ግጥም ብቻ 📘
68K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
172 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ይብላኝለት ለኔ
።።።።።።።።።።።

ያልወረደ መና ፣
ልቡን ለሰቀዘው፣
ያልተበላ ዳቦ፣
፣አንጀቱን ለያዘው።
ባልተጠጣ ወተት ፣
ምናቡ እያገሳ፣
ስጋው ሲደነድን፣
ልቡ ለሚከሳ።

ይብላኝለት ለኔ...
ኖርኩ እያለ ሲሞት፣
አፈር ለማይለብሰው፣
ይብላኝለት ለኔ
በነፍስና ስጋ፣ ድንበር ተገትሮ፣
መኖር ላልቀመሰው።
ዛሬ ቀኑ ፀሀይ ፣ ነግ ደሞ ዳመና፣
ታቻምና ረሀብ ነው ፣ አሁን ብልፅግና።
ፍቅር ይተኮሳል፣ ከወዲያኛው ማዶ፣
ዘመድ ይገናኛል፣ ተራራው ተንዶ።
ምናምን ምናምን...
ይሉት እንቶፈንቶ...

ቢያገኝ ለሚበላ ፣ቢያጣ ለሚጋደም፣ ተመስገኑን በልቶ፣
ምን ሊፈይድለት፣ አንዱ አደረ ቢባል፣ በሰው ስጋ አግስቶ?

ይብላኝለት ለኔ...
ከሰው አብራክ ወጥቶ ፣
ሰው ለማይናፍቀው፣
ዕልፍ ችግኝ መሀል፣
ተስፋው ለደረቀ
እኔን ባይ ለራቀው።
ይብላኝለት ልቤን ፣
ይብላኝለት ገላ፣
ብርድ አያውቅ ሙቀት፣
የአፍላነት ዘለላ።
እንባ የለው ዐይኔ፣
ላብ የል ከአካላቴ፣
እንዲህ ያል ድርቅናን፣
ከማን ሸመትኩ እቴ?
ሳቅ እማያስቀኝ ፣
ሰቆቃ እማይገደኝ፣
ምን ያል የሰው አውሬ ፣
አምጦ ወለደኝ?

ይብላኝለት ዐይኔን ...
የሱ ብጤ በርባን፣
አማትሮ ለሚያጣ፣
ውንብድናው አንሶት፣
አምላክ ለሚቀጣ።
ባልሰመረ ቅኝት፣
ለሚደክር ከንፈር፣
መሳም ላልታከተው
ያለመተፋፈር።
ለማይደክም እግሬ፣
በየብስ ባህሩ፣
ንዳድ ለሚነዳው
አልፎ ከድንበሩ።
ይብላኝለት ለኔ...
ሰው ተብሎ ላልሞላው፣
የ "ሰ"ን አንድ ቅኔ።
ይብላኝለት ለኔ!

በማዕዶት ያየህ
18/09/2014 ዓ.ም.

@getem
@getem
@getem
እኔ ቅብዝ ቅብዝብዚት
ችኩል ችኩልኩሊት
ወረት ወርትሪትሪት
አቋም አልባ ሽክርክሪት

ቀን ለሰላት የምፋጠን
ጎህ ሲቀዳድ የ'እግዜር መቅደሱን የማጥን።

ድንጉጥ ድንጉጥጉጢት
ፓስተር ይዞኝ መፅሀፍ ሲገልጥ
የጌታ ነኝ ብዬ ማቀልጥ።

እኔ ልጂት
ጅላ ጅሊት
ቂላ ቂሊት

ያዋቂ ቤት ተንበርካኪ
የ'አትሮንሱ ፊት ሰባኪ
ቀን የሚያምረኝ ቲሪኪሚሪኪ
ማታ ሚያምረኝ መጠጥ ዉስኪ
የማለዳዉ ቅዱስ ባሪያ
የከሰዓት የ'አላህ ባሪያ
የፓስተሩ አማካሪ
ድምብር ደምበርባሪ።

