ዐውደ ምሕረት
3.66K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
AB

ጥያቄ ነበረኝ
ሰመዓትነት በቤተክርስቲያን እንዴት ይገለጻል እና ስንት አይነት ሰመዓትነት አለ ስለነዚህ ትንሽ ቢብራራልኝ🙏

ሰላም ናቸው ብያለሁ
ሴት ልጅ ቢቻላት ፀጉሯን ትሸፋፈን እሚለውን ጥቅስ የት ነው እማገኝው
፩) ሰማዕት ‹‹ሰምዐ› › ከሚል የግእዝ ቃል የተወሰደ ሲሆን፤ ትርጉሙም
ያየነውን፣ የሰማነውን መመስክር መቻል እንደሆነ የኪዳነ ወልድ ክፍሌ
መጽሐፈ ስዋስወ ወግስ መዝገበ ቃላት ገጽ 671 ይነግረናል፡፡ ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ‹‹እኔ ለእውነት ለመመስከር
መጥቻለሁ›› በማለት እውነትን እንድንመሰክር አብነት ሆኖናል /
ዮሐ.18፥37/፡፡
ሰማዕትነት በሃይማኖታዊ ትርጉሙ ስንመለከተው ስለ እግዚአብሔር፣
ስለቅድስት ቤተክርስቲያን፣ ስለ ሃይማኖታቸው በእውነት
በመመስከራቸው ጀርባቸውን ለግርፋት፣ ሰውነታቸውን ለእሳት፣
እግራቸውን ለሰንሰለት፣ አንገታቸውን ለስለት አሳልፈው ለሰጡ፤
በድንጊያ ተወግረው በመንኮራኩር ተፈጭተው በጦር ተወግተው
አልያም በግዞትና በስደት በዱር በገደል ተንከራተው ለዐረፉ ቅዱሳን
አባቶችና ቅዱሳት እናቶች የሚሰጥና ተጋድሎአቸውን ጠቅለል አድርጎ
የሚገልጽ ቃል ነው፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊው እመቤታችንን
ባመሰገነበት ድርሳኑ “ሰማዕታት የዚህችን ዓለም ጣዕም በእውነት
ናቁ፤ ደማቸውንም ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ፤ስለ መንግሥተ
ሰማያትም መራራ ሞትን ታገሱ” በማለት የሰማዕታት ተጋድሎአቸው
መራራ እንደሆነ ገልጿል፡፡ (ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ)
ጌታችን ‹‹በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት
ባለው አባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፡፡ በሰው ፊት የሚክደኝን ሁሉ
ደግሞ በሰማያት ባለው አባቴ ፊት እክደዋለሁ›› ሲል ስለ
ሃይማኖታችን የምንመሰክረው ከሰማዕትነት ጋር ያለውን ቁርኝት
ነግሮናል፡፡ /ማቴ.10፥32-33/፡፡ ከዚህ አንጻር ያለ ክርስትና
ሰማዕትነት ያለ ሰማዕትነት ክርስትና የለም ማለት ነው፡፡
ሰማዕትነት መመስከር ከሆነ እንዴት ነውየምንመሰክረው የሚል ጥያቄ
ማንሳታችን አይቀርም፡፡ ለዚህ ጥያቄያችን መልስ የምናገኝባቸው
ሦስት የመመስከሪያ መንገዶች አሉ፡፡ እነሱም፡-
በአንደበታችን
እግዚአብሔር አምላካችን አንደበት የሰጠን እውነትን በመመስከር
ለክብር እንድንበቃበት እንጂ ውሸት በመናገር አምላካችንን
እንድናሳዝንበት አይደለም፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ በመልእክቱ ‹‹አንደበቱን
ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው
ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው›› በማለት በአንደበታችን
እውነትን እንድንመሰክርበት ይመክረናል /ያዕ. 1$26/፡፡ ሐዋርያው
ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉ መስክሮም
ይድናልና›› እያለ እውነትን መመስከር ለመጽደቅና ለመዳን ወሳኝ
ጉዳይ ነው ይለናል /ሮሜ 10፥10/፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን
በዓለም ዞረው ያስተማሩት በአንደበት መመስከር ያለውን ሰማያዊ
ዋጋ ስለተረዱ ነው፡፡ አንደበታችን እውነትን በመመስከር ለሰማዕትነት
የሚያበቃን መሆኑን ተገንዝበን አንደበታችን ሰዎችን ከማማት፤
ያለሥራቸው ስም ከመስጠት ሊቆጠብ ይገባዋል፡፡
በሕይወታችን
በሕይወት መመስከር ያላመኑትን ወደ ማመን የሚያመጣ ትልቅ
መሣሪያ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሕይወት መመሪያችን ነው፡፡
በሕይወት መመስከር ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተቀመጡትን
ሕግጋትና ትእዛዛት በተግባር ለውጦ ማሳየት መቻል ነው፡፡ ለስም
አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ በተራራ ላይ ስብከቱ ያስተማረን ‹‹መልካሙን ሥራችሁን
አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ
እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ›› በማለት ነው /ማቴ.5፥16/፡፡ በቅዱሳን
የሕይወት ምስክርነት እግዚአብሔር ታይቷል፡፡ በእኛ ሕይወት
እግዚአብሔር ታይቷል ወይ ብለን ሁላችን ራሳችንን ልንመረምር
ያስፈልጋል፡፡
በአላውያን ፊት
ከባዱና ታላቁ ሰማዕትነት በአላውያን ነገሥታትና እግዚአብሔርን
በማያምኑ ሰዎች ፊት ያመኑትን እምነት ሳይፈሩ መመስከር መቻል
ነው፡፡ አላውያን ነገሥታት የእግዚአብሔርን አምላክነትና ፈጣሪነት
ስለማያምኑ ሰማዕታትን ያሰቃያሉ፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ሰማዕት
የሚሆኑት ክርስቲያኖች የሚያገኙትን ሰማያዊ ክብር ስለሚያስቡ ወደ
እሳት ቢጣሉ፣ በሰይፍ ቢቆረጡ፣ በድንጋይ ቢወገሩ ምንም
አይመስላቸውም፡፡ በዘመነ ሰማዕታት የኖሩ ክርስቲያን ወገኖቻችን ላይ
የተፈጸመው ግፍና ስቃይ ለዚህ አባባላችን መሳያ ነው፡፡ ቀዳሜ
ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ እውነትን በሐሰት ለውጠው
የእግዚአብሔርን አምላክነት በመካድ በሥልጣናቸው ተመክተው
ለነበሩ አይሁድ ያላንዳች ፍርሃት ስለ እግዚአብሔር የባሕርይ
አምላክነት በመመስከሩ በድንጋይ ሲወግሩት፣ ዓይናቸው በኃጢአት
ለታወረ አይሁድ ‹‹ጌታ ሆይ ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው›› በማለት
ለወጋሪዎቹ ምሕረትን ለምኗል /የሐዋ. ሥራ 7፥60/፡፡
የሰማዕትነት ዓይነቶች
የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት የሰማዕትነት ዓይነቶች ሁለት ናቸው
ይሉናል፤ ሲተነትኑትም ሰማዕት ዘእንበለ ደም (ደማቸውን ሳያፈሱ
ሰማዕት የሆኑ) እና ደመ ሰማዕታት (ደማቸውን በማፍሰስ ሰማዕት
የሆኑ) በማለት በሁለት አበይት ክፍሎች መድበውታል፡፡ እነዚህ
ብያኔዎች እንደተጠበቁ ሆነው፣ ሰማዕትነትን ከአፈጻጸም አንጻር
በሦስት መሠረታዊ ቀለሞች ይመስሉታል፡፡ (ማኅበረ ቅዱሳን፤ ሐመረ
ተዋሕዶ፤ ገጽ 130 ነሐሴ 2002 ዓ.ም.)
አረንጓዴ ሰማዕትነት
እንደማንኛውም ሰው በከተማ እየኖሩ ዓለምን ለማሸነፍ የሚጥሩ
ከራሳቸው ጋር ታግለው ዲያብሎስን ድል ማድረግ የቻሉ አረንጓዴ
ሰማዕታት ይባላሉ፡፡ የሚበላ፣ የሚጠጣ ሳያጡ ሁሉን የሰጣቸውን
ፈጣሪ እያመሰገኑ ራሳቸውን በጾምና በጸሎት በመወሰን ያጡ የተቸገሩ
ወገኖቻቸውን ለመርዳት የማይሰለቹ የጽድቅ ሥራ በመሥራት
የሚያገኙትን ሰማያዊ ጸጋ በማሰብ የሚደሰቱ ናቸው፡፡ ከዚህ መልካም
ሥራቸው የተነሣ ስድብ፣ ነቀፌታ፣ ስደት፣ እስራት ሲደርስባቸው
መከራውን ሁሉ በአኮቴት (በምስጋና) ተቀብለው ፈጣሪያቸውን
የሚያመሰግኑ ናቸው፡፡
ነጭ ሰማዕትነት
ይህን ዓለም አሸንፈው ግርማ ሌሊትን ጸብአ አጋንንትን ታግሰው በዱር
በገደል የኖሩ አባቶቻችን ሕይወት የምናይበት ነው፡፡ ጌታችን ‹‹ማንም
ከእናንተ መካከል ያለውን ሁሉ ትቶ የማይከተለኝ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን
አይችልም›› ብሎ የተናገረውን ቃል በተግባር ያሳዩትን የሚወክል
ነው /ሉቃ 14$27/፡፡ ይህ የሰማዕትነት ጥሪ ለሁላችንም የቀረበ
እንደሆነ እንድንረዳው ‹‹እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ
መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ›› ብሎናል /ማቴ. 16፥24/፡፡
ስለሆነም ራሳችንን ከውስጣዊ ፈተና ለማዳንና ከልቦና ኃጢአት
ለመጠበቅ በጾም፣ በጸሎት፣ በትኅርምት በትሕትና ጸንተን በመዓልትና
በሌሊት እግዚአብሔርን እያመሰገን ልንኖር ያስፈልጋል፡፡
ቀይ ሰማዕትነት
ይህ ሰማዕትነት በደም የሚመጣ የሰማዕትነት ዓይነት ነው፡፡
እግዚአብሔርን በማምለካችን፣ ቅዱሳንን በማክበራችን፣ ማተብ
በማሠራችንና በአጠቃላይ ክርስቲያን በመሆናችን የሚመጣብንን
መከራና ስቃይ ስለ እግዚአብሔር ፍቅር በመታገስ በሰይፍ ተቀልተን፤
በመንኮራኩር ተፈጭተን፤ ወደ እቶን እሳት ተጥለን የሕይወት
መስዋዕትነት በመክፈል የምናገኘው ክብር ነው፡፡ ይሔ ሰማዕትነት
የመጨረሻ ደረጃ ነው፡፡ (ያረጋል አበጋዝና አሉላ ጥላሁን፤ ነገረ
ቅዱሳን፤ ገጽ 26-30፤ 1997 ዓ.ም.)

፪ ) ቢቻላት ትከናነብ ሳይሆን በግዴታ መከናነብ እንዳለባት ነው ሐዋርያው የተናገረው ጸጉርን ለመሸፋፈን መቻል አለ መቻል ብሎ ነገር የለም ጸጉሯን መሸፈን የማትችል ወይም የሚያዳግታት ሴት የለችምና ምን አልባት አላማዋ መታየት መገላለጥ መፈለግ ካልሆነ በቀር

"፤ በእናንተ በራሳችሁ መካከል ፍረዱ፤ ሴት ራስዋን ሳትሸፍን ወደ እግዚአብሔር ልትጸልይ ይገባታልን? "

ወንድ ጠጉሩን ቢያስረዝም ነውር እንዲሆንበት፥
ሴት ግን ጠጉርዋን ብታስረዝም ክብር እንዲሆንላት ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁምን? ጠጉርዋ መጎናጸፊያ ሊሆን ተሰጥቶአታልና። "
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11: 13-15)
Audio
ዓውደ ስብከት

አስተማሪ: #ልዑል_እግዚአብሔር

ተናጋሪ: #መምህር #ኢዮብ_ክንፈ

ርዕስ: #ከኛ_ጋር_እደር ሉቃ 24:29

ክፍል አንድ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
ዓውደ ስብከት

አስተማሪ: #ልዑል_እግዚአብሔር

ተናጋሪ: #ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ማርያም

ርዕስ: #ሕግህን ለሚወድዱት ብዙ ሠላም ነው እንቅፋትም የለባቸውም"
መዝ 118(119) ÷165

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
#መዝሙር
#ዐረገ_በስብሐት

በዘማሪት #ሰብለ_ስፍር

ዐረገ በስብሐት ዐረገ በእልልታ
በስብሐት በእልልታ
ዐረገ(2) በእልልታ
ሞትን ድል አድርጎ የሰራዊት ጌታ
ዐረገ(2) በእልልታ

                    
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
Audio
#መዝሙር #ሐዋርያት_ተባበሩ

#በወንድማችን_ዳዊት_ክብሩ

#መሰንቆ #ሀብታሙ_ሽፈራው

#ክራር #አቤኔዘር_ማሙሸት

ሐዋርያት ተባበሩ
በአዲስ ቋንቋ እየተናገሩ
ቃሉን አስተማሩ

ከዐረገ በኋላ በአስረኛው ቀን
ወደ ዓለም ላከው ጰራቅሊጦስን
በዝግ ቤት ውስጥ ቆዩ ቀኑን ሲጠብቁ
የተሰጣቸውን ተስፋውን እስኪያውቁ

ቀኑም ደረሰና ሃምሳኛው ዕለት
ተሰብስበው ሳሉ በአንድነት ጸሎት
መንፈስ ቅዱስ ታየ በነደ እሳት

ያ የተነገረው ያ የተስፍ ቃል
ወረደ ከሰማይ በእሳት አምሣል
ጴጥሮስ አሳመነ ሶስት ሺ ነፍሳት
ያን ጊዜ ገሊላ በሰጠው ትምህርት

ከሦስት አካል አንዱ መንፈስ ቅዱስን
ልኮ አናገራቸው ሁሉን በልሳን

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ወደ አዲሱ የየኔታ ቻናል ይቀላቀሉን

#የኔታ
ምርጥ መንፈሳዊ ቻናል
የአብነት ትምህርት በየቤታችን
#ውዳሴ_ማርያም ንባብ እና ዜማው
👉ንባብ
👉ዜማ

👉#በግእዝ_እንነጋገር

#ጥንታዊ የግእዝ ቋንቋ ትምህርት በመሪ ጌቶች ይሰጥበታል

#ጊዜና ሁኔታውን ያገናዘበ መንፈሳዊ ጽሁፎች
#ውይይቶች የግእዝ መዝሙሮች ከነ ትርጉማቸው
#ስብከቶች
#ጥያቄና መልሶች
#PDFጥንታዊ መዛግብቶችና መጻሕፎች ወደ እናንተ ይፈሱበታል

የዓውደ ምህረት እህት ቻናል
👇👇👇👇👇👇👇👇

https://telegram.me/YENETAY
https://telegram.me/YENETAY
ዐውደ ምሕረት pinned «ወደ አዲሱ የየኔታ ቻናል ይቀላቀሉን #የኔታ ምርጥ መንፈሳዊ ቻናል የአብነት ትምህርት በየቤታችን #ውዳሴ_ማርያም ንባብ እና ዜማው 👉ንባብ 👉ዜማ 👉#በግእዝ_እንነጋገር #ጥንታዊ የግእዝ ቋንቋ ትምህርት በመሪ ጌቶች ይሰጥበታል #ጊዜና ሁኔታውን ያገናዘበ መንፈሳዊ ጽሁፎች #ውይይቶች የግእዝ መዝሙሮች ከነ ትርጉማቸው #ስብከቶች #ጥያቄና መልሶች #PDFጥንታዊ መዛግብቶችና መጻሕፎች…»
Audio
#የእግዚአብሔር_ሰው_ሆይ_በሚቻልህ እርዳኝ


