ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
ዘመነ ኔሮን ቄሣር፣ ዘመነ ዲዮቅልጥያኖስ፣ ዘመነ ድምጥያኖስ፣ ዘመነ አብርልዮስ፣ ዘመነ ትራጃን፣ ዘመነ ቨሌርያን፣ ዘመነ ግኖስቲክ፣ ዘመነ .....አልፏል። ራሷ ክርስቶስ ሞቶ እንዳሸነፈ አካሉ ቤተክርስቲያንም ታሸንፋለች።

#አንዲት_ቤተ_ክርስቲያን
#አንድ_ሲኖዶስ
#አንድ_ፓትርያርክ
#eotc_one_holy_synod
#one_church
#one_patriarch
#his_holiness_abune_mathias
#oriental_orthodox

"ሐዋርያት በሰበሰቡአት በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን" ጸሎተ ሃይማኖት

ጸልዩ በእንተ ፓትርያርክነ አባ ማትያስ!!
ይድረስ ለተዋሕዶ ሃይማኖት እናታችን ለእምዬ ማርያም።እንደምን አለሽ? አንልም።የሚሰግዱልሽ መላእክት፣የወዳጆችሽ የቅዱስ ኤፍሬምና የቅዱስ ሕርያቆስ በረከት ይደርብንና በኃጢአታችን ብዛት እንዳዘንሽብን እናውቃለን።ዛሬ በሰማይ በምድር በሚደረግ በዓልሽ እጅግ ደስ ይለናል ለእኛ ለኃጥአን መድኃኒታችን ነሽና!!!

እመቤታችን ዐረፍሽን?የአንቺስ ዕረፍት ልዩ ነው።ሁሌም ሲያስደንቀን ይኖራል።ወዳጅሽ ያሬድ ተደንቆ "ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐፅብ ለኩሉ" (ሞትስ ለሟች ይገባል የማርያም ሞት ግን ለሁሉ ይደንቃል) ያለው ለዚህም አይደል!!!የአንቺ ዕረፍት ለሁላችን ቤዛ መሆኑን ከልጅሽ ስትሰሚ "አንዴ ሳይሆን ሰባት ጊዜ ልሙት" ያልሽበትን ርኅራኄ መቼም አንረሳውም።ታውፉንያስ ቢሆን ቅዱስ ሥጋሽን ለማቃጠል ሲዳፈር መልአከ እግዚአብሔር እጆቹን ከቆረጣቸው በኋላ በለመነሽ ጊዜ እጆቹን በቸርነትሽ መመለስሽን እንዴት እንረሳዋለን?!

እምዬ ለተጠማ ውሻ በወርቅ ጫማሽ አጠጣሽ እኮን!!!ምን ከውሻ በክብር ብንበልጥም ግብራችን ግን ከአውሬ ከፍቷልና እናታችን ይቅር በይን!!!አንቺ ከጠለ ምሕረትሽ ያላረሰረስሽው ሰው ዋጋ የለውምና እናታችን ራሪልን!!!የልጅሽ ቅድስትና አንዲት አካል የሆነች ክብርት ቤተክርስቲያን ላይ የሆነውን ምን እነግርሻለሁ?በበዓለ ዕረፍትሽ አሳርፊን እንጂ!!!

እምዬ ማርያም ለልጅሽም እንዲህ በይልን!!!"በኃጢአታችን ከሰደቡህ ፈሪሳውያን ከሰቀሉህም አይሁድ ጋር እንዳበርን እናውቃለን።እጆቻችንም ለጸሎት በአንተ ፊት እዳይዘረጉ ሰልለዋል።ዓይኖቻችንም "ዐይን ሁሉ ተስፋ ወደሚያደርጉህ" ወዳንተ እዳያንጋጥጡ ዓለምንና ምኞቱን በማየት ፈዝዘዋል።በቃ እንዲሁ ይቅር በለን!!!እንዲሁ ማረን!!!እንዲሁ ራራልን!!!የእናትህን ንጹሕ ልብና ቅዱሳት እጆቿን ተመልከት!!!ከአንተ ጋር የደረሰባትን ጭንቅና ከብሩሃን ዓይኖቿ የፈሰሰውን መሪር ዕንባ አስብ!!!

አደራ በምድር አደራ በሰማይ!!!

ኢዮብ ክንፈ !!!

