቂ
ሴት መሳይ፤ ሴት ነገር
ምላሷን አውጥታ፤ ልቧን ማትናገር
ይቺ ይቺ ይቺ..፤ ስሟ አይቆላመጥ
ውበቷ ሳያንሳት፤ሰውነቷ ማይቀብጥ
(ወይም የተማረች)
አምላኬ ልበልህ፤ "ማናት እሷ አበባ?"
ስትስቅ እያየኃት፤ ጥርሷ የሚያነባ
እኔ የምትመስለኝ፤ የማትመስል ነገር
እንደ ሰው ያነሰች፤ ምትሰፋ ከሀገር..
ማን ብዬ ልንገርህ፤ ማንስ አልላትም
ከወንዶች ባትበልጥም፤ ከሴቶች አታንስም
ወይስ ታውቃታለህ
ቤተል ሄም ልበላት፤ የአምላክ ማደርያ?
የማርያም ማህፀን፤ የፍቅር ማሰርያ?
ታድያ ምን..?፤ ማን ልበላት እኔ
አዳሟ ነኝ እኔ፤ እሷ ናት ሄዋኔ?
ወይስ የሁልጊዜው፤ ሁና ነው ምኞቴ
ቀለበት ባትሆነኝ፤ አርጋት ማርያም ጣቴ
ይቺ ግራ ገቧ፤
ቀኝ አሳቢ ልቧ፤
ምናምን የምላት፤ ምናምን ያልሆነች
የተለየች ነገር፤ ወይም ያልተለየች
የምልህ ምታውቃት፤ የማላውቃት ማ'ነች?!
አባት ታውቀኛለህ፤
ከናፍሯ ጡቷ፤ ዳሌዋ'ና ጭኗ
ኑሮዋ አልታየኝም፣ የትውልድ ቀኗ
የሆነ ነገሯ፤ ከነገር ተለየ
ወይስ ልቦናዬ፤ በመታወር አየ?
ኧረ ተው ተናገር፤ አጥንቶቼ ሰጉ
ከጉድለት ለመሙላት፤ ለመደሰት ጓጉ
ኧረ ተው ተናገር፤ ይቺ ማናት እሷ
በእጆቼ ጨዋነት፤ ይሰፋ ቀሚሷ
ወይ አታጠራጥረኝ፤ ንፈገኝ ውበቷን
ብዙም አትጫነኝ፤ ስጠኝ መንትያዋን፡፡
[አብርሃም ሙሉ] | ፯-፲፪-፳፻፲፩
@getem
@getem
@GETEM
ደሞ ስለፍቅር፤ ይቺ ማናት እሷ
በሙዚቃ ቃና፤ ምትፅናና ነፍሷ
ይቺ ማናት አሉ፤ ቤትህን ናፋቂ
ምን ብዬ ምጠራት፤ እየከፋት ሳቂ
ሴት መሳይ፤ ሴት ነገር
ምላሷን አውጥታ፤ ልቧን ማትናገር
ይቺ ይቺ ይቺ..፤ ስሟ አይቆላመጥ
ውበቷ ሳያንሳት፤ሰውነቷ ማይቀብጥ
(ወይም የተማረች)
አምላኬ ልበልህ፤ "ማናት እሷ አበባ?"
ስትስቅ እያየኃት፤ ጥርሷ የሚያነባ
እኔ የምትመስለኝ፤ የማትመስል ነገር
እንደ ሰው ያነሰች፤ ምትሰፋ ከሀገር..
ማን ብዬ ልንገርህ፤ ማንስ አልላትም
ከወንዶች ባትበልጥም፤ ከሴቶች አታንስም
ወይስ ታውቃታለህ
ቤተል ሄም ልበላት፤ የአምላክ ማደርያ?
የማርያም ማህፀን፤ የፍቅር ማሰርያ?
ታድያ ምን..?፤ ማን ልበላት እኔ
አዳሟ ነኝ እኔ፤ እሷ ናት ሄዋኔ?
ወይስ የሁልጊዜው፤ ሁና ነው ምኞቴ
ቀለበት ባትሆነኝ፤ አርጋት ማርያም ጣቴ
ይቺ ግራ ገቧ፤
ቀኝ አሳቢ ልቧ፤
ምናምን የምላት፤ ምናምን ያልሆነች
የተለየች ነገር፤ ወይም ያልተለየች
የምልህ ምታውቃት፤ የማላውቃት ማ'ነች?!
