ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
ዐውደ ምሕረት
Photo
" #ደስታ_ተክለ_ሃይማኖት_ተወለደ"

#የሚገቡት
እንኳን ማርያም ማረችሽ ፣
አሜን!
እንኳን ማርያም ሁለት አረገችሽ
አሜን!
#የሚወጡት
ማርያም ጭንሽን ታሙቀው
አሜን!
ማርያም በሽልም ታውጣሽ.......ይሏታል
የእመጫቷ መልስ አሜን !አሜን! የሚል ብቻ ነው። ይህ የእግዚእኃረያ ቤት ነው። ባሏ ፀጋ ዘአብ ደስታውን መቋቋም አቅቶታል ቤቷ በወዳጆቻቸው እና በጠያቂዎቻቸው እንዲሁም ባለ መውለዳቸው እንደ ኃጢያተኛ ቆጥሮ ይጠቋቆሙባቸው በነበሩ ሰዎች ተጨናንቃለች መካን ሚስቱ ወንድ ልጅን ወልዳለችና ። ለሁሉም እንደ ማዕረጋቸው ምሳ አደረጉላቸው ማጋረጃ ገልጠው እናቲቱንና ልጇን ቅቤ እስኪቀቡ የቸኮሉ ሳይኖሩ አይቀሩም ሌላው ግን ስለ አወላለዷ ለመረዳት ሰሀናቸውን ይዘው የወላዲቱ አልጋ አጠገብ ጠጋ ብለው የተቀመጡም አልጠፋም ።

#እርሷም_የእግዚአብሔርን ቸርነት የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት እየመሰከረች ከሞተለሚ ምርኮ እንዴት ባለ ተአምር እደዳነች እያወራች ከባሏ ከፀጋ ዘአብም ጋርም ወንድ ልጅ ስለ መውለዷ አስቀድመው ዕራይን እንዳዮ እየነገረቻቸው ቀኑን በደስታ አሳለፈች ደስታ የሆነ ልጅ ወልዳለችና ።

*ስሙንስ ማን አላችሁት ?
ፍስሐ ጽዮን ( የጽዮን ደስታዋ) ብለነዋል ። ነገር ግን መላእኩ እንደነገረን ስሙ ሌላ ነው ከእናንተም የተሰወረ በልበ ሥላሴ የተጻፈ አዲስ ስም ይወጣለታል ብሎናል። "ተክለ ሃይማኖት"! ሕጻናት እንደሚያለቅሱም አያለቅስም ነበር "ቅኖች ሰዎች ሁል ጊዜ ደስ ይላቸዋል" እንደሚል

"ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን ለእራስህ አዘጋጀህ " አንደተባለም ሕጻኑ ፍስሐ ጽዮን በተወለደ ገና በሦስተኛው ቀን ከእናቱ እቅፍ ወርዶ "አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ" ብሎ ሥላሴን በአንድነት በሦስትነት አመስግነ:: መዝ 9÷2

#ልጆች_የእግዚአብሔር ስጦታዎች ናቸው የእግዚአብሔር ስጦታ ሁሉ ደግሞ ደስ ያሰኛል ። ይልቁኑ እግዚአብሔር በእነርሱ አድሮ ድንቅ ሥራውን ይሰራባቸው ዘንድ ያዘጋጃቸው የቅዱሳን ሰዎች ልደታቸው ብቻ ሳይሆን እነርሱ እራሳቸው ደስታ ናቸው :: " በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል ተድላና ደስታም ይሆንልሃል" ዮሐ1፥14 ተብሎ እንደተጻፈ እውነት ነው በመወለዱ ብዙዎች ደስ ብሎናል በሉቃስ ወንጌል ላይ መላእኩ ቅዱስ ገብርኤል በመጥምቀ መለኮት በቅዱስ ዮሐንስ መወለድ ብዙዎች ደስ እንደሚሰኙ አስረግጦ ነግሮናል።

እነሆ ዛሬ ደግሞ እንደ ዮሐንስ በድንግልና የኖረ እንደ መጥምቁ ካህን ያውም ሰማያዊ የሆነ እንደ አዋጅ ነጋሪው በምድረ ኢትየጵያን ሁሉ እየዞረ ወንጌልን የሰበከ ለእናትና ለአባቱ እንዲሁም ለብዝዎቻችን የደስታ ምንጭ የሆነ የጽዮን ደስታዋ የተባለ ፍስሐ ጽዮን ተወለደ እነሆ እኛም እንደ ተስፋው ቃል ዳግማዊው ዮሐንስ ተወልዶልናልና ደስ አለን::
#መፍቀሬ ጥበብ ቅዱስ ሰለሞን" ጻድቃን በበዙ ቁጥር ሕዝብ ደስ ይለዋል" እንዳለ አባታችን ተክለ ሃይማኖት በተወለዱ ሰዓት ክርስቲያኖች ደስ ብሏቸዋል ምክንያቱም ጻድቁ ሕሙማነ ነፍስን በትምህርታቸው ሕሙማነ ሥጋን በተአምራታቸው እያዳኑና እየፈወሱ ለሕዝብ ደስታ ምንጭ ሆነዋል ያን ጊዜ ብቻም ሳይሆን ዛሬም በአፀደ ነፍስ ሳሉ ለኛ ለክርስቲያኖች የደስታችን ምንጭ ናቸው " የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለችና " ስለኛ የጽድቅ ሕይወት የሰላም እጦት የሃይማኖት ጉለት የምግባር ዝቅጠት ዕለት ዕለት ወደ ፈጣሪ እየጸለዮ ያማልዱናልና ነው #ያዕቆ 5÷16

በጻድቃን መወለድ ሕዝብ ደስ የሚለው በተወለዱበት ዘመን እና ወር ብቻ አይደለም አንዴ ጻድቃን ከተወለዱ በኃላ ሕዝብ ለዘለአለሙ ደስ ይለዋል ጻድቃን በአፀደ ሥጋም በአፀደ ነፍስም በምልጃቸው ደስ ያሰኛሉና ..... .. ልክ እንደዛሬው......

" #እኔ ግን ለዘለዓለሙ ደስ ይለኛል
ለያዕቆብ( #ለተክለ_ሃይማኖት )
አምላክም ዝማሬን አቀርባለው" #መዝ76÷9
...........ይቆየን........

የጻድቁ አባታችን የተክለ ሃይማኖት እረድኤትና በረከት በሀገራችን ኢትዮጵያ እና በሕዝበ ክርስቲያኖች ላይ ሁሉ ለዘለዓለሙ ቀንቶ ይኑር ....!!!

ኃ/ማርያም አ.አ ኢትዮጵያ
ታህሳስ 22/2013ዓ/ም
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በዚህ ዘመን ዶሮ መሆን በራሱ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ መታደል ነው።
#እንዴት?
በውድ ነዋ የምትሸጪው !
#በውድ ተሸጭክም ፤ በርካሽ ያው መታረድህ አይቀር
ቢሆንም በክብር ተሽጦ ክብርን በሚመጥን መንገድ መሞት ሰማዕትነት ነው ።
#በርኳሽ ስትሸጥ መቆየትህ ቁጭት አሳድሮብሃል ማለት ነው?
እንዴታ ለምን አያሳድርብኝም የዛሬን አያድርገውና ኮ እኛ የነ አይደፈሩ የነ ዳይኖንሰር ዘር እኮነን። ዶሮ የዳይነንሰር የመጨረሻ ዝርያው ነው ያሉትን የሳይንቲስቶች ምርምር አልሰማሽምን?
#ዶሮን ሲያታልሏት ዳይኖሰር ነሽ አሏት ኩኩኩኩኩኩኩ
ምን ያስካካሻል ውሸት ነው ልትይ ነው ዳይኖንሰርም ዶሮም ተመሳሳይ አቆም እንዳላቸው እራስሽ ማረጋገጥ ትቺያለሽ
#እንዴት አረጊ?
ላባው የተራገፈ አንድ ዶሮና አንድ ዳይኖንሰር በአምሮሽ ሳይ በሁለት እግራቸው የቆሙ
ሁለት እጃቸው አጠር ብሎ ወደ ደረታቸው የተጠጋ በመጠን ብቻ የሚለያዮ ተመሳሳይ ፍጥረት ይመጣልሻል።
#አስብኩት..... በእውነቱ እውነት ይመስላል ። ቆይ ግን አንተ መታረድህ ነው ወይስ የነ ዳይኖንሰር ዘር ሆኜ እንዴት በርኳሽ ተሽጬ እታረዳለሁ የሚለው ነው የሚያሳስብህ ?
ሁለቱም ያሳስቡኛል ክብሬም ሕይወቴም
#ወገኛ የቱ ክብርህ የክብር ባለቤት እንኳ በሰላሳ ዲናር ተሽጦ ያለ እርራዬ መታረዱን አትዘንጋ።
ዛሬ ጥሬ ስትለቅሚ የነበረው ከ ቤተ ክርስቲያኑ ደጅ ነበር እንዴ?
#እንዴ አዎ ለምን ጠየከኝ?
ሰባኪ መሰልሽኛ!
#እእእእ_በነገራችን ላይ ላስተዋለው ሁሉም ፍጥረት በራሱ ሰባኪ ነው “ሰማያት #የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ ” እንዳለ መጻሕፉ መዝ 19፥1

አሁን ከካህናቱ ጋር ሰንበቴ እንደምትቀመጪ ጭምር አረጋገጥኩ። ለነገሩ እታች ሰፈር ጥሬ ፍለጋ እያልሽ ገብስማው ዶሮጋ ከምትሄዲብኝ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ መሄድሽ ይሻለኛል።

" #የአውራ ዶሮ ወዳጅ መች ጠርቶ ሊጠራ
ሲወጡ ሲገቡ ሁል ጊዜ ጥርጠራ"

ምን አልሽ አንቺ ??

#አረ ጌታው ምንም አላልኩም ወዲ ነው
እኔ የምለው እስከ ዛሬ መታረዴ ሳይሆን በርኳሽ ስሸጥ መቆየቴ የግር እሳት ሆኖብኛል እያልክ ነው።
#አዎን
ለምን ይመስልሃል ግን ዋጋችን እንዲህ ውድ የሆነው?
#እኔ ምን አውቃለሁ አንቺን ልጠይቅሽ እንጂ ግን ፈጣሪ መናቃችንን አይቶ እየካሰን ይመስለኛል

አይደለም ባክህ ሰው ስለረከሰ ነው።
#አታመጪው ጉድ የለ !። ምን?
አዎ ወዳጄ ሰው ሲረክስ ለሰው የተዘጋጁት ነገረሮች ሁሉ ይወደዱበታል በስግብግብነት ሲረክስ በአቋራጭ ለመበልጸግ ሲረክስ ነገሮች ሁሉ ውድ ይሆኑበታል።

#ይልቁኑ በበዓላት ሁሉም ሲወደድ ካየህ የሰው ልጅ እረክሷል ማለት ነው

ስኳር ውስጥ ሩዝ ፣በርበሬ ውስጥ ሸክላ ፣ቅቤ ውስጥ ሙዝ ፣እንጀራ ወስጥ ጀሶ የሚጨምረው ቢረክስ አይደለምን??!
#ሊጡ ውስጥ እንኳ ጀሶ መኖሩ አሁን አሁን ሳስበው ጥሩ መሰለኝ
እንዴት?
#ያው ያ ሀገር አቆርቋዥ ጁንታ እንደልማዱ ሰርቆ ሲጠጣ አድርቆ ያስቀርልናል።

የሚገርመው እንደዚህ በዐድ ነገር ቀላቅሎ እንኳን የሚሸጭበት ዋጋ የትዬ ለሌ ነው። ይህ እጅግ በጣም መውረዱን ነው የሚያሳየው።
#የኔ_ውድ ምን አልባት እኛም የተወደድነው እንተ እንዳልከው የዳይኖሰር ዘሮች ስለሆንን ሳይሆን ከሆነ በዐድ ነገር ጋር ቀላቅለውን ሊሆን ይችላል ። በዘርህ ማሰብህ አቁም
ምን ? ከብዐድ ነገር ጋር ቀላቅለውን ይሆናል? ለዛነው ሣር ሳይ ጋጥ ጋጥ ፣ሜዳ ሳይ ደግሞ ተደባለል ተደባለል የሚለኝ ?
#አዎን የሐበሻውን ዶሮ ከፈረንጅ ዶሮ ጋር የፈረንጁን ዶሮ ከሰጎን እዋስ ጋር መቀላቀሉ ሳይንስ ዐዋቂነት ሆኟል።
ሰው ግን ለምን እንዲህ ከፋ ?
#ያወቀ እየመሰለው አንድም ጽድቅና ኩነኔን ቢረሳ ነዋ እኛኸ ታላቅ ሰው ያሉትን የሚያስተውል መቼ ይሆን ? "ጽድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም
ከክፉት ደግነት ሳይሻል አይቀርም"
አ.አ ኢትዮጵያ
ኃ/ማርያም ተርቢኖስ ሰብስቤ
ታኅሣሥ 28 ቀን 2014 ዓ.ም
ዐውደ ምሕረት
Photo
" ምነው #በእንቁላሉ ጊዜ በቀጣሽኝ " ነው ወዳጄ!
ስለ #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ የሚባሉ ተአማኚነት ያላቸው ይትባህሎች

