ዐውደ ምሕረት
3.66K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
Forwarded from ዐውደ ምሕረት
Forwarded from ዐውደ ምሕረት
ረቡዕ (የምክር ቀን)

ይህ ዕለት የምክር ቀን ይባላል፣ ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጻሕፋት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር የጀመሩበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ወቅቱ አይሁድ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት በመሆኑና ብዙ ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረከ ተአምራቱንም
የሚያደንቁ ስለነበር ምናልባት ሁከት ይፈጠራል ብለው ሕዝብን እየፈሩ ሊይዙት ያመነቱ ነበር። ተሳክቶላቸው እንያዘው ቢሉ እንኳን ኢየሱስ ክርስቶስን ከደቀ መዛሙርቱ ለይተው አያውቁትም ስለዚህ እርሱን በቅርብ የሚያውቅ ሰው ያስፈልጋቸዋልና በክፉ ምክራቸው እጅግ ተጨነቁ። ትንሽ ቆይቶ ግን ከደቀመዛሙርቱ መካከል አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ በክፉ ምክራቸው በመሳተፍ ጌታን በመሳም አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ቃል ገባላቸው ። ለምልክት ይሁናቸውም ዘንድም እኔ ሄጄ የምስመው ሰው እርሱ ክርስቶስ ነውና ያዙት ብሎ ተማከረ ጭንቀታቸው ተወገደ ለወረታውም ሰላሣ ብር መዘኑለት (ማቴ 26፡1-5 ፣ ማቴ26፡14-15 ፣ ማር 14፡1-2፣ ሉቃ 22፡1-6) 
ዕለተ ዕረቡ(ረቡ) መልካም መዓዛ ያለው ቀን ይባላል፣ ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት (ባለ ሽቶዋ ማርያም) ከእንግዲህ ወዲህ በኅጢዓት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ፣ ኀጢዓትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ፣ በአልባሲጥሮስ ብልቃጥ የሞላ ሽቱ ይዛ በመሄድ በጠጉሩ (በራሱ) ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ነው፡፡ የእንባ ቀን ይባላል ይህም ስያሜ የተሰጠበት ምክንያት ይህችው ማርያም እንተእፍረት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ መላ ኃጢዓቷን ይቅር እንዲልላት በእንባዋ እግሩን አጥባዋለችና፣ በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና፡፡ በጠጉሯም ማበሶ አክሊሌ ነክ ስትል ነው ። የማርያም እንተእፍረትን ኃጢዓት ይቅር ብሎ መባዋን የተቀበለ አምላክ ዛሬ በመካከላችን አለና በማንኛውም ጊዜና ሰዓት የራሳችንን ኃጢዓት በማሰብ በማልቀስና የተወደደ መስዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር በማቅረብ በመልካም ሥራዋ ልንመስላት ይገባል፡፡ (ማቴ 26፡6-13 ፣ ሉቃ 7፡36
፣ ማር 14፡3-9 ፣ ዮሐ 12፡1-8)

ይቆየን…

አዘጋጅ #ተርቢኖስ_ሰብስቤ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
#ሕጽበተ_እግር

በመምህር ዲያቆን #ፋሲል_አስማማው

👇👇👇👇👇👇
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👆👆👆👆👆👆
📢ዓውደ ምህረት 🎤


ዕለተ ሐሙስ

ሕፅበተ ሐሙስ ይባላል

በዚህ ዕለት መምህራቸው ሆኖ ሳለ ክርስቶስ በአጭር ታጥቆ አደግድጓ ወገቡን አስሮ የደቀመዛሙርቱን እግር ያጥብ ዘንድ በትህትና ዝቅ አለ:: ቅዱስ ጴጥሮስም እንዴት የእኛን እግር ታጥባለህ አንተኮ ጌታዬ ነኘ ብሎ ላላመታጠብ በትህትና እግሮቹን ሰበሰበ ጌታችንም በጥምቀት አክብሮ ልጅነትን ሊሰጣቸው ወዶ ነበርና ዛሬ ያልታጠበ ከእኔ ጋር ጽዋ ተርታ ዕድል ፍንታ የለውም አለው። ይህን ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ደንግጦ እንደዛማ ከሆነ እንሬን ብቻ ሳይሆን ሰውነቴንም ጭምር እጠበኝ ብሎ ተናገረ ጌታችን ግን እግሩን የታጠበ ሰውነቱ ንፁዕ ነው ነገር ግን ሁላችሁ ንፁዕ አይደላቹሁም አላቸው አሳልፎ የሚሰጠው ይሁዳ በመካከላቸው ነበርና ዮሐ13÷10 ይህን ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ታጠበ::
ይህም የሚያሳየው ከትህትናው ባሸገር የዓለምን ኃጢዓት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው ‹‹ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘያአትት ኃጢዓተ ዓለም›› የዓለምን አጢኃት የሚስወግድ የእግዚአብሔር በግ ዮሐ 1÷29 እንዲል፡፡ ይህንን ለማስታወስ ዛሬም ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳትና የደብር አስተዳዳሪዎች በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝብህን ኃጢዓት እጠብ ሲሉ በዕለቱ በአጸደ ቤተክርስቲያን የተገኙትን ምዕመናንን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ሲያጥቡያረፍዳሉ፡፡


የምሥጢር ቀንም ይባላል

ለደቀ መዛሙርቱ ይህ ስለ እናንተ የሚፈሰው ደሜ ነው ይህ ደግሞ ስለ እናንተ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው ብሎ ዕብስቱን ባርኮ ወይኑንም ቀድሶ ለሐዋርያት የሰጠበት ቀን ነው ሐዋርያትም ከእጁ ተቀብለው በልተዋል ጠጥተዋል በዚህም ምስጢረ ቁርባንን ፈጽሞላችዋልና ዕለቲቱ የምስጢር ቀን ተብሎ ይጠራል ። ማቴ 26÷ 26-28

ጸሎተ ሐሙስ ይባላል

በፍጥረታት የሚለመንና የሚመሰገን አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለምንና አላዋቂ የሆነውን ሥጋ የተዋሐደ አምላክ፣ ፍጹም ሰው መሆኑን ለመግለጥ አንድም የስጋ ሞት እጅግ አስፈሪ መሆኑን ለማጠየቅና በመከራቹ ጊዜ ወደ ሰማይ አባታችሁ ጸሎትን ጸልዮ ሲል ለአርያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ በጌቴ ሰማኔ በአታክልቱ ሥፍራ ሲጸልይ አድሮል በዚህም ዓብይ ምክንያት ይህ ዕለት ጸሎተ ሐሙስ ተብሏል፡፡ (ማቴ 26፡36-46 ፣ ዮሐ 17)


.......ይቆየን...
አዘጋጅ :-ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ማርያም
👇👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE

🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤
📢 @AwediMeherit📢
📢 @AwediMeherit📢
📢📢📢📢📢📢📢📢
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

"...ስቅሎ ስቅሎ..." ማቴ 27:23

በ5534 ዓ.ዓ የዛሬ 2012 ዓ.ም መጋቢት 27 በዕለተ አርብ የፀሐይ አበቅቴ/ጥንተ ኦን/ 7 :የጨረቃ አበቅቴ 14 : መጥቅዕ 16 : ወንበሩ 4: ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ/ዘመነ ማርቆስ/ ዓመቱ 34 :የአይሁድ ፍሥሕ በዋለ ማግስት አይሁድ "ስቅሎ ስቅሎ" በማለት በሲኦል ሆኖ ማዳኑን ለሚጠባበቀው አዳም ድምፅ ይሆኑ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ አፃፍቶ እርሱ ባወቀ አስጩሆ አናገራቸው በመስቀል መሰቀሉ ግድ ነበርና ይሰቀል ብለውም ጮሁ ፡ ምድርም ልተሸከመው የማትችለው የፈጣሪዋ በፍጡር መሰቀሉ ነበርና፡ሰማይንም አስደንቆ መኑ ከመ አምላክ ብለው ተደመው ተገርመው በዚች ቅድስት ቀን አምላክ በፈጠረው ፍጥረት በመስቀል ተሰቅሎ እርቃኑን በእለተ አርብ አዩት ፀሐይ ጨለመች አምላኳ ተሰቅሎ ታይዘንድ አልወደደችምና፡ ከተቸነከሩት እጆቹ እግሮቹ የሚፈሰውን ደም አይታ መቋቋም የተሳናት ጨረቃ ደም መሰለች ፡፡ከዋክብት የሰማዩ ጌጥነታቸው አልፀናም ወደምድር እረገፉ ፡ ፍጥረቱ በሚችሉት መልኩ የአምላክን መከራ በቋንቋቸው ገለጡ መቃብራት ተከፈተና በመሞቱ ህይወት የሰጣቸው ሙታን ለትንሣኤ ዘጉባኤ ምሳሌ ይሆኑ ዘንድ ከሞት አስነስቷቸዋልና ወደ ከተማ ወጥተው ለብዙዎች ታዩ በዚያኛው ወገን ደግሞ ድኅነቱን የሚጠበቀው አዳም ሱባኤ ቆጥሮ ዘመን ቀምሮ የድኅነቱን ቀን የቃልኪዳኑን መፈፀሚያ የአምስት ቀን ተኩል ኪዳን ሲፈፀም እርሱን አለሙን እንዲሁ ያድናልና ድኅነትን ያገኝ ዘንድ ከአምላክ የተሰጠውን ቃልኪዳን በተስፋ ይጠባበቅ ስለነበር በአንድ በኩል አዳም የአምላክ ሞት ያስፈልገዋል ከልጅ ልጅ ተወልጄ አድንሃለው ተብሏልና በመስቀል ተሰቅሎ መሞቱን በሶስተኛውም ቀን ከሞት መነሳቱን የሚሻ በሲኦል ሆኖ አድኅነኒ እግዚኦ ይላል፡፡እግዚአብሔር የፈጠረው ፍጥረት በአንድ በኩል ሞቱን በሌላይኛው በኩል ትህትናው በማሰብ የአምላክን መሰቀል በሁለት መንገድ ሲመለከት የነበረ ፍጥረት ሁሉ አምላክ በመስቀል ላይ በመሰቀሉ በተዋሕዶ አንድ ሆነ የሁሉም ዓይን ወደመስቀሉ ሆነ እርሱም የተስፋው ኪዳን ፍፃሜ ሆነ፡፡ ለዚህም የድኅነት መንገድ ጴላጦስ ሌላይኛው ተሳታፊ ሆነ በፈቃዱ የሚሞተው አምላክ ሞቱ የግድ ነበርና ""የ ወይቤሉ በርባንሃ ። ወይቤሎሙ ጲላጦስ ምንተ እንከ እረስዮ ለኢየሱስ ዘስሙ ክርስቶስ ። ወይቤሉ ኵሎሙ ስቅሎ ። "" ገዢውም መልሶ ፦ ከሁለቱ ማንኛውን ልፈታላችሁ ትወዳላችሁ ? አላቸው ፤ እነርሱም ፦ በርባንን አሉ ። ጲላጦስም ፦ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን እንግዲህ ምን ላድርገው ? አላቸው ፤ ሁሉም ፦ ይሰቀል አሉ ።
የማቴዎስ ወንጌል 27:22
ህዝቡ ሁሉ ይህን በማለቱ ክርስቶስን የጎዱ መስሏቸው የአዳምን የተስፋ መንገድ ጠረጉ ከአዳምም ጋር ተባበሩ አዳም በሲኦል ሱባኤ ይቆጥር ስለነበር ከአምላክ ዘንድ የተገባለት ቃል ኪዳን ስላለው ህዝቡ ሁሉ ይሰቀል አሉ የትንቢቱ መፈፀምያ የአዳም ልጇች ናቸውና
"ወይቤሎሙ መልአክ ምንተ እኩየ ገብረ ። ወአፈድፈዱ ጸሪኀ እንዘ ይብሉ ስቅሎ ስቅሎ ። ጲላጦስ ፦ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን እንግዲህ ምን ላድርገው ? አላቸው ፤ ሁሉም ፦ ይሰቀል አሉ ።
የማቴዎስ ወንጌል 27:22-23
አባቶችም ስቅለቱ ቀን ዝቅ ካለ <መጋቢት 24 ከፍ ካለ ሚያዚያ 28 >ኢይወረድ ኢየዐርግ ብለው ስርአት ሰሩልን።

እንኳን ለብርሃነ ስቅለቱ በሰላም አደረሰን

…ይቆየን…

#አዘጋጅ #መምህር #ማርቆስ_አለማየሁ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
የዕርቅ ሰነድ
📖📖📖📖📖

