ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
ሰብዓ ሰገል በኮከቡ መሪነት ጌታችንን ካገኙ በኋላ ይዘውት የመጡትን ስጦታ ከመስጠት በተጨማሪ እኛ ሁላችን በሙሉ ደስታ ለምንሰግድለት ጌታ ሰግደውለታል።

እነዚህ ሰዎች ለሕጻኑ ሲሰግዱ በወቅቱ በዚያ ሥፍራ ላይ ስግደት የሚገባቸው ሌሎች ሰዎች ስላልነበሩ ለማንም አልሰገዱም።

ምናልባት በወቅቱ ከነበሩት ሰዎች ስግደት የሚገባው አካል ኖሮ እነርሱ ግን ሳይሰግዱ የቀሩ ከሆነ የመጀመሪያዎቹ መናፍቃን እነርሱ ናቸው ማለት ነው።

መጽሐፉ እንደሚነግረን የሰገዱት ለእርሱ ብቻ ነው። በእርግጥም ስግደት የሚገባው እርሱ ብቻ ነውና ለእርሱ ብቻ ለመስገድ የወሰናችሁ እውነተኛውን አምልኮ እየፈፀማችሁ ነውና በርቱ!!


(የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 2)
----------
9፤ እነርሱም ንጉሡን ሰምተው ሄዱ፤ እነሆም፥ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ ባለበት ላይ መጥቶ እስኪቆም ድረስ ይመራቸው ነበር።

10፤ ኮከቡንም ባዩ ጊዜ በታላቅ ደስታ እጅግ ደስ አላቸው።

11፤ ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ #ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም #ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም #አቀረቡለት

@gedlatnadersanat
@gedlatnadersanat