እግዚአብሔር ከመረጣቸውና ከ አከበራቸው ቅዱሳን አባቶች አንዱ የሆኑት ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት አንዱ ናቸው ።
እኚ ቅዱስ አባት በኖሩበት ዘመን ሁሉ የሰው ልጅ ጠላት የሆነውን ዲያቢሎስ ከምድር አጥፍተዋል ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው ጸጋ በአጋንንት ላይ ፅኑ መከራን አደረገባቸው። መሄጃ አጥተናል እስኪሉ ድረስ አባታችን ቅዱስ ተክለሃይማኖት አጋንንትን ላይ በረታባቸው ይህም ድንቅ አይደለ ክብር ይግባውና ጌታችን በወንጌሉ እንዲህ ብሉ ለቅዱሳኑ እንደተናገረ ማር 16÷ 17_ 18 " ያመኑት እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል በስሜ አጋንንት ያወጣሉ………… እጆቻቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ" እንዳለ ጻድቁ አባታችንም በአካለ ሥጋ እያለ ያደረገውን ድንቅ ነገር እንናገራ። ክቡር አባታችን መላ ኢትዮጵያን ሲያስተምሩ በአንዲት ቀን ዞረሬ ከምትባል ሀገር ደረሰ በዛም ከቀድሞ ጀምሮ ሴሰኛ የነበረች አንዲት ሴት አየ። እንዲህም አላት አንቺ ሴት እስከ መቼ እንደዚህ ባለ ጒስቁልና ትኖሪያለሽ ይህ መሰሰኑ አይበቃሽምን አላት ። እርሶም መልሳ እንዲ አለች ቅዱስ አባቴ ሆይ ይህ የዝሙት ነገር ለማቆም አልችልም በልቤ ውስጥ እንደ እሳት ይነዳልና ያለ ፍቃዴም ያሰራኛል አባቴ #የእግዚአብሔር ሰው ሆይ በሚቻልህ እርዳኝ አለቸው ። አባታችም ከእግዚአብሔር በተሰጠው ሐዋርያዊ ስልጣን በውስጧ የደረውንን እና ያለ ፍቃዷ እንድትሰስን ያደረገውን ጋኔን በመስቀል አማትቦ አስወጣው ። ያቺም ሴት ባለ ዘመኑ ሁሉ እግዚአብሔርን በመፍራትና በማመስገን ኖርች የአባታችን የቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በረከት ረድኤት ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይሰውረም አሜን ። ይህቺ ሴት ምንኛ ታላቅ እምነት አላት በሚቻለው ሁሉ የሚረዳ ቅዱስ ተክለሃይማኖትን ረዳትነት አምና ለምናለች እና የለመኑትን መስጠት ልማዱ የሆነ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖትም የምትሻውን አደረገላት ።
ዛሬም እኛ ልጆቹ አባታችንን በሚቻልህ ሁሉ እርዳን ብንለው እሱ ሁሉን የሚችል ቅዱስ ነውና ሁሉ ያደርጋል ።
እንዴት ቢባል ክብር ይግባውና የሚሳነው የሌለው ጌታችን በወንጌል እንደተናገረ ዮሐ 14÷12 "በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገው ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል ከዚህም የበለጠ ያደርጋል ብሏልና" ስለዚህ ዛሬም ለልጆቹ በአካለ ነፍስ ድንቅ የሚደርገውን አባት ተክለሃይማኖት ልንጣበቅ ይገባል ። እርሱ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በክንፉ ጋርዶ አስፈሪ ከተባለ ነገር ይጠብቀን ዘንድ የእርሱ ቅዱስ ፍቃድ ይሆን እኛም ልጆቹን በሚቻለው ሁሉ ይርዳን… … አሜን የአባታችን ረድኤት በረከት ምልጃ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን


ወስብሐት ለእግዚአብሔር

አዘጋጅ ።#እንግዳ ወርቅ ብርሃኑ ኃ/ሚካኤል

23/ 2012 ዓ.ም
+++++ መንፈስ ቅዱስ ማነው ? +++++
በነገረ መለኮት መምህራን ዘንድ ስለ መንፈስ ቅዱስ የምንማርበት
ዘርፍ (pneumatology -ንዩማቶሎጂ) ይባላል፡፡ በዚህ የትምህርት
ዘርፍም ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ስለ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ
ማንነት እርሱ በገለጠላቸው መጠን አምልተው አስፍተው
ያስተምራሉ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ላይ የተነሡ የክሕደትና የኑፋቄ
ትምህርቶችን ይመረምራሉ :: ለክህደት ትምህርቶችም ኦርቶዶክሳዊ
ምላሾችን ይሰጣሉ፡፡ የክሕደቱ አመንጪ መናፍቃንን ማንነትና የክሕደት
ምክንያቶችን ይገልጣሉ፡፡ እኛም የአባቶቻችን ልጆች ነንና እርሱ
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በገለጠልን መጠን መንፈስ ቅዱስ
ማነው? የሚለውን ሐሳብ አንስተን አጠር አጠር ያሉ ነጥቦችን
እንመለከታለን፡፡
+++ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው +++ ::
ቅዱስ ባስልዮስ "እኔ እግዚአብሔር በምልበት ጊዜ አብ ወልድ
መንፈስ ቅዱስ ማለቴ ነው" ብሎ እንደተናገረው እግዚአብሔር
የሚለው ስም የሥላሴ መጠርያ ነው፡፡ የአብ የወልድ እስትንፋሳቸው
የሆነ መንፈስ ቅዱስም ከአብ ከወልድ ጋር በዕሪና በፍጹም መተካከል
(co substantial with the father and the son) ያለ የሚኖር
ነውና እግዚአብሔር መሆኑን እንመሠክራለን፡፡ ይኽውም የቅዱሳን
ነቢያት ሐዋርያትና መምህራን ምሥክር ነው፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ
በትንቢቱ ስድስተኛ ምዕራፍ ላይ ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት
እግዚአብሔርን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ እንዳየው߹
ሱራፌልም በሁለት ክንፎቻቸው ፊታቸውን በሁለት ክንፎቻቸው
እግሮቻቸውን እየሸፈኑ በሁለት ክንፎቻቸውም ከጽንፍ ጽንፍ እየበረሩና
አንዱም ለአንዱ "ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር
ምድር ሁሉ በቸርነትህ ተሞልታለች" እያሉ እንደሚያመሰግኑት
ነግሮናል፡፡ ሊቃውንቱ ሱራፌል ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ብለው
ያመሰገኑበትን ምሥጢር ሲያብራሩ ቅዱስ የሚለው ቃል አለመለወጡ
ሦስቱ አካላት በባሕርይ በህልውና በሥልጣን በአገዛዝና በመሳሰለው
አንድ መሆናቸውን ߹ ሳይለወጥ ሦስት መሆኑ የእግዚአብሔርን የአካል
ሦስትነት የሚገልጥ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ ይህ የሊቃውንቱ ትምህርት
እውነተኛ መሆኑ ማስረጃው ነቢዩ ኢሳይያስ በኦሪት እንደተመለከተው
በሐዲስ ኪዳንም የራእይ አባት (አቡቀለምሲስ) የሚባል ወንጌላዊው
ቅዱስ ዮሐንስም በእግዚአብሔር ዙፋን መካከል ያሉ የሰው የአንበሳ
የላምና የንሥርን ፊት የሚመስሉ የተባሉ ኪሩቤል ቃሉ ሳይለወጥ
"ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ
ጌታ አምላክ" እያሉ ቀንና ሌሊት ያለ እረፍት እንደሚያመሰግኑ መናገሩ
ነው ራእይ ፬÷፰ ፡፡ ዳግመኛም ነቢዩ ኢሳይያስ በቁጥር ፱ ላይ
"የጌታንም ድምጽ ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል?" ሲል ሰማሁ
ይላል፡፡ ተናጋሪው ጌታ እግዚአብሔር ማንን እልካለው? ማለቱ
ባህሪያዊ አንድነቱን ማንስ ይሄድልናል? ብሎም ሦስትነቱን ገልጧል፡፡
ነቢዩ ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል? ብሎ እግዚአብሔር
ለተናገረው ነገር "እኔን ላከኝ" ካለው በኋላ በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን
ተቀምጦ የተገለጠለት እግዚአብሔር "ሂድና ይህን ሕዝብ መስማትን
ትሰማላችሁ አታስተውሉም ማየትንም ታያላችሁ አትመለከቱም
በላቸው" አለኝ ይላል፡፡ ለነቢዩ ኢሳይያስ ሂድና ሕዝቡን እንዲህ
በላቸው ያለው እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን
ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ ምእራፍ ፲፪ ከቁጥር ፴፱-፵፩
ሲገልጽ
ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ ነቢዩን ሂድና ለሕዝቡ ይህን በል
ያለው በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋንም የተገለጠው እግዚአብሔር መንፈስ
ቅዱስ መሆኑን ሲመሰክር "መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ ኢሳይያስ
ለአባቶቻችን ወደዚህ ሕዝብ ሂድና መስማትን ትሰማላችሁ
አታስተውሉም ማየትንም ታያላችሁና አትመለከቱም…ሲል መልካም
ተናገረ" ብሏል፡፡ የነዚህ የሁለት ሐዋርያት ምሥክርነት እንዴት ይረቅ ?
(የሐዋ ፳፰÷፳፭-፳፯) ፡፡
በዚህ ስፍራ ብቻ ሳይሆን ቅዱስ ጳውሎስ በኦሪት በነቢያት በጸጋ
በረድዔት አድሮባቸው ሕዝቡን ሲመክር፣ ሲያስተምር፣ ሲገሥጽ የነበረ
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ደጋግሞ አስተምሯል (ዕብ.
፫÷፯-፲፭) ፡፡
ይኽው ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ በፍጹም የማይመረመር የማይታወቅ
