#ሱባዔ
ሱባዔ በሰዋሰው ትርጉሙ ቆየ ሰነበተ ዘገየ ሰባት ማለት ሲሆን ምሥጢራዊ ትርጓሜውም ደግሞ አንድ ሰው ከዚህ ቀን እከዚህ ቀን ድረስ ፈጣሪዬን በጸሎት እገናኛለሁብሎ የሚያቅደው ዕቅድ ነው። ሰባት ቁጥር በእስራኤላዊያን ዘንድ በሥራም በቃልም የሚገለጥ ፍጹም ቁጥር ነው ፈጣሪ ዓለማት እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ሥነ ፍጥረትን ከመፍጠር አረፈ እንዲል በጸሎት የሚተጉ ምዕመናንም በቀን ሰባት ጊዜ ማመስገናቸው የሰባት ቁጥርን ፍጹምነት ያመለክታል ። ሱባዔ የተጀመረው ከመጀመሪያው ሰው አዳም ውድቀት በኋላ ነው ቅዱሳን መላእክት አዳምን ጸሎት እንዴት እንደሚጸለይ እንዳስተማሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ይናገራሉ። ለአዳምም የጸሎት ጊዜያትን አስተምረውት አስተምረውት ነበርና ጥፈቱን አምኖ ሱባዔ በመግባቱና በመጸለዩ እግዚአብሔርም በማይታበል ቃሉ ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጁ ተወልዶ እንደሚያድነው ቃል ኪዳን ገባለት ።
ሱባዔ ለምንምክንያት እንገባልን ቢሉ የመጀመሪያው የሚሆነው የሰው ልጅ በባህሪው ኃጢአት የሚስማማው ነው በሥጋ ሰውነቱ ፈጣሪን ይበድላል በፈጸመው በደል / ኃጢአት/ ሕሊናው ይወቅሰዋል በዚህም ያዝናል ይጸጸታል በሰራው ኃጢአትም ልቡ ይደነግጣል በዚህ ጊዜ የፈጣሪን ይቅርታ ለማግኘት ሲል ሲል ሱባዔ ይገባል ።እግዚአብሔርን ለመማፀን የሚገባ ሱባዔ አለ ። ማንኛውም ሰው ሱባዔ በገባ ቁጥር ወደ ፈጣሪው የሚያቀርበው ተማጽኖ ሊኖረው ይገባል ምንም የምንለምነውና የምንጠይቀው ነገር ሳይኖር ሰባዔውን ብንገባ የምናገኘው ምንም አይነት መልስ አይኖርም
ስለዚህ ተማፅኖ ሊኖረን ይገባል ። ያለ ምንም ቅድመ ሆኔታና ዝግጅት ሱባዔ የሚገቡ ሰዎች ከሱባዔው በኋላ ምን እንደተመለሰላቸው የሚያውቁት ነገር ስለማይኖራቸው ሱባዔ በመግባታቸው የሚገኙት ነገር አይኖርም ይህን ተገንዝበው ከመግባታቸው በፊት የሚገቡበትን ምክንያት ራሳቸውን መጠየቅ አለባቸው ። ቅዱሳን አባቶችና ቅዱሳት እናቶቻችን ደማቸውን ካፈሰሱበት አጥንታቸውን ከከሰከሱበት ድንቅ ድንቅ ገቢረ ተአምራት የሰሩበት ቦታ ገዳማቸውና አድባራት ላይ የሚገባ ሱባዔ ከቅዱሳኑ ረድኤት ተካፋይ ይደርጋል ። ሱባዔ የተደበቀን ምሥጢር የሚገለጥበት ቁልፍ የቤተክርስቲያን ሥርዓት ነው ቅዱሳን አባቶቻችን ያዩት እራይ ምሥጢሩና ትርጉሙ አልገለጥ ሲላቸው ሱባዔ ይገቡ ነበር እግዚአብሔርም በንጽሕና ሆነ ነው የገቡትን ሱባዔ ተመልክቶ ምሥጢሩንና ትርጉሙን ይገልጥላቸዋል ። ነቢዬ ዕዝራ የመጽሐፍታት ምሥጢር እንዲገልጥለት ሱባዔ ገባ እግዚአብሔር አምላክም ሁሉን ገለጸለት የጠፉትን የብሉይ ኪዳን መጽሐፍታት ደግሞ ለመጻፍ ችሏል ይህ ምሥጢር የተገለጠለት በሱባዔ ነው ።
ከብሉይ ጀምሮ ያሉ የሱባዔ አባቶቻችን የገቡት ሱባዔ ሱባዔ አዳም ፣ ሱባዔ ሔኖክ ሱባዔ ነብያት
፣ሱባዔ ዳንኤል ሱባዔ ዳዊት በተጨማሪም የግል ሱባዔ የማኀበር ሱባዔ የአዋጅ ሱባዔ በመባል ይታወቃሉ በሐዲስ ኪዳን ከአራት ቀን በኋላ የምገባ ሐዋርያት የገቡት ሱባዔ ነው የፍልሰታ ሱባዔ በዚህ ሱባዔ ተሰውሮ የነበረውን የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ሥጋ የተገኘበት ትንሣኤዋ እንዲገለጥላቸው የተገባ ሱባዔ ነው ። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን 14 ቀን ያክል በጻም በጸሎት ተማጽነው ትንሣኤዋን ገለጠችላቸው ። እንግዲህ ሱባዔ ከብዙ በጥቂቱ ይህንን ይመስላል ወቅቱ የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የፍልሰታ ስባዔ እንደ መሆኑ መጠን እኛም የሐዋርያቱን ፈለግ በመከተል በንጹሕ ልቦና በትሁት መንፈስ ሆነን የእናታችን ትንሣኤ ይገለጥልን ዘንድ በሱባዔው እንትጋ ። ለሐዋርያቱ በሙሉ የልባቸውን መሻት የፈጸመች የጌታችን እናት ድንግል ማርያም የእኛንም የልባችንን ትፈጽምልናለች። ወቅቱን የጾም፣የጸሎት፣የስግደት፣ የምጽዋት፣ ስለ ሀገራችን ኢትዮጲያ የምናለቅስበት ነው ። ስለዚህ ሁላችን በሱባዔው እንበርታ
“በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቍረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር።”
— ሐዋርያት 2፥42
#ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
.....ይቆየን.......
