ዐውደ ምሕረት
3.67K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
Audio
#መዝሙር #መቼ_ነው_ጌታ

#በዘማሪ #ሀብታሙ #ሽፈራው

መቼ ነው ጌታ አረ መቼ ነው 
መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ/2/ 

አልተማርኩም አልል አስተምረኸኛል/2/ 
ቃለህን እንደ ወተት አጠጥተኸኛል/2/ 

የታል አኗኗሬ አንተን የሚመስለው/2/ 
በልማድ ሕይወት ነው የምመላለሰው/2/ 

ይህ አንደበቴማ በቃልህ ሠልጥኗል/2/ 
ልቦናዬ ካንተ ከፊትህ ኮብልሏል/2/ 

አንተን እንደማውቅህ አብዝቼ ባወራ/2/ 
የተዘራው ሁሉ ፍሬ አላፈራ/2/ 

እዘንልኝና መንገዴን አቅናልኝ/2/ 
የአመጻ ሥራዬን በደሌን ተውልኝ/2/ 

ቃልህ እንዳይሰደብ በእኔ ድካም/2/
አርመው እርሻህን መድኃኔዓለም/2/

ከእስራቴ ፈተህ ነጻነት ስጠኝ
በቀኝህ አቁመህ አምላኬ ባርከኝ ጌታዬ ባርከኝ/2/

ኃጢአት ሞትን ወልዶ እንዳያጠፋኝ/2/
የብርሃን ፊትህ ይገለጥልኝ/2/

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit