አትሮኖስ
282K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
490 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ባለፈው አርብ ለት እንደ ሁልጊዘው አምቦውሃና ጂን ቀላልቅሎ በፍጥነት መጠጠት ከጀመረ በኋላ ሆቴል
ይዞኝ ሄደ ሁልጊዜም የተረፈውን መጠጥ ይዞ ነው ወደ ሆቴል የሚገባው። ሩም እንደገባን ከረቫቱን አላላና የሸሚዙን ቁልፎች በግማሽ ፈታቶ አልጋው ጫፍ ላይ እንደተቀመጠ ድንገት በሀሳብ እልም ብሎ ጠፋ። እኔ ከላይ ልብሴን አወላልቄ እየጠበቅኩት ነበር እሱ ብድግ ብሎ ወደ ሶፋው ሄደና ሶፋው ላይ
ተንጋሎ በአንድ እጁ ጂኑን እንደያዘ በሌላ እጁ የዲኤስቲቪውን ሪሞት አንስቶ ዜና ማየት ጀመረ። እኔን መፈጠሬንም ሳይረሳኝ አልቀረም፡፡ ብታገሰው፣ ብታገሰው፣ ሊመጣ ነው?!

ዶክተር በላ! አውልቅና ኮንዶም አጥልቅ….!» አልኩት ሳላስበው። የእውነት አስቤው ሁሉ አልነበረም
እንደዚያ ያልኩት። እሱ እቴ! ለምን ደሙ አይፈላም፣ ይቺን በመናገሬ ብቻ ያን ምሸት የደረሰብኝ መከራና ያየሁትን ፍዳ… እኔ ነኝ የማውቀው። የአንድ ሰዓት ሌክቸረር ለቀቀብኝ። ቋቅ እስኪለኝ።

መጀመርያ ደምስሩ ተገታተረ። ቀጥሎ በዚያች ቁመቱ ሽቅብ በንቀት እያየኝ ተንጰረጰረ። አጫጭር ወንዶች እንኳን ዶክተር ሆነው እንዲሁም ኮምፕሌክሳምና ተንኮለኛ እንደሆኑ አውቃለሁ። የዚህ ሰው
ግን በዛ። አስጠላ።

«ስሚ! ባታውቂኝ ነው እንጂ!» ብሎ ሦስት ተከታታይ ሾርት የምሰራበትን ሰዓት ሙሉ ነዘነዘኝ። አምባረቀብኝ። ዛተብኝ። በአፉ ሸናብኝ ብል ይቀላል። ብቻ ያልሆነው የለም። ሌላ ጊዜ ማንም ወንድ
ምንም አይነት ብር ይከፈለኝ ንቀት ካሳየኝ ጥየው ነው የምሄደው። ይሄ የኔ ባህሪ ነው። ለንቀት ትዕግስት የለኝም። ያን ምሸት ግን ያልጠበቅኩት ስለነበረ ነው መሰለኝ ደንዝዤ ቀረሁ።

ሱሪ አውልቅና ኮንዶምህን አጥልቅ» ማለት ቆይ ምኑ ነው የሚያናድደው? አቤት እንዴት ቆሽቴን
እንዳሳርረው ያን ቀን!

ለሱ ሀኪም መሆን እግዚያአብሔር ከመሆን ለይቶ አያየውም መሰለኝ። «…ባታውቂኝ ነው…» ይለኛል
እንዴ ደሞ? አሁን እሱን ማወቅና ኮንዶም ማጥለቅ ምን አገናኛቸው!? ዶክተር መሆኑን ሲሰሙ ቫይረሶቹ እግሬ አውጭኝ ብለው የሚፈሰጥጡ መሰለው እንዴ?

ከኔ ይበልጥ የጦፈው ግን እሱ ነበር ለካ። በንዴት ሪሰፕሽን ደወለና ሌላ ቦትል ጂን አስመጥቶ መጠጣት ጀመረ። የጀመረውን ትቶ ማለት ነው። ገና እኮ የያዘውን ሳያጋምስ ነው ሌላ የሚያዘው። ሩም ድረስ ያመጣለትን አስተናጋጅ ሁለት የመቶ ብር ኖቶችን አውጥቶ ቲፕ አረገው። አስተናጋጁ ከቁጥጥሩ ውጭ
በሆነ የደስታ ስሜት ጭራውን ቆላለት።እሱም ይሄንን ነበር የፈለገው መሰለኝ፤ ሁሉም ሰው ጭራውን
እንዲቆሳለት። አይገርመውም! እኔ በፍጹም ጭራዬን ለሰው አልቆላም። ባፋንኩሎ፤ “የናትህ እምስ ትለው ነበር ራኪዬ ብትኖር። የማነው በናታችሁ!

“ለመሆኑ ስንት እንደሆንን ታውቂያለሽ? ብሎ ነበር ማንቋረር የጀመረው። በወቅቱ ምን ማለቱ እንደሆነ አልገባኝም ነበር።

Believe it or not ለዚህ አሸዋ ለሆነው 70 ሚሊዮን ህዝብ ሁለት ሺ እንኳ አንሆንም፣ ያለንለት።
ሆኖም እንደምታይው ነው! በቃ.ስለኛ ግድ አጥቷል.…አይንከባከበንም። እንዲያው ያንጓጥጠናል።
yeah…ንቆናል፣ መፈጠራችንንም ረስቶታል፤ yeah…ትዝ የምንለው ታይፎይድ ሲያንደፋድፈው ብቻ
ነው። እንኳን ሕዝቡ ሸሌ ንቆናል። ባንናቅ እንዲህ አትናገሪኝም ነበር።

ይቅርታ ልጠይቀው ስል አስቆመኝ።

"ታምኚያለሽ!?ታክሲ ከህዝብ ጋር ተጋፍተው የሚሄዱ ባልደረቦቼ እንዳሉ?እየዋሸሁ አይደለም። literally ከተራው ህዝብ ጋር ታከሲ የሚጋፉ ሀኪም ጓደኞቹ አሉኝ! Yeah True story ነው የምነግርሽ።
ህዝቡ ነጭ ጋውን ካልለበስን ሀኪም መሆናችንንም ማወቁን እንጃ፤yeah…ይሄ ህዝብ እንዲያከብረን በየመሸታ ቤቱ፣ በየጎዳናው ጋውን ለብሰን መገኘት አለብን?l Tell me አለብን? ይሄ ህዝብ እሺ በስም አይወቀን፤ ነገር ግን በመልክ እንዴት አያውቀንም? 2ሺ የማንሞላ ሀኪሞቹን በመልከ ማወቅ እንዴት
ያቅተዋል?..አሁንማ ስጋ ነጋዴም የኛኑ ጋውን ማጥለቅ ጀምሯል።ህዝቡ ከበሬ አራጅ እኩል ቢያየን የሸፈረድበታል ታዲያ? ዉርደት እኮ ነው ይሄ!

ይንጎራደዳል ደሞ አጠጣጡ ጂን ሳይሆን ጁስ የሚጠጣ ነው የሚመስለው። አስፈራኝ። ስላስፈራኝ ደርቄ አየዋለሁ።
"You see_ህዝብ ብቻ አይደለም የረሳን፣ ጤና ጥበቃ ረስቶናል፤ አንድ ቀን የበሽታ ወረርሽኝ ተከስቶ በደንብ የምንፈለግበት ቀን ይመጣል ብዬ እጠብቃለው የጤና ባለሙያዎችን ወያኔ ረስታናለች።የወያኔ እንኳ ተይው፤ አይነሳ! ወያኔ ድሮም ደንቆሮ ናት፤ አሁን ደሞ ብሶባታል። እንኳን ሕዝብን እኛንም መስማት አቁማለች። እንኳን እኛን ራሷንም አትሰማም። እርስበርሷ መደማመጥ አቅቷታል…ነጻ አወጣሃለሁ
ብላ የተዋጋቸለትን ሕዝብ እንኳ ትዝ የሚላት ምርጫ ሲደርስባት ነው…ተምቤን ስሰራ ሁሉንም ጉዷን
አይቼዋለሁ? የራሷን ሕዝብ እንኳ ረስታለች። yeah

“ሐኪም የሚንቅ መንግስት እድሜው አጭር ነው። ይሄ ታሪክ የመሰከረው ነው። ሕዝብና ሐኪም የናቀ መንግስት አብቅቶለታል። ወያኔ አልገባትም እንጂ ቢሆን ቢሆን ቄጤማ እያነጠፈች፣ አበባ
እየበተነች፣ዘምባባ እያውለበለበች ነበር ልትንከባከበን የሚገባት። yeah…ተሳሳትኩ? ከተሳሳትኩ እታረማለሁ?

“አሁንማ የንቀቷ ንቀት ፎርጅድ ሐኪም በየጎጡ እንደ አሜባ እያራባች ህዝቡን ልታስጨርሰው ቆርጣ ተነስታለች። የራሷን ሹመኞች ታይላንድ እያሳከመች፣ ህዝቡን በጥቃቅንና አነስተኛ ሀኪም
ታስፈጀዋለች። yeah ተሳሳትኩ?.ለሳል የሬሳ ማድረቂያ መርፌ የሚወጋ ሐኪም በቃለ መሐላ ያስመረቀች በዓለም ላይ ወያኔ ብቻ ናት። yeah ይሄን ታውቂያለሽ? I tell you! ወያኔ ሀኪም ንቃ
ከዚህ በኋላ ብዙ አትራመድም። ከነጻ አውጪነት ተነስታ አሁን እያመነመነች ህዝብና አገር የምትገድል
አደገኛ በሽታ እየሆነች ነው yeah…ተሳሳትኩ? እውነት አይደለም?”

ይህን ተናግሮ ላንቃው እስኪበጠስ ሳቀ! በተናገረው ነገር ኩራት ተሰማው። ወዲያው ደግሞ ፈራ መሰለኝ የሰማው ሰው ካለ በሚል ነው መሰለኝ በሩ መዘጋቱን ሄዶ አረጋገጠ

"ስሚ ደሞ የፈራሁ እንዳይመስልሽ! እኔ ነኝ ወያኔን የምፈራ? ለአቅማዳም ከደረስኩ ጀምሮ እንኳን ሰው ፈጣሪን ፈርቼ አላውቅም! ኦኬ.አይምሰልሽ!…»

ይሄኔ የምር ሳቄ መጣ። ፈርቶ እኮ ነው በሩ መዘጋቱን ሄዶ ያረጋገጠው። የሰካራም ነገር! ቆይ…ሰክሮ
እንዲህ ከፈራ ባይሰክር ኖሮ ምን ሊሆን ነበር? ሽንቱን ሱሪዉ ላይ ሊለቀው ይችል ነበር ማለት እኮ ነው። ሳቄን አፍኜ አቀረቀርኩ። ቆይ እኔ ላይ ጉራውን እንዲህ ከሚቸረችር ጫካ አይገባም? ሁሉም ወንድ ፍርሃቱን በኛ ያስታግሳል። ሲያስጠላ! ቦቅቧቃ ወንድ ያስጠላል!

የያዘው ሩም Luxury Suite ስለነበር በጣም ሰፊ ነው። በዚያ ሰፊ ሩሙ ግራና ቀኝ እየተንጎራደደ ሲያወራ ቲያትር የሚሰራ ነው የሚመስለው..

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍21😱1
Just like that! yeah. ብሎ አውራ ጣቱን ከባለጌ ጣቱ ጋር በማጋጨት በጣቶቹ ድምጽ ፈጠረ።

“…Believe t or not እኔ ይቺን አገር ብለቅ 35000 ሰዎች ይሞታሉ። እነዚህን ሰዎች ገድዬ መሄድ ህሊናዬ ስላልፈቀደ ነው አገሬ የቀረሁት። አሁን ገባሽ ምን ማለት እንደሆነ? አንቺ ማካፈል
እንደማትችይው ሁሉ ይሄ ህዝብ መድኃኒት አወሳሰድ እንኳ በቅጡ አያውቅም። እኛ ጥለነው ብንሄድ
I tell you በአስር ዓመት ውስጥ ረግፎ ያልቃል። ይሄን የሚረዳው ግን ማነው ነው ጥያቄው። ወያኔን ተያት ድሮም ሰው የሚላትን አትሰማም። በረሃ ታደርግ እንደነበረው ሕዝቡን ሁሉ በመጀመርያ
እርዳታ እድሜውን የምትቀጥል መስሏት ይሆናል፤ እስኪ እናያለና ቻይና ኔትዎርክ እንደምትቀጥልለት
የሐበሻን ህይወት የምትቀጥልበት ከመሰለው እስኪ እናያለን..."

አንድ ሙሉ ጠርሙስ ጅን ሊያጠናቅቅ ሩብ ያክል እንኳን አልቀረውም ነበር ፊቱ ደም እየመሰለ መጣ በትኩረት ስመለከተው ከዚህ በኋላ እንኳን ሴክስ ሊያደርግ አልጋ ላይ ያለ ድጋፍ መተኛት ከቻለ ጎበዝ ነው።በቁሙ እንቅልፍ ሊጥለው ይችላል።

ስሚኝ..ማነሽ sorry ስምሽ አያዝልኝም ማን ነበር ያልሽኝ...?

"ሮ..ዛ" ለስንተኛ ጊዜ እንደነገርኩት እኔ ራሴ አላስታውስም

"ኦኬ ሮዛ ስምሽ ከባድ ነው አይደል? ትንሽ ለማስታወስ ያስቸግራል..ለለነገሩ ማነስ ቢሆን። ስምሽ እኔ ላይ ምን ይጨምራል ብለሽ ነው? ለጊዜው በጄ ላይ ከሚገኙ 35 ሺ ነፍሶች አንዷ ነሽ ልበል ያ ማለት ደግሞ አንቺ ለኔ ተራ የሆስፒታል ነካርድ ቁጥር ነሽ ማለት ነው እኔ ግን ላንቺ ህይወትሽ ነኝ። see the different ይህንን ነው መረዳት ያቃታችሁ"

ብሽቅ አልኩ!

እኔ ሕይወትሽ ነኝ ይለኛል እንዴ ደፋር! እየሱስ እንዳይሰማህ አልኩ በሆዴ እሱ ግን በስካር ብዛት ዓይኑ ቡዝዝ ብላ ዜሮ አምፖል እስክትመስል ድረስ አንደበቱ ከመናገር ወዳ መላዘዝ እስክትሸጋገር ድረስ እንቅልፍ በቁሞ አዙሮ እስኪደፋው ማውራቱን አላቃመም ነበር።

"..እኮ ማንም ይሁን ስምሽ..። አንቺ ነሽ እኔን እንደ አንድ ተራ ወመኔ "ሱሪ አውልቅ ኮንደም አጥልቅ ብለሽ የምታመናጭቂኝ !? You bitch...!

ይሄንን ተናግሮ ከመቼው ማንኮራፋት እንደጀመረ ሳስብ ዛሬም ድረስ ያስቀኛል።

💫ይቀጥላል💫

#Like 👍 እና #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍2
አሮጌ ብትሆንም ግን ደስ ትላለች፤ ውልውል ተደርጋ የተቀመጠች መኪና ነው የምትመስለው ቤቱ እንደ ሦስት ፎቅ ክብድ የሚል ነገር የለውም
እንዲያውም ጭራሽ ፎቅ ቤት አይመስልም በሌላኛው የግቢው ጥግ አንድ የባስኬት ቦል መጫወች ቅርጫት ይታያል።

ወደ ውስጥ ዘለቅን።

"He...llo Anybody home?ማሬ Are you there?.." ብሎ ተጣራ

ትንንሽዬ ዉሾች ከየት መጡ ሳልል እግሬ ሥር ተንጫጩብኝ። ፈርቼ ወደኃላ ሳፈገፍግ ዶክ መጥቶ ምልከት ሰጣቸው።እሱን ሲያዩ ሦስቱም ድንክ የሳሎን ዉሾች እየሮጡ እላዩ ላይ ተጠመጠሙበት እያሻሸ አቀፉቸው። ልጆቼ ናቸው። ይሄኛው ቴዎድሮስ ነው ስሙ። ቆራጥ ነው። ሽጉጥ አጥቶ ነው
እንጂ ድሮ ነበር ራሱን የሚያጠፋው፡፡ እቺኛዋ ብርቱካን ትባላለች፣ በጣም ነው የምንወዳት። እዚ ቤት የመጣ ሰው ሁሉ ነው የሚወዳት። ይሄ ጎረምሳው በላይ ዘለቀ እያልኩ ነው የምጠራው። ማሬ
ግን “ቢስማርክ” ነው የምትለው። ሳቄ መጣ። ነገር ግን ዶክ ቡችሎችን የሚያሳድገው ልጅ ስለሌለው
እንደሆነ ሲገባኝ በራሴ አፈርኩ።

ቤቱ ጭር ሲልበት እንደገና ተጣራ! “ሄሎ ማሬ! Are you there?"

በጣም ረዥም፣ ወፈር ያለች፣ የወንድ ሰውነት ቢመስልም የደስ ደስ ያላት ፈረንጅ የሳሎኑን ደረጃ ወርዳ
ወደኛ ስትመጣ ተመለከትኩ። ግራ ገባኝ! ምናይነቷ ጅል ነኝ? እስከዚያች ደቂቃ ድረስ ሚስቱ ፈረንጅ ልትሆን አንደምትችል ምንም አልተከሰተልኝም ነበር፤ እሱ ራሱ ለምን እስከዛሬ ሳይነግረኝ ቀረ?

ተዋወቁ! ማሬ this is Roza... I was telling you about!
Oh Finally ! Happy to meet you Roza, ኢኔ ሲሜ ማሪያ!"አለችኝ ከለማጅ አማርኛና ሞቅ ካለ ፈገግታ ጋር my husband told me quit a lot about you

"Really?"

'Yes. I know a lot of stuff about you more than you can imagine!"

የምመልስላት ነገር ጠፍቶኝ ተቁለጨለጭኩ፤ «thank you» ማለት ሲገባኝ እንዲሁ በፈገግታ አለፍኳት

አይፈረድብንም! በዚያች ቅጽበት አእምሮዬ ብዙ ነገር በማሰብ ሊፈነዳ ደርሷል። ምንድነው ስለኔ
የነገራት? አልፎ አልፎ ትበዳኛለች ያልኩሽ ልጅ እሷ ናት» አይላትም መቼም። ካላበደ በስተቀር። ታዲያ ምን ቢያወራላት ነው ስላንቺ ከምትገምቺው በላይ ብዙ አውቃለሁ የምትለኝ?» እሱስ ለምን
ሚስቱ ፈረንጅ እንደሆነች እስካሁን ሳይነግረኝ ቀረ? At least ተዘጋጅቼ እመጣ ነበራ፤ በወሬ መሐል
ነግሮኝ እኔ ዘንግቼው ይሆን እንዴ? እንዴት ዶክ ስለሚስቱ ነግሮኝ ልረሳ እችላለሁ? የጋብቻ ጥያቄ
ቢያቀርቡልኝ ባንዳፍ» ከምላቸው ሶስት ወንዶች አንዱ ነው እኮ ዶክተር ቃልአብ። ከሲስ ነፍሴ ቀጥሎ በጣም የምወደው ሰው ነው ዶክ። ስለዚህ በፍጹም ስለሚስቱ ነግሮኝ ልረሳ አልችልም።

በሚቀጥሉት ደቂቃዎች ስለ ምንድነው የማወራው? የሚለው ጥያቄ ራስ ምታት ለቀቀብኝ። እጄን አስር ጊዜ ከሌላኛው እጄ ጋር እያፋተግሁ ቆየሁ።

ከሰፊው ሳሎን ትይዩ «ሜዘኒን» ላይ «ዳይኒንግ ሩም» አለ። ከዳይኒንጉ ጎን ትንሽዬ የምታምር ባር አለች። ባሯ ጓደኛዬ ሰኑ የምትሰራበትን ጩኒ ፐብን ታከላለች። አራት ባለጌ ወንበሮች አሏት። ልዩ ልዩ
ቮድካና ዉስኪዎች መደርደሪያው ላይ በቄንጥ ተንጠልጥለዋል። መደርደሪያው ከወዳደቀ እንጨትና በወፍራሙ ከተፈተለ ገመድ የተሰራ ቀላል፣ ግን በጣም የሚያምር ነው። ጭንቀት ባናወዘው አእምሮዬ ሆኜም የቤታቸውን ዉበት ማስተዋል ቻልኩ።

ማርያ ናት የስራችው፣ የወዳደቅ ነገር ትወዳለች» አለኝ፤ በመደርደሪያው አሰራር መመሰጤን
አስተውሎ።

"አንተንም ወድቀህ አንስታህ መሆን አለበት…» አልኩትና በራሴው ቀልድ ፈገግ አልኩኝ፤
እሱ ግን እቲ የሳቅ ጥይት ተኮሰ። ቤቱን በሳቅ ረበሸው፤ ተንከተከተ! ወትሮም ትንሽ ነገር በጣም የሚያስቀው ሰው እንደሆነ አውቃለው።

ማሬ ማሬ Listen to this . ብሎ ቀልዱን በእንግዝኛ ክሽን አድርጎ ነገራት። ስሟ ማሪያ ቢሆንም እሱ ግን ማሬ እያለ ነው የሚጠራት

ባልጠበቅኩት ሁኔታ እሷም ትከን ብላ ሳቀች።

| ሳቋን ተከትሎም እንዲህ አላት- What did tell you ማሬ ! She is extremely funny

"Yeahl can see that ብላ ጥላን ወደ ኪችን ሄደች። ዘና የማለት ስሜት ተሰማኝ።

ወደ ኪችን ስትራመድ ከኋላዋ እየገመገምኳት ነበር። ማሪያ ልክ እንደ ብዙዎቹ ፈረንጆት አነስተኛ )
ቂጥ ያላት ብትሆንም ሰውነቷ ወፍራም ሆኖ ነገር ግን ቅልጥፍጥፍ ያለና የሚያምር ነው። ቀጥ ያለችና .
ሁሉ ነገሯ እስትክከል ያለ አይነት ነው። ፀጉሯ ጥቁር ሳይሆን ፊልም ላይ ብሎንድ የሚሉት ወርቃማ ቀለም ያለው ነው። በጣም ረዥም ከመሆኗ የተነሳ እኔን ራሱ ትበልጠኛለች። ሱሪም ሆነ ቁምጣ
| አላጠለቀችም። አንድ ረዥም የወንድ የሚመስል ቀለል ያለ ቲሸርት ነው የለበሰችው።ቲሸርቱ ረዥም ከመሆኑ የተነሳ ቂጧን ሸፍኖላታል። ምናልባት የውስጥ ፓንት አድርጋበት ይሆናል። ጡት መያዣ እንዳላረገች ግን አስተውያለሁ። ከፍሉ ውስጥ በተራመደች ቁጥር ጡቶቿ ዝልል ዝልል ይሉባታል። "
እርጋታ የሚባል ነገር የፈጠረባት አትመስልም። ሁሉንም ነገር በጥድፊያ ነው የምታካሄደው።

የሷን ግዝፈትና ቁንጅና ስመለከት ለምን እንደሆነ አላውቅም ራሴን ጠላሁት። የሆነ የቆሸሽኩ ትንሽ ፍጥረት የሆንኩ አይነት መስሎ ተሰማኝ። ቅልል ያለ አለባበሷን ሳስተውል ደግሞ እኔ ኮተታም የሆኑክ መሰለኝ፤በካፖርት ላይ ጋቢ የዴበርኩ ያህል ተሰማኝ። በርግጥ አጭር ሚኒ ቀሚስና እምብርቴ ላይ
የምትቀር ባለቁልፍ ሸሚዝ ነበር የለበስኩት። ያንን የሚያክል ሂል ጫማ ግን ማድረግ እንዳልነበረብኝ ተሰማኝ፡ ሰው ቤት የተጋበዝኩ ሳይሆን ለኡስማን ቢዝነስ የወጣሁ ነበር የምመስለው።

ማሪያ ወደ ኪችን እንደገባች የሳሎኑን በር ተደግፈን በቆምንበት ዶክተር ቃልዓብ እጁን ከወገቤ አንሸራቶ ቂጤን በስሱ ሲደባብሰኝ ተሰማኝ። በድንጋጤ ክው ብዬ ቀረሁ። ምን እያረገ ነው ይሄ ሰውዬ?
ተስፈንጥሬ ሸሸሁትና በዓይኔ ተቆጣሁት።
"ሮዚ እንደዛሬ አምረሽኝ አታቂም! Swear to heaven ልሞትብሽ እችላለው! So you better be have ምንም ነገር እምቢ እንዳትይኝ" ብሎ በለሆሳስ አንሾካሾከልኝ...

💫ይቀጥላል💫

#Like 👍 እና #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍5
መለሰላት ግን አልተሰማኝም። ወደ ላይብረሪው ገብቼ ቅድም ወድቆ አይቼው የነበረውን «transgender» የሚለውን መጽሐፍ ቦታው ከመለስኩ በኃላ ለመረጋጋት
ሞከርኩ። ራሴን በድጋሚ በደንብ ማስተካከል ጀመርኩ። ናፕኪን ከቦርሳዬ አውጥቼ ሊፒስቲኩን ሙልጭ አድርጌ ከጠረኩት በኋላ ሶፍቱን እዚያው ከሚገኝ ከቀርከሃ የተሰራ ባስኬት ውስጥ
ጨመርኩት። አዲስ ቻፒስቲክ ደመቅ አድርጌ ተቀባሁ።

ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በዚህች ላይብረሪ ምን እየሆንኩ እንደነበረ ሳስታውስ ድንጋጤዬ አገረሸብኝ።
ፍርሃት ሁለመናዬን ዉርርር አደረገኝ። በዚያው ቅጽበት ማሪያ ስሜን ስትጠራው ሰማሁ።

“Comning!” ብዬ መልስ ሰጠሁ። ከዚያም እያነበብኩ የቆየሁ ለመምሰል አንድ VOGUE PARIS
የሚል ደማቅ የፈረንሳይ የፋሺን መጽሔትና ቅድም ባለጌ ነገር ስናረግ ወድቆ በኋላም ቦታው መልሺው
የነበረውን transgender የሚለውን መጽሐፍ በጄ ይዤ ደረጃውን መውረድ ጀመርኩ።

"You guys have amazing library. It took my breath away. Envy you guys! By the way,
was reading these two!” ብዬ መጽሔቱንና መጽሐፉን አሳየኋት። ዶክተር ቃልአብ በፍርሃት የታፈነሳቅ አፍኖት ፊቱን የኪችን ሲንክ ውስጥ ሲደብቅ አየሁት አንገቱን አቀርቅሮ ብርጭቆ በማለቅለቅ ላይ ነበር።

Wow! Thank you! This all has happened because of my beloved husband! ብላ ከንፈሩ
እስኪገነጠል ድረስ ሳመችው። ይህን ጊዜ ድንጋጤ ተፈጠረብኝ፡፡ ሚስቱ ስትስመው የተለየ ጣዕም ከንፈሩ ላይ ልታስተውል ትችላለች በሚል ነበር ስጋቴ፡፡ ምንም አላለችም። ተመስገን አምላኬ!

የረጠበውን እጇን ከሲንኩ ጎን በተንጠለጠለ ሰማያዊ ፎጣ ካደራረቀች በኋላ transgender የሚለውን
መጽሐፍ ተቀበለችኝና ለቃልአብ እያሳየችው በሳቅ መንከትከት ጀመረች። ቃልአብም “oh yeah! That
thing your story. oh no are you gonna tell her?!” ብሎ እሷን በሳቅ ማጀብ ጀመረ። ለምን እንደሚስቁ መጀመርያ አልተገለጠልኝም ነበር።እንዲያውም ፎቅ ላይ የሆነውን ነገር ያወቀችብን መስሎኝ በድንጋጤ ዉሀ መሆን ጀምሬ ነበር። ዶክተር አብሯት ሲስቅ ጊዜ ነው የተረጋጋሁት። በኋላ
ግን ነገሩን በጠቅላላ ሳስበው ቃልአብ እየሳቀ እኔ ለምን ድንብርብሬ እንደሚወጣ ግርም ይለኝ ጀመር።
የኔ ትዳር አይፈርስ ነገር ምን አሸማቀቀኝ!

What is funny?” ብዬ የሞት ሞቴን ጠየቅኩ።

"It is a Lo....g long story ሮዝ i will tell you over the lunch ብላኝ ምግቡን እያቀራረበች እንደ አዲስ በሳቅ መንፈር ጀመረች። ቃልአብም ሳቋን አጀበው። ሳስበው ቃልአብ ፍርሃቱን ለመሸፈን አሪፍ አጋጣሚ ተፈጥሮለታል።ለዚያም ነው ወሬዋን እያዳመቀ የሚስቀው። አሁን ስጋቱ ሁሉ በኖ ጠፍቶለታል መሰለኝ። ከደቂቃዎች በፊት ምንም እንዳልተፈጠረ ሆኖ ኪችን አብሯት ሲንጎዳጎድ ገርሞኝ ነበር። እኔ በጭንቀት መከሳት ጀምሪያለሁ፤ እሱ ሆዬ ይስቅልኛል።

ማሪያ ምሳችንን በሙሉ አቀራረባ ስታበቃ lunch is served!" ብላ ሁለታችንም ወደ dining room እንድንመጣ ጋበዘችን፤

ሶስታችንም ወንበሮቻችንን ስበን ተቀመጥን። ማሪያና እኔ ፊት ለፊት ትይዩ ተቀመጥን። እሱ ግን ከኔ
ጎን ያለውን ወንበር ስቦ ተቀመጠ። ከማሪያ ጎን ይቀመጣል ብዬ ነበር ያሰብኩት። ለምን እንደሆነ
ባላውቅም የመረጠው ቦታ ትክክል እንዳልሆነ ተሰምቶኝ ነበር።
ድንገት ሁለቱም ጣቶቻቸውን አጣምረው መጸለይ ጀመሩ። ከዚያም እኩል ««ኤሜን!» ብለው ምግቡን ባረኩት...

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍51
በሩን ከፈትኩት። ፊቴ መረጋጋቱን ስታይ እፎይታ ተሰማት።
ሲያመኝ ከፍተኛ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰምቷት እንደነበር ገለጸችልኝ፡፡ በሷ ቤት የሷ ሽሮ ያሳመመኝ ነው የመሰላት የፈረንጅ ምስኪን!

ከባዝ ሩም ወጥቼ ስራመድ እግሬ እርስ በርሱ መምታታቱን እንዳላቆመ ተረዳሁ። ዶክ ባላንሴን የሚያስት የሆነ ብሎኔን "ባቢሼ" ውስጥ ገብቶ ሳይፈታብኝ አልቀረም።

ዶክተር ቃልአብ ወጥ ያበላሸው ሸሚዙን ቀይሮ የባስኬት ቦል ኳስ ፎቶ ያለበትን ቲሸርት አድርጎ ደረጃውን ሲወርድ አየሁት። ደህና መሆኔን በእንግሊዝኛ ጠየቀኝ። ፊቱ ላይ የሆነ ፈገግታ ብልጭ ሲል አየሁ ያሰበውን በማሳካቱ ደስ ሳይለው አልቀረም።በትክክል አላማው ምን እንደ ነበር ግን እስካሁንም አልተገለፀልኝም።

ለአንድ ሰአት ያህል ተረጋግተን ዉስኪ እየጠጣን ተጫወትን። በመሐል ቡችሎቹ እየመጡ እላዬ ላይ ሲመጡ እየፈራሁ ተቸገርኩ። ሆኖም እነሱን በፍፁም እንዳላመናጭቅ ዶክ አስጠንቅቆኝ ስለነበር እንደማጫወት እያረኩ ተከላከልኳቸው። ያማምራሉ። የሚደረግላቸው እንክብካቤ ግን ለሰው ልጅ ከሚያደርገው በላይ ነው።

ሳሎን ባር ቁጭ ብለን ዘና ብለን ማውራት ጀመርን።

Transgender የሚለው መጽሀፍ ሙኒክ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እያለች በወንዶች ድርጊት ከመማረሯ የተነሳ ጾታዋን ለማስቀየር በወሰነች ጊዜ የገዛችው መጽሐፍ እንደነበረ ነገረችኝ። ሆኖም በኋላ ላይ በአባቷ ምክር ሀሳቡን እርግፍ አድርጋ እንደተወችው በድጋሚ ተረከችልኝ። ወንዶችን እንዴት መያዝ እንዳለባት አባቷ ድንቅ ምክሮችን መከራት። ምክሩን ተግባራዊ አድርጋ በአንድ አመት ውስጥ ዉጤት ካላገኘችበት ጾታዋን የመቀየር ዉሳኔዋን እንደሚያከብር በጊዜው አባቷ ቃል ገብቶላት እንደነበርም ደግማ አጫወተችኝ። እኔ በበኩሌ አባቷ አበሻ አባት ቢሆን ቀጥቅጦ ይገድላት እንደነበር
አስረዳኋት።ትስቃለች ብዬ ሳስብ ግን ደነገጠች።

ዶክተር ቃልአብም በየመሀሉ እየገባ ይቀልድባት ጀመር። ዉሳኔዋን ገፍታበት ቢሆን ኖሮ ዛሬ ቆንጅዬ
የወንድ ጓደኛው ልትሆን ትችል እንደነበር እያወራ አሳቃት።

እሷ በበኩሏ ወንዶች ሲባልጉ እሷም በምላሹ መባለግ ስትጀምር እንዴት የበለጠ እየወደዷትና እያከበሯት እንደመጡም ታስረዳኝ ጀመር። ይህን ስታወራ ዶክተር ቃለአብ ፊቱ ከአንዴም ሁለት ሶስት ጊዜ ሊለዋወጥ እያስተዋልኩ። በሁለቱ ግንኙነት ወስጥ የሆነ አንድ ያልገባኝ ነገር እንዳለ እርግጠኛ ሆኑክ...