ምንጭ :-እናት ማህበሬ ምክሐ ደናግል ሰሌዴ መጽሔት ሐምሌ ና ነሀሴ2010ዓ.ም የተለጠፈ

#ሱባዔ ነቢያት
እግዚአብሔር ለአዳም የገባውን ቃል ኪዳን መሠረት በማድረግ ቀደምት ነቢያት በተነሡበት ዘመን ቅደም ተከተል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆንና ዳግም መምጣት ትንቢት ተናግረዋል፡፡ ሱባዔም ቆጥረዋል፡፡ ኢሳ.7.14፡፡ መዝ.49.3፡፡ ዘካ.13.6፤ ዘካ.14.1፡፡ የአንዱ ነቢይ ትንቢታዊ ንግግርና ሱባኤ በአነጋገርና በአቆጣጠር ከሌላኛው ነቢይ ጋር ይለያያል፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ትንቢቱን ሲያናግር ምሳሌውን ሲያስመስል ጐዳናው ለየቅል በመሆኑ ነው፡፡ «ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጐዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናገረ፡፡» እንዲል፡፡ ዕብ.1.1፡፡ የአቆጣጠር ስልታ ቸውና የሱባዔ መንገዳቸው ቢለያይም ዓላማና ግባቸው ግን አንድ ነው፡፡
#ሱባዔ አዳም
አዳም ትንቢት በመናገርና ሱባዔ በመቁጠር የመጀመሪያውን ሥፍራ ይይዛል፡፡ ምክንያቱም በገነት ሰባት ዓመት ከአንድ ወር ከዐሥራ ሰባት ቀን በተድላና በደስታ ከኖረ በኋላ ሕግ በማፍረሱና የፈጣሪውን ቃል በመጣሱ ያለምንም ትካዜና ጉስቁልና ከሚኖርበት ዔደን ገነት ተባርሯል፡፡ ዘፍ.3.24፡፡ እርሱም ፈጣሪው እንዲታረቀው፣ በዐይነ ምሕረት እንዲጐበኘው፣ ቅዝቃዜው ሰውነት ከሚቆራርጥ ባሕር ውስጥ በመቆም ለሠላሳ አምስት ቀን /አምስት ሱባዔ/ ሱባዔ ገብቷል፡፡ በባሕርዩ የሰውን ልጅ እንግልት የማይወድ ቸሩ ፈጣሪ የአዳምን ፈጽሞ መጸጸት ተመልክቶ «በኀሙስ ዕለት ወበመንፈቃ ለዕለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ ወእድኅክ ውስተ መርህብከ ወእቤዝወከ በመስቀልየ ወበሞትየኸ በአምስት ቀን ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ» ብሎ ተስፋውን ሰጠው፡፡ አዳም የተሰጠውን ተስፋ ይዞ በዓለመ ሥጋ ለዘጠኝ መቶ ሠላሳ አመት ከኖረ በኋላ መከራና ችግር ከበዛበት ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡
በወንጀል ተከሶ በወኅኒ የተፈረደበት ሰው ከእስር የሚፈታበትን ዕለት በማውጣት በማውረድ ወራቱንና ዓመታቱን እንደሚቆጥር፣ አዳምም በሞት ቢለይም በሲኦል የነፍስ ቅጣት ካለበት ሥፍራ ይኖር ስለነበር የተሰጠውን ተስፋ በማሰብ ሱባዔውን እየቆጠረ የተናገረውን የማያስቀር የማያደርገውን የማይናገር ጌታየ «እነሆ አድንኀለሁ» ብሎ የገባልኝ ዘመን ተፈጸመ፤ ሰዓቱ አሁን ነው፤ እያለ ሲያወጣ ሲያወርድ ቸር አምላክ ሰው ኾኖ ሥጋ ለብሶ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ፡- «ተንሥኡ ለጸሎት ለጸሎት ተነሡ፤ ሰላም ለኩልክሙ፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን» በማለት አዳምን ከነልጅ ልጆቹ ነጻ አውጥቶታል፡፡ አዳምን በመከተል ልጆቹም አበው ቅዱሳን ነቢያት ሱባዔ በመግባት የተስፋን ዘመን በመቁጠር በመልካም ግብር ተከትለውታል፡፡ በዚህም መሠረት በርካታ ነቢያት በተለያየ ስልት ሱባዔ ቆጥረዋል፤ እኛም ሱባዔ ከቆጠሩ ነቢያት የተወሰኑትን በዚህ ጽሑፍ እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡
#ሱባዔ ሔኖክ
ጻድቁ ሔኖክ፣ የያሬድ ልጅ ሲሆን፣ በትውልድ ከአዳም ሰባተኛ ነው፡፡ እርሱም በሕይወቱ እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ቤት ንብረቱን በመተው በሱባዔና በትሕርምት እግዚአብሔርን አገልግሏል፡፡ ፍጹም አካሔዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገ ሰው በመሆኑ በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን መልካም ግብር ተመስክ ሮለታል፡፡ «ሔኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ፡፡» ዘፍ.5.22፡፡ ይህም በመሆኑ እግዚአብሔር የሱባዔውን ዋጋ ቅዱስ መንፈሱን በረድኤት ስለ አሳደረበት ትንቢት ተናግሯል፤ ሱባዔ ቆጥሯል፡፡ በሰማይ ተሰውሮ ሳለ ስለ ቅዱሳን መላእክት፣ ስለ መሲሕ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ስለ ፀሐይና ጨረቃ አመላለስ /ዑደት/ የሚተርክ በስሙ የተሰየመውን መጽሐፍ ጽፏል፡፡ ዘፍ.5 21-24፡፡ ይሁዳ ቁ.14፡፡ ሔኖክ 1.9፡፡
ሱባዔ ሔኖክ የሚባለው ነቢዩ ሔኖክ በመስፈርት የቆጠረው ሱባዔ ነው፡፡ መስፈርቱ /ማባዣ ቁጥር/ 35 ሲሆን 35'19 ሲበዛ በውጤቱ 685 ዓመት ይሆናል፡፡ 685'12 ስናባዛው 7980 ይሆናል፡፡ ይኸውም ሐሳብ የሚያስረዳው ስለክርስቶስ ምጽአት ነው፡፡
ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ አሁን የደረስንበት ዘመን 7497 ይሆናል፡፡ ይህን ለማረጋገጥ በ5500 ዓመት ላይ 1997 ዓመትን መደመር ነው፡፡ በዚህን ጊዜ ከላይ ያስቀመጥነውን 7497 ዓመት ይሰጠናል፡፡ በነቢዩ ሔኖክ አቆጣጠር መሠረት ምጽአተ ክርስቶስ በ7980 ይሆናል፡፡ ከላይ ሔኖክ የቀመረውን ቁጥር ይዘን ከ7980 ዓመት ላይ አሁን ያለንበትን ዘመን /1997/ ስንቀንስ 483 ዓመት እናገኛለን፡፡ ስለዚህ በሔኖክ ሱባዔ መሠረት ምጽአተ ክርስቶስ ሊሆን 483 ዓመት ይቀራል፡፡
#ሱባዔ ዳዊት
