Deleted Account
አንድ ሰው በተክሊል ማግባት የሚችል ወይም የምችል መቼ ነው? በምን ሁኔታስ ነው?
ተክሊል ማለት ከለለ አከበረ ከሚለው ግሥ የተገኘ ቃል ሲሆን ትርጓሜውም ክብር ማለት ነው። ተክሊል ምሥጢር ተብሎ መጠራቱ ሙሽራውና ሙሽሪት በግብር አምላካዊ አንድ የሚሆኑበት የጋብቻ ሥርዓት በመሆኑ ነው። ጋብቻ በቤተ ክርስቲያን ሲፈጸም ምሥጢርነት አለው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም "... ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው" ማለቱ ይህንኑ ያረጋግጥልናል።
#የተክሊል አፈጻጸም
እንደ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ /ሥርዓት/ ተክሊል ከሥርዓተ ቅዳሴና ከቅዱስ ቁርባን ጋር ተያይዞ የሚፈጸም ምሥጢር ነው። እንጂ ብቻውን አይፈጸምም። ጸሎተ ተክሊል ተደርሶ ቅዱስ ቁርባን መቀበል ከቀረ ግን ተክሊሉ ፍጹም አይደለምና ጋብቻው አይጸናም።
#ሥርዓተ ተክሊል ለማን ይፈጸማል?
ተክሊል የሚፈጸመው ንጽሕናዋን ጠብቃ ከወንድ እርቃ ለኖረች ጥብቅ ልጃገረድ ወይም በሥጋ ድንግልናዋን ለጠበቀች በተግባር ዝሙት ላልፈጸመች ኦርቶዶክሳዊ ሴት ነው። ሴትን በምንጣፍ ተገናኝቶ የማያውቅ ንጽሕናውን ጠብቆ ልኖር ኦርቶዶክሳዊ ወንድ ብቻ የሚፈጸም የጋብቻ መፈጸሚያ አይነት ነው። በአጠቃላይ ተክሊል ከሥጋዊ ድንግል ጋር አብሮ የሚሄድ ምሥጢር መሆኑን ቤተ ክርስቲያን የሥርዓት መጽሐፍቶች ሁሉ ተባብረው የሚመሰክሩት ጉዳይ ነው። ለምሳሌ ፍትሃ ነገስት እንዲህ ይላል ፦ "ይህ ተክሊል በጋብቻ ጊዜ ለድንግል ወንድና ለድንግል ሴት ይገባል።" ፍትሃ ነገስት 24:906 ከላይ ያነሳነው ሥርዓት ግን በደንብ ካልተብራራ ተክሊልን በተመለከተ የሚነሱትን ጥያቄዎች ከምንጫቸው ማድረግ የሚችል አይሆንም። ሰለዚህ በዚህ ምሥጢር ዙሪያ ለሚነሱት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እንድንችል ድንግልና እንደቤቱ ክርስቲያናችን አስተምህሮ እንዴት ይታያላል /ይብራራል/ የሚለውን በደንብ መመልከት ይገባል።
#ድንግልና ምንድን ነው?
ድንግልና የሚለው ቃል ተደነገለ ተጠበቀ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም መጠበቅ ማለት ነው። ድንግልና እንደ ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ንዑስ ሕዋስን /Hymen/ ለመግለጽ ብቻ ሳይሆን የንጽሕና አኗኗር ለማስረዳት አንድ ድርጊት መፈጸም ወይም አለመፈጸሙን ለማመልከት አገልግሎት ላይ የሚውል ቃል መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
ሰለዚህም አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ሴት ሥጋዊ የሆነው የድንግል ማሕተም ስላልፈረሰባት ብቻ ሥርዓተ ተክሊል መፈጸም ትችላለች ሌላኛዋ ኦርቶዶክሳዊት ደግሞ ሥጋዊ የድንግልናዋ ማሕተም ሰለፈረሰ ብቻ ተክሊል አይገባትም ማለት አይደለም። በቅድሚያ እዚህ ላይ ያለውን ውዥንብር መደንብ ለማጥራት በሴቶች ተፈጥሮ ውስጥ የሚገኘውን የድንግልና አይነቶችን ማየት ይጠቅማል።
#የሴቶች ድንግልና ተፈጥሮ ዓይነቶች
