አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አመውዴ

እናምልሽ ውዴ…
አንቺን በመውደዴ
በግ ማይጠፋው ቤት
ዶሮም አልታረደ
ዘይት ዋጋው ንሮ
እህል ተወደደ
ለነገሩ ይሁን
ቀን ነግቶ ይመሻል
እንኳን ኑሮ ቀርቶ
አንቺም ተወደሻል

እናምልሽ ውዴ…
አንቺን በመውደዴ
የቤታችን ቲቪ
ሪሞቱ ጠፍቶበት
የመኪናው መንገድ
አህያ ሄዶበት
ዕምነበረዳችን
ድንጋይ ተጠርቦበት
ያ ፅዱ ጎዳና
ተዝረክርኮልሻል
ለነገሩ ይሁን
አንቺም ሰው ጥለሻል

እናምልሽ ውዴ…
አንቺን በመውደዴ
በአውቶቡስ ፌርማታ
ባቡር ተጠበቀ
ሌባው እየኮራ
ፖሊስ ተደበቀ
ጥርስ ያለው አይስቅም
ድዳሙ እየሳቀ
ለነገሩ ይሁን
ቀን ነግቶ ይመሻል
እንኳን ሌላው ቀርቶ
አንቺም የኔዋ ጉድ
የኔን ልብ ሰርቀሻል

እናምልሽ ውዴ…
አንቺን በመውደዴ
በዝግ ቤት ውስጥ ሆኜ
ብጠብቅሽ እንኳ
.

.


.
በራችን ተንኳኳ!!


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

🔘ልዑል ሀይሌ🔘

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
19👍2😁2
#እየመቱህ_ስራ

በህይወት ዘመንህ በስኬትህ መሀል
ለመነሳት መውደቅ ይጠበቅብሀል
ተቸገር ግድ የለም አይከፋ ልብህ
ከእንቅልፍህ ለመንቃት መተኛት አለብህ
ከፍ ብለህ ታይተህ እንድትኖር በኩራት
ይጠበቅብሀል ዝቅ ብሎ መስራት

ራሱን ዝቅ አድርጎ ችግር የሚፋለም
በግድ የሚሰራ እንደ ሚስማር የለም
በአናፂው ጉልበት በሀይል ተመትቶ
አይከፋም አንዴም ይሰራል ተጎድቶ
ውጤታማ እስክትሆን ፍሬ እስክታፈራ
አንተም እንደ ሚስማር እየመቱህ ስራ


  #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
12👍5😁1
#ምንም\_አልል

እሺ እንግዲህ በዝምታ
የልቤን ደም ሥር ትርታ
በደቂቃ ዕድሜን ትዝታ
ትር ስትል አፍታ ለአፍታ
እያዳመጥኩ እያስታመምኩ ጊዜዬን እያሰላሰልኩ
ሳልናገር ሳልጋገር፤ እየደገምኩ እያሰላሰልኩ
ሳልሰለች እያመላለስኩ ..........
እሺ እንግዲህ በጸጥታ
የልቤን ደም ሥር ትርታ
የእስትንፋሴን ቃል ጉምጉምታ
ትር ስትል አፍታ ለአፍታ
ሳልሰለቸ እየደጋገምኩ
በእግረ ሕልና እያደቀቅኩ
እየቋጠርኩ እየቆጠርኩ
እሺ እንግዲህ አልናገርም
በአንደበቴ አልተነፍስም
በልሳኔ አልመሰክርም
አልልም፡፡ ምንም አልልም
እንዲያው ዝም እንጂ ዝም ዝም ............
የልቤ ደም ሥር ሲያቃጭል
ልሳኔን ሲያስነሳ ሲያስጥል
ቃላቴን ሲቃኝ ሲያጋግል
ትንፋሼን ሲያንር ሲያደውል
ክል ሲል ትር ድም ሲል
ማዳመጥ ማስታመም እንጅ ፤ ሌላ ምንም ምንም አልል

🔘ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን🔘


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
19👍5🥰1
#ምስጋና_ቢስ_ፀሎት!


እዛ ጎዳናው ላይ ...

ስንኩል ሽባነቱን ለሰማይ የሚያሳይ

"እጅ ከሰጠኸኝ  ልመና አቆማለሁ" ብሎ እየማለ
አብዝቶ የሚያለቅስ ፥ አንድ ለማኝ አለ።
እናም የዛ ለማኝ!

የኔ ቢጤን ፀሎት...

እግዜር ኖሮ ሰምቶት...

በጥልቅ እንቅልፍ ጥሎ እጅ አበጃጀለት

ላፈሰሰው እንባ ፣ ለጠለየው ፀሎት መልሱ ተላከለት።

ግን እርሱ ሲነቃ...

እጅ አገኘሁ ብሎ አላመሰገነም

ለገባው ቃልኪዳን

ለተሳለው ስለት ምላሽ አላኖረም

ዛሬም እንደ ፊቱ...

ዛሬም እንደ ትናንት ማልቀሱን አልተውም።

እንዲህ ሲል ቀጠለ...

"መንገድ ላይ ወድቄ

ተዘከሩኝ እያልሁ በስምህ ስጣራ

ጤነኛ ነው ብለው...