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ትዝታ ወልዴ
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

@TIZITA21
@getem
@getem
@getem
#የት_አባቱ



ስትቀርበው ከራቀ፤
ስትሰጠው ከሰረቀ፤
ስትይዘው ከለቀቀ፤
ስትክበው ካፈረሰ፤
ስታፀድቀው ካረከሰ፤
ስታለብሰው ካራቆተ፤
ስታርመው ካሳሳተ፤
.
.
.
አትለምነው እንዲ አይነቱን፤
ይብቃ እሰረው ቀረጢቱን።
ገመድክን የዝምድና፤
አትቋጥረው በልመና።
ያቀረብከው ካልሆነልክ የሰው ብርቱ፤
ፍታው ተወው ጥንቅር ይበል የት አባቱ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem
@getem
@getem
#እንዳትረሺኝ_ብዬ
:
:
እንድታስታውሺኝ ሁሌም እንዳትረሺኝ ብዙ ለፍቻለሁ፤
ግን ይህ ድካሜ ፍሬ እንዳላፈራ በርግጥ አይቻለሁ።
:
:
ብዙ ቀልድ አውርቼሽ ብዙ ሳቅ ስቀሻል፤
ደግሞም በማግስቱ ሁሉን ረስተሻል።
ስጦታም ስሰጥሽ ወስደሻል በደስታ፤
ይረሳሻል እንጂ ያኖርሽበት ቦታ።
ናፍቀሺኛል ብዬ « አንቺስ?» ያልኩሽ እንደው፤
መልስሽ «ምንም» ነው እንደተለመደው።
:
:
ታዲያ እንደው ምን ላድርግ እስኪ እንደው ምን በጀኝ፤
በሷ መረሳቴ ውስጤን እኮ ፈጀኝ፤
እያልኩኝ ስጨነቅ ስንት ቀን አለፈ፤
ተመስገን ነው ዛሬስ ዕድሜ «ለአበው» ተረት ገልግሎኝ አረፈ።
:
:
አዎ...
ክብሩ ለአበው ይሁን አበው ይሰንብቱ፤
«የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም»ብለው ለተረቱ።
:
:
እናምልሽ ፍቅሬ...
ከዛሬ ጀምሮ ቀልድም አልነግርሽም፤
ስጦታ አልሰጥሽም፤
ናፈኩሽ ወይ ብዬም ከቶ አልጠይቅሽም።
:
:
ይልቅ በዚ ፈንታ...
ጤና ለተረቱ ማድረግ ያለበትን ውስጤ ስለነቃ፤
ከሰሞኑን ውዴ እንዳትረሺኝ ብዬ ልወጋሽ ነው በቃ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@henockba
@getem
@getem
@getem
ግጥም ብቻ 📘 pinned «https://youtu.be/IbBxL9IfCro»
፮፱~~
እወይ አሉኝና አይሞላም ረብቷል፣
በክታብ በርሜሎች መከራችን ሞልቷል፣

ደሞ ምን ገዶን ነው፥ ገዶን ገፍ ገፍ፣
ዘንበል ዘንበል ሲል ነው፥ ውስጥ ያለ ሚደፍ፣
-----------------
ልቃቂት በርሜሎች
----------------
ግዕዝ ሙላት

@getem
@getem
@getem
ገና ከጥንስሱ ቀመር ሳይቀመር
አንድ ሲደመር አንድ
መልሱ አንድ ነበር
ግና በኛ ጊዜ
ነገር ተለውጦ በቀመር ተለክፈው
አንድ ሲደመር አንድ
ሁለት ሆኖ አረፈው።

ይሁና መሆኑ ካልቀረ
ባዲስ ሂሳብ ስሌት
መደመር ከመቀነስ ተለያይቶ ቀረ

ዮኒ
ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
አመል አይለቅ ነገር ከራስ ውሎ ያድራል
የዘመመዉ ልብሽ ሄዶም መች ይቀናል።
አንቺ
መሄድ መጓዝ ስራሽ ባገኙበት መፍሰስ
ይህ ተቀማጭ ልቤ ሄደች ብሎ ማልቀስ
አዎን
ተቀማጭ ነው ልቤ በ.ቃ.ል የታሰረ
ቃልሽን ...ከቅዱስ ቃል እኩል የቆጠረ።
ጠዋት እና ማታ ጡዋፍ እና መባ
አንቺን ከሰጠኝ ብዬ በ'እንባ.....
ለመንኩት
ከቃልሽ ቃል ጠቅሼ አምላኬን ሰበኩት
ግና
ልብሽ መቼ ቀና.....!!!
ያልቀደሰች
ያልመነነች ነፍሴን ማረፊያ አታሳጫት
መሄዴ ነው እያልሽ ተይ አታበሳጫት💔

በረከት
( @berii34 )
@getem
@getem
@getem
ጦሩ ፍቅርሽ
ልቤን ወጋው፤
እንዳልነግርሽ
በጣም ፈራሁ።
አያልቅብሽ ጦር ውርወራው፤
ስንቱን አዳም ልቡን ገዛው።
ልክ እንደንብ እኛ ሆነን፤
አበባ አንቺን፤
ልንቀስምሽ በጣም ጓጉተን።
በዙሪያሽ ስንዞር
ልንከብሽ ስንሞክር።
ገለል አርጎ የከለለሽ።
አንቺን ያዘ ብልጡ አፍቃሪሽ።
ላንቺ ብለን ንብ ስንሆን፤
በብልሁ በአትክልተኛው ተቀደምን።

@abela_black

@getem
@getem
@getem
#አልልሽም
:
:
:
ከፍጥረት ለይቶ እንደሰራሽ በማር፤
የውበትሽና የፀባይሽ ማማር፤
ባንድ ተሰባጥሮ አቅሌን አስቶኛል፤
አንደኛዬ ነሽ ግን ማለት ይከብደኛል።
:
:
ጡት እንዳጣ ዕፃን ልጅ ስነፋረቅ ውዬ፤
ልክ ዐይንሽን ሳየው በደስታ ዘልዬ፤
ማልቀሴን ረስቼ ሰላም አድሬያለሁ፤
አንደኛዬ እኮ ነሽ ማለት ግን ፈራለሁ።
:
:
የህይወቴ ግማድ የመኖሬ ጉዳይ፤
የደስታዬ ወሰን የአንድ ልቤ ሙዳይ፤
አንቺ እንደሆንሽ ባውቅም፤
የኔ አንደኛ ብዬሽ አልመፃደቅም።
:
:
ተንጠራርተሽ ደርሰሽ አቅፈሽ በሹክሹክታ፤
ዓይን ዓይኔን እያየሽ ስትዪኝ የኔ ጌታ፤
ሀሴት ይወረኛል ከእግር እስከ ፀጉሬ፤
አንደኛዬ ነሽ ግን አልልም ደፍሬ።
:
:
እውነት ነው የኔ ውድ እንዴትስ ደፍራለሁ፤
አንቺን እንዲ ማለት በጣሙን አፍራለሁ።
:
:
አንቺን አቅፎ ኖሮ አንቺን አቅፎ መሞት ምን ልቤ ቢመኝም፤
ተቀየሚኝ እንጂ አፈር እስክገባ አንደኛዬ አትሆኚም።
እንደው ቢሆን እንኳን አንደኛዬ እንድልሽ እውን ፈልገሽም፤
ሲያምርሽ ይቅር እንጂ መቼም አልልሽም።
:
:
ለምን ካልሺኝ ውዴ ...
አንደኛ ነው ሲባል አንድ ነገር ደርሶ፤
ሁለተኛ ሆኖ ከእርሱ ትንሽ አንሶ፤
የሚፎካከረው ሌላ አካል እንዳለ፤
መረዳት አይከብድም ቃሉን ላስተዋለ።
:
:
ስለዚም እንቁዬ ...
በውበት በፀባይ ሁለተኛ ሆኖ ካንቺ ሚወዳደር፤
ቢፈለግ አንዳች ሰው በሌለበት ሀገር፤
አንደኛዬ እኮ ነሽ እንዴትስ እላለሁ፤
ብቸኛዬ ሆነሽ ብቻሽ ሆኜ ሳለሁ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@henockba
@getem
@getem
@getem
ግጥም ብቻ 📘 pinned «https://www.youtube.com/watch?v=mWuVrTcU44U»
፡፡፡ የይሁዳ ደብዳቤ ፡፡፡
<< አለም ሑሉ ያልፋል >>
ቢሆንም የአምላክ ቃል ከህይወት ይፃፋል÷
የ ሰላሳዉ ዲናር የማይሻር ዳፋ የማን ነዉ ጥፋቱ?
ግሳንግሱን ትቶ ዘመን እያለፈ ቃል ካልሆነ ከንቱ÷
የቀደመዉ ቃልህ ከበደል ከፃፈኝ
ደህና ሁን ክርስቶስ
ስሞ ከመሸጥ ዉጭ አንዳች ምርጫም የለኝ፡፡