 ከሰው ባዳ ከሀገር ምድረ በዳ መርጦ በበርሃ በጫካ ያለ ሽፍታ ቀስት ከእጁ አይጠፋም በሩቅም ሆና ሲመለከት ጠላቱን ጠበኛውን ባለ ጋራውን ሲያይ የቀስቱን መወጠሪያ አውታር  ወደ እራሱ ለጥጦ ቀስቱንም በውስጡ ቀስሮ የቀስቱን ጎበን ወይም አባጣ ክፍል ወደ አየው ጠላቹ አነጣጥሮ ይጠብቀዋል ዋላም ወግቶ ሰንቅሮ ይገለዋል:: ወዳጁን ያየ እንደሆነ ግን የቀስቱን ስርጉድ ክፍል ወደ ወዳጁ የቀስቱንም ጎባጣ ክፍል ደግሞ ወደ እራሱ አድርጎ ሳይወጥር ቀስቱንም በመካከሉ ሳያገባ በጀርባው በተሸከመው አቅፋዳ ሳያወጣ በደስታ ቆሞ እስኪመጣ በናፍቆት ይጠባበቀዋል ::ወዳጁም የሽፍታውን ኩኔታ ተመልክቶ ይርቀዋል ወይም ይቀርበዋል  :: ልክ እንዲሁ ዛሬም ሚያዝያ09/2012 ዓ.ም በደብራችን ሰማይ ሥር ከቀኑ 11ሰዓት ከ33 ደቂቃ ሲል  ሲሚ ሰርክል የሆነ አባጣው ክፍል ከወደ ላይ ስርጉዱም ክፍል ወደ እኛ ወደ ምድር የሆነ ይህ የወዳጅነት ቀስተ ደመና ታይቷል:: ዕብሩም ልዮ ልዮና የሚያምር ነበር ቀስተ ደመና የእመቤታችን ምሳሌ ነው:: የሰው ልጅ በጥፋት ውኃ ከጠፋ በኃላ ኖኃ እና ሰባቱ ቤተሰቡ ከመርከቡ ከወጡ ወጡ እግዚአብሔርም ከእንግዲህ የሰውን ዘር በጥፋት ውኃ ላያጠፋ መተማማኛ ምልክት አድርጎ በሰማይ አሳየው::


"፤ እግዚአብሔርም አለ። በእኔና በእናንተ መካከል፥ ከእናንተም ጋር ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል፥ ለዘላለም የማደርገው የቃል ኪዳን ምልክት ይህ ነው፤  "፤ ቀስቴን በደመና አድርጌአለሁ፥ የቃል ኪዳኑም ምልክት በእኔና በምድር መካከል ይሆናል። "  ፤ በምድር ላይ ደመናን በጋረድሁ ጊዜ ቀስቲቱ በደመናው ትታያለች፤ "  ኦሪት ዘፍጥረት 9÷ 13-14
 የሚገርመው ታዲያ ከእራሱ ከእግዚአብሔር ንግግር ማስተዋል እንደምንችለው  ቀስተ ደመና የእናቱ የእመቤታችን ምሳሌ መሆኗን መናገሩ ነው " ቀስቲቱ" እያለ በአንስታይ(በሴት) ጾታ መጥራቱ ይህን ፍንትው አድርጎ ያሳያል:: ይህውም  ደመና ልዮ ልዮ ዕብረ ቀለም እንዳለው በልዮ ልዮ ዕብረ ንጽሕና የደመቀች የቅድስት እናቱ የድንግል ማርያም ምሳሌ መሆኑን ጭምር "ቀስቲቱ"በሚለው ሐረግ በጉልህ ማስገንዘቡን ማስተዋል ይቻላል  እንደ ተጨማሪ ቀስተ ደመና የእመቤታችን ምሳሌ መሆኑን ለመመልከት የሚከተሉት የመጻሕፍት ክፍሎች መመልከት ይቻላል
"፤ ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆም፥ ዙፋን በሰማይ ቆሞአል በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤ "፤ ተቀምጦም የነበረው በመልኩ የኢያስጲድንና የሰርዲኖን ዕንቍ ይመስል ነበር። በመልኩም መረግድን የመሰለ ቀስተ ደመና በዙፋኑ ዙሪያ ነበረ። " የዮሐንስ ራእይ 4÷2- 3 እመቤታችን ዙፋን ከተባለ ከሥላሴ መንበር ዙፋን ከተባለ ከመስቀሉ ሥር አትታጣም:: መስቀል ዙፋን ተብሏል ማቴ20÷21በዛም ከዮሐንስ ጋር ነበረች ዮሐ19÷  ልጇ ባለበት እርሷ እናቱ ደግሞ በዛ አለች ስለዚህ ልጅን ከእናት እናትን ከልጅ አንነጥል ::  "፤ በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤ "  እንዳለ መጻሕፍ የዮሐንስ ወንጌል 2: 1ዙፋን ካለ ንጉሥ አለ ንጉሥ ካለ ንግስት አለች ::እመቤታችን ዘወትር በንጉሱ ቀኝ የምትቆም ንግሥተ ሰማይ ወምድር ነች "፤ የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው፤ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች። " መዝሙረ ዳዊት 45÷ 9


በአሁኑ ሰዓት ማለትም COVID -19  በዓለም ላይ የሞት ጥላውን አጥልቶ ባለበት በዚህ በምጥ ጣር መጀመሪያ ይህ የምህረት ቀስተ ደመና  መታየቱ የእርቅ የሰላም ዘመን እንዲመጣ በየ ልቡናችን ተሰፋን ያሰንቀን ነው :: ዕለቱ ለወትሮ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስቅለተ የምናስብበት የስግደትና የጥብጣብ ሥርዓት የሚፈጸምበት ልዮ ቀን ቢሆነም በዚሁ ጠንቀኛ በሽታ ምክንያት ቤተ ክርስቲያን ያለ ምዕመኗ ምዕመኗም ያለ ቤተ ክርስቲያን ዕለቱን በእርቀት ለማሳለፍ ተገደዋል ::ይህን ማየቱ በእውነቱ መንፈስን ይረብሻል:: "፤ ጳውሎስም በአቴና ሲጠብቃቸው ሳለ፥ በከተማው ጣዖት መሙላቱን እየተመለከተ መንፈሱ ተበሳጨበት። "   አንዳለ መጻሕፍ የሐዋርያት ሥራ 17: 16 ይባስ ብሎ የመፍትኤ አካል ነኝ ባዮ የመፍትኤ ችግር መሆኑ ይበልጥ እያሳዘነ ያስገርማል ሁለትና ሦስት ሆኖ ተገትሮ አፍ ለአፍ ገጥሞ  ወሬውን እየሰለቀ  የአንዱን ትንፋሽ አንዱ እየማገ የሚገለፍጥ ፖሊስ   መፍትኤ ሳይሆን እራሱ ችግሩን መሆን ነው:: ከዚህ የከፋው ሌላኛው አሳዛኝ ነገር ደግሞ የዓለምን ግፊያና ክፉሁ ምክር ተቋቁሞእንደ እምነቱ ወደ ቤተ ክርስቲያን በፍቅር ሲገሰግስ የመጣውን  ምዕመን በጠመንጃ አፈ ሙዝና በቆመጥ እያስፈራሩ በማባረር  CORONA ን የመቆጣጠር ሥራ እየተሰራ መሆኑ  መታሰቡ ነው በእውነቱ ግን ይህ ማፋፋም እንጂ የነደደውን እሳት ማጥፊያ አይደለም  ፖሊሶስ ይሁን  በዓለም ያለ ዓለማዊ በመሆኑ ብዙ አያስገርመንም ከዛ በላይ የሚጉዳው የቤተክርስቲያኗ አገልጋይ ነኝ ባዮች አጉብዳጅ ነው:: ይበልጡኑ በዚህ ሰዓት ለምዕመኑ እንክብካቤና ደጀን ሆኖ መቆም ሲገባን ሁሉን ትቶ የመጣውን ምዕመን ማንጓጠጥ ፣ ማመናጨቅ፣ አልፎ ተርፎም በአማራጮች ተጠቅሞ የሚገባ ምዕመን ላይ እየደወሉ ጥቆማ መስጠት ያስተዛዘበን ጉዳይ ነው ::ከሰደበኝ የደገመኝ እንዲሉ አበው ከነዚያኞቹ ይህ ይበልጥ ይጠዘጥዛል !ይህ ሁሉ ሳይ  ታድያ ፈጣሪ አብዝቶ እደተቀየመን ታሰበኝ  ይህን ሳወጣና ሳወርድም:ይህ ዕብሩ ልዮ ልዮ የሆነ ቀስተ ደመና ተመለከትኩ  ደህ ኖኅ እና ቃል ኪዳኑም ትዝ አለኝ  ፈገግም እያልኩ ማስታወሻ ለማስቀረት ሞከርኩ ..... ይህ ቀን አልፎ  ምዕመናን ከምዕመናን ምዕመናን ከቤተክርስቲያን ምዕመናን ከነፍስ አባታቸው ምዕመናን ከፈጣሪያቸው ተቀራርበው የማይበትም ቀን እሩቅ እንደማይሆን በልቤ ተስፋን ሰነኩ ... ይቆየን ....አቤቱ ታረቀን ይህን ምልክትህንም የዕርቅ ሰነድ አስብ...አሜን!

ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
አስተያየት ጥቆማ ሀሳብ ከልዎ
👇👇👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE

አዘጋጅ :-ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ማርያም
ሚያዝያ 9/2012ዓ.ም
"፤ አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል። "
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15: 20)
ድንጋዩን ከመቃብር ደጃፍ ማን ያንከባልልልና ?
/መኑ ይከሥታ ለነ ለእብን እምኆኅተ መቃብር/
የማርቆስ ወንጌል 16:3

ክርስቶስ ተንስአ እም ሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አጋዝኦ ለአዳም
ሰላም
እም ይዕዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሠላም።