ፈራንካ ለመስጠት ሰው እንዳይኮራ

ይህን አስብበት ጌታ ሆይ አደራ!!

🔘ሚካኤል አስጨናቂ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
22👏9
#የልብ_ቅርፅ

ፍቅርን ያህል ነገር...
ተሸክሜ ስኖር ፣ በልቤ ትከሻ
"ቃል አጠረኝ" የሚል....
ቃል ካፌ አይወጣም ፣ ላወድስሽ ስሻ።

እንደውም ሳፈቅርሽ ፣ ቃል ነው የተረፈኝ
ሁሉ ያጥርብኛል.....
በልብሽ ቅርፅ ውስጥ ፣ መውደድሽ ሲያገዝፈኝ።

ሳፈቅርሽ ይህ ሆነ...
ሰፊ ያልሁት አለም ፣ ባንድ እርምጃ አለቀ
ሳልሄደው ሚደክመኝ...
ተራራና ጋራው ፣ ከግሬ ስር ጠለቀ።
"ሩቅ" ያልሁት ሰማይ..
ሩቅ የሚመስለኝ ፣ ነካሁት በስንዝር
ጨረቃና ፀሀይ....
ከኮከብ ያንሳሉ ፣ ከፍቅርሽ ግዝፈት ስር።

ሳፈቅርሽ ይህ ሆነ...
ንጉስን ከዙፋን ፣ ማርከው የሚያወርዱ
የሀያላንን አቅም ፣ በጥቅሻ ሚያርዱ
ቆነጃጅት ሴቶች ...
"ቃል አጠረኝ" በሚል ቃላት የተሞሉ
ከፍቅርሽ ግዝፈት ስር..
ቃል ተገኝቶላቸው ፣ "ፋንጋዎች" ተባሉ።

ሳፈቅርሽ ይህ ሆነ...
"ቃል አጠረኝ "በሚል...
ባፍቃሪ አንደበት ፣ ቃል ተትረፈረፈ
ሁሉን አሳንሶ...
በልቡ ቅርፅ ውስጥ ፣ ፍቅሩን አገዘፈ
አለሙን ሰርዞ ፣ ፍቅሩን ብቻ ፃፈ!!!

ሳፈቅርሽ ይህን አልሁ...
ፍቅርን ተሸክሞ ፣ የሚኖር ልቦና
ሁሉም ከፍቅርሽ ስር ፣ መሆኑን አውቅና
አንቺን ለማወደስ..እኔም ቃል ያጥረኛል
"ቃል አጠረኝ "ማለት...
ቃል እንደሆነ ግን ፣
ፍቅርሽ ይነግረኛል!!!

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
15👍4🔥1
#ጠብ_መንዣ

ለአህያ ማር ...ጥሟት
ውሻ ግጦሽ ...ወርዳ
በቅሎ ፅንስ ቋጥራ
ዝንጀሮ ሠው ወልዳ
እርጎ ቢወጣቸው ፥ ባህሮች ሲናጡ
ፀሀይም ጨረቃ ፥ ባንድነት ቢወጡ
ሌት .......የሚሉት ቢቀር
ውሀ ሽቅብ   ቢቀር!
ተብሎ እንደሚያስብ
የሞኝ ሠው ምናብ
እንዲህ በራቀበት.....
ጦርነትን ሸሽቶ ፥ በሰላም መዳኘት
የራስ ውድ በልጦ ፥ ካምሳለ ፍጥረቱ
ለስጋ ባደረ ፥ ተረስታ ነብሲቱ
ትግስት እንደ ፍርሀት ፥ ሆኖ መገነዣ
ብረት ሁሉ ሆነ ፥ ለሠው ልጅ ፥

ጠብ_መንዣ


🔘 አብርሀም ተክሉ🔘
           
         #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose      
👍178
#አዲስ\_እብድ

አስለፈለፈኝ
አስለፈለፈኝ፤
ካንቺ ጋር ሆኜ
ከእብደት በቀር አንድ አልተረፈኝ፤
.
ልብሴን አውልቄ
በየጎዳናው ስዞር ውላለሁ፤
አንቺን የቀደድኩ እየመሠለኝ
አንቺን ያቃጠልኩ እየመሠለኝ
የለበስኩትን አቃጥያለሁ፤
.
ሠው ይሄን አይቶ
"ለሴት አበደ" "በሴት አበደ" ብሎ ያማኛል፤
ልብሴ ላይ ያለው
ውብ ጠረንሽን
ታጥኜ እንደኖርኩ መች አውቆልኛል፤
ከጎንሽ ርቆ
ከትዝታሽ ጋር መኖር ይከብዳል፤
ማያገኙትን ጠረን ሸክፎ
መንከላወሱ ሠው ያሳብዳል፤

ለዚህ ብዬ ነው
ከእብደት ሽሽት እርቃን የወጣሁ፤
በማውለቅ ሳይሆን
በመልበሴ ነው እብደት ሚመጣው፤

🔘ልዑል ኃይሌ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
17👍6😢3
ከሔድኩ አልመጣም!

