#በኩረ_ሙታን_ወትንሳኤ
#ክፍል ሁለት
ክርስቶስ ተንስዓ ሙታን
በአቢይ ኃይል ወስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግአዞ ለዓዳም
ሰላም
እምይዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም
የተወደዳችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት ልጆች የቅዱሳን ወዳጆች እንደምን ቆያችሁ?
አሜን የትንሳኤያችን በኩር አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከባሕሪይ አባቱ ከእግዚአብሔር አብ ከባሕሪይ ሕይወቱ ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጋር ዛሬም ዘውትርም እስከ ዘለዓለም ድረስ በፍጥረቱ አንደበት የከበረ የተመሰገነ ይሁን፡፡
በመጀመሪያው ጽሑፋችን ክርስቶስ በኩር እንዲሁም በኩረ ሙታን የተባለበትን ምክኒያት በሰፊው ተመልክተን ነበር፡፡ ለዛሬ ደግሞ ክርስቶስ በኩረ ትንሳኤ የተባለበትን ምክኒያት እንመለከታለን፡፡
ትንሳኤ ማለት ‹‹ተንስአ›› ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ከሙታን ተለይቶ መነሳት ማለት ነው፡፡ ክርስቶስ በኩረ ትንሳኤ ነው ማለት ከሙታን ተለይቶ ለመነሳት ቀዳሚ የመጀመሪያ ነው ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ከክርስቶስ በፊት ከሙታን ተለይቶ የተነሳ የለም ማለት ግን አይደለም፡፡ ታዲያ ስለምን በኩረ ትንሳኤ ተባለ ቢሉ አባቶች ስለ ሁለት ምክኒያት እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡
፩. ሞትን ድል አድርጎ የተነሳው በሥልጣኑ በመሆኑ ነው፡፡ ሌሎች ከሙታን ተለይተው ቢነሱ ለእነርሱ አስነሺ አካል አላቸው፡፡ ለምሳሌ በዮሐ 11፡11-44 ስንመለከት ከሞተ አራት ቀን የሆነውን አልአዛርን ጌታችን ከሞት እንዳስነሳው እንመለከታለን፡፡ አልአዛር ከሞት የተነሳው በራሱ ስልጣን አይደለም፡፡ ይልቁንስ ለመነሳቱ ሌላ አስነሺ አካል አስፈልጎታል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲነሳ ግን ለእርሱ አስነሺ አካል አላስፈለገውም በስልጣኑ ተነሳ እንጂ፡፡ ነገር ግን በሐዋ 3፡15 ላይ ‹‹እግዚአብሔር ከሙታን አስነሳው፡፡›› ተብሎ ተጽፎ እናገኛለን፡፡ ይህ ቃል ለክርስቶስ ሌላ አስነሺ አካል አለው አልያም በስልጣኑ አልተነሳም ለማለት አይደለም፡፡ በመሰረቱ ክርስቶስ ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ ዮሐ 1፡3 ዮሐ 5፡17 ታዲያ እግዚአብሔር አስነሳው ቢባል መለኮትነቱ በሥልጣኑ አስነሳው ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ራሱን በራሱ ማክበር ልማዱ እንደሆነ እንዲሁ እግዚአብሔር አስነሳው ቢባል መለኮትነቱ በስልጣኑ አስነሳው ማለት ነው፡፡ ጌታችን ሳይሞት ከሙታን ተለይቶ የሚነሳው በራሱ ስልጣን፤ ሌላ አስነሺ አካልም አንደማያስፈልገው በዮሐ 2፡19 ላይ ‹‹ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በሦስት ቀንም አስነሳዋለው ፡፡›› ብሏል፡፡ መቅደስ የተባለው የራሱን ሰውነት እንደሆነም ቁጥር 21 ላይ ይመሰክራል፡፡ ከሙታን ከተነሳም በኋላ ሐዋርያት ይህን ቃል አስታውሰውት ነበር፡፡ ዮሐ 2፡22 በመሆኑም በዚህ ምክኒያት ክርስቶስ በኩረ ትንሳኤ ይባላል፡፡
፪. ሁለተኛው ምክኒያት ክርስቶስ ስለ ምን በኩረ ትንሳኤ ተባለ ቢሉ ሌሎች ቢነሱ የሥጋ ሞት ዳግመኛ ያገኛቸዋል፡፡ ክርስቶስ ግን ሞትን ድል አደርጎ ሲነሳ ሞት ዳግመኛ አያገኘውምና በኩረ ትንሳኤ ተብሏል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንጦስ መልዕክቱ 1ኛቆሮ 15፡55 ላይ ‹‹ሞት ሆይ መውጊያህ ወዴት አለ? ሲዖል ሆይ ድል መንሳትህ ወዴት አለ?›› እንዲል፡፡
ስለዚህ ከላይ ባነሳናቸው ሁለት ምክኒያቶች አንደኛው ክርስቶስ ሲነሳ ለእርሱ አስነሺ አካል እንዳላስፈለገው ይልቁኑ በራሱ ኃይል እና ስልጣን በመነሳቱ እንዲሁም ዳግመኛ የሥጋ ሞት ክርስቶስን ስለማያገኘው ክርስቶስ በኩረ ትንሳኤ ተብሏል፡፡ መልካም ዘመነ ትንሳኤ ይሁንልን፡፡
የልዑል እግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን አማላጅነት የቅዱሳኑ ተራዳኢነት አይለየን፡፡ ይቆየን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር፡፡
አዘጋጅ #አቤኔዘር_ማሙሸት
👉 @AwediMeherit

Audio
ዓውደ ስብከት
አስተማሪ: #ልዑል_እግዚአብሔር
ተናጋሪ: #መምህር #ኢዮብ_ክንፈ
ርዕስ: #ቅድስት_ትንሳኤ
ክፍል አንድ
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
አስተማሪ: #ልዑል_እግዚአብሔር
ተናጋሪ: #መምህር #ኢዮብ_ክንፈ
ርዕስ: #ቅድስት_ትንሳኤ
ክፍል አንድ
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