፩. #አስታራቂነት ፡-ነብርና አንበሳ አይስማሙም፤ በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሥዕል ሥር ግን ነብርና አንበሳ ተስማምተው ይታያሉ፡፡ በዚህ የተነሣ ለመታረቅ አስቸጋሪ የሆኑ ሰዎችን ለማስታረቅ የሚሄዱ ሽማግሌዎች ‹አቦን ሆነን መጥተናል› ይላሉ፡፡

፪. #የአቦ_ጠበል ፡- አንድ ሰው እየተመገበ ቢያንቀው ‹የአቦ ጠበል› እያልክ ውኃን ሦስት ጊዜ ጠጣው ይባላል፡፡
፫. #የአቦ_ብቅል ፡- አንድ ሰው ከማያውቀው ቦታ ስሙ ቢጠራና በአካባቢው የሚያውቀውን ሰው ቢያጣ የጠራው ሰይጣን ሊሆን ስለሚችል ‹‹የአቦን ብቅል እፈጫለሁ› በል ይባላል፡፡

፬. #የአቦ_መገበሪያ ፡- አንድ ሰው አንድን ነገር አጥፍቶ ተሠውሮ እንደማይቀመጥ ለመግለጥ ‹‹የአቦን መገበሪያ የበላ ሲለፈልፍ ይውላል›› ይባላል፡፡

፭. #አቦ_ሰጥ ፡- አንድ ሰው የማያውቀውን ነገር በግምት ሲናገር ‹አቦ ሰጥ› ይባላል፡፡

፮. # በአቦ_ይዤሃለሁ ፡- አራዊት የቤት እንስሳትን እንዳይበሉባቸው ገበሬዎች ‹በአቦ ይዤሃለሁ› ብለው ይገዝቷቸዋል፡፡

፯. #የአቦ_መንገድ ፡- በሰሜን ሸዋ መራኛ አካባቢ ባሉ ሕዝቦች ዘንድ ‹የአቦ መንገድ› የሚባል ብሂል አለ፡፡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሚዳ ከሚገኘው የአቡነ መልከ ጼዴቅ ገዳም ጥቂት ጊዜ ቆይተዋል ይባላል፡፡ በኋላ ከዚያ ገዳም ሲወጡ አቡነ መልከ ጼዴቅ ‹‹የት ሊሄዱ ነው›› ብለው ቢጠይቋቸው ‹እርሱ ወደ መራኝ›› ብለው መለሱላቸው፡፡
ከተማው ‹‹መራኛ›. የተባለው በዚህ ምክንያት ነው ይባላል፡፡ ታድያ በዚህ ምክንያት አንድ ሰው መድረሻውን በውል ሳያውቀው መንገድ ሲጀምር መንገዱ ‹የአቦ መንገድ› ይባላል፡፡

፰. #የአቦ_ቁራ ፡- ሰይጣን በቁራ ተመስሎ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ዓይናቸውን ሊያወጣ ስለመጣ በጎ ነገር የያዘ መስሎ የሚመጣ ክፉ ሰው ‹የአቦ ቁራ› ይባላል፡፡

፱. #በአቦ_በሥላሴ ፡- በሕዝቡ ብሂል ውስጥ ከሥላሴ ጋር ተያይዘው ብዙ ጊዜ የሚጠሩት ገብረ መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ ‹በአቦ በሥላሴ› ሲባል አጥብቆ መለመን ነው፡፡ በሕዝባዊ መዝሙሮችም ውስጥ ‹በአምስት አቦ ናቸው በሰባት ሥላሴ› የሚል ሐረግ በተደጋጋሚ ይሰማል፡፡
ስለ አቡዬ  ሌሎች የሚያውቋቸው ይት ባህሎች ካሉ ይጨምሩበት!

#የጻድቁ እረድኤት አይለየን...አሜን!

#ምንጭ :- ከሙሃዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ጽሁፍ የተቀነጨበ
የብዙ ቅዱሳን ማረፊያና መፍለቂያ #የቅዱሳን_ወደብ_ሀገረ_እግዚአብሔር_ኢትዮጵያ

