አትሮኖስ
283K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
501 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ምድር ቤት ያስቀብራል እየተባለ ስለሚታማ ሀሜቱ ተጠናክሮ ቀጠለ። “ጥቁር ሴት ቅጠር ተብሎ በአውሊያ ተነግሮት ነው” ተባለ። “እህቱ ናት” ይሉ የነበሩ ሰዎች የሴት ቢዝነስ ሊያሰራት እንደሆነ ሲያውቁ አፋቸውን ዘጉ።

ደሜ ገንዘብ ያገኘው በመተት እንዳልሆነ አውቃለሁ። አዱንያ የዘነበለት ኤርትራዊያን ሲባረሩ ነው። ቄራ አንድ ጋራዥ ዉስጥ ይሰራ ነበር። የቤቱ ባለቤት አባ አስገዶም ይባሉ ነበር። ደሜ ያኔ የቅርብ ረዳታቸው ነበር። ኤርትራዊያን ከአገር ይዉጡ ሲባል ደሜ ጋራጁን በአደራ እንዲያስተዳድር ተሰጠው።
ከቀበሌ ጋር ተሞዳምዶ እንደኾነ ነገር አድርጎ ጠቀለለው። አሁንም ድረስ “የሱ አይደለም፣ ሚኒስትር የሆኑ የአገሩ ሰውዬ ናቸው በሱ ስም አድርገው የሚሸቅሉበት” ይባላል። እኔ ግን አይመስለኝም። አንድ ሚኒስትር ምንም ቢልከሰከስ ከአንድ ጋራጅ ቤት ምን ብር ያስለቅመዋል? ደሜ ጋራጁን ሸጦ እዚ
ሮማን ሕንጻ ዉስጥ አሪዞናን ከፈተ።

አሁን ደሜ ተወደደም ተጠላ የአሪዞና ጌታ ነው። በከተማው ቁጥር አንድ የሆነ፣ በየምሽቱ ብር፡ሪያልና ዶላር የሚታተምበት ክለብ ነው በባለቤትነት የሚያንቀሳቅሰው። እንኳን እሱ እኛ ለሱ የምንሰራው እንኳ አንዳንዴ ብር በዝቶብን ያስነጥሰኛል፤የሚሰራንን ያሳጣናል። እሱም እንዲያ አድርጎት ይሆናል።ዝናሽን እየቀጠራት ያለው።

አሁን ዞሮ ዞሮ ዝናሽ ሸሌ ልትኾን ነው። ደሜ ባቀናው “ክለብ አሪዞና” ዝናሽ ቢዝነስ ልትጀምር ነው
በውነቱ ይሄን ማን ያምናል?

ዝናሽ በሂል ጫማ

እውነትም ሰው ከጣራ የትም ይደርሳል ይኽው ዝናሽ በሂል ጫማ ተራመደች ተባለ። ያን ምሽት ሂልተን ቢዝነስ ወጥቼ
ስለነበረ አሪዞና አላደርኩም፡፡ ወሬውን ስሰማ ግን ሳቅኩኝ። መጀመርያ ስትራመድ በአይኔ በብረቱ ካላየሁ አላምንም ብዬ ድርቅ አልኩ። የምሬን ነበር። በፍጹም ዝናሽ በሂል ጫማ
ስትራመድ ማሰብ አልቻልኩም። በቃ ሊመጣልኝ አልቻለም። በቃ ሊዋጥልኝ አልቻለም፡፡ ሴቱ ሁሉ የውስጥ እጄን እየጠፈጠፈ ሲምልልኝ ግን ዝናሽ እውነትም በሂል ጫማ ተራምዳ ሊኾን እንደሚችል ጠረጠርኩ። ሁኔታውን እነ ሳሪ አዳምቀው ሲነግሩኝ በጣም በስሜት ተውጠው ነበር።

መጀመርያ ሁለት የአሪዞና ጋርዶች ማለትም ተሼና ሳሚ ባሪያው በግራና በቀኟ ቆመውላት እነሱን ተደገፈች ተባለ። ከዚያም ለአንድ ደቂቃ ያህል ሚዛኗን ለመጠበቅ ሞከረችና ልቀቁኝ አለቻቸው።
እርግጠኛ ነሽ ዝናሽ” አሏት ተባለ፤ እኵል ደንግጠው። “አዎ ግን ቀስ ብላችሁ ልቀቁኝ” አለቻቸው።ተሼና ሳሚ ባሪያው ሰፈሩና ሲቸሩ ቀስ ብለው ለቀቋት።

ከሳሚ ባርያው ተላቃ ስትቆም አሪዞና ፐብ ሴቶች ቤት በቀውጢ ጭብጨባ ተናጋ አሉ።

እንደገና ዝናሽ ሚዛኗን ጠብቃ ከቆመችበት አንድ እግሯን ስታነሳ የሴቶች ቤት በጸጥታ ተዋጠ ተባለ።
ትንሽ ከተንገዳገደች በኋላ ሁለተኛ እግሯን ስታነሳ የተሰበሰበው ሴት ባለማመን አፉን ከፍቶ ቀረ።እንደዚህ አይነት የአድናቆት አፍ አከፋፈት የታየው የኒውዮርክ መንታ ሕንጻዎች ላይ ጥቃት የደረሰ ጊዜ ብቻ ነበር ተባለ። ለሦስተኛ እርምጃ ቀኝ እግሯን ስታነሳ በደስታ እምባ የተናነቃቸው የአገሯ ልጆች ነበሩ ተባለ። ነገሩን አጋነው ሲያወሩልኝና ስስቅ ከረምኩ።