ማኅተመ ድንግልና ሴት ከወንድ ጋር ሩካቤ አድርጋ አለማወቋን የሚያስረዳ የሥራዋ መገለጫ የአኗኗሯ መታወቂያ ልዩ የተፈጥሮ ምልክትና የድንግልናዊ ኑሮዋ ዘውድ ነው። ይህ ተፈጥሮዊ ማኅተም በሴቶች አፈ ማኅፀን ቀለበት በሚመስል ስስ ሥጋነት በጉልህ ይታወቃል። ይህ ማለት ግን ሩካቤና ሰስሎተ ድንግልና /የድንግልና መወገድ/ የተለያዩና
ራሳቸውን የቻሉ ተግባራት መሆናቸውን መገንዘብ ይኖርብናል። አንዲት ሴት ማኅተመ ድንግልና ስላላት ብቻ " ሩካቤ አድርጋ አታውቅም" " ወይም ሩካቤ ስላደረች ማኅተመ ድንግልና ሊኖራት አይችልም። ብሎ ድምዳሜ ላይ መድረስ አለመቻሉን እንረዳለን። በዚህም የተነሳ የድንግልና አይነቶችን ከተክሊል ጋር እያዛመዱ መመልከት ያስፈልጋል። ለምሳሌ ወንዶች እንደ ሴቶች ተጨባጭና ጉልህ የድንግልና ምልክት ስለሌላቸው ከሴት ጋር ሩካቤ ፈጽመው የማያውቁ ሆነው ሳለ ደናግል አይደሉም ማለት አይቻልም። እንደዚሁ ሁሉ ሩካቤን ፈጽመው የማያውቁ ሴቶች የድንግልና ማኅተም ስለሌላቸው ብቻ ደናግላን
ከመባል አይከለከሉም። በሌላ አቅጣጫ ስንመለከት ወንዶች ሩካቤ ፈጽመው ሳለ እንደ ሴቶች የሚገሠሥ ማኅተመ ድንግልና ስለሌላቸው ድንግልናቸውን አልፈረሰም እንደማይባል ሁሉ ሴቶች ሩካቤ ሥጋ እየፈጸሙ በልዩ ልዩ ምክንያት ማኅተመ ድንግልናቸውን ባይገሠሥም መደበኛ ሩካቤ እስከ ፈጽሙ ድረስ ደናግል ሊባሉ አይችሉም። ለዚህም ነው ሰለድንግልና አይነቶች ማውራት አስፈላጊ ሁኖ የተገኘው ፦
#የድንግልና ዓይነት
የድንግልና መለያ ወይም ስስ የክብር ንጽሕና ሽፋን /Hymen/ ዓይነታቸው አራት ሲሆኑ በሁሉም ሴቶች ላይ የሚኖረው ዓይነት ምንም እንኳን በተፈጥሮ ተወስኖ የተፈጠረ ቢሆንም ግን ከግብረ ሥጋ ግንኙነት ውጭ ድንግልና የሚጠፋባቸው በርካታ ምክንያቶች ይኖራሉ። ይህም ከሴቶች የድንግልና ተፈጥሮ አንጻር ነው።
#አንደኛ ደረጃ_የድንግልና ማኅተም /Hymen/ ምልክቶች ፦ ይህ ድንግልና አይነት ያላቸው ሴቶች ንዑስ ሕዋስ የድንግልና ማኅተም ምልክቱ የሌላቸው ሲሆኑ እነዚህ ምንም እንኳን ከአጠቃላዩ ሴቶች ሲታይ ቁጥራቸው አናሳና አንዳንድ መረጃዎች እንደ ሚጠቁሙት ከሦስት እስከ አምስት በመቶ የማይበልጡ ቢሆኑም የዚህ አይነት ተፈጥሮ ባለ ድርሻ የሆኑ እህቶች የሠርጋቸውን የመጀመሪያውን የግብረ ሥጋ ግንኙነት ሲዳርጉ ምናሴም እንኳን ሕመም ቢሰማቸውም እንደሌሎቹ የድንግልና አይነቶች ያለ መድማታቸው አይነቱን የተለየ ያደርገዋል። ይህ አይነቱ ድንግልና ያላቸው ወጣት ሴቶች ምንም እንኳን ከጋብቻ በፊት የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጽመው የማያውቁ ራሳቸውን በቅድስናና በንጽሕና ጠብቀው የኖሩ ቢሆኑም ሆኖም ግን በጋብቻቸው ምሽት የመጀመሪያውን የግብረ ሥጋ ግንኙነት ሲፈጽሙ ደም ባለመታየቱ በባላቸው ዘንድ ተአማኒነት የሚያጡበት አሳዛኝ አጋጣሚ የሚከሰትበት አጋጣሚ አለ።
#ሁለተኛ ደረጃ የድንግልና ዓይነት፦ይህ የድንግልና አይነት በተፈጥሮ ያላቸው ሴቶች የድንግልና መለያቸው በጣም ስስነት ያለው ሲሆን እነዚህ አይነት ሴቶች በቁጥር ከአጠቃላዩ ሴቶች ከሃያ አምስት በመቶ ያላነሱ ናቸው። ይህ የድንግልና አይነት ከግብረ ሥጋ ግንኙነት ውጭ በተለያዩ የጥንቃቄ ጉድለቶች ሊወገድ የሚችልባቸውም አጋጣሚዎችም አሉ። በዚህ የድንግልና አይነት የሚኖሩ እህቶች ከባድ በሆነ አካላዊ እንቅስቃሴ ጥንቃቄ በጎደለው አለባበስ የተነሳ ሊወገድ ይችላል። እነዚህ እህቶች በሩካቤ ሥጋ ግንኙነት በዝሙት ተግባር ሳይገኙ ድንግልናቸውን ሊያጡት ይችላሉ።
