አትሮኖስ
284K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
514 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የኛ_ዘመን

እግዜር ከግር በፊት ፤ መንገድን ፈጠረ
እግር ያለው ፍጥረት፤ መንገዱን አጠረ
ከለለና ኖረ ፤
ይኸው በኛ ዘመን ፤
መንገድ በሌለበት ፤ እግር ብቻ ቀረ
                               
🎴በረከት ታደሰ🎴

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍15👏4🥰21🔥1😁1
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ:
እባክሽ አትሂጂ…..
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-ስምንት


ሆስፒታል እስከአስር ሰዓት ቆየሁና የእለቱን ስራዬን አጠናቅቄ ቅፅር ግቢውን ለቅቄ ወጣሁ፡፡መሄድ የነበረብኝ ቀጥታ ወደ እማዬ ቤት ነው፡፡ምክንያቱም እንግዳዬን ጥዋት ወስጄ እዛ እንደተውኳት ስልክ ደውዬ እንኳን እንዴት እንደሆነች አልጠየቅኳትም፡፡እሷም እስከአሁን አለመደዋሏ ገርሞኛል፡፡እርግጥ እስከአሁን አዛ ላትሆን ትችላለች፡፡ቢሆንም እዛ ሄጄ‹‹ ላገኝሽ እኮ እማዬ ጋር መጥቼ አጣሁሽ ››ማለት ይገባኝ ነበር፡፡
እኔ ግን ይሄው ሁሉን ነገር ችላ ብዬ ወደልዕልት እየነዳሁት ነው፡፡እርግጥ ከነጋ ሁለቴ ደውዬ በሽተኛ ባሏም ሆነ እሷ እንዴት እንደሆኑ  ጠይቄ ሁሉም ነገር ሰላም መሆኑን መረዳት ችያለሁ፡፡ቢሆን ግን በተለይ የእሷን ደህንነት በአይኔ አይቼ ካላረጋገጥኩ የሰላም አዳር እንደማላድር እርግጠኛ ስለሆንኩ ወደእሷው እያመራሁ ነው፡፡እንደተለመደው ሰፈራቸው ስንደርስ ደምበኛ ወደሆኑኩት አንድ ሱፐር ማርኬት ጎራ አልኩና ለልጆቹ ቸኮሌት ለእሷ ደግማ አንቡጥ ፅጌረዳ ገዛሁና ጉዞዬን ቀጠልኩ፡፡ስደርስና የመኪናዬን ክላክስ ሳሰማ ሊከፈትልኝ አልቻለም.፡፡ከመኪናዬ ወረድኩና የጊቢውን ሳይረን በመጫን መጠበቅ ጀመር…በራፉ ተከፈተና ፀሀይ ከፊቴ ፈነጠቀች…ጨረቃ ግማሽ ውበቷን አሳየችኝ… ከዋክብቶቹ ዙሪያዬን ብርሀናማ ቀለማቸውና መርጨት ጀመሩ…ተንደርድሬ ስጠመጠምባት…ያለፉትን አንድ አመት ሳላያት ቆይቼ ናፍቆቷ የበላኝ ነው የሚመስለው…እግዜር ይስጣት እሷም በተመሳሳየ በሞቀና በደመቀ ሰላምታ አፀፋውን መለሰችልን፡፡
‹‹ውይ ዶ/ር ትመጣለህ ብዬ ፍፅም አልጠበቅኩም ነበር››
‹‹እና ልመለስ?››
‹‹እንዴ…በመምጣትህ  በጣም ደስ ብሎኛል እያልኩህ እኮ ነው››
‹‹እኔም እቅዴ እንዲህ ደስ ላሰኚሽ ነበር…››
‹‹እንግዲያው ተሳክቶልሀል..በል መኪናዋን አስገባት በራፉን ልክፈትልህ፡፡›› ብላ ወደውስጥ ተመልሳ በራፉን ስትከፍት እኔ ወደመኪናዬ ተመልሼ  መኪናዋን ወደውስጥ አስገባሁና ካቆምኩ በኃላ ሞተሩን አጥፍቼ እንደወትሮዬ አበባውን እዛው መኪናው ውስጥ ትቼ የቼኮሌት ፓኮውን ብቻ ይዤ ወረድኩ፡፡በረንዳ ላይ ቆማ እየጠበቀቺኝ ነበርና ወደእሷ አመራሁ፡፡እስኪ ምን አለ ትንሽ ድፍረት የሚያበድረኝ ሰው ቢኖርና የገዛሁትን አበባ ከመኪናው ይዤ መውረድና እንዲህ እየተፍለቀለቀች እያለች መስጠት ብችል፡፡እንደማልችል ካወቅኩ ደግሞ  ምን አለ መግዛቴን ባቆም፡፡
‹‹ዶ/ር  ዛሬም?››
‹‹ምኑ ?››
‹‹ይሄ ቸኮሌት ነዋ፡፡››
‹‹ምንችግር አለው…ቀላል ነገር እኮ  ነው፡፡››
‹‹ቢሆን ዶ/ር ..እያስቀየምከኝ ነው፡፡››
‹‹እሺ ሁለተኛ አልደግመውም…››ቃል እየገባሁ ተከታትለን ወደ ውስጥ ገባን፡፡
‹‹ቁጭ በል፡፡››
‹‹መጀመሪያ መስፍኔን ልየው››
‹‹ትቸኩላለህ እንዴ?››
የዚህ ጥያቄ አቅጣጫ አልገባኝም..ግን ዝም ብዬ‹‹አይ አልቸኩልም››ስል መለስኩላት፡፡
‹‹አሁን ሰውነቱን አጣጥቤው.እንቅልፍ ነገር አሸልቦታል…አረፍ በልና ትንሽ ቆይተህ ልትሄድ ስትል ታየዋለህ፡፡››
‹‹ጥሩ ልጆቹን ጥሪልኝና የመጨረሻ ቸኮሌታቸውን ልስጣቸው…፡፡››
‹‹አምጣው… እኔ ወኪል ሆኜ ሰጥልሀላሁ.ወንድሜ መጥቶ ወደከተማ ይዞቸው ወጥቷል፡፡ ቤት ውስጥ ብቻዬን ነኝ፡፡››ብላ ተቀበለቺኝ፡፡
‹‹እንግዲያው በትክክለኛው ሰዓት ነዋ የመጣሁት፡፡››
የድንጋጤ አስተያየት አየችኝና…‹‹እንዴት ዶክተር?››ስትል ጠየቀቺኝ፡፡እውነት እንዴት ?ትክክለኛ ጥያቄ ነው የጠየቀቺኝ? ምን ለማለት ፈልጌ ነው?
‹‹ማለቴ እንዳይደብርሽ ጥቂትም ቢሆን አወራሻለሁ ለማለት ነው፡፡››
‹‹አዎ ትክክል ነህ…መጣሁ፡፡›› ብላ ወደውስጥ ገባችና ኩኪስ እና ዳቦ ቆሎ የመሳሰሉትን ነገሮች በሰሀን ይዛ መጣችና አጠገቤ አድርጋ..‹‹ ምርጫህን ሳልጠይቅህ ብና ጥጄለሁ…››አለችኝ፡፡.
‹‹ደስ ይለኛል›› አልኳት…ፊት ለፊቴ ተቀመጠች…
ከዳቦ ቆሎ ዘገን አድርጌ እየቆረጠምኩ..ስለእሷ የሚቆረጥመኝን ጥያቄ ጠየቅኳት፡፡
‹‹መስፍን ግን ታድሏል››
ድንግጥ አለች…..ብትደነግጥ አይፈረድባትም…አንዴት በአልጋ ላይ ተዘርሮ ተኝቶ ለህይወቱ እየለመነ ያለ ሰው ታድሏል ይባላል.. ብላ አስባ እንደደነገጠች ተረድቼለሁ..እኔ ታድሏል ያልኩት ግን  በዛ መልኩ አይደለም‹‹አይ ማለት.. ያለበት ሁኔታ አስቸጋሪና በስቃይ ተሞላ እንደሆነ አውቃለሁ ..እንደዛም ቢሆን ግን አንቺን የመሰለች..ውብ…ቀና …እርሁሩህና ..የተሟላች ሴት ስላለችው ማለቴ ነው፡፡››
‹‹አይ ዶ/ር..አሁን እሱ ባለበት ሁኔታ እነዚህ እኔ ላይ አሉ ብለህ የጠቀስካቸው ነገሮች ምን ይረቡታል.?.እኔ ሳልኖረው ጤናው ሙሉ ቢሆን የበለጠ እድለኛ ይባል ነበር፡፡››
‹‹አይ አይመስለኝም…..መቼስ ምረጥ ቢባል አንቺ ኖረሽው ሌላውን መከራ መጋፈጥ እንደሚመርጥ እርግጠኛ ነኝ፡፡››
ግማሽ ሳቅ ሳቀች..መገረም ያጀበው ሳቅ…‹‹አይ ዶ/ር…ነገሮችን ወደራስ ወስዶ ማሰብ ጥሩ ነው››
‹‹ማለት?››
‹‹ለምሳሌ አንተ በራስህ ውሰደው…ከፍቅረኛህ ጋር ሆነህ እንዲህ አይነት ችግር ላይ መውደቅ ነው…ወይስ ፍቅረኛህን አጥተህ በሙሉ ጤና መኖር ነው የምትመርጠው?››
‹‹ፍቅረኛዬ ሁለ ነገሯ ማለት መልኳ ፀባዬ..ስነ-ምግባሯ… እናትነቷ  እንደአንቺ ከሆነች..ለምን ዘላለም አልጋ ቁራኛ አልሆንም፡፡››
‹‹እንዴ ዶ/ር ሰው ከላይ እንደሚታየው አይደለም እኮ..ስለእኔ ስታወራ  ስለሌላ ሴት ምትተርክልኝ ነው የምትመስለው፡፡እኔም እኮ ያው ሰው ነኝና ለመስፍን የማይመቹት  ባህሪያቶች ይኖሩኛል፡፡››
‹‹አንቺ ..ፈፅሞ ይንን ማሰብ አልችልም….እስኪ እንዴት ተዋወቃችሁ..?ማለቴ ከመስፍን ጋር?›› 
አይኖቾ ቦዘዙ…ከንፈሯን ሸረፍ አደረገችና በሚንቦገቦጉ አይቾን እያነከባለለች መናገር ጀመረች፡፡‹‹መስፍኔን በጣም አፍቅሬው በእንብርክ ሄጅና ለምኜ ነው ያገባሁት››አለቺኝና በትዝታ ባህር ሰመጠች፡፡
ንግግሯ ምኑም አልገባኝ ..አፍቅራ እሺ ታግባው..እንዴት ነው በእንብርክክ ሄዳና ለምና ልታገባው የምትችለው…? ፡፡የመስፍንን አቋሙንና ጠቅላላ መልኩን በምናቤ አስብኩት…እርግጥ እኔ የማውቀው በበሽታ ከተዳከመና ከጠቋቆረ በኃላ ነው..ቢሆንም ያንን ከግንዛቤ በማስገባት የማውቀው ውበቱን በግማሽ ብጨምርለት እራሱ አሁን እሷ ካላት ውበት፤ ፀባይና ድምቀት አንፃር  እሷን ለማኝ እሱን ተለማኝ አድርጎ ለማሰብ ፈፅሞ አይቻለኝም፡፡ምን አልባት ስለመስፍኔ  ፀባይ ስብዕና፤ያፈቀራትን ሴት የመንከባከብ ብቃት..ከዛም አልፎ የወሲብ ብቃቱ ምንም የማውቀው ነገር ስለሌለ ሚዛን ላይ አስቀምጬ ፍርድ ልሰጥበት አልችልም   ግን ደግሞ ሌሎቹን እንኳን ለጊዜው ብንተወው ስብዕናና ፀባይን በተመለከተ ልዕልትን ለመወዳደር የሚችል ሰው በቀላሉ ይገኛል ብዬ አላስብም….እንዴ የመላዕክት ዝርያ ያለባት እኮ ነው የምትመስለው፡፡ለማንኛውም እሷ ማውራት ሰለጀመረች እኔ የተበታተነ ሀሳቤን ሰባስቤ እሷን ወደ ማዳመጡ አዘነበልኩ፡፡

