አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ዐልቦ
:
:
#በሕይወት_እምሻው
:
#ክፍል_አንድ
:
''ፍ...ቅ...ር...ተ!''

ስሜ በሴት ሲጠራ ሰማሁና እጆቼን አጎንብሼ ክሰል ከምጎለጉልበት ማዳበርያ ሳላወጣ ቀና አልኩ።

ሴት ናት።

ለሰፈራችን ከልክ በላይ የለበሰች፣ ለተቦዳደሰ ኬር መንገዳችን ከሚመጥነው በላይ ሸላይ ጫማ ያደረገች ፣ ቂ...ቅ ያለች ሴት ናት። ከመስታወት የተሰራ የሚመስለው ባለ ረጅም ስፒል ጫማዋ በሚፈቅድላት ፍጥነት ሚዛኖን ላለመሳት ፣ አንዴ መሬቱን፣ አንዴ እኔን፣ አንዴ ሰፈሩን፣ እያየች አጠገቤ ደረሰች።

አላምንም፣ በጭራሽ አላምንም፣ እስከዳር ናት።

የልጅነት ጓደኛዬ እስከዳር፣ ለዐስራ ስምንት ዐመት ያላየኋት አብሮ አደጌ፣ አሜሪካ ከሄደች ወሬዋን ሰምቼ የማላውቀው፣ የአሁኗ ዲያስፖራ የጥንቷ ባልንጀራዬ እስከዳር ናት።

የአሜሪካ ኑሮ እንደ እጅ ስራ ፎቶ ሞላት፣ አቀላት፣ እንጂ ፣ መሰረቱን በሳተ መልኩ አልተለወጠችም።

እስከዳር ናት!

በዚህ አኳኋኗ ልታቅፈኝ አጠገቤ ሰትደርስ እጆቼ ከሰል ሲቦረቡሩ እንደነበር ታወሰኝ ። ልጄ ያበረሸበት '' ቲቢን በጋራ እንከላከል'' የሚለው ቀበሌ የሰጠኝ ካኔተራዬ ትዝ አለኝ ፣ ጭኔ ላይ የተቦተረፈው ቱታዬ ተከሰተልኝ።

በምን አይነት ቀን ተያዝኩ....? በምን ዓይነት አሳቻ ሰአት ላይ ተገኘሁ ? እግዜሩ ምይ በደልኩት ?ዐስራ ስምንት አመት ጠብቆ ጡቶቻችን ቶሎ እንዲወጡልን የውሃ እናት ካጠባችን የልጅነት ጓደኛዬ፣የዛሬ ዲያስፖራ
- ዘናጭ- ቆንጆ - ብራም - ደስተኛ - ያለፈላት ሴት ፊት በዚህ ሁኔታ ያገናኘኛል? ለእንዲህ ያለ ክፉ አጋጣሚ አሳልፎ ይሰጠኛል?

ሐሳቤ ሳያልቅ ደረሰችብኝ።

''ወይኔ...ጥላሸት በጥላሸት..ምንድን ነው የምታቦኪው ፍቅርዬ? ነይ ቀስ ብለሽ እቀፊኝ...'' አለችኝ።

እያፈርኩ መዳፎቼ ቢጫ እና ነጭ ሸሚዞን እንዳይነካ አንጨፍርሬ ለወጉ አቀፍኳት።

''ኦህ ማይ ጉድነስ...! ፍቅርዬ...ደህና ነሽ...? ምንድን ነው እንዲህ የተጎሳቆልሽው...? ኑሮው ነው ? እኔማ አገኝሻለውም አላልኩ፣ ምንድን ነው ይሄ ሁሉ...? ሰፈራችን የት ደረሰ...? ምን ሆኖ ነው ሁሉ ነገር ብትንትኑ የወጣው...? ሰውስ የት ሄደ...?

የጥያቄ ጎርፍ።

''የቱን ልመልስል....? ብዙ ጥያቄ ነው...ደህና ነሽ ግን...? መቼ መጣሽ?'' አልኩ የተቦተረፈውን ቱታ ሱሪዬን በረጅም አሮጌ እና ቆሻሻ ካኔተራዬ ለመሸፈን እየሞከርኩ፣ ጎላ ድስትን በሚጢጢ ድስት ክዳን እንደመክደን እየሆነብኝ።

''ሦስት ሳምንቴ...ዋ....ው! እኔማ...''አለችኝ! በዐይኖቿ እያጠናችኝ። ሰው እንዴት በዐስራ ስምንት ዓመት ውስጥ ዐይኑ በአንድ መስመር እንኳን አይከበብም....? የኔን ዐይኖች ዐሥራ ስምንት መስመሮች ያጅቧቸዋል ።

