#የት አባቱ#
"""''"''''''"""''''''''''''''''
ስትቀርበው ከራቀ
ስትሰጠው ከሰረቀ
ስትይዘው ከለቀቀ
ስትክበው ካፈረሰ
ስታፀድቀው ካረከሰ
ስታለብሰው ካራቆተ
ስታርመው ካሳሳተ
.
.
.
አትለምነው እንዲ አይነቱን
ይብቃ እሰረው ቀረጢቱን።
ገመድክን የዝምድና
አትቋጥረው በልመና።
ያቀረብከው ካልሆነልክ የሰው ብርቱ
ፍታው ተወው ጥንቅር ይበል
የት አባቱ።
#ሄኖክ#
@getem@getem