ከአስር አመት በፊት ነው..ትዝ ይለኛል..በረንዳ ላይ ሆኜ ፀጉሬን እያበጠርኩ ነበር፡፡እዚህ ቤት ውስጥ ከሴት አያቴ ጋር ነበር የምኖረው..እቤቱ የሴት አያቴ ነው፡፡እኔን በልጅነቴ ጡት አስጥላ ነው ከወላጆቼ የወሰደችኝ…እና በራፋ  ሲንኳኳ  የተንጨፈረረ ፀጉሬን እየላግኩ ሄድኩና በራፉን ከፈትኩት…በራፍ ላይ ቆሞ የማየውን ወጣት ለመጀመሪያ ጊዜ የልቤን መሰንጠቅ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ያተረዳሁበት ነው፡፡ጠይም አሳ መሳይ መልክ..ዝንጥ ያለ አለባበስ፣..በስርዓት የተበጠረ አፍሮ ፀጉር….ነጭ ሀጭ በረዶ የሚመስሉ ችምችም ብሎ የተደረደሩ ጥርሶች..ዝም ብዬ ከላይ
👍389😁2🤔1
እስከታች አይኖቼን እያንከባለልኩ  አያው ጀመረ..
‹‹ቆንጂት እኔን የመሰለ ሰው ጠፍቶብሻል እንዴ?››ብሎ ሲጠይቀኝ ነው..ከድንዛዜዬ በመጠኑ የባነንኩት፡፡
‹‹አይ እንዲሁ ነው…ምን ፈልገህ ነው?››ስል የሞት ሞቴን ጠየቅኩት፡፡ 
‹‹የሚከራይ ቤት እንዳለ ተነግሮኝ ነበር›››ሲል ልቤ በውስጤ ስትጨፍር ይታወቀኝ ነበር…ወዲያው በራፉን በርግጄ ከፈትኩና ከመንገዱ ገለል አልኩለት፡፡እሱ ታዲያ ከቆመበት ሳይነቃነቅ..በሚዋጉ አይኖቹ አጨንቁሮ እየተመለከተኝ…..‹‹አለ ወይንስ የለም?››ሲል ደግሞ ጠየቀኝ፡፡
‹‹ከፈትኩልህ እኮ››
‹‹አሀ በእናንተ ቤት ቋንቋ በራፍ መክፈት ማለት አለ ማለት ነው?››አለና ፈገግ እያለ ወደውስጥ አልፎ ገባ፡፡ በራፉን ዘጋሁና በጓሮ በኩል ከተደረደሩት ሰርቢስ ቤቶች ውስጥ ለኪራይ ባዶ የሆኑትን ሁለት ክፍል ለማሳያት አስከትዬው እየመራው መሄድ ጀመርኩ..ሌላ ሰው ቢሆን እኮ አያቴን ጠርቼ ከእሷ ጋር በማጋፈጥ ወደፀጉር ማበጠሬ ነበር የምመለሰው፡፡ወይ አጉል የፍቅር ወሬ አስጀምረኸኝ ብናውን አስረሳሀኝ ይሄኔ ተንተክትኮ አልቋል….መጣሁ››ብላኝ በትኩረትና በጉጉት አያዳመጥኳት የነበረውን የፍቅር ታሪኳን አቆርጣ ወደ ውስጥ ሄደች…ከኃላ በተመስጦ ተመለከትኳት…በቢጃማ ውስጥ የተከተተ ውብ ገላዋን በመጎምዠት እየተመለከትኩ ሸኘኋት..እኔ አሁን ባለሁበት ሁኔታ ብና የመጠጣት ምንም አይነት ፍልጎት የለኝም……ከዛ ይልቅ የጀመረችልኝን አጉልና አብሻቂ የፍቅር ትረካዋን ብትቀጥልልኝ  ደስተኛ እሆን ነበር፡፡
ከ3  ደቂቃ በኃላ  ቡናዋና በፌርሙዝ ሞልታ ከሁለት ሲኒ ጋር ይዛ በመምጣት እየቀዳችልኝ ሳለ..ከውጭ ብዙ የእግር ኮቴ እና  የድምፅ ጫጫታ ተሰማ …ወዲያው ሳሎኑ ተከፈተና ልጆቾ እየተንጋጉ ገቡ…ሁለቱም እኔን ሲያዩ ተንደርድረው መጥተው ተጠመጠሙብኝ….ከኃላ ሰራተኛዋ ትንሿን ልጅ እንደታቃፈች መጣችና ለልዕልት አስተቀፋቻትና  ወደጓዲያ ሄደች፡፡.ትንሽ ዝግ ብሎ አንድ እድሜው አርባ አካባቢ የሚገመት ባለግርማ ሞገስ ሰው በዝግትታ እርምጃ እኛ ወዳለንበት ተጠጋ…

ይቀጥላል...
ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍366
#ትንግርት


#ክፍል_አርባ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ዶ/ር ሶፊያ በቀኝ ፊቷ ላይ ከሚታየው የተላላጠ ጠባሳ በስተቀር ሙሉ ለሙሉ ከደረሰባት አደጋ አገግማለች ፡፡ወደ ስራዋ መመለስ ብትፈልግም የታዲዬስ ልጆች ግን እስከዛሬዋ ቀን ድረስ አቆይተዋታል፡፡ለዚህም ሰበባቸው የፅዬንን የምረቃ በዓል አብራቸው እንድታከብር ስለፈለጉ ነው፡፡ፅዬን የሙዚቃ ባለሞያ ብትሆንም በህግ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ከሁለት ቀን በፊት ተመርቃለች ..ዛሬ ደግሞ በታዲዬስ ቤት የእንኳን ለዚህ አበቃሽ ዝግጅት ተዘጋጅቶላታል፡፡

ዶ/ር ሶፊያም እንግዳ ከአሜሪካ ድረስ መጥቶባት አዲስአባ እሷ ቤት ቁጭ ብሎ እየጠበቃት እንደሆነ ተደውሎ የተነገራት ቢሆንም ይሄንን ዝግጅት ረግጣ ችላ ብላ መሄድ ስላልተቻላት ከጉዞዋ ቀርታለች፡፡
የዝግጅቱ ዋና አቀናጆች አላዓዛር ፣ቤተልሄም እና የታዲዬስ ልጆች ሲሆኑ የወጪውን 9ዐፐርሰንት የሸፈነው ታዲዬስ ነው፡፡ሁሉ ነገር ተዘጋጅቶ በመጠናቀቅ ወደ ዝግጅቱ የተገባው ከምሽቱ 1 ሰዓት ነው፡፡ዝግጅቱን ከታደሙት ውስጥ የውጭ ሰዎች ሶስት ብቻ ናቸው፤ሌሎች ጠቅላላ የቤተሰቡ አባል ናቸው፡፡

የእራት ፕሮግራሙ ከተጠናቀቀ በኃላ፤ የፕሮግራሙ መሪ መምህር ዓላዛር ወደ ፊት ወጣ ‹‹እንግዲህ የዛሬውን ፕሮግራም የጀግናዋ እህታችን የምረቃ ክብረ በዓል በማስመልከት የተዘጋጀ ነው...እንኳን አደረሰሽ..እንኳን ደስ ያለሽ እያልናት ነው፡፡ ፂ ለእኛ ምርጥ እህታችን ብቻ ሳትሆን መልካም አርአያችንም ነች፡፡ይቺን የእሷን የስኬት ቀን ለማክበር እነ ሄለን ለአንድ ወር ሲጥሩ እና ሲዘጋጁ ነበር፡፡ይሄ ዝግጅት በዋናነት የእነሱ ስለሆነ እያንዳንዳቸው ለእሷ ያላቸውን መልካም ምኞት እንዲገልጹላት መድረኩን ተራ በተራ እሰጣቸዋለሁ፡፡መጀመሪያ ሚጡ ወደ እዚህ ነይና ለጺ የምትያት ነገር ካለ እድሉን ልስጥሽ፡፡››

ሚጡ ቆንጆ ሆና፣ነጭ የአበሻ ቀሚስ ለብሳ፣ትንሽ ሞዴል ወይዘሮ መስላ አላዓዛር ወደ ቆመበት ቦታ መጣችና ቆመች፡፡በእጇ አንድ ወረቀት ይዛለች፡፡ሁሉም ሰው እሷ ላይ ሲያተኩርባት ተደነጋገራት፡፡ወደ ታዲዬስ ፊቷን አዞረች ፡፡‹‹...በርቺ.. አይዞሽ >>ብሎ አበረታታት፡፡መናገር ጀመረች፡፡

.....‹‹ፅዬን እንኳን አደረሰሽ፡፡እኔ በጣም ነው
የምወድሽ፡፡ እኔንም እንደ እነ ሄለንና ሀሊማ ሙዚቃ እንድታለማምጂኝ በጣም እፈልጋለሁ፡፡

ፒያኖ ስትጫወቺም፣ ስትዘፈኚም ደስ ትይኛለሽ፡፡ዛሬ ተመርቀሽ የለበሽው ጥቁር ቀሚስም በጣም ያምርብሻል እና ደግሞ
እኔም እንዳንቺ በደንብ ተምሬ አሁን የለበሽውን
መልበስ እፈልጋለሁ፡፡…››ለተወሰነ ሰከንድ ፀጥ
ብላ ትንፋሽ ወሰደችና ቀጠለች፡፡‹‹...ላንቺ አንድ ግጥም ገጥሜልሻላሁ ...ማን
እንደምታስፈቅድ ባይታወቅም‹….ላንብብ ? >
አላችና ጠየቀች.. ፡፡ሁሉም በአንድ ላይ ‹‹..ጎበዝ አንብቢ….አንብቢ›› አበረታቷት ….ጀመረች፡፡

የግጥሜ ርዕስ

‹ጥቁር ቀሚስ› ነው

‹ጥቁር ቀሚስ›

ኮንግራ ብያለሁ... ፅዮንዬ እናቴ በጣም ነው ምወድሽ… ፍፁም ከአንጀቴ ምርጥ ሙዚቀኛ….ድንቅ መምህር ነሽ ከጎኔ ስትሆኚ ....ደስ ትይኛለሽ ጥቁር ቀሚስ ልበሽ ...ኮፍያም አጥልቂ የላብሽ ውጤት ነው...ኩሪ ተነቃቂ እንኳን አደረሰሽ... ፅዮን ወድሻለሁ እንደአንቺ ለመሆን ...በርትቼ አጠናለሁ፡፡

‹‹...ስላዳመጣችሁኝ አመሰግናለሁ›› አለችና ወደ ፅዬን በመሄድ ጉንጯን ሳመቻትና ግጥም የተፃፈበትን ወረቀት በእጇ አስጨበጠቻት.. ፅዬንም በተራዋ ወደራሷ ጎትታ፣ከደረቷ ለጥፋ በማቀፍ ሙጭምጭ አድርጋ ትንፋሽ እስኪያጥራት አገላብጣ ሳመቻትና‹‹እኔም በጣም ነው የምወድሽ›› አለቻት፡፡

ቀጥሎ ዕድሉ የተሰጣት ለሰላም ነበር፡፡ሰለም እያነከሰች ቢሆንም በእጇ ለፅዬን ያዘጋጀችላትን ስዕል ይዛ ወደ ፊት ወጠችና ንግግር ጀመረች‹‹እኔ እንደምታዩኝ ሸንካላ ነኝ...›› ድንገተኛ ሳቅ በቤቱ ፈነዳ.…ሁሉንም ያሳቃቸው የእሷ እግር አንካሳነት ሳይሆን አገላለጿ ነበር ፡፡ ‹‹....አዎ እውነቴን ነው ...በፊት በፊት በዚህ ጉዳይ በጣም እበሳጭ ነበር፤ይህን እግሬን እንዲህ ያደረገኝ የገዛ አባቴ ነው....ግን ብቻውን ያደረገው አይመስለኝም ነበር፡፡አዎ እግዚያብሄርም ያገዘው ይመስለኝና ሁል ጊዜ ተደብቄ በማልቀስ ሁለቱንም እወቅስና አማርር ነበር ፡፡ በተለይ ትምህርት ቤት አንዳንድ ልጆች



ሲያሾፍብኝ..እንደእነሱ ዘልዬና ተሯሩጬ መጫወት እያማረኝ ያንን ማድረግ ሳልችል ስቀር ..በጣም ያበሳጨኝ ነበር፡፡

ትምህርት ቤት ይሄንን የውስጥ ንዴቴን

ይበልጥ የሚያባብስ ስም ሁሉ አውጥተውልኝ

ነበር < ካንጋሮ› ነበር የሚሉኝ፡፡ አረማመድሽ

የካጋሮን ይመስላል ማለታቸው መሰለኝ፡፡ ብቻ

በወቅቱ ታዲዬስን እየፈራሁ እንጂ ትምህርቱ

ከነጭራሹ ቢቀርብኝ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ውሎ

አድሮ ግን ከዚህ ሁሉ ስቃይ እንድወጣ ፅዬን

አርአዬ ሆነች፡፡በቃላት እየመከረች አይደለም

ያስተማረቺኝ ፤በምግባሯ እንጂ፡፡ሁለት ዓይኖቿ

አያዩላትም፤ግን ከሚያዩት በላይ

ታስተውላለች፣ከዓይናማዎቹ በላይ ውጤታማ

ነች፡፡ማድረግ የፈለገችውን ነገር ለማድረግ

ዓይኖቿን ሰበብ በማድረግ ስታማርር እና

ስትሰንፍ አይቻት አላውቅም፡፡ታዲያ እኔስ

የተሰናከለችብኝን አንድ እግር እያሰብኩ ቀሪ

ህይወቴን ሙሉ እንዴት ጓዶሎ አደርጋለሁ..?