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
1👍1
ከቃልአብ ጋር በፍቅር መክነፍ በጀመሩበት በመጀመሪያው ዓመት ማሪያ የአባቷን ምክር ለመተግበር
አንድ ሁለት የምትልበት አጋጣሚ ነበር። አባቷ ጾታ የመቀየሩን ሀሳብ እርግፍ አድርጋ እንድትተው የመከሯት «ወንዶች ላያቸው ላይ የምታማግጥ ሴትን ይበልጥ ያፈቅራሉ» የሚለውን አስተሳሰባቸውን በሷ ላይ በመጫን ነበር። ይህ ሁኔታ ነው የዶክተር ቃልአብን ልብ ክፉኛ የሚጎዳ ነገር እንዲከሰት
ምክንያት የሆነው።

ከማሪያ ጋር የተማሪ አፓርትመንት ተከራይተው አብረው መኖር ጀምረው ሳለ ከእለታት አንድ ቀን ያልተጠበቀ ነገር ተከሰተ። ይኸውም ዶክተር ቃልአብ የፈተና ሰሞን ስለነበር ድካም ተጫጭኖት
ከላይብረሪ መጥቶ ቤት በተኛበት ሁኔታ የሆነ እንግዳ ድምጽ ይቀሰቅሰዋል። አንሶላውን ከላዩ ላይ ገፎ መለመላውን ድምጽ ወደሰማበት ክፍል ሲሄድ ፍጹም ያልጠበቀ ነገር ተመለከተ። ማሪያ ከአንድ
አልጄሪያዊ የቀድሞ ፍቅረኛዋ ጋር የኪችን ካውንተር ጠረጴዛ ላይ ወሲብ ስትፈጽም በአይኑ በብረቱ ተመለከተ። ይህን አልጄሪያዊ ደግሞ ያውቀዋል። ሲኒየሩ ነው፤ በዚያ ላይ የተማሪዎች አፓርትመንት ዉስጥ ሳሎንና ኪችን ሼር ስለሚያደርጉ በተደጋጋሚ አይቶታል። ሆኖም የማሪያ የቀድሞ ፍቅረኛዋ
እንደነበረ ማንም ነግሮት አያውቅም። ያ ማለት ማሪያ ከዶክተር ቃልአብ ጋር ሆና ራሱ በተደጋጋሚ ከአልጄሪያዊው ጋር ወሲብ ትፈጽም ነበር ማለት ነው። የያኔው ተማሪ ቃልአብ በዐይኑ በብረቱ ያየው
ነገር አዘሮ ሊደፋው ሆነ። «በዚያች ቅጽበት ሆኜ ወደ ጌታ መጸለይ ጀመርኩ»አለኝ ዶክተር ቃልአብ
አምላኬ እባክህን ይህን የማየውን ነገር በህልሜ አድርገውና ዘላለም አንተን ሳመሰግን ልኑር"

ዶክተር ቃልአብ መለመሉን፡ እነሱ ደግሞ የኪችን ካቢኔት ጠረጴዛ ላይ መርፌና ክር እንደሆኑ ደርቀው ቀሩ።

አልጄሪያዊው ከደነዘዘበት ነቅቶ ገፍትሮኝ ወጣ። ማሪያ ጠረጴዛው ላይ ሆና ጭኖቿን ከፍታ እየተንቀጠቀጠች የሚሆነውን ነገር በጥሞና ትከታተላለች።ምን እንደሆነ የማላውቀው ዳቢሎስ ሄደህ ባለችበት እነቃት እነቃት እንደማለት ፋንታ ወስባት ወስባት ብሎ ሹክ አለኝ። የተከፈተውን እግሯን ይበልጥ ከፍቼ በከፍተኛ የአውሬ ስሜት ሴክስ አረኳት። ትዝ የሚለኝ ነገር ቢኖር እያቃሰተች ታለቅስ እንደነበረና ይቅርታ እንዳደርግላት ትለምነኝእንደነበረ ነው። ስንጨርስ ተዝለፍልፈን ወደቅን
ተቃቅፈን አለቀስን። በዚያው ቀን ልታገባኝ እንደምትፈልግ ነገረችኝ። መርፌና ክር ሆነን ሳለ would you marry me » አለችኝ። l will አልኳት።በዚያው ቅጽበት ዘላለም ከኔ መለየት እንደማትፈልግ
ገለጸችልኝ፤ በዚያው ቅጽበት ይቅርታዋንም የጋብቻ ጥያቄዋንም ተቀበልኩት። ሻወር ወስደን ተቃቅፈን |
መልሰን ተኛን። በነጋታውም ተኝተን ዋልን። ብዙ ወሲብ አደረግን። ማሪያ መውለድ ብትችል ያን ቀን ትወልድ ነበር የምናስቀና ባልና ሚስቶች ሆንን ትምህርታችንን ጨርሰን ወደ ኢትዬጵያ መጣን።

ጥያቄ ልጠይቀው አፌን ሳቆበቁብ በእጁ አስቆመኝ። ልጠይቀው ያሰብኩት ነገር ገብቶታል።

ከዚያን ቀን ጀምሮ ግን አንድ ትንሽ ዲያቢሎስ ደሜ ዉስጥ ተሰንቅሮ ቀረ። you know ማሪያን እጅግ በጣም እንደማፈቅራት። you know እሷ አንድ ነገር ብትሆንብኝ በህይወት ልቆይ የምፈልግበት አንድም ምክንያት እንደሌለ። መቼም ልለያት አልፈልግም፡፡ ልጅ መውለድ አልቻልንም። ሦስት ቡችሎችን ነው የምናሳድገው፤ ቴዎድሮስን፣ ብርቱካንና በላይን። አለመውለዳችን ግን እኛን ሊለየን የሚችል ቁም ነገር አይደለም። በሚቀጥለው አመት አንድ ሴት ልጅ በጉዲፈቻ ልናሳድግ ወስነናል። በኔና በሷ
የፍቅር ሕይወት ውስጥ ልጅ ያለመውለድ ጉዳይ ጭራሽ እንደ ችግር አይተነውም አናውቅም። እኛ የምንፈልገው እንደተፋቀርን ቶሎ ቶሎ ኖረን፣ አጠር ያለች የምትጣፍጥ ህይወት ኖረን መሞት ነው።
ችግሩ ያለው ከኔ ነው። እኔን ከያዘኝ ዲያቢሎስ ነው ችግሩ።…”

"ይህ የምነግርሽ ትንሽዬ ዲያቢሎስ ያን ሌሊት የተፈጠረውን ነገር ላለፉት 7 ዓመታት መልሶ መላልሶ ያመጣብኛል። ፀለይኩበት፤ አፀለይኩበት። ሊለቀኝ አልቻለም። ብዙ ቸርች ሄጃለው ከዚህ
ዲያቢሎስ ለመፈወስ። እየባሰብኝ መጣ። ይህ ዲያቢሎስ ስራው አንድ ነው፤ የዛን ሌሊቱን ነገር ቁልጭ
አድርጎ በአእምሮዬ እንደፊልም ያሳየኛል። አልጄሪያዊውን አልሙሳዊን ደጋግሞ ያመጣብኛል። ሮዚ አታምኚኝም ድርጊቱ ልከ ዛሬ እንደተፈጸመ አድርጎ ያሳየኛል። ኪችኑ ውስጥ የነበረውን ሹካ ሳይቀር፣
የአልሙሳዊን መቀመጫ ሳይቀር…። ያን ትዕይነት ለማጥፋት አንቺ ጋር እመጣለሁ በምወዳት ሚስቴ ላይ እባልጋለሁ-። ምን ላድርግ?? እስከመቼ ነው የዚህ እርኩስ መንፈስ መጫወቻ ሆኜ የምቀረው!?….”

ማሪያን በተመሳሳይ መልኩ ብበቀላት ይህ ችግር ለዘላለሙ እንደሚጠፋልኝ የመከሩኝ ሁለት የአሜሪካ ሳይካትሪስቶች የጻፉት መጽሐፍ ነው።ጸሐፊዎቹን ለሥራ ቨርጂኒያ በሄድኩበት ላገኛቸው
ሞከሬ አልተሳካልኝም። በኢሜይል ሁኔታውን ጻፍኩላቸው። የመከሩኝ ነገር አስደነገጠኝ። ግዴለም ሚስትህን ንገራትና ሞክረው አሉኝ። የተለመደ ቴራፒ እንደሆነ ነገሩኝ። እነሱ መፍትሄ ነው የሚሉት ቴራፒ በተመሳሳይ መንገድ እንድበቀላት ነው። እሷ ባደረገችው መንገድ ካልተበቀልካት ትዕይንቱ
ከአእምሮህ ሊወጣ አይችልም አሉኝ። ነገር ግን ፈራሁ፤ የምጎዳት መሰለኝ። በዚህ ፍርሃቴ ውስጥ ሆኜ የፈጸምኩት ድርጊት ነው የዚያ ምሽቱ ድራማ። አንቺ ዘንድ የምመጣው ይህን እርኩስ መንፈስ
ለማስታገስ ብቻ ነው፤ ሮዝ…፤እንጂ ሚስቴን ጠልቼ አይደለም።”

ዶክተር ቃልአብ አንገቴ ውስጥ ፊቱን ቀበረ። ቀና አድርጌ ሳየው የምርም እያለቀሰ ነበር። መነጽሩ ላይ የእንባ ዘለላዎች ይታያሉ። አሳዘነኝ።
የዛን ዕለት ለምን ሚስቱ ፊት ወሲብ ሊያምረው እንደቻለ አሁን ገና በደንብ ተገለጸልኝ። ያን ክስተት
በበቀል መልክ ከአእምሮው ለማጥፋት ያደረገው ከንቱ ሙከራ ነበር። አሳዘነኝ።
የምሩን ነው ማሪያን የሚወዳት። ከንፈሩን ሳምኩት። እያነባ ከንፈሬን ይስመኝ ነበር። ወደ ጓሮ ወስጄው እኛ ብቻ የምንጠቀምበት «የሴቶች ቤት» የምንላት ልብስ መቀየሪያ ክፍል ይዤው ገባው። በሩን ከውስጥ
ቀረቀርኩት። ገንዘብ የሌለበት ንጹህ ፍቅር ሰራን። የሚገርመው ከኔ ጋ ፍቅር እየሰራ ልቡ ግን ያለው ሚስቱ ጋር ነበር! ማሪያ! ማሬ! Tell me that you love me!Tell me you never see him again Tell me you never cheat » እያለ ያቃስት ነበር።

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍51
ያስደስተቻው። ባለሙያዎች ማለት በነዚህ ሀብታሞች ቋንቋ “ጋርዶች ማለት ነው።

የዳንስ ፍሎ ካሉበት Top VIP Room ቁልጭ ብሎ ስለሚታይ እንዲህ አይነት ድርጊቶችን ሞቅ ባላቸው ቁጥር ማድረግ ደስ ይላቸዋል።ለምሳሌ በምሽቱ ቀሽት የምትባል ሴት ይዞ የመጣ ወንድ ካለ
እሱን ታርጌት ውስጥ ያስገቡታል። ከዚያ ልጁ በደስታ ሰክሮ እየጨፈረ ሲያብድ ሀብታሙ ሰውዬ
“ይሄን ልጅ ቀልቤ አልወደደውም” ካለ አጃቢዎቹ ቶሎ ብለው፣ ችግር የለም በ“ባለሙያ” እንዲወጣ ይደረጋል” ይሉታል። ይሄኔ ሳሚ ባሪያው በልዩ ረዳቶቻቸው በኩል ይጠራና በጆሮው የኾነ ነገር ሹክ ይሉታል።

ሳሚ ልጁ ጋር ሄዶ "ወንድሜ በስነስርአት ተዝናና ይለዋል።ልጁ ጥፋቱ ግር ብሎት ምን አጠፋው ይላል።ሳሚ ኮስተር ብሎ በቃ ሥርአት ይዘህ ጠጣ ጠርሙስ አያያዝህ ቤቱን የሚመጥን መሆን አለበት ይሄ ጠላ ቤት አይደለም ይገባሃል? ይለዋል።በገርል ፍሬንዱ ፊት እንደዚህ መባሉ ያንገበገበዉ ወጣት በጣም ደፋር ከሆነ ሳሚን ካልደበደብኩ ይላል።ይሄን ግዜ ሳሚ ባርያው ጆሮውን ይዞ ውጭ አውጥቶ እንደ ጅራፍ ያስጮህዋል።

TOP VIP Room ቁጭ ብለው ይሄ እንዲሆን ያዘዙት ሀብታሞች "ካካካካ...ካካካካ..ካካካካ እያሉ ረጅም የሃብታም ሳቃቸውን ይለቁታል።ቦርጫቸው ለምን በሳቅ ብዛት ረግፎ እንደማይጠፋ አይገባኝም።የተዋረደውን ልጅ ገረል ፍሬንድ ከተቻለ "አንቺን መጋበዝ የሚፈልጉ ባለሀብቶች አሉ ፍቃድሽ ከሆነ .." ተብላ ትጠራለች።እምቢ ካለች ማንም አይነካትም በሰላም የጠጣችበት ተከፍሎላት ትሄዳለች።እሺ ካለችና ዕድለኛ ከሆነች ግን አንድ ኬክ ቤት ሊከፈትላት ይችላል ደግነቱ እነዚህ የናጠጡ ሃብታሞች ለሴት ልጅ ያላቸው ክብር ደስ ይላል።ፍቃደኛ ያልሆነች ሴት በፍፁም አይነኩም

ሳሚ እንደነገረኝ የሞጃዎቹ ፍላጎት ከሆነ ባለትዳርም ቢሆን በዚህ መልኩ ከቤቱ ተዋርዶ ሊወጣ ይችላል።ዋናው ነገር ድርጊቱ እነወዚያ ባለሃብቶች ያዝናናል ወይስ አያዝናናም የሚለው ነው።

አንድ ቅዳሜ ማታ ባለሃብቶቹ ከሚቀመጡበት ክፍል ቀጥሎ ባለው የዲፕሎማቶች ክፍል ነበር ከሁለት የአረብ ሊግ ዲፕሎማቶችና ከእዩኤል ጋር። አረቦቹ ይህን ሪያል ስለሚረጩት ነበር እዩኤል አብሮን ተቀምጦ የነበረው። ሳሚ ባርያው መጥቶ በጆሮው የሆነ ነገር ሹክ አለው። እዩኤል ቱር ብሎ ተነስቶ ለሁሉም ሰው ትእዛዝ መስጠት ጀመረ።ዲጄው በፍጥነት ሙዚቃዎቹን እንዲቀይር ተደረገ።በተለይ የሚመጡት ሁለቱ ባለሃብቶች የሚወዷቸው ቆየት ያሉ አማርኛ ዘፈኖች አሏቸው በቃ እነሱ ተደጋግመው መከፈት ጀመሩ።ቤቱ በአንድ ጊዜ በአንድ እግሩ ቆመ።

ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ሰዎቹ ከአጃቢዎቻቸው ጋር ሆነው ወደ ልዩ ክፍላቸው አመሩ ይህ ክፍል ከነሱ ውጪ ማንም አይገባበትም።ለአንድ አመት ከፍለውበታል።ቢኖሩም ባይኖሩም በቀን በቀን እየተፀዳ ሽቶ ይርከፈከፍበታል።እኔ ገብቼበትም አላቅ።ገባን የሚሉ ሴቶች ግን አሉ በወርቅ የተለበጠ ጠረጴዛና ሶፋ ወንበር አለ ብለው ይ ነግሩናል።

እዩኤል ባለሐብቶቹ ገብተው ቦታቸውን እንደያዙና ነገሮች መልክ መልክ እንደያዙ ሲያረጋግጥ ተልሶ መጣ። ግርማ ነው ያለኝ። ሪያል እንደጠበል እየረጩ ከነበሩ ሁለት የአረብ ዲፕሎማቶች በላይ የሚያንቀጠቅጡት ምን እይነት ሀብታም ቢኾኑ ነው ብዬ አሰብኩ።

ተማልሶ መጥቶ እኛን ከተቀላቀለን በኋላ አንድ ሁለቴ ከመጠጡ ተጎነጨለት። ከዚያ ትንፋሹን ሰብስቦ እኝዲህ አለኝ።

ይሄ ሚስኪን ሕዝብ አዲስአባ የኔ ናት፣ የኔ ናት እያለ ይፋጃል፤ ልንገርሽ አይደል? ፊንፊኔ የኦሮሞም የኢትዮጵያም አይደለችም። የዚህ ሰውዬ ናት" አለ በአፍንጫው ጫፍ Top VIP Room እያመለከተኝ።
ያን ሰምን በአዲስ አበባ የባለቤትነት ጉዳይ ላይ በየዩኒቨርስቲው ረብሻ ተከስቶ ነበር።
የተናገረው ነገር ፖለቲካ ስለመሰለኝ ምንም አላልኩም። እሱም ቀልቡ ሁሉ ሁለቱ ባለሐብቶች ጋር ስለነበረ ተነስቶ ሄደ።

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍4
tradition? Crying on a birthday party" ዶናልድ ግራ ገብቶት ጠየቀ። የመለሰለት ግን አልነበረም።

ለምን እንደሆነ አላውቅም ሁላችንም ስለ ሕይወታችን እያሰብን፣ በሆዳችን እያለቀስን ነበር። ሸሌ ሆነን ወጣትነታችን ፈጀነው፣ እንደ ሙሉ ሰው ትዳር መስርተን፣ ልጅ ወልደን፣ ለራሳችን ከብር ኖሮ ሰውም እንደሰው ቆጥሮን፣ የገላ ሳይሆን የልብ ፍቅር ሰጥቶን፣ አንድም ጊዜ ሳንኖር እድሚያችንን ቀረጠፍነው። ትምኒትም፣ ዉቢትም፣ ሃኒቾም፣ ትዙም እንደዚያ ስላሰብን ይመስለኛል ሸዊትን አጅበን ያለቀስነው። እንጂ የሸዊት ማልቀስ አይመስለኝም ያስለቀሰን። በሺዊት አሳበን ያለቀስነው ለራሳችን
ነው።

እኔ በበኩሌ ብቻዬን ስሆን ይህ ስሜት እየመጣ ብዙ ጊዜ አስለቅሶኛል፤ ለሰው ተናግሬው ግን አላውቅም። ቤት ከሆንኩዲጄ ዲከ የሰጠኝን ምርጥ ምርጥ የማሊ ሙዚቃ ኮሌክሽኖችን ከፍቼ እንባዬን አስቆመዋለሁ፤ ይሳካልኛል። ሙዚቃዎቹ እሩቅ አገር ወስደው ሐዘኔን አስረስተው ይመልሱኛል። የሸዊትን ለቅሶ ተከትሎ ሁሉም ሰው እምባውን በመጥረግ ቢዚ ሆኖ ነበር። ከዶናልድ በስተቀር!
ስለዚህ ቶሎ ጫወታ መቀየር ነበረብን። ትምኒት ነበረች ለዚህ ቀዳሚዋ።

የማልታው ሰውዬ!

እናንተ! የማታው ሰውዬ!”

"የቱ?”

ይሄ “ማልታ” ከምትባል አገር ነው የመጣሁት ሲለን የነበረው። ወይኔ በከርስቶስ (እያማተበች) እንደዚህ አይነት ነገር ያለማታ አይቼም ሰምቼም አላውቅም” ትምኒት ሀዘናችንን ለማስረሳት የጀመረቸው ወሬ እንደሆነ ብናውቅም በደንብ እንድትነግረን አበረታታናት።

"ማነው እሱ?

"ያእንኳ ማታ “ፕራይቬት ኮርነር” ጥግ ላይ አብሮን ሲጠጣ የነበረው ፈረንጅ ነዋ! "ማልታ የምትባል አገር እንዴት አታውቁም ብሎ የተበሳጨው እንኳ?”

እህ ማታ ከዉቢት ጋር ያየነው እንዳይሆን !! እኔ በደንብ አይቼዋለሁ፣ ረዥም መላጣ ሰውዬ አይደል?
አልኳት።

"አዉ! ሮዚ አውቀሽዋል! ማታ ከሱ ጋ ነበር “ዴ ሊዮፖል” ያደርነው። ጂኦግራፊ ሲያስጠናኝ አላደረ መሰለሽ? ሞባይሉን አውጥቶ የዓለም ካርታ ዘርግቶ በቁም ነገር ማልታ የት ቦታ እንደምትገኝ ያሳየኛል።አይገርምሽም? የሚያዋስኗትን አገሮች፣ ወደ ዉጭ የምትልካቸው ሸቀጦች፣ … እሱን እያስጠና ሲበዳኝ
አደረ…ሃሃሃሃሃ አይገርምሽም? ሃሃሃሃ”

“አንቺ እንዴት አታውቂም ማልታን…? ምድረ ኤርትራዊና ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ጣሊያን የሚገባው በዛ በኩል አይደል እንዴ?” አልኳት።

“ሮዚ ሙች! አይገርምሽም ዛሬ ገና አደነቅኩሽ። እሱም ልክ እንደዚያ ሲለኝ ነበር። “የአገርሽን ስደተኞች እኛ ነን የምንቀበላቸው” ብሎ ጉራውን ሲቸረችር ነበር። የተባበሩት መንግስታት ስደተኛ ካምፕ ውስጥ ነው የምሰራው፤ ነው ያለኝ መሰለኝ።”

እና ምን ይጠበስ ነው የሚለው?” የነገሩ ጫፍ አልጨበጥ ያላት ሃና ጠየቀች።

“ምኑ ይጠበሳል በናትሽ! ይልቅ ልነግራቹ የነበረውን አስረሳሽኝ፡፡ እቃው በጣም በጣም በጣሞ ትንሽ ናት። በየሱስ ስም! (አማተበች) ወይኔ ጉዴ! በእጄ ልነካት ስል እንዴት እንደዘገነነችን። እናንተ
ለካስ ትልቅ እቃ ብቻ አይደለም የሚያስፈራው፤ ትንሽም ያስፈራል። የኾነች ጢኒጥ ቃሪያ እኮ ነው የምታከለው። ብታይዋት አኮ…አሁን የተወለደች አይጥ እኮ ነው የምትመስለው፡፡ ሃሃሃ…ወይኔ ጉዴ !
በየሱስ ስም (አማተበች)

እንዴ?እኔ አብሮሽ ሲጠጣ ያየሁት ሰውዬ ግን ግዙፍ ነው! ተሳስቼ እንዳይሆን? አማሩላ ሲጠጣ የነበረው ሰውዬ ነው አይደል? እንዲያውም "የሴት መጠጥ የሚጠጣ ፈረንጅ” ብዬ ገርሞኝ እያየሁት ነበር ማታ አልኳት።

“ሮዚ አንቺ አውቀሽዋል በቃ! እኔም ሰውነቱን አይቼ እቃው በጣም ትልቅ ነው የሚሆነው ብዬ ቢዝነስ እጥፍ ነው የጠየኩት። ይቅር ይበለኝ! (አማተበች) ውስጥ ከገባን በኋላ ግን በእውነት ነው ምልሽ…ሃኒቾ ሙች..ሮዚ..ሙች..ዋጋ ቀንሽለት ቀንሽለት የሚል ሃሳብ ሁሉ ነበር የመጣብኝ።

"So you gave him a discount?” አላት ዶናልድ ጣልቃ ገብቶ።

ሁላችንም ሳቅን።

“የሚገርምሽ እኮ ማልታ የሚላት አገሩ ራሷ ልክ የሱን ወሸላ ነው የምታከለው። ስታሳዝንም አለች ትምኒት ደጋግማ እያማተበች። ሀዘኗ ቅጥ አጣ፤ ለሱም ለአገሩም።

በድጋሚ ሳቅን። ጫወታችንም እየደራ መጣ። “የሴቶች ቤት” የምንላት ክፍል ትኩሳቷ እየጨመረ ነው።
ይበልጥ ሌላ ትኩሳት የሚፈጥር ጥያቄ ከዶናልድ ዱርዬው ተነሳ።

"But ladies, I have a question for you, if you don't mind! How big is "big" for you? ምሳሌ
is this size big or small ብሎ ረዥሙን የመሐል ጣቱን እያዟዟረ ለሁላችንም አሳየን።

በዚህን ጊዜ ሁላችንም ሳቅ አፍኖን ተፋጠጥን።

"It depends! ለምሳሌ...Your middle finger is big enough for Roza but.that may not be
the case or Tizeta…” ብሎ ሲስ መለሰለት።

አማስግናለሁ ሲስ!” አልኩት የተናገረው ውስጠ ወይራ ገብቶኝ። ትዙ ግን የማትወደው ርዕስ በመነሳቱ ሽምቅቅ ብላለች።

በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን እዚህ ስቱዲዮ ድረስ ወይዘሪት ትዝታን ጋብዘናል። ወይዘሪት ትዝታን ባድማጭ ተመልካቶቻትን ስም እናመሰግናለን.….…የመጀመርያው ጥያቄያቸን የሚኾነው…”

ትዙ ከዚህ በፊት ባብሽዋን ደምበኞቿ “ሰፊ ነው” እያሉ ሲያወሩባት ተማራ እሱን ለማስጠበብ ዮጋ ስልጠና ስለወሰደች ነው ሲስ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ የሚቀልድባት።

ተነፋ እሺ!! ባንተ ቤት ቀልደህ ሞተሃል…የምር ግን እናንተ ወንዶች ቁላቹ በከሳ ቁጥር እኛን ማማረር አይደብራችሁም? አንተ የኔ የትዙ ባብሽ ሰፋ ከምትል ቁላዬ ትንሽ ነው ለምን አትልም? ብሽቅ!
፤ ቆይ ያንቺ ሰፊ ነው ከማለትህ በፊት ሞክረከኛል? አንተን አኮ ነው? ወንዶች ስትባሉ ወሬ አለባችሁ!ሁላችሁም ተነፉ እሺ” ትዝታ በአንድ ጊዜ ሰይጣኗ ተነሳባት። ድሮም የምትፈራው ርዕሰ-ጉዳይ ነው የተቀሰቀሰባት።

I think that is a very good point” ብሎ ትዝታ የተናገረችውን ዶናልድ አደነቀ። ትዙ በተመጠነ ፈገግታ ምስጋናዋን ገለፀች።

እኔ እንዳነበብኩት አንድ የሴት ብልት ትልቅ ነው የሚባለው 3 በ4 ሲሆን ነው” አለች ሃና።

እንቺ ደሞ ኮንዶሚንየም አረግሽው እንዴ!” አለቻት ሸዊት።

ኖ ኖ 3 በ4 ሳንቲ ሜትር እኮ ነው ያልኩት!"

እና ኪሎ ሜትር ነው ማን አለሽ?” አለቻት ሸዊት።

ለሸዊት አጨበጨብንላት። ልደቷ ስለሆነ ሞራል መስጠት ነበረብን። ክርክሩ ግን ሳይታሰብ ጦፈ።

"In my country Slovenia, If you hear an echo when you eat her out, she has a big pusy" አለ ዶናልድ።ከዉቢት በስተቀር ሁላችንም ዶናልድ በተናገረው ነገር ዘለግ ላሉ ደቂቃዎች ሳቅን። ዉቢት የዶናልድ እንግሊዝኛ ስላልገባት ማብራሪያ ጠየቀች።

"በቃ ምን ብዬ ልንገርሽ እነሱ አገር የአንዲት ሴት ትልቅ ነው የሚባለው ወንዱ ጎንበስ ብሎ ባብሿ አካባቢ በአፉ ባለጌ ነገር እያረጋት እያለ የገደል ማሚቱ ከተሰማ ነው ያን ጊዜ ነው ሰፊ የሚሉት አያስጠሉም በናትሽ...

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍3🥰1
። ሸዊትን የሚያውቃትም የማያውቃትም ጠጪ ተነስቶ happy Birthday to you! እያለ ቤቱን በዝማሬ አደመቀው። አዳዲስ እንግዶች ነገሩ ሳይገርማቸው አልቀረም። ነገር ግን የሷን ልደት ከማድመቅ
ዉጭ አማራጭ አልነበራቸውም።

ዲጄው “ልዩ ቀን!” የሚለውን የሄኖክን ዘፈን ከእንግሊዝኛ ሙዚቃ ጋር ሚክስ እያረገ አከታትሎ ለቀቀው። ቤቱ በቅጽበት ውስጥ ከጽልመት ወደ እብደት ተሸጋገረ። ሸዊት ፍጹም ያልጠበቀችው ነገር
ስለነበር እምባዋን መቆጣጠር አቅቷት ሲስ ትከሻ ዉስጥ ተደብቃ በደስታ ማልቀስ ጀመረች።
እየጨፈርን አጀብናት ወደ ዳንስ ፍሎሩ መሐል ወሰድናት።ዲጄው በማይክራፎን "ክለብ አሪዞናና ጓደኞቿ በመተባበር ለሸዊት ልደት ያዘጋጁላትን ስጦታ ሚስተር ደመቀ እንዲሰጡልን እንጠይቃለን ብሎ ደሜን ወደ ስቴጅ ጋበዘው።ደሜ ደሞ እዩኤል አስከትሎ ወደ መድረክ ወጣ። ከዚያም በላስቲክ የተጠቀለለ ነገር ለሸዊት ስጧት።እንባዋን እየጠረገች ስጦታዋን ተቀበለች።

"ይከፈት ይከፈት ይከፈት የሚሉ ድምፆች ከያቅጣጫው ተሰሙ።ሸዊት መጠቅለያውን ስትከፍተው ሙሉ ደርዘን ፓኬት የሚደረደርበት የሕይወት ትረስት ኮንዶም ካርቶን ሆኖ አገኘችው።ማየት የሚችለው ሰው ሁሉ ሳቀ።እሷም እንደማፈር ብላ ሳቀች።አልከፋትም። እምባዋን እየታገለችም ቢኾን ሳቀች።ውስጡን ክፈችው!"ተባለች። ውስጡ ብዙ ኮንዶሞችን እንጂ ሌላ ነገር ይኖረዋል ብላ በፍፁም አልጠበቀችም ነበር።

34ሺ ብር አካባቢ የሚያወጣ የአንገት ሃብል ነበር የተቀመጠላት።

አለቀሰች እየሳቀች አለቀሰች።

አልታወቀንም እንጂ ሸዊተሸ ብቻ ሳትሆን ለካንስ ሁላችንም በደስታ እያለቀስን ነበርን።ይህን የተረዳውት ሲስ ራስታ ስሜቱ እርብሽብሽ ብሎበተሸ ከእምባው ጋር እየታገለ ፊቱን በፀጉሩ ለመሸፈን ሲሞክር በማየቴ ነበር።ለካንስ ሰው አግኝቶት የማያውቀው ፍቅር ሲሰጠው ያለቅሳ።ሸዊት የኔ ቆንጆ አንጀቴን በላችው።

