ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች።”
#ኤርምያስ 31፥15

ራሔል ወልዳ ስላልሳመቻቸው ፣ጡቶቿን ስላላጠባቻቸው ፣ በደርባዋ ስላላዘለቻቸው ፣ሌላው ቀርቶ ስም እንኳ ስላላወጣችላቸው ልጆቿ መጽናናትን ሳትወድ አምርራ ካለቀሰች።

በድንግልና ጸንሳ በድንግልና የወለደችው፣የድንግልና ጡቶቿን ያጠባችሁ፣ በእጆቿ የዳሰሰችሁ ፣በከንፈሮቿ የሳመችው፣ በጀርባዋ ያዘለችሁ፣ በጎኗ የታቀፈችሁ ፣ ከአንዱ ሀገር ወደ ሌላው ይዛው ስትሰደድ አንዴ #ኢየሱስ አንዴ #መድኃኔአለም አንዴ #አማኑኤል እያለች አፈራርቃ የሰየመችው 33 ዓመት አብራው የኖረች ምንትያ ቅጥያ ተቀዳዊ ተከታይ የሌለው አንድያ ልጆን ያጣች ራሔል እመቤታችን ሐዘኟ እንዴት የጠለቀ ይሆን ???🙏
#ድንግል_ሆይ ብሩቱሀን የሆኑ አምስቱ ሐዘኖችሽን አሳስቢ🙏 ለጻድቃንም አይደል ለኛ ለኃጥያን እንጂ!
በዚህ ዘመን ዶሮ መሆን በራሱ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ መታደል ነው።
#እንዴት?
በውድ ነዋ የምትሸጪው !
#በውድ ተሸጭክም ፤ በርካሽ ያው መታረድህ አይቀር
ቢሆንም በክብር ተሽጦ ክብርን በሚመጥን መንገድ መሞት ሰማዕትነት ነው ።
#በርኳሽ ስትሸጥ መቆየትህ ቁጭት አሳድሮብሃል ማለት ነው?
እንዴታ ለምን አያሳድርብኝም ? አታስታውሺም ፈንግል የተባለ በርድ ፍሎ የወፍ ጉንፋን በሽታ የመጣ ጊዜ ሁለት ዶሮ በ1ብር የተሸጠበትን የቅርብ ጊዜ ታሪክ? ይህው ዛሬ የሰው ጉንፋን covid 19 መጣና ሰው ረክሶ እኛ ተወደድን ለነገሩ የ ዛሬን አያድርገውና ከጅምሩ እኛኮ እኛ የነ አይደፈሩ የነ ዳይኖንሰር ዘር እኮነን ። ዶሮ የዳይነንሰር የመጨረሻ ዝርያው ነው ያሉትን የሳይንቲስቶች ምርምር አልሰማሽምን?
#ዶሮን ሲያታልሏት ዳይኖሰር ነሽ አሏት ኩኩኩኩኩኩኩ
ምን ያስካካሻል ውሸት ነው ልትይ ነው ዳይኖንሰርም ዶሮም ተመሳሳይ አቆም እንዳላቸው እራስሽ ማረጋገጥ ትቺያለሽ
#እንዴት አረጊ?
ላባው የተራገፈ አንድ ዶሮና አንድ ዳይኖንሰር በአምሮሽ ሳይ በሁለት እግራቸው የቆሙ
ሁለት እጃቸው አጠር ብሎ ወደ ደረታቸው የተጠጋ በመጠን ብቻ የሚለያዮ ተመሳሳይ ፍጥረት ይመጣልሻል።
#አስብኩት..... በእውነቱ እውነት ይመስላል ። ቆይ ግን አንተ መታረድህ ነው ወይስ የነ ዳይኖንሰር ዘር ሆኜ እንዴት በርኳሽ ተሽጬ እታረዳለሁ የሚለው ነው የሚያሳስብህ ?
ሁለቱም ያሳስቡኛል ክብሬም ሕይወቴም
#ወገኛ የቱ ክብርህ የክብር ባለቤት እንኳ በሰላሳ ዲናር ተሽጦ ያለ እርራዬ መታረዱን አትዘንጋ።
ዛሬ ጥሬ ስትለቅሚ የነበረው ከ ቤተ ክርስቲያኑ ደጅ ነበር እንዴ?
#እንዴ አዎ ለምን ጠየከኝ?
ሰባኪ መሰልሽኛ!
#እእእእ_በነገራችን ላይ ላስተዋለው ሁሉም ፍጥረት በራሱ ሰባኪ ነው “ሰማያት #የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ ” እንዳለ መጻሕፉ መዝ 19፥1

አሁን ከካህናቱ ጋር ሰንበቴ እንደምትቀመጪ ጭምር አረጋገጥኩ። ለነገሩ እታች ሰፈር ጥሬ ፍለጋ እያልሽ ገብስማው ዶሮጋ ከምትሄዲብኝ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ መሄድሽ ይሻለኛል።

" #የአውራ ዶሮ ወዳጅ መች ጠርቶ ሊጠራ
ሲወጡ ሲገቡ ሁል ጊዜ ጥርጠራ"

ምን አልሽ አንቺ ??

#አረ ጌታው ምንም አላልኩም ወዲ ነው
እኔ የምለው እስከ ዛሬ መታረዴ ሳይሆን በርኳሽ ስሸጥ መቆየቴ የግር እሳት ሆኖብኛል እያልክ ነው።
#አዎን
ለምን ይመስልሃል ግን ዋጋችን እንዲህ ውድ የሆነው?
#እኔ ምን አውቃለሁ አንቺን ልጠይቅሽ እንጂ ግን ፈጣሪ መናቃችንን አይቶ እየካሰን ይመስለኛል

አይደለም ባክህ ሰው ስለረከሰ ነው።
#አታመጪው ጉድ የለ !። ምን?
አዎ ወዳጄ ሰው ሲረክስ ለሰው የተዘጋጁት ነገረሮች ሁሉ ይወደዱበታል በስግብግብነት ሲረክስ በአቋራጭ ለመበልጸግ ሲረክስ ነገሮች ሁሉ ውድ ይሆኑበታል።

#ይልቁኑ በበዓላት ሁሉም ሲወደድ ካየህ የሰው ልጅ እረክሷል ማለት ነው

ስኳር ውስጥ ሩዝ ፣በርበሬ ውስጥ ሸክላ ፣ቅቤ ውስጥ ሙዝ ፣እንጀራ ወስጥ ጀሶ የሚጨምረው ቢረክስ አይደለምን??!
#ሊጡ ውስጥ እንኳ ጀሶ መኖሩ አሁን አሁን ሳስበው ጥሩ መሰለኝ
እንዴት?
#ያው ያ ሀገር አቆርቋዥ ጁንታ እንደልማዱ ሰርቆ ሲጠጣ አድርቆ ያስቀርልናል።

የሚገርመው እንደዚህ በዐድ ነገር ቀላቅሎ እንኳን የሚሸጭበት ዋጋ የትዬ ለሌ ነው። ይህ እጅግ በጣም መውረዱን ነው የሚያሳየው።
#የኔ_ውድ ምን አልባት እኛም የተወደድነው እንተ እንዳልከው የዳይኖሰር ዘሮች ስለሆንን ሳይሆን ከሆነ በዐድ ነገር ጋር ቀላቅለውን ሊሆን ይችላል ። በዘርህ ማሰብህ አቁም
ምን ? ከብዐድ ነገር ጋር ቀላቅለውን ይሆናል? ለዛነው ሣር ሳይ ጋጥ ጋጥ ፣ሜዳ ሳይ ደግሞ ተደባለል ተደባለል የሚለኝ ?
#አዎን የሐበሻውን ዶሮ ከፈረንጅ ዶሮ ጋር የፈረንጁን ዶሮ ከሰጎን እዋስ ጋር መቀላቀሉ ሳይንስ ዐዋቂነት ሆኟል።
ሰው ግን ለምን እንዲህ ከፋ ?
#ያወቀ እየመሰለው አንድም ጽድቅና ኩነኔን ቢረሳ ነዋ እኛኸ ታላቅ ሰው ያሉትን የሚያስተውል መቼ ይሆን ? "ጽድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም
ከክፉት ደግነት ሳይሻል አይቀርም"
አ.አ ኢትዮጵያ
ኃ/ማርያም ተርቢኖስ ሰብስቤ
ታኅሣሥ 28 ቀን 2014 ዓ.ም
Audio
ዐውደ ምሕረት
Audio
ርዕስ :- #ሚተራሊዮን
ደራሲ :- #ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ
ተራኪ :- #ተርቢኖስ ሰብስቤ
ምዕራፍ 4
ደቂቃ :- #1ዐ ደቂቃ 21 ሰከንድ
መጠን :- # 2.4 m.b ብቻ
Audio
ዐውደ ምሕረት
Audio
ርዕስ :- #ሚተራሊዮን ምዕራፍ 5
ደራሲ :- #ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ
ተራኪ :- #ተርቢኖስ ሰብስቤ
ደቂቃ :- 23 ደቂቃ ከ45 ሰከንድ
መጠን :- 5.6 mb ብቻ
" #ኢትዮጵያ እኮ ሠላም ብታገኝ ጠንካራ የምትሆን ሀገር ናት" ቤተ እስራላዊው #አባ ዮናታን /ሚተራሊዮን /
ዐውደ ምሕረት
Photo
"ኮትኩቼ ኮትኩቼ ያሳደኩት ቀጋ
አለ ጎንበስ ጎንበስ እራሴን ሊውጋ "

__ #ነባር_ኢትዮጵያውያን _
ዐውደ ምሕረት
Photo
“ከዚያም በኋላ ቶማስን፦ ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን አለው።”
#ዮሐንስ 20፥27
#አዲስ_መልአክ_ተክለ_ኤል
________
ተፈጥሮ ከመላእክት ወገን ያልሆነ ሰው ሆኖ ሳለ ነገር ግን በሃይማኖቱ ጽናት በምግባሩ ቅንሐት እና በተጋድሎዎ ብዛት ምድራዊ ሲሆን ሰማያዊ አዳማዊ ሲሆን መላእካዊ ለመሆን የበቃ ሐዲስ መላእክ ነው :: ተክለ ኤል

ቅዱሳን መላእክት በዘር የተገኙ አይደሉም ተክለ ኤል ( #ተክለ_ሃይማኖት ) ግን ከሕግ ዘር የተገኘ ሰው የሆነ አዲስ መላእክ ነው ::

#ተክል › ማለት ፍሬያማ ዕንጨት፣ ዛፍ፣ ቅመም፣ ቅጠላ ቅጠል፣፣ የሚሸተት፣ቢበሉት ጥጋብ ፣ቢያርፉበት ጥላ የሚሆን ገነታዊ ዕፅ፣ እንዲሁም ሕግ ሥርዓት ማለት ነው /ማቴ.፲፭፥፲፫/፡፡

" #ኤል " ማለት ደግሞ እግዚአብሔር ማለት ነው :: ስመ መላእክት ስመ እግዚአብሔርን ያዘለ በመሆኑ የሁሉም ቅዱሳን መላእክ ስም "ኤል" የሚል መቀጽል አለው #ለምሳሌ :-ሚካ-ኤል ፣ ገብር-ኤል ፣ ዑራ -ኤል፣ ወዘተ .... ስለዚህ ተክለ ኤል ስንልም #የእግዚአብሔር _ተክል ማለታችን ነው :: ታላቁ ሊቅ ቅዱስ #ባስልዮስ ዘ ቄሳሪያ እኔስ #እግዚአብሔር ባልኩ ጊዜ #አብ_ወልድ_መንፈስ_ቅዱስ ማለቴ ነው ብሎ እንደተናገረ እኛም እግዚአብሔር ስንል አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለታችንነውና #ተክለ_ኤል ስንለውም የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ተክል ማለታችን ጭምር ነው::

#ቦታው በሸዋ ክፍለ ሀገር ዛሬ ኢቲሳ በመባል በሚታወቀው ከከሰም ጅረት አካባቢ ባለ ቦታ በጥንቱ ፈጠጋር ቡልጋ በደብረ ጽላልሽ አውራጃ ዞረሬ በተባለው ሥፍራ ነው ። በዚሁ ሥፍራ (ዘርዐ ዮሐንስ) ፀጋ ዘአብ የሚባል የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህን የነበረ ጻድቅ ሰው ነበር "ጸጋ ዘአብ " ማለት የአብ ሥጦታ ማለት ነው ካህኑ ጸጋ ዘአብ በሃገሩ ደጋግ ከሆኑ ሰዎች ወገን ሣራ የምትባል ሴት አገባ ።

ሁለቱም ፈሪያ እግዚአብሔር ያደረባቸው በጎ ሥራን የሚሠሩ ሰዎች ነበሩ የፀጋ ዘአብ ሚስት ሣራ ሃይማኖት ከምግባር መልክና ደም ግባት ከሙያ ጋር አሟልቷ የሰጣት ሴት ነበረች ። አማቷ የፀጋ ዘአብ አባት " ወረደ ምሕረት " የሥራዋን ደግነት አይተው " እግዚኀረያ " ብለው ስም አወጡላት ጌታ የመረጣት ማለታቸው ነው።

#በሊቀ_መላእክት_በቅዱስ_ሚካኤል አብሳሪነት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኀረያ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ተወለዱ ወላጆቻቸውም ፍስሐ ፂዮን ።(የጽዮን ደስታዋ)ብለው ሰየሟቸው፡፡ ጻድቁ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው ‹‹ አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ›› ማለትም ‹‹አንዱ አብ ቅዱስ ነው አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው›› በማለት የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነዋል። ይህን ጊዜ እናታቸው እግዚ ኀረያም በመገረም ሆና " ይህ ሥራ የአባት ነው ላንተ የሚገባህ ጡት መጥባት ነው" ብላ ጡቷን አጎረሰችሁ ፡፡

#ቅዱሳን_መላእክት ቀን ከሌት #ቅዱስ_ቅዱስ_ቅዱስ እያሉ ያመሰግናሉ ኢሳ 6፥÷6 ይህም የህጻኑ ሁኔታ መላእካዊ ግብሩን ገና በህጻንነት የገለጠ ሁኔታ ነበር። ካህኑ ፀጋ ዘአብ የወቅቱን የቤተ ክርሰቲያን አገልግሎታቸውን ጨርሰው ወደ ቤታቸው ሲገቡ ሚስታቸው እግዚ ኀረያ በመገረም ሆና የሦስት ቀን ልጃቸው ፍስሐ ፂዮን እንዴት ባለ ምሥጋና ፈጣሪያቸውን እንዳመሰገነ ነገረቻቸው ጸጋ ዘአብም ህጻኑን ተቀብለው ታቅፈው እየሳሙ ልጄ ሺህ ዘመን ኑርልኝ እንዲ እያልክ በቤተ መቅደስ ስትቀድስ አይህ ዘንድ እመኛለው አሉ።
‹‹ #ተክለ_ሃይማኖት ›› ብሎ #የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ፍስሐ ፂዮን የሚለውን ስሙን በፈጣሪው ትዛዝ መሠረት ጠራቸው፡፡ በተወለዱ በ15 ዓመታቸው ዲቊናን፤ በ22 ዓመታቸው ደግሞ ቅስናን ከግብፃዊው ጳጳስ ከአባ ጌርሎስ ወይም (አባ ቄርሎስ) ዘንድ ተቀብለዋል፡፡

ሐዋርያዊ ተግባርንም በከተታ እና በፈጠጋር (በጽላልሽና በአካባቢዋ፣በዳሞት በምድረ ወላይታና አካባቢው ፣በአምሓራና በሸዋ በሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ፣ በኣድያማተ ትግራይ፣በገዳመ ዋሊ (ዋልድባ) ፣በገነተ ማርያም ላስታ በደብረ ዘመዶ ማርያም ገዳም በዚያው በላስታ፣ በኤርትራ ገዳማት ፣በደብረ ዳሞ አቡነ አረጋዊ ገዳም ወዘተ በአገሪቱ ወንጌል ባልተዳረሰበት ቦታ ሁሉ እየተዘዋወሩ ኢትዮጵያ አንዲት የሐዋርያት ወንጌል ሰፍተዋታል ።
#ጻድቁ_አባታችን ሕይወታቸዉን ሙሉ ለእግዚአብሔር በመስጠት፣ እንደ በሬ ተጠምደው፣ እንደ ገበሬ ታጥቀው፣ ይህንን ዓለም ንቀው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በብሕትውና በመኖራቸው፤ እርሳቸው በአሚነ ሥላሴ ጸንተው ሌሎችንም እንዲጸኑና እንዲያምኑ በማድረጋቸው፤ እንደዚሁም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ በመስበክ በጌታችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ድውያነ ሥጋን በተአምራት፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት የፈወሱ ሰባኬ ወንጌል በመኾናቸው ‹‹ #ተክለ_ሃይማኖት ›› ተብለው ይጠራሉ::

