Audio
#መዝሙር #መቼ_ነው_ጌታ
#በዘማሪ #ሀብታሙ #ሽፈራው
መቼ ነው ጌታ አረ መቼ ነው
መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ/2/
አልተማርኩም አልል አስተምረኸኛል/2/
ቃለህን እንደ ወተት አጠጥተኸኛል/2/
የታል አኗኗሬ አንተን የሚመስለው/2/
በልማድ ሕይወት ነው የምመላለሰው/2/
ይህ አንደበቴማ በቃልህ ሠልጥኗል/2/
ልቦናዬ ካንተ ከፊትህ ኮብልሏል/2/
አንተን እንደማውቅህ አብዝቼ ባወራ/2/
የተዘራው ሁሉ ፍሬ አላፈራ/2/
እዘንልኝና መንገዴን አቅናልኝ/2/
የአመጻ ሥራዬን በደሌን ተውልኝ/2/
ቃልህ እንዳይሰደብ በእኔ ድካም/2/
አርመው እርሻህን መድኃኔዓለም/2/
ከእስራቴ ፈተህ ነጻነት ስጠኝ
በቀኝህ አቁመህ አምላኬ ባርከኝ ጌታዬ ባርከኝ/2/
ኃጢአት ሞትን ወልዶ እንዳያጠፋኝ/2/
የብርሃን ፊትህ ይገለጥልኝ/2/
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#በዘማሪ #ሀብታሙ #ሽፈራው
መቼ ነው ጌታ አረ መቼ ነው
መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ/2/
አልተማርኩም አልል አስተምረኸኛል/2/
ቃለህን እንደ ወተት አጠጥተኸኛል/2/
የታል አኗኗሬ አንተን የሚመስለው/2/
በልማድ ሕይወት ነው የምመላለሰው/2/
ይህ አንደበቴማ በቃልህ ሠልጥኗል/2/
ልቦናዬ ካንተ ከፊትህ ኮብልሏል/2/
አንተን እንደማውቅህ አብዝቼ ባወራ/2/
የተዘራው ሁሉ ፍሬ አላፈራ/2/
እዘንልኝና መንገዴን አቅናልኝ/2/
የአመጻ ሥራዬን በደሌን ተውልኝ/2/
ቃልህ እንዳይሰደብ በእኔ ድካም/2/
አርመው እርሻህን መድኃኔዓለም/2/
ከእስራቴ ፈተህ ነጻነት ስጠኝ
በቀኝህ አቁመህ አምላኬ ባርከኝ ጌታዬ ባርከኝ/2/
ኃጢአት ሞትን ወልዶ እንዳያጠፋኝ/2/
የብርሃን ፊትህ ይገለጥልኝ/2/
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ከቅዱስ ያሬድ በተገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የበዓላት ቀኖና መሰረት የዐቢይ ጾም አራተኛው ሰንበት “መጻጉዕ” ይባላል፡፡ መጻጉዕ ማለት “በሽተኛ” ማለት ነው፡ በዚህ ዕለት ጌታችን በቤተ ስዳ መጻጉዕን ማዳኑን ቤተክርስቲያን ትሰብካለች፡፡ ለ 38 ዓመታት ያህል የፈውስ ተስፈኛ ሆኖ በመጠመቂያው አጠገብ የኖረ መጻጉዕን በአልጋው ተኝቶ ሳለ ደዌው እንደጠናበት ፈውስ እንደዘገየበት አይቶ ‹‹አዎን›› እንደሚለው እያወቀ መጻጉዕን ‹‹ልትድን ትወዳለህን?” አለው። መጻጉዕም ‹‹ሰው የለኝም›› በማለት የመዳን ጉጉቱን ከወዳጅ አልባነቱ ጋር ገለጠ። ጌታም ‹‹ተንስና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ” አለው፡፡ ወዲያው አፈፍ ብሎ በፍጥነት ያን ሁሉ ዘመን የተሸከመችውን ጠንካራ አልጋ ተሸክሟት ሄደ (ዮሐ 5፡1-5)።
ጌታችን መጻጉዕን ‹‹ ተነስተህ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ ›› ያለው ስለ ሁለት ነገር ነው፡፡ አንደኛው ቅዱስ ኤስድሮስ እንዳለው አልጋው ጠንካራ የብረት አልጋ ነበረና ጽንዓ ተአምራቱን ለማሳየት ነው፡፡ ሁለተኛው ‹‹ታዲያ ቢያድነኝ በከንቱ መች ሆነና የገዛ አልጋዬን ትቼለት የመጣሁ
ለመዳኔ ዋጋ የከፈልኩበት አይደለምን?›› እንዳይል መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ያለህን ይዘህ ሂድ እኔ ከአንተ አንዳች አልሻም›› ባሰኘ ቃል ‹‹አልጋህን ተሸክመህ ሂድ›› ብሎታል።