#ድህረ_ታሪክ

በሳምሪ ልደት ምክንያት የተገናኙት ሃኒቾና ዶናልድ ያን ቀን ምሽት ከሰርፕራይዝ ፓርቲው በኋላ አብረው አደሩ አዳራቸው የቢዝነስ ሳይሆን የፈቅር ነበር ከዚያ ቀን በኋላ መለያየት አቃታቸው ሃና በስንተኛ ወሯ ቋንቋ መማር ጀመረች ተባለ ከዛያ ቢዝነስ ተወች ተባለ ከዚያ ዶናልድ ራሱን መጠበቅ ጀመረ ተባለ።ፎነቀቀላት ነጠላ ጫማ መልበስ አስተወችው የሚለው ወሬ በመስቀል ፍላወር አካባቢው እንደ ጉድ ናኘ እውነትም የኾነው ጊዜ ጸጉር ቤት ስሄድ መንገድ ላይ ዘንጦ አይቼው እሱ መሆኑን ሁሉ ተጠራጥሬ ነበር።ትንሽ ቆይቶ አረገዘችለት ወድያው ፕሮሰስ ጀመረችና ወደ ስሎቬንያ ሄዱ።ሁሉም ነገር የሆነው በብርሃን ፍጥነት ነበር።

ከስንትና ስንት ጊዜ በኋላ ትምኒት ጋር ለንደን ካፌ ማክያቶ እየጠጣን በሞባይሏ ፌስቡክ ከፍታ አንድ ፎቶ አሳየተኝ።
ዶናልድና ሃና ፈረንጅ የሚመስል ልጃቸውን አቅፈው የተነሱት የሚያምር ፎቶ ነበር።ዶናልድ የዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር ኾኖ፣ እሷ ደግሞ እሱ በሚሰራበት ዩኒቨርስቲ ረዳት የላይብረሪ ሰራተኛ
ሆና ጁብልጃና በምትባል የስሎቬኒያ ከተማ በፍቅርና በደስታ ይኖራሉ። የልጃቸውን ስም ትምኒት ደጋግማ ነግራኝ አልያዝልሽ አለኝ። የገረመኝ ግን የልጃቸው የስሙ ትርጉም ነው። ያ የሚያምረው የድሙቡሽቡሽየው ልጃቸው ስም በስላቪክ ቋንቋ "ትንሹ ዱርዬ"ማለት ነው

አበባ:
ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ በጣም ቅዝቅዝ ብላችኋል ውዶች

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍3😁1
is what is happening now.
የምለው ካልተዋጠልሽ ታሪክን ወደ ኃላ ለማየት ሞክሪ። አስተውለሽ ከኾነ ብዙ ህዝብ ዉስጥ ዉስጡን መንጌን ይወዳል። መንግስቱ ኃይለማርያምን ሙሉ ስሙን ሰው ሲጠራ ሰምተሸ ታውቂያለሽ? ብዙ ሰው አሁንም ድረስ “መንጌ” እያለ ነው አቆላምጦ የሚጠራው። ለምን መሰለሽ…ቂጡን በሳንጃ እየወጋ ስለገዛው ነው። ሕዝባችን ገዳይ ይወዳል። ጀግና የሚለው ቀጥቅጦ የሚገዛውን ነው።

ሄይ ሄይ ሲስ! በናትህ ፖለቲካ አታውራብኝ…ራሴን ያመኛል። በናትህ…”
እኔ የምለውን ችላ ብሎ ማውራቱን ሲቀጥል አቋረጥኩት።

ደሞ ምንድነው የምትዘባርቀው? You are not making sense to me at all. ስለ መኪና አነሳህ ዞረህ ደሞ የሌለ ፖለቲካ ዘባረቅህ። ከዚህ በላይ ዲሞክራሲ ከየት ይምጣልህ…. ማክያቶ እየጠጣህ አፍህ እንዳመጣልህ ሕዝቡን እየተሳደብክ ዲሞክራሲ የለም ትላለህ እንዴ? ደግሞ ሕዝብ ሲባል እኮ አንተም አለህበት። …ደግሞ ቀስ ብለህ አውራ! …» አልኩ ዙርያዬን እየገላመጥኩ።

See Rozil Look at yourself now! በፍርሃት ዙርያሸን እየተገላመጥሽ እንደገና ደሞ ከዚህ በላይ ዲሞክራሲ ከየት ይምጣልህ ትይኛለሽ፡ ድምጽህን ዝቅ አርገህ አውራ እያልሽ፣ ዲሞክራሲ አለ ትያለሽ....

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
ይስቃል። ምንድነው የሚያስቅህ ብዬ ስጠይቀው አንድ የጅማ ነጋዴ ትዝ ብሎት እንደሆነ ነገረኝ።

ቡና ላኪ የአጋሮ ነጋዴ ነው። ያው እነሱ ታውቂያቸዋለሽ በጣም ብር አላቸው ግን ደህና ጫማ እንኳን አይገዙም። ሁለት ግራ እግር ነው የሚጫሙት። እና ይሄ ነጋዴ ጨክኖ መኪና ገዝቶ ቀስ እያለ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች እየነዳ ዓለሙን ይቀጫል። በእግሩ ሲሄድ ከሰው ቆጥረውት የማያውቁት የአዲሳባ ቺኮች ሁሉ መኪና ሲይዝ ከሱ አይናቸውን አልነቅል አሉ። እና … የአዲስ አበባ ሴቶች ደሞ መኪና ከያዝክና ክላክስ ካረክላቸው
ዐይናቸውን አያሹም፤ ይሰጡሃል ፤ እንዲያው ዘለው ነው መኪናህ
ዉስጥ የሚገቡት» ብለውታል ቀድመው የባነኑ ያገሩ ሰዎች።እና በዚህ በቦሌ አቅጣጫ ጥግ ጥጉን ቀስ እያለ እየነዳ ሲሄድ ድንገት «ታጥቦ የተፈጨ 1ኛ ደረጃ ቂጥ» ያያል። አጅሬው ከፊት ከፊቱ ሞንደል ሞንደል እያለ የሚሄደውን ቂጥ ቀስ እያለ ተከተለው። በዜሮ እየነዳ ይሄን ቂጥ እግር በእግር ይከተላል ይከተላል… ይከተላል። እየቆየ ሲሄድ አላስችል አለው። ነፍሱ ቂጥ አይታ ቀጥ ልትልበት ሆነ። የጅማ ጓደኞቹ ምከር ትዝ አለው። ክላክሱን ተጫነው። ጲ…ይ. ጵ! …”

ከላከስ ከኋላዋ ያንባረቀባት ባለቂጥ በድንጋጤ ዞር ስትል ፊቷ በጣም አስፈሪ ከመሆኑም በላይ
በፍጹም የዛ ሞንዳላ ቂጥ ባለቤት የማትመስል፣ እንዲያውም የቦክሰኛው የማይክ ታይሰን ታላቅ እህቱ የምትመስል አስፈሪ ሴት ትሆንበታለች። ይሄኔ ተፀጽቶ ምን ቢል ጥሩ ነው?
አንቺን ማን ጠራ...ሲሚሽ ጲጵ ነው ኢንዴ!?”

ሲስ ቀልዱን ሲያወራው እንዴት እንደሚያስቅ፡፡

ተንከትከቼ እየሳቅኩ ሳለ ዳሽ ቦርዱ ላይ ተቀምጣ የነበረችው የሲስ ሞባይል አንጫረረች። እየነዳ ስለነበረ እኔ አነሳሁለት።

“ሀሎ…ሲሳይ መኪና እየነዳ ነው።…ማን ልበል? "

ሴት ናት። የኔን ድምጽ ስትሰማ ደንግጣ ጆሮዬ ላይ ዘጋችው።
ሲስ የሆነውን ስነግረው መኪናውን ጥግ አሲዞ መልሶ ቁጥሩ ላይ ደወለ።

“በዚህ ስልክ ተደውሎ ነበር

“ተሳስተዋል፤ ይሄ ካልዲስ ኮፊ ነው።”


💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍2
ምድር ቤት ያስቀብራል እየተባለ ስለሚታማ ሀሜቱ ተጠናክሮ ቀጠለ። “ጥቁር ሴት ቅጠር ተብሎ በአውሊያ ተነግሮት ነው” ተባለ። “እህቱ ናት” ይሉ የነበሩ ሰዎች የሴት ቢዝነስ ሊያሰራት እንደሆነ ሲያውቁ አፋቸውን ዘጉ።

ደሜ ገንዘብ ያገኘው በመተት እንዳልሆነ አውቃለሁ። አዱንያ የዘነበለት ኤርትራዊያን ሲባረሩ ነው። ቄራ አንድ ጋራዥ ዉስጥ ይሰራ ነበር። የቤቱ ባለቤት አባ አስገዶም ይባሉ ነበር። ደሜ ያኔ የቅርብ ረዳታቸው ነበር። ኤርትራዊያን ከአገር ይዉጡ ሲባል ደሜ ጋራጁን በአደራ እንዲያስተዳድር ተሰጠው።
ከቀበሌ ጋር ተሞዳምዶ እንደኾነ ነገር አድርጎ ጠቀለለው። አሁንም ድረስ “የሱ አይደለም፣ ሚኒስትር የሆኑ የአገሩ ሰውዬ ናቸው በሱ ስም አድርገው የሚሸቅሉበት” ይባላል። እኔ ግን አይመስለኝም። አንድ ሚኒስትር ምንም ቢልከሰከስ ከአንድ ጋራጅ ቤት ምን ብር ያስለቅመዋል? ደሜ ጋራጁን ሸጦ እዚ
ሮማን ሕንጻ ዉስጥ አሪዞናን ከፈተ።

አሁን ደሜ ተወደደም ተጠላ የአሪዞና ጌታ ነው። በከተማው ቁጥር አንድ የሆነ፣ በየምሽቱ ብር፡ሪያልና ዶላር የሚታተምበት ክለብ ነው በባለቤትነት የሚያንቀሳቅሰው። እንኳን እሱ እኛ ለሱ የምንሰራው እንኳ አንዳንዴ ብር በዝቶብን ያስነጥሰኛል፤የሚሰራንን ያሳጣናል። እሱም እንዲያ አድርጎት ይሆናል።ዝናሽን እየቀጠራት ያለው።

አሁን ዞሮ ዞሮ ዝናሽ ሸሌ ልትኾን ነው። ደሜ ባቀናው “ክለብ አሪዞና” ዝናሽ ቢዝነስ ልትጀምር ነው
በውነቱ ይሄን ማን ያምናል?

ዝናሽ በሂል ጫማ

እውነትም ሰው ከጣራ የትም ይደርሳል ይኽው ዝናሽ በሂል ጫማ ተራመደች ተባለ። ያን ምሽት ሂልተን ቢዝነስ ወጥቼ
ስለነበረ አሪዞና አላደርኩም፡፡ ወሬውን ስሰማ ግን ሳቅኩኝ። መጀመርያ ስትራመድ በአይኔ በብረቱ ካላየሁ አላምንም ብዬ ድርቅ አልኩ። የምሬን ነበር። በፍጹም ዝናሽ በሂል ጫማ
ስትራመድ ማሰብ አልቻልኩም። በቃ ሊመጣልኝ አልቻለም። በቃ ሊዋጥልኝ አልቻለም፡፡ ሴቱ ሁሉ የውስጥ እጄን እየጠፈጠፈ ሲምልልኝ ግን ዝናሽ እውነትም በሂል ጫማ ተራምዳ ሊኾን እንደሚችል ጠረጠርኩ። ሁኔታውን እነ ሳሪ አዳምቀው ሲነግሩኝ በጣም በስሜት ተውጠው ነበር።

መጀመርያ ሁለት የአሪዞና ጋርዶች ማለትም ተሼና ሳሚ ባሪያው በግራና በቀኟ ቆመውላት እነሱን ተደገፈች ተባለ። ከዚያም ለአንድ ደቂቃ ያህል ሚዛኗን ለመጠበቅ ሞከረችና ልቀቁኝ አለቻቸው።
እርግጠኛ ነሽ ዝናሽ” አሏት ተባለ፤ እኵል ደንግጠው። “አዎ ግን ቀስ ብላችሁ ልቀቁኝ” አለቻቸው።ተሼና ሳሚ ባሪያው ሰፈሩና ሲቸሩ ቀስ ብለው ለቀቋት።

ከሳሚ ባርያው ተላቃ ስትቆም አሪዞና ፐብ ሴቶች ቤት በቀውጢ ጭብጨባ ተናጋ አሉ።

እንደገና ዝናሽ ሚዛኗን ጠብቃ ከቆመችበት አንድ እግሯን ስታነሳ የሴቶች ቤት በጸጥታ ተዋጠ ተባለ።
ትንሽ ከተንገዳገደች በኋላ ሁለተኛ እግሯን ስታነሳ የተሰበሰበው ሴት ባለማመን አፉን ከፍቶ ቀረ።እንደዚህ አይነት የአድናቆት አፍ አከፋፈት የታየው የኒውዮርክ መንታ ሕንጻዎች ላይ ጥቃት የደረሰ ጊዜ ብቻ ነበር ተባለ። ለሦስተኛ እርምጃ ቀኝ እግሯን ስታነሳ በደስታ እምባ የተናነቃቸው የአገሯ ልጆች ነበሩ ተባለ። ነገሩን አጋነው ሲያወሩልኝና ስስቅ ከረምኩ።

ብቻ ዞሮ ዞሮ “ዝናሽ በሂል ጫማ ተራመደች።

#ዝናሽ_አገባች

ቆይ እንጂ ወደ ትዳር ዝም ብሎ አይገባም። ትዳር ቀልድ አይደለም። ትዳር ብዙ ዝግጅት የሚፈልግ ነገር መሰለኝ። ትዳር ሾርት አይደለም ዝም ብሎ የሚገባበት። ስለዚህ “ዝናሽ አገባች” ከማለቴ በፊት፣ ዝናሽ ከማግባቷ በፊት ስለነበሩ ሰባት ወራት መናገር አለብኝ። ዝናሽ በነዚህ ወራት በክለብ አሪዞና ምን
አደረገች ? መጀመርያ እሱን ልፃፍ።

To make the short story even shorter እንዲሉ ፈረንጆት ዝናሽ ብሂል ጫማ መራመድ ቀስ በቀስ ቻለች። መጀመርያ አካባቢ ዩሪ ጋጋሪ ጨረቃ ላይ የሚራመድ እንጂ እሷ የምትራመድ አትመስልም ነበር። ከአንድ ጠረጴዛ ተነስታ ወደ ሌላ ስትራመድ ጠጪው ሁሉ በሰቀቀን በዐይኑ ይከተላት ነበር።ለቤቱ አዲስ የሆኑ ሰዎች ሰክራ ስለሚመስላቸው ብዙም አይደነቁም፤ እኛ ባልደረቦቿ ግን እሷን በማየት ስራ ፈታን ።

በነገራችን ላይ ገዝናሽ እንዴት ረዥም እንደሆነች ተናግሪያለሁ። በዚያ ቁመቷ ሂል ጫማ ስታደርግ G+3 ፎቅ ነው የምትመስለው። እንስራ የሚያህለው ጭንቅላቷ ደግም ፎቁ ላይ የተሰራ “ፔንት ሀውስ ይመስላል። እኛ የቤቱ ረዥም ሴቶች እንኳን ኮምፕሌክስ ነገር ስለሚሰማን ከጎኗ ደፍረን አንቆምም።
ታሳጣናለቻ። እሷ ግን ቁመት ብቻ ሳይሆን ጥቁረትም ውፍረትም ክብደትም የሚያህላት ስለሌለ ቤቱን እየረገጠች ታንቋቋዋለች። እሷ ስትራመድ ምድር ትንቋቋለች፤ ይቺ ምድር ስንቱን እንደቻለች ይቅር ይበለኝ።

ዝናሽ ከጡቷ ይልቅ ጎንጯ ጡት መያዣ ይፈልጋል። በዚያ ሰውነት ላይ ፈጣሪ ለምን ትንንሽ ጡቶች እንደተከለላት ይገርመኛል። ሰፊ ደረቷን አይቼ ትንንሽ ጡቶቿን ሳስብ አእምሮዬ ላይ የሚመጣው ሁለት 0 አምፖል የተገጠመለት ሠፊ የሰርግ አዳራሽ ነው ይቅር ይበለኝ።

ያም ኾኖ ሚኒስከርት አድርጋ፣ ሽቶ ተርከፍከፉ፣ የቢራ ጠርሙስ አንቃ ቁጭ ትላለች። ልክ እንደኛ ወንድ ፍለጋ! ባለጌ ወንበር ላይ። ባለጌ ወንበሩ እሷ ስትቀመጥበት ጨዋ ኾነ። ዱካ ኾነ። ረዥም ስለሆነች ቀርጩማ ላይ የተቀመጠች ነው የምትመስለው። ባለጌ ወንበሩ ላይ ምንም ሳትንጠራራ ነው
ሄዳ ጉብ የምትልበት። ሰው ባለጌ ወንበር ላይ ተንጠራርቶ ነው የሚወጣው፤ እሷ ግን እንዲያውም በርከክ ትላለች መሰለኝ
ይቅር ይበለኝ!

