አትሮኖስ
268K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
433 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ከእዳ_ወደ_የምን_እዳ?

#በእውቀቱ_ስዩም

ጋሻው አዳል የተባለ የምወደው የቆየ ዘፋኝ እንዲህ የምትል ዝነኛ ዘፈን አለችው፥

“ማለዳ ማለዳ
ማለዳ መጥተሽ
አይ ! እህህ
ማለዳ መጥተሽ
እኔን ሳታገኝ ትመለሻለሽ"

ዘፈኑን በሰማሁ ቁጥር ጋሻውን እንዲህ እለዋለሁ”  አባ!  በማለዳ የት ሄደህ ነው የማታገኝህ? ውስጥህ የበቀለውን  ችግኝ ስታጠጣ አምሽተህ በዛው መንገድ ላይ የመሰረት ድንጋይ ተንተርሰህ አድረህ ነው?”

   ሳስበው፥ ጋሻው ይህንን ዘፈን የዘፈነው  ለፍቅረኛው ሳይሆን  ለአበዳሪው ይመስለኛል፤ ብድር ስር ምን ትዝ አለኝ !ኢትዮጵያ ብድር መመለስ ከተሳናቸው አገሮች አንዷ ሆና እንደተመደበች  ሰማችሁ አይደል? እምደንቅ እኮ ነው!

ባለፈው ያሜሪካው ያውሮፓ አበዳሪዎች ከኢትዮጵያ ግምጃ ቤት ሀላፊ ጋር ተገናኝተው በጠረጴዛ ዙርያ እና በጠረጴዛ ስር ተወያይተው ነበር;

በቦታው ተገኝቼ እንደታዘብኩት ውይይቱ ይህንን ይመስላል፥

ያሜሪካው - እዳችንን መች ነው ምትከፍሉን?

የኢትዮጵያው- የምን እዳ?🤔

ያውሮፓው- በቢሊዮን  ዶላር የሚገመት ገንዘብ እንዳበደርናችሁ ረሳችሁት እንዴ?

የኢትዮጵያው - ስራ ስለሚበዛ እንረሳለን!

የአሜሪካው - እስቲ መፎጋገሩን ትተን በግልጽ እናውራ፤  በኢኮኖሚ ደረጃ  የት ላይ ነው የምትገኙት?

የኢትዮጵያው፤- ማለት?

የአውሮፓው ፤-  እርሙን የበላ ድሀ ናችሁ ? ወይስ ቀን የሚወጣለት ድሀ ናችሁ?

የኢትዮጵያው - የሰው ሀብት አለን ! መቶ አምሳ ሚሊዮን ደርሰናል ! ጠባይ ካላችሁ  አምሳ ሚሊዮኑን  ህዝብ ልንለግሳችሁ እንችላለን !

የአሜሪካው - እያወራን ያለነው ስለገንዘብ ነው !

የኢትዮጵያው - እንዳታባክኑት እኛው ጋ ይቀመጥላችሁ ብለን ነው እንጂ ገንዘቡም ቢሆን አለ!

የአውሮፓው- ሌላው ቢቀር ወለዱን  ክፈሉን

የኢትዮጵያው-   ለጊዜው አይርወለድ እንጂ ወለድ አላዘጋጅንም!
 
የአሜሪካው-- ሌላ ምን መፍትሄ ይኖራል?

የኢትዮጵያው-- ጥቂት የእፎይታ ጊዜ ስጡን!

ያውሮፓው --ምን ያህል ጊዜ?

የኢትዮጵያው- ትንሽ አምሳ አመት ብትታገሱን

ያውሮፓው- በአምሳ አመት ጊዜ ውስጥ ብድሩን የምትከፍሉበት የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ትደርሳላችሁ?