"አትግፋኝ!"ብዬህ ነበር መዘዙን ፈርቼ፤
"አትንኪው!" ብያለሁ ቁስሌን አሳይቼ፤
"ጠግበው እንደናቁት እንደጣሉት እህል
እስከ ጥግ አይችሉም ሰዎች የኔን ያህል!"
ታግሼ.
አብሼ.
ስከፋ.
በይሆናል ተስፋ.
ባልፍም በጥሞና ቃላት ባላወጣም፣
ሳይገፉኝ አልሔድም
ከሔድኩም አልመጣም!
ተንቄ.
ወድቄ.
ደቅቄ.
ሳልጀምር አልቄ.
ፈርጄ እሔዳለሁ፣ኅዘን ሳጠራቅም፤
በመሸሼ ብቻ፣ብሶቴ ባያልቅም. . .
ከጀመርኩት መንገድ፣ተመልሼ አላውቅም!

🔘ፈይሰል አሚን🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
15👍8🔥1
#ነበረ!

እንደነገርኩህ ነው የለም የምነግርህ
ብቻ ግን ይኸውልህ ፥
ፊቱ እህል ቀርቦ መብላት ያላወቀ
በርሀብ የራደ በችግር ያለቀ ፥
ለእንቆቅልሽ መፍቻ የመሰረት ያለ
ሰንደቃ'ላማ ፊት ሀገሩን 'ሚረሳት አንድ ወጣት ነበረ!

ውሉ የጠፋበት ዳቦ መግዣ ያጣ
ለእርዳታ ስንዴ ገንዘብ የሚያዋጣ፤
ፅድቅ ይሉት ኩነኔ አጣምሮ ሚሰፋ
ቀኑ እንዳይገፋው፥ ቀኑን የሚገፋ!
ካልሲ ለጠየቀው ጫማ እየጨመረ
አፀድ ስር ቁጭ ብሎ እርቃኑን የቀረ
አንድ ወጣት ነበረ!

እንጀራ አቅርቦ መብላት የሚያስጠፋው
እየቀለድክለት ቀልድክ የሚያስከፋው ፣
መርዶ እየነገርከው ጮቤ ሚያሰረግጠው
ተስፋ'ለህ ስትለው ተስፋ ሚያሰቆርጠው፣
መድሃኒት ፍለጋ እንዳቀረቀረ፥ አጎንብሶ የቀረ
አንድ ወጣት ነበረ!

ብርቱ! ሆነ ስንል፤ ደ'ሞ እየደከመ
መዳኑ ነው ሲባል፤ ብሶ እየታመመ፥
መውደቁ ነው ስንል፤ ድሆ እየተነሳ
ሊታወስ ነው ሲባል፤ ሰርክ እየተረሳ፥
ብቻውን የቀረ፣
አንድ ወጣት ነበረ!

ከእንቅልፉ ሲነቃ፤ እንቅልፍ የሚጥለው
ድነሀል ስትለው፣ ድህነት! የገደለው፤
ከመሔዱ ብዛት መንገድ ያከሰረው
ከመንገዱ ይልቅ መድማት ያስተማረው፣
በመንገድ በመድማት በመሔድ የቀረ፣
የማርያም ንግስ እለት ደጃፏ ቁጭ ብሎ ማርያምን ሚረሳት አንድ ወጣት ነበረ!

"በምድር ዘላለም" አቀርቅሮ የቀረ፣
ነበረ የሚለኝ አንድ ወጣት ነበረ!
በጠራራ ፀሀይ ይነጋል እያለ ጨረቃን በመስደብ ብዙ አመት የኖረ፣
አንድ ወጣት ነበረ!
በየ እግረ መንገዱ "በተስፋ" የኖረ፣
እስታውሰኝ የሚለኝ አንድ ወጣት ነበረ!
በአዳም ፊርማ ላይ አሻራ ፍለጋ አቀርቅሮ የቀረ፣
ቀና በል የሚለኝ አንድ ወጣት ነበረ!

እንጀራ ለመብላት፤ እንጀራ የሸጠ
ከሚዲያ ጀርባ ሊቀበል የሰጠ፣
ዝንት አለም ሲጠላ ሲገፋ የኖረ
ሰርአተ ቀብሩ ላይ ምስኪን ነበር እኮ አፈር በልቶት ቀረ፤
ብለው ማያወሩለት አንድ ወጣት ነበረ!

በአንድ ወጣት ታሪክ ተመስጦ የቀረ፣
አንድ ወጣት ነበረ እያለ የሚፅፍም አንድ ወጣት ነበረ!
ነበረ!
ነበረ!!
ነበረ!!!

🔘ዩሐንስ ስለሺ🔘


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
115👍3👏1
#አለሁኝ_በደህና

አንቺ እንደምን አለሽ
…እኔ አለሁ በደህና
ይመስገን ዳመና
በገበሬው አጥንት – መሬቴን እያረስኩ
በገበሬው እንባ – ማሳ እያረሰረስኩ
እንጀራ ቢጠፋ – ገበሬ እየጎረስኩ።
አለሁኝ በደህና
ይመስገን ዳመና

ሰው ሲያፈርስ እያየሁ
ሰው ሆኖ ቡልዶዘር
አንዱ ጭጋ ነገር ሌላው የብረት ዘር
በፈረሰ ሰው ላይ በቆመ ሰገነት
ሲዖል አናቱ ላይ በታነፀ ገነት
ይኽን ኑሮ ብለው ጥቂቶች ሲኖሩ
…ያለምንም ፀፀት
…ያለምንም ሃፍረት
ይህንን እያየሁ በታላቅ ፅሞና
ኣለሁኝ በደህና ይመስገን ዳመና።
በምቾት መዲና
የነዳያን ትዝብት እንደ ሀሩር ልፎኝ
በጠዳ ጎዳና ለማኝ ብላቴና
እንደ ጉቶ አንዳቅፎኝ
ሃፍረት እንደ ዝናር ከፊት ከኋላ አቅፎኝ
ልክ እንደ ደባሎች ለመኖር እያቀድሁ
በጌቶች መሶብ ላይ እጄን እየሰደድሁ።
አለሁኝ በደህና
ይመስገን ዳመና

ወይ በሩን አሳዪን ወይ ጠቁሚን መላ
መዓበል ሲቃረብ ያመልጣል ሽመላ
በነፋስ ገፅ ፊት ይሸሻል ዳመና
የኔ ሃዘን ያለበት ያገሬ ሰው ግና
በስጋ ደም አጥንት የተሰራ ይመስል
እንደ ኮንሶ ሃውልት የመቃብር ምስል
አይሸሽ አያባርር ወይ አይተነፍስ ቃል
እንጨት ሆኖ ቆሞ ሰደድ ይጠብቃል።
.
ይህንን እያየሁ ሁኘ በጥሞና
አለሁኝ በደህና ይመስገን ዳመና
አንቺ ግን አለሽ ወይ እኔ አለሁ በደህና
አለሁ ግርምት ኖሮኝ
ምላሱን በምላጭ እንደተሰለበ
....የማስበው ኖሮኝ
......የምለው ቸግሮኝ


🔘በዕውቀቱ ሥዩም🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
16👍3
#ኑረት_ሂደት_ሂደት

ከገላ ተቆርጦ ዕትብቴ ሲቀበር፤
ለአፈር ማንነቴ
ለሞት ቀብድ ነበር።

ታዲያ...
ምነው ተዘነጋኝ?!

ዳግም የሚቀበር
ቀሪ ገላ እንዳለኝ፤
ትምክህተኛ ሆኜ
በኑረቴ ዘመን
የራቅኩኝ ቢመስለኝ፤
ያው...
አሁንም
ቀብድ የተያዘብኝ ቁራጭ እትብት ነኝ!።

🔘ልዑል ሀይሌ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍128
#ትወጂኛለሽ!!!

እኔ እየፈራሁሽ፣ ልቤ እየደፈረሽ
እኔ እየናኩሽ ፣ ልቤ እያከበረሽ
እኔ እየጠላሁሽ ፣ ልቤ እያፈቀረሽ
ከራሴ ስጣላ...
እኖራለሁ እንጂ ፣ የልቤን ሀቅ ይዤ
አንድም ቀን አልፎልኝ....
ልቤን እንደልቤ ፣ አላውቅም አዝዤ፡፡
አንቺም ልክ እንደኔ...
ልብሽን እንደልብ ፣ ማዘዝ አትችይም
ልብሽ ይወደኛል ፣ ጠላሁህ ብትይም፡፡
ባትወጂኝም እንኳን
የመጥላትሽ መጠን ፣ የቱን ያህል ቢያክል
አንቺን አላምንሽም ፣ ልብሽ ነው ትክክል፡፡
ትወጂኛለሽ!!!

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍62
#ላረፈድሽው

እኔማ ጠባቂሽ
  ማርፈድሽን አላይም  መምጣትሽን ብቻ
ድረሽልኝ እንጅ
   በዘመኔ ማብቂያ   በዕድሜዬ መባቻ

ፀጉሬ ቢሸበባብት   ስጋዬ ቢጃጅም
ይበስል እንደሁ እንጅ 
                         መንፈስ አያረጅም

ነይ ፍቅሬ ወጣት ነው   ልቤም እቶን እሳት
የተገላቢጦሽ ቢያደርገውም ቅሉን
                                   የዘመን መሳሳት
ከመቅረት ይሻላል  ከመጣሽ  ቢረፍድም
ፅልመት ካልገፈፈ  ወትሮም ጎህ አይቀድም ።

#Share #liked hand #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍53
#መለያየት_ማለት

እየው ትላንትና ከትላንትም በስቲያ
ያዩሽ ሰዎች ሁሉ ከእቅፌ ጉያ
ዛሬን ተራርቀን ብቻዬን ቢያዩኝ
ከድታዋለች ብለው ከንፈር መጠጡልኝ
እባክሽ የኔ ዓለም ፈጥነሽ ንገሪያቸው
ሴትን ማፍቀር እንጂ ማባበል አይችልም ብለሽ አስረጃቸው
ለእኔ እና ለአንቺ እኮ መለያየት ማለት
በሩቅ መፋቀር ነው ያለመተያየት
ያለመተያየት መፋቀርም ማለት
በምናልባት ተስፋ የምትቆም ሕይወት
ዘወትር ዘወትር ምናልባት
ምናልባት እያለች የምትኖር ሕይወት
በተስፋዋ መሀል ጥቂት ደስታ አላት
በተስፋችን መሀል መፋቀሩ ካለን
ናፍቆት አካል ገዝቶ እንተያያለን
ብለሽ ንገሪያቸው
ልቤና ልቡናው ተጣብቋል በያቸው
እንጂ በእኛ መሀል መለያየት ማለት
በሩቅ መፋቀር ነው ያለመተያየት
በሩቅ መሰማማት በድምፅ አልባ ቃላት

