አትሮኖስ
280K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
460 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰባ_ስምንት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ጆይስ ወረደችና ሚስተር ካርላይልን ራት ከሚበላበት አስነሥታ ይዛው መጣች

“ ማዳም ቬን ባሰባት እንዴ . . ኮርኒሊያ ? እኔን ፌለገችኝ ?

“ አዎን ልታነጋግርህ ትፈልጋለች ”

ሚስ ካርላይል እየተናገረች በሩን ከፈተችው "መጀመሪያ እሷ እንድትግባ በጁ አመለከታት “ የለም” አለችው “ ብቻህን ገብተህ ብታያት ይሻላል ”

ሊገባ ሲል ጆይስ ክንዱን ያዘችው “ ጌታዬ ተዘጋጅተው ይግቡ“ እማማ
ለምን አይነግሯቸውም ?”

ሁለቱንም ትክ ብሎ አያቸው ሁኔታቸውን ይኸ ነው ብሎ ለመናገር አልቻለም
አንግዳ ነገር ሆነበት " እንዲያውም ወደ ዕብደቱ ወሰድ ያደረጋቸው መሰለው
ፊቷ ምንም ቢሆን ተለውጦ የማያውቀው ኮርኒሊያ እንኳን ምንም ኮስተር ብላ
ብትቆምም ከንፈሮቿ ሲንቀጠቀጡ መቁጣጠር አልቻለችም " ሚስተር ካርላይል ግንባሩን ቋጥሮ ሲገባ እነሱ በሩን ዘጉበት "

በቀጥታ ወደ በሽተኛይቱ አልጋ ቀስ ብሎ ተጠጋና “በጣም አዝናለሁ ማዳም ቬን...” ብሎ የጀመረውን ሳይጨርስ ቀሪዎቹ ቃላት ምላሱ ላይ ተንከባለሉ"
ሊወጡ አልቻሉም . እሱም እንደ ጆይስ የሳቤላን መንፈስ ያየ መሰለው
ከአልጋው ትንሽ አፈገፈገ ወርዶ አንገቷ ላይ የተቆለለው ጸጉሯ የሚያምሩትና የኀዘን ዳመና የጣለባቸው 0ይኖቿ ሳይቀሩ የሳቤላ ቬንን መልክ ቁልጭ አድርገው አሳዩት

አርኪባልድ ! ” አለችው "

የሚንቀጠቀጠው እጅዋን ዘረጋችና እጁን ያዘችው " ትክ ብሎ አያት» ከሕልም የነቃ ይመስል ዙሪያውንም አስተውሎ አየ "

“ነፍሴ ያንተን ይቅርታ ሳታገኝ ከሥጋዋ መለየት አልቻለችም " አለችው
የሰራችውን በደል ስታስብ ዐይኖቿን ስብር አድርጋ “ ተው ' ፊትህን አታዙርብኝ " ለአንዳፍታ ታገሠኝ ይቅር ብየሻለሁ ብቻ በለኝና በሰላም ልሙት

“ ሳቤላ ! አንቺ ነሽ? አንቺ ነሽ ? ማዳም ቬን የነበርሽው ? " አለ የሚናገረውን አላወቀውም።
ይቅር በለኝ ማረኝ... አርኪባልድ | አልሞትኩም » የደረሰብኝ አደጋ ለወጠኝ እንጂ አልገደለኝም » ነገር ግን ማንም አላወቀም ስለዚህ ማዳም ቬን
ተብዬ ወደዚሁ መጣሁ " ተነጥዬና ርቄ መኖር አልቻልኩም » ማረኝ ... አር
ኪባልድ ማረኝ " "

የሚናገረው የሚያደርገው ቅጡ ጠፋው " አምሮው ጠሮ ነፋስ እንደ ገባበት
ተበጠበጠ ግራ ገብቶት ዝም ብሎ እንደ ቆመ ነገሯን ቀጠለች "