#ሦስተኛው ደረጃ የድንግልና ዓይነት፦ ይህ የድንግልና ዓይነት መካከለኛ ደረጃ ውፍረት ያለው ሲሆን የድንግልና መለያ ምልክት በአብዛኛው ሴቶች ላይ ማለትም ከአጠቃላዩ ድንግልና ካላቸው ወጣት ሴቶች ከግማሽ በላይ በሚሆኑት ላይ የሚገኝ የድንግልና ማኅተም አይነት ነው። ይህ የድንግልና አይነት እስከ አሁን ካየናቸው የድንግልና ማኅተሞች በጥንካሬና በውፍረት የተሻለ ከመሆኑ በላይ ከግብረ ሥጋ ግንኙነት በስተቀር በሌሎች የጥንቃቄ ጉድለቶች ማለትም ጥንቃቄ በጎደለው ስፖርትና በመሳሰሉት የመወገድ ዕድሉ በጣም ዝቀተኛ ነው።
#አራተኛ ደረጃ የድንግልና ዓይነት ፦ ይህ የድንግልና አይነቶች ጽኑ የሚባል ነው። ከግብረ ሥጋ ግንኙነት ውጭ በሌላ በምንድን አይነት መንገድ የሚፈርስ የሚወገድ አይደለም። ተክሊል የሚገባት ሩካቤ ሥጋ ግንኙነት ፈጽማ ድንግልናዋ ላልፈረሰባት ሴት አይደለም። ይቺ ሴት ምንም እንኳን የሥጋ ድንግልናዋ ቢኖርም የዝሙት ተግባርን ፈጽማለችና ተክሊል አይገባትም። በተለይ አራተኛው የድንግልና አይነት ላይ የሚገኙ ጽን የድንግልና ማኅተም ያላቸው ሴቶች በመጀመሪያው የሩካቤ ሥጋ ግንኙነት የድንግልና ማኅተማቸው ላይወገድ ይችላል። ይህንን ሩካቤ ሥጋ ግንኙነት የፈጸሙት ከጋብቻ ውጭ ከሆነ ዝሙት ነውና የድንግልና ማኅተም አለኝ ተ

ክሊል ልፈጽም ብለው መጠየቅም አይገባቸውም። ምክንያቱም በጋብቻ ክልል ውስጥ ሊፈጽሙት የሚገባውን ሩካቤ ጋብቻ ሳይመሰርቱ አስቀድመው እግዚአብሔር በማይወደው የዝሙት ተግባር የሩካቤ ሥጋ ግንኙነት ፈጽመዋልና ተክሊል አይፈጸምላቸውም ተክሊል አይገባቸውም።
#ሰለዚህ ተክሊል የሚፈጸመው ንጽሕናዋን ጠብቃ ከወንድ እርቃ ለኖረች ጥብቅ ልጃገረድ ወይም በሥጋ ድንግልናዋን ለጠበቀች በተግባር ዝሙት ላልፈጸመች ኦርቶዶክሳዊ ሴት ነው። ከወንድ ጋር ሩካቤ ፈጽማ የሥጋ ድንግልናዋ ማኅተሙ ሰለአልፈረሰ ብቻ ተክሊል ይገባታል የሚል አስተምህሮ ቤተ ክርስቲያን የላትም።

https://tttttt.me/AwediMeherit
ተመዝግበዋል❓
ሳይነግሩኝ ተመዘገቡ ብለው ከወዳጆ እንዳይጣሉ❗️
👉ሥነ ፍጥረት 👉ባሕረ ሀሳብ
👉ነገረ ማርያም 👉ነገረ ቅዱሳን
👉ትምህርተ ሃይማኖት
👉የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
👉ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር
የመሳሰሉ መንፈሳዊ ኮርሶች በየሳምንቱ በድምጽ ባሉበት ሆነው የሚያማሩበት
❤በተጨማሪም
👉ምን እንጠይቅልዎ? ምዕመናን የፈለጉትን መንፈሳዊ ጥያቄ የሚጠይቁበትና መልስ የሚያገኙበት
👉እርሶ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ የመንፈሳዊ ውይይት ክፍለ ጊዜን ያካተተ ልዮ ቻናል
❤ #ሳይሞላብዎ_በቶሎ_ተቀላቅለው በነፃ ይመዝገቡ

Telegram
ዐውደ ምሕረት
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
#ባለጸጋው_ጎበዝ
እነሆም፥ አንድ ሰው ቀርቦ፦ መምህር ሆይ፥ የዘላለምን ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር ላድርግ? አለው።
#ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ፦ ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ ነው፤ ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ አለው።