ነቢዩ ዳዊት ከእስራኤል ነገሥታት ሁሉ ታላቅና ተወዳጅ ንጉሥ ነበር፡፡ ዘመነ መንግሥቱ 1011-971 ከክርስቶስ ልደት በፊት እንደ ነበር ይታመናል፡፡ ነቢዩ ዳዊት ልበ አምላክ እንደ መሆኑ ትንቢት ተናግሯል፡፡ ሱባዔ ቆጥሯል፡፡ ይኽውም ቀመረ ዳዊት በመባል ይታወቃል፡፡ «እስመ ዐሠርቱ ምእት ዓመት በቅድሜከ፤ ከመ ዕለት እንተ ትማልም ኃለፈት፤ ሺ ዓመት በፊትህ እንዳለፈች እንደ ትላንት ቀን»፡፡ /መዝ.89.4/ የሚለውን መምህራን ሲቆጥሩት 1140 ዓመት ይሆናል፡፡ ይኸውም በጌታ ዘንድ 1140 ዓመት እንደ አንድ ቀን እንደሆነ ነቢዩ ዳዊት ተናግሯል፡፡ ይህም ለዳዊት ሱባዔ መቁጠሪያ /መሥፈሪያ/ ሆኖ አገልግሏል፤ 1140’7= 7980 ዓመት ይሆናል፡፡ ይህም ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ በ7980 ዓመት ክርስቶስ ዳግም እንደ ሚመጣ የሚያመለክት ነው፡፡
#ሱባዔ ዳንኤል
ነቢዩ ዳንኤል ምድቡ ከዐበይት ነቢያት ነው፡፡ እስራኤል ወደ ባቢሎን ሲማረኩ ተማርኮ ወደ ባቢሎን ወርዷል፡፡ እርሱም ስለ ክርስቶስ መምጣት ትንቢት ተናግሯል፤ ሱባዔም ቆጥሯል፡፡ «ሰብአ ሰንበታተ አድሞሙ ለሕዝብከ፤ ሰባ ሰንበት ወገኖችህን ቅጠራቸው፡፡» ይኸውም ክርስቶስ ከ490 ዓመት በኋላ ሰው መሆኑን የሚያመለክት ትንቢት ነው፡፡ እንዲሁም «እስከ ክርስቶስ ንጉሥ ትትሐነፅ መቅደስ ወእምዝ ትትመዘበር፤ እስከ ንጉሥ ክርስቶስ ድረስ መቅደስ ትታነፃለች በኋላም ትፈርሳለች» ሲል ተናግሯል፡፡
የአቆጣጠር ስልቱም በዓመት ሲሆን ይኸውም ሰባቱን ዓመት አንድ እያሉ መቁጠር ነው፡፡ ይኽውም ሱባዔ ሰንበት ይባላል፡፡ ዳንኤል ሱባዔ ከቆጠረበትና ትንቢት ከተናገረበት ጀምሮ ክርስቶስ እስከ ሚወለድ 490 ይሆናል፡፡ መስፈርቱ /ማባዣው/ ሰባት ስለሆነ 7’70 ስናባዛው 490 እናገኛለን፡፡ ይኸውም ነቢዩ ሱባዔ ከቆጠረና ትንቢት ከተናገረ ከ490 ዓመት በኋላ የክርስቶስን መወለድ ያመለክታል፡፡
በአጠቃላይ ከላይ የተመለከትናቸው ቅዱሳን ነቢያት አካሄዳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር በማድረግ ሱባዔ ገብተው በትሕርምት በመኖራቸው ድንቅ የሆነውን የክርስቶስን ልደትና ዳግም ምጽአት ለመተንበይ ችለዋል፡፡ ሱባዔ መግባት የራቀን ለማቅረብ የረቀቀን ለማጉላት ብቃትን ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚያስገኝ መንፈሳዊ ጥበብ መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡
**** ይቀጥላል*****

#የሱባዔ ዓይነቶች
#የግል ሱባዔ/ዝግ ሱባዔ/
የግል ሱባዔ አንድ ሰው ብቻውን ሆኖ በቤትና በአመቺ ቦታ የሚይዘው ማንም ሰው ሳያየው በግሉ የጸሎት በኣቱን ዘግቶ በሰቂለ ኅሊና ሆኖ ፈጣሪው ብቻ እንዲያየው እንዲሰማው በኅቡዕ የሚፈጽመው ሱባዔ ነው፡፡ ማቴ.6፡5-13፡፡ በዚህ ዓይነት መልክ አንድ ሰው ሱባዔ ሲገባ ዘጋ ይባላል፡፡ ዝግ ሱባዔ የያዘ ሰው የሚያስፈልገውን ነገር ይዞ ወደ በኣቱ ከተከተተ በኋላ ሱባዔው እስኪፈጸም ድረስ ከሰው አይገናኝም፡፡ መዝ. 101-6-7፡፡
#የማኅበር ሱባዔ
የማኅበር ሱባዔ የሚባለው ካህናት፣ ምእመናን ወንዶችና ሴቶች፣ ሽማግሌዎችና ወጣቶች በአንድ ሆነው በቤተ ክርስቲያንና አመቺ በሆኑ ቦታዎች ሁሉ ተሰብስበው የሚገቡት ሱባዔ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን የነበሩ ምእመናን ወደ እግዚአብሔር በመሄድ ይጸልዩ ነበር፡፡ 1ኛ ሳሙ.1፡9፤ መዝ.121፡1፤ ሉቃ.18፡10-14፡፡
በሐዲስ ኪዳንም የሐዋርያት ተከታዮች የኾኑ መነኮሳት፣ ካህናትና ምእመናን በገዳማት፣ በአድባራት፣ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች፣ የጽዋ ማኅበርተኞች ስለ ማኅበራቸው ጥንካሬና ከማኅበርተኞቹ መካከል አንዱ ችግር ሲገጥመው የማኅበር ሱባኤ ይያዛል፡፡.
#የዐዋጅ ሱባዔ
የዐዋጅ ሱባዔ በአገር ላይ ድንገተኛ አደጋ፣ አባር ቸነፈርና ጦርነት ሲነደ እንዲሁም ለማኅበረ ምእመናን አስጊ የሆነ መቅሰፍት ሲከሰት፣ እግዚአብሔር መሽቱን በምሕረት ቁጣውን በትዕግሥት እንዲመልስ የሚያዝ የሱባዔ ዓይነት ነው፡፡ ለዚህ ዓይነቱ ሱባዔ የነነዌ ሰዎችና በፋርስ በስደት ይኖር የነበረ እስራኤላውያን ተጠቃሾች ናቸው፡፡ የነነዌ ሰዎች የዮናስን ስብከት ሰምተው ከሊቅ እስከ ደቂቅ ለሦስት ቀን ከመብል ከመጠጥ ተከልክለው በመጾም በመጸለይ እግዚአብሔር መዓቱን በምሕረት ቁጣውን በትዕግሥት እንዲመልስ አድርገዋል፡፡ ሌላው በፋርስ በስደት ይኖር የነበረ አይሁድ በአስቴር ትእዛዝ የያዙት ሱባዔ ተጠቃሽ ነው፡፡ በዚያን ዘመን አርጤክስስ አይሁድ በያሉበት እንዲገደሉ በማዘዙ ከዚህ የጅምላ ጭፍጨፋ ለመዳን አይሁድ በዐዋጅ ሱባዔ ገብተዋል፡፡ አስቴር ገብታ ንጉሡን ስታናግረው ሌላው ሕዝብ በውጭ ዐዋጅ ዐውጀው ሱባዔ ገብተው ፈጣሪያቸውን ተማፅነዋል፡፡ አስቴር 4፡16 - 28፡፡
በአገራችንም ይህን የመሰለ የዐዋጅ ሱባዔ በዐፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ተደርጓል፡፡ ፋሽስት ጣልያን አገራችንን በመውረር ኢትዮጵያን ቅኝ ተገዥ ለማድረግ ድንበሯን አልፎ በመጣበት ወቅት ንጉሠ ነገሥት ምኒልክ፡- «ጉልበት ያለህ በጉልበትህ ጉልበት የሌለህ በጸሎትህ ርዳኝ» በማለት የዐዋጅ ሱባዔ መያዛቸው ይነገራል፡፡ በዚህም መሠረት በየገዳማቱ ምሕላ ተይዟል፤ ንጉሡም ታቦተ ጊዮርጊስን ይዘው ዓለምን እጅግ ያስደነቀ ጥቁሮችን ለነጻነታቸው እንዲነሣሱ የሚያስችል ፋና ወጊ የሆነ ድል አግኝተው አገራችንን ለቅኝ ግዛት ያሰበውን ፋሽስት ጣልያንን ማሸነፋቸው በከፍተኛ ስሜት የምናስታውሰው ነው፡፡
