አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
481 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የእንባ_ቀብድ


#ክፍል_አንድ


#በአሌክስ_አብርሃም


በታላቋ አሜሪካ፣ በግዙፍ ሰማይ ጠቀስ ሕንጻዎች ሥር ሳልፍ፣ በውብ መናፈሻዎች ራስጌና ግርጌ ስመላለስ፣ ሰፋፊ መንገዶች እንኳን በእግር ሄደውባቸው በዓይን አይተው በማያካልሏቸው ትላልቅ የገበያ አዳራሾት መኻል ወዲህ ወዲያ ስል፣ ነፍሴ መደበቂያ የሚሆን አንዳች ሽርኩቻ ፍለጋ ትራወጣለች: አፍንጫዬ ሁልጊዜ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚሸት አየር፣ ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊ የሚሸት ሰው ፍለጋ ይቀሰራል፡፡ በርገር እና ፒዛ
ቤት ገብቼ የዶሮ ወጥ ሽታ አነፈንፋለሁ፡፡ እግሬ የአሜሪካን ምድር ከረገጠበት ቀን ጀምሮ እየተነፈስኩ እታፈናለሁ፣ እያወራሁ እታፈናለሁ። ናፍቆት አይደለም፤አለመመቼትም አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊነት በሚስኪን ነፍስ ውስጥ የታሰረ ግዙፍ መንፈስ ነው ይኼ መንፈስ አሜሪካ ይጠብበዋል፣ ዓለም ይጠብበዋል:: ለአንድ
ኢትዮጵያዊ፣ እንደ ጫማ እና እንደ ልብስ ተለክታ የተሠራች ብቸኛ የመንፈሱ ጓዳ፣በሚጠብበው ዓለም ውስጥ ያለችው ሰፊዋ ኢትዮጵያ ብቻ ናት፡፡ ሌላው ሁሉ ይጠብባኛል፡፡

ለዚህም ሳይሆን አይቀርም፣ ባለችኝ ትንሽ ትርፍ ጊዜ ሁሉ ልክ እንደ እናት ማሕፀን የምትሞቅ፣ ከቤቴ ወደ ሃያ ደቂቃ መንገድ የምትርቅ፣ ጠባብ የሐበሻ ሱቅ ውስጥ የማልጠፋው፡፡ የአብሮ አደጌ የፋሲል ሱቅ ናት፡፡ ፋሲል አስማተኛም፣ አርበኛም
ይመስለኛል፡፡ ሚኒሊክ ፣አሉላ አባነጋ፣ በላይ ዘለቀም ይመስለኛል። አገሬን ከወራሪ ሰላቶ
ማስጣል ብቻ ሳይሆን፤ ተሸክሞ አምጥቶ ነጮች ምድር ያውም መሀል ከተማቸው ላይ በክብር ያስቀመጠ አርበኛ ይመስለኛል። አንድ ሐበሻ አስቁሞ “የኢትዮጵያ ኤምባሲ' የት ነው” ቢለኝ፣ የፋሲልን ሱቅ የምጠቁም እስኪመስለኝ ለእኔ ይህች ሱቅ በወርድም በቁመትም ትንሽ ኢትዮጵያ ነበረች፡፡

የጤፍ እንጀራ የሚቸረቸርባት… መቸርቸር ብቻ አይደለም ስለ እንጀራ ኬሚስትሪ የሚወራበት አብሲቱ በሙቅ ውሃ ተቀይጦ… የእንጀራው ዓይን እንዲህና እንደዛ ሆኖ ሰርገኛ ጤፍ ነጭ ጤፍ የሚባልባት፣ የሐበሻ ቡና የሚሸጥባት፣ የእሳት አደጋ ማስጠንቀቂያ ላይጮኸ እጣን በጊርጊራ የሚቦለቀለቅባት፣ የጀበና ቡና በጤናዳም
የሚጠጣባት፣ ጥሬ ሥጋ በፓውንድ የሚሸጥባት፣ ካለፈቃድ የሴት ልብስ መንካት ዘብጥያ በሚያስጥልባት አሜሪካ ባህሩ ቃኘ “ያዝ እጇን የሚባልባት ሱቅ፣ ጥላሁን ገሠሠ
"ጸልጌ አስፈልጌ፣ አስቴር አወቀ እሹሩሩ ፍቅር” የሚሉባት ሱቅ

የማነብበው ነገር ካለ እያነበብኩ፣ እጽፍም እንደሆነ ላፕቶፕ ኮምፒውተሬን ከፍቼ
ወጪና ሂያጁን ሐበሻ እየቃኘሁ፣ በዕረፍት ቀኔ ከፋሲል ጋር እውላለሁ! ሐበሻ ይመጣል፣
ዶላር ወደ አገር ቤት ይልካል፡፡ ሐበሻ ይመጣል፣እንጀራ ይገዛል፡፡ ሐበሻ ይመጣል፣ ቡና
ይገዛል፡፡ ሐበሻ ይመጣል፣ የወጥ ቅመም ይገዛል፡፡ ሐበሻ ይመጣል፣ የሚከራይ ቤት
ያለው ሰው ይጠይቃል፣ ሐበሻ ይመጣል፣ ፖለቲካ ያወራል፡፡ የአሜሪካ ፓስፖርት ተሸክሞ “አገሩ አሜሪካ ከሽብርተኛ ጋር እዚያ መካከለኛው ምሥራቅ እየተፋለመችና በሚከፍለው ግብር ያመረተችውን ብዙ ቶን ቦንብ እያራገፈች መሆኑን የሚያሳይ ዜና ፊት ለፊቱ ባለ ቴሌቪዥን እየተላለፈ፣ በወረቀት በተሰናበታት ኢትዮጵያ ውስጥ ሲኖትራክ መኪና ስለገጨው የመንገድ አጥር እየተብሰለሰለ በስሜት ያወራል፡፡ ሐበሻ
ነዋ! አንዱ ይመጣል፣ ሱቋ ውስጥ የተለጠፈውን የሚኒሊክን ፎቶ እየገላመጠ እንጀራ ገዝቶ ይሄዳል፡፡ ሌላው ይመጣል፣ በወዲያ በኩል የተለጠፈውን የመለስ ዜናዊን ፎቶ እየረገመ፣ እንጀራ ገዝቶ ይሄዳል፡፡ ሱቋ ውስጥ የሌለ የአገር መሪ ፎቶ የለም- ጥቁረቱም ከንፈሩም መንግሥቱ ኃይለማሪያምን የሚያስንቅ ሐበሻ መጥቶ፣ “ይኼን ሌንጨጫም ባሪያ ምን ይሁን ብላችሁ ለጠፋችሁት ደግሞ!?” ብሎ…ሁለት ፓውንድ ሥጋ አስቆርጦ በላዩ ላይ አሥር እንጀራውን አንጠልጥሎ ይሄዳል፡፡ ሐበሻ … በጤፍ እንጀራ ቀጭን ክር ላይ በሰልፍ የተሰካ የመቁጠሪያ ጠጠር ይመስለኛል፡፡ የተለያየ ግን የተሳሰረ።

ከተማረውና ከፍ ያለ ቦታ ካለው ሐበሻ ጀምሮ፣ እስከ ቀን ሠራተኛውና የታክሲ ሾፌሩ ድረስ ወደ ፋሲል ሱቅ የማይመጣ ሐበሻ የለም፡፡ መናኸሪያ ነበረች፡፡ ወሬ፣ ሐሜትና ፖለቲካው ይጦፋል፡፡ መረጃው ይጎርፋል፣ የሴራ ትንታኔው እየተነሳ ይጣላል፡የእድርና እቁብ ብር ይሰበሰባል፡፡ ፋሲል ሱቅ ስቀመጥ፣ አገሬን ትቼ የሄድኩ ሳይሆን፣ አገሬ ራሷ ውስጧ እንደተቀመጥኩ፣ እንደ አውሮፕላን ይዛኝ በርራ እዚያ ያሳረፈችኝ ይመስለኛል፣
አብረን ያረፍን፡፡ እንዲያውም ከስቋ ስወጣና የፈረንጅ መዓት ወዲያ ወዲህ ሲል፣የተወረርን ነው የሚመስለኝ::

የኑሮን ጎምዛዛ ጣዕም አገር ቤት ጣጥዬው መጣሁ ያልኩ እኔ ፣የሕይዎትን እውነተኛ ገጽ
ያየሁት፣ እንደመስኮት ሁሉን በጨረፍታ በምታስቃኘው በዚች ሱቅ ነበር፡፡ ደግሞ
ምሬቱ፡፡ ዕድል ፈግ ካላለች በስተቀር ምድሩ ወጥመድ ነው! ሥጋ እየደለለ ነፍስ ዐጽሟ
የሚቀርበት ምድር!

የሚመጣው ሁሉ የከሸፈ ታሪክ ልቡ ውስጥ አለ፡፡ የከሸፈ ኳስ ተጫዋች፣ የከሸፈ ሀኪም የከሸፈ ኢንጅነር፣ የከሸፈ ከያኒ፡ የከሸፈ ባለስልጣን ፣የከሸፈች ቆንጆ ሁሉም 'ነበርኩ' የሚለው ትዝታ አለው፡፡ ታዲያ ድፍን ሐበሻ አሜሪካ ላይ ወገቡ እስኪቆረጥ ሰርቶ በሰዓት የሚከፈለውን ድርጎ፣ የላቡ ዋጋ ሳይሆን እዛ አገር ቤት ትቶት ለመጣው፣ ለከሸፈ ትላንቱ የሚከፈል ካሳ ይመስለኛል፡፡

እንድ ቀን አንድ መላጣ ሰውዬ መጣ ዕድሜው ሃምሳዎቹን ያለፈ፤ ቢበዛ አራት ዓመት
የሚሆነው በምቾት ብዛት የተላጠ ብርቱካን የመሰለ ሕፃን ልጅ አቅፏል፡፡ ያስታውቃል
ያቀፈው ልጁ ከብዶታል፡፡ በኋላ ሰውዬው ራሱ "ልጄ ነው አለ እንጂ የልጅ ልጁ ነበር
የመሰለኝ፡፡ ሰውየው ከፋሲል ጋር የቆየ ትውውቅ ስለነበራቸው አረፍ ብሎ ወሬ ጀመረ፡፡ ያማርራል፤ ከፉኛ ያማርራል፡፡ በከንቱ የተበላ ዕድሜውን ከቡና እና ከቅመማ ቅመም ጋር ተደርድሮ ያገኘው ይመስል፣ ዓይኖቹ የሱቋ መደርደሪያ ላይ እየተንከራተቱ ያማርራል፡፡ የተኮሳተረ ጠይም ፊቱ ላይ እርካታ ያጣ ሕይዎቱ ከነሙሉ ሥርዓተ ነጥቡ
ተጽፎ ይነበባል: ከመደርደሪያው ኋላ ከተቀበሩት ድምፅ ማጉያዎች ፣ ኮለል ያላ የጥላሁን
ዘፈን ይፈስሳል፡፡ ሰውዬው ፊቱን ከስክሶና ወዲያ ወዲህ የሚል ልጁ ላይ ዓይኑን ተክሎ
ዘፈኑን እንደ ሙሾ ያደምጣል። በየመሀሉ “ምን የዛሬ ዘፋኞች! እያለ የዘመኑን ዘፋኞት
ያማርራል፤ ድንገት ወደ እኔ ዞሮ፣

አዲስ ህ?” አለኝ::

“ዓመት አለፈኝ

ሥራ ጀመርክ ወይስ ክላስ ምናምን?”

እየተማርኩ ነው

የምትማረውን ተምረህ ወዳገርህ ተመለስ! …ይኼ ቆሻሻ አገር እንደ ሸንኮራ አላምጦ ነው የሚተፋህ
እንዳታገባ፣ እንዳትወልድ፣ወዳገርህ ሰውዬው ኮስተር ብሎ ነው የሚያወራው የምመልሰው ግራ ገቦቶኝ ዝም እንዳልኩ፣ እጅህን ተመልከተው፣ እንደ ሴት እጅ የለሰለሰ ቆንጆ እጅ፡፡ እርግጠኛ ነኝ ከስክርቢቶ ውጭ ምንም ጨብጦ አየውቅም፡፡ እኔም ስመጣ እንዳንተ ነበር እጄ፤ ለማስታወሻ ፎቶው አለኝ…ተመልከት አሁን” አለና እጁን ዘረጋ የተፍረከረከ የደህና አርሶ አደር እጅ ይመስላል፡፡ “የማንንም ሽንት ቤትና ወለል የፈገፈኩበት ነው፡፡ እንኳን ልስላሴው አሻራውም ጠፍቷል፡፡ አሁን
ይሄ አሜሪካ ውስጥ የሚኖር ሰው እጅ ይመስላል?” ብሎ የራሱን እጅ እያገላበጠ
ተመለከተና "ሃሃሃሃ” ብሎ ሳቀ፡፡ ሳቁ ያስፈራል::

ሰውዬው ፋሲል የጋበዘውን ቡና የመጨሻ ጠብታ አጣጥሞ፣ የገዛውን እንጀራ አንጠልጥሎ ልጁን እያቃሰተ አቀፈና ተሰናብቶን ወጣ፡፡ ዓይኔ ሳሩ ላይ መተከሉን አይቶ ፋሲል “የዚያች ልጅ ባልኮ ነው” አለኝ፡፡

የየቷ?”