ያብስራ እዮብ (ደብተራዉ)፡፡

@getem
@getem
@paappii
ይድረስ ለአንቺው፣

በከተማው መሀል መናኝ ላደረግሽኝ
አለምን ጠቅልዬ፣ ስሄድ ለሽኘሽኝ
ደንዳናውን ልቤን ላደረግሽው አመድ
ምን ነክቶት ነው?
ብሎ ሰው ሁሉ እስኪፈርድ
አለም ይወቅልኝ እኔስ መንኛልሁ
ከልብሽ ገብቼ ምርኰኛ ሆኛለሁ

ማን በነገረሽ፣
በፍቅርሽ ወድቄ ከራሴ እንደተጣላሁ
አንድ ሺ አንድ ሌሊት ላንቺ እንዳነባሁ
በዚህ ሰፊ ምድር ሴትም በሞላበት
ምን ይሆን ምስጢሩ እንዲህ ምሆንበት
የፍቅሬንም መጠን ትራሴ ይንገርሽ
ሁሌ ማታ ሲሆን እንዳነባሁልሽ

ፈጣሪን ተቀየምኩ፣
የዳዊትን ትግል አግዝፎ ሲሰጠኝ
በጐልያድ ምትክ አንችን ሲልክብኝ
ዳዊት በጠጠሩ ጐልያድን ጣለው
ምን ይወርውር ልቤ ምርኮኛሽ የሆነው


ያሬድ መኮነን(ሳላዶር)
@pappilon36
@getem
@getem
@getem
   //ልጠብቃት\\
አንዲት ቆንጆ መልከ ቀና፤
    ቀና ብዬ አየሁና፤
 ባለማመን ሳለሁ ገና።
 ፊቴን ሳብስ በተደሞ፤
      በአለም ካለሁ
      ወይም ደግሞ።
እውነት ከሆንኩ ሳረጋግጥ፤
  እኔን ጥላ እሷ ጥፍት።
  እፉዬ ነች የኔ ገላ፤
ታይታ የጠፋች እንደ ጥላ።
ገነት ይሁን እኔ የሄድኩት፤
ሴት መላእክት ነው ያየሁት፤
 ግን እፆታ መች አላቸው፤
 መላእክትስ አንድ ናቸው።
   ብዬ ብዙ ስደናገር፤
   ሳላናግር ስግደረደር።
  ንፋስ መጥቶ አበነናት፤
  እፉዬ ነች በቃ አወኳት፤
ስትዞር ውላ የማይደክማት፤
  ንፋስ ወስዶ እንዳራቃት፤ 
   ማረፊያዋን ካላገኘች
     እየገፋ ከመለሳት፤
ተስፋ አልቆርጥም.........
..................ልጠብቃት።
 
@abela_black

@getem
@getem
@getem
ምን አረቄ ቢግፍ
ምን ጠላ ቢሞላ
ምን ቅራሪ ቢያገኝ
ቀማሹ ነው እንጂ … አይሰክርም ብርጭቆ ።
ለምን ?
ከተንገዳገደ … እንደማይተርፍ አውቆ ።

@getem
@getem
@paappii

#Yoseph Workneh
ይቅር
""""""
እንዴት?