“ ከአንተና ከልጆቼ ተነጥዬ መኖር አልቻልኩም " ያንተ ናፍቆት ሊገድለኝ ሆነ ” አለችው " አነጋግሯ የትኩሳት ቅዠት ይመስል ነበር “ “ እንደዚያ አሳብዶኝ ካን† ከተለየሁ ወዲህ የአንዲት ቅጽበት እንኳን ሰላም አግኝቸ አላውቅም .
መላው ባይጠፋኝ ኖሮ ወዲያው ተመልሸ እመጣ ነበር ከቤት ከወጣሁ አንድ
ሰዓት እንኳን ሳልቆይ ጸጸት ያዘኝ እያደር እየከበደኝ እየጠናብኝ ሔደ ምን እንዳ
ስመሰለኝ ታየዋለህ ? እየው ተመልከተው " ብላ የሸበተው ጸጉሯን የመነመ
ነውን እጁዋን አሳየችው » አንተው ማረኝ ይቅር በለኝ !ጥፋቴ በጣም ከባድ ነው ! የተቀበልኩት ቅጣት ግን ይበልጣል " ለብዙ ዘመን ከባድ መከራ ከባድ
ሥቃይ ተቀብያለሁ " ሕይወቴ ረጅም ዘመን የፈጀ የጻዕረ ሞት ሕይወት ነበር ”

“ እንዲያው ሲጀመር ምን ሆነሽ ሔድሽ?”

“ ለምን እንዶ ሔድኩ አላወቅህም? ”

“ የለም አላውቅም " እስከ ዛሬ ምስጢር እንደ ሆነብኝ ነው ”

“ አንተን ከመውደዴ የተነሣ ነበር የሔድኩት " ከንፈሮቹን በንቀት ቀስቀስ አደረጋቸው " በጣር ላይ ሆናም የምትቀልድበት መሰለው

“ ተው እንደሱ አድርገህ አትየኝ " አቅም የለኝም " ያለው የሌለው ጉልበቴ አልቋል " ከሰውነት ወጥቻለሁ " ዐይንህ ያያል " የምነግርህ እውነት መሆኑን ተረዳልኝ ነገሬ ግልጽ ካልሆነ እንጃ በጣም እወድሀ ስለ ነበር ጠረጠርኩህ፤ እኔን አለሁልሽ ብለህ እያታለልክ ፍቅርህን ለሌላ የሰጠህብኝ መስለኝ » ስለዚህ በጥርጣሬ ቅናት እንደ ቆሰልኩ ከዚያ ክፉ ሰው ወጥመድ ገባሁ " እንድበቀልህ በጆሮዬ ሹክ ይለኝ ነበር ”

“እኔ ግን አንቺን በሐሳብም፡ በቃልም በተግባርም ለማታለል አልሞከርኩም"
ያንጊዜም ታውቂኝ ነበር " ከዚያ ወዲህም ሳታውቂኝ አልቀረሽም

“አርኪባልድ ... አብጀ ነበር " በዕብደት እንጂ በጤንነት እንደዚያ ያለውን ሥራ አልሠራውም ነበር " ስለዚህ እርሳው ' ይቅር በለኝ ”

“ መርሳት አልችልም " ይቅር ካልኩሽ ግን ቆይቻለሁ "

“ ከዚያ ሌሊት ወዲህ ያለፈውን የኀዘንና የብስጭት ጊዜ ለመርሳት ሞክር” አለችው ዕንባዋ በሁለት ጉንጮቿ እየወረደ " ሥጋው አልቆ አጥንቱ ብቻ ቀርቶ በትኩሳት የሚቃጠለውን ክንዷን ወደሱ ዘርግታ : “ በሱ ፈንታ የፍቅር ጊዜአችንን ላለመርሳት ሞክር "
አኔን በመጀመሪያ ወደ ዐወቅህበት ዘመን መልሰው " ከዚህ ቤት ሳቤላ ሼን አየተባልኩ ካባቴ ጋር ደስተኛ ልጅ የነበርኩበትን ዘመን አስታውስ ያኔ ለኔ ባትገልጽልኝም እንዴት ልትወደኝ እንደቻልክ አስታውስ" አባቴ በሞተ ጊዜ የተቸገርክልኝን በዚያች ምናምን ባልነበረኝ ሰዓት አንድ መቶ ፓውንድ የሰጠኸኝን ወደ ካሰል ማርሊንግ የመጣህ ዜ
ሐሳብህን ላንዳፍታ
ላገባህ ቃል የገባሁበትን ለመጀመሪያ ጊዜ ከንፌሬን የሳምከኝን ከተጋባን በኋላ የነበረን ደስታ ትዝ ይልሃል ? አብረን ያሳለፍናቸውን የፍቅር ዘመናት ታስታውሳቸዋለህ ? ሉሲ ስትወለድ ከሞት አፋፍ በመትረፌ የተሰማህን
ሁሉ ትዝ ይልሃል ? ”

“ ታዲያ አሁን እኔን ይህን አጠፋህ የምትይኝ አለሽ ” አላት አሳዛኝ እጅዋን
በእጁ ይዞ ።

አንተን ? በኔ ቀርቶ በአምላክ ዘንድም ጥፋት አይገኝብህም " ከልብህ
ወደከኝ ነበር " ለደኅንነቴ ባያሌ» ስትጨነቅልኝ ነበር » አንተ ደግሞ ምንህ ይወቀሳል? ምን አንደነበርክና ዛሬም እንዴት ያለህ ሰው እንደሆንክ ሳስበውና ከመለስኩልህ ውለታ ጋር ሳነጻጽረው በኃፍረትና በጸጸት መሬት ተከፍታ ብትውጠኝ እወድ ነበር ለራሴም ጥፋት የሚያበቃኝን ቅጣት ተቀብያለሁ ባንተና
በልጆችህ ያመጣሁባችሁን ውርደት ግን ማስለቀቅ አልችልም ”

“ የኔን ፈተና ግን አስበው " አለችው ድምጿ እየደከመ " እሱም እየራቀ የሔደውን ድምፅ ለመስማት ጆሮውን ጠጋ ለማድረግ ተገደደ ። “ በዚህ ቤት ውስጥ ከሚስትህ ጋር ተቀምጬ ምን ያህል እንደምታፈቅራት እኔን ትዳብስኝ እንደ ነበረው ስትዳብሳት እያየሁ ' በቅናት ስንገገብ ኖርኩ አሳልፌ ለሌላ ከስጠሁህ በኋላ ያፈቀርኩህን ያህል አፍቅሬህ አላውቅም ነበር " እስቲ ይታይህ' ዊልያም ልጄ ጉልበቱ እየመነመነ ሰውነቱ እያለቀ ሲሔድ እያየሁ ነፍሱ በምትወጣበት
ሰዓት ካንተ ጋር ብቻችንን ሆነን ስንጠብቀው እናቱ መሆኔን እንኳን ለመናገር
አለመቻሌ እንደ ሞተም ቤተሰቡ ሁሉ ሰምቶ ሲደናገጥ የኔን የወላጅ እናቱን ኀዘን ሳይሆን የስዋን ትንሽ መጠነኛ ኀዘን ነበር የምታጽናኑት " እኔ ባሁኑ ጊዜ ከዚህ ቤት ችየው የኖርኩት ፈተና የሞት ያህል መራራና አስጨናቂ ነበር "

“ለምን ተመልሰሽ መጣሽ ? ” አላት "

“ ነገርኩህ እኮ ካንተና ከልጆቼ ተለይቸ መኖር አልቻልኩም '

“ስሕተት ነበር ! ፍጹም ስሕተት ነበር የሠራሽው
👍10