የኢትዮጵያው--አይ እናንተ ብድሩን የማትፈልጉበት ደረጃ ትደርሳላችሁ’

የአሜሪካው -- ከዛሬ ጀምሮ ከዛምቢያ እና ከጋና ቀጥሎ መበደር ከማይችሉ አገሮች ጎን ተመድባችሁዋል!

የኢትዮጵያው-  ይህንን ጨካኝ  ርምጃ ዝም ብለን አናየውም 🙁🙁

የአውሮፓው- ምን ልታደርጉ ትችላላችሁ?

የኢትዮጵያው---ብድር የተነፈጉ አገሮች ማህበር መስርተን እንታገላለን  !

የአሜሪካው- እናያለን !

እዚህ ላይ፥ የኢትዮጵያው በንዴት ተሰናብቶ ከሄደ በሁዋላ እንደገና ተመልሶ መጣና ፥
“አንድ የመጨረሻ  ጥያቄ ነበረኝ ! “ አለ፤

ሁለቱ ሀያላን - ምንድነው?

የኢትዮጵያው፤-

“ዛምቢያን አስይዘን መበደር አንችልም?”



ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት  እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ማታ #ትንግርት #ክፍል 8 ይኖራል

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
ከዚህ በላይ ሊያናግረኝ
አልፈቀደም፡፡ ለሻዩ ወደ ኩሽና መንገድ ጀመርኩና መለስ ብዬ ዐየሁት

“ኤሊ...”

“እ...?” (ከልቡ ሳይሆን)

“ልቤን ለሴት ከምሰጥ፤ ለድመት ብሰጥ ይሻለኛል ነው ያልከኝ አይደል..?”

“እ...አዎ...”

የኩሽና መንገዴን ቀጠልኩ፡፡ ሻይ ጀበናውን በውሃ ሞልቼ ምድጃው
ላይ ጣድኩ፡፡ ጦስኙን አዘጋጀሁ፡፡

ኤልዬ... የምወደው ልጅ እንዲወደኝ....

የእሱን ልብ እንዳገኝ ሰውነቱ ቀርቶብኝ፤ ምነው ለአንዲት ቀን ድመት ቢያደርገኝ?
የማፈቅረው ልጅ መልሶ እንዲያፈቅረኝ፤ ምነው ለአንድ ሌት

ሚያው ባስባለኝ?

ሚያው....

ሚያው....

            💫አለቀ💫

ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት  እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ማታ #ትንግርት #ክፍል 8 ይኖራል

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት  እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ማታ #ትንግርት #ክፍል 8 ይኖራል

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
🍁🍁ዲያሪው 📝

ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_8


ህዳር 5 ቀን 1978 ዓ.ም

"አማረ ከተለየኝ በኋላ በአስተማሪነት ሥራ ተሰማርቶ አሳይታ መመደቡን ፃፈልኝ፡፡ በየጊዜው ደብዳቤና ገንዘብ ይልክልኝ ነበር፡፡ እኔም ቶሎ ትምህርቴን ጨርሼ ከእሱ ጋር የምንጋባበትንና ውለታውን የምመልስበት ብሎም የአማረ ባለቤት የምባልበትን ቀን ናፈቅሁ፡፡ ግን ነገሮች ሁሉ ባሰብኩት መልኩ ሊፋጠኑልኝ አልቻለም፡፡ ሌላው ትልቁ ችግሬ የእሱ ደብዳቤ በደረሰኝ ቁጥር መረበሽ፣ ማሰብና መጨነቅ ስለማዘወትርና በዚያው ሰሞንም