አስተርዕዮ ማርያም/2015 ዓ.ም
Forwarded from Eyob kinfe
እኔም አሳርፋችኋለሁ.aac
16.5 MB
የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel
Watch "🔴 አዲስ ዝማሬ "መድኀኒታችን ነሽ" ዘማሪ ዳዊት ክብሩ @-mahtot" on YouTube https://youtu.be/O2vyMH5NbX4
ሰምቶ በማሰማት #ለብዙዎች_ማረፊያ ሁኑ !
__________    #ዳዊት በገናን በደረደረ ጊዜ በሳኦል ያደረ ክፉ መንፈስን እያራቀ ሳኦልን ያሳርፈው ነበር።     
      #ይህው ዛሬም በጥዑም ኦርቶዶክሳዊ ለዛው ዝማሬዎችን በየ ዓይነቱ እየደረደረ ጸላዔ ሰናያት የሆነ የዲያቢሎስ ማደሪያዎችን እየጎሰመ በቀናች የሃይማኖት ወደብ ያሳርፉቸው ዘንድ ይዞል።
           |1ኛ #ሳሙ 16፥23
#ድንግል ሆይ አዎን  " #መድኃኒታችን_ነሽ "
" #ኢትዮጵያዊው_ኤልሳዕ
#በአጽሙ_ሙት_ያስነሳ "
_
፪ኛ ነገሥት ፲ ፫÷፳ -፳ ፩
ገ/ተ #ሃይማኖት ም/፶ ፫