ብቻ ዞሮ ዞሮ “ዝናሽ በሂል ጫማ ተራመደች።

#ዝናሽ_አገባች

ቆይ እንጂ ወደ ትዳር ዝም ብሎ አይገባም። ትዳር ቀልድ አይደለም። ትዳር ብዙ ዝግጅት የሚፈልግ ነገር መሰለኝ። ትዳር ሾርት አይደለም ዝም ብሎ የሚገባበት። ስለዚህ “ዝናሽ አገባች” ከማለቴ በፊት፣ ዝናሽ ከማግባቷ በፊት ስለነበሩ ሰባት ወራት መናገር አለብኝ። ዝናሽ በነዚህ ወራት በክለብ አሪዞና ምን
አደረገች ? መጀመርያ እሱን ልፃፍ።

To make the short story even shorter እንዲሉ ፈረንጆት ዝናሽ ብሂል ጫማ መራመድ ቀስ በቀስ ቻለች። መጀመርያ አካባቢ ዩሪ ጋጋሪ ጨረቃ ላይ የሚራመድ እንጂ እሷ የምትራመድ አትመስልም ነበር። ከአንድ ጠረጴዛ ተነስታ ወደ ሌላ ስትራመድ ጠጪው ሁሉ በሰቀቀን በዐይኑ ይከተላት ነበር።ለቤቱ አዲስ የሆኑ ሰዎች ሰክራ ስለሚመስላቸው ብዙም አይደነቁም፤ እኛ ባልደረቦቿ ግን እሷን በማየት ስራ ፈታን ።

በነገራችን ላይ ገዝናሽ እንዴት ረዥም እንደሆነች ተናግሪያለሁ። በዚያ ቁመቷ ሂል ጫማ ስታደርግ G+3 ፎቅ ነው የምትመስለው። እንስራ የሚያህለው ጭንቅላቷ ደግም ፎቁ ላይ የተሰራ “ፔንት ሀውስ ይመስላል። እኛ የቤቱ ረዥም ሴቶች እንኳን ኮምፕሌክስ ነገር ስለሚሰማን ከጎኗ ደፍረን አንቆምም።
ታሳጣናለቻ። እሷ ግን ቁመት ብቻ ሳይሆን ጥቁረትም ውፍረትም ክብደትም የሚያህላት ስለሌለ ቤቱን እየረገጠች ታንቋቋዋለች። እሷ ስትራመድ ምድር ትንቋቋለች፤ ይቺ ምድር ስንቱን እንደቻለች ይቅር ይበለኝ።

ዝናሽ ከጡቷ ይልቅ ጎንጯ ጡት መያዣ ይፈልጋል። በዚያ ሰውነት ላይ ፈጣሪ ለምን ትንንሽ ጡቶች እንደተከለላት ይገርመኛል። ሰፊ ደረቷን አይቼ ትንንሽ ጡቶቿን ሳስብ አእምሮዬ ላይ የሚመጣው ሁለት 0 አምፖል የተገጠመለት ሠፊ የሰርግ አዳራሽ ነው ይቅር ይበለኝ።

ያም ኾኖ ሚኒስከርት አድርጋ፣ ሽቶ ተርከፍከፉ፣ የቢራ ጠርሙስ አንቃ ቁጭ ትላለች። ልክ እንደኛ ወንድ ፍለጋ! ባለጌ ወንበር ላይ። ባለጌ ወንበሩ እሷ ስትቀመጥበት ጨዋ ኾነ። ዱካ ኾነ። ረዥም ስለሆነች ቀርጩማ ላይ የተቀመጠች ነው የምትመስለው። ባለጌ ወንበሩ ላይ ምንም ሳትንጠራራ ነው
ሄዳ ጉብ የምትልበት። ሰው ባለጌ ወንበር ላይ ተንጠራርቶ ነው የሚወጣው፤ እሷ ግን እንዲያውም በርከክ ትላለች መሰለኝ
ይቅር ይበለኝ!

ብቻ ዝናሽ እንደምንም ተኳኩላ ቢዝነስ ጀመረች። የመጀመርያ ቀን ማንም ወንድ ቀና ብሎ ሲያያት ስላላየን ስላላየን በአንድ ድምጽ “የፈራነው ደረሰ" አልን። ከሷ ጋር የሚያድር ወንድ ካለ ሄጄ
አስፈርመዋለሁ ስትል ነበር ትምኒት። እውነቷን ነው። ይህ ነገር ለተከታታይ ሁለት ሳምንታት ቀጠለ።ሁላችንም ተደናገጥን። አሳዘነችን። ምንም ቢሆን እኮ ሴት ናት። የበታችነት ስሜት ተሰምቷት ራሷ ላይ አደጋ እንዳታደርስ ፈራን። እሷ እቴ ምንም አልመሰላትም። ትኩረቷ ሁሉ በሂል ጫማ እንደልቧ መራመድ መቻሏ ላይ ብቻ ነበር ፈ። አንድ ቀን ደፍረን ደሜን ነገርነው....

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍51😱1