አባት ታውቀኛለህ፤
ከናፍሯ ጡቷ፤ ዳሌዋ'ና ጭኗ
ኑሮዋ አልታየኝም፣ የትውልድ ቀኗ
የሆነ ነገሯ፤ ከነገር ተለየ
ወይስ ልቦናዬ፤ በመታወር አየ?
ኧረ ተው ተናገር፤ አጥንቶቼ ሰጉ
ከጉድለት ለመሙላት፤ ለመደሰት ጓጉ
ኧረ ተው ተናገር፤ ይቺ ማናት እሷ
በእጆቼ ጨዋነት፤ ይሰፋ ቀሚሷ
ወይ አታጠራጥረኝ፤ ንፈገኝ ውበቷን
ብዙም አትጫነኝ፤ ስጠኝ መንትያዋን፡፡
[አብርሃም ሙሉ] | ፯-፲፪-፳፻፲፩
@getem
@getem
@GETEM
አንድ ሰው ፈልጉ
®ናትናኤል ዳኛቸው
አንድ ሰው ፈልጉ እስኪ አንድ ሰው ጥሩ
በፍቅር የደማ በፍቅር የታሰረ
በደታ ተፈጥሮ ሺህ እጥፍ የኖረ
ወይም ተበድሎ በፍቅር የታሰረ
አድ ሰው ፈልጉ ልብሱን ያልናፈቀ
እውነትን ለምኖ ከእውነት የታረቀ
ከታወሩ መሃል አይኑን የገለጠ
እንደበግ ሲነዳ ግጦሹን ያጋጠ
አንድ ሰው ፈልጉ ድምፁን ያልረገጠ
አንድ ሰው ፈልጉ ሰውነት የገባው
ዳቦን የማይለምን ዳቦን የሚሰጥ ሰው
ከመተንፈስ አልፎ ተራ ስጋ ለብሶ
ነገ ለሚተዋት ለተበደራት ነፍስ
በንዋይ የማይወድቅ በለቅሶ የማይደንስ
.
.
.
አንድ ሰው ፈልጉ
@Kahlilna
@getem
@getem
@getem
®ናትናኤል ዳኛቸው
አንድ ሰው ፈልጉ እስኪ አንድ ሰው ጥሩ
በፍቅር የደማ በፍቅር የታሰረ
በደታ ተፈጥሮ ሺህ እጥፍ የኖረ
ወይም ተበድሎ በፍቅር የታሰረ
አድ ሰው ፈልጉ ልብሱን ያልናፈቀ
እውነትን ለምኖ ከእውነት የታረቀ
ከታወሩ መሃል አይኑን የገለጠ
እንደበግ ሲነዳ ግጦሹን ያጋጠ
አንድ ሰው ፈልጉ ድምፁን ያልረገጠ
አንድ ሰው ፈልጉ ሰውነት የገባው
ዳቦን የማይለምን ዳቦን የሚሰጥ ሰው
ከመተንፈስ አልፎ ተራ ስጋ ለብሶ
ነገ ለሚተዋት ለተበደራት ነፍስ
በንዋይ የማይወድቅ በለቅሶ የማይደንስ
.
.
.
አንድ ሰው ፈልጉ
@Kahlilna
@getem
@getem
@getem
አንቆርስም!!!!!!!!
በእናቶቻችን ደጅ፣ ባባቶቻችን ቤት፣
በእነ አባ ጉባኤ፣ በአሊሞቹ ፅህፈት፣
በፍቅር ተቃቅፈን፣
የተቀበልነውን፣
የደም ዋጋ ጥሪት፣ መሃላ አናፈርስም፣
ይሁን አሜን ብለን፣
ዳቦውን ነው እንጅ፣ ድካውን አንቆርስም!!!!!!!!
አ፣፣፣፣ን፣፣፣፣ቆ፣፣፣፣ር፣፣፣፣ስ፣፣፣ም!!!!!!!!!!