እርዳታን መሻትና የፍቅር አስገብሮት ጎን ለጎን የተሰለፉበት ያላንዳች ፍርሃት የጨለማውን ዳፍንት ተጋፍጠው የጠባቂዎች ገዳይነት ሳይበግራቸው በመቃብሩ ደጃፍ የደረሱት ከቅዱሳን አንስት መካከል "፤ ሰንበትም ካለፈ በኋላ መግደላዊት ማርያም የያዕቆብም እናት ማርያም ሰሎሜ" ነበሩ። ዳሩ ግን ጌታ እራሱ ያስተማራቸውን ትምህርት ዝንጋዬ በሚመስል አኳኀን የትንሣኤውን ትምህርት ከቶም አላስታወሱትም። ያው በመከራ በጭንቅ ያለ የፊት ፊቱን ብቻ ያስታውሳልና እነሆ እነርሱም የጌታን መቃብር ለመክፈት በጌታ መቃብር ደጅ ተገኙ። እንኳንም በዚያ ለሊት ገስግሰው ተገኙ። እነርሱ የትንሣኤውን ብስራት ለዓለም ሊያበስሩ መፍጠንና በዚህ መከራ ውስጥ ማለፍ ነበረባቸው። ነገር ግን ነገረ ትንሣኤውን በመርሳታቸው እንዲህ ብለው ጠየቁ "እርስ በርሳቸውም" ይላል ቅዱስ ማርቆስ በወንጌሉ ሲጽፍ ፦ "ድንጋዩን ከመቃብር ደጃፍ ማን ያንከባልልልናል ? ይባባሉ ነበር።"
የማርቆስ ወንጌል 16:3
የተጨነቁ ሴቶች በበሩ ቆሙ ድንጋዩ በነርሱ አቅም አይነሳምና እንሆ በልቦናቸው የሳሉት አምላካቸው በመቃብር አለ። ሽቱም መነስነስ ፍቅራቸውን ያረሰርሰዋል ግና ሁለት ነገር ከፊታቸው ይጠብቃቸዋል።
አንደኛው ፡-የመቃብሩ ደጃፍ መከፈት
ሁለተኛው፡-እነርሱ እንዳሰቡት ጌታ በቃብር አለመኖሩ ነው፡፡
በነዚህ ሁለት ነገሮች ከፊት ለፊታቸው የሚጠብቃቸው ሴቶቹ በበር ቆመው የመጀመርያውን ፈተና ለማለፍ እርዳታን ፈልገዋል ነገር ግን ማን እንደሚረዳቸው እራሳቸውን ጠይቀዋል እንጂ ሊራዳቸው የሚችል ሰው አላገኙም ነበር፡፡ ነገር ግን የልብን በጎ መሻት የሚረዳው ጌታ አስቀድሞ የጠየቁትን ጥያቄ መልስ ሰጥቶታል ወንጌላዊው ማርቆስም እንዲህ በማለት ይጽፋል "ድንጋዩ እጅግ ትልቅ ነበርና ፤ አሻቅበውም አይተው ድንጋዩ ተንከባሎ እንደ ነበር ተመለከቱ ። የማርቆስ ወንጌል 16:4
አስቀድመው ተጨንቀው ነበርና መረዳታቸውም ከእግዚአብሔር ነውና ትልቁን ሸክም ተንከባሎ አዩት ነቢዩ እንዳለሁ "፤ አቤቱ፥ እርዳታው ከአንተ ዘንድ የሆነለት፥ በልቡም የላይኛውን መንገድ የሚያስብ ሰው ምስጉን ነው።" (መዝሙረ ዳዊት 84: 5)
ሰማያዊውን መንገድ በልባቸው ፈልገዋል እና እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ ሲመሰገኑ ይኖራሉ። በዚህም የመጀመሪያውን ከፊታቸው የሚጠብቃቸውን ጉዳይ ተገላገሉ እርሱ ጌታ ተራድቷቸዋልና ፡፡
ሁለተኛው እነርሱ እንዳሰቡት ጌታችን በመቃብር አልነበረም። ወንጌላዊው ይህን ሲያስረዳ "ወደ መቃብሩም ገብተው ነጭ ልብስ የተጐናጸፈ ጕልማሳ በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ።"
የማርቆስ ወንጌል 16:5
ያም ጎልማሳ መልአክ ነበር። የሚፈልጉት ማንን እንደሆነ ነገራቸው። "አትደንግጡ ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ ፤ ተነሥቷል ፥ በዚህ የለም ፤ እንሆ ፥ ርሱን ያኖሩበት ስፍራ።"
የማርቆስ ወንጌል 16:6
በማለት የምስራቹን ነገራቸው ጌታ እንደተናገረ መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል ከሙታን መካከል ተለይቶ ተነስቷል በማለት የትንሣኤውን ብርሃን አበሰራቸው። ሴቶቹም ከጎልማሳው ንግግር እንዲሁም ጌታ በመቃብር አለመኖሩ አስደንግጧቸዋልና ከዚህም የተነሳ ተንቀጠቀጡ። ያም መልአክ አንድ ነገር አስታውሶ ሲገልጥላቸው እንዲህ በማለት ነበር፡፡ "ነገር ግን ፥ ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ለጴጥሮስም ፦ ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል ፤ እንደ ነገራችሁ በዚያ ታዩታላችሁ ብላችሁ ንገሯቸው አላቸው።"
የማርቆስ ወንጌል 16:7
በገሊላ እንደሚቀድማቸው በዚሁ ወንጌል እንዲህ ተጠቅሷል
"ነገር ግን ከተነሣሁ በኋላ ወደ ገሊላ እቀድማችኋለሁ አላቸው።"
(የማርቆስ ወንጌል 14: 28)
እንግዲህ ይህ መልአክ ያስታወሳቸው የጌታን የትንሣኤ ትምህርት ነው፡፡
ሌላው የተገለጠው በእጃቸው የነበረው ውድ ለዓለሙ የተላከው ወንጌል ነበር "ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ራሱ ለዘለዓለም ድኅነት የሆነውን የማይለወጠውን ቅዱስ ወንጌል ከፀሓይ መውጫ እስከ መጥለቂያው ድረስ በእጃቸው ላከው።"
የማርቆስ ወንጌል 16:8
ቅዱስ ወንጌሉም በትንሣኤው ብርሃን በዓለም በራ።

…ይቆየን…

#አዘጋጅ #መምህር #ማርቆስ_አለማየሁ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Forwarded from ዐውደ ምሕረት
#በኩረ #ሙታን #ወትንሳኤ

👉👉ክፍል አንድ👈👈👈

ክርስቶስ ተንስዓ ሙታን
በአቢይ ኃይል ወስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግአዞ ለዓዳም
ሰላም
እምይዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም

የተወደዳችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት ልጆች የቅዱሳን ወዳጆች እንደምን ቆያችሁ? አሜን የትንሳኤያችን በኩር አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከባሕሪይ አባቱ ከእግዚአብሔር አብ ከባሕሪይ ሕይወቱ ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጋር ዛሬም ዘውትርም እስከ ዘለዓለም ድረስ በፍጥረቱ አንደበት የከበረ የተመሰገነ ይሁን፡፡ እንኳን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን፡፡

በኩር ማለት የመጀመሪያ ቀዳሚ አለቃ ሹም ማለት ነው፡፡ በኩረ ሙታን ወትንሳኤ ማለት ደግሞ የሙታን እና የትንሳኤ ሁሉ መጀመሪያ ቀዳሚ ማለት ነው፡፡ ይህም የአምላካችን የመድኃታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሞቱ እና ትንሳኤው በኩር እየተባለ ይጠራል፡፡ ይህ ሞት እና ትንሳኤ በኩር ለምን ተባለ የሚለውን ከማየታችን በፊት ራሱ ክርስቶስ በኩር ተብሎ እንደሚጠራ ማወቅ ይኖርብናል፡፡