እነሯ

ትቀልዳለህ?

እውነቴን ነው ማመን አልቻልኩም። አነሯ
👍5
#የእንባ_ቀብድ


#ክፍል_ሁለት


#በአሌክስ_አብርሃም

ከዚያ ቀን በኋላም ብዙ ጊዜ ወደዚህ ሱቅ ስትመጣ፡ ኮስተር እንዳለች የምትፈልገውን ገዝታ ነው የምትሄደው።

ፋሲል መደንገጤን አይቶ እየሳቀ “እስደነበረችህ አይደል?” አለ።

“ምን ሁና ነው እንደዚህ አነር የሆነችው በናትህ?”
“ሚስኪን ልጅ ነች …ባሏ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ታክሲ ምናምን ነበር የሚሠራው፣ በሆን
እክሲደንት' እንዳይሠራ ታግዷል.አሁን እሷ ነች እየሠራች ቤተሰብ የምታስተዳድረው::
አሰበኸዋል? አዲስ አበባ መሬት አይንካኝ የምትል፣ በሕዝብ ጭብጨባና አድናቆት ታጅባ
የኖረች ልጅ፡ እዚህ ሞት የረሳቸው፣ እንደ ድንጋይ የሚከብዱ ባልቴቶችን፣ ስታነሳና ስታስተኛ መዋል ምን ያህል ከባድ እንደሆነ? ከሥራው በላይ የሚጎዳው ግን ከአገር ቤት ይዘውት የሚመጡት አጉል ተስፋ ነው፡፡ መቼም በዕድሜ አባቷ የሚሆን ሰውዬ አፍቅራ አታገባም፡፡ የፈረደበት አሜሪካ ለመምጣት፣ ያገኙትን ያገባሉ በቃ! የማታፈቅረውን ስታገባ፣ ምንጊዜም ውስጥህ ተቀብሮ የሚያሰቃይህ፣ ረግጠኸው የመጣኸ ፍቅር ይኖር ይሆናል፣ ስቃዩ ቀላል አይደለም፡፡ የማታፈቅረውን ሰው አግብታ፣ በምድር ላይ ይኖራል ብላ እንኳ አስባው የማታውቀውን ከባድ ሥራ በቀን አሥር ሰዓት እየሠራች፣ አሜሪካ
አለ የተባለው ነገር ሁሉ አረፉ ሲሆን ህመሙ ቀላል አይደለም፡፡ መፍረድ አይቻልም፡፡በዚያ ላይ ሁለት ልጆች አሏት፡፡ እዚህ አገር ልጅ ማሳደግ ኢትዮጵያ ሁለት ሥራ ከመስራት እኩል ነው … ራሷን እንኳን መጠበቂያ ሰዓት የላትም፡፡ አንዳንዴ ሰላም ሆና ስታወራ ግን እንዴት ጥሩ ልጅ መሰለችህ!”

ከዚህ ሁሉ አገር ሰላም ከሆነ እዛው ቢሰሩስ እንዲህ ብር የማያስታምመው የዕድሜ
ልክሸ ድብርት ተሸክሞ ከመኖር …” አልኩ።

ግው ከአገሩ የሚሰደደው ስላም ስላጣ ብቻ ይመስልሃል? አገሩ በጦርነት እየታመሰ፤
ምድሩን የሚገለባብጥ ቦምብ እየወረደብህ፣ አገሬን የሙጥኝ ልትል ትችላለህ!
ምክንያቱም ከምትወዳቸው ሰዎች ላለመለየት፡፡ የአምባገነን መንግስት እርግጫ ችለህ
እስርና እንግልቱን ተቋቁመህ ከነጠባሳህ ምድርህ ላይ መኖር ትችል ይሆናል. አየህ ሰውን ከአገሩ የሚያሳድደው ጦርነትና አምባገነን ሥርዓት ብቻ አይደለም! ድህነት ያስጨነቀው የእናትህ ፊት… ርሃብና መታረዝ ያጎሳቆላቸው ወንድምና እህቶችህ ፊት የማትጠግበው የእናትህ ፊት ከአንባገነን ስርዓት በላይ አስጨንቆ ወደስደት ሊገፋህ ባይናገሩትም ድረስልን ሲሉህ ሻንጣህን ይዘህ እንድትሰደድ ያስገድድሃል፡፡ አይተህ
ይችላል! ሂድና እርዳኝ የሚል ጎስቋላ ፊቷ ላይ እንባ እየጎረፈ በአንደበቷ 'አትሂድብኝ የምትልህ እናትህ ወደስደት ትገፈሃለች… አብሮ የሚበላ አብሮ የሚጠጣ' የምትለው ጎረቤት በተራ የዓውዳመት ድግስ ፉክክር፣ ለተራ የልብስና ጫማ ውድድር ወደ ስደት ሊገፋህ ይችላል. ህፃናት ወንድም እህቶቸ ጎረቤት የበዓል በግ ሲታረድ አይተው ተስማቸው ብለህ ነፍስህ ወደሚታረድበት ምድር ልትኮበልል ትችላለህ” ፋሲል ክርር ባለ ፊቱ መራር የራሱን ስደት እያስታወሰ ብሶቱን ዘረገፈው፡፡ የሁለተኛ ዓመት የህክምና ተማሪ እያለ ነበር አቋርጦ ወደ አሜሪካ የመጣው፡፡

ልጅቱ ልክ ፋሲል እንዳለው ቆይታ፣ ያውም መንገድ ላይ አውቶብስ ስጠብቅ፣ አዲስ
ቲዮታ ሃይላንደር መኪናዋን ድንገት እፊቴ አቁማ “ግባ ላድርስህ አለችኝ፡፡ ገባሁ።

በቀጥታ ይቅርታ! ባለፈው ትንሽ ባለጌ ሆንኩ፣ ልክ አልነበርኩም፡፡ ሥራ ቦታ አለመግባባት ምናምን ስለነበር እንደ ተበሳጨሁ ፊት ለፊቴ አግኝቼህ ጮኸኩብህ…ሶሪ ፈገግ አለች፤ ፈገግታዋ ያምራል፡፡

“ምንም አይደል?”

አዲስ ነህ መሰል?”

አዎ፣ ብዙ አልቆየሁም::”

እንኳን ደህና መጣህ! አሜሪካ ከተማርክ፣ ከጠነከርክ፣ ቆንጆ አገር ነት አለችኝ፡፡አመስግኜ እቤቴ በር ላይ ወረድኩ፡፡ መኪናውን በሚያስፈራራ ፍጥነት አዙራ እንደእብድ
ተፈተለከች፡፡ እዛ የብዙ ኢትዮጵያዊያን ህልም የሆነ ዘመናዊ መኪና ውስጥ የከሸፈ
ህልም ነበር፡፡

"አብርሽ!"

አቤት ዶክተር!

ሁነኛ፣ ቁመቷ ዘለግ ያለ፣ ቆንጆ፣ ለሚስትነት የምትሆን ልጅ አገር ቤት አታውቅም,,

"ልታገባ አስብክ እንዴ ዶክተር?”

አወቀ ብቸኝነት በቃኝ! ከአገር ቤት አንዲት ቆንጆ፡ጨዋ ሴት አግብቼ እርፍ ብዬ መኖር ነው የምፈልገው ትክ ብዬ አየሁት፡፡ ከሠላሳ ዓመት በላይ አሜሪካ ኗሯል፤ ብዙ ከመቆየቱ ብዛት፡
አሜሪካን ያገኛት እሱ ነው የሚመስለኝ:: ኢሕአፓ ጊዜ አሲምባ ወደሚባል ቦታ ዘምቶ፣ ጓደኞቹ ሲደመሰሉ እሱ ተርፎ አሜሪካ የገባ ሰው ነው። ከዚያ በኋላ ፖለቲካ የሚባል እርግፍ አድርጎ ትቶ፣ ፊቱን ወደ ትምህርት አዞረ: አንዳንዴ ግን እያገረሸት ፖለቲካ ማውራት ሲጀመር ማቆሚያ የለውም ፡፡ እዚያው ፋሲል ሱቅ ጓደኞቹ ጋ ሲመጣ ነው የተዋወቅነው:: ጥሩ ሰው ነው፡፡ ጨዋታ እና ሳቅ ይወዳል፡፡ ስለፈታት ሚስቱ ማውራት
ከጀመረ፣ ጥርስ እያስከድንም፡፡ እሱ እንደሚለው ከሆነ፣ ሚስቱ ቀናተኛ ነበረች፡፡“ተሳስቶ በቲቪ አንዲት ቀጭን ሴት ካደነቅሁ፣ ጧት ተነስታ መሮጥ ትጀምራለች፡፡አንዳንዴ በእልህ ረዥም ርቀት ሩጣ መመለስ ስለማትችል፣ ደውላ ና ወደ ቤት መልሰኝ ትላለች ይላል እየሳቀ፡፡ ሰው እንዴት መመለስ ወደማይችልበት ርቀት ይሮጣል?
ሃሃሃሃሃ

ታዲያ ስለ ፖለቲካ ሲያወራ በብስጭት ወደ እኔ እየተመለከተ “ፖለቲካ ሸርሙጣ ነው !ተመልከት፡ ከንጉሱ ጀምሮ የፖለቲካ እሳት ደሃውን እንጂ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ መሪዎችን አቃጥሎ አያውቅም፡፡ ካላመንክ አንድ በአንድ እያነሳን እንጫዎት… እዚህ አገር ተምሮ እና ተንደላቆ የሚኖረው ብዙኃኑ፣ ግፋ በለው! ሲል የኖረ ነው፡፡ መንግሥቱ ኃይለማርያም ያንን ሁሉ የደሃ ልጅ ማግዶ እሱ ዛሬ የት ነው? 'ዚንባቡዌ ተንደላቆ
ይኖራል፡፡ የኦነግ መሪዎችን ተመልከት፥ ወያኔዎችን ተመልከት ምን ሆኑ? ኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም እርስ በእርስ ጦርነት ወጣቱ ነው የሚማገደው ሚስኪን ወጣቶች በፕሮፖጋዳ ያበደ አለማስተዋል ነው፡፡ ወጣት አልዋጋም ካለ፣ መሪዎች ሲጨባበጡ ነው የምታገኛቸው! እንዲህ ብለው ስንጥር አያነሱም፡፡ ምድረ ደም መጣጭ! ስንት ጓዶቻችን በርሃ ላይ ቀሩ! ስንት ጅኒየሶች! እንኳን ጦርነቱ፣ የፖለቲካ ወሬው ያደንዝሃል፡፡ ከዚህ ከብከተ እንቶፈንቶ ራቅ! ተማር! ተማር! አሁንም ተማር! ማንም መሀይም መተኮስ ይችላል! መግደል ጀብዱ አይደለም፤ ጅብም ሰው ይገድላል! ታይፎይድም፣ ወባም ሰው ይገድላሉ! ዓላማ የሌለው ሞት፣ አገር ሽርፎ ከመሸጥ እኩል
ነው ለምንድነው የምትሞተው?…ለምንድነው ወጣት የሚሞተው? ሊታረድ እንደሚነዳ
በሬ የማይረሳ ተስፋና ጥቅማጥቅም እንደ እርጥብ ሳር እያሸተቱ ወጣቱን ወደ ቄራ
ይወስዱታል፡፡ ወጣቱም ብልጥ የሆነ፣ ከሌላው የተለየ የገባው የረቀቀ፣ የመጠቀ አድርጎ
ራሱን ያያል ፤ሲሰተሙ ነዉ እንደዚያ የሚያደርግህ ከአንተ በላይ አዋቂ የሌለ መስሎ እንዲሰማህ እለፍ ብለህ እጅህን ስትዘረጋ አረፋ ነው ፡፡ ፖለቲካ እንኳን ይዘቱ ቅርፁ ለማንም ገብቶ አያውቅም ፤ፈሳሽ ውሃ ነው ፤ቅርፅ የለውም፡፡ አንተ ውስጥ ሲገባ አንተን ይመስላል፣ እኔ ውስጥ ሲገባ እኔን ሁላችንም ብርጭቆዎች ነን፡፡ በስልጣን ከፍ ያሉ
ያጋጩ ችርስ' የሚባባሉብን” በብስጭት ይናገራል፡፡ ሁልጊዜም እንዲህ ካወራ በኋላ
ሲጋራ ያጨሳል፡፡