ብቻ ዝናሽ እንደምንም ተኳኩላ ቢዝነስ ጀመረች። የመጀመርያ ቀን ማንም ወንድ ቀና ብሎ ሲያያት ስላላየን ስላላየን በአንድ ድምጽ “የፈራነው ደረሰ" አልን። ከሷ ጋር የሚያድር ወንድ ካለ ሄጄ
አስፈርመዋለሁ ስትል ነበር ትምኒት። እውነቷን ነው። ይህ ነገር ለተከታታይ ሁለት ሳምንታት ቀጠለ።ሁላችንም ተደናገጥን። አሳዘነችን። ምንም ቢሆን እኮ ሴት ናት። የበታችነት ስሜት ተሰምቷት ራሷ ላይ አደጋ እንዳታደርስ ፈራን። እሷ እቴ ምንም አልመሰላትም። ትኩረቷ ሁሉ በሂል ጫማ እንደልቧ መራመድ መቻሏ ላይ ብቻ ነበር ፈ። አንድ ቀን ደፍረን ደሜን ነገርነው....

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍51😱1
ሞባይላችንን አውጥተን ዜናውን ባንድ ጊዜ ነዛነው፡፡ የደወልንላቸው ሁሉ ለተጨማሪ መረጃ እኛ ሴቶች ቤት ተንደርድረው መጡ። ግማሹ ሱዳናዊው ሰውዬ እጣን ነጋዴ ነው ይላል፤ ግማሹ ደቡብ ሱዳን ውስጥ የነዳጅ ማጣሪያ አለው ይላል። ግማሹ ባህርዳር ካርቶን ፋብሪካ አለው ይላል። ያየውም ያላየውም እኩል አውቀዋለሁ ማለት ጀመረ።

ዝናሽን የሰርጉ ቀን እስኪደርስ ሳር ቤት ካናዳ ኤምባሲ ጀርባ በአንድ ቪላ ቤት ውስጥ አሳርፏታል ተባለ። መጥቶ ከዚህ የወሰዳት እንዲያዉም በነጭ መርሴዲስ ነበር ተባለ። የገረመኝ ይሄ ሁሉ ሲሆን እኔ የት እንደነበርኩ ነው።

ከዚያ በኋላ ጆርዬ መስማት ከሚችለው በላይ መረጃ ደረሰኝ። የሰርጓን ቪሎ እንድትመርጥ ደቡብ አፍሪካ ይዞት ሊሄድ ነው ተባለ። ሰርጉ በአንድ ሳምንት ልዩነት ካርቱምና አዲስ አበባ ነው የሚካሄደው
ተባለ። ለሰርጉ እኔ ራሱ በጣም የምወደው አንድ ዘፋኝ ተጠርቷል ተባለ። የሰው ሰርግ ላይ ይዘፍናል ብዬ የማልጠብቀው ዘፋኝ ነበር።

የሱዳን ታዋቂ ዘፋኞችም አዲስ አበባ ይገኛሉ ተባለ። “ታዲያ በርበሬ መቀንጠስ እንጀምራ? ስንል ሰርጉን የሚያሰናዳ ድርጅት በብዙ ሺህ ብር ስለተቀጠረ ማንም ምንም ማድረግ አይጠበቅበትም
ተባለ። የሰርጉ ቀን እስኪቃረብ ለሦስት ሳምንታት ያህል ክለብ አሪዞና በጭራሽ ሌላ ወሬ አልተወራም ዝናሽ ነበረች በሁሉም ሰው አፍ ዉስጥ የምትታኘከው

#መደምደሚያ

ይሄን ማስታወሻ ስጽፍ ጎልፍ ክለብ ሰርጓን በልቼ መግባቴ ነው። በሕይወቴ ብዙ ሰርግ አይቻለው።እንዲህ ዊስኪ የተረጨበት፤ እንዲህ ሙዚቃ የተደለቀበት፤ እንዲህ ቁርጥ የተቆረጠበት፣ እንዲህ ሩዝ የተደፋበት ሰርግ ግን አጋጥሞኝ አያውቅም። ሦስት ታዋቂ የሱዳን የሰርግ ዘፋኞችና አንድ ሙሉ ባንድ
ከካርቱም አዲስ አበባ መተው ነበር። ስማቸውን እየጠሩ ዘፈኑላቸው።ዝናሽን በሱዳንኛ ዘይና እያሉ ነበር የሚጠሯት።እሷም ባሏም ሚዜ አልነበራቸውም።ለምን እንደዚሉ እንዳደረጉ አልገባኝም።ያለሚዜ ሰርግ ሲካሄድ ሳይ የመጀመርያየሰ ነው።ቢሆንም ቅልጥ ያለ ሰርግ ነበር።

በመስቀል ፍላወር አካባቢ ሴት አንዷም አልቀረችም።ሁሏም እስክትፈነዳ በልታ፤ እስክተሸና ጠጥታ ነው የሄደችው።ቀታሪክ ብዙ ሸሌ የተገኘበት ሰርግ ይመስለኛል።

አቤት ግን ዛሬ ሰውን እንዴት እንደታዘብከለት ዝናሽን እንደዛ እንዳላበጠለጠሏት እንደዚያ እንዳልሳቁባት እንዳላፌዙባት እንዳልሸሿት ሞጃ አግብታ ሞጃ መሆኗን ሲያውቁ ስሟን ከመቼው ከዝናሽ ወደ "ዜድ" እንደቀየሩት።ከመቼው ቁንጅናዋ እንደታያቸው።ከመቼው ከንፈሯ እንደሳሳባቸው ያ የምድር ወገብን የሚያክለውን ወገቧን እኮ "ችቦ አይሞላም"ሲሉት ምንም አላፈሩም። እነ ተሼ በሷ ዕይታ ውስጥ ለመግባት እንዴት በእስክስታ እንደተርገፈገፉ።እነ ውቢት እሷ እንድታያቸው እንዴት ቂጣቸውን እነደቆሉ። ይቺ ቅሳነት ድፍረቷ ድፍረቷ! የሷ እንኳን ለጉድ ነው።ሱዳንኛ በተዘፈነ ቁጥር ከሙሽራው ፊት እየሄደች " ኡ ያዙኝ ልቀቁኝ !" ስትል ሰው ይታዘበኛል እንኳን አትልም?የምር ሰውየው ሁለተኛ ሚስት አድርጎ እንዲወስዳት የፈለገች የሸመስል ነበር።

ለካስ ቁንጅና ማለት ገንዘብ ነው።ለካስ ውበት ማለት ሃብት ነው።እኔ ራሴ ዝናሽ እንዴት ያን ቀን ቆንጆ ሆና እንደታየችኝ ዐይኔ ተጭበረበረላት እኮ! ሳኩላት ቀናሁባት ብቻ ልእልት መስላ ታየችኝ።በአእምሮዌ ውስጥ ያቺ ጭስ ጭስ እየሸተተች ቢጫ ፊስታል ይዛ የዛሬ ሦስት ዓመት ያየኋት ባላገርና የዛሬዋ ሙሽራ ለየቅል ናቸው።ላመሳስላቸው ብሞክርም አልቻልኩም። ለካንስ ውበት ማለት አስተሳሰባችን ውስጥ ነው የሚሳለው።ዝናሽ ልቅም ያለቸሸ ቆንጆሆና ታየችኝ።

#ድህረ_ታሪክ

ዝናሽ ከዛ በኋላ ወደ ክለብ አሪዞና ብቅም አላለችም።ነገር ግን የክለቡ ጋርዶች የነበሩትን ተሼንና ሳሚ ባርያውን ሕይወተሸ ለወጠችላቸው።ሁለቱም የሷና የባሏ ረዳቶች ሆነው ካርቱም ሄዱ ከባሏ ጋር የምትዟዟርበት የዓለም ጥጉ ሁሉ አብረዋት ይሆናሉ።ደሞዛቸው ሲነገረኝ ስላላመንኩበት በማስታወሻዬ አልፃፍኩትም።ሳሚ ባርያው እንኳን አውስትራሊያ ለሽርሽር እስኪሄዱ ነው እንጂ እዚያ ሲደርስ እንደሚጠፋ እርግጠኛ ነኝ የሱ የአውስትራሊያ ፍቅር የአውስትራሊያ ዜጎች እንኳ የላቸውም

ደሜ ደግሞ በደቡብ ሱዳን ቅርንጫፍ የሀበሻ ክለብ እንደሚከፈትለትና ለዚህ ሁኔታዎች እንደሚመቻቹለት ቃል ተገብቶለታል፡፡ ይኸው ነው ዝናሽን ግን ምንም ብንጥር ያን ቀን ከሩቅ ከማየት ውጪ በቅርብ ልናገኛት አልቻልንም በሁላችንም እእምሮ ግን አንድ ነገር ሲብሰለሰል ቆየ ይህን ዲታ ሱዳናዊ ከመቼው በእጇ አስገባችው? እንዴት ነገሮች በዚ ፍጥነት ተለወጡ?ምኗ ማረከው?ምን አስነካችው?

መልሱን ያገኘሁት ከውቢት ነው።

እሷ እንደነገረችኝ ሰውየው አዲስ አበባ
በየጊዜው ለመዝናናት ይመጣል። ሀበሻ ሴት ደግሞ ነፍሱ ነው። ግን
ወሸላው ኢይቆምለትም። ለብዙ ዓመታት ተሰቃይቷል አይቆምለትም!

ዝም ብሎ ይዞሸ ይገባና ደባብሺኝ፣ ንከሺኝ፣ ቦጫጭሪኝ ብሎሽ ስሜቱ ሲመጣ በሱዳኛ እየጮኸ እየቀበጣጠረ ቂጥሽን ንክስ ያረግሽና ስሜቱን ይጨርሳል ስለነከሰሽ ብቻ ሞቅ ያለ ብር ይሰጥሻል።ታድያ ዝኑን እንደለመደው ሊነክሳት ሲል ወሸላውን ጭምቅ አድርጋ ይዛው አይኗን ጨፍና ትጮሃለች ይሄኔ ያልተጠበቀ ተዓምር ተፈጠረ ሰውየው ወሸላው ቆመለት ይታይሽ ከ 30 ምናምን ዓመት በኋላ ዘንድሮ Liverpool ዋንጫ እንደበላው ማለት ነው
የሱም ከ30 ዓመት በኋላ ነው ይሄ የሆነለት። በደስታ ሰከረ ደጋገሙት። ቁላው ሰራለት። ዝናሽ ይህን ያረገችው በመተት ይሁን ባጋጣሚ ግን የማውቅልሽ ነገር የለም ብቻ ስውየው በደስታ አለቀሰ። ሁለቱም ራቁታቸውን እያሉ እዛው አንደር ግራውንድ ቤት እግሯሥር ተንበርክኮ ለመናት፤ እንድታገባው እግኝታ ነው!! “ባንዳፍ
አለችው። ቁላው እንደቆመ በደስታ የሚያደርገውን አሳጥቶት፤ እስኪነጋ እንኳ መጠበቅ አቅቶት ያንኑ ምሽት በነጭ ማርቼዲስ ይዟት በረረ ወጀ ሳር ቤት።

“ ሮዝ! ይሄንንም ወሬ ብለሽ ልትጽፊው እንዳይሆን ደግም…”

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍5
ሴት ገነትን አትወርስም፡ንሰሀ ግቡ!ከዚህ ውጉዝና ቆሻሻ ህይወት ዛሬውኑ ውጡ!” ብሎ
የይምሰል መንፈሳዊነቱን በአደባባይ ሊያሳይ ይፈልጋል። አስቹ You tube ላይ በተለቀቀ አንድ ስብከቱ
"እውነተኛ ህይወት ያለው በሰማይ ቤት ነው” ሲል ቢታይም የሱ ቤት ግን ክለብ አሪዞና እንደሆነ ነው የምናውቀው፡፡ በክለብ አሪዞና መኪናና ቆነጃጅትን እንደ ሸሚዝ ሲቀያይር ነው የምናየው፤ ያማረውንና ያሻውን መጠጥ አስወርዶ በውስኪ ሲራጭ ነው የምናውቀው።

መምህር አስቹ ወደ ክለብ አሪዞና ሲመጣ ዘወትር እንደሚያደርገው ማንነቱ ለመቀየር ይታትራል።
የምታምር ሰማያዊ ስካርፍና ትልቅ መነጽር አድርጎ ነው የሚመጣው። እኛ ሁላችንም የክለብ አሪዞና ሴቶች ለይተን እናውቀዋለን። ከሱ ጋር ሾርት አዘውትራ የምትወጣው ግን ዉቢት ናት። አስቹ መጥቷል ስንላት እስቲ ሾርትና ንስሀ ገብቼ ልምጣ” ትለናለች። እንስቃለን፡፡

ሁልጊዜም ጋብዞን ነው የሚለየን። ንግግር ሲችልበት ለጉድ ነው። ሲያወራ አፍ ያስከፍታል። አማርኛው እንዴት ስክትክት እንደሚልለት ግርም ነው የሚለኝ። በከተማው አንድ ጥግ መሬት ገዝቶ የሚያምር ቪላ እያስገነባ እንደሆነ በአንድ አጋጣሚ አጫውቶኛል። ህይወት በሰማይ ቤት ነው እያለ ምድር ላይ
ቪላውን ያጣድፈዋል። መቼስ መምህር አስቹ ከፀደቀ እኛም ለመጽደቅ ተስፋ አለን ማለት ነው።

ግን አስቹን በምን አስታወስኩት? የሜርሲ ባል የገዝሽ ተለዋዋጭ ጠባይ ነው መምህር አስቻለውን

ያስታወሰኝ።መቼም ይቺ ፌክ አለምና ይህ ህይወት የማያሳየን ጉድ የለም።

ከፍሪጅ በረዶ አውጥቼ የሜርሲን የፊት እብጠቶቸ ነካካሁ። ፊቷን እያሻሸሁላትም መዛቷን አላቆመችም ከዚህ በኋላ አብራው እንደማትቀጥል ትምላለች።ነገር ግን ገዝሽ አብራው ካልሆነች በሽጉጥ ግንባሯን ሊያፈርሰው እንደሚቻል ትሰጋለች። ሜርሲ እንደምትለው የድሮ ቦይፍሬንዷ ሄኖክ “ለገና እንኳን አደረሰሽ የሚል መልእክት ልኮላት ገዝሽ ስልኳን ሲበረብር ይሄንኑ ሜሴጅ በማግኘቱ ነበር እንዲህ መቶ ንብ የነደፋት እስክትመስል የደበደባት።የፊት እብጠቶቿን በበረዶ እያሸሁላት ድንገት በሀሳብ ነጎድኩ። ሜርሲ እያወራችኝ እኔ ግን እንዴት እንደተዋወቁ፣ እንዴት እንደተጋቡ በማሰብ ተጠምጄ ነበር የሜርሲን በምስል የተደገፉ የህይወት ገፆች እየገለጥኩ ማሰብ ጀመርኩ...