ይህ ሰንበት የሕሙማን ፈውስ መታሰቢያ ዕለት ነው። የሰንበቱም ስያሜ በዕለቱ የሚነበቡትን የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢርና የጾመ ድጓውን ይትበሀል ተከትሎ የተሰየመ ነው፡፡ በመልእክታቱ የሚነበቡት (ገላ 5፡1 እና ያዕ 5፡14) ስለ ድውያን መፈወስ የሚያወሱ ናቸው፡፡ ከሐዋርያት ሥራ የሚነበውም እንዲሁ (ሐዋ 3፡1)፡፡ የዕለቱ ምስባክ እንዲሁ የድውያንን መፈወስ የሚሰብክ ሲሆን “እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ላይ ሳለ ይረዳዋል፤ መኝታውንም ሁሉ ከበሽታው የተነሳ ይለውጥለታል፡፡ እኔስ “አቤቱ ይቅር በለኝ፤ አንተን በድያለሁና ለነፍሴ አስተስርይላት” አልሁ፡፡” ይላል (መዝ 40:3)
ጌታችን መጻጉዕን የፈወሰባት ቦታ ቤተ ሳይዳ ሳትሆን ቤተ ስዳ ናት፡፡
ቤተ ስዳ (Bethesda) በይሁዳ ግዛት ከሚገኙና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተአምራቱን ከፈጸመባቸው ሥፍራዎች አንዷ ናት፡፡ ቤተ ሳይዳ (Bethesaida) ደግሞ በገሊላ አውራጃ የምትገኝ ከተማ ነበረች፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በይሁዳ ኢየሩሳሌም በበጎች በር አጠገብ ያለችዋን ቤተ ስዳን ‹‹በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ስዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት። (ዮሐ 5፥2)›› ብሎ ሲገልጻት በገሊላ የምትገኘዋን ቤተ ሳይዳን ደግሞ ‹‹እነርሱም ከገሊላ ቤተ ሳይዳ ወደሚሆን ወደ ፊልጶስ መጥተው ጌታ ሆይ፥ ኢየሱስን ልናይ እንወዳለን ብለው ለመኑት(ዮሐ 12፥21)›› ብሎ ገልጿታል፡፡
ቤተ ስዳና ቤተ ሳይዳ የተለያዩ ቦታዎች ከመሆናቸው በተጨማሪ የስማቸውም ትርጉምም እንዲሁ የተለያየ ነው፡፡ ቤተ ስዳ ማለት ‹‹ቤተ ሣህል (የጸጋ/የምህረት ቤት)›› ማለት ሲሆን፣ በግሪኩ ቤተ ዛታ ወይም ቅልንብትራ ትባላለች፡፡ ቤተ ስዳ ባለ አምስት በር መመላለሻ አምስት ዓይነት ድውያን ፈውስን ከመጠመቂያው ውኃ ሲጠባበቁ የሚኖሩባት የጌታችን ማዳን የተገለጠባት ሥፍራ ናት። የእግዚአብሔር መልአክ ውኃውን ሲባርክ/ሲያናውጥ ቀድሞ የገባ የሚነጻባት በዕለቱ ከአንድ በቀር ለሌላው ፈውስ የማይደገምባት ቦታ ነበረች። ለዚህም ነው ይህች ስፍራ መጠመቂያና መመላለሻ ያላት በመሆኗ የምህረት ቤት የተባለቸው፡፡ እንደስሟ ትርጓሜ ‹‹ቤተ ስዳ›› የተባለችበትም ምክንያት የሰሎሞን ቤተ መቅደስ አጠገቧ የሚገኝ ሲሆን ለቤተመቅደሱ መስዋእት የሚሆኑ በጎች ሁሉ በዚህ መጠመቂያ ሳይጠመቁ ወደ መስዋእቱ መሰዊያ ቦታ አይቀርቡ ስለነበረ ነው (ዘሌ 9፡2)። ጌታችን በቤተ ስዳ መዳንን ይጠባበቅ የነበረውን መጻጉዕን ፈውሷል፡፡
በቤተ ስዳ መጠመቂያ ይፈጸም የነበረው ድኅነት ምሳሌው እንዲህ ነው፡፡ ውኃውን ያናውጥ (ይባርክ) የነበረው መልአክ የቀሳውስት ምሳሌ፣ ውኃው የጥምቀት ምሳሌ፣ አምስቱ መመላለሻ (እርከን) የአምስቱ አዕማደ ምስጢር፣ የአምስቱ ድውያንና የአምስቱ ፆታ ምዕመናን ምሳሌ ናቸው፡፡ ቤተ ስዳ በዕለተ ቀዳሚት የሚፈወሰው አንድ ሰው ብቻ ነበር፡፡ አንድ ብቻ መሆኑ አለመቅረቱን ሲያሳይ አለመደገሙ ደግሞ ፍጹም እንዳልነበረ ያሳያል፡፡
በአንጻሩ ቤተ ሳይዳ ማለት ደግሞ “የማጥመጃ ቤት” ወይም ‹‹የዓሳ ቤት›› የሚል ትርጉም ያላትና በተለይ ከሐዋርያቱ አሳ አጥማጆቹ ወንድማማቾች እና ቅዱስ ፊልጶስ የነበሩባት መንደር ነበረች (ዮሐ·1፡45)። ይህች ከተማ ‹‹የዓሳ ቤት›› የተባለችውም ከገሊላ ባህር ዳር የምትገኝ ስለሆነችና ዓሳ የሚያሰግሩ ሰዎች የሚነግዱባት ስለሆነበረች ነው። በዚህ በሞቀ ንግዷ የተነሳ ከተማዋ የተሰበከላትን ወንጌል ለመስማት ባለመቻሏ ጌታችን በተናገረው ትንቢት መሰረት ከሌላዋ ከተማ ከኮራዚን ጋር አብረው ጠፍተዋል (ማቴ 11፣21)፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተ ሳይዳም ድውያንን ፈውሷል (ማር 8፡22-25)፡፡
መጻጉዕ ግን ያዳነውን ረሳ፤ በሐሰትም መሰከረበት፤ ወደቀደመ “ደዌውም” ተመለሰ፡፡