(((((((( ልብ በሉ!!!!!! ድካ ማለት ትርጉሙ ፣ድንበር፣
ወሰን ማለት ነው።))))))))))
((( ጃ ኖ )))💚💛❤️
ሸጋ ቀን!💚
@getem
@getem
@balmbaras
በእናቶቻችን ደጅ፣ ባባቶቻችን ቤት፣
በእነ አባ ጉባኤ፣ በአሊሞቹ ፅህፈት፣
በፍቅር ተቃቅፈን፣
የተቀበልነውን፣
የደም ዋጋ ጥሪት፣ መሃላ አናፈርስም፣
ይሁን አሜን ብለን፣
ዳቦውን ነው እንጅ፣ ድካውን አንቆርስም!!!!!!!!
አ፣፣፣፣ን፣፣፣፣ቆ፣፣፣፣ር፣፣፣፣ስ፣፣፣ም!!!!!!!!!!
(((((((( ልብ በሉ!!!!!! ድካ ማለት ትርጉሙ ፣ድንበር፣
ወሰን ማለት ነው።))))))))))
((( ጃ ኖ )))💚💛❤️
ሸጋ ቀን!💚
@getem
@getem
@balmbaras
የወቶአደር ቅኔ
------------------------------
⭐_______©ሲራክ_______⭐
ከአምባው ላይ ቆሜ
ከሰላሙ ፍቅርሽ ትዝታን ቀስሜ
በተራራው አናት በተኙ ጉሞች ላይ
እንደእኔ ሆድ ብሶት ከሚያለቅሰው ሰማይ
መሀከል ላይ ቆሜ ትዝታን ሳስታምም
አልታየኝ ይሆናል ፂሜም ሲያቀመቅም
ችግር በቆፈረው በቀበሮ ጉድጓድ
የአረሩን ፉጨት በጣቶቼ ሳግድ
በእንዲህ ያለ ኑረት ያ ልቤ ቢዛክር
አይቻለው ጎኔ ሳያስብሽ ሊያድር
ፈገግታሽን ቋጥረሽ ላኪልኝ በአህያ
ውብ አይንሽን ላኪው ይደር ከእኔ ጉያ
ፈገግታሽ በሶዬ ህይወቴን ማቆያ
ስንደዶ ፀጉርሽን ላኪልኝ እባክሽ
የጠላት መትረየስ ሲንደቀደቅ ቢያድር ተከልዬ ልሽሽ
ውብ ከንፈርሽ ይምጣ ባይኔ ይበል ውልብ
ጠላት ማርኮ ከቦኝ ይሰማኝ የልብ ልብ
ትንፋሽሽን ላኪው ህመሜን ማበሻ
ይሆነኛል እና ለቁስሌ ፋሻ
አንቺ የአይኔ አበባ
በኔ ስጋት ምድር ወዲያ ዳር ያልሽው
ቅዠት ብቻ ሆኗል ሰሞኑን የማየው
እንጃ እኔን ዘንድሮ (፪)
የጥይት ዝናማት በኔ ባይዘንቡብኝ
ናፍቆትሽ ነው ቀድሞ አፈር የሚያለብሰኝ
ፍቅርሽ ጢያራ ነው ክንፍ አውጥቶ በሯል
ከጠላቴ በላይ ዙሪያዬን ከቦኛል
ናፍቆትሽ አዜብ ነው ያነጋግረኛል
በአድማስ ሹክሹክታ ድምፁን ያሰማኛል
ድምፁ ይሰማኛል
ድምፁ ይሰማኛል
በተራራው አናት በተኙ ጉሞች ላይ
እንደእኔ ሆድ ብሶት ከሚያለቅሰው ሰማይ
መሀከል ላይ ቆሜ ትዝታን ሳስታምም
ባክሽ ተሰቃየው ህይወት ሆናኝ አረም
እናልሽ አንቺዬ
#እኔ በሀገሬ ወቶአደር ነኝ አሉ
ለሀገራቸው ሲሉ ነፍሴን ከማይሉ
አጠገብ ምመደብ (፪ )
ስጋዬ ጦር ሜዳ ፍቅርሽን ያቀፈ
ልቤ ካንቺ ጋር ነው በናፍቆት ያደፈ
ልቤ ከኔ የለም ሆኗል ወጥቶ አዳሪ
ስጋ ብቻ ለጦር #ይህን_ጊዜ_ፍሪ_(፫)
⭐ ⭐ ⭐ ⭐ ⭐
ሲራክ
ነሀሴ ፪ ሺ ፲፩ ዓ.ም
በመርበብተ ምድር ሚዛን ተፈሪ