ለክፋት ፊት ሰጠን፥
ፍቅር አመለጠን...
ጥላቻ ወረሰ፥
ውሸት እውነት ጣሰ...

እንዴት?

ለመኳረፍ ተጋን፥
ለመታረቅ ሰጋን...
ብዙ ደስታ መዘን፥
ሀዘን ገዘገዘን...

እንዴት?

ላሳለፍነው ተድላ
ጉድ እስከሚለን ሰው፤
ምን ክፉ በቅሎ ነው
ውዴታውን ትተን ስህተት የም'ነቅሰው?

እንዴት?

ሰይጣን ገዘፈብን
ፈጣሪ ኮስሶ፤
ነቅንቀን ዘመመ
የቤቱ ምሰሶ...

ለቆፈን ገላችን
ሙቀት ላያዘልቀው፤
እንዴት ነው ጎጆዋችን
ተቃጥሎ የሞቅነው?

እንዴት?

ላጠፋነው ሁሉ
ለጠፋብን ነገር፤
አደላድሎን ኖሮ
ለሰበርነው ወንበር፤
በአንድ አቆራኝቶ
ፍቅር ከፍ አድርጎ ላቀናጀን መንበር፤
እልህ ገፍቶን እንጂ
ላሳለፍነው ሁሉ እርቅ አያንስም ነበር።

....ይቅርታ....

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)

@getem
@getem
@paappii
በህልሞቼ ታዛ
ስር በመኖርህ አንተ
ሴትነቴ ሁሉ
በፍቅርህ ማደሪያ ስለተከተተ፣
ከእኔ እየቀደመ
አመት ነው እሚያረጅ
ዘመነ ነው የባተተ።

@getem
@getem
@paappii

#Elsa mulugeta
ንገሪኝ ካልከኝስ💔

ደረቅ፣ግትር፣ጨካኝ ልብ የለሽም አልከኝ
ድንጋይ መሆኔንም በሰዉ አስነገርከኝ
አዎ ነኝ ይግረምህ
እረግጠሀኝ ብትሄድ ምትህ እንዳይገባኝ
አንስተህ ብትጥለኝ ዉስጤን እንዳትጎዳኝ
በሚያማምር ቃላት ልቤን አረስርሰህ
ደርሰህ እንዳታደማኝ
በጥርስህ እየሳክ ልቤን እንዳትወጋኝ
አይዞሽ አይዞሽ ብለህ ሂጅ ጥፊ እንዳትለኝ
ወደድኩሽ እያልከኝ ፍቅሬን እንዳትቀማኝ
ድረሺልኝ ብለህ አልይሽ እንዳትል
በሳቅህ እኔም ስቄ
በደስታህ ቦርቄ
ሲከፋህ አልቅሼ
ስታዝን ሳይ ደሞ ማቅ አመድ ለብሼ
ስኖር እኖርና.................
ድንገት ብትቀየር
ሳቄ ጣዕሙን ያጣል
ሀዘኔ ያስቃል
ደስታዬ ያስለቅሳል
ለቅሶዬ የደስታ መገለጫ ይሆናል
እና በአጠቃላይ ትርጉሜ ይጠፋል
እናምልህ ስማኝ
እህ ብለህ አድምጠኝ
ይህ ዝርክርክ ልቤን በደምብ ስለማቀዉ
ለዛ ነዉ ደንድኜ በሩን የማልከፍተዉ
አንዳንድ ልጆች አሉ
አንኳክተዉ መሮጥን ጀግንነት ያስባሉ።

በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ


@TIZITA21
@TIZITA21
@getem
@getem