ማጥናት ስለሚያዳግተኝ በትምህርት ውጤቴ ላይ የመቀነስ አዝማሚያ መታየት ጀመረ፡፡ አማረ ደግሞ በተቃራኒው ከእኔ ዘንድ ደብዳቤ ቶሎ ቶሎ የሚጠብቅና ቶሎ ቶሎም የሚፅፍ በመሆኑ የማደርገው ጠፋኝ፡ አማራጭ ስላልነበረኝ እሱ በተከታታይ ቢፅፍም እኔ ግን አለፍ አልፍ እያልኩ መጻፍ ጀመርኩ፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ ተቀይሞ ይሁን ወይም በሌላ ምክንያት ባይገባኝም ቀስ በቀስ መጻፉንም ሆነ ለምጽፋቸውም ደብዳቤዎች መልስ መስጠቱን ካቆመ ከአያሌ ጊዜ በኋላ ዛሬ ለመጨረሻም አንድ ደብዳቤ ላከልኝ፡፡ ይህ ደብዳቤ የማልጠብቀውና ላምነው የማልችል፣ ተስፋዬን በሙሉ አጨልሞ ያሟጠጠና የሕይወቴንም አቅጣጫ የለወጠ ነበር፡፡ እንዲህ ይላል፤ ይድረስ ለውድ ጓደኛዬ ለአልማዝ አስፋው፡፡ በመጀመሪያ እንደምን ሰንብተሻል፡፡ ዛሬ የምጽፍልሽን ይህን የመጨረሻ ደብዳቤ ስታነቢ በመጠኑም ቢሆን ማዘንሽ እንደማይቀር እርግጠኛ ነኝ :: ነገር ግን የመጨረሻው ሐዘን ይበልጥ ሊከፋ ስለሚችል ከአሁኑ መወሰን ስለነበረብኝ መወሰኔ አልቀረም:: እንደምታውቂው አብረን ያሳለፍናቸው የፍቅር ቀናት ለእኔም ሆነ ለአንቺ እስከመቼም ቢሆን የሚረሱ አይመስለኝም:: ግን ይኸ ትዝታ ፍጹም መቆም እንዳለበት ለእኔ ይሰማኛል፡፡ ምክንያቱም እኔና አንቺ ዛሬ በተለያየ ደረጃ ላይ የምንገኝና ምናልባት ወደፊት ትዳር ብንመሰርት እንኳን በምንም ዓይነት ሁኔታ የማንመጣጠን ሆኖ ተሰምቶኛል፡፡ አንቺ ምንጊዜም ብትማሪ ጥሩ ደረጃ ላይ መድረስ የምትችዪ፣ እኔ ግን ትምህርት አልሆንና አልሳካልህ ብሎኝ ከከተማ ርቄ የምኖር ምስኪን አስተማሪ ነኝ:: የእኔና የአንቺ መጋባት አንቺን ወደ አዘቅት ጎትቶ ማውረድ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ሊሆን እንደማይችል ከተሰማኝ ብዙ ጊዜ ሆኗል:: ስለዚህ ጉዳዩን አውጥቼና አውርጄ፣ ከህሊናዬም ጋር መክሬ የራሴን ውሳኔ ወስኛለሁ፡፡ ውሳኔዬንም በምድር ላይ ሊያስቀይረኝ የሚችል ምንም ኃይል ስለማይኖር በዚህ በኩል እንዳትደክሚ እመክርሻለሁ፡፡ ውሳኔዬም ሌላ ሳይሆን ለእኔ የምትሆነኝን በደረጃዋ ከእኔ ጋር የምትመጥን ሴት አግኝቼ ማግባት ነው:: በዚህ ውሳኔ ለጊዜው ላስከፋሽ እንደምችል ይገባኛል፡፡ ወደፊት ግን ጥቅሙን ውሎ ሲያድርና ይህንን ውሳኔዬን በሚገባ ስትገነዘቢው ትረጂያለሽ ብዬ በማሰቤ በእርምጃዬ አልተፀፀትኩም:: ሁልጊዜ ላንቺ ጥሩ ነገር በማሰቤ ምክንያት ሳይታወቀኝ አሳዝኜሽ ቢሆን እንኳ እባክሽን አትቀየሚኝ፡ ከእንግዲህ ወዲያ ምንም ዓይነት ደብዳቤ ባትጽፊልኝ ደስ ይለኛል፡፡ የእኔን ሰላማዊ ሕይወት ከመረበሽ በስተቀር የሚለውጠው ነገር የለምና፡፡ ስለዚህ ይቺ ደብዳቤዬ ከደረሰሽ ዕለት አንስቶ አንቺም የሚመጥንሽን ሰው በጊዜ ብትፈልጊ የተሻለ ነው፡፡ ግን በሕይወት እስካለሁ ድረስ ምን ጊዜም ቢሆን አልረሳሽም፡፡ ላንቺ ያለኝ ፍቅር እና ልባዊ አክብሮት ሁሉ እንዳለ እንዲቆይ መቼም ቢሆን የማይለወጠውን ሃሳቤን ለማስለወጥ አትሞክሪ።