🔘ኤፍሬም ስዩም🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍127
#ለየ_ቅል

የየግል ብሶት ፣ የየግል ችግር
የየግል ሩጫ ፣ የየግል ውድድር
የየግል ሀይማኖት ፣ የየግል ብሔር
የየግል አላህ ፣ የየግል እግዜር
የየግል ሀገር ፣ የየግል ስልጣን
የየግል መልአክ ፣ የየግል ሰይጣን
ይዘን እየወጣን...
በየ ግል ቆስለን ፣ የጋራ ፈውስ አጣን!!!

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍207
#እድሜን_ያሸነፈ

እድሜ ሚሉት ቋጥኝ
በእርጅና መዳፉ አካሌን ደርምሶ
ውበቴን
አጥንቴን ስጋየን አኩስሶ
እንደ ሃር ነዶ
የጠቆረ ጠጉሬን ከበረዶ አንፅቶት
ለስላሳ አካላቴን
እሳት የገረፈው ፌስታል አስመስሎት
ባምሳሉ የተሰራ
ቁመና ወበቴን ሸብሽቦ አበላሽቶት
በጊዜ ዳኝነት ሁሉም ተበይኖ
የነበረው ሁሉ እንዳልነበር ሆኖ
ዘመን አሸንፎት ቀና ያለው ሁሉ እያቀረቀረ
ያንቺ ፍቅር ብቻ በልቤ ላይ ፀበል እየተነከረ
ዘመንን ረግጦ እንደ ፅጌሬዳ እንደፈካ ቀረ።


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
14👍3
ቀናሁ

ለመንኩት አምላክን
አበባ እንዲያደርግሽ
ንብ ሆኜ መጥቼ
እየዞርኩ ልቀስምሽ
ማለዳ ማለዳ
በበራፋችሁ ሳልፍ
ብመለከት ጊዜ
ፀሀይ ስትሞቂ
ፈጣሪን ለመንኩት
"ፀሀይ አርገኝ "ብዬ
ውብ ሠውነትሽ ላይ
እንዳርፍ ዘና ብዬ፡፡
ያንገትሽ ማተብ
ያለ ማንም ከልካይ
ገብቶ ሲንከላወስ
በጡቶችሽ ክፋይ
ብመለከት ጊዜ...
ቀናሁ በማተብሽ
ቀናው በመስቀሉ
ጡትሽን ተንተርሶ
በመዋል በማደሩ፡፡
ቅዳሜ እረፋድ ላይ
ስትመጭ ከገበያ....
ትኩስ ለጋ ጎመን
በክንድሽ ታቅፈሽ
በሌላኛው እጅሽ
ዘንቢል አንጠልጥለሽ..
ብመለከት ጊዜ...
እንደ ጎመን መሆን
ተመኘው ለቅፅበት
በአካሌ እንዲሠራጭ
የአክናድሽ ሙቀት
ተመኘው ለቅፅበት
መሆን እንደ ዘንቢል
ውብ ለሥላሳ ጣትሽ
በገላዬ እንዲውል፡፡
ትናንትና ደግሞ..
ከኛ ቤት ፊት ለፊት
ውሐ ስትቀጂ
ከየት እንደ መጣ
ያልታወቀ ንፋስ
ቀሚስሽን ገልቦ
ጀምበር የመሠለ
ያ ውቡ ጭንሽን
ቢያሳየኝ በስሱ
እምልልሻለው
ቀናሁ በንፋሱ፡፡

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
12👏7😁5
ድርሳነ ፍቅር!


አንቺ የእኔ ጣዖት!
እኔ ያንቺ አማኝ
የምዕመኑ ጠሎት ቅዳሴና አዛኑ
በየት በኩል ይሰማኝ?

እሳት ያንቺ ገላ መብረቅ ያንቺ መውደድ
በየት መንገድ ልጓዝ እምን ላይ ልራመድ?
ዓይኖችሽ ጉልላት
ጥርሶችሽ በረዶ
ጣቶችሽ አለንጋ....
ሠንበር የወረሰው ቁስል ልቤን ይዤ
እንደምን አልሰጋ?

እኔ
መድሀኒቴ አንቺ
በሽታዬም አንቺ
አንቺን እየዋጥሁኝ አንቺን የምታመም
ባንቺ እየታመምሁኝ ባንቺ የምታከም

ባለ አንድ ድዌያም ባለ አንድ ክኒና
ወይ አልሞት ፥ ወይ አልድን
ወይ አልኖር በደህና!