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍1
የሰርጉ መርሀ ግብር እንደሚጠናቀቅ አወጀ፤
“.ከቡራትና ክቡራን -የፕሮግራማችን የመጨረሻ ሰአት ላይ ደርሰናል፤ አንድ ፕሮግራም ብቻ ነው የሚቀረን። there is a surprise guest አንድ ልዩ እንግዳ አለን.አንድ እጅግ የምትወዱት ልዩ እንግዳ አለን። ይህ የምንወደው፣ የምናደንቀውና የምናከብረው፣ እንደ አይናችን ብሌን የምንሳሳለት
እንቁ ወጣት አርቲስት በአጋጣሚ የሙሽራችን የገዝሽ አብሮ አደግና ቀዳሚ ሚዜ የልብ ወዳጅ ነው።አርቲስቱ የልብ ወዳጁን ጥሪ አክብሮ ከግማሽ ሰአት በፊት እዚህ ከመሀላችን ተገኝቷል። ይህ የአገራችን ቁጥር አንድ አርቲስት እዚህ መገኘትም ብቻ ሳይሆን ሙሽሮቹንና እንግዶቻቸውን ለማስደሰት ሁለት
የሰርግ ዘፈኖችን ሊያቀርብ ቃል ገብቷል። ሰርፕራይዝ ገስት ስለሆነ አሁን ስሙን አልነግራችሁም። ታውቁታላችሁ”

ከአፍታ በኋላ ልዩ እንግዳው ገና መድረኩን እንደረገጠ ሙሉ ታዳሚው ሆ ብሎ ተነሳ። አንድም ታዳሚ ከወንበሩ ያልተነሳ አልነበረም። ሁሉም ሰው ይህን ተወዳጅ አርቲስት ከበበው።

አስገራሚው ነገር የተፈጠረው ይሄኔ ነው። ሜርሲ የዘፋኙን ማንነት ስታይ ብድግ ብላ ወንበሯን ለቃ የስርግ ዘፈን ወደሚያቀርበው አርቲስት ቬሎዋን እየጎተተች በጥድፊያ ተመመች። ከምኔው ከአርቲስቱ
አጠገብ እንደተገኘች እግዜር ነው የሚውቅም። የሚገርመው አርቲስቱ ሁለቱንም የሰርግ ዘፈኖች ሲያቀርብ ከጎኑ አልተለየችውም ባሏን መፈጠሩንም ረስተዋለች።

በእውነቱ የሙሽራውን በጥልቅ የብቸኝነት፣ የሀዘንና የብስጭት ስሜት ከፉኛ የጨፈግግ ፊት ዞር ብሎ ያየ ማንም አልነበረም። አዳሜ በታዋቂው ዘፋኝ ዙርያ ይራኮታል። ከተቀመጠበት ወንበር ላይ
እንደሚስማር ተቸንክሮ የቀረው ሙሽራው ብቻ ነበር። ሙሽሪት ሜርሲ አርቲስቱ ሁለት የሰርግ ዘፈኖቹን ካቀረቡ በኋላም ወደ ቦታዋ አልተመለሰችም። አብራው የማስታወሻ ፎቶዎችን ለመነሳት
ከካሜራ ማኑ ፊት ተገተረች ሁሉም የሰርጉ ታዳሚ ከአርቲስቱ ጋ የማስታወሻ ፎቶ ለመነሳት ቋምጦ ይጠብቃል። ሙሽሪት ግን እርቲስቱን የሙጥኝ ብላ ቀረች። ሙሽራው ገዝሽ ከመንበሩ ላይ ለብቻው እንደተቀመጠ ተክዟል። በህይወቴ እንደዛ አይነት የእልህና የንዴት፣ የሀፍረት፣ የብስጭትና የበቀል
ስሜትን በአንድ ላይ ያቋረ ኮስታራና ጨፍጋጋ ፊት ተመልክቼ አላውቅም፡፡

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
1👍1
የምቀበል
ሸርሙጣ ስሆን እነሱ ትዳር መስርተው ወልደውና ከብደው የክብር ህይወትን ይመራሉ። በዚያ ቢያቆም ጥሩ ነበር። ዘመዶቼና ጓደኞቼ በሆቴሎች፣ በክለቦችና በሌሎች ስፍራዎች ከነጭ ሴቶች ጋ
ሲያግኙን የማያሳምን ሰበብ ፈጥሮ መዋሸቱ ታከተኝ። አዲሳባ እንደምናስበው ሰፊ አይደለችም፤ ጥቂት የመዝናኛ ስፍራዎች ስላሉ በሄድሽበት ሁሉ የምታውቂያቸውን ሰዎች ማግኘትሽ አይቀርም። አንድ እለት ከአባቴ ባልተናነሰ በድሃ አቅሙ ያሳደገኝ አጎቴ ከጨርጫሳ ጀርመናዊት አሮጊት ጋ ሂልተን የዉሃ
ና ፍል ዉስጥ አገኘኝ። አጎቴ ሀብታም ነጋዴ ሆኗል። እኔም ጀርመናዊቷም በዋና ልብስ ብቻ ዉሀ ዉስጥ እየተንቦራጨቅን ነበር። ያን እለት መሬት ተሰንጥቃ ብትውጠኝ ወይም እዚያው ዉሀ ዉስጥ
ሰምጬ ብቀር ደስተኛ ነበርኩ። አየሽ ሮዚ! በሕይወታችን ደስታ የሚሰጡ የሚመስሉን ነገሮች ፍጹም ደስታ የሚያርቁን ናቸው፤ እኔ ሲኒማራስ በያይነቱና ሽሮ በልቼ ስውል የነበረኝ ደስታ ከኡስማን ያን ሁሉ ዶላር እያፈስኩ ከማገኘው ደስታ የበለጠ ነበረ። ፈጣሪ በማይወደው ስራ ዉስጥ እስካለሽ ድረስ
ህሊናሽ እንደመርፌ እየወጋ ሰላምሸን ይነሳሻል…”

ድንገት የኤርሚን ፊት ትካዜ ወረሰው፤ ለአፍታ በመካከላችን ዝምታ ሰፈነ። ዝምታውን መስበር ፈለግኩና አፌ ያመጣልኝን ጥያቄ ጠየቅኩት፤

"አጎትህ ሲያገኙህ ግን ምን አሉህ?"

ኤርሚ ባልጠበኩት ሁኔታ በቁጣ አፈጠጠብኝ፤

“ቆይ እኔ የምለው ሮዝ፤ ለምንድነው ጥያቄ የምታበዢብኝ?የሕይወቴን ሲሶ ከሴት ጋር ነው ያሳለፍኩት ያንቺን ያህል የምትጠይቅ ሴት አላየሁም።በፈጠረሽ ጥያቄ አታብዥብኝ ጥያቄ አልወድም በተጠየቁ ቁጥር ለፍረድ የቀረብኩ ይመስለኛል ህሊናዬ የሚጠይቀኝ አንሶ ደግሞ አንቺ..."

ክው ብዬ ቀረሁ። በሰላም እያወራኝ ድንገት ሲቆጣኝ ቀልቤን ገፈፈው፡፡ በሌላ እንዳይጠረጥረኝ ብዬ ዝምታን መረጥኩ፡ከአፍታ በኋላ የጨዋታ ርእሱን ቀየርከት። በራሱ ጊዜ ካላወራ ምንም ጥያቄ ላለማንሳት ወሰንኩ።ከብዙ ዚጠጥና ጨዋታዎች በኋላ ጥቂት የመቆስቆሻ ሀሳብ ሳቀርብለት ሳያስበው ምክንያቱን መናገር ጀመረ።

“በየሆቴሉ፣በየክለቡናበየመዝናኛስፍራው ከነጮቹ ጋ ሆኜ የማገኘው የቅርብ ሰው ሲበዛብኝ ከአዲሳባ ርቄ መሄድ እንዳለብኝ ተሰማኝ። ከቱሪስቶቹ ጋ ሆኜ የማገኛቸው ጓደኞቼና ዘመዶቼ ሁሉ ስራዬን የሚያውቁብኝ እየመሰለኝ በሀፍረት ልቀውስ ደረስኩ። ከፈረንጆቹ ጋ በመንገድ ላይ ስሄድ ለደቂቃዎች
የሚያፈጥብኝ ሁሉ ሸርሙጣነቴን ጠንቅቆ የሚያውቅ ያህል ተሰማኝ። በጣም ተጠራጣሪ ሆንኩ።
አዲሳባ መኖር የጀመሩት 2ቱ ታናናሽ እህቶቼ ስራዬን ሲያውቁ የሚሰማቸውን አስቤ ተረበሽኩ፣እንቅልፍ አጣሁ። ማንም የማያውቀኝ ሩቅ አገር መሄድ እንዳለብኝ ወሰንኩ። በዚህ መብሰልሰል መሀል ነበር ኑኑሻ ወደ አእምሮዬ የመጣቸው። ዱባይ አብረን እንድንኖር ብዙ ጊዜ ትወተውተኝ ነበር። ኑኑሻ በጣም እንደምትወደኝ አውቃለሁ፥ ሮዝ ሙች! በጣም ነው የምታፈቅረኝ። ከሷ ጋ የነበረኝን ግንኙነት
አለመቁረጤ ጠቀመኝ። ከዚያ ሁሉ ጊዜ በኋላ ደውዬ ሳገኛት ፊትዋን አላዞረችብኝም። የሌት ተቀን ሀሳቤ በተገኘው አጋጣሚ አዲሳባና ኢትዮጲያን መልቀቅ ነበር። ተሳካልኝ፤ ከዚያም በየሰከንዱ ህሊናዬን ክፉኛ ከሚቀጠቅጠኝና ቀና ብዬ እንዳልሄድ ካደረገኝ ቆሻሻ ህይወት ወጣሁ፤ አሁን የኑኑሻን ንግድ በበላይነት የማስተዳድር የቢዝነስ ሰው ሆኛለሁ…” ካለኝ በኋላ በረዥሙ ተነፈሰ። ዝም ተባባልን።

“..ይቅርታ ግን እሺ፤ሮዝ

“ለምኑ?”

ቅድም ሳላስበው ጮህኩብሽ መሰለኝ?”

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍21
ሸት

ጥገኝነት ያገኙ ነበር። አሁን ግን ያ ቀርቷል። ማኅበራቸው ነው የሚመሰክርላቸው። እና እሌኒ መኪናው የተሰጣት ከዚህ ማኅበር ነው። የመኪናዋ ቀለም ራሱ የቀስተደመና አይነት ናት። ለቡሽቲዎቹ ወንዶችን አማልላ በየቀኑ
እንድታመጣላቸው ይቺን መኪና አውሰዋታል። ለአገልግሎቷ ወፈር ያለ ክፍያ እንደሚፈጽሙላት

መረጃ አግኝተናል ነው ያለኝ ሀገዞም..."

እነኑ ደግሞ በየቀኑ የሚያገኟቸውን ወንዶች በአልኮል እስክረውና በመጠጥ ውስጥ የእንቅልፍ ኪኒን

መሲ እውነቷን ሳይሆን አይቀርም፡፡ የጠቀሰቸወም ክለብ ዉስጥ ሰዶሞች እንደሚበዙ አውቃለሁ።እነሱ ደሞ በየቀኑ የሚያገኟቸውን ወንዶች በአልኮል አስክረውና በመጠጥ ውስጥ የእንቅልፍ ኪኒን ጨምረው በማደንዘዝ ብዙ ወንድ ማጥመድ አይችሉም። ሁል ጊዜ በዚህ መንገድ የሚወስዷቸውን ሰለባዎች አያገኙም።እሌኒ ግን በሴትነቷ ተጠቅማና አማልላ በየቀኑ እነሱ ካሉበት ቤት ድረስ ለዚህ ተግባር በሰጧት መኪና ታቀርብላቸዋለች። መሲ እንደምትለው እሌኒ መኪና ይዛ ሲያዩ ወንዶች
በፍጹም አይጠረጥሯትም። ወንድ የጠማት ሀብታም ሴት ትመስላቸውና ሰተት ብለው ይገቡላታል። ይህንን በመረዳት ነው ቡሽቲዎቹ መኪና በሚስጢር ማሀበራቸው ስም ገዝተው በውሰት የሰጧት።

እሌኒን አምርሬ ጠላኋት። የሆነ ወቅት ላይ ከዚህች የሰይጣን ቁራጭ ጋር አብሬ መስራቴን ሳስብ ዘገነነችኝ። ሰው ሲባል ግን እንዴት አይነት ጨካኝ ፍጡር እንደሆነ….አሁን እሌኒ እዚህ ሁሉ ልቦለድ የሚመስል ወንጀል ውስጥ ትገባለች ብሎ ማን ያምናል?

መሲን ጠየኳት።ቆይ ግን ባልሽ ሀገዞም ይህን ሁሉ እያወቀ ለምንድን ነው እርምጃ የማይወስድባት?

“ሮዝ! እኔም ጠይቄው ነበር፤ ምን እንዳለኝ ታውቂያለሽ? መጀመርያ ሳቀብኝና…የዋህ ስለሆንሽ እኮ
ነው የምወድሽ ብሎ ከንፈሬን ከነከሰኝ በኋላ «ወንጀል ክትትል ዉስጥ አንድን ተጠርጣሪ አንድ ወንጀል ስለፈፀመ ብቻ ተንደርድሮ መያዝ ብዙ ዱካዎችን እንደማጥፋት ይቆጠራል እንደምታስቢውም ቀላል አደለም እዚህ ድርጅት ውስጥ ከተራ ሰው ጀምሮ ትላልቅ ባለስልጣናት አጅ አለበት በየቲቪው በከረባት ታንቆ የምናየው ባለስልጣን የማታ ማታ መዳርያቸው ነው አንድም ቡሽቲነትን ከሚያስፋፉት ሰዎች እነሱ በዋነኝነት ይጠቀሳሉ እንጂማ እሌኒን ገና ድሮ ከሁለቱ ከፖሊሶች ጋር የምትፈጽመውን ወንጀል እንደደረስንበት በቁጥጥር ስር አውለናት ቢሆን ኖሮ
ከሰዶማዊያኑ ጋር ስለነበራት ግንኙነት ምንም ማወቅ አንችልም ነበር። አሁንም በሷ ላይ ለጥቂት ወራት ክትትሉ ይቀጥላል። ጊዜው ሲደርስ እሌኒም፣ ሁለቱ ፖሊሶችም፣ የምታገለግላቸው ሰዶማውያኑም ከነማኅበራቸው ተለቃቅመው እስር ቤት ይገባሉ፤ ባለቀስተደመናዋ ቶዮታ ቪትዝም ለመንግስት ገቢ ትደረጋለች።››

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍41
ወፈፌ ይመስል ነበር።በየተራ አፈጠጠብን፤

“እስቲ ንገሩኝ! እዚህ ሰፈር ውስጥ ምን አይነት ድግምት ነው የተደረገብኝ? ሺ ጊዜ ሰፈሩን በድጋሚ ላለመርገጥ ምዬ ብገዘትም አክለፍልፎ የሚያመጣኝ አዚም አለ። ምንድነው ያረጋቸሁብኝ? ምን
አይነት አፍዝ አደንግዝ ነው የነሰነሳችሁብኝ? ብሌን ምንም ሳትደብቂ ንገሪኝ የምትለማመኚው ቃል።
፣ ጠንቋይ ፣ ሼክ ወይም ቆሪጥ በኔ ላይ ምን እንድታደርጊ ነው ያዘዘሽ? ያው ባንቺ ቤት ስንት ዘመኔ ሌሎች የሰፈሩ ቡና ቤቶችና ፐቦች ጋ ቆይቼ አንቺ ቤት ነው ሁሌም የማሳርገው። ያንቺን ቤት ሳልሳለም ይህን ኩሻንኩሽ ሰፈር የተለየሁበት ጊዜ የለም። ይህን አንቺም አሳምረሽ ታውቂዋለሽ ስለዚህ የዚህ ሰፈር ሴቶች በኔ ላይ ምን እንዳደረጋችሁብን ሳትደብቂ ንገሪኝ ብሌን አንቺን ነው የማናግርሽ"

የሆነ ማይም ቲያትር የሚሰራ መሰለኝ። ፍቅሮቭስኪ አመልካች ጣቱን ብሌን ላይ ቀስሮ ረዘም ላለ ቅፅበት አፈጠጠባት።ብሌን አልፈራችውም ።እንዲህ እያማረረ ይህው ስንት አመቱ።ችላ ግን አላለችውም።ልታረጋጋው ሞከረች፣

“ምነው ፍቅሮቭስኪ….ምን ሆንክብኝ…ኧረ እኔ ካልካቸው ቦታዎች አንዱም ጋ ሄጄ አላውቅም፤ወላዲት አምላክን እኔ እንዲህ አይነት ልማድ የለኝም"

-ፍቅሮሽስኪ አሁንም እይኖቹን ከብሌን ላይ አልነቀለም፤

“ቀጣፊ ሸርሙጣ ነሽ፤ በመጀመሪያ አላመንኩትም እንጂ ሰናይ ሁሌም ቤትሸን ምሸት ላይ ልትከፍቺ ስትይ አዶ ከርቤ እንደምታጨሺና አውሊያሽን እንደምትለማመኚ ብዙ ጊዜ ነግሮኛል። እሱም በስንት ጸበል ነው ከዚህ ስፈር የተነቀለው።እምቢ አልኩት እንጂ ጻድቃኔ ማርያም አብሬው ጸበል እንድጠመቅ በተደጋጋሚ ወትውቶኝ ነበር።”

ፍቅሮቭስኪ እንደገና ባለጌው ወንበር ላይ ተቀምጦ ባንኮኒውን በቡጢው መድቃት ጀመረ፤ አይፎኑን በንዴት ወርውሮ ከአንዱ ግድግዳ ጋር አላተመው፤ ፊቱን በድጋሚ ወደኛ አዞረ። ደም ስሮቹ በቀይ ፊቱ ላይ ተገታትረው

በጉልህ ይታያሉ፤ይህን ጊዜ ሶስታችንም በድንጋጤ ደርቀን ቀረን።

"ወይዘሪት ብሌን! እያወቅሽ አትደብቂኝ፣ ይሄ ድግምታምና መተተኛ ሰፈር ምን አድርጎብኝ ነው ለዘመናት የሰፈሩ ቋሚ እስረኛ ያደረገኝ?! የቢዝነስ አጋሮቼ አርብና ቅዳሜን ሸራተን በጋዝላይት፣
በዱባይና በባንኮክ እየተዝናናን እንድናሳልፍ ለዘመናት በየሳምንቱ ሲወተውቱኝ አንድም ጊዜ እንኳን
ግብዣቸውን ሳልቀበል እዚህ ሰፈር ኩሽና በሚያካክሉ ቤቶች እንድልከሰከስ የሚያደርገኝ ድግምት ምንድን ነው? ብሌን ምንም ቢሆን የዘመናት ደምበኛሽ ነኝ፤ በፈጠረሽ ሚስጥሩን ንገሪኝ!”