#ቅድመ ሱባዔ(ከሱባዔ በፊት) ዝግጅት
ሱባዔ መግባት የሚፈልግ ምእመን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ያለምንም ዝግጅት ሱባዔ መግባት ለፈተና ያጋልጣል፡፡ ስለዚህ ቅድመ ሱባዔ /ሱባዔ ከመግባት አስቀድሞ/፣ ጊዜ ሱባዔ/ በሱባዔ ጊዜና ድኅረ ሱባዔ /ከሱባዔ በኋላ/ ዝግጅት አስፈላጊ ነው፡፡
ቅድመ ሱባዔ /ሱባዔ ከመግባት አስቀድሞ/በመጀመሪያ ሱባዔ የምንገባበትን ምክንያት ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ አንድ ሰው ሱባዔ የሚገባበትን ዓላማ ለይቶ ካስቀመጠ ከሱባዔ በኋላ የሚጠበቀውን ነገር ማግኘት አለማግኘቱን ይረዳል፡፡ ይህ ሳይሆን ሱባኤ ቢገባ ከሱባኤው በኋላ የጠየቀው ነገር ስለሌለ ትርጉም ያጣል፡፡ ስለዚህ ሱባዔ ከመግባታችን በፊት ለምን ሱባኤ ለመግባት እንዳሰብን ለይተን ማወቅ ይኖርብናል፡፡
ሱባዔ ለመግባት የወሰንበትን ምክንያት ከለየን በኋላ ምክንያታችንን ይዘን የንስሐ አባታችንን ማማከር ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም በምክረ ካህን መጓዝ መጀመር ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር በአባትነታቸውና በሕይወት ልምዳቸው ምን ማድረግ እንደሚገባን ምክር ለማግኘት እገዛ ያደርግልናል፡፡ ቅድመ ሱባኤ ከንስሐ አባት ጋር መመካከር ተገቢ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው በሱባዔ ወቅት የተለያዩ ፈተናዎች ቢያጋጥሙት የተሰጠውን ምክር በመጠቀም ፈተናውን ለመቋቋም ይችላል፡፡ እንዲሁም የንስሐ አባቱ በሱባዔ ወቅት በጸሎት እንዲያስቡት መማከር የራሱ የሆነ ድርሻ አለው፡፡
ሱባዔ ለመግባት ስናስብ ለምን ያህል ቀናት መቆየት እንዳለብን መወሰን ያስፈልጋል፡፡ ሱባዔ ከዚህ እስከዚህ እቆያለሁ ብለን ዕቅድ የምንይዝበት ነው፡፡ እንደ አቅማችንና እንደ ችሎታችን ከዚህ ቀን እስከዚህ ብለን በመወሰን ሱባዔ መግባት ተገቢ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ፡- ምንም ዓይነት ልምድ ሳይኖረው አንድ ሰው «በዋሻ እዘጋለሁ» ቢል ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል፡፡ ምክንያቱም በሱባዔ ወቅት ፈተና ስለሚበዛ የሚመጣበትን ፈተና መቋቋም ባለመቻል ሱባዔው ሊቋረጥ ይችላል፡፡ ስለዚህ ቅድመ ሱባዔ ዐቅምንና ችሎታን አገናዝቦ መወሰን ተገቢ ነው፡፡
ሌላው ቅድመ ሱባዔ ለሱባዔ ተስማሚ የሆነ ወቅትና ቦታ መምረጥ ተገቢ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን በአብዛኛው ሱባዔ የሚገባው አጽዋማትን ተከትሎ ነው፡፡ ስለዚህ ሱባዔ የምንገባበት ወቅት የጾም ወቅት መሆን አለመሆኑን መለየት ያስፈልጋል፡፡ በአጽዋማት ወቅት የሚያዝ ሱባዔ ለተሐራሚ ጠቀሜታው እጅግ የጐላ ነው፡፡ ምክንያቱም በአጽዋማት ወቅት ብዙ አባቶች ሱባዔ ስለሚይዙ ከአባቶች ጸሎት ጋር ልመናችንና ጸሎታችን ሊያርግ ይችላል፡፡ ስለዚህ ወቅትን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
እዚህ ላይ «ከወርኃ አጽዋማት ውጭ ሱባዔ አይያዝም» የሚል አቋም ለመያዝ አይደለም፡፡ አንድ ሰው ፈተና ከአጋጠመው በማንኛውም ጊዜ ሱባዔ ሊገባ እንደሚችል እዚህ ላይ ለመጠቆም እንወዳለን፡፡ ከዚህም ባሻገር ሱባዔ የምንይዝበትን ቦታ መምረጥ አለብን፡፡ ለሱባዔ የምንመርጣቸው ቦታዎች ለፈተና የሚያጋልጡ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ይኸውም ሱባዔ ከተገባ በኋላ ኅሊናችን እንዳይበተን እገዛ ያደርግ ልናል፡፡ ጫጫታና ግርግር የሚበዛበት ቦታ በሰቂለ ኅሊና ለመጸለይ አያመችም፡፡ ስለዚህ ሱባዔ የምንይዝባቸው ቦታዎች ከከተማ ራቅ ያሉ ገዳማትና አድባራት ተመራጭ ናቸው፡፡
#ጊዜ ሱባዔ /በሱባዔ ጊዜ/
በጸሎት ሰዓት ዓምድና ግድግዳ ሳይደገፉ መቋሚያ ሳይዙ በሁለት እግር ቀጥ ብሎ በመቆም መጸለይ ይኖርብናል፡፡ እንዲሁም ፊትን ወደ ምሥራቅ መልሶ መቆም ወዲያና ወዲህ ወደ ግራ ወደ ቀኝ አለመዟዟር በሰፊሐ እድ በሰቂለ ኅሊና ኾኖ መጸለይ ይገባል፡፡ መዝ.5፡3፤ መዝ.133፡2፤ ዮሐ.11፡41፡፡
በሱባዔ ወቅት በቅደም ተከተል መጸለይ አለብን፡፡ መጀመሪያ «በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አአትብ ገጽየ ወኩለንታየ በትእምርተ መስቀልኸ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አንዱ አምላክ መላ ሰውነቴን በትእምርተ መስቀል አማትባለሁ» እያለ ሰጊድን ከሚያነሣው ሲደርስ መስገድ መስቀልን ከሚያነሣ ላይ ስንደርስ ማማተብ ይገባል፡፡
በማስከተል አቡነ ዘበሰማያት፣ መዝሙረ ዳዊት፣ ውዳሴ ማርያምና ሌሎች በመዝገበ ጸሎት የተካተቱትን መጸለይ፤ ቀጥሎ አቡነ ዘበሰማያት፣ ጸሎተ እግዝእትነ ማርያምን፣ ጸሎተ ሃይማኖትን ከጸለይን በኋላ አቡነ ዘበሰማያት መድገም፤ ከዚያ 41 ጊዜ ኪርያላይሶን ይባላል፡፡ ሌላው በሱባዔ ጊዜ ከተሐራሚ የሚጠበቀው ነገር ኃጢአቱን እያሰበ ማዘን ማልቀስ ነው፡፡ ሲያለቅስም ለእያንዳንዱ በደል እንባ ማፍሰስ ያስፈልጋል፡፡
በመጨረሻም ሱባዔ የገባ ሰው ሱባዔውን ሳይጨርስ ወይም ሱባዔውን አቋርጦ ከማ

ንም ሰው ጋር ፈጽሞ መገናኘት የለበትም፡፡
#ድኅረ ሱባዔ /ከሱባዔ በኋላ/