ክርስቶስ በኩር የተባለው ቀዳሚ የሌለው ቀዳማዊ ማንም ያልሾመው አምላክ ማንም ሊሽረው የማይችል አለቃ እርሱ በመሆኑ በኩር ተብሏል፡፡ ኢሣ 9፡6 አንድም በኩር የእናቱን ማሕጸን የከፈተ የመጀሪያ ልጅ ማለት ነው፡፡ ጌታችንም የአብ ተቀዳሚም ተከታይ የሌለው አንድያ የባሕሪይ ልጁ በመሆኑ በኩር ተብሏል፡፡ አግዚአብሔር አብ ጌታችንን ሲወልደው በጊዜ ባለመቀዳደም በስልጣን ባለመበላለጥ እንጂ ሥጋዊ አባት ልጁን እንደሚበልጥ ያለ አይደለም፡፡ ይልቁኑ በስልጣን የሚተካከለውን አንድ የሚሆነውን በጊዜም የማይበልጠውን አንድያ ልጁን ከፍጥረት ሁሉ በኩር የሆነውን አንድያ ልጁን ወለደው እንጂ፡፡ ዮሐ 10፡30 መዝ 2፡7
አንድም ክርስቶስ በኩረ ማርያም ነው፡፡ የእመቤታችን የመጀመሪያና ብቸኛ ልጅ በመሆኑ በኩረ ማርያም ተብሏል፡፡ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለ ተፈትሖ ማሕጸን በድንግልና በመሆኑ ከሌሎች የሰው ልጆች በኩራት ሁሉ የተለየ ነው፡፡ ማቴ 1፡18 ኢሣ 7፡14
ሌላው ከላይ በርዕሳችን እንዳነሳነው ክርስቶስ በኩረ ትንሳኤ እንዲሁም በኩረ ሙታን ይባላል፡፡ የሰው ልጅ ሁሉ ይሞታል፡፡ ለሞት ያልተገዛ ወደፊትም የማይገዛም ማንም የለም፡፡ ክርስቶስም ቢሆን ሞትን ቀምሷል፡፡ ነገር ግን የኛ የሰው ልጆች እና የጌታችን ሞት ልዩ እንደሆነ ማወቅ ይገባል፡፡ ይህም ስለምንድን ነው ቢሉ ሁለት ምክንያቶችን ማንሳት ይገባል፡፡
፩. ሞት ሁሉን እንዲገዛ ስልጣን የሰጠው ራሱ እግዚአብሔር በመሆኑ፡፡ ይህ ማለት ሞት ሁሉንም ቢገዛም ክርስቶስ ግን በሞት አልተገዛም፡፡ ይህንንም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲናገር ‹‹ሁሉ በክርስቶስ ሕያው ይሆናሉ፡፡ … የኋለኛው ጠላት የሚሻረው ሞት ነው፡፡ ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቷልና፡፡ ነገር ግን ሁሉ ተገዝቷል ሲል ሁሉን ካስገዛለት በቀር መሆኑ ግልጥ ነው፡፡ ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል፡፡›› 1ኛ ቆሮ 14፡22-28 በቃሉ መሰረት ሞት ሁሉን እንደገዛ ነገር ግን ሁሉን ካስገዛለት በቀር ብሎ ክርስቶስ በሞት እንዳልተገዛ ይነግረናል፡፡ ነገር ግን ክርስቶስም ሞትን መቅመሱንም ቀጥሎ ባለው ቃል አስረድቷ፡፡ ‹‹በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል፡፡›› በማለት፡፡
፪. ሁለተኛው ምክኒያት ክርስቶስ ሞትን የቀመሰው ራሱ እግዚአብሔር በወደደ ጊዜ በፈቃዱ በመሆኑ ነው፡፡ ለእኛ ለሰው ልጆች ሞት በፈቃዳችን ወይም በእቅዳችን አይደለም፡፡ የጌታችን ሞት ግን ባሰባት እና ባቀዳት ጊዜ ነው የተፈጸመችው፡፡ ‹‹ጊዜዬ ገና አልደረሰም፡፡›› ዮሐ 2፡2 እንዲሁም ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት በትንቢት ‹‹እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፡፡›› ብሎ የጌታችን ሞት በራሱ በፈቃዱ መሆኑን ገልጦልናል፡፡ መዝ 3፡5 በኋላ ጊዜው ሲደርስም ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ሲለይ ‹‹አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለው፡፡›› ብሎ በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው ለየ፡፡ ሉቃ 23፡46 እኛ የሰው ልጆች ግን መሞታችንን አናውቅም፡፡ ለዚህ ነው ‹‹ቀኒቱን እና ሰዓቱን አታውቁምና እግዲህ ንቁ፡፡›› ብሎ ጌታችን በወንጌል የተናገረው፡፡ ማቴ 25፡12 ሉቃ 12፡20 ጌታችን ግን ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው የሚለየው በፈቃዱና በስልጣኑ እንደሆነ ሲናገር ‹‹ነፍሴን ላኖራትም ላነሳትም ስልጣን አለኝ፡፡›› ሲል አስቀድሞ ተናግሯ፡፡ ዮሐ 10፡18 ሌላው ማስተዋል የሚገባን ክርስቶስ ሞተ ሲባል እንደኛ በድን ሆነ ማለት አይደለም፡፡ እንዴት ቢሉ ወደ መቃብር የወረደው ሥጋ መለኮት የተዋሐደው ነፍስ የተለየው በመሆኑ ነው፡፡ ‹‹እኔ ተኝቻለው ልቤ ግን ነቅቷል፡፡›› ብሎ ጠቢቡ ሰለሞን በትንቢት ሲናገር እንዲሁም ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹በሥጋው ሞተ በመንፈሱ ግን ሕያው ሆነ፡፡›› ብሎ አስረግጦናል፡፡ መኃ 5፡2 እና 1ኛ ጴጥ 3፡19
በመሆኑም ከላይ ባነሳናቸው ሁለት ምክንያቶች ክርስቶስ በኩረ ሙታን እንደሚባል አይተናል፡፡ በቀጣዩ ጽሑፋችን ደግሞ ክርስቶስ በኩረ ትንሳኤ የተባለበትን ምክንያት እንመለከታለን፡፡ የእግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን አማላጅነት የቅዱሳኑ ተራዳኢነት አይለየን፡፡

ይቆየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር፡፡

በወንድማችን #አቤኔዘር የተዘጋጀ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Forwarded from ዐውደ ምሕረት
#በኩረ_ሙታን_ወትንሳኤ

#ክፍል ሁለት

ክርስቶስ ተንስዓ ሙታን
በአቢይ ኃይል ወስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግአዞ ለዓዳም
ሰላም
እምይዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም

የተወደዳችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት ልጆች የቅዱሳን ወዳጆች እንደምን ቆያችሁ?