ዓውደ ስብከት
አስተማሪ: #ልዑል_እግዚአብሔር
ተናጋሪ: #መምህር #ኢዮብ_ክንፈ
ርዕስ: #ቅድስት_ትንሳኤ
ክፍል ሁለት
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
አስተማሪ: #ልዑል_እግዚአብሔር
ተናጋሪ: #መምህር #ኢዮብ_ክንፈ
ርዕስ: #ቅድስት_ትንሳኤ
ክፍል ሁለት
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
ዓውደ ስብከት
አስተማሪ: #ልዑል_እግዚአብሔር
ተናጋሪ: #መምህር #ተርቢኖስ_ሰብስቤ
ርዕስ: #ከበላተኛ_ውስጥ_መብል_ወጣ መሳ 14:14
ክፍል አንድ
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
አስተማሪ: #ልዑል_እግዚአብሔር
ተናጋሪ: #መምህር #ተርቢኖስ_ሰብስቤ
ርዕስ: #ከበላተኛ_ውስጥ_መብል_ወጣ መሳ 14:14
ክፍል አንድ
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
ዓውደ ስብከት
አስተማሪ: #ልዑል_እግዚአብሔር
ተናጋሪ: #መምህር #ተርቢኖስ_ሰብስቤ
ርዕስ: #ከበላተኛ_ውስጥ_መብል_ወጣ መሳ 14:14
ክፍል ሁለት
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
አስተማሪ: #ልዑል_እግዚአብሔር
ተናጋሪ: #መምህር #ተርቢኖስ_ሰብስቤ
ርዕስ: #ከበላተኛ_ውስጥ_መብል_ወጣ መሳ 14:14
ክፍል ሁለት
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
#ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነኝ አላለም?????
#ክፍል አንድ
በወንድማችን #አቤኔዘር
👇👇👇👇👇
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👆👆👆👆👆
#ክፍል አንድ
በወንድማችን #አቤኔዘር
👇👇👇👇👇
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👆👆👆👆👆
Audio
#ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነኝ አላለም?????
#ክፍል ሁለት
በወንድማችን #አቤኔዘር
👇👇👇👇👇
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👆👆👆👆👆
#ክፍል ሁለት
በወንድማችን #አቤኔዘር
👇👇👇👇👇
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👆👆👆👆👆
#ተከተሉኝ
ይህ የተስፋ ቃል ፍቅሩ የማያልቀው የህያው እግዚአብሔር አብ ልጅ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥሪ ነው። ይህም ታላቅ ጥሪ ከጥንት ጀምሮ እስካሁኗ ሰዓት ዘወትር ይጣራል ብዙኀኑ ሰምተውት ነገር ግን ጥቂቶች ኖረውበታል። አንድ ቀን ጌታችን ደቀመዛሙርቱን "እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ። ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ያጠፋታል፤ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል።" አላቸው ከዛም ከሐዋርያት ወገን በችኩልነቱ እና በፍጥነቱ የሚታወቀው እንዲሁም በእርሱ አለትነት ላይ ቅድስት ቤተክርስትያን የተሰራችበት ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲህ ብሎ ጠየቀ " እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ ፤ እንኪያስ ምን እናገኝ ይሆን ?" ሲል ጠየቀ ጌታችንም መልሶ " እውነት እላችኀለው እናንተስ የተከተላችሁኝ፣ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን ላይ በሚቀመጥበት ጊዜ እናንተ ደግሞ በዐሥራ ሁለቱ የእሥራኤል ነገድ ልትፈርዱ በዐሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ።" ብሎ በምጽዐቱ ዕለት ፈራጅ ዳኛ አድርጎ እንደሚሾማቸው ቃል ገባላቸው። ቀጥሎም " ስለ ስሜም ሴቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል። የዘላለም ህይወት ይወርሳል ነገር ግን ብዙዎች ፊተኞች ኋለኞች ፤ ኋለኞች ፊተኞች ይሆናሉ" ብሎ ጸሐፍት ፈሪሳውያንን ፊተኞች ሐዋርያቱን ኋለኞች እንደሚሆኑ ነግሮአቸዋል ። መቶ እጥፍ ይቀበላል ማለት ፍፁም ክብርን ያገኛል ማለት ነው።....ታድያ ስንቶቻችን ነን ያህን ጥሪ ያስተዋልን? ማነውስ ፍፁም ክብርን መንግስተ ሠማያትን የማይፈልግ? ክብሩን እምንፈልገው ያክል ጥሪውን እንፈልገዋለን? ...ብርሃንን ለማየት በጨለማ ማለፍ ግድ ይለናል ምክንያቱም እሥራኤል ብርሃን ሽተው በጨለማ ተጉዘዋልና ፤ ከፍ ለማለት ዝቅ ማለት ግድ ይለናል ቅድስ ዳዊት ከክብሩ ይልቅ ክርስቶስን አስቀድሞ ዝቅ ብሎ የክብር ጌታ ከፍ ያደረገው ፤ ሰማያዊቷን ርስት መንግስተ ሰማያትን ለማግኘት ትንሹን ምናምንቴውን ዓለም ንቀን ትተን መስቀል የተባለውን መከራ በመሸከም ራስን መካድ ፣ ሥጋችንን መተው ፣ ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ መኖር ያስፈልጋል። ስለዚህ እንከተለው ሕጉ ለመንገዳችን ብርሃን ነውና ...."ሰው አለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ሁሉን ቢገዛ ነፍሱን ቢያጎድል በነፍሱ ከተጎዳ ገሃነመ እሣት ከወረደ ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? መሪረ ገሃነምን ፣ ጣዕመ መንግሥተ ሰማያትን ባያውቅ ነው እንጂ ፤ ቢያውቅማ ኖሮ ለነፍሱ ቤዛ በሰጠ ነበር.. ብሏልና ጌታችን። በአጠቃላይ ይህ ጥሪ እግዚአብሔር ለኛ ያለውን ፍቅር የምናውቅበት ነው እንዴት ብንል የበጎች ጠባቂ ለበጎቹ ካለው ፍቅር የተነሳ ቀን በመስክ በማሰማራት ይውልና በማታ አውሬ እንዳይወስድበት እየገፋ በጩኸት እየተናገረ አንዳንዴም እየቀጣ ከቤቱ ያስገባቸዋል የኛ አምላክ ክርስቶስም ዘወትር ከዚህ አብልጦ በብዙ ነገር ወደ ፈተና ገብተን ወድቀን እንዳንቀር በመላእክቱ ያስጠብቀናል ፣ ተከተሉኝ እያለ ወደ ሕይወት ጎዳና ይመራናል። እስቲ ይህን እናስተውል እኛ ከመኖራችን በፊት ወደደን ስለዚህ ፈጠረን ከጥልቅ ፍቅሩም የተነሳ በአርአያውና በአምሳሉ ፈጠረን። ከመፈጠራችን አስቀድሞ ሁሉን ነገር አዘጋጀልን ሰማይን እንደጣሪያ ሠራና መሬትን አዘጋጀ በመቀጠል ብርሃናትን ፣ውኀ፣አትክልቶችን እና ገነትን አዘጋጀልን በኋላ እኛን ፈጠረ። በኀጢአት ተሰነካክለን በወደቅን ጊዜ የምንድንበትን የድኅነት በር ንስሃን አዘጋጀ ፤ ከፍቅሩ የተነሳ ይመሩን ይመክሩን እና ያስተምሩን ዘንድ ነቢያትን ላከ ክፉውን እና ደጉን የምንለይበትን አስተዋይ ልቡና ሰጠን አስተዋይነታችንንም እንዲያበራልንም የተጻፈ ሕግን ሰጠን በኀጢአት ስንጎብጥ በንስሃ ቀና እንድንል የምትረዳንን ምርኩዝ ድንግል እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን ለዘለዓለም እናት አድርጎ ሸለመን። የእኛን ባሕርይ ባሕርይ አድርጎ ሰው የሆነውም ለኛ ካለው ጥልቅ ፍቅር ነው በእኛ እንደኛ ሆኖ ሕግንም አከበረ ስለወደደን ስለኛ ራሱን ለሕማም ለሞት አሳልፎ ሰጠ። በመስቀልም የፍቅር ስጦታ ሆኖ ቀረበ የዓለምን ኀጢአት ተሸክሞ በደሙ ፈሳሽነት አነጻው ስለኛ ሲል ኀጢአት ሳይኖርበት እንደ ኀጢአተኛ ተቆጠረ።
፦ ለኛ ካለው ፍቅር የተነሳም እነዚህን የተስፋ ቃላት ሰጠን
+ አዲስም ልብንም እሰጣችኃለሁ፤ አዲስም መንፈስንም በውስጣችሁ አኖራለው ..ሕዝ 36፥26
+ በጎቼ ድምጼን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል እኔም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ ለዘለዓለም አይጠፋም ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም ዮሐ 10፥27
+ በአባቴ ቤት ብዙ መደሪያ እን ማረፊያ አለ ፤እንዲህ ባይሆን ኖሮ ቦታ ላዘጋጅላችሁ እሄዳለሁ እላችሁ ነበር። ከሄድሁና ቦታ ካዘጋጀሁላችሁም ዳግመኛ እመጣለሁ፤እናንተም እኔ በአለሁበት ትኖሩ ዘንድ ወደ እኔ እወስዳችኋለሁ። ዮሐ 14፥2-7
+++እነዚህ ሁሉ ለእኛ የተሰጡ ስጦታዎች ናቸው እርሱ እግዚአብሔር እንደወደደን እና እንዳፈቀረን እርስ በእርሳችን ተዋድደን ተፈቃቅረን እሩስም በመራን እና በሚመራን መንገድ እንድንከትለነው የእርሱ ፈቃድ ይሁንልን።
...+++ በቸርነቱ ልቦናችንን አብርቶ የጥሪው ታዳሚ አድርጎ ወደ ሰማያዊዉ መሰብሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ይሰብስበን..አሜን!
ቀን 20/8/12
አዘጋጅ ብሩክ መልሣቸው

ተራ ረቁ
መንገዱ ይከፈት የተጨናነቀው
መተፋፈጉ ነው ሕመም ያስከተለው
መጨካከኑ ነው እርሱን ያስጨከነው
ተራራቁ ወገን አንድም ተራ ረቁ
በንሰሐ መኖር ክርስትና ዕወቁ
ዘረኛውም ቢበዛ አጥንት ቆጣሪው
አቆራርጦት ቀረ ሕዝቡን ከፈጣሪው
የቤተክርስቲያኑ በር ተሳላሚ እራበው
ምዕመን ናፈቀው ጉበኑ እና መቃው
አረ እንዴት ነው ታዛው የተባላንባት
ቦታዬ እርስቴ የተባባልንባት የተጣላንባት
ይህው ሳንወርሳት ወይም ሳንወርስባት
ገረገራው ባዶ ጻድቅ የት አለባት ?
ተራራቁ ወገን አንድም ተራ ረቁ
ብዙ ሰው በመቅረብ እንዳለቀ ዕወቁ
ይቅርብን መመገብ ያልበሰለ ሥጋ
የነፍስ ይሻለናል የዛች በሳል ዋጋ
ተራራቁ ወገን አንድም ተራ ረቁ
በንሰሐ መኖር ክርስትና ዕወቁ
ሚያዝያ 21/2012 ዓ/ም ዕለተ ዕረቡ
ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ማርያም
አዲስ አበባ ኢትዮጲያ
👇👇👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
የእናንተ
መንገዱ ይከፈት የተጨናነቀው
መተፋፈጉ ነው ሕመም ያስከተለው
መጨካከኑ ነው እርሱን ያስጨከነው
ተራራቁ ወገን አንድም ተራ ረቁ
በንሰሐ መኖር ክርስትና ዕወቁ
ዘረኛውም ቢበዛ አጥንት ቆጣሪው
አቆራርጦት ቀረ ሕዝቡን ከፈጣሪው
የቤተክርስቲያኑ በር ተሳላሚ እራበው
ምዕመን ናፈቀው ጉበኑ እና መቃው
አረ እንዴት ነው ታዛው የተባላንባት
ቦታዬ እርስቴ የተባባልንባት የተጣላንባት
ይህው ሳንወርሳት ወይም ሳንወርስባት
ገረገራው ባዶ ጻድቅ የት አለባት ?
ተራራቁ ወገን አንድም ተራ ረቁ
ብዙ ሰው በመቅረብ እንዳለቀ ዕወቁ
ይቅርብን መመገብ ያልበሰለ ሥጋ
የነፍስ ይሻለናል የዛች በሳል ዋጋ
ተራራቁ ወገን አንድም ተራ ረቁ
በንሰሐ መኖር ክርስትና ዕወቁ
ሚያዝያ 21/2012 ዓ/ም ዕለተ ዕረቡ
ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ማርያም
አዲስ አበባ ኢትዮጲያ
👇👇👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
የእናንተ
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🤝ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
🤝 በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
🤝አሰሮ ለሰይጣን
🤝አግዐዞ ለአዳም
🤝ሰላም
🤝እምይዜሰ
🤝ኮነ
🤝ፍስሐ ወሰላም
ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ጥያቄዎቻችሁን ማድረስ ትችላላችሁ
👇👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE
ዓውደ ምህረት የእናንተ
@AwediMeherit
@AwediMeherit
🤝ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
🤝 በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
🤝አሰሮ ለሰይጣን
🤝አግዐዞ ለአዳም
🤝ሰላም
🤝እምይዜሰ
🤝ኮነ
🤝ፍስሐ ወሰላም
ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ጥያቄዎቻችሁን ማድረስ ትችላላችሁ
👇👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE
ዓውደ ምህረት የእናንተ
@AwediMeherit
@AwediMeherit
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
የተወደዳችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአሥራት የቃልኪዳን ልጆች የቅዱሳን ወዳጆች እንደምን ቆያችሁ?
አሜን በቸርነቱ እስከዚህች ሰዓት ያደረሰን የአባቶቻችን የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን፡፡
በዛሬው በምን እንጠይቅልዎ አምዳችን የደረሰንን የዶግማ ጥያቄ እንደሚከተለው እንመልሳለን፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ‹‹ሥላሴ›› የሚል ቃል ተጽፎ እናገኛለን ወይ የሚል ሲሆን መልሱም አዎ በሚገባ ተጽፎ እናገኛለን የሚል ነው፡፡
ነገረ ሥላሴ ጽንሰ ሐሳብ ብቻ ከመሆንም ባለፈ በኦሪትም ሆነ በሐዲስ ኪዳን የሚታወቅና የሚታመን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሥጢር ነው፡፡ በኦሪቱ በምሳሌ እንዲሁም እግዚአብሔር ለወደዳቸውና ለመረጣቸው ቅዱሳን አንድነቱን ሦስትነቱን ገልጦ አሳይቷዋል፡፡ ለምሳሌ በዘፍ 18 ከቁጥር አንድ ጀምሮ እግዚአብሔር ለአብርሃም በሦስትነት ተገልጦ ታይቶታል፡፡ በኢሳ 6 ላይም እንዲሁ ነቢየ ልዑል ቅዱስ ኢሳይያስም የእግዚአብሔርን ልዩ ሦስትነት ተመልክቷል፡፡ ‹‹ማንን እልካለው ማንስ ይሄድልናል›› የሚለው የእግዚአብሔር ንግግር ይህን ያጠነክርልናል፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ሦስቱ አካላት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስን የሚያመለክተው ሥላሴ የሚለው መጠሪያም በመጽሐፍ ቅዱሳችን ላይ ሰፍሮ እናገኘዋለን፡፡
በመሠረቱ መጽሐፍ ቅዱስ የምንለው በቁጥር ተሰፍረው የምናገኛቸውን 81 መጽሐፍትን ነው፡፡ (46ቱ የብሉይ እና 35ቱ የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት) ይህን የቁጥር መጠን በቀኖና ሰፍራ የምትቀበለው ደግሞ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነች፡፡ ከ81ዱ ሳታጎድል ሳትጨምር ትቀበላለች፡፡ በነዚህ መጽሐፍት ውስጥም "ሥላሴ" የሚለው ቃል ተጠቅሶ እናገኛለን። ለአብነትም ጥቂቶቹን እነሆ።
ሄኖክ 5፡38 ‹‹ምዕመናን ለሥላሴ እንዲሰዉ እነርሱም ለአጋንንት ይሰዉ ዘንድ ሰዎችን ያስቷቸዋል፡፡››
ሄኖክ 6፡23 "ፍጹም መቻያቸውን እስተሚቀበሉባት ቀን ድረስ እስከ ጊዜያቸውም ቀን ድረስ እነሱን የሚያኖሩባቸው እነዚህን ቦታዎች ሥላሴ ፈጠሩ።"
ሲራክ 3:22 "ሥላሴ ከሰው ሁሉ ይልቅ የገለጡልህ ምሥጢር የለምና ከግብር ገብተህ የሥላሴን ባሕርይ አትመርምር።"
ሄኖክ 13:14 "በመረጥኋቸው በጻድቃንም እጅ ሥላሴ ይጥሏቸዋል።"
ዮዲት 11:18 "ሥላሴ ለእኔ እንዲህ ያለ ነገር ፈጽመው ነግረውኛ…"
ጥበብ 6: 6 "ለደኃው፣ ግን ሥላሴ ከቸርነት ሥራ የትነሣ ያቃልሉለታል። ኃይለኞች ሰዎችን ግን ጽኑ ምርመራ፣ ይመረምሯቸዋል።"
ሄኖክ 17:17 ፣ ሄኖክ 38:10፣ ጥበብ 17:10፣ ሲራክ 15:17፣ ሲራክ 39:21፣ ሲራክ 44:10 …
ጥቂቶቹ ናቸው።
እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ኃይለ ቃላት የቀኖና መጽሐፍት ተብለው ከሚመደቡት መካከል ሲሆኑ ካለነዚህ መጽሐፍት መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ ሊሆን አይችልም። ለምሳሌ ሉቃ 12:19 ከ ሲራክ 11:19 ጋር ተመሳሳይ የሆነ ሀሳብ ይዘዋል። ማቴ 27:9 ላይ የተፈጸመው ትንቢት የተነገረው ተረፈ ኤር 7:3 ላይ ነው። ይሁዳ በመልእክቱ 1:14 ላይ ያለውን ቃል ቀድሞ የተናገረው በብሉይ ኪዳን ሄኖክ ነበር። ሄኖክ 1:9
የተወሰኑት ማሳያዎች ናቸው።
ይቆየን።

#ቅኔ #ዘአምላኪየ
#በመሪጌታ #አምሳለ_አበበ
ልደተ ድንግል ማእድ አመ ተሠርዐ በሠርክ
አቅረበ ማኅቶተ ብርሃን ራጉኤል መልአክ
ኃይለ ማኅቶት ይስሕብ እምነ ኤልያስ ዐርክ
#ትርጉሙን፣ #ሰሙን እንዲሁም #ወርቁን ይከታተሉ። ለሌሎችም ያጋሩ።
መልካም በዓል!!!!