@siraaq
@getem
@getem
@getem
------------------------------
⭐_______©ሲራክ_______⭐
ከአምባው ላይ ቆሜ
ከሰላሙ ፍቅርሽ ትዝታን ቀስሜ
በተራራው አናት በተኙ ጉሞች ላይ
እንደእኔ ሆድ ብሶት ከሚያለቅሰው ሰማይ
መሀከል ላይ ቆሜ ትዝታን ሳስታምም
አልታየኝ ይሆናል ፂሜም ሲያቀመቅም
ችግር በቆፈረው በቀበሮ ጉድጓድ
የአረሩን ፉጨት በጣቶቼ ሳግድ
በእንዲህ ያለ ኑረት ያ ልቤ ቢዛክር
አይቻለው ጎኔ ሳያስብሽ ሊያድር
ፈገግታሽን ቋጥረሽ ላኪልኝ በአህያ
ውብ አይንሽን ላኪው ይደር ከእኔ ጉያ
ፈገግታሽ በሶዬ ህይወቴን ማቆያ
ስንደዶ ፀጉርሽን ላኪልኝ እባክሽ
የጠላት መትረየስ ሲንደቀደቅ ቢያድር ተከልዬ ልሽሽ
ውብ ከንፈርሽ ይምጣ ባይኔ ይበል ውልብ
ጠላት ማርኮ ከቦኝ ይሰማኝ የልብ ልብ
ትንፋሽሽን ላኪው ህመሜን ማበሻ
ይሆነኛል እና ለቁስሌ ፋሻ
አንቺ የአይኔ አበባ
በኔ ስጋት ምድር ወዲያ ዳር ያልሽው
ቅዠት ብቻ ሆኗል ሰሞኑን የማየው
እንጃ እኔን ዘንድሮ (፪)
የጥይት ዝናማት በኔ ባይዘንቡብኝ
ናፍቆትሽ ነው ቀድሞ አፈር የሚያለብሰኝ
ፍቅርሽ ጢያራ ነው ክንፍ አውጥቶ በሯል
ከጠላቴ በላይ ዙሪያዬን ከቦኛል
ናፍቆትሽ አዜብ ነው ያነጋግረኛል
በአድማስ ሹክሹክታ ድምፁን ያሰማኛል
ድምፁ ይሰማኛል
ድምፁ ይሰማኛል
በተራራው አናት በተኙ ጉሞች ላይ
እንደእኔ ሆድ ብሶት ከሚያለቅሰው ሰማይ
መሀከል ላይ ቆሜ ትዝታን ሳስታምም
ባክሽ ተሰቃየው ህይወት ሆናኝ አረም
እናልሽ አንቺዬ
#እኔ በሀገሬ ወቶአደር ነኝ አሉ
ለሀገራቸው ሲሉ ነፍሴን ከማይሉ
አጠገብ ምመደብ (፪ )
ስጋዬ ጦር ሜዳ ፍቅርሽን ያቀፈ
ልቤ ካንቺ ጋር ነው በናፍቆት ያደፈ
ልቤ ከኔ የለም ሆኗል ወጥቶ አዳሪ
ስጋ ብቻ ለጦር #ይህን_ጊዜ_ፍሪ_(፫)
⭐ ⭐ ⭐ ⭐ ⭐
ሲራክ
ነሀሴ ፪ ሺ ፲፩ ዓ.ም
በመርበብተ ምድር ሚዛን ተፈሪ
@siraaq
@getem
@getem
@getem
❤1
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (ልዑል)
ተስፋ የግጥም ስብስብ መፅሀፍ ምረቃ
በ አስታውሰኝ ረጋሳ (አስቱ)
አርብ ነሀሴ 10
ክ 11:00 ጀምሮ
በ አዲስ አበባ ቲያትር እና ባህል አዳራሽ (ማዘጋጃ) ፒያሳ
@getem
@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
በ አስታውሰኝ ረጋሳ (አስቱ)
አርብ ነሀሴ 10
ክ 11:00 ጀምሮ
በ አዲስ አበባ ቲያትር እና ባህል አዳራሽ (ማዘጋጃ) ፒያሳ
@getem
@tebeb_mereja
@tebeb_mereja