#ጎበዙም ፦ የትኞችን? አለው።
#ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ፦ አትግደል፥ አታመንዝር፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥ አባትህንና እናትህን አክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው።
#ጎበዙም ፦ ይህንማ ሁሉ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ፥ ደግሞስ የሚጐድለኝ ምንድር ነው? አለው።
#ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም፦ ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ አለው።
#ጎበዙም :- ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ብዙ ንብረት ነበረውና እያዘነ ሄደ።
#እርሶ_ቢሆኑ_ምን_ያደርጋሉ ?
ሕግን ሁሉ ጠብቃችሁ ትዕዛዛትን ሁሉ ፈጽማችሁ በምድራዊ ሀብታችሁ ቢመጣ ምን ዓይነት ምላሽ ይሰጣሉ።
👉ለነፃ ሀሳቦ
👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
#ዓውደ_ምሕረት_የናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit

#የከበረ ዘር ማነው?
አንተ ሞኝ አማራ ነው! ፣ኦሮሞ ነው! ፣ ትግሬ ነው!፣ ጎራጌ ነው!፣ አረ ከንባታ ነው! የለም አድያ ነው? ትል ይሆናል ። ነገር ግን እነዚህ ሁሉ አይደሉም የከበረው ዘር "ሰው" ነው። እነዚያማ ሰዎች ልማዳቸውን ባህላቸውን ቋንቋቸውን የመሳሰሉ የዕለት ተዕለት አድራጎታቸውን ከቀደምቶቻቸው የወረሱበት የትውፊታቸው መገለጫ የሆነ ስመ ስያሜ ነው። አማራ ሥጋ የለችም ! ኦሮሞ ነፍስም አልተፈጠረችም ! ሁላችን ሰው ሆነን ተፈጠርን ሰው ሆኖ መኖርና ሰው ሆኖ መሞት ግን አቃተን።
የሰው ዘር የከበረ ዘር ነው:: የከበረ ዘር ማነው ? #እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ዘር አይደለምን?
የሰው ዘር የጐሰቈለ ዘር ነው ጐስቋላ ዘር ማነው? #የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የማይጠብቁ ሰዎች ዘር አይደለምን? መ.ሲራክ 10÷19-20
ለቀደሙት አትግደል እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል። #ማቴ 5÷21-22
በፖለቲካና በብሔር ሰበብ ክርስቲያን በመሆናችን ብቻ የምንፈናቀል እኛ የምንገደል እኛ ቤት ንብረታችን የሚወድም የእኛ የባለ ማዕተሞቹ ብቻ ነው።
ክርስትናን ዝም ብሎ በሰበብ በአስባቡ ማጥፋት አይቻልም !። ጠላት ይህን ቢያውቅ ኖሮ ዝናሩን ባልታጠቀ ቀስቱንም በከንቱ ባልጨረሰ ነበር። ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ። 1ኛ ጴጥ 1፥23
" #ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? #ስለ_አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው። የምገደለው ስለማን እንደሆነ እናውቀዋለን ስለ አንተ ስለ ማዕተማችን ነው! ስለ አንተ በክርስቶስ ክርስቲያኖች ስለመባላችን ስለ ስም ነው !
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።” #ሮሜ 8 ፥35_37