ካኔተራዬን ይበልጥ ወደ ታች ጎተትኩት።

''ፍቅርዬ ምንድነው እንዲህ ውድቅድቅ ያልሽው? እንዳገባሽ፤ እንደወለድሽ ሰምቼ ነበር....ምንድን ነው ግን...በጣም እኮ ነው የተጎሳቆልሽው፤ ኑሮሽ ጥሩ አይደለም?'' አለች ዙርያ ገባውን እያየች።

ያላረጀ ዐይኗ ማየት ቢችል፤ ኑሩዬ ጥሩ እንዳልሆነ መልስ አትፈልግም ነበር።

ቡና እና ሻይ ፊት ለፊት ፣ ቀልጦ አገር ያቀልጥ በነበረው መንደር ውስጥ፣ በፍርስራሽ በተከበበ እና በግማሹ የፈረሰ ቤት ውስጥ ነው የምኖረው። ቤቱ በልማት ተገምጧል። ነገ ደሞ ስልቅጥ ተደርጎ ይበላል።

ፈገግ ብዬ ዝም አልኳት።

''እንግባ አይባልም ታድያ?.....''ስትለኝ፣ በከሰል ንክር እጄ እየመራሁ ቤት ወደምለው የግድግዳና የጣርያ ድምር ወሰድኳት።ገባን። እፈረው ቤት ገባን።

ሳሎን ብለን የምናጋንናት ሦስት በሦስት ክፍላችን ውስጥ ፣ ከሞቱት አባትና እናቴ ከወረስኳቸው ፎቶዎች - ሁለቱ አሉ። ሌላው ለወሬ አይበቃምና ይቅርባችሁ።

እኔና ባሌ በርሄ... ቤርዬ ከስድስት ወር ልጃችን ጋር፣ በንፅፅር ሳሎኑን ፈረስ በምታሰኝ፤ በቅርጽ ለቱቦ በምትቀርብ ክፍል ውስጥ እንተኛለን። ትልልቆቹ ልጆቻችን ሰምሃልና ዳንአረል ሳሎን ይተቻሉ።

ይኼወ ነው።

''አይ ካንት ብሊቭ! እስከ ዛሬ እዚህ ቤት እንደምትኖሪ...! ልጆች ሆነን እዚ ሳሎን ጋሽ አባይ እጅ በጆሮ ያስሲያዙን ትዝ ይልሻል?''

አለችኝ።

''እህ...አዎ....ዛሬ ደሞ እኛን ኑሮ እጅ በጆሮ አሲዞናል....ያው የቀበሌ ቤት አይደል...አዲስአባ ዛሬ ለእኛ ዓይነቱ ቦታ የላትም...ስለዚህ የቤተሰብ ቀበሌ ቤት ወርሰን እንኖራለን....እንኖር ነበር ...አሁን እንደምታይው ነው...ሰፈሩ ሁሉ ፈርሶ...ሰው ሁላ...''

''አይ ኖው ! ዋር ዞን እኮ ሚመስለው ! ያልደወልኩለት ሰው የለም እኮ..ግን ሁሉም ሰው ከዚህ ሰፈር እንደወጣ ሰማሁ ለምሳሌ ሀውልት ቦሌ ምን የመሰለ ቤት ሠርታለች አሉኝ። ሠመረና ቢኒ፣ ሁሉም አግብተው ገርጂ አካባቢ መሆናቸውን ሰምቼአለሁ። ፈትለ አሜሪካ ናት...ራሄሌ ስዊድን ነው የምትኖረው፤ ሌላ... ሌላ ኦ...ታሪኳ እንኳን ከዛ መቃብር ከሚመስል ቤት ወጥታ፣ ሰሚት ምን የመሰለ ፓላስ ውስጥ መሰለሽ የምትኖረው...''

ወደ ላይ ሊለኝ ፈለገ።

እሷ አንድ ቦታ ላይ ሩጫ ጀምረን ጥለውኝ የሄዱትን ደርበውኝ የሮጡትን፣ የሰፈራችንን ልጆች የዛሬ ኑሮ ስትነግረኝ፣ ወደ ላይ ሊለኝ ፈለገ። ስሜቴ የገባት አልመሰለኝም።ይሄ አሜሪካ የስሜት ማንበብያ በቀዶ ጥገና ያስወጣል እንዴ?