ለቀረበ ተማኅፅኖ እግዚአብሔር የሚያደርግልንን ነገር መጠበቅ ይኖርብናል፡፡ እግዚአብሔር ላቀረብንለት ምልጃና ጸሎት እንደ ልባችን መሻት እንደ እርሱ ቸርነት እርሱ በወደደ ጊዜ ያደርግልናል፡፡ ሱባዔ የገባ ሰው ሁሉ ራእይ ላያይ ይችላል፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር መልስ አሰጣጥ ለማንም ግልጽ አይደለም፡፡ ከሱባዔ በኋላ መጀመሪያ የምናገኘው የኅሊና ሰላምን ነው፡፡ ይህ ትልቅ የአምላክ ስጦታ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ሱባዔ ገብተን ያሰብነውን ካላገኘን ዳግመኛ ተዘጋጅተን እስከ መጨረሻው ሰዓት መማፀን መጽናት ይኖርብናል፡፡
ምንጭ:-Info:- Mk website
#ዓውደ ምህረት የኛ
👇👇👇👇👇👇

#ድንግል_ትንሣኤሽን
_______________
#ድንግል ትንሣኤሽን እስከምናይ ድረስ
ገብተናል ሱባዔ በአንድነት በመንፈስ
ለኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት
አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነ ምሕረት (2× አዝ )
ሞትን የረገጠ ልጅሽ ካንቺ ጋር ነው
ውጦ የሚያስቀርሽ የቱ መቃብር ነው
የዕርገትሽን ዜና ከቶማስ ሰምተናል
ትንሣኤሽ እውነት ነው ሰበንሽን ዐይተናል
*
ሞትማ በሞት #ተሸንፏል
#ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል(2×)
አዝ » » » » »
______
ልናው ወደድን የቶማስን ክብር
ለምን ተሰወረን የትንሣዔሽ ምሥጢር
በራችንን ዘግተን በጸሎት ወድቀናል
ተገልጠሽ አብሪልን ልጆችሽ ናፍቀናል
*
ሞትማ በሞት ተሸንፏል
#ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል(2×)
አዝ » » » » »
__
መዝሙረኛ አባትሽ # ዳዊት ጽፎልናል
ሞትን የማያይ ሰው ማን አለ ብሎናል
ይህ እውነት በዘመን ባንቺ ላይ ቢደርስም
በሞት ተሸንፈሽ መቃብር አትቀሪም
*
ሞትማ በሞት ተሸንፏል
#ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል(2×)
አዝ » » » » »
_______
ቶማስ ከደመናው ወርዶ ሲያናግረን
ስለሆነው ነገር እጅጉን ተመሰጥን
እኛም ይህን ክብር ለማየት ተመኘን
#ድንግል አሳስቢልን #ኪዳነ_ምሕረት
*
ሞትማ በሞት #ተሸንፏል
#ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል(2×)
አዝ » » » » »
አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ነሐሴ ፫/፳ ፻ ፲ ፫
_______________
#ድንግል ትንሣኤሽን እስከምናይ ድረስ
ገብተናል ሱባዔ በአንድነት በመንፈስ
ለኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት
አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነ ምሕረት (2× አዝ )
ሞትን የረገጠ ልጅሽ ካንቺ ጋር ነው
ውጦ የሚያስቀርሽ የቱ መቃብር ነው
የዕርገትሽን ዜና ከቶማስ ሰምተናል
ትንሣኤሽ እውነት ነው ሰበንሽን ዐይተናል
*
ሞትማ በሞት #ተሸንፏል
#ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል(2×)
አዝ » » » » »
______
ልናው ወደድን የቶማስን ክብር
ለምን ተሰወረን የትንሣዔሽ ምሥጢር
በራችንን ዘግተን በጸሎት ወድቀናል
ተገልጠሽ አብሪልን ልጆችሽ ናፍቀናል
*
ሞትማ በሞት ተሸንፏል
#ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል(2×)
አዝ » » » » »
__
መዝሙረኛ አባትሽ # ዳዊት ጽፎልናል
ሞትን የማያይ ሰው ማን አለ ብሎናል
ይህ እውነት በዘመን ባንቺ ላይ ቢደርስም
በሞት ተሸንፈሽ መቃብር አትቀሪም
*
ሞትማ በሞት ተሸንፏል
#ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል(2×)
አዝ » » » » »
_______
ቶማስ ከደመናው ወርዶ ሲያናግረን
ስለሆነው ነገር እጅጉን ተመሰጥን
እኛም ይህን ክብር ለማየት ተመኘን
#ድንግል አሳስቢልን #ኪዳነ_ምሕረት
*
ሞትማ በሞት #ተሸንፏል
#ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል(2×)
አዝ » » » » »
አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ነሐሴ ፫/፳ ፻ ፲ ፫
#እነርሱ_በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፥ ጽድቅን አደረጉ፥ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ፥ #የአንበሶችን አፍ ዘጉ፥ የእሳትን ኃይል አጠፉ፥ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፥ ከድካማቸው በረቱ፥ በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ።
#ቅዱስ_ጳውሎስ
#ዕብ 11÷33-34
#ቅዱስ_ጳውሎስ
#ዕብ 11÷33-34
ስለ ታቦቲቱ የባዕዳኑ መልከታ
...... #ካለፈው የቀጠለ.....
#ጀምስ_ብሩስ /james bruce/
____________________________
#የዓባይን ምንጭ ወይስ #ታቦቲቱን ፍለጋ ???
_________________________________
ባለፈው ጽሑፋችን ግራሃም ሐንኰክ የጠፋው ታቦት ዘራፊዎች/#Raiders_of_the_Lost_Ark/ በሚል ርእስ የተሠራውን የሆሊውድ ፊልም በ 1983 ናይሮቢ ውስጥ ካየ በኋላ ታቦቲቱን ለማግኘት እንደተነሳሳ ዓይተን ነበር። አሁን ደግሞ ጀምስ ብሩስን በሽፋን ስም ታቦቲቱንና መገኛዋን ለማግኘት ያደረገውን ምሥጢራዊ ጥረት እንመለከታለን።
#ከክርስቶፈር ደጋማ ሞት በኋላ "የክርስቶስ ሠራዊት" ስለ ኢትዮጵያ ለማወቅ የነበረው ጉጉት እየቀዘቀዘ ሲመጣ የስኮትላንዱ "ምሥጢራዊ የወንድማማቶች ማህበርም " ስለ ሰሎሞን ቤተ መቅደስና የቃል ኪዳኑ ታቦት የወረሳቸው አንዳንድ ምሥጢራዊ የሃይማኖት ሥርዓቶች ሲኖሩ በነዚህም ውስጥ ታቦቱ ጉልህ ሚና አለው።
በመሆኑም በዚህ ረገድ በድፍረቱና በቆራጥነቱ ስለሚታወቀውና ቴምፕላሮችን ካዳነው ከንጉስ ብሩስ ጋር የዘር ግንዱን ስለሚቆጠረውና ኢትዮጵያ በስፋት ስለጎበኘው የእስኮትላንዱ ተወላጅ ጀምስ ብሩስ መለመለ።
#ረጅሙና ግዙፉ ጀምስ ብሩስ ስኮትላንድ ውስጥ 1730 ተወለዶ ከፍተኛ ትምህርቱን በኤደን ብራ ዩኒቨርሲቲ ያጠናቀቀ ምሁር ነው። በትምህርቱ በኋላ ኢስት ኢንድያ በተባለ ድርጅት ተቀጥሮ ሠርቷል። ይሁንና በ1754 ባለ ቤቱ ስለሞተች በደረሰበት ብስጭት የተነሣ ከሀገር ወደ ሀገር መዘዋወር የጀመረ ሰው ነው።
የነበረው የቋንቋ ችሎታው በማጤንም በሰሜን አፍሪካ አልጀርስ ውስጥ የብሪቲሽ ቆንጽላ በመሆን እንዲሰራ ከመደረጉም ባሻገር ወደ ቅድስቲቱ ሀገር ወደ ኢየሩሳሌምም ተጉዟል። በቋንቋ ረገድ አረብኛ፣ፖርቱጋልኛ እንዲሁም ጥንታዊ የሆነውን የኢትዮጵያ ቋንቋ (ግእዝን) ያውቅ ነበር።
#ጀምስ_ብሩስ በ1759 የግእዝ ቋንቋ ያጠናበት ዋነኛ ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ ለመዝለቅ ላሰበው ጉዞ ዝግጅት ለማድረግ ሲሆን ከእርሱ በፊት ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘው የነበሩ ሰዎችን የጻፏቸውንም በማንበብ በማጥናት ስለ ሀገሪቱ በቂ ዕውቀት ጨብጦ ነበር ዘዚያም 1768ወደ ካይሮ በመሄድ ታሪካዊ ጉዞዎን ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቀቀ።
ብሩስ ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ ምን አነሳሳው? እርሱ እንደሚለው የዓባይን ወንዝ ምንጭ ለማግኘትከ1768-1773በተከታታይ የተደረጉ ጉዞዎች( Travels to Discover The Source of Nile in The Years 1768-1773 የሚል ባለ 3ሺህ ገጽ መጻሕፍ በ5 ተከታታይ ጥራዝ ጽፎል። ቢሆንም ግን ቅሉ የዓባይን ወንዝ ምንጭ በትክክል እንኳ አላወቀውም፤አልደረሰበትም የዓባይ ወንዝ ጣና እንደሆነ አስፎሯልና
#ኢትዮጵያዊያን ሊቃውንት ግን የዓባይ ምንጭ ግሽ ዓባይ ሰከላ እንደሆነ እና ዋነኛ ምንጩም ገነት እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስን ዋቢ አድርገው ይገልጻሉ ፤ያምናሉ #ዘፍ 2÷10 -13 የሱ ዓላማ ታቦቲቱን ማግኘት እንጂ የዓባይን ምንጭ ማግኘት ስላልነበረ ነው ያን የሚያክል ባለ ብዙ ገጽ መጽሐፍ ጽፎ ከስተት የደረሰው ። በኢትዮጵያም ሁለት ዓመት ከቆየ በኋላ ሦስት የመጽሐፈ ሄኖክ ቅጂዎችን ሰርቆ ኮብልሏል።
ኢትዮጵያ አ.አ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ነሐሴ ፯ / ፳ ፻ ፲ ፫

Forwarded from ዐውደ ምሕረት (ተርቢኖስ ሰብስቤ)
" #ቀርታ_ያስቀረችን_ምርጥ_ዘር "
ጊዜው ክረምት ወቅቱም የዘር የመከር ወቅት በመሆኑ ዘርና ፍሬ ዝናብና ጠል ገበሬና በሬ ያለ መነጣጠል ይነሱበታል ። የክረምት ወቅት ምሳሌያዊ ትርጉም ዘርፈ ብዙ ነው ። አንዱ ና ዋናው ግን የ5500 ዘመን ወይም የብሉይ ኪዳን ዘመን ፣ የመከራ ፣ የስቃይ ፣ የጨለማ ጊዜ ምሳሌ መሆኑ ነው :: ይኸውም ክረምት የ5ሺህ 500 ዘመን ወይም የብሉይ ኪዳን ምሳሌ ነው መባሉ በክረምት ጭጋግ ፣ ጉም ፣ደመና ይበረታሉ ነጎድጓዳት ይሰማሉ መባርቅት በርቀው ያስደነግጣሉ ይልቁኑ ደግሞ ውኃ ይሰለጥናል :: የክረምት ወቅት ሰቆቃ ይበዛዋል ይልቁኑ በስደት በደጅ ላሉ ሰውች ይብስባቸዋል “ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ፤”
የሚለው የጌታችን ምክርም የዚህን የክረምት ወቅት ጠንካራነት ያሳያል። ማቴ24፥20
የ5500ዘመንም ዘመነ ፍዳ ዘመነ መከራ ዘመነ ጨለማ ነውና በእግረ አጋንንት ተገዝተን በሲዖል እሳት ውስጥ ተግዘን ኖረናል ። በክረምት ውኃ እንዲሰለጥን በብሉይ ኪዳንም ውኃ ሰልጥኖ ፍጥረትን አጥፍቷል ገኃነመ እሳት በርትቷል በክረምት ምድር በውኃ እረክታ ትረሰርሳለች መሬት ትጨቀያለች በብሉይም ሰዎች በኃጢያት ዝናብ በስብሰው በሰዶም ግብር ጨቅይተው ነበር በዚህ ሰበብም ፈጣሪና ፍጡር ሰማይና ምድር ሰውና መላእክት ነፍስና ሥጋ ተጣልተው ከርመዋል በመሆኑም ዘመነ ብሉይ (5500 ዘመን) ከአሰቃቂው የክረምት ወቅት ጋር በእጅጉ ይመሳሰላል ። በመካከላቸውም የጠብ ግድግዳ ተገንብቶ ቆይቷል ቤተ ክርስቲያን በዚህ ወቅት ዘሪ ሊዘራ ወጣ እያለች የመንገድ ዳር፣ የጭንጫ ፣የሾህ ልቡና ያላቸውን ምዕመኖቿን ልብ በስብከተ መልካም መሬት አድርጋ በወንጌሏ ታቀናዋለች ቃል ዘርታ ሕይወት ታጭዳለች ።
ዛሬ ዛሬ ዓለማችን ነጭ ጥቁር ሀገራችን ደግሞ ኦሮሞ ትግሬ አማራ ጉራጌ በመባባል ተከፋፈለዋል። ሁሉም ዘሩ ምርጥ ዘር እንደሆነ ያስባል ሌላው ዘር ሁሉ እንክርዳድ የሚመስለው ነቀዝ ብዙ ነው ። ከሰዶምና ከጎሞራ ቅጣት የተረፍንባት ምርጥ ዘራችን ድንግል ማርያም ነች። ሶሪያዊው ቅዱስ ኤፍሬም የመመኪያችን ዘውድ የድኅነታችም መጀመራያ ብሎ እንደጠራት ትምክተ ዘመድነ የምትባል እመቤታችን ነች ። ከእርሷ በቀር ምርጥ ዘር የሚባል የለንም ።
ይህች ንጽሕት ዘር ወርቅ ነች ወርቅ ከጭቃ ይገኛል ግን ጭቃ አይደለም እመቤታችንም በኃጢያት ጭቃ ከወደቁት ከአዳም እና ከሔዋን ዘሮች የተገች ዳግማዊት ሔዋን ብትሆንም የበደል ጥንት አልነካታም የመተላለፍ እድፍ አላጎደፋትም ስለዚህ በአዳም ገላ ውስጥ ታበራ የነበረች ነጭ እንቁ ነች።
ነቢየ ልዑል ቅዱስ ኢሳይያስ “የሠራዊት ጌታ #እግዚአብሔር_ዘርን_ባያስቀርልን_ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንን እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር።” ብሎ የተናገረላት ከኃጢያት መተዳደፍ በመንጻት ከከፋት ሥራ ሁሉ ቀርታ ከጥፈት ያስቀረችን ምርጥ ዘራችን እመቤታችን ነች። ኢሳ 1፥9 ይህችሁም ንጽሕይት ዘር በወርኃ ክረምቱ ማዕከላዊ ጊዜ በሆነው በነሐሴ 7 (ሰባት)በዛሬዋ ቀን ከሐናና ከኢያቄም ተጸንሳልናለች ይህ ቀን የእመቤታችን ብቻ ሳይሆን እያገዳደለን ካለው የዘረኝነት ግዳይ ዓለማችንንና የሀገራችንን ትንሳኤ የምታደርግበት የድኅነታችን ጽንስ መጀመሪያም ቀን ነው።
በክረምት ወቅት የሰማይ መስኮቶች ተከፍተው ዝናብ ለዘር ጠል ለመከር ይሰጣሉ ታዲያ ይህ ጊዜ ለትጉህ ገበሬ ምቹ ነው በሬውን ይጠምዳል መሬቱን ያርሳል ዘሩን ይዘራል ዝናቡን በጉድጓድ ያጠራቅማል መባርቅቱን ፣ ነፋሳቱን ይታገሳል። በመጨረሻውም የድካሙን ፍሬ አዝመራውን ያጭዳል በመከራ እንዳልዘራ በደስታ ይሰበስባል " በልቅሶ የሚዘሩ በደስታ ይለቅማሉ ። በሄዱ ጊዜ፥ ዘራቸውን ተሸክመው እያለቀሱ ተሰማሩ፤ በተመለሱ ጊዜ ግን ነዶአቸውን ተሸክመው ደስ እያላቸው ይመጣሉ ። መዝ (125) 126 ÷5 ሰነፍ ገበሬ በአንጻሩ ብርዱን ቸነፈሩን ተሰቆ ቤቱ ይተኛል እገሌ ከኔ ወገን ነው ደግ ነው እገሊት ከወንዝ ማዶ ናት አትመስለንም ባለፈችበት እንዳታልፉ በዞረችበት አትዙሩ የሚል ነው የአጥንት እንጂ የእህል ዘር የማያውቅ :: ዘረኝነት ኃጢያት ነው ኃጢያት ደግሞ ማጣት ማለት ነው ባለ ብዙ ዘሮች ነን የሚሉ ዘረኞች ሃይማኖቱን፣ ምግባሩን ፣ ፖለቲካውን ፣ ሥልጣኑን ፣ ዕውቀቱን፣ ውበቱን ፣ ሙቀቱን ፣ድምቀቱን፣ ዝናውን ፣ተሰሚነቱን የያዙ ይመስላቸው ይሆናል ነገር ግን አንዱም እንኳ የላቸውም አጥተውታል። ሰው ኃጢያትን (ዘረኝነት) ዘርቶ እንዴት አንድነትን ሊያጭድ ይችላል ??? በእኩልነት ሰበብ በኩይ ከከፋፈሉን በኃላ በእንድነት ደግሞ እንምራቹ አሉን በአንድ ገመድ ሁሉንም ከብቶች አስሬ ልምራቸው የሚል እረኛ የለም ቢኖር ግን ይህ ምንደኛ እንጂ እረኛ አይደለም ምክንያቱም ከብቶቹን በአንድ ታስረው ወደ ሚፈልጉት የልማት ጉዳና የሥልጣኔ ማማ መድረስ አይቻላቸውምና። አንዱ ወድቆ ሊላውን የሚጠልፍበት የውድቀት ትርምስ ነው የሚሆንባቸው ። ከዛም አልፎ ከለመለመው መስክ ሳይሰማሩ በረፍትም ውኃ ዘንድ ሳይቀርቡ ከናፈቁት በረታቸውም ሳይገቡ የነጣቂ ተኩላ ሲሳይ የጅብ እራት ሆነው ይቀራሉ ። “ኃጢአትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፥ ”ምሳሌ 22፥8 " ማሰር መፍትኤ የሚሆነው ጠባቂ ከሌለ ብቻ ነው! " ። እረኛ ካለ ገመድ ለምኔ ?
........ ይቆየን.............
@YEAWEDIMERITE
አዘጋጅ :- ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ማርያም
ነሐሴ 7 ቀን 2012ዓ,ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ከአክራሪ እስልምና ወደ አፍቃሪ ክርስትና
የጥንቷ የከፋ መናገሻ የአሁና ጂማ ክርስትና ከተስፋፋባቸው የመካከለኛው ዘመን የስብከተ ወንጌል ዋና መዳረሻዎች ውስጥ አንዷ ናት ከጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ደቀመዛሙርት መካከል አባ ዮሴፍ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የወንጌልን ብርሃን ካበሩ አባቶቻችን አንደኛው ናቸው።
ጅማ የቀድሞዋ እናርያ ያለችው ቅድስት ቤተክርስቲያን በመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ጉልህ ሚና የነበራት አሁንም ያላት የኢትዮጵያ ግዛት ናት ዛሬ ዛሬ እነ ዋቢያ እነ ሰለፊያ እነ ሱኒዎች ወዘተ ባልኖሩበት ዘመን ቅድስት ቤተክርስቲያን በዚያ አካባቢ ያለውን ምዕመን ፈሪኃ እግዚአብሔር እንዲኖረው ለሺ ዓመታት ደክማበታለች እበሚያሳርፉባት መከራ በተለያየ ጊዜ ቅድስት ቤተክርስቲያን በጂማ አገረ ስብከት መከራ አሳልፋለች የዛሬው ታሪክም በጂማ ከተማ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን በተደጋጋሚ የቃጠሎ የማፍረስ እና ምዕመኗን የማንገላታት ሂደትም ውስጥ ከተሳተፉት አንዱ ቃሲም አባ ሁሴን ይገኝበታል (ስሙ የተቀየረ) ከቃሲም ጋር የተገናኘነው አዲስ አበባ ሲሆን ስለቅድስት ቤተክርስቲያን አንዳንድ ጉዳዮችን ከበቆጂ የተዋሕዶ ልጆች ጋር በማወራበት ስዓት ነበር ይሄን በሌላ ጊዜ አጫውታችዋለሁ ድንገት ቃሲም አንድ ቃል ወረወረ ጅማ ቤተክርስቲያን ሲቃጠል ግምባር ቀደም ሆኜ ሳቃጥል ነበር በማለት ወዲያው ትኩረቴን ሳበው የ2002 ረብሻው ሲነሳ በስራ አጋጣሚ እዛ ስለነበርኩ ጆሮዪን ሳበውና በደምብ ላወራው ፈለኩ ተቀጣጥረን ድምፁንም እንደምቀዳው ነገርኩት በዚህም ተስማምተን ተለያየን በቀጠሯችንም በሳምንቱ ተገናኘን።
ከመጀመርያ ጀምሮ ያለውን ታሪክና እንዲህ በማለት አጫወተኝ እኔ በአጭሩ አቅርቤዋለሁ።
2000 ላይ ሁለት ጊዜ በረብሻው ተካፍያለሁ ቁራን የምንቀራበት የጅማው አኗር መስኪድ ኢመማ በማይክራፎን ሙስሊም አደጋ ላይነው አደጋውንም የሚያደርሱት ኦርቶዶክሶች ናቸው በማለት ቅስቀሳ አደረገ እኛም ተሰብስበን በመሄድ ቤተክርስቲያኗ ላይ ጥቃት አደረስን ትርምስ ሆነ በዚህ መልኩ በዚሁ ዓመት ሁለቴ ተሳትፊያለሆ ለመጨረሻ ጊዜ የተሳተፍኩት 2002 ሲሆን እንደቀድሞው ተቀሰቀስን ለሊት ስድስት ሰዓት ላይ ቤተክርስቲያኗን ማቃጠል አለብን ብለን ተነስተን ሄድን እንደ ሌላው ጊዜ ግን አልሆነም ከአዕምሮ በላይ የሆነ ለዓይን የሚከብድ ብርሃን ሆነ እኔ ብቻ አይደለም ያየሁት ቤተክርስቲያኗን ለማጥቃት የሄድነው ሁላችንም አንድላይ ነው ያየነው አላዋክበር ሌላም ሌላም በማለት ተበታተንን ይሄ ቂያማ ነው እያልን ወደቤት የሚሄደው ወደ ቤት የተቀረው ወደ መስኪድ ተበተነ በነገራችን ላያ ቂያማ በእስልምናው የመጨረሻው ቀን እንደማለት ነው። ቃሲም ይቀጥላል ብቻዬን ቀረው በውስጤ ሁለቴ አልሞትም ከሞትኩ አንዴነው በማለት እዛው የሚሆነውን አየው የታየው ብርሃን ጠፋ ብርሃን የወረደበት ቦታው ላይም ጠበል ፈለቀ በሌላ ቀን በጠዋት ሲነጋጋ ሰብሰብ ብለን ለማጣራት ሄድን ቄሶቹ የፈለቀውን ጠበል ምዕመኑን እያጠመቁ ከምዕመናኑም መካከል ሲፈውሱ አየሁ እስላሙም እየተጠመቀ እየተፈወሰ ሲሄድ በአይኔ ተመለከትኩ ብርሃኑን ባየሁበት ቅጽበት ውስጤ በጥያቄና በመልስ ተሞልቶ ስለነበር እንዴት ሃይማኖት መግደል ይሰብካል፤ ኢሳ አልሞተም መሐመድ ሞቷል እንዴት የኢሳን ልደት አላከበርንም እንዴት ስለማርያም አያስተምሩንም የሚሉ ጥያቄዎች በአዕምሮዬ ተመላለሱ ወዲያው ነበር መስኪድ ቁራን ለሚያስቀራን ኢማም አስር ሆነን ጠየቅን ኢማሙም እናንተ ገና ናቹ በማለት ሳይመልስልን ቀረ እኛም ድጋሚ እንደዚህ አይነት ግጭት ውስጥ ከወንድሞቻችን ጋር አንገባም በማለት እራሳችንን አገለልን በወቅቱ ከፌደራል ታዞነው ተብሎ ክርስቲያኑ መስኪድ ኢስላሙ ደግሞ ቤተክርስቲያን እንድንሰራ ሆነ አስር የምንሆን ወጣቶች ከዛ ቡድን ተለየን እንደዚህ አይነት ብርሃን አይቼ አላውቅም ፈጣሪ ነው ይህን ተአምር የገለጠው በማለት ከአጥፊዎቹ መሃል ተለየ ፈጣሪ ክፉ ነገርን አያዝምና ።
ከጂማ እስከ አዲስ አበባ ደብረ አሚን ተክለሃይማኖት ቃሲም ይቀጥላል.........
@YEAWEDIMERITE
አዘጋጅ :- መ/ር ማርቆስ አለማየሁ
ነሐሴ ቀን 2012ዓ,ም

#እዛ_ማዶ ጭስ ይጨሳል አጋፋሪ ይደግሳል
____________________________________
ማለት እስራኤል ከግብጽ ባርነት በወጡ ጊዜ በጭስ የተመሰለ ጉምና ደመና እየመራቸው ቅዱስ ሚካኤል መና እያወረደላቸው ስለወጡ ጭስ የተባለው የደመናው ምሳሌ ፤ አጋፋሪ የተባለው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡
#ያችን_ድግስ ውጬ ውጬ በድንክ አልጋ ተገልብጬ
____________________________________
ማለት በድግስ የተመሰለውን መና እስራኤል 40 ዘመን በአጋፋሪ በተመሰለው በቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት እየተመገቡ በድንክ አልጋ የተመሰለችውን ኢየሩሳሌምን መውረሳቸውን የሚያመለክት ነው፡፡ “ያቺ ድንክ አልጋ ሆ አመለኛ ሆ ያለ አንድ ሰው ሆ አታስተኛ” ሆ” መባሉ እስራኤል ከግብጽ ሲወጡ 600,000 ሆነው ሲሆን ነገር ግን ሁሉም በምድረ በዳ አልቀው ኢየሩሳሌምን የወረሳት አንድ ኢያሱና አንድ ካሌብነው ለማለት ነው፡፡ #መልካም በዓል

#ማርያም_ዐርጋለች
ማርያም አርጋለች ወደ ገነት (2)
የሰማይ መላእክት እያረጋጓትት
እርሷም እንደ ልጇ ተነሥታለች
የአባቷ ዳዊትን ትንቢት ልትፈጽም
ወርቁን ተጎናጽፋ በቀኙ ልትቆም
ወደ አምላክ ማደሪያ ወደ ሰማያት
ዐረገች በእልልታ ድንገል የኛ እናት
ዐርጋለች ማርያም ተነሥታለች
#አዝ » » » »
ሰማይም ይከፈት ደመናም ይዘርጋ
ዝምታ አይኖርም እመ አምላክ ዐርጋ
አንደበት ይከፈት ማርያምን ያመስግን
ከዘለዓለም ጥፋት በምልጃዋ እንድንድን
አርጋለች ማርያም ተነሥታለች
#አዝ » » » »
የአምላክ ማደርያ ያ ቅዱስ ሥጋሽ
አምላክን ያቀፉት እነዚያ እጆችሽ
ሙስና መቃብር ይዞ አላስቀራቸው
ተነሥተዋል በክብር በእምነት አየናቸው
ዐርጋለች ማርያም ተነሥታለች
#አዝ » » » »
ሐዋርያት አበው እንኳን ደስ ያላችሁ
በክብር ዐረገች ማርያም ሞገሳችሁ
ወደ ዓለምም ውጡ ሰበኗን ይዛችሁ
የድንግል ዕርገቷን ንገሩ ተግታችሁ
ዐርጋለች ማርያም ተነሥታለች
#አዝ » » » »
#ሊቀ_መዘምራን ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
ማርያም አርጋለች ወደ ገነት (2)
የሰማይ መላእክት እያረጋጓትት
እርሷም እንደ ልጇ ተነሥታለች
የአባቷ ዳዊትን ትንቢት ልትፈጽም
ወርቁን ተጎናጽፋ በቀኙ ልትቆም
ወደ አምላክ ማደሪያ ወደ ሰማያት
ዐረገች በእልልታ ድንገል የኛ እናት
ዐርጋለች ማርያም ተነሥታለች
#አዝ » » » »
ሰማይም ይከፈት ደመናም ይዘርጋ
ዝምታ አይኖርም እመ አምላክ ዐርጋ
አንደበት ይከፈት ማርያምን ያመስግን
ከዘለዓለም ጥፋት በምልጃዋ እንድንድን
አርጋለች ማርያም ተነሥታለች
#አዝ » » » »
የአምላክ ማደርያ ያ ቅዱስ ሥጋሽ
አምላክን ያቀፉት እነዚያ እጆችሽ
ሙስና መቃብር ይዞ አላስቀራቸው
ተነሥተዋል በክብር በእምነት አየናቸው
ዐርጋለች ማርያም ተነሥታለች
#አዝ » » » »
ሐዋርያት አበው እንኳን ደስ ያላችሁ
በክብር ዐረገች ማርያም ሞገሳችሁ
ወደ ዓለምም ውጡ ሰበኗን ይዛችሁ
የድንግል ዕርገቷን ንገሩ ተግታችሁ
ዐርጋለች ማርያም ተነሥታለች
#አዝ » » » »
#ሊቀ_መዘምራን ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