ከዕሴ ሥር በትር ወጣች
ቤተ ክርስቲያን ግንቦት አንድ ቀን (የግንቦት ልደታ) የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት የሚከበርበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም ‹‹የመመኪያችን ዘውድ፣ የንጽሕናችንም መሰረት›› ያላት ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም የተወለደችበት ነው፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ ‹‹ድንግል ትጸንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች (ኢሳ 7፡14)›› ብሎ ትንቢት የተናገረላት ያቺ ድንግል በዚህች ዕለት ተወለደች፡፡ ይህች ቀን ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት ‹‹ የወርቅ ልብስ ተጎናጽፋ ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች (መዝ 44፡9)›› ብሎ የተናገረላት ንግሥት የተገኘችባት ዕለት ናት፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም በራዕዩ ‹‹ፀሐይን የተጎናጸፈች፣ ጨረቃን የተጫማች፣ አስራ ሁለት የክዋክብት አክሊል በራሷ ላይ ያላት (ራዕ 12፡1)›› ብሎ የመሰከረላት የብርሃን እናቱ ድንግል ማርያም የተወለደችባት ቀን ናት፡፡ የእርስዋም ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ ድንገት የተከሰተ ሳይሆን አስቀድሞ በትንቢት፣ በምሳሌና በራዕይ የሰውን ልጅ ድኅነት በጉጉት ሲጠባበቁ ለነበሩ ቅዱሳን ሲገለጽ የነበረ ነው፡፡
የድንግል ማርያም ልደት በነቢያት አንደበት
መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፡ መሠረቶችዋ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፡፡ መዝ 86፡1-7
እግዚአብሔር የዝማሬና የትንቢት ጸጋን ያበዛለት ክቡር ዳዊት ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥርወ ልደት አስቀድሞ በመንፈስ ቅዱስ መነጽርነት ተገልጾለት ‹‹መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን /መሠረቶችዋ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው/›› በማለት ትንቢት ተናግሯል፡፡ ‹‹የተቀደሱ ተራሮች›› ያለውም የእመቤታችን ሥርወ ልደት ከቤተ መንግሥትና ከቤተ ክህነት ከሆኑት ከተቀደሱት ከኢያቄምና ከሐና የመሆኑን ነገር ሲያመለክት ነው፡፡ ይህንን ትንቢትና እውነተኛውን የእመቤታችንን የትውልድ ሀረግ አስማምታ ቤተክርስቲያን ‹‹የእመቤታችን ማርያም ትውልዷ ባባቷ በኩል ከንጉሡ ከዳዊት ወገን ነው፤ በናቷም በኩል ከካህኑ ከአሮን ወገን ነው፤ የአባቷ ስም ኢያቄም ነው፤ የእናቷም ስም ሐና ነው፡፡›› ብላ ታስተምራለች፡፡
ትወፅእ በትር እምሥርወ ዕሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ፡ ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ አበባም ከእርሷ ይወጣል፡፡ ኢሳ 11፡1
ቁጥሩ ከዐበይት ነቢያት ወገን የሆነው ነቢዩ ኢሳይያስም ጥበብንና እውቀትን በሚገልጽ ስለሚመጣውም ነገር ትንቢትን በሚያናግር በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት ከነገደ ዕሴይ እንደሚሆንና እርሷም ጽጌ (አበባ) የተባለ አካላዊ ቃል ክርስቶስን በሕቱም ድንግልና እንደምትወልድ ተገልጾለት ‹‹ትወፅእ በትር እምሥርወ ዕሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ /ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ አበባም ከእርሷ ይወጣል/›› በማለት ታላቅ ትንቢትን ተናግሮ ነበር፡፡ ይህች በትርም ከእሴይ ዘር የተገኘችው በዚህች ዕለት ነውና ልደቷን በታላቅ ድምቀት እናከብራለን፡፡ ይህንን መሰረት በማድረግ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ‹‹መልካሟ ርግብ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ፤ ከእሴይ ሥር የተገኘሽ መዓዛሽ ያማረ አበባ አንቺ ነሽ›› በማለት በውዳሴ አመስግኗታል፡፡ ‹‹በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ (መዝ 131፡13)›› የተባለልን የአባቶቻችን ልጆች እኛም እንዲሁ እያልን እናመሰግናታለን፡፡
ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ፡ ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ፡፡ መኃ 4፡8
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት መሰረት የእመቤታችን የትውልድ ስፍራ ሊባኖስ የተባለው ተራራማ ሀገር ነው፡፡ በሊባኖስ ስለመሆኑ አስቀድሞ ጠቢቡ ሰሎሞን ‹‹ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ ንዒ ወተወፅኢ እምቅድመ ሃይማኖት እምርእሰ ሳኔር ወኤርሞን አምግበበ አናብስት ወእምአድባረ አናምርት /ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ ከአማና ራስ ከሳኔር ከኤርሞን ራስ ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ ተመልከች/›› በማለት ተናግሮ ነበር፡፡ የዚህ ትንቢት ምስጢርም የእመቤታችን መካነ ልደት የሊባኖስ ተራራ ስለመሆኑ የሚያጠይቅ እንደሆነ ምስክርነታቸው የታመነ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡ ትንቢቱም ሲፈጸም ቅድስት ድንግል ማርያም ግንቦት 1 ቀን በ15 ዓ.ዓ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በሊባኖስ ተራራ ተወልዳለች፡፡
ኢትዮጵያዊ ቄርሎስ የተባለው የነገረ ማርያም ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ እመቤታችን በሊባኖስ እንደምትወለድ አስቀድሞ ሰሎሞን የተናገረው ቃልም መፈጸሙን ሲገልጽ ‹‹….የአናብስት ልጅ አልኩሽ፡፡ ሰሎሞን እንዲህ ሲል እንደተናገረ፡- ሙሽራዪት ሆይ ከሊባኖስ ተራራ ነዪ፤ ከአንበሶች ጒድጓድ ወጥተሽ ነዪ፤ ከምርጥ ነገድነት የተነሣ ከሚመካ ወገን የመወለድሽ ዜና እጅግ ግሩም ነው፡፡›› በማለት አመስጥሮታል፡፡ እመቤታችንም በሊባኖስ ተራራ እንድትወለድ ምክንያት የሆነው በማሕፀን ሳለች የአርሳባንን ልጅ ዓይን በማብራቷና ሳሚናስ የሚባለውን የጦሊቅን ልጅ ከሞት በማስነሳቷ አይሁድ በቅናት ተነሳስተውባቸው ስለነበር ሐናና ኢያቄም ወደ ሊባኖስ ተራራ እንዲሄዱ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለኢያቄም ተገልጾ ስለነገራቸው እንደሆነ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ያስረዳሉ፡፡የድንግል ማርያም ልደት በራዕይና በምሳሌ
ከትንቢቱ በተጨማሪም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት በራዕይና በምሳሌም አስቀድሞ የተገለጸ ነበር፡፡ ከእነዚህም መካከል ከእርሷ ሰባት ትውልድ አስቀድሞ ለነበሩት ደጋግ ሰዎች እንዲሁም ለእናትና ለአባቷ የተገለጹት ምሳሌዎች በቅዱሳት መጻሕፍት በሰፊው ሰፍረው ይገኛሉ፡፡
ሰባተኛዪቱ እንቦሳ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋ ደግሞ ፀሓይን ስትወልድ አየሁ (ቴክታ)
በቅድስና የሚኖሩ ነገር ግን መካን የነበሩት ቴክታና ጴጥርቃ ነጭ እንቦሳ ከበረታቸው ስትወጣ ፤ እንቦሳይቱ እንቦሳ እየወለደች እስከ ስድስት ስትደርስ ፤ ስድስተኛዪቱ ጨረቃን ጨረቃዋም ፀሐይን ስትወልድ አይተው በሀገራቸው መፈክረ ሕልም (ሕልም ፈች ሊቅ) አለና ሂደው ነገሩት፡፡ ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ፤ ጨረቃይቱ ከፍጡራን በላይ የምትሆን ልጅ ትወልዳላችሁ፡፡ የፀሐይ ነገር ግን አልተገለጸልኝም፤ እንደ ነቢይ እንደ ንጉሥ ያለ ይሆናል አላቸው፡፡ እነርሱም ጊዜ ይተርጉመው ብለውት ሄዱ፡፡ ከዚህ በኋላ ልጅ ወለዱ፡፡ ስሟንም ‹‹ረከብኩ ስእለትዬ፤ ረከብኩ ተምኔትዬ›› /የተሳልኩትን አገኘሁ፤ የተመኘሁትን አገኘሁ/ ሲሉ ‹‹ሄኤሜን››አሏት፡፡ ሄኤሜን ዴርዴን፤ ዴርዴ ቶናን፤ ቶና ሲካርን፤ ሲካር ሄርሜላን፤ ሄርሜላ ሐናን ወለደች፡፡ ሐና ለአካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ ይሁዳ ለተወለደ ኢያቄም ለሚባል ደግ ሰው አጋቧት፡፡ ከኢያቄምና ከሐናም በጨረቃ የተመሰለች ድንግል ማርያም ተወለደች፡፡
ፀዓዳ ርግብ ሰባቱ ሰማያትን ሰንጥቃ መጥታ በማሕፀኔ ስታድር አየሁ (ቅድስት ሐና)
ኢያቄምና ሐና መካን ስለነበሩ እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ጸልየው፤ ሲሰጣቸውም መልሰው ለእርሱ እንደሚሰጡ ስዕለትን ተስለው ነበር፡፡ ጸሎታቸው ሲደርስ ለሐና በሕልም ተገልጾላት ለባለቤቷ ለኢያቄም ‹‹ብእሴሃ አነኑ ርኢኩ በሕልምየ ርግብ ጸዐዳ መጽአት ኀቤየ ወነበረት ዲበ ርእስየ ወቦአት ውስተ እዝንየ ወኀደረት ውስተ ከርሥየ /ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብቶ በማሕፀኔ ስትተኛ አየሁ፡፡›› ብላዋለች፡፡ የዚህ ራእይ ምስጢርም ርግብ የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስትሆን፤ ፀዓዳ (ነጭ) መሆኗ ንጽሕናዋ፣ ቅድስናዋ፣ ዘላለማዊ ድንግልናዋ ነው፡፡ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ

ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማሕፀኔ ስትተኛ አየሁ›› ማለቷ ብሥራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ በግብረ መንፈስ ቅዱስ አምላክን የምትፀንሰውን ንጽሕት ርግብ የተባለችውን እመቤታችንን የምትወልድ መሆኗን ሲያጠይቅ ነው::
ከሰባተኛው ሰማይ ነጭ ዖፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ (ቅዱስ ኢያቄም)
በተመሳሳይ ኢያቄምም በሕልሙ ያየውን ለባለቤቱ ለሐና ‹‹እንዘ ይትረኀዉ ሰብዐቱ ሰማያት ዖፍ ጸዐዳ መጽአ ኀቤየ ወነበረ ዲበ ርእስየ /ሰባቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ዖፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ›› ብሎ በሕልሙ የተገለጸለትን ነግሯታል፡፡ የዚህም ራዕይ ምስጢር ዖፍ የተባለው አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፤ ነጭነቱ ንጽሐ ባሕርዩ ነው፡፡ ኢያቄም ‹‹ከላይ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ›› ማለቱ የኢያቄምን ባሕርይ ባሕርይ እንደሚያደርግ የሚያጠይቅ ሲሆን ሰባቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ባህርይው፣ ምልአቱ፣ ስፍሃቱ፣ ርቀቱ፣ ልእልናው፣ ዕበዩና መንግስቱ ናቸው:፡