የእግዚአብሔር ጥልቅ ባሕርይ የሚታወቀው በራሱ በእግዚአብሔር
መንፈስ ቅዱስ ብቻ እንደሆነ አስተምሯል ፩ቆሮ ፪÷፲፩፡፡
ከእግዚአብሔር በቀር የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ማን ሊያውቅ
ይችላል ?
ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ የቃል ሥጋ ኮነን ትምህርት ባሰተማረበት
የወንጌሉ መግቢያ ላይ "በመጀመሪያ ቃል ነበር ቃልም በእግዚአብሔር
ዘንድ ነበር ቃልም እግዚአብሔር ነበር ይኽም በመጀመሪያ
በእግዚአብሐር ዘንድ ነበር " ዮሐ፩÷፩-፫ ይላል ፡፡ ነባቤ መለኮት (ስለ
መለኮት አምልቶ አስፍቶ የሚናገር) የተባለ ወንጌላዊው ቅዱስ
ዮሐንስ መጀመሪያ ያለው መጀመሪያ የሌለውን መጀመሪያ ነው ::
እግዚአብሔር መጀመሪያ የሌለው መጀመሪያ ነውና ፡፡ ቃል ያለውም
ቃለ አብ ቃለ መንፈስ ቅዱስ ሥግው ቃል ወልድን መሆኑ ግልጽ ነው ፡፡
ስለ ቃል ቅድምና አኗኗር ሲነግረን መጀመሪያ ነበር አለን ::
ስለማንነቱም ሲነግረንም እግዚአብሔር ነበር ብሎ እግዚአብሔርነቱን
ነገረን ፡፡ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመንበረ ጸባዖት በዘባነ
ኪሩቤል እንደነበር ሲነግረንም ሁለት ጊዜ በእግዚአብሔር (አብ) ዘንድ
ነበር ይኽውም በእግዚአብሔር (መንፈስ ቅዱስ) ዘንድ ነበር ብሎ
አስተማረን ፡፡ በዚህ ሥፍራ ሐዋርያው የመንፈስ ቅዱስን
እግዚአብሔርነት በእውነት እንደመሠከረ ልብ ማለት ይገባል፡፡
+++ መንፈስ ቅዱስ ፈጣሪ ነው +++
ፈጣሪነት የእግዚአብሔር የባሕርይ ግብሩ ነው፡፡ ያለ እርሱና ያለ
ፈቃዱ የተፈጠረ አንዳች ፍጥረት የለም፡፡ ከእርሱም ውጭ ሊፈጥር
የሚቻለው ማንም የለም፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍት አብ ወልድ ፍጥረታትን
ካለ መኖር ወደ መኖር አምጥተው የፈጠሩ መሆናቸውን እንደመሠከሩ
መንፈስ ቅዱስም ፈጣሬ ፍጡራን አምጻኤ ዓለማት መሆኑን
ይመሠክራሉ፡፡
ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት በመዝመሩ "የእግዚአብሔር ቸርነት ምድርን
ሞላች በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ ሠራዊታቸውም በአፉ
እስትንፋስ" ብሎ አብ ምድርን በቸርነቱ በፍጥረት በሰው፣ በእንስሳት፣
በአራዊት፣ በአዕዋፍ፣ በዕጽዋት፣ በአዝርዕትና በሌሎች ፍጥረታት
እንደሞላ፤ ሥግው ቃል ወልድ ሰማዮችን ያለ ባላ አቁሞ እንዳጸና
(እንደፈጠረ) ከገለጠ በኋላ የሰማይ ሠራዊት የሚባሉ ቅዱሳን
መላእክትን አንድም ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ክዋክብትን የፈጠረ እርሱ
መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ሲገልጽ "ሠራዊታቸውም በአፉ እስትንፋስ"
በማለት ተናግሯል (መዝ ፴፪÷፮) ፡፡
በኢዮብ መጽሐፍም "የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ ሁሉን የሚችል
የአምላክ እስትንፋስ ሕይወትን ሰጠኝ" (ኢዮ ፴፫÷፬) "በመንፈሱ
ሰማያት ውበትን አገኙ " ኢዮ ፳፮÷፲፫ ተብሎ ተደጋግሞ መነገሩ
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ፈጣሪ መሆኑን ያስረዳል፡፡ እነዚህ
በኢዮብ መጽሐፍ የተነገሩት ኃይለቃላት መንፈስ ቅዱስ ፈጣሪ߹ ሁሉን
ቻይ߹ የአምላክ (የአብ የወልድ) እስትንፋስ መሆኑን ይነግሩናል ፡፡
+++ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ ነው ::+++
እግዚአብሔር አካላዊ ነው ፡፡ አካሉ ግን እንደፍጡራን አካል
የሚመረመር አካል አይደለም (ኢዮ ፲፩÷፯ ፩ቆሮ ፪÷፲ _፲፭ ሮሜ
፲፩÷፴፫ መዝ ፴፫÷፲፭ ኢሳ. ፶፱÷፩) ፡፡ ጌታችን አምላካችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር አካል ረቂቅ መሆኑን
ሲያስተምር "እግዚአብሔር መንፈስ ነው" (ዮሐ ፬÷፳፬) ብሎናል፡፡
እግዚአብሔር መንፈስ መባሉ አካል የሌለ
ው ማለት ሳይሆን አካሉ
የማይመረመር የማይዳሰስ የማይጨበጥ የማይታይ መሆኑን
እንደሚገልጽ መንፈስ ቅዱስም መንፈስ መባሉ አካላዊና አካሉም
ረቂቅ መሆኑን ያሰረዳል ፡፡
ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ቃለ ሰብእ እንደ ቃለ
መላእክት ዝርው ያይደለ የአብ የመንፈስ ቅዱስ አካላዊ ቃል
እንደሚባል (ዮሐ ፩÷፩-፫) ሁሉን የሚችል የአምላክ እስትንፋስ የተባለ
መንፈስ ቅዱስም የአብ የወልድ አካላዊ እስትንፋስ ነው፡፡ አካላዊ
በመሆኑም ከአብና ከወልድ ጋር በዙፋን ተቀምጦ ለነቢዩ ኢሳይያስ
ተገልጧል (ኢሳ ፮÷፩-፱ የሐዋ ፳፰÷፳)፡፡ አካላዊ በመሆኑ የአካል
ክፍል በሆነው አንደበቱ እየተናገረ መክሯል "መንፈስ ግን በግልጥ
በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች
ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንት ትምህርት እያደመጡ ሃይማኖትን
ይክዳሉ ይላል (ይናገራል)" ፩ጢሞ ፬÷፩ እንደተባለ፡፡ መምከር ብቻ
ሳይሆን ለቅዱሳን ሐዋርያትም ስለ አገልግሎታቸው መመሪያን
ይሰጣቸው ነበር "እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ
በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ" እንዲል የሐዋ
፲፫÷፪ ፡፡ በሰማይ ድል ስለነሱ ቅዱሳን "ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ
የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው" ተብሎ በተነገረ ጊዜም እግዚአብሔር
መንፈስ ቅዱስ የእኛን አካል የፈጠረ አካላዊ ነውና "አዎን ከድካማቸው
ያርፉ ዘንድ ሥራቸውም ይከተላቸዋል " ብሎ እንደነገረው ቅዱስ
ዮሐንስ ነግሮናል ራእይ ፲፬÷1፲፫ ፡፡
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከዕርገቱ በኋላ
መንፈስ ቅዱስ ወደ እነርሱ እንደሚመጣ ሁሉን እንደሚያስተምራቸው
፣ ምሥጢራትን እንደሚገልጥላቸው ፣ ተአምራትን የሚያደርጉበት
ጸጋና ሥልጣን እንደሚሰጣቸውና መከራንም ሁሉ እንዲችሉ ኃይልን
እንደሚያስታጥቃቸው በሚገባ አስተምሯቸዋል ዮሐ ፲፬÷፳፮ ፡፡
++መንፈስ ቅዱስ የሚሰርጸው ከአብ ብቻ ነው::++
አካላዊ ቃል ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ይግባውና
መንፈስ ቅዱስ የሚሰርጸው ከአብ ብቻ እንደሆነ "ዳሩ ግን እኔ ከአብ
ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ
በመጣ ጊዜ እርሱ ስለእኔ ይመሰክራል" ዮሐ ፲፭÷፳፮ በማለት
አስተምሯል ፡፡መንፈስ ቅዱስ ከአብ ጋር ወልድን ለድኅነተ ዓለም
እንደላከ ("አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል" እንዳለ
ፊተኛና ኋለኛ አልፋና ዖሜጋ መጀመሪያውና መጨረሻው የሆነ ወልድ
ኢሳ ፵፰÷፲፪-፲፮ ራእይ ፩÷፰ ፤ ፳፪÷፲፫) ወልድም ከዕርገቱ በኋላ
የባሕርይ ሕይወቱ የሆነ መንፈስ ቅዱስን ለማንጻት ምሥጢራትን
ለመግለጽ ለማረጋጋት በመንፈሳዊ ሐሴት ደስ ለማሰኘት ኃጢአትን
ለማሥተሥረይ ከአብ ጋር ሆኖ ልኮታል ፡፡ ሠለስቱ ምዕት በጉባዔ ኒቅያ
መቶ ሃምሳው ሊቃውንት በጉባኤ ቁስጥንጥንያ ጌታችን በወንጌል
ያስተማረውን ትምህርት መሠረት አድርገው በጸሎተ ሃይማኖት
"ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ ዘሰረጸ እም አብ ንስግድ ሎቱ ወንሰብሖ
ምስለ አብ ወወልድ ዘነበበ በነቢያት፡- በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን
እርሱም ጌታ ሕይወትን የሚሰጥ ከአብ የሠረጸ ከአብና ከወልድ ጋር
በአንድነት እንሰግድለታለን እናመሰግነዋለን እርሱም በነቢያት አድሮ
የተናገረ ነው" ብለው አውጀዋል ፡፡ ይህን አባቶቻችን ሠለሥቱ ምዕትና
አንድ መቶ ሃምሳው ሊቃውንት ያወጁትን ያስተማሩትን "ዘሠረጸ እም
አብ ፡-ከአብ የሠረጸ" የሚለውን መሠረተ እምነት የካቶሊክ
ቤተክርስቲያን በ589 እ.ኤ.አ በስፔይን ቶሌዶ በተደረገ ጉባዔ
"ከወልድም የሠረጸ" የሚል ሥርዋጽ አስገብታለች ፡፡ በዚህም
ሥርዋጽ ምክንያት በኦርቶዶክስ እና ካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት
መካከል ሌላ መሠረታዊ ልዩነት ተፈጠረ ፡፡ ይህም አለመግባባት
በነገረ መለኮት መምህራን ዘንድ "Filioque controversy" እየተባለ
ይጠራል፡፡
+++ መንፈስ ቅዱስ ባለበት ስፍራ +++
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ባለበት ሥፍራ ሁሉ አርነት አለ "የጌታ
መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ" ተብሎ እንደተጻፈ (፪ቆሮ ፫÷፲፯) ፡፡
አርነቱም ከዲያብሎስ አገዛዝ፣ ከሰይጣናዊ አሠራር፣ ከኃጢአትና
ከሥጋ ፈቃድ ሁሉ ነው :: (ገላ ፭÷፲፱ ፣ ፪ጴጥ ፪÷፲፱ ፣ ሮሜ ፮÷፲፯-፪ ፣
፩ቆሮ ፯÷፲፪ ፣ ፩ቆሮ ፮÷፲፪) ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ጸጋውን የሚያድለው
እርሱም የሚገኘው አንድነትና መተባበር ባለበት ሥፍራ ነው ፡፡ በዕለተ
ጰራቅሊጦስ መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት ጸጋውን ያደላቸው በአንድነት
በእምነት ተሰብስበው በነበሩበት ሁኔታ እንደነበር መጽሐፍ ሲነግረን
"በዓለ ኃምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው
አብረው ሳሉ" ይለናል የሐዋ ፪÷፩-፪፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት የመንፈስ
ቅዱስ ጸጋ በወረደላቸው ጊዜ አልጮኹም ተንቀጥቅጠው
አልወደቁም የነበሩበትን አካባቢ በጩኽት አላወኩም የእግዚአብሔር
የሆኑትን አልተሳደቡም፡፡ የተገለጠላቸውና የተናገሯቸው ቋንቋዎችም
በወቅቱ ከመላው ዓለም የመጡ ሰዎች ይናገሩባቸው የነበረን
ቋንቋዎች (ልሳናት) ነው፡፡ ለዚህም ሰዎቹ "እኛም እያንዳንዳችን
የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን ?" በማለት
በአንክሮ ተናግረዋል የሐዋ ፪÷፰ ፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ከመንፈስ ቅዱስ
በተገለጠላቸው የተለያዩ ቋንቋዎች ዓለም ክርስቶስን በማመን ጽድቅን
በመከተል የሰውን ዘር በሙሉ እንደራሱ እንዲወድ ለኔ የሚያስፈልገኝ
ለሌላውም ያስፈልገዋል እንዲል አስተማሩት፡፡ መንፈስ ቅዱስ ባለበት
ሥፍራ ከልዩነት አንድነት ከእኔነት ይልቅ ለእኛ ማለት ከመገፋፋት
መደጋገፍ ከመበታተን መሰባሰብ ከትዕቢትና ከዕብሪት ትኅትና ጎልቶ
ይታያል፡፡ ስለዚህም "በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ
::" (፪ቆሮ ፲፫÷፭) "መንገዳችንን እንመርምርና እንፈትን :: " (ሰቆ ኤር
፫÷፵) ተብሎ እንደተነገረ ያለንበትን ሁኔታ እየተጓዝንበት ያለንበትን
መንገድ አስተሳሰባችንን ከዚህ አንጻር ልንመረምር ይገባናል ፡፡ የጸጋ
ሁሉ ባለቤት ፈጣሬ ፍጡራን አምጻኤ ዓለማት እግዚአብሔር መንፈስ
ቅዱስ በቸርነቱ ለክብር ለመንግሥተ ሰማያት ያብቃን አሜን!!