አጥንት በመጻሕፍ ቅዱስ ውስጥ በምሳሌነት ሲጠቀስ ሦስት ነገሮችን ያመለክታል።
፩ የሰው ኃይልን ያመላክታል መዝ ፶ ፫፥፭ ኢሳ፴ ፰፥፲ ፫
፪ የቅርብ ዝምድና መግለጫ ሆኖ ቀርቧል ዘፍ ፳ ፱÷፲ ፬ ሳሙ ፱÷፪
፫ የሞተ ሰውን ክብር ያስረዳል ዘፍ ፶÷፳ ፭ ዕብ ፲ ፩÷፳ ፪
#ይበልጡኑ_የቅዱሳን_ሰዎች ሞት /አጥንት (አጽም)/ እጅግ የከበረ ነው ። መዝ ፻ ፲ ፭ (፻ ፲ ፮) ÷፲ ፭ ለአብነትም ተቀብሮ የነበረው የኤልሳዕ አጥንት /አጽም/ ሌላ የሞተ ሰው ከሞት እንዳስነሳ መመልከት በቂ ነው። ከሞዓብም አደጋ ጣዮች በየዓመቱ ወደ አገሩ ይገቡ ነበር።ሰዎችም አንድ ሰው ሲቀብሩ አደጋ ጣዮችን አዩ፥ ሬሳውንም በኤልሳዕ መቃብር ጣሉት፤ የኤልሳዕንም አጥንት በነካ ጊዜ ሰውዮው ድኖ በእግሩ ቆመ። ፪ኛ ነገሥት ፲ ፫÷፳ -፳ ፩
በተመሳሳይ ኢትዮጵያዊው ኤልሳዕ ጻድቁ አባታችን ተክለ ሃይማኖትም የሥጋ ድካም ከትጋቱ እንዳያስታጉለው በስምንት ሰለታም ጦር እራሱን ከቦ ከደብረ አስቦ ዋሻ ከቆመ ሳይቀመጥ ከዘረጋ ሳያጥፍ ፳ ፪ ዓመት ሲጋደል ሳለ ከመቆም ብዛት አንዲቷ የእግሩ አገዳ ተሰበረችና ከሰውነቱ ተለይታ ወደቀች።
#ደቀ_መዛሙርቱም እንደ ማንም መስሏቸው ስባረ እግሩን ከመቃብር ሥፍራ ወረወሯት የኤልሳዕን አጽም ሲነካው ከሞት ድኖ እንደተነሳው ሰው የአባታችን የእግራቸው አጥንት የነካው በመቃብሩ ሥፍራ ተቀብሮ የነበረ አንድ ሰው አፈፍ ብሎ ድኖ በእግሩ ቆመ ። ገ/ተ ሃይማኖት ፶ ፫
የአባታችንንም ስባረ አጽም (ስባረ እግር) እያመሰገነ ሰላምታ ሰጠ " ይህን ያዮ ደቀ መዛሙርቶቻቸውም የጻድቁ ስባረ አጽም ገባሬ ተአምራት መሆኗን አውቀው ከመንበሩ እግር በታች አክብረው በሰበን ጠቅልለው ቀብረዋታል::
" #የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው፥ እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል። እግዚአብሔር አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል፥ ከእነርሱም አንድ አይሰበርም። " መዝ ፴ ፫{፴ ፬}÷፲ ፱-፳ ይህ የቅዱሳን አጥንት (አጽም) እግዚአብሔር የማይለየውና ሌት ተቀን የሚጠብቀው ነውና ቅዱሳን ጻድቃን ካረፉበት ሄዶ መሳለም በረከትን ያሰጣል ከሥጋም ከነፍስም ህመም አድኖ በጤና ያቆማልና የአጽማቸውን በዓል ማክበር እጅግ የሚገባ ነው ::
ቅዱስ ጳውሎስ በልብሱ ጨርቅ " (ሐዋ፲ ፱÷፲ ፩-፲ ፪) ቅዱስ ጴጥሮስ በሰውነቱ ጥላ ድውያንን ሁሉ ይፈውሳቸው ነበር ። ( ሐዋ ፭÷፲ ፭ ) ቅዱሳን የነፍሳቸው ቅድስና ለሥጋቸው፣ የሥጋቸው ቅድስና ለለበሱት ልብስና ለአካላቸው ጥላ ተርፎ ድንቅ ተአምራትን የሚሰራ ከሆነ እግዚአብሔር የሚጠብቀው አጽማቸውማ እንዴት አብልጦ ድንቆችን አይሰራ?!::
#አጥንት_ለሰዉ ልጅ ተክለ ሰውነት ወሳኝ ድርሻ አለው። ከሚሰጣቸው ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች መካከል የተወሰኑት ብንዳስስ፤ ለሰዉነታችን ቅርፅ ለመስጠት፣ የሰዉነት የውስጥ አካላት (Organs) ከአደጋ ለመከላከል #ለምሳሌ ደረት የሚያርፍበት ክፍለ አጥንት ለሳንባና ለልብ ከለላ(covering) ይሰጣል፤ የራስ ቅል አጥንት አንጎል ምንም አይነት ጉዳት እንዳይገጥመው ጠንካራ ልባስ ሆኖ ይከላከላል ፣ ሥጋና ጡነቻዎቻችንን አጣብቆ ለመያዝና የካልስየም ንጥረ ነገርን ለማጠራቀም ይረዳል፡፡
ክቡር የሆነ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖትም ለቀናች ሃይማኖቱ አጥንት ነው። አጥንት የሌለው አካል ጤፍ እንደሌለው ማዳበሪያ መቆም አይቻለሁም:: ሀገሪቱና ቤተክርስቲያኒቱ ዶግማ ቀኖናና ትውፊቷን ይዛ ቅርጻን ሳትለቅ ቀጥ ብላ እንድትቆም አድርጓታልና።
# ምዕመኗ ልዮ ልዮ በሆነ በእግዳ ትምህርት ከበረትቷ እንዳይኮበልሉ ኖላዊ ትጉሁ ሆኖ
በጾም በጸሎቱ የሀገር ዋልታ በመሆንም አካል ለምትባል ቅድስት ቤተክርስቲያን እንደ
አጥንት ጋሻ፣ መከታ፣ ጥላ ፣ከለላ ሆነላት።
የሃይማኖት ማነስ የምግባር ጉድለት እንዳያጋጥማትም በቃሉ ትምህር በእጁ ተአምራት
በበረከቱ ሞላት፤ በረድኤቱ ጋረዳት እንደ አጥንት የሃይማኖት መፍሰሻ ነቅ የወንጌል
መፍለቂያ ምንጭም አደረጋት።
#የምታበረታ_አጥንት_በረከቱ_ትደርብን ! #አሜን!!