ቀጠለች፣

''...ግን ፍቅር...ምን ሆነሽ ነው ያ ሁሉ ሰው ሲወጣ አንቺ ብቻ እኮ የቀረሽው...ማለቴ ኦልሞስት ትዊንቲ ይርስ..ዛት ኢዝ ኤ ሎንግ ታይም ኖት ቼንጅ...መቼም ህልምሽ ይሄ አይመስለኝም..ምን ሆንሽ...''

''ለስላሳ ነገር ላምጣልሽ?'' አልኳት ፍንጥር ብዬ ተነስቼ።

''ለስላሳ ላምጣልሽ..ምን ይሁንልሽ...?''

''ኦ ኖ...ለስላሳ አልጠጣም....ዳይት ላይ ነኝ... አታይኝም ተዝረጥርጬ...'' አለችኝ። ልብሷ ብቻ ሳይሆን ቆዳዋ እንደጠበባት ያስተዋልኩት ገና አሁን ነው።

''አሜሪካ ያወፍራል መሰለኝ....''

''አዎ ምግቡ...ዝም ብለን በመኪና ስለምንዞር፣ በዚያ ላይ....በነገርሽ ላይ...መኪና ያቆምኩት በፊት ጠጅ ቤት የነበረበት ቦታ ነው። ሴፍ ነው አይደል..? የሆኑ ልጆች እንደ ጉድ ሲያዩኝ ነበር..''

ሣቅ አልኩና ፣ ''ሰላም ነው...ምንም አይሆንም እና ምንም አትበይም...?''ባዶ ቤት አጉል ሰአት መጣሽ...'' አልኳት።

''ኖ ፣ ዛት ኢዝ ሶ ኦኬ ይልቅ...ማታ እንውጣ... አንቺም ፈታ በይ...ቀና ቀና ብሏል ዘፋኙ...'' አለች ብድግ ብላ።

''ማን ነው እሱ ደግሞ?''

''አብርሃም ወልዴ ነው ማነው?...አይ ላቭ ዛት ሶንግ ! ''

''እሺ ፣ ግን...ባሌን ልንገረው መጀመርያ...'' አልኩ እያቅማማው። የማስበው ልለብሰው ስለምችለው ልብስ ነው። የማስበው ስለተንጨበረረው ጸጉሬ ነው። ታኮዋ ስለላላችው፣ ብቸኛዋ ''የውጪ ጫማዬ ነው።

''ኦ ማይ ጋድ! ዋት ኢዝ ዚስ...ናይንቲን ሰርቲስ..? የሱን ፍቃድ መጠየቅ አለብሽ እንዴ..?

''እንዴ አስኩ..ትዳር እኮ ነው..በዛ ላይ ህፃን ልጅ አለኝ..መያዝ አለበት''

''ቢሆንም..ኤኒ ዌይ...አስካሁን አለመጠየቄ ይገርማል..ማነው ስሙ ባልሽ...?

''በርሄ...በርሄ ይባላል።''

ልክ እንዲህ ስላት ፣ እጆቿን እያማታች፣ በሹል ጫማዋ የተቦረቦረ ሊሾ መሬቴን እየደቃች፣ ''ኖ ዌይ...! '' አለች።

''ምነው...አታውቂም ነበር...? ቤሪን እንዳገባሁ...'' አልኳት ፊቷን እየሰለልኩ። የዋሸችኝ መሰለኝ...

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት።
👍3
#ዐልቦ
:
:
#በሕይወት_እምሻው
:
#ክፍል_ሁለት
:
''በጭራሽ...! ታድያ የሰፈር ልጅ...ያውም የእቃ'ቃ ባልሽን አግብተሽ ነዋ እዚህ ተቀብረሽ የቀረሽው....! ወይኔ በጣም ይገርማል..በጣም..''

ሳትጨርስ ልጄ አለቀሰ።

በሕይወቴ ፣ ''እሰይ ልጄ አለቀሰ'' የሚያስብለኝ አጋጣሚ ይፈጠራል ብዬ አስቤም አላውቅ፣ ግን ተፈጠረ። በቆመችበት ትችያት፤ አንስቼ ላባብለው ወደ ''መኝታ ክፍሌ'' ሮጥኩ።

