ሰንበት እኛም የታመሙትን መጎብኘት እንዳለብን የምንማርበት ነው፡፡
ይህ ሳምንት “መጻጉዕ” ጌታችን ድውያንን ስለመፈወሱ የሚነገርበትና እኛም ባለን አቅም በነፍስ በሥጋ የተቸገሩትን ሁሉ መርዳትና ማገዝ እንዳለብን የምንማርበት ሳምንት ነው፡፡ ሕሙማንን መጠየቅ፣ የታሰሩትን መጎብኘትና ማስፈታት፣ የተራቡትን ማብላት፣ የተጠሙትን ማጠጣት፣ የታረዙትን ማልበስ ያዘኑትን ማረጋጋት ከጌታችን የተማርናቸው ክርስቲያናዊ ምግባራት ናቸው፡፡ ይህንን በማስተዋል የሚያስፈልገንን ሁሉ የሰጠንንና ከክፉ ነገር የጠበቀንን አምላክ ውለታውን እያሰብን ልናመሰግነው ይገባል፡፡ መጻጒዕ መጀመሪያ የነበረበት ደዌ ሥጋ ነበር፣ ይህንንም ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አራቀለት/አዳነው፡፡ ይሁንና በጌታችን ስቅለት ከአይሁድ ጋር በመተባበሩ፣ ያዳነውን ባለማመኑ ግን ደዌ ነፍስ አገኘው፡፡ እኛም እንደ መጻጒዕ ደዌ ነፍስ እንዳያገኘን ያዳነንን አምላካችንን ልናውቀው፣ ልናምነው፣ በህጉና በትዕዛዙም ልንሄድ ያስፈልጋል፡፡ ያን ጊዜ ከደዌ ነፍስ እንድናለን፡፡ ያንን ተስፋ ያልነበረውን በሽተኛ ከደዌ ሥጋው ፈውሶ ሕይወትን የሰጠው አምላክ፣ እኛንም በውስጥ በአፍአ ካለብን ደዌ ሥጋና ደዌ ነፍስ እንዲፈውሰን፤ ቁስለ ኃጢአታችንን እንዲያደርቅልን፣ በሕይወትና በጤና እንዲጠብቀን የእርሱ የጌታችን ቅዱስ ፈቃድ ይሁንል አሜን🙏
ምንጭ :-አስተምህሮ
#ለከበረው ሀሳብዎ
👉@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE
ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
#ዓውደ-ምህረት የእናንተ
🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤
📢 @AwediMeherit 📢