ብዬ ጠነከርኩ፡፡ የሚያሾፉብኝን ልጆች በፊት
ሲያሾፍብኝ..እንደእነሱ ዘልዬና ተሯሩጬ መጫወት እያማረኝ ያንን ማድረግ ሳልችል ስቀር ..በጣም ያበሳጨኝ ነበር፡፡

ትምህርት ቤት ይሄንን የውስጥ ንዴቴን ይበልጥ የሚያባብስ ስም ሁሉ አውጥተውልኝ ነበር < ካንጋሮ› ነበር የሚሉኝ፡፡ አረማመድሽ የካጋሮን ይመስላል ማለታቸው መሰለኝ፡፡ ብቻ በወቅቱ ታዲዬስን እየፈራሁ እንጂ ትምህርቱ ከነጭራሹ ቢቀርብኝ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ውሎ አድሮ ግን ከዚህ ሁሉ ስቃይ እንድወጣ ፅዬን
አርአዬ ሆነች፡፡በቃላት እየመከረች አይደለም

ያስተማረቺኝ ፤በምግባሯ እንጂ፡፡ሁለት ዓይኖቿ
አያዩላትም፤ግን ከሚያዩት በላይ ታስተውላለች፣ ከዓይናማዎቹ በላይ ውጤታማ ነች፡፡ማድረግ የፈለገችውን ነገር ለማድረግ
ዓይኖቿን ሰበብ በማድረግ ስታማርር እና ስትሰንፍ አይቻት አላውቅም፡፡ታዲያ እኔስ የተሰናከለችብኝን አንድ እግር እያሰብኩ ቀሪ
ህይወቴን ሙሉ እንዴት ጓዶሎ አደርጋለሁ..?
ብዬ ጠነከርኩ፡፡ የሚያሾፉብኝን ልጆች በፊት
አዝንባቸው ነበር ፤አሁን ግን አዝንላቸው ጀምሬያለሁ፡፡.ባለማወቃው ነው .፡፡

ሰው ለሀገሩም ለቤተሰቦቹም ሸክም የሚሆነው የአካል ጉዳተኛ ስለሆነ ሳይሆን ፤ የአስተሳሰብ ጉዳተኛ ሲሆን ነው፡፡ፅዬን ያንን እንድረዳ ስላረግሺኝ አመሰግናለሁ፡፡ እንኳን ደስ ያለሽ፡፡ይሄ ስጦታዬ ነው›› ብላ ወደ እሷ በመሄድ በገዛ እጆቿ የተሳላውን ስዕል አበረከተችላት... ሁሉም በጭብጨባ አጀቧት፡፡

ቀጥሎ የጽዮን የሙዚቃ ተማሪ የሆኑት ሄለን እና ሀሊማ ናቸው ወደ መድረክ የወጡት፤ ግን አልተናገሩም፡፡ ከታዳሚዎቹ ፊት ለፊት ወደሚታዩት ፒያኖ እና ጊታር ነው የሄዱት፡፡ ሀሊማ ጊታሩን ስትይዝ ሄለን ፒያኖውን ያዘች፡፡ ከዛ መጫወት ጀመሩ ፡፡ኮሽታ እንኳን አልነበረም፡፡ ፀጥ ባለ ድባብ በፍፅም ተመስጦ ነበር ሁሉም ጆሮውን ሰጥቶ ሚያዳምጣቸው ፡፡ ሙዚቃው ለሁሉም ጆሮ አዲስ ልዩ ጣዕም ያለው የሚያንሳፍፍ ነበር፡፡ከሁሉም ዕድምተኛ በተለየ መልኩ በዚህ ሙዚቃ የጽዮንን ያህል የተመሰጠ ፣የተገረመና ግራ የተጋባ ሰው አልነበረም፡፡ከየት አገኙት…? ማ
አለማመዳቸው…?ይሄን ድንቅ የሙዚቃ ድርሰትስ ማን ደረሰላቸው....? የዚህን ያህል ደረጃቸው እንዳደገ ገምታ አታውቅም ነበር.፡፡
👍599🤔3
ሲጨርሱ ከመቀመጫዋ ተነስታ እነሱ ወደሉበት ሄደች... አቀፈቻቸው፤ ሁለቱንም አገላብጣ ሳመቻቸው፡፡እነሱም አንዷ ቀኝ ሌላዋ ግራ ጆሮዋ ላይ ተለጠፉባትና‹‹ እንወድሻለን›› አሏት..እሷም ድምፆን ከፍ አድርጋ‹‹እኔም
በጣም በጣም እወዳችኋለው...ደግሞ በጣም በጣም ኮርቼባችኋለው፤አሁን ስራችሁን ይዛችሁ ወደ አደባባይ የምትወጡበት ጊዜ.መቃረቡንም እንድገነዘብ አድርጋችሁኛል፤ በጣም ነው ያስደመማችሁኝ፤ ችሎታችሁ በአይድል
ከመወዳደር በላይ ነው፡፡›› አለቻቸውና ወደ መቀመጫዋ ተመለሰች..፡፡

ቀጥሎ ዓላዛር ዕድሉን የሰጠው ለሙሴ ነው‹‹...ሙሴ ለፅዬን ስጦታ አለኝ ብሏል ... ሙሴ ወደ እዚህ መጥተህ ስጦታህን ስጣት›.

ሙሴ ኮሪደር አካባቢ ለብቻው ፈንጠር ብሎ የሆነ መነጽር የመሰለ ነገር በእጁ ይዞ ተቀምጧል ..ስሙ እየተጠራ ቢሆንም አልተንቀሳቀሰም፡፡

‹‹ሙሴ ትሰማኛለህ…?ለእህታችን ፅዬን ልትሰጣት ያዘጋጀኸውን ነገር ናና ስጣት…፡፡››

አሁንም ንቅንቅ አላለም..ታዲዬስ ከተቀመጠበት ተነሳና ወደ ሙሴ ሄደ ፡፡በርከክ አለና በሹክሹታ ማንም ያልሰማውን ነገር ነገረው፤ከዛ ሙሴ ከመቀመጫው ተነሳና
ታዲዬስን ተከትሎ ወደ ጽዮን በመሄድ የያዘውን
መነፅርና አነስተኛ ሪሞት በእጇ አስይዟት ወደ
መቀመጫውም ሳይሆን ቤቱን ለቆ ወደ ራሱ
ምርምር ክፍል ተፈተለከ፡፡ለእሱ ፀባይ እንግዳ
የሆኑ በእለቱ የተጋበዙ ሰዎች ግራ ገባቸው፡፡

አንደኛ የልጁ ፀባይ፤ ሁለተኛ ስጦታ ብሎ
የሠጣት ነገር መነፅር መሳይ ነገር ቢሆንም
ምኑም የማያምር መሆኑ…፡፡ በዛ ላይ ከጆሮው
ጋር የሚያገናኘው ዘንግ ላይ አነስተኛ ብትሆንም ትንሽ ሳጥን ነገር አለው፤ይሄ ደግሞ ለማድረግ ምቹ አይመስልም..፡፡ከዛ ይልቅ አሁን ጽዮን ያደረገችው ጥቁር መነፅር በጣም ዘናጭ እና ውበት ያለው ነው፡፡

ጽዮን እራሷ የተሰጣት ስጦታ ግራ ቢገባትም ‹‹አመሰግናለሁ ሙሴ..››አለችው፡፡ ከእሱ ምንም ዓይነት ነገር አልጠበቀችም ነበር፤ዝግጅቱ ላይ መገኘቱም ገርሟታል፡፡ አንዳንዴ ስታስበው የሚያውቃት ሁሉ አይመስላትም፡፡ ምንም ይሰጣት ምንም ሀሳቡ እራሱ አስደምሟታል..፡፡በአጠቃላይ በእነዚህ ልጆች ፍቅር ልቧ እየተፈረካከሰ እና ብትንትኗ እየወጣ ነው፡፡በፍቅር መፈረካከስ፣በፍቅር መበታተን፣በፍቅር መቅለጥ፣በፍቅር መፍሰስ በጣም ያስፈራል፡፡

ታዲዬስ በዓላዓዛር ፍቃድ ባይሰጠውም መድረኩን ተረክቦ መናገር ጀመረ‹‹ይቅርታ አላዓዛር ... ለሙሴ እንደ ዓሮን ሆኜ ልናገርለት ነው...ሙሴ የምታውቁት እንደምታውቁት መስራት እንጂ መናገር አይችልም፡፡ይሄንን ለፅዬን የሰጣት ስጦታ ስታዩት ግራ ሚገባ
ብዙም ውበት የሌለው ነገር ነው፤እኔ ይሄንን ያየሁት ትናንትና ነው፡፡ሙሴ ግን ስድስት ወር ሙሉ ለፍቶበታል …ደክሞበታል፡፡ፅዬን እውነቴን ነው ትናንትና አሁን በእጅሽ ስላለው ልዩ

መሳሪያ ሙሴ ሲያስረዳኝ እንባዬን መቆጣጠር
አቅቶኝ ከስንት አመት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳላስበው አለቀስኩ፡፡ማልቀስ ብቻ ሳይሆን ባንቺም ቀናውብሽ ፡፡››

ታዲዬስ ይሄን ሲናገር ጽዮን ግራ ገብቷታል፡፡ በዓይኗ ባታይም በእጇ ዳግመኛ በመዳበስ የዕቃውን ምንነት ለማጣራት ሞከረች፡፡አሁንም አልገባትም..፡፡በታዲዬስ ንግግር ጽዮን ብቻ አይደለችም ግራ የተጋባችው ዶ/ር ሶፊያም እንጂ‹‹ ምን ሰጥቷት ይሆን? ››ስትልም በውስጧ እያብሰለሰለች ነው፡፡ ‹‹ታዲዬስ እንዲህ ያስገረመውና ያስደመመው ነገር በጣም የተለየ መሆን አለበት >>ስትል የነገሩን ምንነት ለማወቅ ያላት ጉጉት ጨመረ ፡፡ በተጨማሪም ታዲዬስ እንዳለው እሷም በፅዬን ቀንታለች፡፡እሷን በዚህ መጠን በአሁኑ ሰዓት የሚወዳት ሰው ባለመኖሩ የባዶነት ስሜት ተሰማት፡፡ለፅዬን ሚጡ የገጠመችላት ግጥም፣እነሀሊማ የተጫወቱላት ልዩ ጥዑመ ዜማ ፣ሰላም ያበረከተችላት በትናንሽ እጆቾ የተሳለ ስዕል..አሁን ለማንም ግድ የማይሰጠው ሙሴ እንኳን ምንም ሆነ ምን ያበረከተላት ስጦታ ‹‹ታድላ፡፡ >>አለች፡፡

‹‹የዚህን ቤት ፍቅርማ የግሌ ማድረግ አለብኝ፡፡

በምንም መስዋዕትነት ቢሆን የዚህ ቤት አካል
መሆን አለብኝ››በማለት በውስጧ ውሳኔ አስተላለፈች፡፡ ለዚህ ተስፋ የሰጣት ደግሞ በትንግርት የደረሳባትን አደጋ ተከትሎ ታዲዬስ ለእሷ ሲያሳይ የከረመውን አዲስ አይነት
ቀናነትና አሳቢነት ነው፡፡ ታዲያ ‹ብረትን መቀጥቀት እንደጋለ ነው› እንደሚባለው
እሷም ይሄ በታዲዬስ ላይ የተከሰተው አዲስ ስሜት ሳይቀዘቅዝ ቀስቷን መወርወር አለባት፤እሱን በፍቅር ለማንበርከክ ፤ ከዛ የዚህ ታሪካዊ ቤተሰብ አባል መሆን፡፡እርግጥ ባለፈት ህይወቷ ተከስተው ያልተዘጉ ሁለት የፍቅር
ታሪኮች አሁንም ከጀርባዋ አሉ፡፡አንዱ የትንግርት ጉዳይ ነው፡፡ ሰሞኑን የተከሰተውን ሁኔታ ስትቃኝና ትንግርት ለእሷ ያላት ጥላቻ ምን ያህል ስር የሰደደ፤በእሷ ምክንያት የደረሰባትም በደልም ምን ያህል የከፋ እንደሆነ እንድታነብ ከላከችላት ዲያሪ ከተረዳች በኃላ ሁኔታው ተስፋ ያለው ነገር እንዳልሆነ
ተረድታለች፡፡እሷን ለዘለአለሙ አስባት መኖር ነው የምትችለው፡፡

ሁለተኛው ያልተቋጨው የፍቅር ጣጣዋ አሜሪካ እያለች ለሶስት ዓመት በፍቅረኝነት አብሯት ቆይቶ የነበረው አሁንም ድረስ ግንኙነታቸው ያልተቆረጠው የፕሮፌሰር ዬሴፍ ጉዳይ ነው፡፡በጣም የሚገርመው በአሁኑ ጊዜ ይህ ፍቅረኛዋ ከአሜሪካ መጥቶ አዲስ አበባ የገዛ ቤቷ ውስጥ ይገኛል፡፡ቢሆንም የእሱ ጉዳይ የትንግርትን ያህል ብዙም አስቸጋሪ አይደለም፡፡ድሮም ብቸኝነቱ አስቃይቷት እንጂ የእሱ ፍቅር አነሁልሏት አልነበረም አብራው እነዛን ዓመታቶች ያሳለፈችው፡፡እርግጥ
ውቅያኖስ አቆርጦ የመጣው እሷኑ ብሎ ነው፤ቢሆንም ‹‹ፍቅርና ይሉኝታ አብረው አይሄዱም›› ስትል እራሷን አፅናናች፡፡አሁን እሷ በጣም ምታፈቅረው ሌላ ሰው ነው እሱን ካጣች ደግሞ መጽናኛ ሊሆናት የሚችለው፣የምትፈልገውን የመንፈስ እርካታ ሊሰጣት፣.የፍቅር ረሀቧን ሊያስታግስላት የሚችለው ታዲዬስ ብቻ ነው፤አዎ ታዲዬስ ከነልጆቹ ፡፡አዎ ከነልጆቹ፤አንድን ሰው ከነልጆቹ ማፍቀር አይገርምም..?አለች፡፡

ቀልቧን ወደ አለችበት ዝግጅት ስትመልስ ታዲዬስ መነጽሩን ከፅዬን እጆች ላይ በማንሳት ዓይኖቿ ላይ እያደረገላት ነው፡፡ከዛ እጇ ላይ ያለውን አነስተኛ ሪሞት ተቀበለና ፈንጠር ብሎ መናገር ጀመረ‹‹እንግዲህ ይሄ መሳሪያ ሙሴ እንዳስረዳኝ ከሆነ ገና ሊሻሻሉ የሚገባቸው ነገሮች ቢኖሩትም እጅግ ልዩ የሆነ፣በሀገራችንም ምን አልባትም በዓለማችንም እስካአሁን ያልተሞከረ አዲስ ፈጠራ ይመስለኛል፡፡ይሄንን ፈጠራ ይዘን ሰኞ ወደ ሳይንስና ቴክኖሎጂ በመሄድ የፈጣራ ባለቤትነት ማስረጃ እንዲሰጡን ማመልከቻ እናስገባለን፡፡ ይሄ መሳሪያ እንዴት እንደሚሰራ በጥቂቱ ላስረዳችሁ ..>> አለና ከሪሞቱ አንዷን ጡት ተጫነ ...ጽዮን ያደረገችው መነጽር ጋር የተያያዘች በጆሮዋ አካባቢ ያለችው ትንሽ ሳጥን አረንጎዴ አበራች፤ከሳጥኗ በመውጣት የተንጠለጠለች የጆሮ ማዳመጫን ጆሮዋ ላይ ሰካላት፡፡ ከዛ ታዲዬስ ዶ/ር ሶፊያን በምልክት ጠራት፡፡ መጣችለት፡፡ ጽዮን ፊት ለፊት አቆማትና እሱ ገለል አለ <<አሁን ጽዮን ፊት ለፊቴ ምን አለ…? ብለሽ ቃላት አውጥተሸ ጠይቂ›› በማለት ከሪሞቱ ሌላ አንድ ጡት ተጫነ ፡፡ግራ ቢገባትም እንደተባለችው ‹‹ከፊት ለፊቴ ምን አለ?›› ስትል ጥያቄ አቀረበች፡፡

ከሶስት ሰካንድ በኃላ በጆሮዋ ድምጽ መጣ ... ከመቀመጫዋ ድንገት ተነሳች፤መልሳ ቁጭ አለች፡፡

‹‹ፅዮን በጆሮሽ የሰማሽው ነገር አለ..?››

‹‹አዎ ..ከፊት ለፊቴ በአንድ ሜትር ርቀት አንድ ሴት ቆማለች፤ደማቅ ቀይ ቀሚስ ለብሳለች፤የሰውነቷ ቀለም ቀይ ነው ፤ፀጉሯ ጥቁር ሁኖ ረጅም ነው፡፡››
👍537😁2
‹‹ከእሷ ኃላ ያለውን ነገር ደግመሽ ጠይቂ››አላት ታዲዬስ፡፡

‹‹ከሴትዬዋ ኃላ ያለውን ነገር ማወቅ እፈልጋለሁ?›› ጠየቀች፡፡አሁንም በተመሳሳይ ከሁለት ሰከንድ በኃላ በጆሮዋ ድምፅ መጣላት፡፡አዳምጣ ስትጨርስ ምትለውን ለመስማት ለሚጠብቋት ሰዎች መናገር ጀመረች ፡፡ከሴትዬዋ ኃላ በቀኝ በኩል ፔያኖ በግራ በኩል ሰማያዊ ቀለም የተቀባ ግድግዳ ላይ የተደገፈ ጊታር ይገኛል ፡፡ከጊታሩ ወደ ጐን በሁለት ሜትር ርቀት ባለአራት እግር አንድ ጠረጴዛ አለ››ብላ ተናገረች... ሰዉ ሁሉ በመደመም የሞቀ ጭብጨባ አሰማ፡፡

‹‹ትክክል ነሽ ፅዮን፡፡ እንግዲህ ይሄንን ነው ሙሴ ለአንቺን በማሰብ የፈጣረው ፈጠራ፡፡

እርግጥ..እንዳልኳችሁ እሱም እንደነገረኝ

በተለይ ከፊት ለፊቱ የሚገኙ ግኡዝ ዕቃዎችን
ምስል በመረጃው መዝግቦ ያንን ወደ ቃላት ቀይሮ ለተጠቃሚው ተፈላጊውን መረጃ ለመስጠት ገና ተጨማሪ ስራ ያስፈልጋዋል፡፡ ውበቱና ቅለቱ ላይም እንደዛው መስተካከል ያለበት ነገር አለ፡፡ያም ሆኖ የዚህ ፈጠራ ዋና አላማ ፅዮን የማንንም እርዳታ ሳትፈልግ ትራፊክ የሚበዛበትን አውራ መንገድ በዜብራ
እንድትሻገር፣የማታውቀው ሀገር እንኳን ቢሆን
የፈለገችው ሆቴል ወይም የምትፈልግበት ቦታ
መሳሪያውን ብቻ አቅጣጫ እየጠየቀች ያለረዳት መጓዝ እንድትችል ነው፡፡የለበሰውን
ልብስና ቁመናውን ነግሯት የቀጠራት ሰው ካለም በቀላሉ ወደሚጠብቃት ቦታ በማምራት እንድታስደምመው : ታዲያ ለፅዬንና ተመሳሳይ ችግር ላለባቸው ምን ያህል
ኑሮቸውን እንደሚያቀልላቸው አይታያችሁም ፡፡
ለማንኛውም ሙሴ ለጽዮን ያበረከተው ስጦታ
ይህ ነው፡፡ አመሰግናለሁ >>ብሎ ተቀመጠ፡፡
ዓላዓዛር መድረኩን ተረከበና‹‹ምን እንደምል አላውቅም፤በህይወቴ የምኰራበት አንድ ነገር ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? የዚህ ቤተሰብ አባል መሆኔ ፡፡ለማንኛውም ጽዮን የምትናገረው ነገር አለ ብዬ አስባለሁ፤ ዕድሉን ቀጥታ ለእሷ ሰጣለሁ፡፡››

ከወንበሯ ተነሳችና እዛው በቆመችበት ፊቷን ወደ ሰዎቹ ዞራ መናገር ጀመረች‹‹ ... በመመረቄ ካገኘሁት እርካታ በላይ ውስጤ በደስታ ስንጥቅጥቅ እስኪል ድረስ በሀሴት የምሆነው የጠፋኝ አሁን ነው፤ አሁን በዚህ ሰዓት እውነት እንደ እኔ አይነት ዕድለኛ ሰው አለ?እኔ እንጃ... ሚጡ በተኰላተፈ አንደበት ያነበበችውን ግጥም ፣ ለጊዜው ባላየውም ሰላም ያበረከተችልኝ የፈጠራ ስዕል፣የእኔው ሁለቱ ተማሪዎቼ ለእኔ ሲሉ ተጨንቀውና ተጠበው ያሰሙን የራሳቸው ልዩ ፈጠራ የሆነ ሙዚቃ፣ከሁሉም ደግሞ የሙሴ ይገርማል…፡፡ ይሄ የሙሴ ስጦታ ማለት ለእኔ ብቻ አይደለም ፋይዳው፤ታዲ እንዳለው ለመላው ዓይነ ስውራን ነው፡፡ብዙ ችግሮቻቸውን ሊቀርፍላቸው ፣ኑሮቸውን ሊያቃልልላቸው የሚችል ልዩና ድንቅ ፈጠራ ነው፡፡ ይሄን በ5ዐ እና 6ዐ አመት
ዕድሜ ባላቸው 3ዐ እና አርባ አመት በምርምሩ
ባሳለፉ ድንቅ ና በጣም እድለኛ በሆኑ ሳይንቲስቶች መፈጠር የሚገባው ግኝት
ነበር…፡፡፡በ11 ዓመት ልጅ የማይታመን ተዓምር ነው፡፡ሙሴ ለእኔ በሙዚቃው ዓለም ተከስቶ እንደነበረው ሞዛርት ነው፡፡ሞዛርትም
እንደእሱ በ5 ዓመት ዕድሜው ነበር መጠበብ
የጀመረው፡፡እኔ ዛሬ ዓይኔን እንዳበራልኝ ነው የምቆጥረው፡፡በዚህ መሳሪያ የመጠቀም
ዕድሉን ባላገኝ እንኳን ሙሴ የእኔን ችግር ለመቅረፍ እስከ ምን ድረስ እንደባከነ ሳስብ ...በቃ ሰው ለሰው ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ
በጥልቀጥ እንድረዳ አድርጎኛል፡፡ …ብቻ ታዲዬስ ወደ እዚህ ቤተሰብ እንድቀላቀል ፤ ከእነዚህ በጣም ልዩ ና ብርቅዬ ልጆች ጋር እንድዋሀድ እድሉን ስላመቻቸህልኝ ዕድሜዬን ሙሉ ሳመሰግንህ እኖራለሁ፡፡አንተ ልዩ ነህ፤ልዩ ባትሆንማ እነዚህን ልዩ ልጆች ማፍራት
አይቻልህም ነበር፡፡
.....ታዲ እኔ እነዚህ ልጆችህን በጣም በጣም ነው የማፈቅራቸው፡፡ከመሃፀኔ የወጡ፣ጡቴን ጠብተው ያደጉ መስሎ ነው የሚሰማኝ፣ሌላም አንድ ሚስጥር ልንገርህ አንተንም በጣም ነው የማፈቅርህ…፡፡››

ዶ/ር ሶፊያ ጆሮዋን ተቀሰረ፡፡ በተቀመጠችበት ሰውነቷ ሲንዘፈዘፍ ተሰማት..ለነገሩ በፅዮን ንግግር ቤቱ ጠቅላላ ታዲዬስም ጭምር ነው የደነገጠው ፡፡

...ቀጠለች‹‹አዎ..…እርግጥ እኔና አንተ ስለእንደዚህ አይነት ጉዳይ ቁጭ ብለን የማውራት እድል አጋጥሞን አያውቅም ፡፡አዎ እውነቴን ነው በጣም ነው የማፈቅርህ፡፡ያንተ ሚስት ሆኜ የእነዚህ ድንቅ አምስት ልጆች እናት መሆን ብችል አቤት!!!! ዳግም አንደተወለድኩ ነበር የምቆጥረው፡፡ለማንኛውም ባንተ ልብ ውስጥ ሰው ይኑር አይኑር አላውቅም፡፡ ደግሞም እኔም የምትወዳት ዓይነት ሴት ልሁን አልሁንም እርግጠኛ አይደለሁም፡፡..ብቻ የውስጤን ህመም መተንፈስ በመቻሌ ቀለል
ብሎኛል ፡፡ ሁላችሁንም እወዳችኋለው አመሰግናለሁ››ብላ ቁጭ አለች፡፡በቤቱ ፀጥታ ሞላበት፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍766🔥3😁2
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  አስራ ሶስት


እናትሽ የት ሄደች?

እናቴ ቆንጆ፣ ዘናጭ፣ ሳቂታና ደስተኛ ሴት ነበረች፡፡ በዚያ ዕድሜዬ እንደዚያ ነበር የማስበው፡፡ በጥቁር ቆዳዋ ላይ የሚያምሩ ነጫጭ ጥርሶቿ ያስደነግጣሉ፡፡ እንደ ወንዝ ድንጋይ ለስላሳና ጽድት ያለ ወደ ጥቁረት የሚወስደው ቆዳ ያላት፣ ሌሎች

ሰዎች ጋር ስትቆም ረዥም ቁመቷ የተለዬ ሞገስ የሚሰጣት- ቆንጆ ሴት፡፡ ሦስት ልጅ ወልዳ እንኳን ንክች ያላለ ውበት። አዲስ የወጣ ዘፈን የማያመልጣት፣ ፓናሶኒክ ቴፓችን ከጧት እስከማታ ካልተከፈተ የሚጨንቃት፣ እኔና ሁለት ታናሽ ወንድሞት ምንም እናውራት ምን “እስቲ ልቤን አታንሸራቱኝ ሂዱ ለአባታችሁ ንገሩት” የምትል፣ ከዘፈን ሌላ እኛን መስማት የሚደክማት፤ ሙሉ ቀን ስንዘፍን ብንውል ግን በፈገግታ የምትመለከተን እናት ነበረች። እናቴን ለመቅረብ በስምንት ዓመቴ እዚያ ፓናሶኒክ ቴፕ ሥር ራሴን ደቅኘ ያልሸመደድኩት የዘፈን ግጥም አልነበረም፡፡ ዘፈን ወደ እናቴ መድረሻ ድልድይ ነበር “ውይ የድምፅዋ ማማር ደግሞ'' ትልና የቀለበት መዓት በተደረደረባቼው ለስላሳ ጣቶቿ ጉንጭና ጉንጨን ይዛ ከንፈሬን ትስመኛለች፤ የእጇ ልስላሴ_እስካሁን ይታወሰኛል፣ የእናት እጅ እንዴት እንደዚያ ይለሰልሳል!? “ተይ! ይኼን ከንፈር መሳም'' ይላታል አባባ ደስ አይለውም። “እንዴ ምናለበት?'' ትልና እንደገና ከንፈሬን እሟ እሟ...እልኅ በሚመስል አሳሳም: ፡አባባ በቅሬታ ፊቱን ወደ ሌላ ቦታ ያዞራል ወደ መስኮት፣ ወደ ወንድሞቼ ወደሚያነበው ነገር፣ እዚያ ጥግ ላይ ወደተቀመጠው የሸክላ ሰሃን እና ብርጭቆ ወደታጨቀበት ትልቅ ቡፌ፣ ወይም ወደ ላይ ወደ ኮርኒሱ፡፡ መከራከር አይወድም። የአባባ ዓይኖች ሲሸሹ እናቴ በድል አድራጊነት ድምፅዋን ከፍ አድራጋ በጣም የምትወደውን ዘፈን “ይላል ዶጁን” እያንጎራጎረች የምትሠራውን ትሠራለች። ብዙ ጊዜ የምትሠራው በእስክርቢቶ ካሴት ማጠንጠን ነበር፤አባባ ጋር ብዙ አያወሩም፤ ስልቹ ነበረች፡፡ አባባን በተደጋጋሚ የምትጠይቀው ጥያቄ “እስቲ እስክርቢቶ ስጠኝ" የሚል ነበር። ካሴት ለማጠንጠን፤ እንዲያውም አባባ ከአባትነትም፣ ከባልነትም በላይ የሆነ የእስክርቢቶ ማስቀመጫ ዕቃ መስሎ ሳይታያት አይቀርም፡፡ እውነቱን ለመናገር ለእኛም ለልጆቿ ያን ያኽል ፍቅር ነበራት ብዬ አላስብም፡፡ በተለይ እኔ እንደ እናት ልቀርባት የምደክመው ድካም አሁን ላይ ሳስታውሰወ ያመኛል፡፡

እስከ አሁን በሕይወቴ የሚከተሉኝ ድክመቶች ከእርሷ ግዴለሽ ባሕሪ የተፈለፈሉ ቫይረሶች ይመስሉኛል፡፡ ፈሪ፣ ግራ የምጋባ፣ ሰው አብዝቼ የምለማመጥ እና በራሴ የማልተማመን ነኝ። ሰዎች ሁሉ የሚሰለቹኝ፣ የማይወዱኝ እና የሚርቁኝ ይመስለኛል፡፡ ሁሉም የእርሷ ጦስ ነው፡፡ ለማሳበብ ሳይሆን ይኼ የተለማማጭነት ባሕሪዬ፣ ስሜቱ እሷን ለመቅረብ ከምታገልበት ስሜት ጋር አንድ ዓይነት ነው፡፡ ሰዎች ትንሽ ፊታቼውን ዞር ያደረጉብኝ ከመሰለኝ ጭንቀት ሊገድለኝ ይደርሳል፡፡ እቤታችን የነበሩትንና እናቴ ጋር የተነሳናቼውን ፎቶዎች በሙሉ ተመልሼ ሳያቼው፣ ወገቧን ለማቀፍ ተንጠራርቼ፣ ትከሻዋ ላይ በመለማመጥ ተደግፌ.... እነዚያን ፎቶዎች ሳያቼው ያመኛል፡፡ አባባን የምወደው እሱም ቢሆን እንደ አባት ስለቀረበኝ አልነበረም፣ እናቴን ለመቅረብ ልክ እንደ እኔ በዓይኑ፣ በንግግሩ፣ የምትናገርና የምትሠራው ልክም ሆነ ስሕተት በማዳነቅ ሊቀርባት ሲሞክር፣ ሲለማመጥ ሳዬው አሳዝኖኝ ሳይሆን አይቀርም፡፡ በቤታችን 'ቤሳቤስቲን' ስሜት ከሌላት ስስታም ሴት የፍቅር ለማኞች ነበርን!! ያቺን ሴት ለማስደሰት የማልፈነቅለው ድንጋይ አልነበረም፤ እሷ ግን ሁልጊዜ የመስኮታችንን መጋረጃ በትንሹ ከፈት አድርጋ ወደውጭ መመልከት ነበር ሥራዋ፡፡ ያንን መስኮት አብዝታ ነበር የምትወደው፡፡ በተለይ አባባ ከሌለ ቴፑን ድብልቅልቅ አድርጋ ከፍታ፣ በመስኮት ዐሥር ጊዜ ወደ ውጭ ከማዬት በስተቀር ሥራ እልነበራትም፡፡ አባባም ቢኖር ባለፈች ባገደመች ቁጥር ዓይኗን ወደ መስኮት መወርወሯ አይቀርም ነበር፡፡ በመስኮት አስተያዬቷ የሆነ የሚያጓጓ ነገር ነበረው፤ ለዚያም ሳይሆን አይቀርም ቁመቴ መስኮቱ ጋ ስለማይደርስ ወንበር ጎትቼ ያዬቸውን ለማዬት ብዙ ጊዜ እሞክር የነበረው... ምንም የለም፣ ምንም! ከዚያ አስቀያሚ ጋራዥ በስተቀር፡፡ እኛም ሆንን አባባ ምን እንብላ፣ ምን እንልበስ ግድ የሌላት ሴት ነበረች፡፡ አልፎ አልፎ ሠራተኛችን ዘመድ ጥዬቃ ብላ ስትሄድ፣ እናቴ እየተማረረች ወደ ኩሽና ትገባለች፡፡ አንዱ ዕቃ ጠፋ ስትል፣ ሌላኛው ተደፋ እያለች ስታማርር ብዙ ሰዓት ቆይታ እሀል ውሃ የማይል ነገር ሠርታ ብሉ ትለናለች፤ አንበላም፤ እንዲያውም እሷ

ምግብ ስትሠራ የሚደፋው ይበዛል፡፡ ጓዳው ባልታጠበ ዕቃ ይሞላል፡፡ በዚያ ላይ ፊቷን በቁጣ ጥላው ነው የምትውለው። በሠራተኛ ነው ያደግነው፤ አብራን የኖረች እንደ እናት የምናያት ሠራተኛ ነበረችን፡ ታዲያ ደጋግሜ ምንም እንደሌለ ባረጋግጥም እናቴ በዚያ መስኮት ምንድን ነው የምታዬው? እያልኩ እጓጓ ነበር፤ እሷ ስትቆም ታይቶ እኔ ብቅ ስል የሚጠፋ አንዳች ተአምር ምንድን ነው!? ቆይቶ በዕድሜ ከፍ ስል ነው- ተክሌ ጋራዥ መኪና ሊያሠሩ የሚመጡ የከባድ መኪና ሹፌሮችን ትመለከት እንደነበር የገባኝ፡፡ በዚያ ዕድሜ እነዚያ ወንዶች ጋር የነበራት ነገር ባይገባኝም፣ አንዳንዶቹ እቤታችን ድረስ መጥተው በመስኮት በኩል ያወሯትና ይሳሳቁ ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ በሚያማምሩ የፕላስቲክ ማሸጊያዎች የታሸጉ ከረሜላና ቸኮሌቶች በብዛት ያመጡላት ነበር። ከጅቡቲ ነው ያመጣነው ሲሉ ስለምሰማ በዚያ ዕድሜዬ፣ ጀቡቲ ከረሜላና ቸኮሌት የሚዘንብባት አገር ትመስለኝ ነበር። እናቴ ጣፋጭ ነገር በጣም ነበር የምትወደው። ቡና ጨምሮ መረር የሚል ነገርና የሚያቃጥል ምግብ ደግሞ በሩቁ ነው የምትሸሸው። ለዚያም ሳይሆን አይቀርም ቤታችን አልጫ ወጥ የሚዘወተረው፡፡ እኔም እስከ ዛሬ ቡና አልወድም። ያንን ሾፌሮቹ የሚያመጡላትን ጣፋጭ ለእኔም እያፈሰች ትሰጠኛለች። በቦርሳዬ ዉስጥ እየደበቅሁ ትምህርት ቤት እወስድና ሃይሚ ጋር ሆዳችን ከበሮ እስከሚያክል እናሻምዳለን። አንዱ ሾፌር ያመጣው ሳይጋመስ ሌላው ስለሚያመጣ ያ የጣፋጭ ጎርፍ ዘላለም የሚያልቅ አይመስልም ነበር። በተለይ የማልረሳው “ጥቁር ዕንቁ” የሚላት ሰውዬ ነበር፡፡ የሸሚዙ ቁልፍ ተከፋፍቶ ደረቱ ላይ ችፍግ ያለ አስቀያሚ ጸጉሩ የሚታይ፤ በተራመደ ቁጥር እንደ ጸናጽል የሚንሿሿ ባለዘለበት ቡትስ ጫማ የሚያደርግ፡፡ ሁልጊዜ ቤታችን ካሉት ወንበሮች አባባ የሚወደውን ባለ ስፖንጅ ወንበር ታወጣለትና በር ላይ፣ መስኮቱ ሥር ይቀመጣል፡፡

እናቴ ወደ ቤት ትመለስና ከወገቧ በላይ በመስኮት ብቅ ብላ ገበያ እንደጠረረበት በለ ሱቅ የመስኮቱን ደፍ ተደግፋ ድምፃቼውን ቀንሰው ያወራሉ- ይሳሳቃሉ። እንዲህ ሲያወሩ ታዲያ እቤት ሆኜ ከኋላዋ አያታለሁ፡፡ እግሯ አያርፍም፤ በነጠላ ጨማዋ ትጫዋታለች ፣ ሽፍን ጫማ ብታደርግ እንኳን የአንድ እግር ጫማዋን አውልቃ (ብዙ ጊዜ የቀኟን) እግሯ በጫማዋ ይጫዎታል፤ ወይም በረዣዥምና በሚያምሩ የእግሯ ጣቶች ምንጣፉ ላይ የማይታይ የሐሳብ ሥዕል ትሥላለች፤ ወይም በቀኝ እግሯ ጣቶች የግራ እግሯን ከተረከዟ ከፍ ብሎ እስከ ጉልበቷ ያለውን ክፍል ትነካካለች፤ እኔም ይኼ ነገር ለምዶብኝ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ቢሮዬም ይሁን ሌላ ቦታ ስቀመጥ፣ ጫማዬን አወልቅ ነበር፡፡ ብዙ ባሕሪዋ ሳልፈልግ ውስጤ ተቀምጦ ራሴን እንደ እሷ ሳደርግ የማገኝበት ጊዜ ነበር፡፡ ታዲያ ሁልጊዜ ወሬዋን ስትጨርስ የአንድ እግሯ ጫማ ስለሚጠፋት
👍453😁2🔥1🥰1
“የታባቱ ገባ?" ትላለች በብስጭት፤ ልክ ጫማው የራሱ ነፍስ ኖሮት ሮጦ እንደጠፋ ወይም የሆነ ሰው እንደደበቀባት ዓይነት። እናቴ ከልቧ ስትስቅ የማያት እዚያ ሰውዬ ጋር ስታወራ ብቻ ነበር፤ ስለ ሰውዬውም፣ ስለ ወሬውም፣ ሳይሆን ስለሳቋ ስል ሁልጊዜ ቢመጣ እመኝ ነበር፡፡ ያ ሰውዬ ከሄደ በኋላ ግን ድብርት ይጫጫናታል፡፡ እዚያ ሰውዬ ጋር እያወራች፣ እኔም ሆንኩ ሠራተኛችን ወይም ታናናሽ ወንድሞቼ፣ ካናገርናት እንደ እብድ ነበር የሚያደርጋት፡፡ አንድ ቀን ትምህርት ቤት ስታድጉ ምን መሆን ትፈልጋላችሁ? ተብለን ተጠይቀን ዶክተር አልኩ ተጨበጨበልኝ፡፡ ለአባባም ስነግረው ደስ አለው። በቀጣዩ ቀን እናቴ ጀርባዋን _ ሰጥታኝ _ መስኮት ላይ እንደቆመች “ሳድግ ዶክተር መሆን ነዉ የምፈልገው'' አልኳት፤ ጀርባዋን እንደሰጠችኝ በሰለቼ ድምፅ... “ምንያረግልሻል?'' አለችኝ፡፡ “ሰው ለመርዳት!” ያው ሲባል እንደሰማሁት፡፡ ድንገት ወደ እኔ ዞራ፣

''መጀመሪያ አንቺ ደስተኛ ሁኚ! ደስ ካላለሽ ሰው አትረጂም፡፡ እንዲያውም ለሰው ዕዳ ነው የምትሆኚው፡፡ ይልቅ በዚህ ድምፅሽ ጎበዝ ዘፋኝ ሁኚ፤ አታያቼውም እንዴት ሰው _ እንደሚወዳቼው? እንደሚዘንጡ፣ የማንም በሽተኛ ጋር ምን አዳረቀሽ?...ሰው ከቀኑ ላያልፍ! ዘፋኝ ሁኝ ዘፋኝ፡፡ በዚህ ውበትሽ ላይ ዘፋኝነት ሲጨመር ዘላለም መኖር ነው፡፡ ይኼ ሕዝብ እንደሆነ ሥጋው ቢድን ልቡ አይድን፣ ምን ያደርግልሻል ዶክተር? አገሩን ቲቢና አባላዘር አላፈረሰው፣ የሕዝቡ ክፋት እንጂ! ...ክፋት በመርፌ አይድንም...ዘፋኝ ሁኚ፣ ቆንጆ ወንዳወንድ ወንድ አግቢ!'' ብላኝ ወደ መስኮቷ ተመለሰች፡፡ ዘፋኝነት ነፍሴ ውስጥ ገባ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የታመሙ ሰዎች ሁሉ ሆስፒታል ከመሄድ ይልቅ ሙዚቃ ቤት በር ላይ ቢቀመጡ የሚፈወሱና አልጋቼውን ተሸክመው የሚሄዱ ይመስለኝ ነበር፡፡ እንደዚያ _ ነበር ለዓመታት ኑሯችን፤ እንደዚያ ነበር የልጅነት ጊዚዬ ያለፈው፡፡ አንድ ቀን ታዲያ፣ የአራተኛ ክፍል ትምህርቴን በአዲስ ሞራል በጀመርኩበት ዓመት፣ ጥቅምት አጋማሽ ላይ እኔንና ሁለት ታናናሽ ወንድሞቼን ለአባቴና ለሠራተኛችን ትታን ጠፋች። ከልብሷና ተከምረው ከነበሩ የዘፈን ካሴቶች ውጭ ሌላ ነገር አልወሰደችም፡፡ የሄደች ቀን አባባ እቤት አልነበረም፣ እኔ ግን ነበርኩ። “አሳይሜንት” ተሰጥቶን _ የምግብ ጠረንጴዛው ላይ ትልቅ ነጭ ወረቀት ዘርግቼ፣ የአፍሪካ ካርታ ለመሳል እየታገልኩ ነበር፡፡ ልብሷንም፣ ካሴቷንም እንዴት ከቤት እንዳወጣችው አላዬሁም፤ መጨረሻ ላይ ግን ነጠላ ለብሳ (ልክ ገበያ እንደምትሄድ) መጣችና አጠገቤ ቆም ብላ፣ የምሠራውን እያዬች በችኮላ "ምን እየሠራሸ ነው?" አለችኝ፡፡ ትምህርት ጋር በተያያዘ የምሠራውን _ ስትጠይቀኝ የዚያን ቀን የመጀመሪያዋም፣ የመጨረሻዋም ነበር። “የአፍሪካን ካርታ እየሣልኩ'' አልኩ ወደ ላይ አንጋጥጨ በደስታ እያዬኋት፡፡ “እንደ ደህና ነገር አፍሪካን. . .?'' ብላ ጎንበስ አለችና፣ ድንገት ጉንጭና ጉንጨን ይዛ እሟ! እሟ! እያደረገች ከንፈሬን፣ ዓይኖቼን ሳመችኝ፡፡ ከወትሮው የተለዬ የሽቶ ጠረን እንዳወደኝ እስከ ዛሬ አልረሳዉም፡፡ እናም ከመሬት ተነስታ ስትስመኝ የተሰማኝ ደስታ እንደ ሽቶው ሁሉ የሆነ አስደሳች መዓዛ ነበረው። ምን ሠርቼ

እንደሳመችኝ ግራ ገብቶኝ አንዴ እሷን አንዴ ዙሪያዬን ሳማትር፣ ጽጌን (ሠራተኛችንን) ጠርታ ሹክሹክታ በሚመስል ድምፅ “እንደነገርኩሽ” አለቻት። ወደኋላ እንኳን አላዬችም፤ ጎረቤት የሚጫዎቱ ታናናሽ ወንድሞቹንም አልጠራቻቼውም። በቃ ወጥታ ሄደች፤ በጭራሽ እየጠፋች ነው ብዬ አላሰብኩም ነበር። ሠራተኛችን በመስኮት ቆማ ስትመለከት ቆይታ በረዥሙ ተነፈሰችና ወደ ጓዳ ገበች... በቃ፡፡ ይኼው ነበር አጠፋፏ፡፡ እናትን ታኽል ነገር እንደዚህ ነበር የሄደችው፡፡ ከሄደች በኋላ 'አሳይሜንቴን' እየሠራሁ ጮኽ እያልኩ ስዘፍን ነበር፤ እናቴ የምትወደውን ይላል ዶጁን...! አባቴ በጣም ያፈቅራት ስለነበር ከሄደች በኋላ ሌላ ሴት አላገባም(የሰፈሩ ሰው የሚለው እንደዚያ ነው) የዚያን ቀን አምሽቶ ሲመጣ፣ግራና ቀኝ ተከምረው የነበሩ ካሴቶች ተወስደው ብቻውን ወደተቀመጠው ቴፕ እዬተመለከተ “እናትሽ የት ሄደች?" አለኝ፣ ምንም መልስ አልነበረኝም፡፡ ትካሻዬን ወደ ላይ ሰብቄ ዝም አልኩ። እናቴ ምንጊዜም ድንገት ወጥታ ለሰዓታት ቆይታ የመመለስ ባህሪ ስለነበራት፣ ለእኔ ምንም የተለዬ ነገር አልነበረም፤ አባባ ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ ባልሰማሁት ጩኸት “አንችን'ኮ ነው የማናግረው!" ብሎ ሲጮኽብኝ በድንጋጤ የያዝኩት እርሳስ ከእጄ ላይ እረገፈ፡፡ ጽጌ ጩኸቱን ሰምታ እጇን ቀሚሷ ላይ እየጠራረገች ከውስጥ መጣችና፣ የሆነ ወረቀት ሰጥታው፣ እጎኔ ቁጢጥ ብላ አቀፈችኝ፡፡ አስተቃቀፏ ከሆነ አደጋ ግልገሏን የምትጠብቅ ነብር ዓይነት ነበር፡፡ አባባ ያቺን ወረቀት በችኮላ ከፍቶ ማንበብ ጀመረ፡፡ ጽሑፉ ብዙም _ አይመስለኝም፤ _ ወዲያው ነው አንብቦ የጨረሰው፡፡ እንደጨረሰ በረዥሙ ተንፈሶ ዝም አለ፡፡ በቃ! ያ ደብዳቤ ምን እንደተጻፈበት እስከ ዛሬ አባባ ነግሮኝ አያውቅም፡፡ እኔም ጠይቄው አላውቅም፡፡

ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍451
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ:
እባክሽ አትሂጂ…..
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-ዘጠኝ


‹‹ያሬዶ ተዋወቁ…መስፍኔን የሚከታተለው ዶ/ር ያልኩህ እሱን ነው››
በትህትና ከጭንቅላቱ ዝቅ አለና..‹‹ያሬድ እባላላሁ›› ብሎ ለትውቅቅ እጁን ዘረጋልኝ..እኔም እላዬ ላይ የተንጠለተሉትን ልጆች እንደያዝኩ ከተቀመጥኩበት ትንሽ ቀና ለማለት እየሞከርኩ ..‹‹ኤልያስ›› ስል ስሜን ነገርኩትና የዘረጋውን እጅ ጨበጥኩት፡፡
ልዕልት‹‹‹ልጆች በቃ ሰላም ካላችሁት ወደውስጥ ግቡና ልብሳችሁን ቀይሩ››አለቻቸው..ልጆቹ በየተራ ጉንጩን እየሳሙ ተለይተውኝ ወደውስጥ ሄዱ፡፡ወንድሞ ከእሷ ጎን ተቀመጠ…
‹‹ቡና ትጠጣለህ ወንድሜ ?››
‹‹አይ ይቅርብኝ…››
እኔ ቡናውን መጠጣት ጀመርኩ…ቀዝቀዝ ብሎ ስለነበረ ቶሎ ሳብ ሳብ አድርጌ አጠናቀቅኩት ..‹‹አሁን መስፍንን ልየው ››ስል ጠየቅኳት፡፡
ልጆን እያጠባች ስለነበረ.‹እሺ ዶ/ር…. ያሬዶ አብረሀው ሂድ›› አለችው ወንደሞን…ተነሳው ተከትሎኝ መጣ..እኔስ ከእሷ ግር ቢሆንልኝ ነበር ደስ የሚለኝ ግን  ይሁን..በዝምታ ተከታትለን ገባን…አልጋው ላይ ተዘርሮ እንደተኛ አይኖቹን እያቁለጨለጨ ደረስን..ወደእሱ ተጠጋውና ጎንበስ ብዬ ‹‹መሰፍኔ እንዴት ነህ..?እየበረታህ ነው?››ብዬ ጠየቅኩት፡፡ አይኖቹን በማንከባለል ደህና መሆኑን ሊያስረዳኝ ሞከረ…እዛ ቤት በቋሚነት ያስቀመጥኳቸውን መሰረታዊ የህክምና መመርመሪያ እቃዎች ወደማስቀምጥበት ቦታ ሄድኩና ወደመስፍን ተመልሼ አንዳንድ ነገሮችን ቼክ አደረኩ፡፡ ጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለ በመረዳት እቃዎቹን ወደቦታቸው መልሼ ‹‹በቃ  ምንም አዲስ ነገር የለም…ከሶስት ቀን በኃላ ሆስፒታል መጥተህ ሙሉ ቼክ አፕ እንዳርግልሀለን..ሰእስከዛው በርታ››አልኩት፡፡ አሁንም አይኑን ከፍ ዝቅ በማድረግ ምስጋና እንደሆነ የተረዳሁትን የምልክት አስተላለፈልኝ...ክፍሉን ለቅቄ ስወጣ ክፍሉ ውስጥ ከመጀመሪያ ጀመር በዝምታ ሁኔታውን ሲከታተል የነበረው ወንድሟ ተንቀሳቀሰና ከኃላ ተከተለኝ…ወደሳሎን አልፈን ከመግታችን በፊት በረንዳ ላይ አስቆመኝና በዝግተኛ ድምፅ‹‹ይቅርታ ዶ/ር ይሄ ነገር ተስፋ ያለው ይመስልሀል?››
ስለምን እያወራ እንደሆነ ቢገባኝም‹‹ የቱ ነገር ?ስል ጠየቅኩት፡
የመስፍን ነገር ነዋ…እህቴ እኮ ከሚገባው በላይ እየተጎዳች ነው…እኔ የምፈራው ከእሱ ቀድማው እንዳትሞት ነው፡፡››
‹‹አይዞህ …እንዳዛ እንዲሆን አንፈቅድም..ለማንኛውም ሲመችህ ደውልልኝና እናወራለን..››አለኩትና የቢዝነስ ካርዴን ሰጥቼው ሌላ ምን ሳልለው ወደሳሎን አመራሁ..ጥያቄዎችና ስጋቶቹ ከእኔ ሰጋት ጋር ስለሚመሳሰሉ ደስ ተሰኝቼለው..ለዛ ነው ቁጥሬን የሰጠሁት… ከእሷ ተሰናብቼ መኪናዬን አስነስቼ ወጥቼ መሄድ ጀመርኩ ፡፡ከግቢዋ  ግማሽ ኪሎ ሜትር ያህል  ከተጓዝኩ በኃላ አንድ ነካ የሚያደርጋት አዲስ እብድ መሳይ አስፓልቱ ጠርዝ ላይ ቁጭ ብላ መሬት ስትጭር አየውና መኪናዬን ከእሷ አሳታክኬ አቆምኩና ለልዕለተ መስጠት ያልቻልኩትን እንቡጥ አበባ አነሳሁና መስኮቱን ከፍቼ ፊት ከለፊቷ ወረወርኩላት..
በቅልጥፍና አነሳችውና እያገላበጠች አየችው….፡
‹‹ምነው አበባውን አልቀበል አለችህ እንዴ?››ብላ አስገረመችኝ
‹‹አዎ አልቀበል አለቺኝ››
ከዛ ወደእኔ አትኩራ አየችና… ‹‹እኔ ግን 50 ብር ስለሰጠኸን እቀበልሀለው፡፡
‹‹50 ብር አወጣሁና ወረወርኩላት፡›››
አበባውን ተቀብላኝ እያገላበጠች ማንጎርጎር ጀመረች፡፡ መክናዬን ወደፊት አስፈነጠርኩ..ቀጥታ ወደእማዬ ቤት ነው ያመራሁት፡፡
///
እቤት ስደርስ ከጥዋቱ በተቃራኒው ጭርና ቅዝቅዝ ብሏል…ሳሎኑን ከፈትኩና ገባው፡፡ ባዶ ነው…ወደሶፋው ሄድኩና ቁጨ ብዬ ቴሌቪዝን እየከፈትኩ ሳለ የእማዬ ሰራተኛ ደዝ ደዝ እያለች ከኪቸን ወጥታ መጣች..‹‹እንዴ ጋሼ ምንጊዜ መጣህ?››
‹‹አሁን ነው የመጣሁት..እማዬ የለችም እንዴ..?››
‹‹እትዬ ከእኔ ጋር ኩሽና እራት እያበሰሉ ነው››
‹‹ጥሩ በቃ መምጣቴነ ንገሪያት አልኳት››
‹‹እንዳልክ፡፡››ብላኝ ተመልሳ ገባች፡፡ እርግበን ያልጠየቅኳት በመሄዶ እርግጠኛ ስለሆንኩ ነው፡፡ስልኬን አወጣሁና ደወልኩላት ሊዘጋ የመጨረሻ  ጥሪ ላይ ተነሳ፡፡
‹‹ሄሉ እንዴት ነህ? አለቺኝ፡፡ይህቺ ልጅ ፀባዬ እንዴት እንዴት እየሆነ ነው? ቀኑን ሙሉ የት ወደቅሽ ብዬ በስልክ እንኳን ሳልጠይቃት ሄሉ ብላ በተደሰተች ጊዜ በምትጠራኝ የቁልምጫ ድምፅ...የጠበቅኩት እሺ ዶ/ር እንድትለኝ ነበር፡፡
‹‹ሰላም ነኝ…እማዬ ጋር ትኖሪያለሽ ብዬ ነበር…ስቆይብሽ ቤተሰቦችሽ ጋር ሄድሽ አይደል?››
‹‹አይ ዛሬ አንደማልሄድ እኮ ነግሬህ  ነበር፡፡››
‹‹ነው አንዴ ?ታዲያ የት ሄድሽ…..?››
‹‹ቅርብ ቦታ ነኝ ካልቸኮልክ ጠብቀኝ እመጣለሁ››…አለቺኝ፡፡
‹‹እሺ ጠብቅሻለሁ፡፡››ከማለት ውጭ ሌላ ምርጫ የለኝም፡፡
ከመቀመጫዬ ተነሳሁና መኝታ ክፈሌ አመራሁ… ይሄ ክፍል ከልጅነቴ ጀምሮ ስጠቀምበት የኖርኩት የልጅነቴና የወጣትነቴን ታሪክ አጭቆ የያዘ የግል ቤተመዘክሬ ነው..አሁንም በሳምንትም ሆነ በአስራአምስት ቀን እማዬ ስትናፍቀኝ መጥቼ ምተኛበተና ሁሌ ለእኔ ፀድቶና ተነጣጥፎ የሚጠብቀኝ ክፍል ነው፡፡አሁንም እዚህ ድረስ መጥቼ ክፍሌን ሳላየው ላለመሄድ እንጂ ምንም ጉዳይ ኖሮኝ አልነበረም ..ከፈት አድርጌ ስገባ ግን  ጠላታችሁ ቡን ይበል ቡን አልኩላቸው፡፡ እርግበ አልጋው ላይ ሙሉ በሙሉ  ቁጭ ብላ ትራሱን ተደግፋ ስትተክዝ ነበር…
‹‹እንዴ?›› ብዬ ወደኃላ ልመለስ ስል፡፡
‹‹እንዴ ፍቅር ግባ እንጂ…የራስህ ክፍል እኮ ነው››አለቺኝ፡፡
‹‹አንዴ አስደነገጥሺኝ እኮ፡፡ እዚህ ሆነሽ ነው እንዴ ምትሸውጂኝ?›› እልኩና ወደ እሷ ቀርቤ ጉንጯን ሳምኩና ከጎኗ ተቀመጥኩ፡፡
‹‹እንቅልፍ ወስዶሽ ነበር እንዴ?››
‹‹አዎ.. ከእማዬ ጋር ወዲህ ወዲያ ስል በቃ ድቅቅ ነው ያልኩት፡፡››
‹‹የእሷንማ ተይው.. ልጇ የመጣችላት እኮ ነው ያስመሰለችው?››
ሳላስተውል በተናገርኩት ቃል ፊቷ ቅይርይር አለ‹‹ምን ለማለት ፈልገህ ነው….?እና ልጇ ካልሆንኩ እዚህ ምን እሰራለው?››
‹‹አረ አረጋጊው…እንደዛ ለማለት ፈልጌ አይደለም?››
‹‹እና ምን ለማለት ፈልገህ  ነው…?ቆይ እማዬን የምወዳት አንተ ባሌ ለማደረግ ባለኝ ፍላጎት መክንያት ይመስልሀል..?እኔ እሷን እማዬ የምላት እሷም እንደ ልጇ ስለተቀበለቺኝ ነው፡፡የአንተ ባልነት ገደል ቢገባም የእኔና የእሷ እናትና ልጅነት የሚቆረጥ አይምሰለህ..ደግሞ እወቀው አንተን ለማግባት ሙጭጭ ምልብህ ከእሷ ጋር ይበልጥ የመቀራረብና የመዋሀድ ምክንያት ለማግኘት ነው፡፡››
መጥፎ ቃላቶችን ከአንደበቷ እውጥታ የበለጠ ልቤን ከመሰባበሯ በፊት ‹‹ኦይ በቃ ተነሽ...ወደ ሳሎን እንሂድና የእማዬ እራት ከደረሰ  እንብላ…እርቦኛል፡››ብዬ ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ፡፡ ተከትላኝ ተነሳችና ከአልጋዋ ወረደች፡፡ተያይዘን ወደሳሎን ስገባ እማዬና ሰራተኛዋ እራት ሲያቀራርቡ ደረስን፡፡
እማዬ ተንጠራርታ ጉንጬን ሳመችኝና ‹‹ውይ ልጄ ምነው ጠቋቆርክ..?››ስትል ተየቀችኝ፡፡
‹‹ሰላም ነኝ፡፡›› አልኳት፡፡
‹‹እጃቹሁን ታጠብና ቁጭ በሉ፡፡››
እርግበ‹‹እማዬ እኔ ግን ቢቀርብኝ››ስትል መሞላቀቋን ቀጠለች፡፡
‹‹ምን ማለት ነው..ለአንቺ ስል አይደለ እንዴ ስንደፋደፍ ያመሸሁት፡፡?››
‹‹እኮ ገና  አንድ ሰዓት ተኩል ነው….ልቆይና ሶስት ሰዓት አካባቢ እበላለሁ ..የበላሁት መክሰስ እኮ ንቅንቅ አላለም፡፡››
👍558🥰1😁1
‹‹ካልሽ እሺ እሱን እንድታባይው ብዬ ነበር..በል አንተ ታጠብና ቁጭ በል..››በዝምታና ግራ በመጋባት እንዳለችኝ እጄን ታጥቤ ምግብ ጠረጴዛው ፊት ለፊት ተቀመጥኩ…ያው እናቴ የተቆረጠ እንጀራ ለራሰዋም መብላት ለሰውም ማቅረብ ስለማትፈልግ…በመለስተኛ ትሪ አቀረብልኝ…እርግበ ከጎኔ መጥታ ተቀመጠች…መብላት ጀመርኩ …እነእማዬ ወደ ውስጥ ሲገቡልኝ ጠብቄ‹‹እንዴ እስከ ሶስት ሰዓት እኮ መቆየት አንችልም››አልኳት
ግራ እንደመጋባት አለችና ዝም ብላ አፍጥጣ አያየቺኝ‹‹ማለት?››
‹‹እራት በልተን ቢያንስ ሁለት ሰዓት ከዚህ መንቀሳቀስ አለብን››
‹‹ወዴት?››
‹‹ወዴት አትያለሽ እንዴ? ወደቤት ነዋ፡፡››
‹‹እ..አይ እኔ እዚሁ እማዬ ጋር ነው የማድረው…››ለመጉረስ ወደአፌ እየወሰድኩ የነበረውን ምግብ መልሼ አስቀመጥኩትና‹‹እውነትሽን ነው….እዚህ ነው የሚታድሪው?››
‹‹ምነው ያስገርማል እንዴ…?.በዛ ላይ አንተን ከገዛ አልጋህ ላይ አባርሬ ሶፋ ላይ ስትንገላታ እንድታድር ማድረግ አልችልም፡፡››በማለት እግረመንገዷን በውስጧ የቀበረችውን ቅሬታ ተነፈሰች፡፡
‹‹ደስ እንዳለሽ››አልኩና ከቅሬታ ጋር ምግቡን በዝምታ ወደውስጥ አስገባ ጀመር…ወዲያው ሰራተኛዋ ቡና ለማፍላት ሲኒ ማቀራረብ ጀመረች….እኔም በፍጥነት ወደቤቴ የመሄድ ሞራሌ እየሞተ ሄደ፡፡