🔘ሚካኤል አስጨናቂ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
11👍9👎1
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///

አለም የሆቴሉን የተወሰነ ክፍል አገልግሎት ዝርዝር የሚያሳየውን ካርድ አንስታ ተመለከተች። የአርብ ምሽት የአካባቢው ዘመናዊና ባህላዊ ባንድ በጥምረት ከምሽቱ አንድ ሰዓት እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ የሙዚቃ ድግስ እና ትርኢት ያሳያሉ።
ክፍል 125 ተከራይታ ጓዟን አሳረፈችና ልብሷን መቀያየርና እራሷን ማስዋብ ጀመረች፡፡ የመዋቢያ እቃዎቾን ከያዘው ሻንጣ ግርጌ ላይ የጥፍር መቁረጫ  አገኘች። ጥፍሯን ከሞረደች በኃላ አለባበሷን እና ጠቅላላ አቋሟን ለማየት መስታወት ፊት በመቆም ለመጨረሻ ጊዜ እራሷን ተመለከተች...።

በምትገናኛቸው ሰዎች ላይ የመጀመሪያ አስደናቂ የስሜት ትስስር ለመፍጠር ትፈልጋለች። ማንነቷን ስትነግራቸው በጣም እንደሚገረሙ እርግጠኛ ነች፣ ነገር ግን የበለጠ  ጠንካራ  ተጽእኖ  መፍጠር  ፈልጋለች።ከዚህ  ቀደም  ከሚያውቋት  ሴት ጋር እንደሚያነፃፅሯት ጥርጥር የለውም። እሷ ያንን መከላከል አትችልም፤አትፈልግምም፡፡. እሷን በትክክል መመዘንና መገምገም ከቻሉ እርግጠኛ ነች ሰሎሜ ጎይቶምን ለማስታወስ ይገደዳሉ ።የምትለብሰውን በጥንቃቄ መርጣለች። ሁሉም መዋቢያዎችና ጌጣጌጦች በተገቢው ልኬትና መጠን ተጠቅማለች፡፡በዛም የተነሳ በጣም ጥሩ የሚባል የተለየ እይታ እና ልዩ አይነት ውበት እንደተላበሰች ተሰምቷታል ። ሴትነቷን በጥበብ አጉልቶ የሚያሳይ ልዩ አይነት ብርሀን የሚንቦገቦግባት የውበት መቅረዝ ነው የምትመስለው፡፡

ግቧ መጀመሪያ እነሱን ማስደነቅ ነበር፣ እዚህ ወደ ሻሸመኔ በመምጣቷ እንዲገረሙ ብቻ ሳይሆን በዛው ልክም እንዲደነግጡ ነው የምትፈልገው።ከመጣችበት የሀገሪቱ ዋና ከተማ አዲስአበባ ጋር ሲነፃፀር ሻሸመኔ የአንድ ክፍለከተማን ያህል እንኳን ስፋት የሌላት ከተማ ነች፡፡ግን ደግሞ በሀገሪቱ ካሉ ማንኛውም ከተሞች የበለጠ ፤ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚደረግባት…በየቀኑ በሚሊዬን የሚቆጠሩ ሰዎች ገብተው የሚወጡባት በጣም ደማቅ ከተማ ነች፡፡እና አሁን ፊት ፊት የምትጋፈጣቸው ሰዎች የዚህ ከተማ የጡት አባት ተደርገው የሚታዩ….ናቸው፡፡

አለም ያሰበችው ስራ በስኬት ካጠናቀቀች በሀገሪቱ የመገናኛ ብዙሀን ዜናዎችን በዋናነት የሚቆጣጠር ርዕሰ አንቀፅ እንደሚሆን እርግጠኛ ነች።ለበርካታ ደቂቆች መኝታ ክፍሏ ባለው መስታወት ፊት እየተሸከረከረች መልኳን ሆነ ጠቅላላ ቁመናዋን ደጋግማ ካየች በኃላ ሁለ ነገሯ እንከን ሊወጣለት እንደማይችል በመደምደም የእጅ ቦርሳዋን ትከሻዋ ላይ አንጠልጥላ ፣ የፍይል መያዣ ፎልደሯን አነሳችና እና የክፍል ቁልፍ እንደያዘች እርግጠኛ ሆና  ወጣች፡፡  የክፍሉን  በር  ዘጋችው።  የሆቴሉን  ህንፃ  ለቃ  ወጣችና ቀጥታ ወደመኪናዋ በመግባት መሃል ከተማውን እየሰነጠቀች ወደቀጠሮ ቦታ መንዳት ጀመረች፡፡ይሄንን ስብሰባ ያዘጋጀላት የዞኑ ዋና አቃቢ ህግ ነው፣ያንንም ስላደረገላት ለእሱ ታላቅ ምስጋና አላት፡፡ የትምህርት ቤት መለቀቂያ ሰዓት ስለሆነና ..አስፓልቱን በሰዎችና በተማሪዎች ስለተጨናነቀ እንድልቧ በፈለገችው ፍጥነት ለመንዳት ከባድ ሆኗባት ነበር፡፡

አለም ወደእዚህች ውብ ከተማ የመጣችው ለጉብኝት አይደለም፡፡ወይንም ዓላማዋን ከግብ እስክታደርስ ድረስ በእንግድነት አይደለም፡፡የከተማዋ ምክትል አቃቢ ህግ ሆና በመመደቧ ምክንያት ነው የመጣችው፡፡የትምህርት ዝግጅቷን እና ብቃቷን በማየት ይህን ሹመት የተሰጣት የአካባቢውን ህብረተሰብ ፍትህ እንዲያገኝ እንድታግዝ ነው፡፡ የእሷ ተልእኮ ግን የተለየ ነው፡፡የራሷ የሆነ አላማ እና ፍላጎት ባይኖራት ኖሮ በሞያዋ ለመስራትና ለማገልገል ከአደገችበት እና እድሜዋን ሙሉ ካሳለፈችባት አዲስአበባ እግሯን አታነሳም ነበር፡፡ የእሷ ተልእኮ እና ዓላም ለህብረተሰቡ ምንም ረብ እንደሌለው ስታስብ ትፀፀታለች። እሷ ለምን ወደእዚህ እንደመጣች ባስታወሰች ጊዜ የሚሰማትን የጥፋተኝነት ስሜት ነው፤ግን ደግሞ ምርጫ የላትም፡፡
በህይወቷ ውስጥ ወደዚህ ደረጃ እንድትደርስ ገፊ ምክንያት የሆናትን ጉዳይ ለአንድ ሰከንድ እንኳን ከረሳች እና ችላ ካለች ራሷን መቼም ይቅር ለማለት አትችልም፡፡ አካባቢው ስትደርስ ወደቀኝ ታጠፈችና ወደመዘጋጃ የሚወስደውን ጠባብ የአስፓልት መንገድ ተያያዘችው፡፡መዘጋጃ ጽ/ቤት ከመድረሷ በፊት አሁንም ወደቀኝ ታጠፈችና ከቀበሌ ጽ/ቤት ጎን ካለው የፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ መኪናዋን አስገባችና ምቹ ቦታ ፈልጋ በማቆም
… ሞተሩን አጥፍታ ቦርሳዋንና የፋይል ፎልደሯና ይዛ ወረደች፡፡ በግቢው ውስጥ ያሉ የቢሮ ሰራተኞች ሆኑ የባለጉዳይ አይኖች ሁሉ እሷ ላይ ሲንከራተት ይታወቃታል…ብዙም ትኩረት ያልሰጠቻችው በማስመሰል ወደውስጥ ገባች፡፡

የፍርድ ቤቱን በር አልፋ ወደውስጥ ገባች፡፡ የተላላጠ ቀለምና የተፋፋቀ ግድግዳ እያየች ኮሪደሩን አቋርጣ ወደአንድ ክፍል ገባች፡፡
የፍርድ ቤቱ እንግዳ ተቀባይ የተለየ አይነት ሽቶ ስለሸተተው በደስታ ካቀረቀረበት ቀና አለ
…ቆንጆ መልክና ማራኪ አለባበስ የለበሰች ውብ ሴት ወደእሱ ስትመጣ ተመለከተ..ለሴቶች ስስ ልብ ያለው ወጣት ፀሀፊ በተቀመጠበት ተቁነጠነጠ፡፡

….አለም ወደፀሀፊው እየተራመደች በጎሪጥ ቀጣዩን ቢሮ በጉጉት ተመለከተች።

ስሩ ደረሰችና ‹‹ጤና ይስጥልኝ››አለችው፡፡

‹‹አቤት የእኔ እመቤት ….እንዴት ነሽ….?ይሄንን የመሰለ ውበት ይዘሽ መቼስ ተከሰሽ አይሆንም ወደዚህ የመጣሽው?››አላት፡፡

‹‹አረ በፍፅም››ስትል መለሰችለት፡፡

‹‹እና ከሰሽ ነው?››

ስለመቅለብለብ እያሰበች ‹‹እንደዛም አይደለም››ስትል መለሰችለት፡፡

‹‹እና….እኔን ፈልገሽ ብቻ እንዳይሆን?››

ከንግግግሩ በላይ ጉንጭ ውስጥ እያላመጠ ያለው ማስቲካ ሲታኘክ የሚያሰማው ድምፅ ምቾት ነሳት።ቢሆንም ፈገግ አለችለትና ሌላ ነገር ለመናገር እየተቅለበለበ እያለ፡፡"እኔ ከዞኑ አቃቢ ህግ ቢሮ ነው የመጣሁት። ዋና አቃቢ ህጉ ክቡር ግርማ ጠያቂነት ክብሩ ዳኛው የጠሩት ስብሰባ ነበር ››

ፈጎ የነበረው ፊቱ ሲኮሳተር እና ልቅ የነበረው ንግግሩ ሲሰበሰብ ታወቃት….

