ጠፍተናል እንደውም
(ከ Pablo Neruda "We Have Lost Even " ግጥም የተተረጎመ )
ምድር - ሰማያዊ ምሽት ደርባ ፣
እጅ ለእጅ ተያይዘን በሰው አይን ሳንገባ ፣
ከቶ ማንም ልብ ሳይለን ፣
ፅልመት መሃል ጠፋን ቀልጠን ፣
በመስኮቴ ወዲያ ማዶ - ከግዑዙ ተራራ አናት ፣
ይታየኛል የ'ጣይ ግባት - የሽኝቷ ውብ ትዕይንት ፣
አንዳንዴ -
ጀንበር ጠፈር ላይ ተኩላ እንደ ደማቅ የእሳት ድቡልቡል ፣
መዳፌ መኻል እንዳለ-
ትንሽ የሳንቲም ዲናር ቀልጦ መሰወር ሽታ ነዳ ስትንበለበል ፣
ጥንት ታውቂው በነበረ የነፍሴ ጥልቅ ሃዘን መኻል ፣
አንቺን የእኔን ንግስት ሊያስታውስሽ ልቤ ይተጋል ፣
ለምን መራቅሽ ሲሰማኝ ፣
ሳዝን ጠብቆ ሊያጠቃኝ ፣
ናፍቆትሽ ከእኔ ተገኘ ?
ትውስታሽ ቤቴን ጎበኘ?
ፍቅርሽስ ስለምን ብሎ በእኔ ላይ እንዲህ አየለ ?
አሁን ወዴት ሆነሽ ነው? -
ማነውስ ማታ አብሮሽ አድሮ ቀኑን ከጎንሽ የዋለ?
ይሄው አመሻሹ -
ሁል ጊዜ እየመጣ ታሪኩን ቀጥሎ መፅሃፉን ይሞላል ፣
ገመምተኛሽ ግና አናቱ ተረግጦ ዛሬም ይማስናል ፣
ሰአቱን ጠብቆ ዘወትር ያዘግማል ፣
አንቺ ወደሄድሽበት ወደዛ ጨለማ ፣
የአመሻሹን ድባብ ከል ወዳለበሰው የምሽቱ ግርማ ።
@getem
@getem
@paappii
#elsa mulugeta
(ከ Pablo Neruda "We Have Lost Even " ግጥም የተተረጎመ )
ምድር - ሰማያዊ ምሽት ደርባ ፣
እጅ ለእጅ ተያይዘን በሰው አይን ሳንገባ ፣
ከቶ ማንም ልብ ሳይለን ፣
ፅልመት መሃል ጠፋን ቀልጠን ፣
በመስኮቴ ወዲያ ማዶ - ከግዑዙ ተራራ አናት ፣
ይታየኛል የ'ጣይ ግባት - የሽኝቷ ውብ ትዕይንት ፣
አንዳንዴ -
ጀንበር ጠፈር ላይ ተኩላ እንደ ደማቅ የእሳት ድቡልቡል ፣
መዳፌ መኻል እንዳለ-
ትንሽ የሳንቲም ዲናር ቀልጦ መሰወር ሽታ ነዳ ስትንበለበል ፣
ጥንት ታውቂው በነበረ የነፍሴ ጥልቅ ሃዘን መኻል ፣
አንቺን የእኔን ንግስት ሊያስታውስሽ ልቤ ይተጋል ፣
ለምን መራቅሽ ሲሰማኝ ፣
ሳዝን ጠብቆ ሊያጠቃኝ ፣
ናፍቆትሽ ከእኔ ተገኘ ?
ትውስታሽ ቤቴን ጎበኘ?
ፍቅርሽስ ስለምን ብሎ በእኔ ላይ እንዲህ አየለ ?
አሁን ወዴት ሆነሽ ነው? -
ማነውስ ማታ አብሮሽ አድሮ ቀኑን ከጎንሽ የዋለ?
ይሄው አመሻሹ -
ሁል ጊዜ እየመጣ ታሪኩን ቀጥሎ መፅሃፉን ይሞላል ፣
ገመምተኛሽ ግና አናቱ ተረግጦ ዛሬም ይማስናል ፣
ሰአቱን ጠብቆ ዘወትር ያዘግማል ፣
አንቺ ወደሄድሽበት ወደዛ ጨለማ ፣
የአመሻሹን ድባብ ከል ወዳለበሰው የምሽቱ ግርማ ።
@getem
@getem
@paappii
#elsa mulugeta
[ሰካራም እይታዎች]
---------------------------
ይህቺ የኛ ህይወት፣
ከደቦ እይታችን፥ ከመንጋ ሃሳባችን የተገነባች ናት፣
ማለዳ_
ከግዙፉ ባህር ከሰፊው ውቅያኖስ፣
መረብ ጥለን ነበር ገዳችን ቢቀና እልፍ አሳ ለማፈስ፣
ስንታክት ውለን፣
ስንባዝን ደክመን፣
ጀንበር ስትዘቀዝቅ መረቡን ሰብስበን፣
ውስጡን ብናስተውል፣
እጃችን ዛለ እንጂ አንድ እንኳ አሳ የታል?
በዚያ ሰፊ ውቅያኖስ በታላቁ ባህር፣
ጨለማው አይሎ ምሽቱ ቢጀምር፣
ከመካከላችን 'ካንዱ ሰው በስተቀር፣
ወደ ቤቱ የገባ ሌላ የለም ነበር፣
ያ ሰው_
'የእይታዬ ጥልቀት ከጀንበሯ ብርሃን ተሰርቷል' የሚለው፣
ብርሃን በምትሰርቅ በጨረቃ ጉልበት ከቶ ያልተማመነው፣
ንጋት እስኪመጣ መረቡን ሰባስቦ ጥሎን ገባ ጎጆው፣
እኛ ግን ሳቅንበት፣
በድኩም እይታው እጅግ አሾፍንበት፣
ወዲህም ጨረቃ፣
ያለ የሌላትን የሌባ ብርሃኗን ሰጥታን ስታበቃ፣
በእርሷ እየተመረን በደቦ እይታችን ሃይቁን የቃኘነው፣
በአሶቹ ምትክ እልፍ አእላፍ ከዋክብት ባህሩ ላይ ፈሰው፣
ነበር ያስተዋልነው፣
እኛም በፊናችን በሃይቁ የፈሰሱ ኮከቦች ለማጥመድ ስንታትር ስንለፋ፣
ከመሃከላችን ነፀብራቅ ነው የሚል አንድ እንኩዋን ሰው ጠፋ።
@getem
@getem
@paappii
#Elsa mulugeta
---------------------------
ይህቺ የኛ ህይወት፣
ከደቦ እይታችን፥ ከመንጋ ሃሳባችን የተገነባች ናት፣
ማለዳ_
ከግዙፉ ባህር ከሰፊው ውቅያኖስ፣
መረብ ጥለን ነበር ገዳችን ቢቀና እልፍ አሳ ለማፈስ፣
ስንታክት ውለን፣
ስንባዝን ደክመን፣
ጀንበር ስትዘቀዝቅ መረቡን ሰብስበን፣
ውስጡን ብናስተውል፣
እጃችን ዛለ እንጂ አንድ እንኳ አሳ የታል?
በዚያ ሰፊ ውቅያኖስ በታላቁ ባህር፣
ጨለማው አይሎ ምሽቱ ቢጀምር፣
ከመካከላችን 'ካንዱ ሰው በስተቀር፣
ወደ ቤቱ የገባ ሌላ የለም ነበር፣
ያ ሰው_
'የእይታዬ ጥልቀት ከጀንበሯ ብርሃን ተሰርቷል' የሚለው፣
ብርሃን በምትሰርቅ በጨረቃ ጉልበት ከቶ ያልተማመነው፣
ንጋት እስኪመጣ መረቡን ሰባስቦ ጥሎን ገባ ጎጆው፣
እኛ ግን ሳቅንበት፣
በድኩም እይታው እጅግ አሾፍንበት፣
ወዲህም ጨረቃ፣
ያለ የሌላትን የሌባ ብርሃኗን ሰጥታን ስታበቃ፣
በእርሷ እየተመረን በደቦ እይታችን ሃይቁን የቃኘነው፣
በአሶቹ ምትክ እልፍ አእላፍ ከዋክብት ባህሩ ላይ ፈሰው፣
ነበር ያስተዋልነው፣
እኛም በፊናችን በሃይቁ የፈሰሱ ኮከቦች ለማጥመድ ስንታትር ስንለፋ፣
ከመሃከላችን ነፀብራቅ ነው የሚል አንድ እንኩዋን ሰው ጠፋ።
@getem
@getem
@paappii
#Elsa mulugeta
👍27❤4🤩3