የድንግል ማርያም ልደት በሐዲስ ኪዳን ሊቃውንት
የሐዲስ ኪዳን ሊቃውንትም ትንቢተ ነቢያትንና ወንጌልን በማጣጣም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ልደት አመስጥረው አስተምረዋል፤ አመስግነዋል፤ ተቃኝተዋልም፡፡ የእርሷን ልደት እጅግ ብዙ ሊቃውንት በስፋትና በጥልቀት ያመሰጠሩት ሲሆን ለምሳሌ ያህል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡
ማርያምስ ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች (ቅዱስ ያሬድ)
ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ስለእመቤታችን ልደት ‹‹ማርያምሰ ተኀቱ እምትካት ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባሕርይ ጸዓዳ/ ማርያምስ (ማርያም ግን) ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች፡፡›› በማለት እርሷ በደፈረሰው ዓለም በንጽሕና፣ በቅድስናና በድንግልና ስታበራ እንደነበርና ኋላም የዓለም ብርሃን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን መውለዷን አመስጥሮ ተናግሯል፡፡ በተጨማሪም ስለ ሥርወ ልደቷ ‹‹እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕጹቂሃ…ሐረገ ወይን/ ሥሮቿ በምድር ጫፎቿም በሰማይ ያሉ…የወይን ሐረግ›› በማለት የተወለደችው በምድር ከነበሩት ኢያቄምና ሐና መሆኑን የወለደችው ግን ሰማያዊውን ንጉሥ እንደሆነ በማመስጠር ዘምሯል፡፡ በዚህም ሰውና እግዚአብሔርን ያገናኘች መሰላል መሆኗል ገልጾ አስተምሯል፡፡
ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም፤ በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐናና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ (አባ ሕርያቆስ)
የብህንሳው ሊቀ ጳጳስ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም ‹‹ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ/ ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም፤ በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐናና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ›› በማለት የድንግል ማርያም ጽንሰትና ልደት እንዴት እንደነበር በድርሰቱ አስፍሮታል፡፡ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት የሚላት የሁላችን እናት ድንግል ማርያም በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐናና ከኢያቄም ነሐሴ 7 ቀን ተፀንሳ ከዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በኋላ ግንቦት 1 ቀን ተወልዳለች፡፡ እርስዋም ስትፀነስ ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ ከጥንተ አብሶ (original Sin) ጠብቋታል፤ አበሳው አልነካትም፡፡ ይህንንም ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ በኃጢአት በተከበበ፣ መርገም በሞላበት ዓለም ውስጥ ከኃጢአት ከበደል ርቃ (ተለይታ) እንደ ጌዲዮን ጸምር በንጽህና የጠገኘች ንጽህት ዘር መሆኗን ሲያስረዳ ‹‹የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንን እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር (ኢሳ 1፡19)፡፡›› በማለት ተናግሯል፡፡ እንዲሁም ጠቢቡ ሰሎሞን ንጽህናዋን በትንቢት መነጽር አይቶ “ወዳጄ ሆይ፣ ሁለንተናሽ ውብ ነው፣ ምንም ነውር የለብሽም፡፡ ሙሽሪት ሆይ ከሊባኖስ ነዪ፡፡” (መሓልይ 4፡7-16) በማለት በንጽህና በቅድስና ያጌጠች፣ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ያልነካት፣ የድህነታችን ምክንያት፣ የንጽህናችን መሰረት የሰው ባህርይ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲዋሀድ ምክንያት የሆነች ንጽሕት የሰርግ ቤት ድንግል ማርያም በሊባኖስ የመወለዷን ነገር አስቀድሞ ነግሮናል፡፡ይህች ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀባት ዕለት ናት (ቅዱስ እንድርያስ)
የቀርጤሱ ቅዱስ እንድርያስ የከበረ ስለሆነው ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልደት ታላቅነት ‹‹ይህ በዓል በሐዲስና በብሉይ ኪዳን መካከል መገኛ ሆነ፡፡ ምሳሌዎቹ በእዉነታ፣ አሮጌው በአዲስ ቃል ኪዳን ተተኩ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በደስታ ይዘምራል፤ የዚህን ቀንም ደስታ ይካፈላል፡፡ ይህ ዕለት (ጌታ) መቅደሱን የሰራበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀበት ዕለት ነው፡፡” በማለት ገልጾታል፡፡ በእውነት የእርሷ ልደት የልዑል ማደሪያው መቅደስ የተሰራበት ዕለት ነውና ሁላችን እናከብረዋለን፡፡ በዚህም ዕለት ‹‹ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም/ እነሆ ዛሬ በእመቤታችን ልደት ደስታ ሆነ›› እያልን እንዘምራለን። ይህችን የልዑል ማደሪያ እናቷ ሐናና አባቷ ኢያቄምም በእጅጉ ተደስተው በተወለደች በስምንተኛ ቀኗ ስሟን ‹‹ማርያም›› ብለው ሰይመዋታል፡፡
የእመቤታችን የልደት በዓል አከባበር
አባታችን አዳም በኃጢአት ከወደቀ በኋላ፣ ንስሃ በገባ ጊዜ አምላካችን ጌታ እግዚአብሔር የድህነት ቃል ኪዳን ገባለት፡፡ ቃል ኪዳኑም “ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ” የሚል ነበር፡፡ ስለሆነም አዳም 5500 ዘመን የሕይወት ምክንያት የሆነች የልጅ ልጁ እመቤታችን ድንግል ማርያም ከአብራኩ ከተከፈሉ ቅዱሳን ልጆቹ የምትወለድበትን ቀን ተስፋ እያደረገ ኖረ፡፡ የእመቤታችንን የድንግል ማርያምን የመወለዷን ዜና ተስፋ በማድረግ “ሴት” ይላት የነበረውን ሚስቱን ሔዋንን በእመቤታችን ምሳሌነት “ሔዋን”፣ የሕያዋን ሁሉ እናት ብሎ ሰየማት፡፡ (ዘፍ. 3፡20) ዳግማዊ አዳም የተባለ ክርስቶስም የአዳምን ተስፋ በመስቀል ላይ በፈጸመ ጊዜ እውነተኛዋን ሔዋን (ዳግሚት፣ አማናዊት ሔዋንን) ድንግል ማርያምን በዮሐንስ ወንጌላዊ በኩል ለሕያዋን ምዕመናን ሁሉ እናት አድርጎ ሰጠ፡፡ (ዮሐ. 19፡26) ይህን የከበረ ምስጢር የማይረዳ “ክርስቲያን” እንዴት ያሳዝናል!? እኛ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ግን የቀዳማዊ አባታችንን የአዳምን፣ እንዲሁም በዳግም ተፈጥሮ ያከበረንን ዳግማዊ አዳም የተባለ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቃል ተቀብለን “የሕያዋን ሁሉ እናት” ድንግል ማርያምን ልደቷን በፍፁም ደስታ እናከብራለን፣ ከተወደደ ልጇ ምሕረትን ትለምንልን ዘንድም ወደ እርሷ እናንጋጥጣለን፡፡
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያለን ምዕመናን ከጌታችን ልደት ቀጥሎ በታላቅ ድምቀት የምናከብረው የልደት በዓል የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያም የልደት ቀን ነው፡፡ ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል (ሉቃ 1፡14)›› ከተባለ የድንግል ማርያም ልደት ምንኛ የሚያስደስት ይሆን?! የነቢያቱ ትንቢት የተፈፀመበት፣ የታየው ራዕይም በገሀድ የተከናወነበት፣ የብሉይ ኪዳን ማብቂያ የሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ ናትና ልደቷ ለሰው ልጆች ሁሉ (ለሕያዋን ሁሉ) ታላቅ የደስታ ቀን ነው፡፡ ሰማያውያን ቅዱሳን መላእክትም በንጽህናዋ በቅድስናዋ ተደንቀው “እህትነ ነያ/እህታችን እነኋት” ብለው ያመሰግኗታል፡፡ በዘመናችን ያሉ የሰዎች ልደት በድምቀት የሚከበር ከሆነ ለሰው ልጅ መዳን ምክንያት የሆነች የአምላክ እናት የተወለደችበ

ት ቀን ምንኛ ሊከበር ይገባው ይሆን?! ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ድንግል ማርያምን ልደት በታላቅ ድምቀት የምታከብረው ከዚህ ታላቅ በዓል በረከት ረድኤትን እንድናገኝበት ነው፡፡ የሕይወት ክርስቶስ እናት ዛሬ ተወልዳለችና፡፡
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትዉፊት መሰረት ሐና እና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደዉ በአድባረ ሊባኖስ ስር እመቤታችንን ወለዱ፡፡ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸዉ ‹‹ንፍሮና ጥራጥሬ›› ነበር፡፡ይህንን ትዉፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ዉጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡ነገር ግን በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ ዓላማዉን ማስፈጸም የሚፈልገዉ ዲያቢሎስ በማር መካከል መርዝን ከሚጨምርባቸዉ መንፈሳዊ በዓላት አንዱ የግንቦት ልደታ (የእመቤታችን የልደት በዓል) ነዉ፡፡ በዚህ ዕለት አንዳንዶች ባለማወቅ ሌሎች ደግሞ በድፍረት ‹‹ለአድባር አዉጋር ነዉ፤ ቆሌዉን ለመለመን ነዉ›› እያሉ ለማያውቁት አምልኮ ንፍሮ የሚበትኑ፣ ቡና የሚረጩ፣ ቅቤ የሚቀቡ፣ የከብት ደም የሚያፈሱ አሉ፡፡ እውነታው እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸው፡፡ እኛ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ግን እነዚህን የሃይማኖት ለዋጮች ሥራቸውን እንጸየፋለን፡፡ ስለሆነም ከእንደዚህ ዓይነቱ ባዕድ አምልኮ በመለየት ይህንን ታላቅ በዓል በተገባና በተረዳ ነገር ልናከብረው ይገባል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን በሠራችልን ሥርዓት መሰረት በቀናች በተዋሕዶ እምነት ሆነን፤ በምሕረቱ የጎበኘንን አምላካችንን ብቻ እያመለክን፤ የድኅነታችን ምክንያት የሆነችውን ድንግል ማርያምንም እያመሰገንን ልናከብረው ይገባል፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ይክፈለን፡፡ አሜን፡፡
ምንጭ :- አስተምህሮ ዘተዋህዶ መካነ ድዕር
ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇👇👇