ትምህርቱ በትክክል ለምን እንደሆነ እንጃለት፣ ብቻ በሆነ የባዮሎጂ ትምህርት ዶክትሬቱን ይዟል! አግብቶ ሁለት ልጆች ወልዶ፣ አድገው ዩኒቨርስቲ ገብተዋል፡፡ከሚስቱ ጋር የተፋቱት ከአራት ዓመት በፊት ነበር፡፡ ሰውዬው ታሪክ ብዙ ነው፡፡ የሆነ ሆኖ አሁን ግን ዘለግ ያለ የሬሳ ሣጥን በመፈለጊያ
👍1
#የእንባ_ቀብድ


#ክፍል_ሶስት(የመጨረሻ ክፍል)


#በአሌክስ_አብርሃም

ተይዛለች ኢንሪሌሽንሽፕ ይላል ስታተሷ…ወንዱ መች ተኝቶ ያድራል “

ሃሃ…ይችን ይችን ለኛ ተዋት… ዝም ብለህ ጻፍላት…” በየአፋቸው እየተንጫጩ
አበረታቱት !ዶከተር ጻፈላት!

1

2

3ቀን

መለሰች፡፡ መልሶ ጻፈላት

4..

5...

መለሰችለት፡፡ የጻፈውን ጮክ ብሎ ያነብልናል፡፡ የመለሰችውንም እንደዛው :: በግልጽ ፎቶዎችሽን አይቼ ደስ ስላሉኝ መተዋወቅ ፈለኩ፡፡ ብችልና ስልከሽን ብትሰጭኝ ደውዬ ብናወራ ደስ ይለኛል”ብሎ ጻፈላት ስልኳን ትልካለች፣ አትልከም፣ ውርርዱ ቀለጠ፡፡
ጭራሽ ከየዋሌታቸው የመዘዙትን የውርርድ ገንዘብ፣ እኔው ያዥ ሁኜ አረፍኩ፡፡ ትንሽ
ውስጤን ጸጸተኝ! አንዲት ነገር ዓለሙን የማታውቅ፣ በአዲሰ አበባ ብልጣብልጥነት፣
የሕይወትን ማሳለጫ የምታቋርጥ በመሰላት ሚስኪን የአገሬ ቆንጆ ላይ፣ ዕጣ ሲጣጣሉ
ማስጣሉ ሲቀር፣ የውርርድ ገንዘብ ያዥ መሆኔ፣ ውስጤን እንደ አንድ ነገር ሲያቃጥለው
ይሰማኛል፡፡ የወጋሪዎቹን ልብስ ጠባቂ ሆንኩ፡፡

7..8... 9 ስልኳን ላከችለት፡፡

የውርርዱ ገንዘብ ጥሬ ሥጋ ተቆረጠበት፡፡ ውስኪ ወረደበት፡፡

“አብርሃም ና እንጂ …”

“ጥሬ ሥጋ አልበላም

“ማነሽ ጥለሽለት”

“ያዝ ውስኪ

አልጠጣም

"ለስላሳ አምጭለት …”

11..12….13….14 ምን እንዳላት እንጃ…ምን እንዳወሩ እግዜር ይወቅ፣ ዶክተር በደፈናው
“ስለቁም ነገር እያወራን ነው” አለ፡፡ ከዛን ቀን ጀምሮ የዶክተር ጓደኞች ስለልጅቱ ሲያወሩ
ቆጠብ ማለት እንደጀመሩ አስተዋልኩ፡፡

15.. 16….17…18.…19..20 ቀናት አለፉ፡፡ ገርሞኝ የፊደላዊትን የፌስቡክ አካውት በዓይነቁራኛ እከታተላለሁ ትሰጥፈዋለች ይኼን ፎቶ! በምኞት የሰከረ ወንድ ከሚያጎርፈው ላይክ መኻል፣ ዓይኔ ዶክተርን ይፈልጋል፡፡ አገኘዋለሁ! “ላይክ ያደርጋል፡፡ ፈገግታዋ አንዳች የሚነዝር ውበት አለው፡፡ አንድ ወር..ሁለት ወር..ዓይኔ
ነው ወይስ ..እስከምል የፊደላዊት የፌስቡከ ስታተስ' ተቀይሮ አረፈው::
"relationship" የነበረው ወደ "open relationship" ተቀይሯል።

የሽማግሌዎቹ ባሕሪ ቁማር ነበር፡፡

“ተከፈተ! ሃሃሃሃ… አላልኩህም! ገና ሲንግል ትሆናለች” አለ አንዱ ሽማግሌ፡፡ ሌላው ይቀበላል…

"ሲንግል ምን አላት? ገና ድንግል ትሆናላች፡፡ አሜሪካኮ ነው 'ብራዘር …ሃሃሃሃሃ ኡሁ!
ኡሁ ሳል የቀላቀለ የሽማግሌዎች ሳቅ

ፋሲልን “ይችን ልጅ ማስጠንቀቅ አለብኝ” አልኩት፡፡

“አንተ ምን ቤት ነህ? አርፈህ ተቀመጥ!”

“ምንም አይሰማህም? ይች ልጅ ነገ መጥታ እንደ እነሯ የስቃይ ሕይዎት ውስጥ ብትገባስ?
እዚህ እንድ ሐሙስ የቀረው ሽማግሌ ጋር ምንድነው የምትሆነው?”

