#ድንግል_ትንሣኤሽን
_______________
#ድንግል ትንሣኤሽን እስከምናይ ድረስ
ገብተናል ሱባዔ በአንድነት በመንፈስ
ለኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት
አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነ ምሕረት (2× አዝ )
ሞትን የረገጠ ልጅሽ ካንቺ ጋር ነው
ውጦ የሚያስቀርሽ የቱ መቃብር ነው
የዕርገትሽን ዜና ከቶማስ ሰምተናል
ትንሣኤሽ እውነት ነው ሰበንሽን ዐይተናል
*
ሞትማ በሞት #ተሸንፏል
#ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል(2×)
አዝ » » » » »
______
ልናው ወደድን የቶማስን ክብር
ለምን ተሰወረን የትንሣዔሽ ምሥጢር
በራችንን ዘግተን በጸሎት ወድቀናል
ተገልጠሽ አብሪልን ልጆችሽ ናፍቀናል
*
ሞትማ በሞት ተሸንፏል
#ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል(2×)
አዝ » » » » »
__
መዝሙረኛ አባትሽ # ዳዊት ጽፎልናል
ሞትን የማያይ ሰው ማን አለ ብሎናል
ይህ እውነት በዘመን ባንቺ ላይ ቢደርስም
በሞት ተሸንፈሽ መቃብር አትቀሪም
*
ሞትማ በሞት ተሸንፏል
#ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል(2×)
አዝ » » » » »
_______
ቶማስ ከደመናው ወርዶ ሲያናግረን
ስለሆነው ነገር እጅጉን ተመሰጥን
እኛም ይህን ክብር ለማየት ተመኘን
#ድንግል አሳስቢልን #ኪዳነ_ምሕረት
*
ሞትማ በሞት #ተሸንፏል
#ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል(2×)
አዝ » » » » »
አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ነሐሴ ፫/፳ ፻ ፲ ፫
_______________
#ድንግል ትንሣኤሽን እስከምናይ ድረስ
ገብተናል ሱባዔ በአንድነት በመንፈስ
ለኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት
አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነ ምሕረት (2× አዝ )
ሞትን የረገጠ ልጅሽ ካንቺ ጋር ነው
ውጦ የሚያስቀርሽ የቱ መቃብር ነው
የዕርገትሽን ዜና ከቶማስ ሰምተናል
ትንሣኤሽ እውነት ነው ሰበንሽን ዐይተናል
*
ሞትማ በሞት #ተሸንፏል
#ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል(2×)
አዝ » » » » »
______
ልናው ወደድን የቶማስን ክብር
ለምን ተሰወረን የትንሣዔሽ ምሥጢር
በራችንን ዘግተን በጸሎት ወድቀናል
ተገልጠሽ አብሪልን ልጆችሽ ናፍቀናል
*
ሞትማ በሞት ተሸንፏል
#ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል(2×)
አዝ » » » » »
__
መዝሙረኛ አባትሽ # ዳዊት ጽፎልናል
ሞትን የማያይ ሰው ማን አለ ብሎናል
ይህ እውነት በዘመን ባንቺ ላይ ቢደርስም
በሞት ተሸንፈሽ መቃብር አትቀሪም
*
ሞትማ በሞት ተሸንፏል
#ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል(2×)
አዝ » » » » »
_______
ቶማስ ከደመናው ወርዶ ሲያናግረን
ስለሆነው ነገር እጅጉን ተመሰጥን
እኛም ይህን ክብር ለማየት ተመኘን
#ድንግል አሳስቢልን #ኪዳነ_ምሕረት
*
ሞትማ በሞት #ተሸንፏል
#ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል(2×)
አዝ » » » » »
አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ነሐሴ ፫/፳ ፻ ፲ ፫