አሜን የትንሳኤያችን በኩር አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከባሕሪይ አባቱ ከእግዚአብሔር አብ ከባሕሪይ ሕይወቱ ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጋር ዛሬም ዘውትርም እስከ ዘለዓለም ድረስ በፍጥረቱ አንደበት የከበረ የተመሰገነ ይሁን፡፡

በመጀመሪያው ጽሑፋችን ክርስቶስ በኩር እንዲሁም በኩረ ሙታን የተባለበትን ምክኒያት በሰፊው ተመልክተን ነበር፡፡ ለዛሬ ደግሞ ክርስቶስ በኩረ ትንሳኤ የተባለበትን ምክኒያት እንመለከታለን፡፡

ትንሳኤ ማለት ‹‹ተንስአ›› ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ከሙታን ተለይቶ መነሳት ማለት ነው፡፡ ክርስቶስ በኩረ ትንሳኤ ነው ማለት ከሙታን ተለይቶ ለመነሳት ቀዳሚ የመጀመሪያ ነው ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ከክርስቶስ በፊት ከሙታን ተለይቶ የተነሳ የለም ማለት ግን አይደለም፡፡ ታዲያ ስለምን በኩረ ትንሳኤ ተባለ ቢሉ አባቶች ስለ ሁለት ምክኒያት እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡

፩. ሞትን ድል አድርጎ የተነሳው በሥልጣኑ በመሆኑ ነው፡፡ ሌሎች ከሙታን ተለይተው ቢነሱ ለእነርሱ አስነሺ አካል አላቸው፡፡ ለምሳሌ በዮሐ 11፡11-44 ስንመለከት ከሞተ አራት ቀን የሆነውን አልአዛርን ጌታችን ከሞት እንዳስነሳው እንመለከታለን፡፡ አልአዛር ከሞት የተነሳው በራሱ ስልጣን አይደለም፡፡ ይልቁንስ ለመነሳቱ ሌላ አስነሺ አካል አስፈልጎታል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲነሳ ግን ለእርሱ አስነሺ አካል አላስፈለገውም በስልጣኑ ተነሳ እንጂ፡፡ ነገር ግን በሐዋ 3፡15 ላይ ‹‹እግዚአብሔር ከሙታን አስነሳው፡፡›› ተብሎ ተጽፎ እናገኛለን፡፡ ይህ ቃል ለክርስቶስ ሌላ አስነሺ አካል አለው አልያም በስልጣኑ አልተነሳም ለማለት አይደለም፡፡ በመሰረቱ ክርስቶስ ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ ዮሐ 1፡3 ዮሐ 5፡17 ታዲያ እግዚአብሔር አስነሳው ቢባል መለኮትነቱ በሥልጣኑ አስነሳው ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ራሱን በራሱ ማክበር ልማዱ እንደሆነ እንዲሁ እግዚአብሔር አስነሳው ቢባል መለኮትነቱ በስልጣኑ አስነሳው ማለት ነው፡፡ ጌታችን ሳይሞት ከሙታን ተለይቶ የሚነሳው በራሱ ስልጣን፤ ሌላ አስነሺ አካልም አንደማያስፈልገው በዮሐ 2፡19 ላይ ‹‹ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በሦስት ቀንም አስነሳዋለው ፡፡›› ብሏል፡፡ መቅደስ የተባለው የራሱን ሰውነት እንደሆነም ቁጥር 21 ላይ ይመሰክራል፡፡ ከሙታን ከተነሳም በኋላ ሐዋርያት ይህን ቃል አስታውሰውት ነበር፡፡ ዮሐ 2፡22 በመሆኑም በዚህ ምክኒያት ክርስቶስ በኩረ ትንሳኤ ይባላል፡፡

፪. ሁለተኛው ምክኒያት ክርስቶስ ስለ ምን በኩረ ትንሳኤ ተባለ ቢሉ ሌሎች ቢነሱ የሥጋ ሞት ዳግመኛ ያገኛቸዋል፡፡ ክርስቶስ ግን ሞትን ድል አደርጎ ሲነሳ ሞት ዳግመኛ አያገኘውምና በኩረ ትንሳኤ ተብሏል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንጦስ መልዕክቱ 1ኛቆሮ 15፡55 ላይ ‹‹ሞት ሆይ መውጊያህ ወዴት አለ? ሲዖል ሆይ ድል መንሳትህ ወዴት አለ?›› እንዲል፡፡
ስለዚህ ከላይ ባነሳናቸው ሁለት ምክኒያቶች አንደኛው ክርስቶስ ሲነሳ ለእርሱ አስነሺ አካል እንዳላስፈለገው ይልቁኑ በራሱ ኃይል እና ስልጣን በመነሳቱ እንዲሁም ዳግመኛ የሥጋ ሞት ክርስቶስን ስለማያገኘው ክርስቶስ በኩረ ትንሳኤ ተብሏል፡፡ መልካም ዘመነ ትንሳኤ ይሁንልን፡፡
የልዑል እግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን አማላጅነት የቅዱሳኑ ተራዳኢነት አይለየን፡፡ ይቆየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር፡፡

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ከትንሳኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡

☞ ሰኞ- #ማዕዶት ይባላል።
ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡
.
☞ ማክሰኞ- #ቶማስ ይባላል።
በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29
.
☞ ረቡዕ- #አልአዛር ይባላል።
በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡
.
☞ ሐሙስ- #አዳም_ሐሙስ ይባላል።
በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡
.
☞ አርብ- #ቅድስት_ቤተክርስቲያን ይባላል።
በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡
.
☞ ቅዳሜ- #ቅዱሳት_አንስት ይባላል።
በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡
.
☞ እሁድ- #ዳግም_ትንሳኤ ይባላል።
በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡


🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤
📢 @AwediMeherit📢
📢 @AwediMeherit📢
📢📢📢📢📢📢📢📢
#በኩረ #ሙታን #ወትንሳኤ

👉👉ክፍል አንድ👈👈👈

ክርስቶስ ተንስዓ ሙታን
በአቢይ ኃይል ወስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግአዞ ለዓዳም
ሰላም
እምይዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም

የተወደዳችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት ልጆች የቅዱሳን ወዳጆች እንደምን ቆያችሁ? አሜን የትንሳኤያችን በኩር አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከባሕሪይ አባቱ ከእግዚአብሔር አብ ከባሕሪይ ሕይወቱ ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጋር ዛሬም ዘውትርም እስከ ዘለዓለም ድረስ በፍጥረቱ አንደበት የከበረ የተመሰገነ ይሁን፡፡ እንኳን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን፡፡

በኩር ማለት የመጀመሪያ ቀዳሚ አለቃ ሹም ማለት ነው፡፡ በኩረ ሙታን ወትንሳኤ ማለት ደግሞ የሙታን እና የትንሳኤ ሁሉ መጀመሪያ ቀዳሚ ማለት ነው፡፡ ይህም የአምላካችን የመድኃታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሞቱ እና ትንሳኤው በኩር እየተባለ ይጠራል፡፡ ይህ ሞት እና ትንሳኤ በኩር ለምን ተባለ የሚለውን ከማየታችን በፊት ራሱ ክርስቶስ በኩር ተብሎ እንደሚጠራ ማወቅ ይኖርብናል፡፡

ክርስቶስ በኩር የተባለው ቀዳሚ የሌለው ቀዳማዊ ማንም ያልሾመው አምላክ ማንም ሊሽረው የማይችል አለቃ እርሱ በመሆኑ በኩር ተብሏል፡፡ ኢሣ 9፡6 አንድም በኩር የእናቱን ማሕጸን የከፈተ የመጀሪያ ልጅ ማለት ነው፡፡ ጌታችንም የአብ ተቀዳሚም ተከታይ የሌለው አንድያ የባሕሪይ ልጁ በመሆኑ በኩር ተብሏል፡፡ አግዚአብሔር አብ ጌታችንን ሲወልደው በጊዜ ባለመቀዳደም በስልጣን ባለመበላለጥ እንጂ ሥጋዊ አባት ልጁን እንደሚበልጥ ያለ አይደለም፡፡ ይልቁኑ በስልጣን የሚተካከለውን አንድ የሚሆነውን በጊዜም የማይበልጠውን አንድያ ልጁን ከፍጥረት ሁሉ በኩር የሆነውን አንድያ ልጁን ወለደው እንጂ፡፡ ዮሐ 10፡30 መዝ 2፡7
አንድም ክርስቶስ በኩረ ማርያም ነው፡፡ የእመቤታችን የመጀመሪያና ብቸኛ ልጅ በመሆኑ በኩረ ማርያም ተብሏል፡፡ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለ ተፈትሖ ማሕጸን በድንግልና በመሆኑ ከሌሎች የሰው ልጆች በኩራት ሁሉ የተለየ ነው፡፡ ማቴ 1፡18 ኢሣ 7፡14
ሌላው ከላይ በርዕሳችን እንዳነሳነው ክርስቶስ በኩረ ትንሳኤ እንዲሁም በኩረ ሙታን ይባላል፡፡ የሰው ልጅ ሁሉ ይሞታል፡፡ ለሞት ያልተገዛ ወደፊትም የማይገዛም ማንም የለም፡፡ ክርስቶስም ቢሆን ሞትን ቀምሷል፡፡ ነገር ግን የኛ የሰው ልጆች እና የጌታችን ሞት ልዩ እንደሆነ ማወቅ ይገባል፡፡ ይህም ስለምንድን ነው ቢሉ ሁለት ምክንያቶችን ማንሳት ይገባል፡፡
፩. ሞት ሁሉን እንዲገዛ ስልጣን የሰጠው ራሱ እግዚአብሔር በመሆኑ፡፡ ይህ ማለት ሞት ሁሉንም ቢገዛም ክርስቶስ ግን በሞት አልተገዛም፡፡ ይህንንም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲናገር ‹‹ሁሉ በክርስቶስ ሕያው ይሆናሉ፡፡ … የኋለኛው ጠላት የሚሻረው ሞት ነው፡፡ ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቷልና፡፡ ነገር ግን ሁሉ ተገዝቷል ሲል ሁሉን ካስገዛለት በቀር መሆኑ ግልጥ ነው፡፡ ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል፡፡›› 1ኛ ቆሮ 14፡22-28 በቃሉ መሰረት ሞት ሁሉን እንደገዛ ነገር ግን ሁሉን ካስገዛለት በቀር ብሎ ክርስቶስ በሞት እንዳልተገዛ ይነግረናል፡፡ ነገር ግን ክርስቶስም ሞትን መቅመሱንም ቀጥሎ ባለው ቃል አስረድቷ፡፡ ‹‹በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል፡፡›› በማለት፡፡
፪. ሁለተኛው ምክኒያት ክርስቶስ ሞትን የቀመሰው ራሱ እግዚአብሔር በወደደ ጊዜ በፈቃዱ በመሆኑ ነው፡፡ ለእኛ ለሰው ልጆች ሞት በፈቃዳችን ወይም በእቅዳችን አይደለም፡፡ የጌታችን ሞት ግን ባሰባት እና ባቀዳት ጊዜ ነው የተፈጸመችው፡፡ ‹‹ጊዜዬ ገና አልደረሰም፡፡›› ዮሐ 2፡2 እንዲሁም ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት በትንቢት ‹‹እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፡፡›› ብሎ የጌታችን ሞት በራሱ በፈቃዱ መሆኑን ገልጦልናል፡፡ መዝ 3፡5 በኋላ ጊዜው ሲደርስም ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ሲለይ ‹‹አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለው፡፡›› ብሎ በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው ለየ፡፡ ሉቃ 23፡46 እኛ የሰው ልጆች ግን መሞታችንን አናውቅም፡፡ ለዚህ ነው ‹‹ቀኒቱን እና ሰዓቱን አታውቁምና እግዲህ ንቁ፡፡›› ብሎ ጌታችን በወንጌል የተናገረው፡፡ ማቴ 25፡12 ሉቃ 12፡20 ጌታችን ግን ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው የሚለየው በፈቃዱና በስልጣኑ እንደሆነ ሲናገር ‹‹ነፍሴን ላኖራትም ላነሳትም ስልጣን አለኝ፡፡›› ሲል አስቀድሞ ተናግሯ፡፡ ዮሐ 10፡18 ሌላው ማስተዋል የሚገባን ክርስቶስ ሞተ ሲባል እንደኛ በድን ሆነ ማለት አይደለም፡፡ እንዴት ቢሉ ወደ መቃብር የወረደው ሥጋ መለኮት የተዋሐደው ነፍስ የተለየው በመሆኑ ነው፡፡ ‹‹እኔ ተኝቻለው ልቤ ግን ነቅቷል፡፡›› ብሎ ጠቢቡ ሰለሞን በትንቢት ሲናገር እንዲሁም ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹በሥጋው ሞተ በመንፈሱ ግን ሕያው ሆነ፡፡›› ብሎ አስረግጦናል፡፡ መኃ 5፡2 እና 1ኛ ጴጥ 3፡19
በመሆኑም ከላይ ባነሳናቸው ሁለት ምክንያቶች ክርስቶስ በኩረ ሙታን እንደሚባል አይተናል፡፡ በቀጣዩ ጽሑፋችን ደግሞ ክርስቶስ በኩረ ትንሳኤ የተባለበትን ምክንያት እንመለከታለን፡፡ የእግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን አማላጅነት የቅዱሳኑ ተራዳኢነት አይለየን፡፡

ይቆየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር፡፡

በወንድማችን #አቤኔዘር የተዘጋጀ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit