#አላገባህም
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
/////
ዘሚካኤል ስቲዲዬ ቆይቶ ገና ወደቤት እንደገባ ነበር ስልኩ የጠራው፡፡
የደወለችለት አዲስ አለም ነበረች፡፡የጠበቀው ሚካኤል ይደውልልኛል ብሎ ነበር ፡፡ከአባቱ ጋር የሚገናኙበትን ቀን ከወህኒ ቤቱ አስተዳዳሪ ጋር ተነጋግሮ እንደሚደውልለት ነገሮት ነበር፡፡እና ይሄን ቀን በፍርሀትና በጉጉት ነበር እየጠበቀ ያለው፡፡ስለአባቱ ዜና ለመስማት፡፡ስልኩን አነሳው፡፡
‹‹ሄሎ አዲስ እንዴት ነሽ?››
‹‹ሰላም ነኝ አንተስ?››
‹‹እኔ በጣም ደህና ነኝ…ሚካኤል ይደውልልኛል ብዬ እየጠበቅኩ ነበር፡፡››
‹‹ይደውልልሀል..አሁን ኩማንደሩ ቀጥሮት ሊያገኘው ሄዶል …ከእሱ እንደጨረሰ እርግጠኛ ነኝ ይደውልልሀል፡፡…አታስብ ኩማንደሩ ደግሞ ያንተ አድናቂ ስለሆነ ከአባታችሁ እንድትገናኙ ሁኔታውን ያመቻቻል….በዛ እርግጠኛ ነኝ፡፡››አለችው
‹‹ጥሩ ታዲያ አንቺ ሰላም ነሽ?››
‹‹በጣም ሰላም ነኝ…ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ ነበር››
‹‹ምን?››
‹‹ከፀዲ ጋር እንዴት ናችሁ?››
ያልጠበቀውን ጥያቄ ነው የጠየቀችው‹‹በጣም አሪፍ ነን…ከቦንጋ ከተመለስን በኋላ በአካል ባንገናኝም በስልክ ግን በቀን ሁለት ሶስት ጊዜ እንደዋወላለን…እንደውም የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ከከተማ ወጣ ብለን ለማሳለፍ ተነጋግረናል፡፡
ግን ምነው ጠየቅሺኝ?››
‹‹ግልፅ ሆነህ ንገረኝ…ስለእሷ ምን ታስባለህ..ማለቴ አሁንም በፊት እንደነገርከኝ ታፈቅራታለህ?››
‹‹እንዴ!እንዴት በአንድ ወር ፍቅሩ ይተናል ብለሽ አሰብሽ? እንደውም ጥሩ ነገር አነሳሽልኝ…የሆነ ቀን አመቻችቼ ካንቺ ጋር መነጋገር እፈልግ ነበር..እኔ ላገባት እፍልጋለው..በቅርብ ቀን..እና እንዴት ጠይቄ ላሳምናት የሚለውን ከእኔ ይልቅ አንቺ ስለምታውቂ እንድታማክሪኝ እፈልጋለው፡፡››
‹‹እንግዲያው እንደዛ ከሆነ ሳይረፍድብህ ፍጠን››
‹‹አልገባኝም?››
‹‹ያንተን ልጅ አርግዛለች..››
የሰማውን ነገር ማመን አልቻለም…በደስታ ጮኸ…
‹‹ማለት…በፈጣሪ እየዋሸሺኝ አይደለም አይደል? ››
‹‹አርግዛለች..ለእኔም አልነገረችኝም ፡፡
በአጋጣሚ አንድ የግል ሆስፒታል ካርድ ክፍል የምትሰራ ወዳጅ ነበረችኝ …አሁን ከደቂቃዎች በፊት ደውላ ጓደኛሽ ፀንሳ እኛ ሆስፒታል ለማስወረድ መጥታ ነበር…ብላ ነገረችኝ፡፡መጀመሪያ አላመንኩም ነበር..በኋላ ግን ሆስፒታሉ ድረስ ሄጄ በሌላ መንገድ እራሷ መሆኗን አረጋግጬያለው…ልታስወርደው ለተነገወዲያ ቀጠሮ አሲይዛለች….ቀጥታ ላናግራት ፍልጌ ነበር….ጭራሽ እልክ ትጋባለች ብዬ ስለፈራሁ ምንም ልላት አልቻልኩም…አንተ ምታደርገው ነገር ካለ ሞክር››
‹‹ወይኔ በፈጣሪ..ለእኔ አረገዘችልኝ…..››በበቃ ቻው አዲስ አንቺ አትጨነቂ እኔ አስተካክለዋለው፡፡
የአዲስን ስልክ ከዘጋ በኃላ ቀጥታ ልብሶቹ በሻንጣ መክተት ነው የጀመረው፡፡ሁለት ሻንጣ ልብስና በወሳኝ የሚፈልጋቸውን ነገሮች ሰበሰበና አፓርታማውን ለቆ ወጣ …ቀጥታ ወደአዳማ ነው የነዳው፡፡
ፀአዳ ቤት ሲደርስ በራፏ ዝግ ነበር..ሊደውልላት አልፈለገም ፡፡ሻንጣውን አወረደና በራፏ በረንዳ ላይ አድርጎ እሱ መኪናው ውስጥ ሆኖ መጠበቅ ጀመረ…ከምሽቱ አንድ ሰአት ስትመጣ እሱ መኪና ውስጥ ሻንጣው በረንዳ ላይ ሆኖ ስታየው ፍፁም ነው ግራ የተጋባችው…ምስር እሱ መሆኑን ስታውቅ ከእናቷ ተነጥላ ወደእሱ መሮጥ ስትጀምር እሱም ፈጥኖ ከመኪናው ወረደና እጇቹን እንደክንፍ ዘርግቶ ጠበቃት…ተጠምጥማበት በደስታ ጉንጩን ትስመው ጀመር…
ወደቤት እንደገቡ ፀደይ‹‹ምንድነው ጉዱ?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹ምንም ..ለጥቂት ሳምንታት እረፍት ስለሆንኩ እዚህ ከእናንተ ጋር ለመቆየት ወስኜ ነው፡፡››
‹‹እዚህ ከእኛ ጋር?››
‹‹አዎ ከእናንተ ጋር››
ህፃኖ ምስር ‹‹ታድለን…ታድለን›› እያለች መጨፈር ጀመረች፡፡
ፀአዳ ልጇ ምስር ፊት ምንም ማለት አልቻለችም.‹‹እንግዲያው እደቤትህ ዘና በል…እኔ ልብስ ልቀይር ››አለችና መኝታ ቤት ገባች፡፡ከዛ እራት ሰርታ በሉና ከሶስት ሰዓት በኃላ ምስርን አስተኝተው ነበር እንደአዲስ ጭቅጭቁን የጀመሩት፡፡
‹‹ምን እየሰራህ ነው?››
‹‹እንደምታገቢኝ ቃል ገብተሸ ቀለበት እስክታስሪልኝ ድረስ ከዚህ ቤት ወጥቼ ወደቤቴ አልመለስም››ሲል ቁርጡን ፍርጥም ብሎ ነገራት፡
‹‹ጭራሽ ማግባት? እየቀለድክ ነው፡፡››
‹‹በፍፅም …ብቀልድ ነው እንደዚህ አይነት እርምጃ የወሰድኩት፡፡››
‹‹ስማ..እኔ ካንተ ጋብቻ ፍቅር ምናምን አልፈልግም››
‹‹ታዲያ ምንድንው ምትፈልጊው?››
ትኩር ብላ አየችው….
‹‹ንገሪኝ ከእኔ ምንድነው የምትፈልጊው….. ?››
‹‹ካንተ ወሲብ ብቻ ይበቃኛል….ማለቴ እስከአሁን የደረግነውን ለማለት ነው …ደግሞ አሁንም እናድረግ እያልኩህ አይደለም፡፡››
በንግግሯ ሆድን እስኪያመው ሳቀ…በመሀል ስልክ ተደወለለት ..ከወንድሙ ነበር…በጉጉት አነሳው‹‹እሺ ሚካኤል ደህና አመሸህ?››
‹‹ሰላም ነኝ…ነገ ጥዋት ሶስት ሰዓት ላይ አዳማ መገኘት ትችላለህ?››
‹‹ምነው ?አባዬን እንድናገኝ ፈቀዱልን እንዴ?››
‹‹አዎ በጣም ደስ የሚለው ደግሞ አንድ ላይ እንድናገኘው ነው ያመቻቹልን ቅር ካላለህ አዲስንና ቅዱስንም ይዘናቸው እንሄዳለን››
‹‹አረ ቅር አይለኝም ጥሩ ሀሳብ …ግን አባዬ እኔን ለማናገር ፍቃደኛ የሚሆን ይመስልሀል?››ሰሞኑን ሲብሰለሰልበት የነበረውን ስጋቱን አንስቶ ጠየቀው፡፡
‹‹ትቀልዳለህ እንዴ…ከመሞቱ በፊት ማግኘት የሚፈልገው ብቸኛ ነገር እኮ አንተን ማናገር ነው…በደስታ ነው የሚያነባው….እንኳን በአካል አግኝተሀው አባዬ ብለህ ስጠራው ሰምቶ ይቅርና ባለፈው ፎቶህን ሳሳየው እንዴት እያገላበጠ ሲስምና ሲያለቅስ እንደነበረ እኔ ነኝ የማውቀው…በል በዛ እርግጠኛ ሁን..ምንም አትጨናነቅ፡፡››
‹‹ምን ያስፈልገዋል…?ማለት ምን ይዤለት ልሂድ?››
‹‹የሚያስፈልገወን ነገር ሁሉ አዘጋጅተናል…አንተ ደግሞ ሚፈልገውን ነገር እንጠይቀውና በሚቀጥለው ዙር ትወስድለታለህ…ደግሞ ደስ የሚለው ከቦንጋ ያመጣችሁትን ከዶ/ሩ ጋር ያደረጋችሁትን ውይይት ለኩማንደሩ አሰምቼው በጣም ነው ያዘነው..እናም አባዬን ከሌሎች እስረኞች ጋር ተቀላቅሎ እንዲኖር ወስነዋል…››
‹‹በጣም የሚያስደስት ነገር ነው እየነገርከኝ ያለሀው..ወንድሜ በጣም ጥሩ ሰው እንደሆንክ ታውቃለህ አይደል… በጣም ነው የምኮራብህ፡፡››
ሚካኤልም እንባ እየተናነቀው‹‹እኔም በጣም ነው የምኮራብህ››አለው
‹‹በቃ እሺ …...ሶስት ሰዓት ነው ያልከኝ አይደል?፡፡››
‹‹አዎ…መድረስ ትችላለህ አይደል…?››
‹‹በደንብ እንጂ ሁለት ተኩል ደርሼ ደውልልሀለው››
‹‹ጥሩ በቃ ደህና እደር››ስልኩን ዘጋ፡፡
ንግግራቸውን ሁሉ በገረሜታ ስትሰማ የነበረችው ፀደይ‹‹እርግጠኛ ነህ ግን ሁለት ተኩል ትደርሳለህ?››ስትል በፈገግታ አሾፈችበት፡፡
‹‹ትቆጪኛለሽ ብዬ ነው እንጂ እዚህ ነኝ ልለው ነበረ››
‹‹ልፋ ቢልህ ነው ….ግን ለእናንተ ደስ ብሎኛል››
‹‹ማለት?››
‹‹አንተና ወንድምህ እንዲህ እየተደዋወላችሁ በሰላም ማውራት መቻላችሁ ትልቅ ነገር ነው…አረ እንደውም ከመነጋጋርም አልፋችሁ መሞጋገስ ጀምራችኃል››
‹‹እድሜ ለአንቺ ….ባንቺ ቀናነትና ጥረት ነው ለዚህ የበቃነው….››
‹‹እኔን ማሞገሱን እንኳን ለሌላ ጊዜ አቆየው..በነገራችን ላይ የአባትህ ጉዳይ ላይ ይግባኝ ለመጠየቅ ሚቻል ከአሆነ አንድ ጎበዝ ጠበቃ አግኝኝቼ ሁኔታውን አስረድቼው ነበር….››
‹‹በእውነት ..ታዲያ ምን አለሽ?››

👍67❤21👎1👏1
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_ዘሪሁን_ገመቹ
ራሄል ከሁለት ረዳቷቾ ከሮቤልና ሎዛ ጋር ስብሰባ ላይ እያለች ነበር ስልኳ የጠራው…ንግግሯን ሳታቋርጥ ስልኩን አነሳችና አየችው፤ አባቷ አቶ ቸርነት ናቸው የደወሉላት ፡፡ስብሰባ ላይ ነኝ ብላ ልትዘጋባቸው አልፈለገችም…አባቷ በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ባይሆን ኖሮ በዚህ ሰዓት አይደውሉላትም ነበር፡፡
‹‹አንዴ ይቅርታ… ይሄንን ስልክ ማንሳት አለብኝ››ብላ ከተቀመጠችበት ግዙፍ ተሸከርካሪ ወንበር ተነሳችና ቢሮውን ለቃ ወጣችና….ከዛ ስልኩን አነሳችው፡፡
‹‹ሄሎ አባዬ ..እንዴት ነህ?››
‹‹ሰላም ነኝ ልጄ››
ድምፃቸው ተጎተተባት‹‹ምነው አባዬ? ችግር አለ እንዴ?››
‹‹አይ ልጄ ሁሉ ነገር ሰላም ነው…እኔ እና እናትሽ አንድ ነገር ልናማክርሽ ነበር››
‹‹ምንድነው?››
‹‹ይሄውልሽ ልጄ ምን መሰለሽ..እኔና እናትሽ ጡረታ ወጥተን ቤት መዋል ከጀመርን በኃላ ህይወታችንን ታውቂያለሽ…ብቸኞች ነን..አንቺም አሻፈረኝ ብለሽ በራስሽ ቤት ነው የምትኖሪው…፡፡››
ራሄል በምትሰማው ነገር ፊቷን አጨማደደች….የገመተችው አብረሽን ኑሪ የሚለውን የዘወትር ጥያቄያቸውን ደግመው ሊያነሱባት ነበር የመሰላት፡፡
አባቷ ትንፋሽ ወሰዱና ንግግራቸውን ቀጠሉ‹‹እህት እንዲኖርሽ ፈልገን ነበር››
ደነገጠች‹‹እህት!!››
‹‹አዎ ቅር ማይልሽ ከሆነ እኔ እና እናትሽ እህት እንዲኖርሽ ፈልገናል…የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ከመድረሳችን በፊት ያንቺን አስተያየት ማወቅ ስለፈለግን ነው የደወልንልሽ፡፡››
‹‹ብዥ አለባት…እናቴ በሰባ አመቷ አረገዘች እንዴ?››ስትል በውስጧ እራሷ ጠየቀች፡፡‹‹አባቴ የአብረሀምን አይነት የዋህነት ስላለው እግዜር በዚህ አድሜዋ የማዬን ማህፀን ቢከፍት አይገርመኝም››ስትል በራሷ ሀሳብ ሳቀችና ትኩረቷን ወደስልኩ መለሰች፡፡
‹‹አባዬ አልገባኝም..እንዴት ነው እህት ሊኖረኝ የሚችለው?››
አንድ የሁለት አመት ቆንጅዬ ሴት ልጅ በጉዲፈቻ ልንወስድ ነው….››
‹‹በጉዲፈቻ…በጣም ደስ ይላል….ጥሩ ውሳኔ ነው የወሰናችሁት..››
ሀሳባቸውን ለመደገፍ ጥቂት ማሰብ እንኳን አላስፈለጋትም…የሁለት አመት ጣፋጭ ልጅ እዛ ግዙፍ ቪላ ቤት ውስጥ ስትሯሯጥ…አንዴ አባቷ ላይ አንዴ ደግሞ እናቷ ላይ እየተንጠለጠች ስታስቃቸውና ሰታዝናናቸው፣እነሱም ሲያሞላቅቋት…እሷን መሀላቸው አድርገው ግራና ቀኝ እጇን ይዘው ወደቤተክርስቲያን ይዘዋት ሲሄዱ .... በአይነ ህሊናዋ ታያትና በደስታ ተፍለቀለቀች፡፡
‹‹ልጄ አሁን እሷን ልናይ ሆስፒታል ነው ያለነው ..ከቻልሽ ጋንዲ ነን …ብትመጪ ደስ ይለኛል፡፡››
መልሶ መደነጋገር ውስጥ ገባች‹‹ሆስፒታል…ምን ትሰራለች?››
‹‹ትንሽ አሟታል…ከቻልሽ ነይ፡፡››ደገሙላት፡፡
‹‹በቃ መጣው››……ስልኩን ዘጋችና ወደቢሮዋ ተመልሳ ለረዳቶቾ ወደስራ እንዲመለሱ ትዕዛዝ ሰጥታ ቦርሳውን አንጠልጥላ ወጣችና ቀጥታ ከፓርክ መኪናዋን በማንቀሳቀስ ስለአዲሷ እጩ እህቷ ምን እንደምትመስልና…ምኗን ታማ ሆስፒታል ልትገባ እንደቻለች እያብሰለሰለች ወደጋንዲ ሆስፒታል ነዳችው፡፡
ደርሳ ወደውስጥ ስትገባ ሰውነቷ መንቀጥቀጥ ጀመረ…ይሄ የተለመደ ስሜቷ ነው…ሆሲፒታል ሂጂ ከሚሏት ጦርነት ዝመቺ ብትባል ትመርጣለች…እንደምንም ግን ወደውስጥ ዘለቀች… አባቷን ደውላ አገኘችው…እጇን ይዞ እየመራ የተባለቸው ህፃን ወደተኛችበት ክፍል ይዟት ገባ፡፡ክፍሉ ውስጥ ከህፃኗ ጋር የገዛ እናቷ ብቻ ነች ያለችው፡፡ ከበራፉ አንድ እርምጃ ወደውስጥ ተራምዳ እንደቆመች ደንዝዛ ቀረች …ከዛ ማለፍ አልቻለችም፡፡
ፍፅም የሚባል ድንዛዜ ውስጥ ነው የገባችው…ልጅቷ ቢያንስ ከሶስት ማሽን ጋር በቱቦ ተያይዛለች…መልኳ ውብ ፀጉሯ ግንቧሯ ላይ ድፍት ያለ አጎጊ ብትሆንም ስልምልም ብላ እራሷን ስታ ተዘርራለች..እንደውም ነፍሷ ውስጧ እንዳለ እርግጠኛ መሆን አልቻለችም….
በቃ ውስጧ ግልብጥብጥ ነው ያለባት…ከአመታት በፊት ምትወደውና ልታገባው ስታልመው የነበረው እጮኛዋ ኪሩቤል እንዲህ እንደህፃኗ እራሱ ስቶና ዝርግትግት ብሎ በማሽን እገዛ ለመተንፈስ ሲያጣጥር የነበረው ትዝታ መጣባትና እራሷን ልትስት ተንገዳገደች..አጠገቧ ያለው አባቷ ፈጠን ብሎ ደገፋት…እናቷ በድንጋጤ ከተቀመጠችበት ተነሳችና ስሯ ደረሰች፡፡
‹‹ምነው ልጄ..አመመሽ እንዴ?››ሁለቱም ተቀባብለው ጠየቋት፡፡
‹‹አይ ደህና ነኝ …የመድሀኒት ሽታና የህክምና ማሽኖቹ ድምፅ ነው የረበሸኝ››
‹‹ቸሬ አንተ እኮ ነህ..እሷ ሆስፒታል እንዴት እንደምትጠላና እንደሚያማት እያወቅክ ነይ ያልካት፡፡››
‹‹እውነትሽን ነው አጥፍቻለው….በቃ ልጄ ነይ…ይሄን ያህል ካየሻት ይበቃሻል….ብለው እየጎተቱ ወደውጭ ወሰዷት…መኪናዋ ድረስ አደረሷት፡፡‹‹እርግጠኛ ነሽ ሰላም ነሽ…?መኪና መንዳት ትችያለሽ››
‹‹አታስብ አባዬ..ሰላም ነኝ..በቃ ተመለስ››
መኪና ውስጥ ገባታ ስትንቀሳቅስ አባትዬው ወደውስጥ ተመለሱ፡፡ቀጥታ ወደቤቷ ነው የሄደችው፡፡የልጅቷ ምስል ከአእምሮዋ ሊወጣ አልቻለም….ወላጆቾ ምን አስበው ያቺን በህይወት እና በሞት መካከል ባለች ቀጭን ክር ተንጠልጥላ ያለችን ልጅ በማደጎ ለመውሰድ እንዳሰቡ ሊገባት አልቻሉም…እንዴት አድርገው ሊንከባከቧት ነው…?ከለመዷትና ከወደዷት በኃላ ብትሞትባቸውስ…..?የሚወዱትን ሰው በሞት መነጠቅ እንዴት ልብን እንደሚሰብር እና ተስፋን እንደሚያከስም በራሷ ታውቀዋለች…እና በእሷ የደረሰ አይነት ሀዘን በዚህ እድሜያቸው በወላጆቾ እንዲድርስ አትፈልግም…፡፡
‹‹ግን ምን ማድረግ እችላለው?››ስትል እራሷን ጠየቀች፡፡እንዲሁ ስትብሰለሰል አደረች…ሳምንት ሙሉ አሰበችበት..አንድ ውሳኔ ወስና ለወላጆቾ ምንም ነገር ማለት ሳትችል…ወላጆቹ ህጋዊ የአሳዳጊነት ፕሮሰሱን ጨርሰው ልጅቷን ወደቤታቸው እንደወሰዱ ሰማች፡፡በቃ ከዛ በጊዜ ሂደት የሚሆነውን ጠብቃ ለመመልከት ወሰነችና ወደወላጇቾ ቤት ሄዳ አዲሷን እህቷን አየቻት…ምንም እንኳን ከዛ ሁሉ ማሽን ነፃ ሆና ብታያትም..አሁንም ግን በጣም ደካማ እና የሰለለ ሰውነት ያለት ሆና ነው ያገኘቻት፡፡ግን ደግሞ በዛው ልክ አሳዛኝና ተወዳጅ ልጅ መሆኗን መካድ አልቻለችም፡፡
============
ራሄል ከረዳቷ ጋር እያወራች ነው፡፡
‹‹ሮቤል ወ.ሮ ላምሮት ልገሳዋን ለእኛ ፋውንዴሽን እንድታደርግ አሁን በስልክ አናግሬታለው፡፡እሷን ማሳመን ከቻልኩ እና ውሳኔዋ ለእኛ ለመለገስ ከሆነ ለፋውንዴሽናችን ትልቅ ስኬት ነው››
ራሄል ወረቀቶቿን ወደ ቦርሳዋ አስገባች፣ አንድ አይኗ በእንጨት በተሸፈነው የቢሮዋ ግድግዳ ላይ በተሰቀለው ሰዓት ላይ ተሰክቶ ነበር።
‹‹ ለማውራት ጊዜ የለኝም። በሃያ ደቂቃ ውስጥ በወላጆቼ መኖሪያ ቤት በተዘጋጀው የምሳ ግብዣ ላይ መገኘት አለብኝ ››አለች፡፡
ረዳቷ ማንኛውንም አይነት ቅሬታ ከማንሳቱ በፊት አቋረጠችውና ‹‹ እንደገና ሴትዬዋ ከደወለች ብቻ አሳውቀኝ።››አለችው፡፡
ስልኳን ዘጋችና ሞባይሏን ቦርሳዋ ውስጥ ለትንሿ እህቷ ጸጋ ከገዛችው ትንሽ ስጦታ ጋር አስቀመጠችው፣ ፀጋ ወላጇቾ ሊያሳድጓት በቅርብ የተረከቧት እህቷ ነች፡፡ ራሄል ወደ መኪና ማቆሚያ ጋራዥ በፍጥነት በምትወርድበት ጊዜ የኖብል ፋውንዴሽን ቢሮዎችና ኮሪደሮች በፀጥታ ተውጠው ነበር።

❤91🔥2😱1