ለምን ግማሽ ሐሙስ አይቀረውም! …ሲጀመር ልጅቱ ራሷ ምቀኛ ነው የምትልህ፡፡ ወር እንኳን ሳይሞላት፣ በሯን ስትከፍት አይገባህም እንዴ? አዲስ ነህ! እንዲህ ዓይነት ነገር ውስጥ ጣልቃ አትግባ! እነዚህ በተንኮል ጥርሳቸውን የነቀሉ ሽማግሌዎች አንዴ ከጠመዱህ፣ጥሩ አይደለም. ወዲህም ገባያዬን እንዳትዘጋው… ሄደው አንዲት ቃል ቢተነፍሱ ሐበሻ እዚህ ሱቅ ዝር አይልም” ዝም አልኩ፡፡

ፊደላዊት ደወለች! ደወለች… ደወለች ቤቢ…… ደወለች…" ጎበጥ ጎበጥ እያለ ወደ ውጭ ይወጣል ዶከተር፡፡ አይመለስም! ለሰዓታት ስልክ ላይ ነው! ቀናት ሄዱ፣ ወራት ተከተሉ፣ ሁለት፣ ሦስት፣ አራት ወር፡፡

ምናገባኝ ብዬ መከታተሌን ትቸ ከርሜ አንድ ቀን ሳላየው የቆየሁትን የፊደላዊትን አካውንት ተመለከትኩ፡፡ ጭር ብሏል፡፡ የለጠፈቻቸውን ፎቶዎች ሁሉ አንስታቸው ነበር፡፡ ምን መጣ ብዬ መመልከቴን ቀጠልኩ፡፡ ከረዥም ቀናት መዘናጋት በኋላ ስመለስ፣ ስታተሏ ሲንግል” ሆኗል። ደነገጥኩ! ፍቅረኛዋ በአደጋ ሞቶ መሆን አለበት አልኩ ለራሴ፡፡ ዝግመተ ለውጥ እንዲህም ፈጥኖ አያውቅ:: አዎ ዝግመተ ለውጥ፡፡ እንዲህ ነበር ዝንጀሮ መሰል ፍጥረት ቀስ በቀስ ወደ ሰው ተቀየረ ያሉን፡፡ መሆን አለበት:: ቀን ከተለጠው፣ ዝንጀሮም ሰው፣ ሰውም ዝንጀሮ መሆን ሳይችል አይቀርም: ሰው የአገርህ ልጆች በረሃ አቋርጠው ተሰደዱ ሲባል ከንፈር ይመጣል፡፡ እግርማ በረሃን አቋርጦ ካለፈ እሰዬው ነው፡፡ እንዲህ ልቦቻችን ውስጥ ያቆጠቆጠውን ሰውነት፣ ፍቅር፣ እውነት፣
ጨፍጭፈን ዘላለም የማንሻገረውን በረሃ ልባችን ውስጥ ከመፍጠር የባስ፣ ከንፈርየሚያስመጥጥ ምን ሰቆቃ አለ?

አንድ ምሽት ድንገት ዶክተር ደወለና “ወደ አገር ቤት የምትልከው ቀለል ያለ ነገር ካለ፣ ነገ ይዘህ ና፣ መሄዴ ነው አለኝ

“የት?”

አገሬ ነዋ! ጕዳይ አለኝ” አልጠየኩም፣ ጉዳዩ እንዲሁ ይገባኛል!

ቀናት ተቆጠሩ፡፡ ዶክተር ወደ ኢትዮጵያ ከሄደ ከሃያ ቀናት በኋላ የፊደላዊትን የፌስቡክ አካውንት” ተመለከትኩ፡፡

“ሰው ዝም ብሎ እግዚአብሔርን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው ከሚል ጥቅስ ጋር ረዥም ቬሎ ለብሳ ፣ብቻዋን የተነሳችው የሚያምር ፎቶ ተለጥፏል። ቬሎዋን ሳይ ያንን ትኩስ ሰውነት በበረዶ ያጀሎት ዓይነት ሰውነቴ ቅዝቅዝ ሲል ተሰማኝ፡፡ እጅግ በጣም ብዙ የእንኳን ደስ አለሽ አስተያየት ጎርፎላታል።

እግዚአብሔር የቅኖች አምላክ ነው?”

“ይገባሻል የኔ ቆንጆ?”

“የእብርሃም የሣራ....በሳምንቱ ከቤተሰቦቿ ጋር በወርቃማ ጥልፍ ያበደ ጥቁር ካባ ለብሳ፣ በሹሩባዋ ሳይ ወርቃማ አከሊል ደፍታ፣ የማላውቃትን ንግሥተ ሳባ መስላ
(ለምን እንደሆን እንጃ እንደዚያ መሰለችኝ) የተነሳችውን የምላሽ ፎቶ ለጠፈች፡፡ በጣም
ውብ ልጅ ነት፡፡ ያንለታውኑ ከአሥር በላይ የሚሆኑ ተደጋጋሚ የሰርግ ፎቶዎቿን
ለጠፌች፡፡ መንፈስ ያገባች ይመስል አንዱም ላይ የባሏ ፎቶ የለም።

ፋሲል እየሳቀ እና የአንድ ሽማግሌ ፎቶ፣ ባል ብላ ለጥፋ ሐበሻ ለብር ነው ለቪዛ ነው እያለ፣ አዛ ያድርጋት እንዴ? ዋናው ማግባቷ ነው፣ በቃ!” አለቀ፡፡ ከሠርግ የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ፣የእኔ ባሉት ነገር እየታፈረ እንዴት ይኖራል?… እያልኩ ፎቶዎቹን እመለከታለሁ፡፡
ዓይኔ አንዱ ፎቶዋ ላይ አረፈ፡፡ ዓይኖቿ እንባ ሞልተው፣ በሚያማምሩ ጣቶቿ አፏን
እፍና፣ እናትና አባቷ ፊት ለስንብት ቆማለች፡፡ ፋሲልን አሳየሁት፡፡“ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ!” ብሎ እንደሚተርት እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ግን እንደዚያ አላለም፡፡ ቅሬታ ይሁን ሐዘን ባረበበት ፊት፣

የእንባ ቀብድ! ብሎ ዝም አለ፡፡

የዶክተርን አካውት ተመለከትኩ፡፡ ጭር ባለው የፌስቡክ አካውንቱ ላይ፣ አንዲት ዐረፍተ ነገር በጎሉ እንግሊዝኛ ፊደላት ተለጥፋለች፡፡

love never gets old"

ፍቅር አያረጅምህ!


አንብበው ጨርሰዋል አሁን ደሞ ከዚሁ ሳይወጡ #UNMUTE አድርገው ይውጡ አመሰግናለው

ጨረስን

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍41
#የእንባ_ቀብድ


#ክፍል_ሁለት (የመጨረሻ ክፍል)


#በአሌክስ_አብርሃም

እራገማለሁ አዎ! ተራግሜ ነው የምሞተው… ጨረሬን የነበረችበት መልሱ… ሕግ ታውቁ እነደሁ በህግ ፈጣሪን ትፈሩ እንደሆን በፈጠራችሁ ብያለሁ ጨሬን መልሱ አለዛ እራገማለሁ አዎ ተራግሜ ነው የምሞተው… እንዲሁ ተገንዤ የምሄድ እንዳይመስላችሁ ከነዘር ማንዘራችሁ የሚያጠፋ ርግማን ተራግሜ ነው የምሞተው
ጨረሬን የነበረችበት መልሱ!