ኃ/ማርያም አ.አ ኢትዮጵያ
ጥር ፳ ፬\፳ ፻ ፲ ፫ ዓ.ም
" የታላቂቱ ከተማ ጾም"
የታላቂቱ ከተማ የነነዌ ኃጢያት ከመብዛቷ የተነሳ እግዚአብሔር ፊት ደረሰች ።ት.ዮና ፩÷፪ ነቢዮ ዮናስ ሄዶ በዛች በታላቂቁ ከተማ በነነዌ እንዲሰብክ #እግዚአብሔር ላከው የዋህው ዮናስም #እግዚአብሔር መሐሪ ነው በኃላ ሄጄ ካልተመለሳችሁ ከሰማይ እሳት ወርዳ ትበላችዋለች ብዬ ከሰበኩ በኃላ ቢምራቸው እኔ ሐሰተኛ ነቢይ እባላለው ብሎ ወደ ነነዌ መሄድ ትቶ ወደ ተርሴስ በመርከብ ተሳፍሮ ኮበለለ።
አዳም እጸ በለስን ከበላ በኃላ ከእግዚአብሔር ፊት ለመደበቅ ሞክሮ ነበር እግዚአብሔር አምላክም እንደ አባት ነውና እንዳይሳቀቅበት አንድም በኃላ ዘመን አላዋቂ የሰው ሥጋን ተዋህጄ አድንሃለው ሲለው ባላዋቂ ልማድ ከፊቱ የተሰወረበት ይመስል " አዳም አዳም ሆይ ወዴት አለህ " ሲል በፍቅር ጠይቆት ነበር።
አበው " #እግዚአብሔር አምላክ ሞኝ ነጋዴን ይመስላል መንግስተ ሰማያትን የምታክል ውድ ነገር በጥርኝ ውኃ ልስጣችሁ ብሏልና" ይላሉ ማቴ ፲ ÷ ፴ ፱ የዋህው ዮናስ ይህን ብሒለ አበው ሳይሰማ የቀረ አይመስልም እግዚአብሔር እንደ ሞኝ ቆጥሮ አካሄዱንም እንደማያውቅበት አስቦ ከፊቱ ኮበለለ ።

የዳዊትን መዝሙር ያልሰማህ ይህ አይሁዳዊ ሰው ምነኛ የዋህ ነው።
"ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ?
ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ?
ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤
ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ።
እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥ በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች።በውኑ ጨለማ ትሸፍነኛለች ብል፥ ሌሊት በዙሪያዬ ብርሃን ትሆናለች፤ ጨለማ በአንተ ዘንድ አይጨልምምና " #መዝ ፻ ፴ ፰(፻ ፴ ፱) ÷ ፯-፲ ፩

እግዚአብሔር ግን የተሳፈረበትን ታንኳ በማዕበልና በሞገድ አስጨነቃት ይህም ሁሉ በእርሱ ምክንያት እንደሆነ ለመረከበኞቹ ነግሮ እርሱን ወደ ባሕር ቢጥሎት በጸጥታ መጓዝ እንደሚችሉ ገለጠላቸው ። ባንተ በእግዚአብሔር ሰው ላይማ ይህን አናደርግም ባይሆን ዕጣ እናውጣ ተባባሉ ዕጣውም ሲወጣ ለሦስት ጊዜ ያክል በዮናስ ላይ ደረሰበት ወደ ባሕሩም ጨመሩት ወዲያውም ታላቅ ዓሳ አንበሪ ከእግዚአብሔር ታዞ ዮናስን ዋጠው መንገዱንም ከተርሴት ወደ ነነዌ ሀገር ቀየረው ነነዌም ሲደርስ ከደረቅ የብስ ላይ አውጥቶ ተፋው “ከሰው ይልቅ #የእግዚአብሔር ሞኝነት ይጠበባልና፥ ” ፩ኛ ቆሮ ፩፥፳ ፭

ዮናስም የእግዚአብሔር ሥራ እያደነቀ ወደ ነነዌ ከተማ ገብቶ ንስሐን ፣ጾምን፣ ጸሎትን ሰበከላቸው ካልተመለሱ ግን የእሳት ዲን እንደሚበላቸውም አስጠነቀቃቸው ነነዌም ሰማች ወደ ልቧም ተመለሰች ንጉሱም ህጻናትና የሚጠቡ ልጆች ሳይቀሩ የእናታቸውን ጦት እንዳይጠቡ እንሰሳትም ቢሆኑ እስከ ሦስት ቀን ድረስ አፋቸው ታስሮ ከምግብ ተከልክለው እንዲቆዮ የጾም አዋጅ አወጀ። ከሦስት ጾም ቀናት በኃላ እግዚአብሔር ለነነዌ ምሕረትና ይቅርታ አደረገላት።
በዚህም ከሰማይ ይመጣባቸው የነበረ የእሳት ዲን ቀረላቸው ነቢዮ ዮናስም ይህው እግዚአብሔር ማራቸው እሳቱም ቀረላቸው። ስለዚህ እኔ የታለ እሳቱ ?ውሸታም እባላለው ብሎ ሰጋ እግዚአብሔር አምላክ ግን ቅዱሳኑ ዝቅ ብለው እሱ ይከብር ዘንድ ሰው አይደለምና ዮናስም አልዋሸም ባትመለሱ ይበላችሁ ዘንድ ያለው እሳት ይህቺ ነበረች ሲል ለምልክት እሳት ከሰማይ አውርዶ የነነዌን ከተማ እረጃጅም ዛፎች ጫፎቻቸውን አቃጥላ ተመልሳ እንድትሄድ አድርጓል ።