"ከአቃቢ ህግ ቢሮ ሰው እንደሚልኩ ተነግሮኝ ነበር…ግን ተወክሎ የሚመጣው ሰው ወንድ ይሆናል ብለን ነበር የጠበቅነው"አላት፡፡

"እንደምታየው እኔ ነኝ የመጣሁት…ምነው የክብሩ ግርማ ምክትል መሆኔ አላሳመነህም?ነው ወይስ አላስደሰተህም?፡፡››ሰውዬው ሴት አውል ከመሆኑም በተጨማሪ የወንድ ትምክት እንዳለበት ተረዳች፡፡እናም አበሳጫት፡፡

ከተቀመጠበት  አሻግሮ  ጉልበቷ  ጋር  የቀረውን  አጭር  ቀሚሷን  እየተመለከተ…"ደህና
..በቀጠሮ ሰዓት ነው የተገኘሽው። "ስሜ ቶሌራ ይባላል። ቡና ትፈልጊያለሽ? ››አላት ፡ የእሱን ግብዣ ችላ ብላ "የተጠሩት ሁሉም እንግዶች መጥተዋል?"
ከእሱ መልስ ከመስማቷ በፊት ከተዘጋው በር የፈነዳ ተንከትካች የወንዷች ሳቅ ተሰማ ።

‹‹አዎ…ሁሉም ተገኝተዋል!!››

‹‹ለቡናው አመሰግናለው….መግባት አለብኝ ››አለችና ቦታውን ለቃ ወደክፍሉ ተራመደች…አለም በህይወቷ ውስጥ በጣም ወሳኝ ለሆነው ስብሰባ ራሷን አበርትታ ወደ ቢሮ ተጠጋች።በስሱ ስታንኳኳ ሳቁ ተቋረጠና ፀጥታ ሰፈነ፡፡ገፋ አድርጋ አንገቷን አስቀድማ ወደውስጥ ገባች ፡፡በክፍሉ ውስጥ ያሉት ወንዶች ሌላ ወንድ ሲጠብቁ እንደነበረ ከተረጋጋ መንፈሳቸው በግልፅ መረዳት ችላ ነበር። በራፉን ተሻግራ ወደውስጥ በገባች ቅጽበት በራፉ ከኃላዋ ሲዘጋ ተሰማት፡፡.የአራት ሰዎች ጥንድ ስምንት አይኖች እሷ ላይ ተተከሉ….በሁሉም ላይ ተመሳሳይ አይነት ግራ የመጋባት እና የመደነቅ ስሜት አነበበች…የፈለገችውም እንደዛ እንዲሆን ነው፡፡
57👍5
ቀጥታ ሄደችና ባዷቸውን ካሉት ወንበሮች አንዱን ሳበችና ፎልደሩን የጠረጴዛው ጫፍ ላይ አስቀምጣ ከላይ የለበሰችን ኮት ቀስ ብላ በቄንጥ አወለቀችና የወንባሯ እጄታ ላይ አስተካክላ ከስቀመጠች በኋላ በእርጋታ ተቀመጠች….ይሄን ሁሉ ስታደርግ እነሱ ያለምንም ንግግር ትንፋሻቸውን ውጠው በመገረም ሲመለከቷት ነበር፣እሷም የፈለገችው ያንን ነው፡፡
ጤና ይስጥልኝ..ከዞኑ ዋና አቃቢ ህግ ቢሮ ክብሩ አቃቢ ህግ አቶ ግርማን ወክዬ ነው የመጣሁት ….ስብሰባው በእኔና እና በእናንተ መካከል ይደረጋል ማለት ነው፡፡››የሚል ያልተጠበቀ አይነት አጭር ማብራሪያ ሰጠች፡፡

ከመሀከለኛው ወንበር የተቀመጡት በእድሜያቸው መጨረሻ ላይ ሚገኙት አዛውንቱ ሰው"ምንም ችግር የለውም, ለአንቺ እና ለሀለቃሽ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ፍቃደኞች ነን…እኔ ዳኛ ዋልልኝ እባላለው፡፡እሱ የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኩማንደር ገመዶ ይባላል፡፡ሁለት ሰዎች ተራ በተራ እየጠቆመ። "እሳቸው አቶ ፍሰሀ ይትባረክ ይባላሉ እሱ ደግሞ ልጃቸው ጁኒየር ይባላል።የሶሌ ኢንተርፕራይዝ ዋና እና ምክትል ስራአስኪያጅና ባለቤት ናቸው፡፡የሶሌ ኢንተርፕራይ ማለት ከተማዋ የጀርባ አጥንት የሆኑትን በጣም

በርካታ ድርጅቶችን በጥምረት የሚያስተዳድር ግዙፍ ድርጅት ነው፡፡አቶ ፍሰሀ እና ልጃቸው በከተማዋ እጅግ የተከበሩ እና የተመሰገኑ ግለሰቦች ናቸው፡፡››ሲሉ የማስተዋወቅና የመግቢያ ንግግር አድርገው ከጨረሱ በኋላ ራሷን እንድታስተዋውቅ አይን አይኗን ይመለከቷት ጀመር፡፡

አለምም የዳኛውን ማብራሪያ በፅሞና ስታዳምጥ ከቆየች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እነዚህ ከፊት ለፊቷ ያሉትን ዳኛው የዘረዘሯቸውን ሶስት ሰዎች በማየቷ እንግዳ እና ሀይለኛ የማወቅ ጉጉት በውስጧ ሲንተገተግ ተሰማት፡፡በውስጧ ለእነሱ ያዳበረችው ጥላቻም ሲገለባበጥ ይታወቃታል፡፡ እነሱ ስለእሷ እና ስለ ስብሰባው አለማ ለማወቅ እንደጓጉ ሁሉ እሷም እነሱን ለማወቅ ፈልጋለች፣

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍3717👏1