=========-------===========
''ቤቷ ብቻ ስንት ካሬ እንደሆነ ታውቃለህ...? ሁለት መቶ ሃምሳ! ሁለት መቶ ሀምሳ ካሬ! አስበው..... ከዚህ እስከ ደብረወርቅ ህንፃ ማለት ነው.... ቤቷ፣ ከእኛ ቤት እስከ ደብረወረቅ ሕንፃ ነው....! በዛ ላይ እቃዎቿ....ሶፋ ብትል....የእኛን አልጋ ሦስት እጥፍ የሚሆን ሶፋ...ፍላት ስክሪን ቲቪ... የውጭ በር የሚያክል ፍላት ስክሪን ቲቪ አላት.... ምንጣፉ.... እዚያ ሁሌ የማየው..... ሁሌ የምመኘው ሁሌ ግዛልኝ የምልህ ኮምፎርት ትዝ ይልሀል....ያ ሳሪስ ያለው ቤት....እሱን ነው የሚመስለው.... እሱን ነው የሚረግጡት.. እ...''

እየተስገበገብኩ ነው የማወራለት - ለቤሪ። እስኩ ጋር አምሽቼ ምምጣቴ ነው። የአሜሪካው ቤቷን በስልክ ላይ፣ ፎቶና ቪዲዮ አይቼ መምጣቴ ነው። በቢራና በቅናት ተሞልቻለሁ።

''ፍቅር....'' አለኝ ቤሪ፤

''ወዬ...'' ገና አልጨረስኩልህም እኮ.....መኝታ ቤቷ ባርኮን ይሙት....''

''በልጅሽ አትማይ! ከመቼህ ወዲህ ነው በልጃችን የምትምይው?''

''አይደለም እኮ...''

''ኡፍ...በቃኝ ስለሷ ቤት መስማት አንቺም ይበቃሻል....መሽቷል፤ እንተኛ....ልጄንም እንዳትቀሰቀሽው....'' አኮረፈኝ መሰለኝ።

''ለምን ታኮርፈኛለህ?'' አልኩት ወደ መኝታ ስንሄድ እጁን ጎትቼ አስቁሜው። ለብታዬ ወደ ሞቅታ እያደገ መሰለኝ።

''አላኮረፍኩም ፍቅር ግን ሰለቸኝ...እኛ ብዙ የምናስበው ነገር አለ ልጆች አይደለንም ልጆች አሉን....''

''ጥሩ ነገር...ጥሩ ነገር ማውራት ይሰለቻል....? እኛ ባይኖረን ሌላው ያለውን ማውራት ይበዛብናል?'' አልኩት አልጋው ውስጥ ሲገባ ቆሜ እያየሁት።

''ምን ሆነሻል....? ሌላ ሰው ሆንሽብኝ... አራት ቢራና ነገር አጠጥታ ላከችብኝ ሚስቴን...ቀንተሻል...? በድሮ ጓደኛሽ ኑሮ ቀናሽ?''

ቤሪ እንደዲህ ነው። ዙርያ ጥምጥም አያቅም ፣ ነገር ማሰላሰል አያውቅም። መሸፋፈን፣ መጀቧበን፣ በስውር ማውራት አይችልበትም።

በዚህ እወደው ነበር ፣ ደስ ይለኝ ነበር ፣ ዛሬ ግን አበሳጨኝ።

''ብቀና ሀጥያት ነው...?'' አልኩት ድምፄን ከፍ አድርጌ።

''አትጩኺ'' ባርኮን ይነሳል፣ ደግሞ አዎ...ቅናት ሀጥያት ነው''

''ባክህ አትመፃደቅብኝ....ጥሩ ነገር መመኘት ሀጥያት አይደለም...እኔስ ሰው አይደለሁም...? ጥሩ ነገር አያምረኝም...አይገባኝም...? ዘላለም እንዲህ ያለ ጉሮኖ ውስጥ እየኖርኩ፤ እህል ቅጠል የማይል ወጥ ቀቅዬ እንድበላ፣ የልጅ ቅርሻት ስጠርግ እንድኖር የተፈረደብኝ ይመስልሀል..? ደህና ነገር አይወድልኝም...?'' አልኩት። የራሴ የምሬት ድምፅ ይሆን ያለመድኩት ቢራ አፌን ሲመረኝ ይሰማኛል።

ቤሪ ቅስሙ ሲሰበር ዐየሁት፣ በሚታይ ሁኔታ ቅስሙ ስብር አለ።

አንደሚያስብ ሰው ትንሽ ዝም አለና ፣ አለና ፣ ይሄ ሁሉ የታየሽ ዛሬ እሷ ስትመጣ ነው...? የሌለሽን ነገር እስኪ እዪው ብላ ፊትሽ ላይ ስትወረውረው ነው ኑሮሽ ያስጠላሽ? ፍቅር ሰክረሻል...የምትይውን አታቂም እንተኛ...ነገ እናወራለን...'' ብሎ እጁን ዘረጋልኝ። ዝም ብዬ አየሁት።