አነጋገራቸው ሁሉ የሚያስፈራራ ነበር፡፡ ያች ገራገርና ፈግታ የማይለያቸው ሴትዮ ፊታቸው በቁጣ አስፈሪ ሆኖ ነበር፡፡ በዛ ላይ በየመሀሉ “ወዮዯዮ ጨረሬን” ብለው ይጮሃሉ ፡፡ከዘጠኝ ዓመት በፊት ለጥምቀት ሲዘፍኑ ካልሆነ፣ ከዛ ወዲህ እንዲህ ሲጮሁ አይቻቸው አላውቅም፡፡ የሰፈሩ ሰው ግራ ገብቶት እርስ በርስ ይተያያል ። ልክ እኔ ስደርስ ቤት ውስጥ የነበረው ሰው በሙሉ ዙሮ አየኝ፡፡ አስተያየታቸው አንተው ቤት እናድስ ብለህ ያመጣችውን ጣጣ አንተው እንደምታደርግ አድርግ የሚል ነበር ፡፡ ባወጣ ባወርድ የስራሁት ስህተት ኤልገባህ አለኝ፡፡ ምንድነው ጥፋቴ? የአንዲት አልጋ ላይ የዋሉ አቅመ ደካማ ቤት የተሸነቋቆረ አሮጌ ጣራ ሰፈሩን አስተባብሬ ማሳደሴ ማስመረቁ ቢቀር እንዴት ድፍን መንደር ያስረግማል …?

• ነግሪያለሁ እስተነገ ጨረሬን የነበረችበት ካልመለሳችሁ ውርድ ከራሴ ጨረሬን ነው የምፈልግ የእናት ጉርብትና ይቅርብኝ እህል ውሃችሁም ይቅርብኝ አልፈልግም
ርሃብ እንደሆነ ለምጀዋለሁ፥ ምን ያረገኛል …. ጨረሬን ብቻ ቦታዋ መልሱ፡፡ የሰፈር ልጆታ ጋር ተጠቃቅሰን ወጣንና ምን እንደምናደርግ መመካከር ጀመርን፡፡ ነገሩ እንግዳ ስለሆነብን
እንዳንዶቹ ትንሽ አእሞሯቸው ተቃውሶ ይሆናል 'ጠበል' እንውሰዳቸው አሉ አንዳንዶቹ ደግሞ እስቲ ይተኙና ነገ ጧት ምናልባት ይረሱት ይሆናል አሉ። ወደ እማማ ቤት ሰንመለስ ጩኸው ጩኸው እንቅልፍ ሸለብ አድርጓቸው ነበር፡፡

በቀጣዩ ቀን እማማ የወሰዱላቸውን ቁርስ አልበላም አሉ፡፡ እናቴ ሲጨንቃት በምሬት
ማትገባበት የሌለ ልጅ ምናለ አርፈህ ብትቀመጥ? ብላኝ እቤታቸው ሄደች፡፡ፈታቸውን አዞሩባት፡፡ ይሄን ነገር ስሰማ የምወዳቸውን ያህል በእማማ ተበሳጨሁ፡፡ ቀጥ ብዬ እናፂው ግርማቸው ቤት ሄድኩ፤ ከቤት ሊወጣ ሲል ነበር የደረስኩሰት፡፡ ገና ሲያየኝ እየሳቀ ደሞ የማንን ቤት ሥራ ልትለኝ ነው?” አለ።

አረ እባክህ ግራ የገባው ነገር ገጥሞናል”

“ምነው? እቤት ሰላም አይደሉም እንዴ!?”

አይ እቤት አይደለም …” ብዬ የሆነውን ሁሉ ነገርኩት። እንዲሁ ሽንቁሩ መደፈኑ ደስ
እንዳላላቸው ሲያዳምጠኝ ቆይቶ በሳቅ ፍርስ አለ!

ኧረ አያስቅም ግርማቸው! ሴትዮዋኮ እራገማለሁ እያሉ ነው።

እራገማለሁ …. ግርማቸው በጉዴ ወጣሁ !ያንን ሰሌን የመሰለ ጣሪያ ጥቀርሻውን አራግፈን ባደሰን ነው የምትረግመን? እና ምን ይሁን ነው አሁን?” ብሎ በእማማ ተቆጣ።

“ምናልባት ድፍንፍን ሲል ጨልሞባቸው ከሆነ የሆነ ሽንቁር ነገር ብትሰራላቸው "

“ምናሻኝ .ና እንሂድ ወንፊት ነው የማስመስልላት! “ ብሎ ወደ ቤቱ ገባና የአናጺ እቃውን ይዞ ተመለሰ ፡ ሆሆ ሃያ ዓመት አናጺ ሁኜ ስሰራ ጣራዩን ብሳልኝ ብሎ የመጣ ሰው ገጥሞኝም አያውቅ” እያለ ነበር በግርምት እማማ ቤት ስንደርስ ትክ ብለው አዩኝና እብራም አንተ ነህ አሉ ያስዴፈንከው አሉኝ፡ ወቀሳቸው ያስፈራ ነበር፡፡
ድንገት ሂጀ አልጋቸው ስር ተንበረከኩና እጃቸውን በሁለት እጄ ያዝኳቸው መዳፎቻቸው ከፉኛ ይቀዘቅዙ ነበር፡፡ እማማ ይቅርታ አድርጉልኝ እኔ ክረምት ሲመጣ አልጋዎት ላይ ዝናብ እንዳያፈስ አሰቤ ነው አሁን ግርማቸውን ጠርቸዋለሁ መልሶ እንደነበረ ይበሳልዎታል” አልኳቸው እማማ ድንገት እንደትንታ ቡፍ ብለው ሳቁና ትከሻቸው እየተንቀጠቀጠና እያሳሉ ከትከት ብለው ሳቁ፤ በውስጤ ይች ሴትዮ አዕምሯቸው ተናግቷል በቃ ብዬ አሰብኩ፡፡

እይ !አብርሃም ልታስበሳ አናጢ ይዘህ መጣህ…?”