አዘጋጅ :-መምህር ቢትወደድ ወርቁ
ግንቦት ፴ ቀን ፳፲፪ ዓ ም
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ዋኖቻችሁን አስቡ። ዕብ 13:7

ይህን ኃይለ ቃል ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለዕብራውያን ሰዎች በላከው መልዕክቱ ያሰፈረው ሲሆን ፍጻሜው ግን በክርስቶስ ክርስቲያን ለተሰኘን ለኛ ለምዕመናን ሁሉ ነው።

ዋኖቻችን እነማን ናቸው? በአጭር ቃል ሐዋርያው «የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁ» በማለት መልሶልናል። እነርሱም ከቀደምት አበው ጀምሮ ነቢያት ሐዋርያት ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ ቅዱሳን ናቸው።

ቅዱሳንን ማሰብ ለምን ይጠቅማል?

1 ከሀሳብ ኃጢአት እንጠበቃለን። ኃጢአት በሀሳብ ይጸነሳል። በነቢብ (በመናገር) ደግሞ ይወለዳል ኋላም በተግባር ሲፈጸም ይጎለብታል ከእግዚአብሔር ይጣላል። ሰው ቅዱሳንን በማሰብ ጊዜውን የሚያሳልፍ ከሆነ ኃጢአትን ለማሰብ ጊዜ አይኖረውም።

2 ከቅዱሳኑ ረድኤት በረከት እናገኛለን። ጠቢቡ ሰለሞን በምሳሌ ምዕራፍ 10 ቁጥር 7 ላይ «የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው።» እንዲል ።

3 ቅዱሳንን አርአያችን በማድረግ እነርሱን ለመምሰል እንጥራለን። ፈጣሪያችን በኦሪቱ «እኔ አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ።» እና በሐዲስ ኪዳንም «የሰማይ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ ፍጹማን ሁኑ።» በማለት የቅድስና ጥሪን ለሰው ልጆች አቅርቧል። ሰው ቅዱስ መሆን የማይችል ቢሆን ይህንን ጥሪ አምላካችን ባላቀረበ ነበር። ነገር ግን ሰዎች ይህንን የቅድስና ጥሪ ተቀብለው በጽድቅ በቅድስናና በንጽሕና መኖር እንደሚቻል ያሳዩን ቅዱሳን ናቸው። ይህንን የቅድስና ጥሪን ተቀብለው በኑሮአቸው ቅዱሳን የሆኑትን ስንመልከት ለጽድቅ ለትሩፋት እንነሳለን። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «እኔ ክርስቶስን እንድመስል እናንተም እኔን ምሰሉ።» 1ቆሮ 11:1 ላይ እንዳለን እነርሱን በማሰብ የበምግባር በሃይማኖት እነርሱን ለመምሰለል እንጥራለን። ጥረታችንም ተሳክቶ ለቅድስና እንበቃለን። ኋላም እነርሱ የገቡበት እንገባለን። እነርሱ የወረሱትን እንወርሳለን።

4 በእግዚአብሔር ላይ ያለን እምነትና ተስፋ እንዲጠነክር ያደርጋል። ለምሳሌ ልጅ ባለመውለድ እየተፈተኑ ያሉ ሰዎች አብርሃምና ሳራን በማሰብ እነርሱን ያልተወ በእርጅናቸው ወራት ልጅ የሰጠ እግዚአብሔርን ተስፋ በማድረግ በእምነት ይጸናሉ።

እንዴት እናስብ?

1 ገድላቸውንና ዜና ሕይወታቸውን በማንበብ። “ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም፥ ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሳራ ተመልከቱ።” ኢሳ 51፥2 እነርሱ በሥጋ ከተለዩን ብዙ ዓመታት ነውና እንደምን ልናያቸው እንችላለን? አብርሃምን በእምነት መነጽር ለማየት ገድለ አብርሃምን ማንበብ ያስፈልጋል።

2 በዓላቸው በማክበር በስማቸው ለመታሰቢያ በታነጸ ቤተ ክርስቲያን በመገኘት ማስቀደስ፣ መሳለም፣ ጠበል መጠጣት፣ እጣንና ጧፍ በመስጠት ማሰብ ያስፈልጋል።

3 በስማቸው ዝክርን በመዘከር (መታሰቢያን በማድረግ) ነድያንን ማብላትና ማጠጣት። ማቴ 10:41

በመጨረሻም ሐዋርያው እንዳለ ቅዱሳኑን አስበን የነሱን አሰረ ፍኖት ተከትለን በምግባር በሃይማኖት እንድንመስላቸው አምላካችን በቸርነቱ ይርዳን። እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ሰዓሊተ ምሕረት ፍቅሯን በልባችን ጧሟን በአንደበታችን ታኑርልን። ቅዱስ አባት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤታቸውን በረከታቸውን ያሳድሩብን።

ይቆየን።

(አቤኔዘር ወልደ ተክለሃይማኖት)

ሰኔ 04 2012 ዓ.ም

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ሥርዓተ ቅዳሴ01
<unknown>
ሥርዓተ ቅዳሴ ክፍል አንድ

በቀሲስ #አስተርአየ ጌጤ

ይዘት
👉ሥርዓተ ቤተክርስቲያን

"ወናስተብቑአክሙ አሐዊነ
ገስጾሙ ለዝሉፋነ" ....

፤ ወንድሞች ሆይ፥ እንመክራችኋለን፤ ያለ ሥርዓት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤
(1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5: 14)

👉 @awedimeherit
👉 @awedimeherit
👉 @awedimeherit