''ፍቅር ነይ አልጋ ውስጥ ግቢ...የኔ ሰካራም አቅፌ አስተኛሻለሁ... ነይ...'' አለኝ የተዘረጋ እጁን ሳያጥፍ።

አልጋውን አየሁት፣ ሲያስጠላ። ክፍሉን ዐየሁት፣ ሲቀፍ።

የተቦረቦረ ግድግዳችንን፣ የተበሳሳ ጣርያችንን፣ ምንጣፍ አልባ ወለላችንን፣ ቁምሳጥን የለሽ ርካሽ ልብሶቻችንን፣ መስኮት አልባ፣ የሚሰነፍጥና የሚያፍን ሕይወታችንን ዐየሁት። ሁሉንም ተጠየፍኩት።

ባሌን አየሁት፣ ደጅ ድንጋይ ላይ ቁጢጥ ብሎ፣ በግራው ሚጢጢ መስታዎት ይዞ፣ በቀኝ እጁ ራሱ የሚከረክመውን ጢሙንና ፀጉሩን ዐየሁት። በላብ የሚያበራ ጎስቋላ ፊቱን ተመለከትኩት፣ የለበሰውን የወንድሙን ውራጅ ፒጃማ ዐየሁት።

የምወደው ቤሪንም ከቤቱና ከቅራቅንቦዬ ጋር ደምሬ ተጠየፍኩት።

''ነይ እንጂ የኔ ሰካራም...ነይ!'' አለኝና ገብቶ ከነበረበት አልጋ ተነስቶ ወደ እኔ መጣ። ልሄድ ፈለኩ ግን እግሬ አልሄድ አለ ።እግሮቼ ዝናብ ከመታው ግንድ ከበዱኝ።የሞት ሽረቴን ልጠጋው ስሞክርና ''ቤቢ ፊያት'' የምታክል አይጥ በባዶ ቀኝ እግሬ ላይ ስትሄድ አንድ ሆነ። ከተበሳሳው ጣርያችን በላይ ጮኽኩ።

''ምነው ምን ሆንሽ....?'' ብሎ ተስፈንጥሮ አቀፈኝ። ከእቅፉ ለማምለጥ እየሞከርኩ፣ ኤጭ አሁንስ! ወይኔ አሁንስ...ኤጭ...!'' እያልኩ መጮኼን ቀጠልኩ።

''ምንድን ነው ፍቅ...ር...? ምንም አላየሁም እኔ...ሳትተኚ ቅዠት ጀመርሽ እንዴ!'' አለኝ ሊይዘኝ እየሞከረ።

''ከዚህ በላይ ቅዠት አለ? ቅዠት ከዚህ ኑሮ በላይ አለ የማይባንኑበት ቅዠት!''

''ምንድን ነው የምታወሪው...?

''እግሬ ላይ የሄደችውን ግብዲያ አይጥ አላየሁም ለማለት ነው?'' አልኩት የረገበ አልጋችን ላይ ብቻዬን እየወጣሁ። ልጄን ለማባበል ነው የሄድኩት። ልጄ በጩኽቴ ተቀስቅሶ ማልቀስ ጀምሮል።

''እና አይጥ አዲስ ነገር ነው እዚህ ቤት? ስም ሁሉ አውጥተንላቸው የለ...? ማናት የሄደችብሽ ዘርትሁን ወይስ ባንቺ ይሩጉ....? እያለ መሳቅ ጀመረ።

እጄ ውስጥ ያለው ልጄ ባይሆን ወርውሬ ጥርሱን ብሰባብረው ደስ ይለኝ ነበር።

''በርሄ አያስቅም ፣ በዚህ አትሳቅ...አባዬ ይሙት አታናደኝ''
''በርሄ ደሞ ማነው...? ሃ ሃ ሃ...'' አረ ለመሆኑ ከመቼ ወዲህ ነው በአይጦቻችን መሳቅ ያቆምነው?''

'' ከዛሬ ጀምሮ!'' አልኩት የልጄን ለቅሶ ለማስቆም ከግራ ወደቀኝ ከቀኝ ወደ ግራ እየወዘወዝኩት።

''ለምን..?''

''ስለመረረኝ፣ ስለታከተኝ፣ ከአይጥ ጋር መኖር ስለታከተኝ...አንተም ሊመርህ ይገባል። ከአይጥ ጋር መኖር የሚፈልገው ድመት ብቻ ነው።ድመትም ቀለቡ ስለሆኑ ብቻ...እኔ ምኔ ድመት ይመስላል?''

''ወይ ጉዴ...እኮ ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው፣ እንዲህ ባንዴ የተለዋወጥሽው?'' አለ በስጨት ብሎ።

ዝም አልኩት።

ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው፣ አስቤዛ እየተሰፈረላቸው የኖሩት አብሮ አደጎቼ አይጦች እንዲህ ያማረሩኝ ...?ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው፣ የምወደውና እና የሚወደኝ ባሌ እንዲህ ቱግ ቱግ የሚያሰኘኝ.? ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው፣ የማርፍበት ቤት እረፍት የነሳኝ....?

''አስከዳርይን ስታገኚ ሕይወትሽ አስጠላሽ...? እኛ አስጠላንሽ አይደል ፍቅር...? እኛ አስጠላንሽ አይደል ፍቅር.....?'' አለ በተሰበረ ድምፅ ወደ እኔ እየመጣ።

ዝም አልኩት።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍42
#ዐልቦ
:
:
#በሕይወት_እምሻው
:
#ክፍል_ሦስት (የመጨረሻ ክፍል)
:
:
....''ልጄን ስጪኝ...! እንዲህ ሆነሽ ማልቀስ አያቆምም'' አለና ባርኮንን ተቀበለኝ፣ ሳላንገራግር አቀበልኩት። ቤሪ ልጃችንን በለመድነው ወጉ፣ በእሹሩሩ ዜና ለማስተኛት ሲያባብል፣ በለመደው ወጉ ጥሩ አባት ሲሆን እያየሁ እራሴን እንዲህ አልኩት።

'' እውነት ግን ምን ሆኜ ነው?''
===========================

በሱ ቀሚስ ብታስነጥሺ የጡቶችሽ ጫፍ ሳይታዩ አይቀሩም አለኝ ቤሪ፣ ከእስኩ ጋር ላለኝ የማታ ቀጠሮ ስበጃጅ።

ትላናንት ማታ ከተፈጠረው ነገር በኋላ ፣ ለቀልድ የሚሆን ፍቅር ስለቀረው አንጀቴን በላው። ፊቴን ባልለመደው አኳኋኑ ስቀባና ሳጠፋ፣ ሥሰራና ሳፈርስ፣ አዲስ ሰው ስሆን ፤ እያየኝ ለመሳቅ መሞከሩን ሳይ አንጀቴ ተንሰፈሰፈ። ዞር ብዬ አየሁት።

ባርኮንን እያጫወተ ሳይሰርቅ ያየኛል።

''በጣም ጠበበ እንዴ....''? ሊያይወም እሷ ድሮ ገዝታው ሳትለብስ የቀረችውንእኮ ነው የሰጠችኝ
.. አሁንማ ተቀዶም ሌላ ቀሚስ ገብቶበትምአይሆናት'' አልኩት፣ እኔም ሳቅ ለመፍጠር እየሞከርኩ።

''ቢጠብም ያምርቦሻል...የኔ ሚስት እንኳን ሦስት የወለድሽ በልተሽ የምታድሪ አትመስይም እኮ....! አለኝ፣ ልጁን እንደያዘ እየተጠጋኝ።

ማታ እንድያ ጥንብ እርኩሱን አውጥቼው ጠዋት ቅዱስ የሚሆን ይሄ ሰው ከምንድን ነው የተሰራው ..? ለምንስ ነው ለኔ የተሰጠኝ..? ጸጸት ሹክ አለኝ።

''ቂጣምዬ....'' አለኝ ፣ ባርኮንን ባልያዘው እጁ ቂጤን ቸብ እያደረገኝ።

''አንተ እረፋ...''

''ምን አገባሽ በኔ ቂጥ....''

''ሂድ ወደዛ...የኔ ነው...''

በሚጢጢ ቤታችን ውስጥ እንኳን መሮጥ ፈጠን ብዬ ብራመድ ከግድግዳ እጋጫለሁ እንጂ፣ ሮጬ የህንድ ፊልም ነገር ብንሰራ ደስ ይለኝ ነበር። ይሄንን ጊዜ ልሰጠው ፣ ይሄንን ጨዋታ ልሸልመው ብችል፣ ደስ ይለኝ ነበር።

''እረፍ እየጠበቀችኝ ነው አሁን ቶሎ ልሂድ..'' ስለው ፣ ወደ አሮጌው ፎቴ ተመለስና ዝርፍጥ አለ።

''ቤሪ...?'' አልኩት ሊፒስቲኬን መልሼ እያስተካከልኩ። ከንፈሬ ወሰኑ አይታወቅም። አገጬን እየተቀባሁ ተቸገርኩ።

''ወይ ፍቅር..''

''እንዲህ ብዘንጥ ደስ አይልክም ሁሌ...? ማለቴ እንዲህ ቁልትልት ብል..ዝንጥንጥ...?''

''አንችን ደስ ይልሻል ፍቅር...? ያ ሰባራ ድምፁ ተመልሶ መጣ። ''መዘነጥ ማን ይጠላል...? ዞር ብዬ ወገቤን ያዝኩና መለስኩለት።
''ለኔ ጆንያም ብትለብሺ ውብ ነሽ..ደስ ካለሽ ግን ዘንጪ...''

ቮድካ በዚህ መጠን ጠጥቼ አላውቅም። ነገሮች ሁሉ ይበወዝብኝ ጀመር። አስኩ አራት ከንፈር፣ ስድስት ጆሮና አራት ዐይን ያላት ይመስለኝ ጀመር።

የጎደለ ብርጭቆዬን ልትሞለው ስትል በደመነፍስ፣ አንቺ በቤሪ ሞት...በቃኝ...'' አልኩኝ፣ የብርጭቆዬን አፍ በእጄ ለመክደን እየሞከርኩ።እኔ ይህን እያልኩ፣ ክዳን ያደረኩትን እጄ ላይ ቮድካውን ስትቀዳ፣ ነገር አለሙን ትተን እንደ ቂል መሳቅ ጀመርን።

''አንቺ እረፊ....ሰካራም!'' እላታለሁ፣ ትስቃለች።

''ወይኔ ቤሪ ይሙት...ቤሪ ይሙት...በቃኝ አልኩሽ እኮ!'' አልኩኝ እየሳቅኩ።

እጄ ላይ መቅዳቷን ሳታቆም አሁንም ትስቃለች። የሞት ሞቴን ጠርሙሱን ተቀበልኳትና ሶፋው ላይ በጀርባዬ ተጋለልኩ። ስገባ በብርሀን ተሞልቶ የነበረው ክፍል ጨላለመብኝ። አይኖቼን አሸሁ። አሁንም እንደጨላለመብኝ ነው።

''ውሃ...ውሃ ስጪኝ አስክዬ...'' አልኳት በተንጋለልኩበት።

''ምን ሆንሽ....?'' አለች፣ ውፍረቷ እና ጫማ የጨመረው ቁመቷ ተኝተው ሲያዩት ያስፈራል። ቀና ለማለት ሞከርኩ።

''ተቃጠልኩ አስኩ...ቅጥል አደረገኝ...''

''ጎሽ...የሚያቃጥልሽን አቃጠለው ማለት ነው አሁን...ሠርቷል ማለት ነው...!'' አለችና መውደቅን እንደ ፈራ ሰው እየተጠነቀቀች አጠገቤ ቁጭ አለች።

''አረ እኔ በዚህ ሁሉ የሚቃጠል ነገር የለኝም!'' አልኳት፣ አልታዘዝ ያለኝ አንገቴን አዙሬ ላያት እየሞከርኩ።

''እስኪ ማይልኝ...!'' አለችኝ እግሯን ወደ እጆቼ እየላከች፣ ክትክት ብለን ሳቅን።

''ቤሪ ይሙት..!'' አልኳሏት አየሩን በእጄ በመሀላ እየመታው።

''ወይ ይሄ ቤሪ ይሙት..ከእነረ እኮ በባሌ ብምል.'' አለችኝ እየሳቀች፤

''እ...'' አልኳት

''ይሙት ካሉክ ምኞት ነው እንጂ መሀላ አይሆንም''

''ሃ ሃ አስኩ ቀልደኛ ነሽ....''

''ቀልዴን አይደለም..." ክልትው ይበል!''

ሣቋ በዚህ ፍጥነት የት ገባ?

''አንቺ በቮድካ የሚቃጠል የለኝም አልሽ አይደል እኔ ግን አለኝ...ውቅያኖስ የሚያክል ቮድካ አቃጥሎ የማይጨርሰው ነገር ውስጤ አለ ፍቅር...ተቃጠልኩልሽ....''

በድንገት እንደሚያቅፍም እንደሚደግፍም ሰው፣ በተቀመጥኩበት አፍናኝ ታለቅስ ጀመር። ወዝገብ አለብኝ።

''እንዴ...! ምን ሆንሽ ድንገት...?'' አልኳት፣ ሶፋው ላይ ተመቻችቼ ላመቻቻት እየሞከርኩ።ቆዳ ነኝ የሚለው ጥቁር ፕላስቲክ ልብሱ፣ መልሶ መላልሶ ያንሸራትታል።

''ኑሮ አቃጠለኝ...ተቃ...ጠልኩ አልኩሽ በቃ...ጓደኛዬ ሕይወቴ አቃጠለኝ....''

ለቅሶዋ ባሰ፣ ሁሉ ነገር ድንገት ሆነብኝ። እንባዋ ቮድካዬን የመጠጠው ይመስል ስካሬ ሲበን ተሰማኝ። ቀና አልኩ።

''ምን ሆንሽ..?'' ምን ጎደለብሽ....? ሰክረሽ ነው.. የምትቀባጥሪው...? '' ምን አለኝ...? ምንም የለኝም እኮ ጓደኛዬ...ባዶ...ባዶ ነኝ እኮ እኔ... ኔፓ ...ዜ...ሮ...ዜ....ሮ....!''

ለሀጯ እየትዘረበረበ፤ ንፍጧ እየትዘረከረከ፤ እምባዋ እየወረደ፤ ሳያት፣ ቮድካው ሳይሆን እሷ እያወራች መሆኑ ገባኝ።

''ምን የለሽም....? ቤት መኪና... ልጅ.... ባልሽ.. እኔ ምን አለኝ...? ሩዬን እያየሽው ባንቺ ኑሮ ትማረርያለሽ ? ቤቴን አይተሽው ምንም የለኝም ትያለሽ..እኔኮ መንግስጥ የሰጠኝ ኮንደሚኒየም ቤት አድሼ መግባት አቅቶኝ፣ እዛ ጉሮኖ ውስጥ የምኖር ሰው ነኝ...እንቺ ምን የለሽም?'' አልኳት እያቀፍኳትእያቀፍኳት፤ እንደ ህፃን ልጅ እያናፈጥኳት፣ እንደ ባርኮን እያባበልኳት።

'' ባሌ...ቴዲ...ባሌ እኮ ጥሎኝ ከሄደ ዓመት ሞላው ፍቅር....ጥሎኝ ሄደ.....ትቶኝ ሄደ.....''

ደነገጥኩ።

''እንዴ....መቼ....?''

''አመት አልኩሽ አይደል....?''

''አይደለም...እንዴት ማለቴ ነው...? መቼ ሳይሆን እንዴት....? ደንበርበር አልኩች።

እስካሁን ያልነበረኝ እንግዳ መረጃ ነው። ያን ሁሉ የምቾት ክምሯን በፎቶ ላይ፣ በቪዲዬ ስመለከት ፣ ''ባልሽ የታለ?'' ብዬም አልጠየቅኩ፣ እሷም አልነገረችኝ።

''ይሄውልሽ ....'' አለች፣ እየተንፏቀቀች ከተጋደመጅበት የሆቴሏ ሶፋ እየተነሳች ፣ ''ይሄውልሽ...ጢቢጢቢ ሲጫወትብኝ ኖሮ... ጥሎኝ ሄደ...''

''እ...ማለት....ምን ብሎ?''

''ከአንዷ ደጋን እግር ጋር ፍቅር ያዘኝ ብሎ'' ዝም አልኩ።

ለእንዲህ ያለው ነገር ምን ተብሎ ይመስላል? ጓደኛዬ፣ ''ባሌ ጢቢጢቢ ተጫወተብኝ፣ ሌላ ሴት ወዶ ጥሎኝ ሄደ....ተቃጠልኩ!'' ብላ ስትል ፣ ምን ማለት ነው ያለብኝ?

''አይዞሽ አስኩዬ....''

ለማለት የቻልኩት ይህችን ብቻ ነበር።

''አይዞሽ አሰኩዬ...'' ደገምኩት

''አውሬ ነበር፣ የሰው አውሬ።እኔ ጫካ ሆኜለት ችዬው ኖርኩ እንጂ፣ አውሬ ነበር...እላዬ ላይ ሴት ይዞ ይመጣል፣ ልጁን ይክዳል ፣ ሌላውን ተይው ፍቅር....እርጉዝ ሆኜ...እርጉዝ ሆኜ እንኳን ፍቅር..'' ለቅሶ አሸነፋትና መናገር አቆመች።

የምላት ነገር አጣሁ።
👍51👎1