#በየ_ደረሱበትም ከሥራው ጽናት ከተአምራቱ ብዛት የተነሳ አንተ ሰውነህን ወይስ መላእክ ነህ ንገረን ይሉት ነበር በዚህም በደብረ ዳሞት አቡነ አረጋዊ ገዳም 10 ዓመት ከቆዮ በኃላ ተሰናብቷቸው ሊሄድ ተነሳ ሁሉም ከፍቅሩ ጽናት የተነሳ አለቀሱለት አበምኔቱም ይህን ሰው ኃጢያቴ አባሮታልና ወየውልኝ ብሎ መነኮሳቱን ሰብስቦ ሊሸኙት ተነሱ ከገዳሞም ያለ እረጅም ገመድ (ጠፈር) መውረድም ሆነ መውጣት አይቻልም ነበርና የመውረጃውን ገመድ (ጠፍር) ይዞ ይወርድ ዘንድ ጀመረ ጥንተ ጠላት ዲያቢሎስ ገመዱን ከካስማው ላይ ቆረጠው አባታችንም ይህን አስደንጋጭ ክስሀት ተከትሎ የተሰጣቸው የፀጋ ክንፍ በገዐድ ተገለጠ አበ ምኔቱና መነኮሳቱም ከገዳሙ አፈፍ ሆነው የሚሆነውን ያዮ ነበር ጻድቁም እንደ ሰማያዊ መላእክ በክንፉቸው በረው በደህና ከመሬት ደረሱ መነኮሳቱም መንክር እግዚአብሔር በላዕለ ቅዱሳኒሁ ብለው አደነቁ::
ከዚህም ባለፈ ህዳር 24ቀን መላእኩ ከምድራዊ ቦታቸው ነጥቆ ወስዶ ከሱራፌል ጋር ቀላቀላቸው በልጅነት አንደበታቸው አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ብለው ያመሠገኑት አግአስተ ዓለም ቅድስት ሥላሴን ዛሬ ደግሞ በዙፋኑ ላይ እናዳለ እያዮት በከንፈሮቻቸው ሰለሱት ቀደሱት በወርቅ ማዕጥንትም ዙፋኑን አጠኑ ።ወደ ቀደመም ኑሯቸው መላኩ መለሳቸውና ተጋድሏቸውን ቀጠሉ።

#በገዳመ አስቄጥስ ግብጽ እና ከኢየሩሳሌም።ጉብኝት በኃላ እየዞሩ ወንጌልን ለማስተማር ባይቻላቸው ስለዚህ በአንድ ቦታ መቆምን መረጡ ከፊት ከኃላ ከግራ ከቀኝ የሚያነቃ የሶር ሶማያ ስለው በመትከል በደብረ አስቦ በደብረ አስቦ ዋሻ ከዘረጉ ሳያጥፉ ከቆሙ ሳይቀመጡ ለ22 ዓመታት በጸሎት ጸኑ ጥር 4 ቀን 12 88ዓ.ም በ92 ዓመት ሲሆናቸው አንዲቱ የእግራቸው አገዳ ከመቆም ብዛት ተሰብራ ወደቀች ጸሎታቸውንም ሳያቆርጡ በአንድ እግራቸው 7 ዓመት አክለው በጸሎት ተጎ በድምሩም 29 ዓመት በጸሎት ተጋደሉ :: ከፈጣሪ ዘንድም ብዙ ጸጋና ቃል ኪዳን ከተቀበሉ በኃላ በ99ዓመት ከ10ወር ከ10ቀናቸው ነሐሴ 24 ቀን በክብር አርፈዋል:: እንደ ሰው በምድር ተወልደው እንደ መላክት የኖሩ አዲስ መላክ ያልናቸውም ለዚሁ ነው።

የጻድቁ አባት የአቡነ #ተክለ_ሃይማኖት እረድኤት በረከታቸው በአማላጅነታቸው የምትገኝ ጸጋ ለዘለዓለሙ ከእኛ ጋር ትኑር .....አሜን!
አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ጥቅምት 2013ዓ.ም