ፍቅሮቭስኪ ከተቀመጠበት የባለጌ ወንበር ላይ ተነሳ፤ ሊረጋጋና ሊሰክን አልቻለም፤ ጥቂት የመቶ ብር
ኖቶችን ከቆጠረ በኋላ ባንኮኒው ላይ ወረወረ። ፊቱን ወደ ብሌን መለሰ፤
ብሌን ካንቺ ጋ እኮ ነው የማወራው ለምን እትመልሺልኝም? አልቀየምሽም እውነቱን ብቻ ንገሪኝ ይሄ ሰፈሩን ለመጨረሻ ጊዜ የምረግጥበት ሌሊት ነው። ከነገ ጀምሮ እንደ ሰናይ ለተወሰኑ ቀናት ጸበል
ለመግባት ቁርጥ ውሳኔ ወስኛለሁ። ስለዚህ አትፍሪ በግልጽ የምታውቂውን ንገሪኝ! ለምንድነው የዚህ ሰፈር ባርያና ምርኮኛ የሆንኩት? የትኛው ደብተራ ጋ ነው ያስደገማችሁብኝ? አርብ፣ ቅዳሜና
እሁድ ቤቴን፤ ሚስቴንና ልጆቼን እንድጠላና ከቤት ጥፋ ጥፋ የሚል ምን አይነት መስተባርር ነው ያረጋችሁብኝ? የትኛው ደብተራ ጋ ሄዳችሁስ ነው ለዘመናት ከዚህ ስፈር ጋ በፍቅር እንድወድቅ ያደረገ ማስተፋቅር ያሰራችሁብኝ? የቀራችሁ እኔን በድግምት ማሳበድ ብቻ ነው፡፡ ምኔ ሞኝ ነው!መስተአድርት አሰርታችሁ ሳታሳብዱኝ ነገ ጸበል እገባለሁ። መጥኔ ለናንተ! እኔስ በቃኝ…በቃኝ አልኩ።

ፍቅርቭስኪ ኮቱንና አይፎኑን ጥሎ ውጪ ወዳቆማት ቡናማ ፕራዶ መኪናው አመራ። ብሌን ኮቱንና ስልኩን ይዛ ወደ መኪናው ሄደች። ከአፍታ በኋላ ስጥታው ተመለሰች።

ብሴን በየተራ ተመልክታን ፈገግታውን ብልጭ አደረገች፤

“ፍቅሮቭስኪ በውሳኔው ከጸና ቺቺንያዊ የከብር ዜግነቱን በነገው እለት እንገፈዋለን።" በረዥሙ ሳቀች።

“በቃ ቤቱን ዘጋግተን ወደኔ ቤት እንሂድ። ጉዞ ወደ ብሌን ኮንዶሚኒየም ዳይ ዳይ….” በድጋሚ ሳቀች እኔ ግን ድንጋጤው አለቀቀኝም ነበር።

ሮዚ ደሞ፤ ፍቅሮቭስኪው ታውቂው የለ? ሁልጊዜም እንደዛተ ነው እኮ ሙዳችንን ሰለበው አይደል ይሄ ሰላቢ…ኑ ባካችሁ ቤት ሄደን የሆድ የሆዳችንን እንጫወት…"
ብሌን በራሷ ንግግር ፐቧ እስክትነቃነቅ በሳቅ አስካካች።ፍቅሮቭስኪ በተናገራት ነገር ዉስጥ ዉስጡን ተብከንከናለች ማለት ነው። የንዴት ሳቅ እንደሆነ ያስታውቅባት ነበር።

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍2
ር ምን መሰለሽ? እኚህ ኣዘውንት ሳቢ ላይ ፈታ ያሉ ናቸው ከላይ ከጠቀስኳቸው ትእዛዞቻቸው አንዱን ባሟላሁ ቁጥር 850 ብር ይለቁብኛል። ከፍያቸው ከዚህ ጨምሮም ቀንሶም
አያውቅም። እኚህ አዛውንት ለምንድነው ወሲብ የማይፈጽሙት? እያልኩ አስብ ነበር፡፡ ይህ ጥያቄ ለረጀም ጊዜ አዛውንቱን ባየሁ ቁጥር ሲያብሰለሰለኝ ቆይቷል አንድ ቀን የመጣ ይምጣ በሚል ጠየቅኳቸው።

በጥያቄዬ ምንም እልተገረሙም፡-

"ውይ የኔ ልጅ! ምን ነክቶሻል! እግዜሩስ ምን ይለኛል?! ከእግዜሩ መጣላት አልፈልግም። ስድስት
ለወግ ማእረግ የበቁ ልጆችን የሰጠችኝና ከቤት የማትወጣ ታማኝ ሚስት አለችኝ። አርባኛ አመት የትዳር ጥምረታችንን ልጆቻችንና ዘመድ አዝማድ በተገኙበት በድምቀት ድል ባለ ድግስ ዘከረናል።
በአክሊል ነው የተጋባነው። ቃል ኪዳኔን አፍርሼ ከሌላ ሴት ጋር ሩካቤ ስጋ ብፈጽም የእግዜሩን ቁጣና እርግማን እፈራለሁ። በንጹህዋ ሚስቴ ላይ ያን አይነት ውስልትና መሞከር ተይውና በፍጹም አላስበውም”

#የፓንት_ፖለቲካ


አንድ ቅዳሜ ከሰአት ከሲሳይ ራስተረ ጋር "ፒኮክ" መኪና ውስጥ ቁጭ ብለን አፕሬቲቭ እየጠጣን አንድ ካልሲ አዟሪ መጣ።ሲስ ሎተሪ ሻጭ፣ማስቲካ አዟሪ ኮንደም ቸርቻሪ ጋር ማውራት ሲወድ።"ምን ይሰራልሃል"ለምን ታደርቃቸዋለሁ፣ሰርተው ይብሉበት እንጂ" ስለው“ሮዚና ምን መሰለሽ… የድሮ
ነገስታት “አዝማሪ ምን አለ?” ይሉ ነበር። በኛ ዘመን የሕዝብ ብሶትን ለመለካት ከነዚህ ቸርቻሪዎች የተሻለ ቴርሞ ሜትር አይኖርም።ለዚህ ነው እህ ብዬ የምሰማቸው” ብሎ ያሾፍብኛል።

ይኸው ፒኮክ ፓርኪንግ መኪናችን ውስጥ ሆነን ሲስ ከአንድ ካልሲ አዘዋሪ ቆምጬ ጋር ይዳረቃል።

“ና እስኪ ጠጋ በል!”

“አቤት ጋሼ ምን ላሳይዎት፤ ካልሲ ላሳይዎት? ሸጋ ሸጋ ካልሲዎች አሉኝ.ፓንቶችም አሉኝ

“የየት አገር ልጅ ነህ”

“ማ! እኔ

ታዲያ ሌላ ሰው አለ እንዴ?

“ጎዣም"

“ባህር ዳር ነው?

እይ ከባህር ዳር እንኳ ትንሽ ወጣ ትላለች፣ ፍኖተ ሰላምን ያውቋታል ጋሼ”

“አላውቃትም፤ ስስም ነው የማውቃት፤ አንተ ባህርዳርን ታውቃታለህ?”

አዎ እንዴት አላውቃት ጌታው! አንድ ሁለት ጊዜ ሄጃለሁ፤ ሸጋ አገር ናት”

እኔ ምልህ! የዛ አገር ሴቶች ፓንት እንደማያደርጉ ታውቃለህ?”

ኧረ ጌታው እኔ በምን አውቄ፣ ገልጠው አያሳዩኝ ነገር." ልጁ ራሱ በተናገረው ነገር ሳቀ።

“ቆይ እሺ እዛ አገር ሴቶች ፓንት ገዝተውህ ያውቃሉ?”

ኧረ ጌታው እኔ እዛ አልነገድኩም፣ ኧረግ የሚያውቁኝ ዘመዶች አሉኝ እያልከዎ፤ ቤተሰቤን ለምን አዋርዳለሁ ጌታው?”

“ሥራ አይደለም እንዴ? ምን ችግር አለው?”

“ኧረግ ችግርማ ቢኖረው እይ እዚያ ማልነግድ፤ ምን ብዬ ነው በአገሬ ሙታንታ ምቸረችር? ምንስ ቢቸግር…”

“ለማንኛውም ጎዣም ብዙ ሴቶች ፓንት ማድረግ ትተዋል፤ ይሄን ታውቃለህ?

ኧረ እኔ አላውቅም? ግና ምነው አሉ ጌታው?”

“በል እንግዲያውስ እኔ ልንገርህ፤ ቅንጅት የተሸነፈ ጊዜ ነው የጎዣም ወጣት ወንድነቱ የተሸነፈ፣ ከ97 በኋላ ለፖለቲካም ለሴትም ያለው ስሜቱ አብሮ ነው የሞተ። ከዚያን ቀን ጀምሮ በከተማው አንሶላ የተጋፈፈ የለም ነው የሚባል።”

“እሱስ እውነት ነው ጌታው፤”
“ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጫት በባህርዳር ከድሬዳዋ ባልተናነሰ ይቃማል። ይሄን ታውቃለህ?

“ልክ ነው ጌታው"

"ታዲያ ሴቶቹን ማን ዞር ብሎ ይያቸው፤”

"አህ! ኧረ እኔን አያናግሩኝ ጌታው! እኔ የነሱን ጉዳይ የት አውቄ!"

እወቃ ካላወቅክ፤ እየነገርኩህ አይደል? እንድታውቅ እኮ ነው የምነግርህ። አሁን አንዲት የጎዣም ሴት አግኝተህ ብትጠይቃት ትነግርሀለች። ፓንት አታደርግም። ከአገሩ ጉብል ይልቅ የብስክሌት ኮርቻ የተሻለ ያስደስታታል። ከ97 በኋላ ብስክሌት ላይ መፈናጠጥ የተሻለ ሆኗል ይሉሀል። ሳትደብቅ
ትነግርሃለች።”

“ኧረ ጉደኛ ኖት ጋሼ! ዉስጠ-ወይራ ነው የሚናገሩ ጋሼ! ኧረግኝ! ተናግረው አያናግሩኝ ጌታው!”

“አሁን ግን ገባህ? ለምን ፓንት እንደማያደርጉ?”

አንገቱን በአዎንታ ነቀነቀና ዙርያ ገባውን መቃኘት ጀመረ።

አየህ ይሄ መንግስት ስንቱን ጉድ እንዳረገ! ስንቱን ያለ ፓንት እንዳስቀረ… "

ኧረ ጌታው እኔን ፖለቲካ አያናግሩኝ፣ ፓንት የሚገዙኝ ከሆነ ይግዙኝ."
ሲሳይ ሳቁ መጥቶበት እንደምንም ተቆጣጠረውና…።

እሺ ለሷ የሚሆን ሸጋ ፓንት አለህ? ሚስቴ ናት! እንደምታየው ቂጧ ትልቅ ነው፤ ከፈለክ እዚሁ ትለካዋለች።” አለው ወደኔ እያመላከተው።

“ልጁ አፍሮ አቀረቀረና ኧረ ጌታው የሴት ፓንት አልይዝም፣ እነሱ ባደባባይ መች ይገዙንና!”

“ግን እንዲሁ ስታያት አሁን ፓንት ያረገች ይመስለሃል? ገምት እስቲ”
ልጁ ሙሉ በሙሉ አፍሮ መሽኮርመም ጀመረ። ቀና ብሎ እኔን ማየት እንኳ አልቻለም።

ሁላችንም ሳቅን።

እሺ የወንድ ፓንት አለህ?ለኔ የሚኾን?”

“ሞልቶ ጌታው፣ ይኸው ይምረጡ!” ከፌስታሉ እያወጣ የፓንት መዓት ዘረገፈለት።

ለምን እንደሆነ አላውቅም የወንድ ፓንት ዉስጤ የሆነ የሚዝለገለግ ነገር ያለው ስለሚመስለኝ ተዘርግፎ ሳየው ይቀፈኛል።

አንተ እውነት ከጎጃም ነኝ የምትል ከኾነ ይሄን ጥያቄ መልስና ነው የምገዛህ”

እሺ ይጠይቁኝ ጌታው፤ ፖለቲካ ካልሆነ ምን ገዶኝ!”

“ኖ! ኖ! ፖለቲካ አይደለም። የአማርኛ ጥያቄ ነው የምጠይቅህ! ፓንት በአማርኛ ምንድነው የሚባል?”
እኛ እንግዲህ ሙታንታ ነው የምንል። አዋቂ ስንሆን ነው እይ ልጅ ሆነንማ ማን አስታጥቆን ጌታው”

“ሙታንታ አይደለም፤ ተሳስተኻል”
እና ምንድነው ጋሼ? ካወቁት እርስዎ ይንገሩና"

«ማኅደረ ቆለጥ» ነው የሚባል”
ልጁ የያዘውን ፌስታል ጥሎ በሳቅ ወደቀ፤ እኔም ሳቄን መቆጣጠር አልቻልኩም። ሲስም እኛን አጅቦ
ሳቀ።

ግማሽ ደርዘን ካልሲ ገዝቶ፣ በተጨማሪም 10 ብር ሸልሞ ሸኘው። በደስታ እየተፍለቀለቀ ጉዞ ሲጀምር
ሲስ እንደገና ጠርቶት ወደሱ ሲዞር በሩቁ የ "V" ምልከት አሳየው። ልጁም ጣቱን ሸሸግ አድርጎ ምላሽ ሰጠ።

ልጁ ሥራ ከጀመረ እንደዚህ ተደስቶ የሚያውቅ አይመስለኝም።


💫ይቀጥላል💫

#ሮዛ_2 ነገ ይጠናቀቃል ሌላ አዲስ ረጅም ድርሰት እንድንጀምር ገንቢም ይሁን የትችት አስተያየታችሁን ስጡን ማስተካከል ያለብንን እናስተካክላለን መልካም ጎናችንንም እናዳብራለን ከዛሬ ጀምሮ አስተያየት እየሰጣቹ መስጠጠት ካልቻላችሁ 👍 እየተጫናቹ።

Like 👍 እና #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍51