ዐውደ ምሕረት
3.67K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
Audio
record20180409101850
Unknown artist
#ሐዲስ_ሱራፊ_ተክለ_ሃይማኖት

#ሱራፊ ማለት መልአክ፣ ከካህናተ ሰማይ አንዱ ማለት ነው፡፡ ሱራፌን፣ ሱራፌል፣ ሱራፌም (በፅርዕ ሴራፊም፣ በዕብራይስጥ ስራፊም) ማለት የነገድ ስም፣ ልዑላን መላእክት፣ ሊቃናት፣ የሚያጥኑ፣ ካህናት፣ ቀሳውስት፣ ቀዳሾች ማለት ነው /ኪዳነ ወልድ ክፍሌ/ ከዚህ ላይ ሱራፊ ነጠላ ቍጥርን ሲያመለክት፤ ሱራፌል ደግሞ ብዙ ቍጥርን ያመለክታል፡፡ ሱራፌል ለቅዱሳን በሰው አምሳል በመገለጣቸው ሽማግሌዎች ተብለው ተጠርተዋል /ኢሳ.24፥23፤ መሳ.13፥2-25፤ /፡፡ በግእዝ ቋንቋ ደግሞ ካህናተ ሰማይ ይባላሉ፡፡ ካህናተ ሰማይ ሱራፌል ቁጥራቸው 24 እንደሆነ ባለ እራዮ ዮሐን ጽፎልናል ይህ ግን 24ሰዓት ያለ እረፍት የሚያመሰግኑ መሆናቸውን ለማመልከት የተጠቀመበት አገላለጽ ነው እንጂ ቁጥራቸውስ 24ብቻ ሆኖ አይደለም ።


ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ ስማቸውን ጭምር በመጥቀስ ለኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ሰላምታ አቅሮቦላቸዋል። በአብ መንበር ዙሪያ ላሉ ለ24ቱ ሰማያውያን ካህናት ሰላምታ ይገባል፤ በእጆቻቸው ውስጥ ላለ ማዕጠንትም ሰላምታ ይገባል፤ በራሶቻቸው ላይ ላሉ አክሊላትም ሰላምታ ይገባል፤ አካኤል፣ ፋኑኤል፣ ጋኑኤል፣ ታድኤል፣ እፍድኤል፣ ዘራኤል፣ ኤልኤል፣ ተዳኤል፣ ዮካኤል፣ ገርድኤል፣ ልፍድኤል፣ መርዋኤል፣ ኑራኤል፣ ክስልቱኤል፣ ኡራኤል፣ ባቱኤል፣ ሩአኤል፣ ሰላትኤል፣ ጣውርኤል፣ እምኑኤል፣ ፔላልኤል፣ታልዲኤል፣ ፐስልዱኤል፣ አሌቲኤል ለተባሉ ስሞቻቸውም ሰላምታ ይገባል) በማለት አወድሷቸዋል (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ተአምኆ ቅዱሳን ንባቡና ትርጓሜው / መጋቢ ሐዲስ ሮዳስ እንደተረጎመው)

ዛሬ በዚህች መጠነኛ ጽሁፍ ኅዳር 24ቀን ከነዚህ ካህናተ ሰማይ ሱራፌል ጋር ተደምሮ የሥላሴን መንበር ያጠነ አዲሱን ምድራዊ ሱራፊን ተክለ ሃይማኖት /ተክለ ኤልን /እናስተዋውቃችዋለን። ካህናተ ሰማይ ሱራፌል ከዘር የተገኙ ምድራዊያን አይደለም ተክለ ኤል ተክለ ሃይማኖት ግን ከሕግ ዘር የተገኘ ምድራዊ ሰው የሆነ ሐዲስ ሱራፊ ነው።
‹ተክል› ማለት ፍሬያማ ዕንጨት፣ ዛፍ፣ ቅመም፣ ቅጠላ ቅጠል፣፣ የሚሸተት፣ቢበሉት ጥጋብ ፣ቢያርፉበት ጥላ የሚሆን ገነታዊ ዕፅ፣ እንዲሁም ሕግ ሥርዓት ማለት ነው /ማቴ.15፥13/፡፡

"ኤል" ማለት ደግሞ እግዚአብሔር ማለት ነው :: ስመ መላእክት ስመ እግዚአብሔርን ያዘሉ በመሆናቸው የሁሉም ቅዱሳን መላእክ ስም "ኤል" የሚል መቀጽል አለው ለምሳሌ ከላይ የጠቀስናቸው የሃያራቱን ካህናተ ሰማይ የሱራፌልን ስም መመልከት ይቻላል :- አካኤል፣ ፋኑኤል፣ ጋኑኤል ወ.ዘ.ተ ስለዚህ "ተክለ ኤል " ማለታችንም ይህ ሐዲስ ሱራፊ ስሙ ከስማቸው ጭምር የሚገጥም መሆኑን ለመግለጥ ነው። የእግዚአብሔር ተክል ተክለ እግዚአብሔር ማለታችን ነው :: ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ባስልዮስ ዘ ቄሳሪያ እኔስ እግዚአብሔር ባልኩ ጊዜ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለቴ ነው ብሎ እንደተናገረ " ተክለ ኤል" ተክለ እግዚአብሔር ሲባልም የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ተክል የሚል ትርጉም ይሰጣል ።


#አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት የተወለዱት በሸዋ ክፍለ ሀገር ዛሬ ኢቲሳ በመባል በሚታወቀው ከከሰም ጅረት አካባቢ ባለ ቦታ በጥንቱ ፈጠጋር ቡልጋ በደብረ ጽላልሽ አውራጃ ዞረሬ በተባለው ሥፍራ በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ዘርዐ ዮሐንስ ወይም ጸጋ ዘአብ (የአብ ሥጦታ) ከሚባል ካህን እና ሣራ ወይም እግዚእ ኅረያ(እግዚአብሔር የመረጣት)በመባል ከምትታወቅ ደጋግ ከሆኑ ባልና ሚስቶች በመላእክ አብሳሪነት መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ገደማ ነው።
ወላጆቻቸውም ፍስሐ ጺዮን ።(የፂዮን ደስታዋ)ብለው ሰየሟቸው፡፡ ጻድቁ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው ‹‹ አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ›› በማለት የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነዋል። ይህን ጊዜ እናታቸው እግዚ ኀረያም በመገረም ሆና " ይህ ሥራ የአባት ነው ላንተ የሚገባህ ጡት መጥባት ነው" ብላ ለህጻኑ ጡቷን አጎረሰችሁ ፡፡ ይህም የህጻኑ ሁኔታ መላእካዊ ግብሩን ገና በህጻንነት የገለጠ ነበር ቀን ከለሊት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ማመስገን የመላእክት መገለጫ ነውና ኢሳ 6÷6 ። ካህኑ ፀጋ ዘአብ የወቅቱን የቤተ ክርሰቲያን አገልግሎታቸውን ጨርሰው ወደ ቤታቸው ሲገቡ ሚስታቸው እግዚእ ኀረያ በመገረም ሆና የሦስት ቀን ልጃቸው ፍስሐ ፂዮን እንዴት ባለ ምስጋና ፈጣሪያቸውን እንዳመሰገነ ነገረቻቸው ጸጋ ዘአብም ህጻኑን ተቀብለው ታቅፈው እየሳሙ ልጄ ሺህ ዘመን ኑርልኝ እንዲ እያልክ በቤተ መቅደስ ስትቀድስ ዐይህ ዘንድ እመኛለው አሉ።

የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ከአብሮ አደግ ጓደኞቹ ጋር በዱር ፈረስ ሲጋልብ ጦር ሲሰብቅ ተገናኝቶት ፍስሐ ጺዮን የሚለውን ስሙን በፈጣሪው ትዛዝ መሠረት ለውጦ ከእንግዲህ ወዲህ "ተክለሃይማኖት" እየተባልክ ተጠራ እንጂ ስም ፍስሐ ጺዮን አይሁን አላቸው አበው ስምን መላእክ ያወጣዋል እንዲሉ ፡፡ አያይዞም ፈረስ መጋለብ ጦር መስበቅ ቀስት መወርወር እንሰሳት ማደንን ተው ከእንግዲህ ወዲህ መስቀል ጨብጥ በወንጌል ስበክ ከአፍህ በሚወረወር በቃለ እግዚአብሔር መረብነት ሰው አድን አለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመላእኩ ክንፍ ላይ ተገልጦ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጌሃለሁ ብሎ በሐዋርያት ሾመት ሐዋርያ አድርጎ ሾመው። ጓደኞቹም ከያሉበት ተሰብስበው ወደ ተክለ ሃይማኖት ቀረቡ ከፊቱ የሚወጣው ብርሃን ግን አላስተያይ አላቸው ስለዚህ ፊትህን ማየት አቃተን ተሸፋፈንልን ሲሉ ተማጠኑት። ሙሴ ከሲና ተራራ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋግሮ በወረደ ጊዜ አሮንና የእስራኤል ልጆች ሁሉ ሙሴ ሆይ ከፊትህ የሚወጣው ብርሃን አላስተያይ ብሎናልና እባክህ ፊትህን ሸፍንልኝ እንዳሉት ዘጽ 34÷29_35

#ጻድቁ በተወለዱ በ15 ዓመታቸው ዲቊናን፤ በ22 ዓመታቸው ደግሞ ቅስናን ከግብፃዊው ጳጳስ ከአባ ጌርሎስ ወይም (ከአባ ቄርሎስ) ዘንድ ተቀብለዋል፡፡ ሐዋርያዊ ተግባርንም በከተታ እና በፈጠጋር (በጽላልሽና በአካባቢዋ፣በዳሞት በምድረ ወላይታ፣በአምሓራና በሸዋ በሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ፣ በኣድያማተ ትግራይ፣በገዳመ ዋሊ (ዋልድባ) ፣በገነተ ማርያም ላስታ በደብረ ዘመዶ ማርያም ገዳም፣ በኤርትራ ገዳማት ፣በደብረ ዳሞ አቡነ አረጋዊ ገዳም ወዘተ በአገሪቱ ወንጌል ባልተዳረሰበት ቦታ ሁሉ እየተዘዋወሩ በመላዋ ኢትዮጵያ ወንጌልን አስፍተዋል።
ጻድቁ አባታችን ሕይወታቸዉን ሙሉ ለእግዚአብሔር በመስጠት፣ እንደ በሬ ተጠምደው፣ እንደ ገበሬ ታጥቀው፣ ይህንን ዓለም ንቀው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በብሕትውና በመኖራቸው፤ እርሳቸው በአሚነ ሥላሴ ጸንተው ሌሎችንም እንዲጸኑና እንዲያምኑ በማድረጋቸው፤ እንደዚሁም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ በመስበክ በጌታችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ድውያነ ሥጋን በተአምራት፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት የፈወሱ ዛሬም በአጸደ ነፍስ ሆነው የሚፈውሱ ሐዲስ ሐዋርያ ሐዲስ ሱራፊ ናቸው።


በየ ደረሱበት ሥፍራ ሁሉ ከሥራቸው ጽናት ከተአምራታቸው ብዛት የተነሳ አንተ ሰውነህን ወይስ መላእክ ነህን ንገረን ይሏቸው ነበር። እርሳቸውም ከንቱ ውዳሴን ነፍሳቸው አጥብቃ ትጸየፈው ነበርና አባቶቼ እንደ

#ቀጣዮይ ይመልከቱ
👇👇👇👇
👆👆👆👆👆
ከላይ የቀጠለ

እናንተ ምድራዊ ሰው እንጂ መላእክ እሆን ዘንድ እኔ ማነኝ? እያሉ የሚያቃጥል የትዕትናን እንባ ከዐይኖቻቸው ይፈስ ነበር ። “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ” 1ጴጥ 5÷ 5 እንደተባለ ይህንን ይህን የትዕትና ሥራ ሲከተል ትዕትናው ፀጋውን አብዝታለት ያኔ በተወለደ በሦስተኛው ቀን ሥላሴን በአንድነት ሦስትነቱ በማመስኑ ተደንቆ ልጄ ሺህ ዘመን ኑርልኝ እንዲህ እያልክ በቤተ መቅደስ ስትቀድስ አይህ ዘንድ እመኛለው ብሎ የመረቀው የአባቱ ምርቃት ደርሳለት ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ ድንገት ነጥቆ ወስዶ ከፀሐይ ይልቅ ወደ ምታበራ ሀገር አደረሰው ።

#አራቱ እንስሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፥ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ አባታችንም ደግሞ እንደነርሱ ያዘ በምድር ብቻ ያይደለ በሰማያዊ መቅደስ ጭምር ገብቶ ከሱራፌል ጋር ሱራፊ ሆኖ ክንፉን ከክንፋቸው ገጥሞ ምስጋናው ከምስጋናቸው አንድ ሆኖ በወርቁን ማዕጥንት ይሰልስ ይቀድስ ዘንድ ጀመረ ራእይ 5፥8 የቅዱስ ጳውሎስን ነገሩን ትምህርቱን የተከተለ ብጹህ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ወደ ሰማይ በመመንጠቅም ተከተለው፡፡ በመከራው መስሎታልና በክብሩ መሰለው “ ወደ ገነት ተነጠቀ ሰውም ሊናገረው የማይገባወን የማይነገረውንም ቃል ሰማ ተብሎ እንደ ተጻፈ 2ቆሮ 12÷4 ስለዚህ በገድሉ መጻሕፍ እንዲ ሲል ሰማነው "ተክለ ሃይማኖት ክፍልህ ከሃያ አራቱ ካህናቶቼ ጋር ይሁን የሚል ቃል ከዙፋኑ ውስጥ ወጣ የወርቅ ጽና አምጥተው ሰጡኝና ከእነርሱ ጋር በአንንድነት አጠንኩ ምስጋዬ ከምስጋናቸው ጋር ልብሴም እንደ ልብሳቸው ሆነ ፈጣሪዬንም በሦስትነቱ ተገልጦ አየሁት" ገ/ተ ሃይማኖት ዘአርብ 43÷ 29

#የሐዲሱ_ሱራፊ_የአባታች_የቅዱስ_ተክለ_ሃይማኖት እረድኤትና በረከታቸው በአገራችን በኢትዮጵያና በሕዝበ ክርስቲያኖች ሁሉ ላይ ጸንቶ ይኑር ! በወርቅ ጥናውም ዘወትር እያጠነ መዓዛ ክርስቶስን የምንሸት እውነተኛ ክርስቲያኖች አድርጎ የመንግሥቱ ወራሾች የስሙ ቀዳሾች እንድንሆን ያድርገን ለዘላለሙ አሜን!


............. ይቆየን............


ኀዳር 24/2013ዓ.ም
#እመ_ሳሙኤል_ሐና
(የሳሙኤል እናት ሐና)

#በተራራማው በኤፍሬም አገር ከአርማቴም መሴፋ የሆነ ስሙ ሕልቃና የተባለ ኤፍሬማዊ ሰው ነበረ፤ ። ሁለትም ሚስቶች ነበሩት፤ የአንዲቱ ስም ሐና የሁለተኛይቱም ስም ፍናና ነበረ፤ ለፍናናም ልጆች ነበሩአት፥ ለሐና ግን ልጅ አልነበራትም።

ያም ሰው በሴሎ ይሰግድ ዘንድ ለሠራዊት ጌታም ለእግዚአብሔር ይሠዋ ዘንድ ከከተማው በየዓመቱ ይወጣ ነበር። የእግዚአብሔርም ካህናት ሁለቱ የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ በዚያ ነበሩ። ሕልቃና የሚሠዋበት ቀን በደረሰ ጊዜም ለሚስቱ ለፍናና ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችዋ ሁሉ እድል ፈንታቸውን ሰጣቸው።


#ሐናንም ይወድድ ነበርና ለሐና ሁለት እጥፍ እድል ፈንታ ሰጣት፤ እግዚአብሔር ግን ማኅፀንዋን ዘግቶ ነበር። እግዚአብሔርም ማኅፀንዋን ዘግቶ ነበርና ጣውንትዋ ታስቆጣት ታበሳጫትም ነበር። በየዓመቱም እንዲህ ባደረገ ጊዜ እርስዋም ወደ እግዚአብሔር በምትወጣበት ጊዜ ታበሳጫት ነበር፤ ሐናም ታለቅስ ነበር፥ አንዳችም አትቀምስም ነበር።

#ባልዋም ሕልቃና ሐና ሆይ፥ ለምን ታለቅሻለሽ? ለምንስ አትቀምሺም? ለምንስ ልብሽ ያዝንብሻል? እኔስ ከአሥር ልጆች አልሻልልሽምን? አላት። በሴሎ ከበሉና ከጠጡ በኋላ ሐና ተነሣች፦ ካህኑም ዔሊ በእግዚአብሔር መቅደስ መቃን አጠገብ በመንበሩ ላይ ተቀምጦ ነበር። እርስዋም በልብዋ ትመረር ነበር፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸለየች፥ ጽኑ ልቅሶም አለቀሰች።