ባትመለሱ ኖሮ ወርዳ ትበላችሁ ነበር ሲል ነው። ዛሬ ዳግማዊቷ ነነዌ ኢትዮጵያ እሳቱ ወርዶ እየለበለባት ነው። ዘረኝነቱ እሳት ነው፣ የሥልጣን ሽኩቻው እሳት ነው፣ እምነት የለሽነቱ እሳት ነው... ግን ዛሬም አልተመለሰችም ዮናሶቿም ስደት፣ ሽሽትን መርጠው ከሩቁም ሆነው የወደፊቷን ይተነቢዮላት ዘንድ ወደዋል። መቆስቆስ ቀላል ነው መማገድ ግን መንደድን በኃላም አመድ መሆንን ያስከፍላል።
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
አ.አ ኢትዮጵያ
የካቲት፲፬/፳ ፲፫ዓ.ም
" የሰማዕታት ደም የክርስትና ዘር ነው ! "
#ሊቁ ጠርጡለስ
ዘር ጥቂት ሆኖ ወድቆ ብዙ እንደሚያፈራ የአንድ ክርስቲያን ደም መፍሰስም የብዙ ክርስቲያኖች መብቀል ነው ! በተገደልን ቁጥር (ሕያው እንሆናለን) እንበዛለን !
" #ወንድሜ ንጹዑ ደምህ በመንገድህ ሕያው ታድርገኝ"
Channel photo updated
"ለሦስት ቀን ነነዌ ላይ እንድናደርገው የታዘዝነው ሐዘንና ሱባኤ በንስሐና በዕንባ ሆነን የእግዚአብሔርን መልስ ለማግኘት ነው። አስተውሉ:: የዐለም መንግሥታት እንዲያዩን ሳይሆን የዐለም ፈጣሪ እንዲያየንና እንዲሰማን ነው። ለአክቲቪዝም ፣ ለፕሮፓጋንዳና ለብሽሽቅ ሳይሆን ልብን በእግዚአብሔር ፊት ለማዋረድና ከእርሱ እርዳታን አግኝተን ለመመለስ ነው። ልብስ ቀይረን ወደ ምሕላ የምንሔድበትን ዓላማ ለአፍታም ቢሆን መርሳት የለብንም...እግዚአብሔር የቲፎዞ፣ የብሽሽቅ፣ የሽንገላ፣ የማስመሰልና በአጠቃላይ ምድራዊ በሆኑ ነገሮች የታጀበን ነገር አይቀበልም። ጾም ጸሎታችንን እንዳናበላሸው እንጠንቀቅ። ከለፍላፊነትና ከተሳዳቢነት በሽታም እንፈወስ... ትኩረታችን ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት ላይ መሆን አለበት ። "

ዲያቆን ብርሀኑ አድማስ

#ኢንፈርህ_ሞተ
#ሞትን_አንፈራውም
#ጸልዩ_በእንተ_ቤተክርስቲያን_ቅድስት
#ሚተራሊዮን ወቅታዊ
| "የሚገባ   አመጽ "
  
Audio
ዐውደ ምሕረት
Audio
ርዕስ   :-   #ሚተራሊዮን
ደራሲ  :- #ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ
ምዕራፍ :- #23
ተራኪ   :-  #ተርቢኖስ ሰብስቤ
#ዐውደ_ምሕረት_የእናንተ 🙏
_°°°°°°°°°°°___
#እኛ_አባቶቻችንን እንሰማለን እንታዘዛቸዋለንም !
|ድምጻቸውን እናውቀዋለንና
#ዮሐ 10÷3-5
አ.አ ልደታ ማርያም /ማኅደረ ስብሐት/ ቤ/ክ