በተረፈ ሁሌም የማይለይሽ አምላክ ከአንቺ ጋር ይሁን፡፡ ውድ ጓደኛሽ አማረ አስረስ። በዚህ ደብዳቤ ያልጠበቅሁትና ያልገመትኩት ነገር ተከሰተ:: የሕይወቴ መስመር አቅጣጫ በአንዴ ዞረ:: የሕይወቴ ውጥን በአጭሩ ተቀጨ:: በዚያኛ ቅጽበት ውስጥ ድካሜ ሁሉ ከንቱ ሆኖ ሁለመናዬን ጨለማ ወረረው ህሊናዬ ባዶ ሆነ፡፡ አማረ ፍቅረኛዬ ብቻ ሳይሆን መላ ሕይወቴ ነበር። ለአንዲት ቀን እንካን ከእሱ ጋር እለያይ ይሆናል ብዬ አስቤ ለማላውቀው ለእኔ ለምስኪኗ ይህ ዱብ ዕዳ ልሽከመው ከምችለው በላይ መራራና ከባድ ነበር። ግን ለምን? እኔ ለአማረ የነበረኝ ፍቅር ቅንጣት ታህል አልቀነሰም:: የእኔ በትምህርት ከሱ መብለጥና የተሻለ ደሞዝ ማግኘት ለእኔ አንዳች ትርጉም አልነበረውም:: ለእኔ ከሁሉምና ከማንኛውም ነገር በላይ አማረ ይበልጥብኛል፡፡ ግን አማረ ከዚህ በኋላ ለእኔ ማማሩ አከተመ:: ተስፋዬን አጨለመው፣ ልቤን ሰበረው:: እኔ መቼ ትምህርቴን ጨርሼ እንጋባ ይሆን እያልኩ ቀኑ አልደርስ ብሎኝ በጉጉት የቀረኝን ቀንና ሰዓት በየዕለቱ ስደምርና ስቀንስ፣ እሱ ግን የእኔን መማር ለመለያያ እንደምክንያት አቅርቦ ሊከዳኝ ወሰነ፡፡ ሕይወት ከዚህ በኋላ ለእኔ ትርጉም እንደሌላት ወዲያውኑ ገባኝ:: በዚች የምትጓዝበት አቅጣጫና ጉዞዋ በተተለመው መንገድ በማትጓዝ የመከራ ዓለም ውስጥ ገብቶ ከመሰቃየት በአጭሩ መገላገልን መረጥኩ:: በመከራ ተጀምራ አሁንም በመከራ ውስጥ በመጓዝ ላይ ያለችውን ሕይወቴን እኔም በራሴ ውሳኔ ልገታት ወሰንኩ፡፡ ከእንግዲህ የቀረኝ ነገር ቢኖር ከሞት ዓይነቶች መካከል የተሻለውን ፈጣን አሟሟት መምረጥ ብቻ ነበር :። ሞት እግዚአብሄር ለሰው ልጆች የሰጠው ክቡር ስጦታ መሆኑን የተረዳሁትም ገና ዛሬ ነበር። ሞት ባይኖር ኖሮ ግን እንዲህ ዓይነቱን አሰልቺ ስቃይ ይዞ መቆየት እንዴት ይቻል ነበር? የሳለፍኩትን መራራ ሕይወትና ትዝታ ወደፊት ማስታወስም ሆነ መድገም አልሻም፡፡ ዙሪያው ገደል የሆነብኝ የፍቅር ሕይወት እልባት ማግኘት አለበት፡፡ ከዚህ በኋላ ውሳኔዬን ተግባራዊ ለማድረግ ጊዜ አልፈጀሁም። ፀረ ተባይ መድኃኒት ጠጥቼ ራሴን ለማጥፋት ወደ ቤተ-ሙከራ አመራሁ:: ወደ ውስጥ ስገባ ግን ክፍሉ በሰው ተጨናንቋል:: ሰው እንዳያየኝ ተጠንቅቄ እና በዝግታ አረማመድ ወደ መደርደሪያው አመራሁ:: “መርዘኛ” የሚል ጽሑፍ ከተለጠፈባቸው _ ጠርሙሶች ውስጥ አንዱን መርጬ ኮት ኪሴ ውስጥ ከተትኩ። ለሙከራ ሥራ የመጣሁ ስለምመስልና ሁሉም በየራሱ ሥራ ላይ ተጠምዶ ስለነበር አንድም ያየኝ ሰው አልነበረም:: ነገር ግን እየተጣደፍኩ ስወጣ ዶ/ር አድማሱን በራፍ ላይ አገኝሁት:: ላገኘው በማልፈልግበት ሰዓት