እርስዋም፦ አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ የባሪያህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ እኔንም ባትረሳ፥ ለባሪያህም ወንድ ልጅ ብትሰጥ፥ ዕድሜውን ሁሉ ለእግዚአብሔር እሰጠዋለሁ፥ ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም ብላ ስእለት ተሳለች። ጸሎትዋንም በእግዚአብሔር ፊት ባበዛች ጊዜ ዔሊ አፏን ይመለከት ነበር። ሐናም በልብዋ ትናገር ነበር፤ ድምፅዋም ሳይሰማ ከንፈርዋን ታንቀሳቅስ ነበር፤ ዔሊም እንደ ሰከረች ቈጠራት።


#ዔሊም፦ ስካርሽ እስከ መቼ ነው? የወይን ጠጅሽን ከአንቺ አርቂው አላት።

#ሐናም፦ ጌታዬ ሆይ፥ አይደለም፥ እኔስ ልብዋ ያዘነባት ሴት ነኝ፤ ጠጅና ሌላ የሚያሰክር ነገር አልጠጣሁም፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ነፍሴን አፈሰስሁ፤ ኀዘኔና ጭንቀቴ ስለ በዛ እስከ አሁን ድረስ ተናግሬአለሁና ባሪያህን እንደ ምናምንቴ ሴት አትቍጠረኝ ብላ መለሰችለት።

#ዔሊም፦ በደኅና ሂጂ፥ የእስራኤልም አምላክ የለመንሽውን ልመና ይስጥሽ ብሎ መለሰላት።

#እርስዋም፦ ባሪያህ በዓይንህ ፊት ሞገስ ላግኝ አለች። ሴቲቱም መንገድዋን ሄደች፤ በላችም፥ ፊትዋም ከእንግዲህ ወዲያ አዘንተኛ መስሎ አልታየም።


ማልደው ተነሥተው በእግዚአብሔር ፊት ሰገዱ፥ ተመልሰውም ወደ አርማቴም ወደ ቤታቸው መጡ። ሕልቃናም ሚስቱን ሐናን አወቃት፤እግዚአብሔርም አሰባት፤ የመፅነስዋም ወራት ካለፈ በኋላ ሐና ወንድ ልጅ ወለደች፤ እርስዋም፦ ከእግዚአብሔር ለምኜዋለሁ ስትል ስሙን ሳሙኤል ብላ ጠራችው።

#እርሶ_ሐናን ቢሆኑ ምን ዓይነት ስሜት ይሰማዎት ነበር ?

👉አንዳች ነገር ቸግሮን ወደ #እግዚአብሔር ቤት ሄደን ችግራች እንዲፈታልን በምናደርገው ጥረት ትልቅ ቦታ የምንሰጣቸው የቤተ ክርሰቲያን አገልጋዮች እንደ ሐና ክፉ ንግግር ቢናገሩን ወይም ቢያስቀይመን ምን እናደርጋለን?
👉አንተን ብሎ ካህን ፣አንተን ብሎ አገልጋይ ብለን ከፍ ዝቅ አርገን እንሳደባለን ወይስ
👉ከአሁን ወዲህ ቤተ ክርስቲያን ብሄድ እግሬን ይቁረጠው ብለን ከእግዚአብሔር ቤት እንርቅ ይሁን?
👉ወይስ እንደ ሐና በትእግስት ጸንተን እግዚአብሔር በተስፋ እንጠባበቅ ነበር

ለነፃ ሀሳብዎ የሚከተሉትን የመልእክት ሳጥን መጠቀም ይችላሉ።
👇👇👇👇👇
@Abenma
@YEAWEDIMERITE

#ዓውደ_ምሕረት_የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ባለፈው ጊዜ ረዓብ ወይም ራኬብ ስለምትባል ደገኛ ሴት ታሪክ አቅረበንላችሁ ነበር

#ማጠቃለያ ሀሳብ ለመስጠት ያክል ረዓብ/ራኬብ ሦስት ነገር የተገኛባት ሴት ነበረች በነዚህም ነገሮች ለመዳን ችላለች።



1)ደግነት ፦ ወደ ቤቷ ሸሽተው የገቡትን ሰዎች ማናችሁ ?ምንድናችሁ ?ሳትል ዘር ፣ጎሳ ፣ መልክ ሳታይ በደግነት ዝም ብላ ተባረው ሰለመጡ ብቻ አዝና ተቀበለቻቸው።
2)እምነት፦ ከተማዋን ሲወርሱና ሲቆጣጠሩ ሊያድኟት እንደሚችሉ ሲነግሯት በቅንነነት ተቀብላቸው መልክት አድርጋ እንድታውለበልበው የነገሯትን ቀይ በፍታ በመስኮታ ላይ አድርጋ የእምነት ማዕተሟን ጠብቃ ኖራለች።
3)ጥበብ፦ 3.1ተሳደው ወደ ቤቷ ያስገባቻቸውን ሰዎች ሰገነቱ ላይ አውጥታቸው ነበር በዚያም በረበረበችው በተልባ እግር ውስጥ ሸሽጋቸው ነበር
3.2 ሌላው ጥበቧ አሳዳጃቸው መጥተው ወደ ቤትሽ የገቡ ሰላዮች አሉ አስወጫቸው ሲሏት አረ አልገቡም ብላ አልካደችም አዎ ገብተው ነበር ግን በዚህ በኩል ወጡ ማለቷ ብልኀተኛ መሆኟን ያሳያል እንደውም በትርጓሜ ላይ መግባታቸውን ስላመነችላቸው ተመልሰው መውጣታቸውን ስትነግራቸው አመኑላት ብሎ ጥበቧን ይገልጣል።

የኢያሪኮ ቅጥር ሰባት ቀን ከዞሩበት በኋላ በእምነት ወደቀ። "ጋለሞታይቱ ረዓብ ሰላዮችን በሰላም ስለ ተቀበለቻቸው ከማይታዘዙ ጋር በእምነት አልጠፋችም።ዕብ11÷30-31

ረዓብ/ራኬብ ከዚህ ክብሯ ባለፈ ከጌታችን ቅድመ አያቶች መካከልም ገብታ ለመቆጠር ችላለች።



“የወንድማማች መዋደድ ይኑር። #እንግዶችን_መቀበል_አትርሱ፤ በዚህ አንዳንዶች ሳያውቁ #መላእክትን እንግድነት ተቀብለዋልና።” ዕብ 13፥1-2
+++ከመዝ ነበርኪ ውስተ ቤተመቅደስ ወመላእክት ያመጽኡ ወትረ ሲሳየኪ፤ ከመዝ ነበርኪ አስርተ ወክልኤተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምዐበ መላእክት+++ቅዳሴ ማርያም+
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደች በሥስት ዓመቷ እናቷ ቅድስት ሀና ለኢያቄም " ይህች ብላቴና ሆዷ ዘመድ ሳይወድ አፏ እህል ሳይለምድ ወስደን ከቤተክርስቲያን አንሰጥምን? ኋላ አንዳች ብትሆንብን ከልጃችንም ከእግዚአብሔርም ሳንሆን እንዳንቀር"..አለችው። እርሱም መልሶ "ፍቅርሽ አያስችልሽም ብዬ ነው አንጂ እኔማ ፈቃዴ አይደለምን" አላት። ከፍቅሯ የተነሳ ከትከሻዋ አውርዳት አታውቅም አንድ ቀን ከቤት ጥላት ውጪ ወጥታ ብትመለስ መለአክ ሰውሮባት ጥራ አግኝታታለች ከዚያ በኋላ ተለይታት አታውቅም። ይህን ተባብለው ከቤተመቅደስ ወስደው ሰጧት የብጽአት ልጅ ናትና። ሊቀ ካህናቱ ዘካር ያስ በደስታ ተቀበላት ነገር ግን የምትመገበውን ከየት ላመጣ ነው ብሎ ሃ ሳብ ወስጥ ገባ ዛሬ እኛ ምን እንበላለን ምን እንጠጣለን ምንሰ እንለብሳለን ብለን እንደምንጨነቀው ነገር ግን ይህ ሁሉ ነገር እኛ ከምናስበው በላይ እንደሚያስፈልገን አምላካችን ያውቃል በወንጌሉም ስለነዚህ ጉዳዮች ከቶ አንዳንጨነቅ አስቀድመን ጽድቁን እንድንፈልግ ምግባር ከሃይማኖት ጋር አስተባብረን እንድንይዝ ጌታችን አስተምሮናል። ካህኑ ዘካርያስ በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ መልአኩ ፋኑኤል ህብስት ሰማያዊ ፣ ጽውዐ ሰማያዊ ይዞ ረቦ ታየ ፤ ዘካርያስ ይህን ሲመለከት ለኔ የመጣ ሀብት ነው ብሎ ለመቀበል ቢነሳ ወደ ላይ ራቀበት አገልጋዩ ስምኦንም ቢሞክር ራቀበት። ከዚህ በኋላ ጥበበ እግዚአብሔር አይመረመርምና ምናልባት ለዚህች ብላቴና የመጣ ሀብት እንደሆነ ብለው እመቤታችንን ለብቻዋ አድርገዋት ፈቀቅ ቢሉ ድንኩል ድንኩል ብላ እናቷን ስትከተል መልአኩ ፈጥኖ ወርዶ አንድ ክንፋን አንጥፎ ፤ አንድ ክንፋን ጋርዶ በቆመ ብእሲ በሰው ቁመት ያህል ቦታ አስለቅቆ መግቧት ዐረገ። ከዚያም ቤተመቅደስ አስገብተዋት በዚያ አስራ ሁለት ዓመት ኖራለች በቤተመቅደስ ቆይታዋ ብዙ ችግሮችን አሳልፋለች አይሁድ በክፉት በቅናት ጦራቸውን አንስተውባታል ነገር ግን የፍጥረት ሁሉ ጌታ ይጠብቃት ነበርና ገና ወደ ቤተመቅደስ ሳይደረሱ ቅጥሩ እሳት እየሆነ መልሷቸዋል እኛም ዛሬ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ ዋጅቶ በመሠረታት በቀደሳት ምግበ ነፍስ የሆነውን የዘላለም ሕይወት የሚገኝበትን አማናዊውን የክርስቶስ ሥጋውና ደሙን አዘጋጅታ ያለዋጋ የምትሰጠንን በቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ እንዳንገኝ ለነፍሳችን ዕረፍት እንዳናገኝ እንዳንፈወስ በቤቱም ሆነን ያማረ የተወደደ እንደ አቤል ያለውን መስዋዕት ፣ ምስጋና፣ ጸሎት አንዳናቀርብ ብዙዎች በኛ ላይ ይነሱ ይሆናል መሠናክል ይሆኑብን ይሆናል እኛ ግን በዚህ ነገር ሳንሸበር እመአምላክ ወላዲተ አምላክን የጠበቀ እግዚአብሔርን አምነን ተስፋ አድርገን በሃይማኖት ልንጸና በምግባር ልንታነጽ ፤ በምክረ ካህን ራሳችንን ልናስመረምር ፤ የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ልንበላ ልንጠጣ ይገባል። ለዚህ ክብር እንድንበቃ እመቤታችን በምልጃዋ በቃል ኪዳኗ ታስምረን! የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅሯን በልባችን ጣዕሟን በአንደበታችን እግዚአብሔር አምላክ ያሳድርብን!!አሜን!!!
*+++ መልካም በዓል+++*

ታህሳስ 3/4/2013
@AwediMeherit
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ውድ ታዳሚዎቻችን እንደምን ዋላችሁ (አደራችሁ) ...አሜን ስለ ቸርነቱ እግዚአብሔር አምላክ የተመሰገነ ይሁን አትለይምና እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ #ቅድስት_ድንግል_ማርያምም እንደተሰጣት ከፍ ያለ ጸጋ የተመሠገነች ትሁንልን አሜን..!::
እነሆ ተወዳጁ የምን እንጠይቅልዎ መርኃ ግብር አሁን ጀምሯል ጥያቄዎን በሚከተሉት አድራሻዎች ይስደዱልን ሊቃውንትን ጠይቀን መጻሕፍትን አገላብጠን ቤተ ክርስቲያናዊ ምላሽ እንሰጥበታለን።
👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
👇👇👇👇👇👇
ዓውደ ምሕረት የእናንተ
@AwediMeherit
@AwediMeherit
Forwarded from Deleted Account
አንድ ሰው በተክሊል ማግባት የሚችል ወይም የምችል መቼ ነው? በምን ሁኔታስ ነው?