“ምን ላድርግ? ተጨነቅንኮ እማማ!”
ግዴለም ተወው እሱንም ሥራ እታስፈታው …ግዴለም!” አሉ፡፡ ግርማቸው ተሰናብቶ
ከሄደ በኋላ አንዲት ዱካ ስቤ እማማ እልጋ አጠገብ ቁጭ አልኩ ። እማማ በጀርባቸው
እንደተኙ ወደ ኮርኒሱ አፍጥጠው ዝም ብለዋል፡፡ዝምታው ያስፈራ ነበር፡፡ ምን እንደምል፣ ምን እንደማደርግ ግራ ገብቶኝ እጄን ሳፍተለትል ድንገት ከሩቅ የሚሰማ በሚመስል ድምፅ

“ያች ጨረር ብለው ጀመሩ “ያች ቀጭን ጨረር …ጌታ የተቀበረበት መቃብር ውስጥ እንደተከሰቱት መልእክት ለኔ የምስራች ነበርች… መቼስ ያየህ እንሆነ አባቴ ከፉ ነበሩ. የከፉ ከፉ ነጋ ጠባ እናታችንን መቀጥቀጥ ነው ፣መስከር ነው …የትም ከርመው መምጣት ነው እንዲሁ በየመጠጥ ቤቱ ሲጣሉ በሚወዱት የመጠጥ ቤት አምባጓሮ ሞቱ፡፡ በኋላ እናታችን እርሻም ከስቡም ብቻዋን አልሆን ሲላት፣ አንዱን ከወደ ቆላ
የመጣ ባለጌ ሰው ነው ብላ አገባች፡፡ መቼስ ለመከራ ሲፈጥር አይለቅህ … የባሰ ነውረኛ ሁኖ ቁጭ አለ፡፡ ገና አንድ ፍሬ ልጅ ነኝ፣ እንጃ ይችን የዘውዲቱን ልጅ ባክል ነው (የጎረቤታችን ዘውዲቱ ልጅ ገና ዘጠኝ አመቷ ነው) ሰው ዞር ካለ ሳልፍም
ሳገድምም መጎንተል ነው ጭራሽ አንድ ቀን የላሞቹ በረት ስገባ ተከትሎ አነቀኝ የለበስኳትን ጥብቆዬን ሊያወልቅ ሲታገል ኡኡ…! ብዬ ስጮህበት እዛው እበቱ ላይ አንከባሎኝ ወጥቶ ሄደ፡፡ በገዛ ቤቴ ፈራሁ፤ የእናቴን ቀሚስ የሙጢኝ ብዬ በሄደችበት መከተል ሆነ፡፡ እሷ ሰው አግኝታ ሙታ ሂጅ አባትሽ ጋ ተጫዎች” ትለኛለች ..
በኋላ በሰበብ አስባቡ መግረፍ ሆነ ስራው ያመታቱ ያጨካከኑ ደሞ ተወው አታንሳው፡፡ የላሞቹ በረት የገባሁ እንደሆን ተከትሎ ከተፍ ነው፡፡ ወደ ጓሮ ለሽንት ዞር ያልኩ እንደሆነ እንደ ጥላ መከተል ነው፡፡ እንደው ነብሴ ተጨነቀች ፡፡ እናቴን አልነግር እንዲህ እንዳሁኑ ዘመን ልጅን ማን ይሰማል!? ገና ዘልዬ ሳልጠግብ ኑሮዬ ካሁን አሁን
መጣብኝ አነቀኝ ጭንቀት ሆነ፡፡ ገጠር ሽውታውም ኩፍኝም እያጣንም መቸም፣ አሞኝ
ጋደም ያልኩ እንደሆነ እናቴ ወጣ ካለች አትሂጅብኝ ለቅሶ ነው እየተንቀጠቀጥኩ
ተከትያት ደጅ ለደጅ ነው፡፡ ከመድኃኒያለምና ከሷ ሌላ ማን አለኝ? ታናናሽ እህቶቼና የሰፈሩ ውሪ ሁሉ ፈሪ ናት ከናቷ ቀሚስ ሥር አትወጣም” እያሉ መሳቂያ መዘበቻ አረጉኝ፡፡ ሲያመጣው ልክ የለው ይሄን ሆንኩ ሳትል እናታችን በሶስት ቀን በሽታ
ሞተችብን፡፡ ከሞቷም ካሟሟቷም በላይ ነብሴ መግቢያዋ መደበቂያዋ ጨነቃት እንዲህ እንዳይመስልህ የናቴ ልጅ ሐዘንተኛው እንኳን እግሩ ከቤት ሳይወጣ ቋንጣ እንዳየች ድመት ዓይኑ እኔ ላይ ነው፡፡

ሐዘኑም ምኑም ሲያበቃ ጎረቤት ቤት እየሄድኩ ብደበቅ አንጠልጥለው እያመጡ እቤቴ! እንዲቹ እንቅልፍ በዓይኔ ሳይዞር አድርና ቀን ወደእርሻው ሲሄድልኝ ቢመለሰ እንኳ ተኝቸ እንዳያገኘኝ እየፈራሁ… ከዚህ እንደጋሽ አለሙ ቤት የሚሆን ማሳው ውስጥ የተሰራ የእህል መክተቻ ጎተራ አለ… አርጅቶ እህል አይዝም እንዲሁ ቁሟል …ትልቅ ነው ያየህ እንደሆነ፣ ክዳኑን ገርበብ አርጌ እገባና መልሼ ከድኜ እዛው እተኛለሁ፡፡አሥር ጊዜ
እየመጣ ወንድሞቼን የት ሄደች? ሲል ይሰማኛል፣እንጃ ይሉታል፤ እየዛታ ይመለሳል፡፡
ድምጼን አጥፍቸ ዝም! ታዲያ በዛ ጨለማ የጭቃ ጎተራ ውስጥ ታፍኜ ለገመድ ማስገቢያ በተበሳው የጎተራው ሽንቁር በኩል የምትገባ ጨር ነበረች ከሰማይ ጀምሮ የተደበኩስት ጎተራ ድረስ ልትፈልገኝ የመጣች የእናቴ ነብስ ነው የምትመሰለኝ፡፡ ጨረሯ ፊቴ ላይ ስታረፍ እምባዬን የምታብስልኝ፡ የግዜር ጣት … በእጆቼ ስጫወትባት፣ እንደሰው በሹከሹክታ ሳወጋት እውላለሁ፡፡
👍1😁1