ስላገኘሁት በጣም ተናደድኩ፡፡ እሱ ግን ትናንት የሰጠኝን የቤት ሥራን ሠርቼ እንደሆን ጠየቀኝ:: እኔ ግን ለምን አገኘኝ በሚል ሁኔታ ተናድጄ ስለነበር ምንም መልስ አልሰጠሁትም:: “አልማዝ ምን ሆነሻል? ደህናም አይደለሽ እንዴ?" አለኝ። ደህና መሆኔን ብነግረውም ሊቀበለኝ አልፈለገም። “ዶክተርነቱ በኢንጂነሪንግ ሳይሆን የጤና ዶክተር የሆነ እስኪመስለኝ ድረስ የለም ታመሻል ሀኪም ቤት መሄድ አለብሽ" እያለ ይጨቀጭቀኝ ጀመር፡፡ :: ይህ ሀሳቡ ተቀባይነት ሲያጣ እቤት አብሬው ሄጄ አረፍ እንድል ጠየቀኝ። አለመፈለጌን ብነግረውም ሊቀበለኝ ባለመፈለጉና ጭቅጭቁ ስለበዛብኝ ቢያንስ በመጨረሻዋ ቀኔ ላስቀይመው ስላልፈለግሁና ለመሞትም ቢሆን የሱ ቤት የተሻለ መሆኑን አስቤ ተከትዬው ወደ ቤቱ አመራሁ:: ዶ/ር አድማሱ ቤት እንደገባሁ ኮቴን አውልቆ ወንበር ላይ አስቀመጠልኝ፡፡ አልጋ ላይ ጋደም እንድል ነገረኝና ጋቢ ከቁምሳጥን አውጥቶ አለበሰኝ:: ሳልወድ በግድ ጋደም አልኩ:: የታመምኩ ስለመሰለው ማስታመሙ ነው መሰለኝ እሱም ወንበር አምጥቶ አጠገቤ ተቀመጠና መጽሐፍ ማንበቡን ተያያዘው:: ምስኪን በመሆኑ አዘንኩለት:: ዛሬ ግን ሬሳዬ ከሱ ቤት ይወጣል፣ ነገም ፖሊሶች መጥተው ሊወስዱት ይችላሉ፡፡ ስለዚህ እንዳይጉላላ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለብኝ ወሰንኩ፡፡ ውሀ እንዲያመጣልኝ ነግሬው