መጻጉዕ ቀድሞ በቤተ ስዳ እያለ የነበረበትን ያንን ሁሉ ጭንቅ ኋላ በሊቶስጥሮስ አደባባይ ሲቆም ረሳው፡፡ ይህ ምስኪን መጻጒዕ “ሰው የለኝም” ብሎ የደረሰለትን ሰው ረሳ፡፡ ያዳነው ማን እንደሆነ ሲጠየቅ እንኳ አላወቀም። ወንጌላዊውም ‹‹የዳነው ያዳነውን አላወቀውም›› ( ዮሐ.5፥13) ይለዋል። በምኩራብ አግኝቶት ያዳነውን እንዳወቀውም ሄዶ ለአይሁድ ያዳነኝ እርሱ “ጌታ ኢየሱስ ነው” ብሎ ነገራቸው፡፡
ጌታችን መጻጉን ‹‹ ልትድን ትወዳለህን ›› ያለው አስፈቅዶ ለማዳን እንዲሁም በዕለተ ዓርብ ‹‹አድነኝ ሳልለው አድኖኝ›› እንዳይል ሲሆን መጻጉዕ ግን ‹‹ ሰው የለኝም›› ያለው ያድነኛል ብሎ ሳይሆን ‹‹ወደ መጠመቂያው ያደርሰኛል›› ወይም ‹‹ከሚከተሉት አንዱን አዝዞ ወደ መጠመቂያው እንዲያደርሰኝ ያደርጋል›› ብሎ ነበር፡፡
አንድ ሊቅ ይህን ‹‹ታሞ የተነሳ ፈጣውን ረሳ›› የተባለለት መጻጒዕ እና በሐሰት የተከሰሰውን ይቅር ባይ አምላኩን እያደነቀ በጉባዔ ቃናው እንዲህ ተቀኘ፡፡ ” ይትዐረቅ ምስለ ብእሲት ደዌሁ፤ ሠላሳ አዝማነ እስመ ነበረት ምስሌሁ ” (ትርጉም፡ መጻጒዕ ከሚስቱ ከደዌ ጋር ይታረቅ ፤ ሠላሳ ዓመታት ከእርሱ ጋር ኑራለችና)፡፡ ለብዙ ዓመታት አብረው የኖሩ ባልና ሚስት ሲፋቱ ከናፍቆት የተነሳ መለያየቱ እንደሚከብዳቸውና ተመልሰው እንደሚታረቁ ሁሉ ‹‹ከዚህ የባሰ እንዳያገኝህ ዳግመኛ አትበድል›› ተብሎ ከጌታ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው መጻጉዕም ያዳነውን ጌታ በጥፊ መትቶ ዳግመኛ ወደ 38 ዓመት “የአልጋ ወዳጁ” ደዌ ተመልሶ ከእርስዋም ጋር መታረቁን የቅኔው ምስጢር ያስተምረናል። ጌትችን ከደዌው ነጻ አወጣው፤ እርሱ ግን ከደዌው ተለያይቶ መኖር ከብዶት ተመልሶ ታረቃት፡፡ኋላም በአውደ ምኩናን የሐሰት ክስ የቀረበበትን ጌታችንንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን ቀድሞ ወደ መጠመቂያው እንኳ ለመቅረብ አቅም ያልነበረው ዛሬ ግን አልጋ ለመሸከም በበቃውና ያለ ተረፈ ደዌ በጸናው ኃይሉ የጌታውን ጉንጮች በጥፊ የመምታት ጉልበትና ድፍረት አገኘ ። አምላከ ምሕረት የክብር ጌታ ቀድሞ ‹‹ከዚህ የጠናው” ስለ ደዌ ሥጋ ፈንታ ደዌ ነፍስ እንዳያገኝህ ዳግመኛ እንዳትበድል” (ዮሐ 5፡14) ያለውን ዘንግቶ ደዌ ዘኃጢአትን ጠርቶ ተወዳጃት፤ በዕለተ ዓርብ የጌታውን ጉንጮች የጸፉች እጁም ደርቃ ቀርታለች፡፡
የዐቢይ ጾም አራተኛው

ሰንበት እኛም የታመሙትን መጎብኘት እንዳለብን የምንማርበት ነው፡፡
ይህ ሳምንት “መጻጉዕ” ጌታችን ድውያንን ስለመፈወሱ የሚነገርበትና እኛም ባለን አቅም በነፍስ በሥጋ የተቸገሩትን ሁሉ መርዳትና ማገዝ እንዳለብን የምንማርበት ሳምንት ነው፡፡ ሕሙማንን መጠየቅ፣ የታሰሩትን መጎብኘትና ማስፈታት፣ የተራቡትን ማብላት፣ የተጠሙትን ማጠጣት፣ የታረዙትን ማልበስ ያዘኑትን ማረጋጋት ከጌታችን የተማርናቸው ክርስቲያናዊ ምግባራት ናቸው፡፡ ይህንን በማስተዋል የሚያስፈልገንን ሁሉ የሰጠንንና ከክፉ ነገር የጠበቀንን አምላክ ውለታውን እያሰብን ልናመሰግነው ይገባል፡፡ መጻጒዕ መጀመሪያ የነበረበት ደዌ ሥጋ ነበር፣ ይህንንም ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አራቀለት/አዳነው፡፡ ይሁንና በጌታችን ስቅለት ከአይሁድ ጋር በመተባበሩ፣ ያዳነውን ባለማመኑ ግን ደዌ ነፍስ አገኘው፡፡ እኛም እንደ መጻጒዕ ደዌ ነፍስ እንዳያገኘን ያዳነንን አምላካችንን ልናውቀው፣ ልናምነው፣ በህጉና በትዕዛዙም ልንሄድ ያስፈልጋል፡፡ ያን ጊዜ ከደዌ ነፍስ እንድናለን፡፡ ያንን ተስፋ ያልነበረውን በሽተኛ ከደዌ ሥጋው ፈውሶ ሕይወትን የሰጠው አምላክ፣ እኛንም በውስጥ በአፍአ ካለብን ደዌ ሥጋና ደዌ ነፍስ እንዲፈውሰን፤ ቁስለ ኃጢአታችንን እንዲያደርቅልን፣ በሕይወትና በጤና እንዲጠብቀን የእርሱ የጌታችን ቅዱስ ፈቃድ ይሁንል አሜን🙏
ምንጭ :-አስተምህሮ
#ለከበረው ሀሳብዎ
👉@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE
ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
#ዓውደ-ምህረት የእናንተ
🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤
📢 @AwediMeherit 📢

እንደምን አመሻችሁልን ውድ የዓውደ ምህረት ተከታታዮቻች እነሆ ሳምንታዊው የምን እንጠይቅልዎ ፖሮግራማችን ጀመረ
1⃣ ጠያቂያች ወለተ ጊዮርጊስ እንዲ የሚል ሀሳብ አዘል ጥያቄ በውስጥ መሰር ወርወር አድርገውልናል::ወቅቱ አንተ የእነ እንታ ዘር አንተ የእነ እንትና ዘር እየተባባሉ እርስ በእርሳቸው በጎራ የሚሻኮቱበት እንደሠሆኑ መጠን ዘረኝነትን አስመልክታችሁ አጠር ያለህ ትምህርት ብታስተምሩን የሚል ነው::
ለጠያቂያችን ለወለተ ጊዮርጊስ የሕይወትን ቃል ያሰማልን እያልን ከክታበ መለከት ካገኘናት ጽሁፍ ለጊዜው ትሆነን ዘንድ ይዘንላችሁ ቀርበናል ተከታተሉን::
ዘር መቁጠርና መዘዙ
የሰው ዘር መገኛ መሠረቶች አዳምና ሔዋን መሆናቸውን ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል:: እኛ የሰው ዘሮች በምልዐት የሰፈርንባት ከመነሻችን ከአዳም መጀመሪያ ሆነን እግዚአብሔር በሰጠን ቡራኬ እየበዛን እስካለንበት ዘመን ደርሰናል::በዘመናችን በተለይ በተለይ በቅድስት ኢትዮጲያ ዲያቢሎስ ያሰለጠናቸው ሰዎች አንደበታቸውን በተቆጣጠረው መንፈስ እየተመሩ የመለያየት መንፈስ እንዲፈጠር በማድረግ ብዙ ጥፋቶችን እየፈጸሙ ነው በዚህ መዘዝ በከንቱ የሚፈሰው ደም ለወደፊቱ አጥፊዎቹ ከስህተታቸው ካልታረሙ የሚያፈሱት የደም ጎርፍ እነርሱኑ አጥፊዎቹን እንደ ባህር ማስጠሙ አይቀርም::
ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በመለያየት ላይ የነበሩትን የግሪክና የአይሁድ ሰዎችን ሲገስጽ እንዲ ብሏል:: "አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም ባርያ ወይም ጨዋ ሰው የለም ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና" ገላ3÷28
እንግዲህ የተቀደሰው ሐዋርያ እንደነገረን እንኳን ኢትዮጲያዊ ዜጋ ቀርቶ አይሁዳዊና የግሪክ ሰው መላው የሰው ዘር የተፈጠረው በእግዚአብሔር ፈቃድና ቸርነት ሰለሆነ እንደ አንድ ሰው ተቆጥሮ በሰላምና በስምምነት በፍቅር ተከባብሮ በአንድነት መኖር ይጠበቅበታል::
ይህ ጥቅሙ ለህሊና ጤንነት ነው :: በጠብና ባለ መስማማት ምን ትርፍ ይገኛል ::ለመሆኑ በጤነኛ አእህምሮ ስናስበው በተፈጥሮ እኛን የሚመስለውን ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት እንዲወጋ ማድረግ ፣ ማፈን ፣ ዐይኑን እጁን እግሩን ስንቆራርጠው ድርጊቱን ለመፈጸም የገፋፋንን መንፈስ እንዴት ለመመርመር ተሳነን ? እንዴትስ ይህን ድርጊት መፈጸም ሰውነታችን ሊቀበለው ቻለ ድርጊቱንስ ስንፈጽመው ሰው እንኳን አጠገባችን ባይኖር ህሊና የሚባለውን ዳኛ እንዴት ሳናፍረው ቀረን? ከዚህ በላይ የፈጠረንን አምላክ እንደምን ችላ አልነው? ማንም ሰው የጭካኔ ሥራን ለመሥራት ሲነሳሳ ሰውነቱን ወይም ምንነቱን ስለረሳ ነው ወደ ጭካኔ አሰራር የሚገባው የትኛውም ሰው ክፉ ተግባርን በሌሎች ሲፈጽም ድርጊቱን በገዛ ሰውነቱ ላይ እንደፈጸመ ይቆጠራል:: ምክንያቱም ወገኑን የሚቆራርጥበት ስለት ሰውነቱን ቢወጋው ጉዳቱ እንደሚሰማው አከራካሪ አይደለም::ስለዚህ ሚዛናዊ አእምሮ ማጣት ካልሆነ በስተቀር በጭካኔ ወንድሙ ወይም እህቱ ላይ ስለቱን ሲያሳርፍ በገዛ ሰውነቱ ላይ እዳሳረፈ ለአፍታ ቢሰማው ኖሮ ለክፉ መንፈስ ተላልፎ መሰጠት አይኖርም ነበር::
