ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
(#ፋሲል_ስዩም)
©
...
ከላይ...
ከወደ ሰማይ...
ለአፍታ ማይጨፈን የፈጣሪ አይን፣
ከውብ ሽፋሽፍቱ የምትምዘገዘግ የስስት እይታ፣
ለፈጠረው ምድር፣እንደ ልብ ትርታ፣
(የዐይኑ ብልጭታ)
.
(ከታች)
ከእኔ ካንቺ መንደር...
ፈጣሪን የሚያሙ ማይዘጉ አፎች፣
እሳት የፀነሱ...እሳት የሚወልዱ...እልፋን አንደበቶች፣
(ክፍት አፎች፣)
.
(ከመሃሉ)
ቀይ ክር ያለበት የታሰረ ስጋ
ነክሶ የሚበርር
ጥምብ አንሳ አሞራ፣
ከነፋስ ጋር ምትዞር አንዲት የርግብ ላባ፣
ከምድር ተነጥቃ ከነፋስ ያበረች
ፅጌ-ሬዳ አበባ፣
(ትንሽ ከፍ ብሎ)
በደመና ስዕላት፣የተቀላለመ፣
የውብ ቆንጆ ስዕል፣
የሆነ መልክም አልባ፣
የሆነ ደምም አልባ፣
የሆነ ገላም አልባ፣
የደመቀ ምስል፣

(እኔ)
ከመንደሬ ካለች ወንዝ ዳር ቁጭ ብዬ፣
ምናቤን፣
ከበላይ...ከመሃል...ከበታች
ደግሞም ካንቺ ጥዬ፣
በትንሽ ዛፍ ጥላ 'ራሴን ጠልዬ፣
(ግጥም እፅፋለሁ)
)ስንኝ እጥፋለሁ(

ከወንዙ ባሻገር፣
ለጋነት ያነቃት፣አንዲት ልጃገረድ፣
ከጋለ አለት ላይ፣ለመብረድ ተቀምጣ፣
እግሮቿን ተከፍተው፣ቀሚሷ ተገልቦ፣
አዳፋ ብጫቂ፣ውራጅ ጨርቅ ታጥባለች፣
.
ቀና ስል ካየሁት፣ዝቅ ስል አጥቼ፣መሃል ላይ ካዋልኩት፣
የውበት ገፅታ፣
እኔን የማረከኝ፣
ብዕሬን ቀጥ አርጎ፣
ግጣም አሳይቶ፣
መግጠምን ያስረሳኝ፣
ከባሻገሬ ላይ፣
ከክፍት ቀሚስ መሃል፣
ተከፍቶ ያየሁት፣የውድዬ ሲሳይ፣!
(ከላይ)
(ፈጣሪ እንዳያይ)


...///...
ዲላ

@getem
@getem
@gebriel_19
(#ፋሲል_ስዩም)
(!የምስራብ ስባሄ!)
.........
አሜን ተባረኪ፣
እድሜሽን 'ባውድ አመት፣
በጠሃይ ምስረቃ፣
ያፍካው ያለምልመው፣
ዱልዱሙ ገፅሽን፣
የዘመን ሽክር ሞረድ፣
ይሞርድ ይሳለው!...
(አሜን ተማረኪ!)
ያ ስሉ ዘመንሽ፣
አንገትሽን ይቅላው፣
አንጀትሽን ያውልቀው፣
ጣየ ምስራቅሽን፣
ምዕራብሽ ይነቀው!
(አሜን ተባረኪ!)
(አሜን ተማረኪ)


...///...
ዲላ

@getem
@getem
[#ፋሲል_ስዩም]
.
ጥፎ ለባሽ!
...///...
ደጋን ጨባጭ መዳፍ፣ቀስትን አስፈንጣሪ፣
የንድ አሳብ ዐውድ፣የፊደል ቃራሚ፣
አጁ 'የሻከረ፣
ጣቱ የተቃማ፣
ልባሱ ተቀዶ፣ገላው የደማማ፣
ሱሪው የወለቀ፣ሳያብድ ያበደ፣
የሰው'ነቱን ልኬት፣አስሮ ያነደ፣
በምናብ የሚነጉድ፣
በምናብ የሚነድ፣
ለምናብ የሚሰግድ፣
'ራቁታም ጫሪ፣
ራቁት ሰዐሊ፣
ራቁት ደራሲ፣
ራቁት አንባቢ፣

የሲቃውን ንባል በብዕሩ አርካሽ፣
ቅዳዱ ልባቡን ዳግ ጥፎ ለባሽ!
...///...

@getem
@getem
@gebriel_19
(#ፋሲል_ስዩም )
...................
(እናት አለም ከወደዚህ)
በደም ቅብ ጌጥ ደምቃ፣
በሚስጢሯ ግምደት ከቁንጅና ረቃ፣
ከብናኝ አፈር ዑደት ርቃ፣
ባቋቋሟ ፀንታ፣
ብርሀን በፀነሰ
የጨለማ ንጥ ውጊያ ታግላ
በልቤ ፅላ ላይ...
በታሪክ ቅጥል-ጥሎሽ ሀረግ ግምጃ
ታትማ ተቀምጣ...፣
እስከ ዛሬ አለች...
(እኔ ከባሻገር)
ለምወዳት እንስት...ለጠዋቴ ጀምበር፣
ላልከዳት
ላልተዋት
ላፈቅራት
ምዬላት
በጡቷ እሽታ....
ፍቅሯን ስምገው፣ክንዷን ተንተርሻት፣
(በሕልም አለም ሳለሁ)
(በሙት ምሳል ጊዜ)
(ደምቄ በደሟ)
(በወዟ በወዜ)
አንዴ በፍጋግ ቅኝት
ደግሞ በትካዜ፣

ኩኩሉን ሳልሰማ...
ጭራፍ የብርሃን ምዛዥ
ከልፍኜ ሳይጠባ...
ድብዙዝ ገፄ ሳይጠራ
ጭላም ቤቴ ሳያበራ...
የኔ ገላ እንደጋለ...
የር'ሷም ገላ እንደቀላ፣
ጩኸት ሰማን የሚያስፈራ፣
አፈር ካ'ፈር ሲቀናና፡፡

(አሁን)

በ'ስር በግልቢያ የመጣው፣
የስሜቴ ፋኖስ፣
ባንዳፍታ ጨለመ፣
በእምባ እርግዛት፣
ዝናብ ላያመጣ፣
ሰማዬም ደመነ፣
በግን-ጥል-ጣይ ዘመን
እላፍ የታሪክ ገፅ፣
የአንድነት ማሰሪያ
ገመዱ ሲበጠስ፣
ያመኑት ሲከዳ፣
ተስፋ እንደጉም ሲበን
(ሲበተን)
የፍቅር ቃል ንዳዱ ሲዳፈን፣
የሀሰት መውደድ ቃል ሲሰፋ፣
ከግቷ የጠባሁትን ፍቅር ስተፋ፣
በስሜት እቅፋት...ውበቴን ሳጠፋ፣
(እቴ ከወደዚያ)
አይኗ በስለት ተኳለ፣
በኔ ግብር ትኩሳት ፊቷ ተቃጠለ፣
የ"ቅር-ፍቅር" ቅኔ...
የ"ቅር ፍቅር" ዜማ፣
ገና ሳይወለድ ፀንሳ አኑራው፣
ሽል ሆኖ በሞተው ልጇ ተዘመረ፡፡
(አንድም ተፈፀመ፣)
(አንድም ተጀመረ፣)
...///....
04;04:2011
ዲላ

@getem
@getem
@lula_al_greeko
(#ፋሲል_ስዩም )
.........በድምፅ..........
(እናት አለም ከወደዚህ)



@getem
@getem
@getem
[#ፋሲል_ስዩም ]
©
እንግዳ አለብኝ ቤቴን ላሳምረው፣
አፈር ሊገባበት ባፈር ልደልድለው፡፡
እንግዳዬ ብናኝ፣የኔ መልከ መልካም
አግረ ነፋስ ጥሎት እኔም ቤት ይገባል፡፡
(በሚል)
የአዝማሪ ግጥም...
የአዝማሪ ዜማ...
ስንት እንግዳ ነኝ ባይ
ደጅ ደጄን ሲጠና...
(እኔ)
ከአዝማሪው ቅኝት፣ዜማውን ተውሼ፣
በመነን ምናኔ፣እምባዬን አብሼ፣
ቅኝቴን በማጣት፣በጉስቁል ስልና፣
የግጥሜን ፍሰት፣በድሎት ፅፍና፣
(ሙዚቃ)
(ሳበቃ)
እንግዳዬ ቆሟል፣ግራም ቀኝም ገብቶት፣
ቤቴ ሸራ ሆኖ መቆርቆሪያው ጠፍቶት፡፡
(ሙሾ)
ዋይ ዋይ ቤቴ ሳንቃ የለሽ
በሲቃ የታነቅሽ...
እንግዳ ቢመጣ ሳታስገቢ ሸኘሽ፡፡
ዋይ ዋይ ሸራ ቤቴ፣አፈር አይደርስባት፣
እራሷም ብናኝ ናት፣ብናኝ አይገባባት፡፡
(...///...)
ስም አልባ ቀን ላይ የተጫረች...

@getem
@getem
@gebriel_19
🔥1