#ልዮ ልዮ ወደቦቻችንን አተናል የቅዱሳን ማደሪያ ወደብ መሆናችንን ካጣን ግን ከቀድሞ ይልቅ አሁን ይብስብናል።

#ኢትዮጵያ_የብዙ_ቅዱሳን_ወደብና_የክርስቲያኖች_ደሴት_ናት !
ከተራ #ዘኢትዮጵያ
_______
#ሳቢ ያልቅ ይ እንጂ ሐሳብ አያልቅም! ስለዚህ ሀሳብ ቦይ እስካገኘ ድረስ ፈሶ
የማያልቅ ወንዝ ነው ። ይልቁኑ መነሻቸው በምድር የማይታወቁ ገነታዊ የሆኑ ወንዞች ለዚህ
ጥሩ ማሳያዎች ናቸው።
ሀገራችን ሁል ጊዜ የጥምቀት በዓልን ምክንያት አድርጋ ዋዜማውን ማለትም ጥር 10 ቀንን
" ከተራ " ብላ ታቦት ከመንበሩ አንስታ ድንኳን ወደ ተተከለበት የታቆረ ፣የተከተረ፣የተገደበ
ውኃ ወዳለበት ሥፍራ ይዛ በመሄድ በልልታና በግርግርታ በድምቀት ከምዕመኞቿ ጋር
ታከብረዋለች ። ኢያሱ 3÷3
#ይህንንም ማድረጓ አምላካችን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እራሱ መጥቶ
ያጥምቀኝ ሳይል ወደ ባሪያው ወደ ዮሐንስ በትሕትና ሄዶ መጠመቁን ለማሰብ ነው።
የትሕትና አባት ! ይህን በማድረግ ባያስተምረን ኖሮ ዛሬ ካህናቱ ቤታችን መጥተው
ያጥምቁን ባልን ነበር። ከተራ የቃሉ ትርጉም መገደብ ፣ በአንድ ቦታ መርጋት (ለፈሳሽ
ነገር)፣ መታቆር ፣መቆም ወይም ማቆም የሚል ነው።
ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ " እነሆ ውኃ ፤ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምንድነው? " ብላ
ከተጠመቀችበት ጊዜ አንስቶ ይህው ዛሬ ድረስ ምሥጢረ ጥምቀትን በሚገባ ለልጆቿ
ስታስተምርና ሥርዓቱንም ስትፈጽም ኖራለች ። ወደ ፊትም ትኖራለች። # ሐዋ 8÷36
#ኢትዮጵያ እንደ ሀገር የጥምቀትን በዓል ማክበር የጀመረችሁ በኩረ ጳጳሳት ዘኢትዮጲያ
የሚባሉት " ፍሬ ምናጦስ" ወይም ሕዝቡ ከፍቅሩ ጽናት የተነሳ ፊደል ቀርጾ ንባብ አደላድሎ
የድንቁርናን ጽልመት ገፏልናልና ብለው " አቡነ ሠላማ ከሳቴ ብርሃን " /የሠላም አባት
ብርሃንን የሚገልጥ / እያሉ ይጠሯቸው በነበሩት በመጀመሪያው ታላቅ ጳጳሳችን ትዕዛዝና
መመሪያ ነበር።
ከዛ በመቀጠል እነ አፄ ገብረ መስቀል፣ እነ አፄ ናዖድ እና አፄ ዘርዓ ያዕቆብ የመሳሰሉት
ቅዱሳን ነገሥታት ይህ ደገኛ የጥምቀት በዓል በአደባባይ እንዲከበር አድርገውታል።
ዛሬ ዛሬ እነዚህን የመሰሉ ቅድስናን ከንግሥና አስተባብረው የያዙ መሪዎችን በማጣቷ
ባህሏን ፣ወጓን፣ ሃይማኖቷን ፣ትውፊቷ ፣ሥርዓቷን በአደባባይ ወጥታ እንዳታከብር ጫና
እያሳደሩባት ትገኛለች።
#እርሷ ግን ተስፋዋ እግዚአብሔር ነውና ዛሬም ወደ ዮርዳኖስን መውረዷን አላቆመችም ።
አንድነት ይዛለች ፣ ፍቅር ከትራለች ፣ ሠላም ጸንሳለች መለያት እንዳያጨነግፋት፣ አጥንት
ቆጣሪነት እንዳይበትናት እንጠንቀቅላት።
ይህ ሀገራዊ ከተራ ከመንፈሳዊ ክትረት ምሳሌነት አልፎ በየ ቤታችን መብራትና እራት ሆኖ
የሚመጣ የብልጥግናችን ቀንዲል ነው። ከተራውን ከተራ ነገሮች ሁሉ ወጥተን በአንድነት
የምንረጨው ጥሩ ውኃ ያድርግልን። # ሕዝ 36÷25
"ሃይማኖት፣ ብሔር፣ዘር የማይለኝ ሰናይ ከተራ... #ዓባይ !"
ኃ/ማርያም
አ.አ ኢትዮጵያ
10/2013ዓ.ም