ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#እህህህ ~ስለኔ!!!

ትዝታ ክፉ ነው
ለሰባራ ልቦች የማይራራ ከቶ
ይኸው በሰቀቀን
ያንከራትተኛል ውስጤን አደህይቶ፡፡
ግን አልደነቅም
ድሮስ ባንቺ ሚዛን ሴትነት ለክቼ
እንዴት ይቻለኛል
ነገዬን መናፈቅ ትላንትናን ትቼ?
አልችልም አለሜ
የምትመጣው ሁሉ ውስጤን ሳትረዳ
በማንነት ስሌት
ከ'ምነት ልትጣረስ ከዙፋኔ ወረዳ
ሰባራውን ልቤን
እንኳንስ ልጠግን ልታክመው ዳብሳ
ትርፏ ሰቀቀን ነው
በለምን ምክንያት ምትዳርግ ላበሳ፡፡
ለዛ ነው ትዝታሽ
ሰርክ እየታወሰ ኑሮዬን ሚቀማኝ
አረሳሁሽ ብዬ
ባወራሁኝ ማግስት ናፍቆት የሚሰማኝ፡፡
እሺ በምን ልዳን?
ከዘመን ልክፍቴ ጩሆ ከማይወጣው
ውስጤን ሳይረዱት
በቀለኛ እያሉኝ በፀፀት ገረጣው፡፡
እኔኮ ጥሎብኝ
እንኳንስ ልበቀል ልስቅ በሴት እንባ
አመታት አልፈዋል
ለሰባራ ልቤ ነፍሴ ሰው ተርባ፡፡
ታዲያ እንዴት ሆኖ
መሰበርን ያየ ሌላውን ይሰብራል
ድሮም ታውቂው የለ
ልቤ እኮ ደግ ነው
እርሱ ጨልሞበት ለሰዎች ያበራል፡

ብቻ ግን ግድየለም
አንቺን አስረስታ
የምታሸንፈኝ እንስት እስክትመጣ
ለሌላው ቢመስልም
በቀል የለም ልቤ ሴትን የሚቀጣ፡፡


((ልብ አልባው ገጣሚ))
@getem
@getem
@gebriel_19
👍2