በትንቢተ ሆሴ 4÷6 ላይ " ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቶል " እንዲል የዕውቀት ማነስ ብቻ ሳይሆን የዕውቀት መብዛትም የብዙ ሰዎችን ዐይን አሳውሮ የማንነትን ጉዞ በማተረማመስ በጨለማ ውስጥ ሆኖ የጥፋት ድርጊቱን ማጧጧፉን ቀጥሏል:: በተለይ ምሁራን ለችግሮች ሁሉ መፍትኤ እንደሚሰጡ ይገመት ነበር እንዳለ መታደል ሆኖ ዛሬ በዘረኝነት ጽኑ ህመም ተይዘው የጸናው ሕመም እራሳቸው ላይ ሰለወጣ ስተው የሚያስቱ ከኤች አይ ቪ ኤድስና በጊዜያችን ከተነሳው ወረሽኝ ከኮሮና ቫይረስ ይልቅ ብዙዎችን እየጨረሰ ያለው የዘር በሽታ ሰለባ መሆናቸው እጁግ ያሳዝናል:: ይህ የዘር በሽታ የሕመሙ መተላለፊያ መንገድ መገናኛ ብዙኃን በመሆናቸው የሚሰማቸውና የሚያቸውን እንዲሁ የሚያነባቸውን ሁሉ የመመረዝ ኃይላቸው ከፍተኛ ነው ::እልቂቱም እጅግ የከፋ ይሁናል :: ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ጥበበኞች ወይም ስለ ሙሁራን መሳት እንደሚከተለው ተናግሯል "ጥበበኛ የት አለ ? ጸአፊስ የት አለ? የዚህ ዓለም መርማሪስ የት አለ? እግዚአብሔር የዚህችን ዓለም ጥበብ ሞኝነት እንዲሆን አላደረገምን?"1ቆሮ1÷20
እጅግ የተመሰገነው የእግዚአብሔር አገልጋይ ቅዱስ ጳውሎስ የጻፈልንን ይህን ንግግር ከዘመናችን አንጻር ብንመዝነው ከዓለም አቀፍ እስከ አህጉራችን እና እስከ ትንሿ ሀገራችን ብናይ ጥበበኞች ጸአፊዎች ተመራማሪዎች ጥበባቸው የከበረ የሰው ልጅ ከመጥቀሙ በተቃራኒው አጥፊ እየሆነ እንደመጣ እየተመለከትን ነው::
ማብቂያ የሌላቸው ጦርነቶች ንጹሐን ሕጻናትን አረጋዊያንን ደካሞችን ብቻ ሳይሆን የጎበዛዚትንም ሕይወት እየቀጠፈ ነው ::ዓለም በትርምስ በእልቂት እየተቀጣ ነው የእልቂቱም መንገድ እጅግ ያስገርማል ሰደድ እሳት ፣ የመሬት ነውጥ ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ፣ ጎርፍ፣ ርሃብ፣ ቸነፈር፣ድርቅ፣ አውሎ ነፋስ ፣የአሸባሪና ተሸባሪ መጠፋፋት ወዘተ በዘመናችን የሚገኙ የእግዚአብሔር ቁጣ መገለጫዎች ናቸው ::አሁን አያላን ነን ብለው የሚስቡ እኔ ከማን እንሳለው በማለት ዓለም ይጠፋል እንጂ ከሥልጣኔ ከዙፋኔ አልወርድም የታላቆች ታላቅ ነኝ የሚል የመከረ መፍለቂያ ንግግር ወደ ማያባራ የነፍስና የሥጋ መከራ ብዙኃኑን ወደ ሞት መንገድ እየወሰደ ይገኛል ::በልዮ ልዮ ደረጃ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች እየተባሉ ውይይቶች ይደረጋሉእጅግ የሚገርመው ነገር ግን በጉባኤው የእግዚአብሔር ስም አይጠራም ታዲያ እንዴት ከቁጣና እልቂት ለመዳን ይቻላል? ያልተፈታ እቆቅልሽ ነው :: ከፍ ብለን በዓለም አቀፍ ደረጃ የተገለጠውን በቅድምያ የመቀመጫና መቆሚያን ወይም ቅድሚያ የሀገር ጉዳይ ካልን ደግሞ ወደ ሀገራችን ኢትዮጲያ መለስ ብለን "ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች " የሚለውን አስበን ወደ ፈጣሪ በችግሮቻችን ዙሪያ መለመን ብንጀምር እና ወደ ቀሪው ጉዳያችን ብናልፍ የሚሻለው መንገድ ይህ ነበር :: መዝ 67(68)÷31
ለዚህ በጎ ሀሳብ አዋቂዎች በጥብዐት ስመ እግዚአብሔርን ጠርተው ቢወያዮ መልካም ሁሉ ለቅድስት ሀገራችን ይሆንላት ነበር::ዘር መቁጠሩም ቀርቶ ሁሉም ፊደል ይቆጥር ነበር :: ፊደሉም እ....ን....ስ....ማ......ማ.....የሚል ነው::
ይህችን ጊዜያዊ የእንግድነት መኖሪያችንን ስንለቅ ዘር ጾታ ቀለም የሥልጣን የሀብትና ዕውቀት ጀረጃ ሳይለያዮባት መልካም የሥራ ሁሉ የአዳም ዘር የሚወርሳት ገነት መንግሥተ ሰማያት አስበን በጊዜያዊ ምድራዊ ሕይወት ጥቅም ዘላለማዊ መንግስት እንዳናጣ እንጠንቀቅ ለዚህም የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን ተራዳይነት አይለየን......አሜን
አዘጋጅ :- ተርቢኖስ ሰብስቤ(ኃ/ማርያም)
@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE
👇👇👇👇
ዓውደ ምህረት የእናንተ
🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤
📢 @AwediMeherit 📢
📢 @AwediMeherit 📢
🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መለከት
27ዓመት ቁጥር2 ገጽ 2012ዓ.ም

አንድ ቀን አለ.mp3
931.8 KB
#መዝሙር #አንድ_ቀን_አለ
#በወንድማችን #ዘማሪ #ሀብታሙ_ሽፈራው
#መሰንቆ #ማርቆስ_አለማየሁ
#ክራር #ሀብታሙ_ሽፈራው
አንድ ቀን አለ የሚያስፈራ
ለጻድቃን የሚያበራ(2)
ጌታ በዚያች ቀን ይመጣል
በክበሩ ይገለጻል(2)
አብረው ከእርሱ ጋር ይመጣሉ
ቅዱሳን መላእክት ሁሉ(2)
ጌታ በዚያች ቀን ይመጣል
በዙፋን ይቀመጣል(2)
የምሕረት አዋጅ ይታወጃል
ነፍስ ሁሉ ይጨነቃል(2)
ኃጥአን ሁሉ ያለቅሳሉ
በግራው ይቆማሉ(2)
ቅዱስ ቃሉን ሰምተው ያመኑ
የጸኑ በኪዳኑ(2)
አብረው በቀኙ ይቆማሉ
ከሀዘን ይሰወራሉ(2)
መኃሪ ጌታ ፈጣሪያችን
ይድረስህ ልመናችን(2)
በዚያ ግሩም ቀን እባክህን
አቁመን በቀኝህ(2)
"በዕለተ ምጽዐት በቀኙ ያቆመን ዘንድ የአምላካችን ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን።"

ዛሬ የደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ካህናት የኮሮና ቫይረስን ለማጥፋት የጻድቁን ቃልኪዳን ይዘው በየሰፈሩ እየዞሩ አጥነዋል።
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
#መዝሙር – እያለፈ ነው ዘመኔ
በወንድማችን #ዳዊት_ክብሩ
#መሰንቆ #ሀብታሙ_ሽፈራው
#እያለፈ ነው ዘመኔ ትዕዛዙን ሳልፈጽም ወየው ለኔ(2)
በጠራኝ ጊዜ ምን እላለው ና ብሎ ወደኔ(2)
በወጣትነቴ ሳልሰራ እያየው አለፈ ብዙ አዝመራ(2)
ከእግዲህ በመስራት ጌታ ሆይ ልኑር ካንተ ጋራ(2)
የማስብበት በየዕለቱ ንጹህ ልብን ስጠኝ አቤቱ(2)
ከትዕዛዝህ ውጪ በመሆን እንዳልቀር በከንቱ(2)
እንደየሥራው ለመክፈል በግርማ መንግሥቱ ሲመጣ(2)
ማን ይሆን የሚቆም ከፊቱ ፈተናን የወጣ(2)
እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁ የተማራችሁ ከቃሉ(2)
ይመጣሉና በእርሱ ስም አምላክ ነን የሚሉ(2)
ትዕግስትን በመያዝ ሁላችሁ እስከ መጨረሻው ጠንክሩ(2)
ያንጊዜ ይሆናል በእርሱ ዘንድ የማዳን ተግባሩ(2)
👇👇👇👇👇👇
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👆👆👆👆👆🖕
በወንድማችን #ዳዊት_ክብሩ
#መሰንቆ #ሀብታሙ_ሽፈራው
#እያለፈ ነው ዘመኔ ትዕዛዙን ሳልፈጽም ወየው ለኔ(2)
በጠራኝ ጊዜ ምን እላለው ና ብሎ ወደኔ(2)
በወጣትነቴ ሳልሰራ እያየው አለፈ ብዙ አዝመራ(2)
ከእግዲህ በመስራት ጌታ ሆይ ልኑር ካንተ ጋራ(2)
የማስብበት በየዕለቱ ንጹህ ልብን ስጠኝ አቤቱ(2)
ከትዕዛዝህ ውጪ በመሆን እንዳልቀር በከንቱ(2)
እንደየሥራው ለመክፈል በግርማ መንግሥቱ ሲመጣ(2)
ማን ይሆን የሚቆም ከፊቱ ፈተናን የወጣ(2)
እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁ የተማራችሁ ከቃሉ(2)
ይመጣሉና በእርሱ ስም አምላክ ነን የሚሉ(2)
ትዕግስትን በመያዝ ሁላችሁ እስከ መጨረሻው ጠንክሩ(2)
ያንጊዜ ይሆናል በእርሱ ዘንድ የማዳን ተግባሩ(2)
👇👇👇👇👇👇
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👆👆👆👆👆🖕
Audio
መዝሙር #መክሊትህን
በዘማሪት #ዘነበች_ክፍሌ
መክሊትህን አድለን
ታማኝ ባርያ ሆነን አድነን
አምስትም ሁለትም የሰጠሃቸውን ጸጋ በረከትህን
እንደ ፈቃድህ ታማኝ ሎሌ ሆነን ስጠን የአቅማችንን
ዘርተን ምናጭደው በትነን ምንሰበስብ የምናተርፍበትን
ምንም አይሳንህ ደንዳናን ልብ ለውጠህ ትሑት አድርገን
መክሊትህን የት አኖርከው
አምላክ የሰጠህን የት ቀበርከው
መክሊትሽን የት አኖርሽው
አምላክ የሰጠሽን የት ቀበርሽው
የተለያየውን የጸጋ ስጦታህን ቀብረን በልባችን
እንደ እምነታችን ቃሉን ሳንፈጽመው እንደ መክሊታችን
በአገልግሎት ቢሆን ትጋቱ ጎድሎን ማስተማር መምከሩን
መመስከር አቅቶን አንዳችም ሳናተርፍ መክሊቱን ቀበርን
መክሊትህን የት አኖርከው
አምላክ የሰጠህን የት ቀበርከው
መክሊትሽን የት አኖርሽው
አምላክ የሰጠሽን የት ቀበርሽው
ጌታችን ስትመጣ ላለው ልትጨምርለት በጥቂት ለታመነው
በብዙ ልትሾመው ደስታህ ባለችበት ግባ ልጄ ስትለው
ለሃኬተኛ ባርያ መክሊቱን ለቀበረው ያለውም ተወስዶበት
ወደ ጨለማ አውጡት ልቅሶ ጥርስ ማፏጨት ብሎ ፈረደበት
መክሊታችን የት አኖርነው አምላክ የሰጠንን እንዳንቀብረው
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
በዘማሪት #ዘነበች_ክፍሌ
መክሊትህን አድለን
ታማኝ ባርያ ሆነን አድነን
አምስትም ሁለትም የሰጠሃቸውን ጸጋ በረከትህን
እንደ ፈቃድህ ታማኝ ሎሌ ሆነን ስጠን የአቅማችንን
ዘርተን ምናጭደው በትነን ምንሰበስብ የምናተርፍበትን
ምንም አይሳንህ ደንዳናን ልብ ለውጠህ ትሑት አድርገን
መክሊትህን የት አኖርከው
አምላክ የሰጠህን የት ቀበርከው
መክሊትሽን የት አኖርሽው
አምላክ የሰጠሽን የት ቀበርሽው
የተለያየውን የጸጋ ስጦታህን ቀብረን በልባችን
እንደ እምነታችን ቃሉን ሳንፈጽመው እንደ መክሊታችን
በአገልግሎት ቢሆን ትጋቱ ጎድሎን ማስተማር መምከሩን
መመስከር አቅቶን አንዳችም ሳናተርፍ መክሊቱን ቀበርን
መክሊትህን የት አኖርከው
አምላክ የሰጠህን የት ቀበርከው
መክሊትሽን የት አኖርሽው
አምላክ የሰጠሽን የት ቀበርሽው
ጌታችን ስትመጣ ላለው ልትጨምርለት በጥቂት ለታመነው
በብዙ ልትሾመው ደስታህ ባለችበት ግባ ልጄ ስትለው
ለሃኬተኛ ባርያ መክሊቱን ለቀበረው ያለውም ተወስዶበት
ወደ ጨለማ አውጡት ልቅሶ ጥርስ ማፏጨት ብሎ ፈረደበት
መክሊታችን የት አኖርነው አምላክ የሰጠንን እንዳንቀብረው
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#የዕጣኑ_ጢስ (Smoke of the Incense) ምንድነው ?
ቅዱሳት መጻሕፍትን ለማይቀበሉ ሰዎች ከእርሱ ጠቅሶ ለሚጠይቁት ጥያቄ መልስ መስጠትም ሆነ ማስተማር የማይታሰብ ነው ፡፡ በዚህ ዘመን ቤተክርስቲያንን በልዩ ልዩ መንገድ የሚዋጉና ለመጣልም የሚታገሉ ሰዎች ቤተክርስቲያን የምታደርጋቸውን ሃይማኖታዊ ድርጊቶችን በተመለከተ ጥያቄ ከመጠየቅ ይልቅ መተቸትና መሳደብ ብሎም ማንጉዋጠጥ ይቀናቸዋል ፡፡ መተቸታቸው ባይደንቅም ስድቡና ትችቱ ግን በአማንያን ላይ የሚጥለው ጥያቄ ይኖራል ፡፡ ወደ ርዕሳችን ስንመለስ ወደ ቤተክርስቲያን ለሥርዓተ አምልኮ (ለጸሎት ለቅዳሴ) የሚመጣ አንድ ምዕመን ከቅዳሴውና ከጸሎተ ሥርዓት ጋር ተያይዞ አንድ ነገር ይመለከታል ፡፡ ከካህናት አባቶች ማዕጠንት ውስጥ የሚግተለተል የዕጣን ጢስ ፡፡ እውነተኞች ካህናት ሕሙማንን ለመፈወስ ጸሎት በሚያደርሱባቸው የመጠመቂያ ስፍራዎችም ይህንኑ እናያለን ፡፡ ባላወቁት ነገር ገብቶ መተቸት ለራስም ሆነ ለሀገር በጎ ነገር አያመጣም ፡፡

ዕጣንና አዳም
አባታችን አዳም ከእግዚአብሔር ጋር ተጣልቶ ከገነት በተሰደደ ጊዜ የዕጣንን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርቧል ኩፋ ፭፥፩ ፡፡
ዕጣንና ሊቀ ነቢያት ሙሴ
እሥራኤል ዘሥጋ ከግብጽ ባርነት ነጻ ከወጡ በኋላ በሌዋውያን ካህናት ለእግዚአብሔር የዕጣን መሥዋዕትን እንዲያቀርቡ ታዘዋል ፡፡ በዚህም መሠረት ሥርዓተ ኦሪትን ሲፈጽሙ መሥዋዕተ ኦሪትን ሲያቀርቡ ዕጣንን ያጥኑ እንደነበር ተጽፏል ዘጸ ፳፭
ዕጣንና ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት
ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት ሀብታተ መንፈስ ቅዱስ የተሰጡት ታላቅ ነቢይ ነው ፡፡ ነቢዩ ፈጣሪው የሚያቀርበውን ልመና እንዲቀበልለት ሲማጸን ”ጸሎቴን በፊትህ እንደ ዕጣን ተቀበልልኝ” መዝ ፻፵፥፪ ብሏል ፡፡ የዕጣን ጢስ እግዚአብሔር የሚወደው መሥዋዕት መሆኑን ትመለከታላችሁን ?
++ ዕጣን በሐዲስ ኪዳን ++
ዕጣንና ቅዱሳን መላእክት
ቅዱሳን መላእክት በሰማይ በእግዚአብሔር ፊት ጸሎተ ዕጣን ያቀርባሉ ፡፡ ይህንም ነቢዩ ኢሳይያስ ሲገልጽ ”የመድረኩም መሠረት ከጭዋኺው ድምፅ የተነሣ ተናወጠ ቤቱንም ጢስ ሞላበት” ኢሳ ፮፥፬-፭ ብሏል ፡፡ ቅዱሳን መላእክት የቅዱሳንን ሰዎች ጸሎት እንኳን ወደ እግዚአብሔር የሚያሳርጉት በዕጣን ጢስ ነው ፡፡ ”ሌላም መልአክ መጣና የወርቅን ጥና ይዞ በመሠዊያው አጠገብ ቆመ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሠዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው ፣ የዕታኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ” ራእይ ፰፥፫-፬ እንደተባለ ፡፡
ዕጣንና ካህኑ ጻድቁ ዘካርያስ
የመጥምቁ ዮሐንስ አባት ካህኑ ዘካርያስም በቤተ መቅደስ ስብሐተ እግዚአብሔር እንዴት ያቀርብ እንደነበር ወንጌላዊው ሉቃስ ሲነግረን "እንደ ካህናት ሥርዓት ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለማጠን ዕጣ ደረሰበት።በዕጣንም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ በውጭ ቆመው ይጸልዩ ነበር። የጌታም መልአክ በዕጣኑ መሠዊያ ቀኝ ቆሞ ታየው " ይላል ሉቃ ፩÷፱ ::
ዕጣንና ልደተ ክርስቶስ
ሰብአ ሰገል ጌታችን በተወለደ ጊዜ ካቀረቡለት እጅ መንሻ አንዱ ዕጣን ነው ማቴ ፪÷፲፩ ፡፡
"የጌታ ነኝ" ያልክ ታዲያ ለምን ጌታ የተቀበለውን ትተቻለህ ?
* ምሳሌነቱ *
++ ዕጣን ምዑዝ (ጣፋጭ) ነው ++ ፡፡
ጌታችንም ምዑዘ ባሕርይ ነውና ሰብአሰገል የዕጣን መሥዋዕት አቀረቡለት ፡፡ በቤተክርስቲያን ዕጣን መቅረቡም ክርስቲያኖች እንደዕጣን ምዑዝ የሆነ ጠባይን ገንዘብ ማድረግ እንደሚገባቸው ያስተምራል
++ ዕጣን መሥዋዕት ነው ++
ጌታችንም ለዓለም መሥዋዕት ሊሆን እንደመጣ ለመናገር ሰብአሰገል ዕጣን አቀረቡለት ፡፡ ዕጣን የክርስትና ሕይወት የመሥዋዕትነት ሕይወት ሊሆን እንደሚገባው ያስተምራል
++ ዕጣን የተስፋ ምሳሌ ነው ++
ዕጣን ከሩቅ እንደሚሸት ተስፋም ያልያዙትን እንደያዙት ያላዩትን እንዳዩት ያደርጋልና
++ ዕጣን በተጋድሎ ያሉ ክርስቲያኖች ምሳሌ ነው ++
ዕጣን ከሩቅ እንደሚሸት ክርስቲያኖችም በተስፋ ይኖራሉና ::
++ መጻሕፍት እግዚአብሔር ለሚያምኑት የሕይወት እሳት እንደሆነ ይመሠክራሉ ዘዳ ፬፥፳፬ ፡፡ ቅዱሳን ደግሞ እንደ ዕጣን ናቸው ፡፡ ዕጣን በእሳት ነዶ ለሌላው መልካም መዐዛን እንደሚሰጥ ቅዱሳንም በእግዚአብሔር ፍቅር ነደው ለዓለም መዐዛ ሃይማኖት መዓዛ ምግባርን ይሰጣሉና ፪ቆሮ ፪፥፲፭ ዘፍ ፳፯፥፳፰፡፡ ++
በመምህር ቢትወደድ ወርቁ
መጋቢት ፳፩ ቀን ፳፲፪ ዓ ም.