ይቀጥላል...
ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍385🤔3
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  አስራ አራት


አልተዘዋወረችም!

እናቱ ትታን ብትጠፋም አልጠላኋትም፤ እንዲያውም ሰው በሌለበት በናፍቆት አለቅስ ነበር፡፡ በተለይ ጠዋት አባባ ወደ ሥራ ከሄደ በኋላ ፣ወንድሞቼ ለጨዋታ አወጡ? ሠራተኛችን እዚያው ሰፈራችን ወዳለ ጉሊት ገበያ ስትሄድ ቤቱ በጸ ይሆንብኛል። ይኼ ሰዓት የእናቴ መንፈስ ቤቱን የሚናኝበት ነው። በዚህ ሰዓት ነበር ሙዚቃ ከፍታ፣ ቤቱ በሽቶ ጠረን ተሞልቶ፣ በቅመም ያበደ ሻይዋን ይዛ መስኮቱ አጠገብ ያለ ወንበር ላይ የምትቀመጠው፣ ባታወራኝም አብራኝ የምትሆነው። ዝምተኛ ነበረች፤ በዓይኖቿ ብቻ የምታወራ፣ እና ዓይኖቿን ከእኔ የምታሸሽ። ሁለቱ ታናናሽ ወንድሞቼ የእናቴ መጥፋት ለምን ግድ እንዳልሰጣቼው እስካሁንም ድረስ አላውቅም፡፡ የበለጠ የገፋችኝ እኔ ግን ለምን በናፍቆቷ እንደተጎዳሁ ዛሬም ድረስ አይገባኝም፡፡ ክፉኛ ትናፍቀኝ ነበር፡፡ እናቴ ጠረኑ በሚያውድ ሽቶና በብዙ ጣፋጭ የተከበበች ገነት ነበረች- ለእኔ። ያ ገነት ሁልጊዜ ውብ ዜማ ከውስጡ ይፈልቅ ነበር፡፡ የሠራሁትን ኃጢአት እንጃ ወደዚያ ገነት እንዳልገባ ብከለከልም በልጅነት እግሮቼ ዳር ዳሩን ስዞር ነው የኖርኩት። በስንተኛው ዙር ያ የመገፋት ቅጥር _ እንደሚፈርስ ባላውቅም _ አንድ ቀን በእናቴ የፍቅር እቅፎች ውስጥ እንደምወድቅ አስብ ነበር... ቅጥሩ ሳይሆን ተስፋዬ ፈራረሰ። በናፈቀችኝ ቁጥር እዘፍናለሁ፡፡ ታዋቂ ዘፋኝ ብሆን ተመልሳ የምትመጣ ይመስለኝ ነበር፡፡ አባባ ግን ስዘፍን ከሰማ ይቆጣል፤ ማቆም አልቻልኩም፡፡ ውሎዬ ሁሉ ልክ እንደ እናቴ ቴፕ ሥር ሆነ። በቁጣም በምክርም ብሎኝ ብሎኝ አልሰማ ስል ያንን ፓናሶኒክ ቴፕ ዬት እንዳደረሰው እንጃ ድራሹን አጠፋው፡፡ ቤታችን : ጭር አለ፤ የሚያስፈራ ጭርታ፡፡ ቤት እንደ ሰው ይሞታል ለካ፤ ቤታችን ሞተ፡፡ ዩኒቨርስቲ ገብቼ እስክመረቅ እቤታችን ቴፕ አልነበረም፡፡ አንዳንዴ እናቴ ትታቼው ከሄደቻቼው ጥቂት ካሴቶች አንዱን ይዠ ጎረቤት ቤት እሄድና ክፈቱልኝ እላለሁ፡፡ብዙ ጊዜ

ባለጋራዡ ክፍሌ ቢሮ(ቢሮ አይበለው መቆሸሹና መዘበራረቁ) እሄድና የብረትና የቅጥቀጣ ድምፅ ጋር እየታገልኩ ዘፈኔን እዬሰማሁ ቁጭ እላለሁ። በዚያ እናታችን ትታን በሄደችበት ዓመት ብዙ ነገር ተዘበራረቀብኝ፡፡ በተለይ የትምህርቴ ነገር እንዳልነበር ሆነ፡፡ ሆኖ የማያውቀውን በመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት በክፍሉ ውስጥ ከነበርነው 55 ተማሪዎች 47ኛ ወጥቼ አባባን እንደ ሴት አስለቀስኩት፡፡ አልተቆጣኝም አቅፎኝ አለቀሰ፡፡ ሠራተኛችን ጽጌ ታዲያ እንደ ፎካሪ ሰሎን ውስጥ እየተንጎራደደች "የምን ማልቀስ ነው? ልጁ ሁሉ እየወደቀ እየተነሳ ነው ትልቅ ደረጃ የሚደርስ፤ ለወደፊቱ ሁሉንም በልጣ አንደኛ ነው የምትሆን!“ ትላለች፡፡ በየመኻሉ ግን እሷም ዕንባዋን ትጠርግ ነበር፡፡ ሪፖርት ካርዳችን በተሰጠን ማግስት አንድ ሰከራም የክፍል ኃላፊ መምህራችን ከነበርኩበት ጎበዝ መደዳ እስነስቶ ሰነፍ መደዳ አስቀመጠኝ “ድሮም ዘፈን ስታበዥ ነው ነገር የተበላሼው!” ከሚል ስላቅ ጋር... ተነስተሽ ካልዘፈንሽ እያለ እንዳላስቼገረኝ... ፊቱ ላይ የነበረው ጥላቻና ንቄት ባሰብኩት ቁጥር ያበሳጨኛል። በዓመቱ መጨረሻ ሪፖርት ካርዴን ስቀበል፣ ልክ ልብ ድካም እንዳለበት ሰው የልጅ ደረቴን ድንገተኛ ውጋት ሰቅዞ ያዘኝ፤ ተዝለፍልፌ የምወድቅ ነበር የመሰለኝ። በቀሪ ዘመኔ ሁሉ አእምሮዬ ውስጥ እንደትራፊክ መብራት ደምቀው በሚያበሩ ቀያይ ፊደላት የተጻፈ ቃል ካርዱ ላይ ታትሞ ነበር “አልተዘዋወረችም'' ይላል፡፡ የሆነ ነገሬ ላይመለስ የተመታው በዚያ ሰይፍ በሆነ ቃል ነበር፡፡ ውዳቂነት፣ ከሰው ማነስ፣ አለመፈለግ፣ አለመሳካት፣ አለመቻል ይኼ ሁሉ በእናቴ የግዴለሽነት ሲሪንጅ ቀስ በቀስ ደሜ ውስጥ ሲሰርግ የነበረ የበታችነት ስሜት፣ በአደባባይ በመላ መምህራኖቼ እና ቦትምህርት ቤቴ ታውቆ የማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የተሰጠኝ ነበር የመሰለኝ፡፡ ከዚያች ቅጽበት ጀምሮ ትምህርት እንደ ቀደሙት ዓመታት በፍቅር አዲስ ነገር ለማወቅ የምጓጓበት ነገር ሳይሆን፤ ፍርኃት፣ ጭንቀት እና አባቴን ላለማሳዘን፣ በሰው ፊት ላለመዋረድ፣ ጓደኞቼ እንዳይርቁኝ ለመለማመጥ የሙጥኝ ብዬ የያዝኩት የገደል ጫፍ ገመድ ነበር፤ ትግል!!

ከዚያ በኋላ ጎበዝ ተማሪ ሆኜ ከምማርበት ክፍል፣ እስከ አጠቃላይ ትምህርት ቤት ከፍተኛ ውጤት እስከ ማስመዝገብ ብደርስም ያ ቃል ያንኮታከተው በራስ መተማመኔ ግን፣ እስከ መጨረሻው አልተመለሰም፡፡ በማንኛውም የሕይወቴ ክፍል አንድም ቀን ይሳካልኛል፣ እችላለሁ የሚል እምነት ኖሮኝ አያውቅም፡፡ በየትኛውም አጋጣሚ ከውድድር እርቃለሁ። ከዚያ የልጅነት ዕድሜዬ እስከ ኮሌጅ የፈተና ውጤት በሚነገርበት ቀን ልቤ ላይ የሚሰማኝ የሚያፍን ጭንቀት አለ፡፡ ውጤት ሲባል ብርክ ይይዘኛል። ከኮሌጅ ከተመረቅን በኋላ ሃይሚን ጨምሮ ብዙዎቹ ጓደኞቼ ያውም ከእኔ ያነሰ ውጤትም፣ ብቃትም : ያላቼው ልጆች በታላላቅ ድርጅቶች በጥሩ ክፍያ ሲቀጠሩ፣ ሥራ ሲቀያይሩ እኔ መጀመሪያ ከተቀጠርኩበት ቢሮ ንቅንቅ አላልኩም። ሥራ እንድቀይር፣ በየሚሠሩበት የውጭ ድርጅት ዕድሌን እንድሞክር ገፋፍተውኝ- ገፋፍተውኝ ሲደክማቼው፣ ሁሉም የራስሽ ጉዳይ ብለው ተውኝ። ያ “አልተዘዋወረችም!'' ያስፈነደቃት ብቸኛ ፍጥረት ጓደኛዬ ሃይሚ ነበረች፤ በደስታ አቅፋኝ ዘለለች፡፡ ምክንያቷ ደግሞ ገና አንደኛ ክፍል ስንገባ፣ ክፍል ደግማ ስለነበር እኩል መሆናችን አብረን እንድንቀጥል ዕድል ይሰጠናል ከሚል ንጹህ የጓደኝነት ፍቅር ነበር፡፡ ከፍ ስል- በዕድሜ ስበስል ታዲያ ያቺን አልተዘዋወረችም እያስታወስኩ በብዙ ሐሳብ እብሰለሰላለሁ። እንደ ቀልድ በወላጆቻችን፣ በመምህራንና ጓደኞቻችን የምትወረወር የቃል ዘር፣ ተራ ቃል ሆና አታልፍም፤ ከእኛ በላይ አድጋ ዛፍ ትሆናለች፤ ማንም ሰው ተጠልሎ የሚኖረው ውስጡ ተተክሎ ባበቀለ የቃል ዛፍ ጥላ ሥር ነው። በቀሪ ዘመናችን ሁሉ የዕድሜ ልክ ፍርኃት፣ አልያም ብርታት ጥለውብን የሚያልፉ ቅጽበቶች የሚበዙት መፈልፈያቼው ቃል ነው። ይኼን ይኼን አጥብቄ ስለማስብ ለንግግሬ በጣም ጥንቁቅ ነበርኩ፡፡ ከዚያ ክፉ ቃል በኋላ በእርግጥ በሒሳብና

በእንግሊዝኛ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ብቻ፣ በሕይወት ፈተና ወደተሻለ ከፍታ እንደማያሻግር ሕይወት ራሱ አስተማረኝ፡፡ በሥራ፣ በፍቅር እና ሌላም ማኅበራዊ ግንኙነቶቼ ያ ማኅተም፣ የእኔ ጠባሳ ብቻ እንዳልሆነ ተረዳሁ፡፡ በስንትና ስንት ጉድ የሕይወት ስንክሳር እንደ ቤተሰብ፣ እንደ አገር፣ እንደ ሃይማኖት “አልተዘዋወርንም” የሚል ማኅተም ኑሯችን ላይ አርፎብናል!! ለመስክ ሥራ ወጥቼ ያንን ውብ መልከዓ ምድር ስቃኝና የሕዝቡን መጎሳቆል ስመለከት፣ አገሬ ራሷ በየሜዳና ሸንተረሯ ላይ በማይታይ ቀለም “አልተዘዋወረችም!!” የሚል ማኅተም የታተመበት ይመስለኛል፡፡ እንደ አገር _ ስንት የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያጋጥመን እንዲህ ፈራረስን? እላለሁ። ምን ያኽልስ በጎርፍ ተጥለቀለቅን? መቼስ ነበር እሳተገሞራ ምድራችን ላይ የፈነዳው? የትኛውስ ወረርሽኝ ነበር ለዓመታት ሕዝባችንን የፈጄው? በየዐሥርና ሃያ ዓመት የሚያጋጥመን ድርቅ በዚያ ሁሉ ዓመታት በመረትነው ምርት የማይመከት ሆኖ ነው ወይ በርሃብ ሕዝባችን የሚያልቀው? ይኼ ሁሉ የተፈጥሮ መርገምት እዚህ ግባ የሚባል ጉዳት የማድረስ አቅም አልነበረውም!! ታዲያ ምንድን ነው እንዲህ ያጎሳቆለን? ምን ነበር ዓይናችንን ሸብቦ ሌሎች ከሩቅ ያዩትን እኛ ከቅርብ እንዳናይ የጋረደን? ይኼን ሁሉ ጦር ያማዘዘን...
👍373🥰2
ደም ያቃባን ሰበብ ምን ነበር? ቃል ነው! ቃል! ቃል ነው ያፋጄን!! በቃል ስንራገጥ ነው የምግብ ሌማታችንን ከአፈር የቀላቀልነው። የሚወረወርብን ቃል ነው ራሳችንን ጠልተን ሌሎችን እንድናመልክ ያደረገን፡፡ የተዋስነው ቃል ነው እንደ ትልቅ ጥበብ በየፖለቲካና በየእምነቱ እየተሰከሰከ ያባላን፡፡ ቃሉ ወጣም ወረደ ውጤቱ ሌላ ቃል ነበር “አልተዘዋወራችሁም'' የሚል መራር ቃል!! ባላችሁበት ርገጡ የሚል መርገምት፡፡ ቃል የሚሰበረው በቃል አይደለም፤ በድርጊት ነው፡፡ ከድርጊት የሚያቆም ቃል ሲዘራብን ልባችንን አለስልሰን ለማጽደቅ ተግተናልና እስከ አሁን እንደ ዘውድ አናታችን ላይ የተጫነው ጨለማ ቃል “አልተዘዋወራችሁም'' ነው የሚለን። ቃል በቃል ቢሰበር ኖሮ እንደ አገር “ተዘዋውረናል፣አድገናል፣ ተለውጠናል፣ መጥቀናል” እያልን ለዘመናት የጮኽነው ጩኸት በሰበረው ነበር።

በዚያ በልጅነት ዕድሜዬ ይኼ ገብቶኝ ሳይሆን፣ ውርደትን እንቢ ብዬ በመቆሚ ቢያንስ በትምህርት ያንን መርዘኛ ቃል ዳግም አላዬሁትም፡፡ ስምን መልአክ ያወጣዋል፣ ሰይጣን ይከልሰዋል! እናቴ ትታን ከሄደች ከአምስት ዓመት በኋላ አንድ ሾፌር አግብታና ልጅ ወልዳ ናዝሬት እንደምትኖር ባለጋራዡ ተክሌ ሹፌሮች ነገሩኝ ብሎ አወራን። አባቴ ይኼን የሰማ ቀን ጓደኛው ጋሽ ተስፋዬ ጋር ሲያወሩ “ታዲያ ለዚህ ከሆነ እኔን ማዬት ባትፈልግ እንኳን ልጆቿን ማኩረፍ ምን _ አስፈለገ!? ያውም እዚህች ናዝሬት ተቀምጣ?'' አለ፤ በእጁ ወደ ታች ወደ ልደታ እየጠቆመ። እስካሁን ናዝሬት በዚያ በኩል ይመስለኛል፡፡ በቃ ይቺኑ ነው ያለው "አልሰማ አልከኝ እንጂ ነግሬህ ነበር እኮ!* አሉት ጋሽ ተስፋዬ፤ ምን ይሆን የነገሩት? እስከዚያ ጊዜ ድረስ ስሜ ማኅደር ነበር፤ ስምንተኛ ክፍል ነበርኩ፡፡ አንድ ቀን አባባ ጠራኝና “ማኅደሬ ስምሽን ላስቀይረው ነው'' አለኝ...እውነቱን ለመናገር ማኅደር ትንሽ የመዝገብ ቤት ስም ዓይነት ይመስለኝ ስለነበር ሊቀዬርልኝ መሆኑ ደስ አለኝ። የኔ ቢሆኑ ብዬ የምመኛቼው አንድ ሦስት ስሞች ነበሩ... ሶስና (የጓደኛዬ ስም)፣ ፌቨን ...ሩሃማ ወዘተ... “ስም ልምረጥ?'' አልኩት በችኮላ፡፡ “አይ! መርጨልሻለሁ! ...ከዚህ በኋላ ስምሽ˙ ማኅደረ ሰላም ነው፡፡'' እንግዲህ የእናቴ ስም ሰላም ነው፤ አባባ ያደረገው ነገር ቢኖር ማኅደር እኔን ከፍቶ የእናቴን ፋይል እኔ ውስጥ አስቀመጠው(ወይስ ቀበረው?)፣ ዳኞች ነገራቼውን ሲጨርሱ ወደ መዝገብ ቤት እንደሚሉት፣ በመዶሻ የተቀመጥንበትን የምግብ ጠረጴዛ አልደቃውም እንጂ፣ ኮስተር ማለቱና ሌላ ጥያቄ እንዳላበዛበት መጣደፉ ቁርጥ ዳኛ። ብዙ ሰዎች ስምሽን እንወደዋለን ይሉኛል፣ _ አብርሽን _ ጨምሮ _ (ስሙን ቄስ ይጥራውና) የሆነ ሰላም ያለው ስም ነው ምናምን ይላሉ፣ ስሜ ውስጥ የተደበቀውን ዘግናኝ ጦርነት ማን በነገራቼው!? ስሜን ማኅደር ያለኝ ራሱ አባባ

ነው በኋላ የከለሰው ግን በአበባ ያደረ ሰይጣን ይመስለኛል፡፡ ታዲያ ስምን መልእክ ያወጣዋል ሰላም ያለሽ ልጅ ነሽ ይሉኛል። እዚህ ላይ እውነት አላቼው፤ አባባ የእኔ መልእክ ነበር፡፡ “ክንፍ የሌለው መልአክ?'' ለሚሉኝ ... “ክንፍ ነበረው እንደተኛ እናቴ ሰርቃ በረረችበት'' እላለሁ፣ለራሴ፡፡ ሰው ድልድይ ላይ አይኖርም! ከዘጠነኛ ክፍል ጀምሮ ሕልሜ ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት መግባትና መማር ሆኖ ነበር፡፡ ይኼ የእኔ ምኞት ሳይሆን በደም ሥሬ የገባ የእናቴ ቅዠት ነው ብልም ሐሳቡ ግን ከአእምሮዬ ሊወጣ አልቻለም። አንድ ቀን በስንት መለማመጥ፣ ማሳሳቅ እና መለሳለስ ይኼን ምኞቴን ለአባባ ነገርኩት “አቢ (አቢ ነው የምለው) ያሬድ ገብቼ ሙዚቃ መማር በጣም ነው የፈለግሁት፤ በእቴትዬ ሞት ፍቀድልኝ" እቴትዬ መቼና መቼ የሞተች እናቱ ናት፤ በእሷ ስም ተለምኖ እምቢ ያለውን ነገር አላስታውስም። ፊቱ ተቀያይሮ፣ ቃል አጥሮት፣ አፍጥጦብኝ ቆዬና ግንባሩን በእጁ እዬፈተገ “የረገመኝ ሰውማ አለ!” ብሎ ተነስቶ ወጣ፡፡ አባባ ፊት ላይ የነበረው ቁጣ እንኳን እኔን አቅመደካማ ልጁን ይቅርና፣ ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤቱን እንደ ባቢሎን የሚያፈራርሰው ይመስል ነበር፡፡ ምኞቴን እርግፍ አድርጌ ተውኩት፡፡ አንኳን አባባ ማንም ፊቱን ሲያዞርብኝ እደነግጣለሁ፤ ውስጤ የሆነ ነገር ይፈራርሳል፡፡ አባባ በቆመ በተቀመጠ ቁጠር እንደ ድመት እየተሻሸሁ፣ ተለማምጨ ከሳምንታት የመረረ ኩርፊያ በኋላ ወደ ቀድሞ ፊቱ ተመለሰ። ቢሆንም ዩኒቨርስቲ ገብቼ እስከምመረቅ በጥርጣሬ ነበር የሚያኝ፡፡ እኔም በውስጤ ስለ ያሬድ ትምህርት ቤት ማሰብ አላቆምኩም። አባባ የሚጠላው ሙዚቃን ነው ወይስ ሙዚቃ ወዳዷን እናቴን? እሺ እናቴ ሐኪም ብትሆን ኖሮስ? አካውንታት ወይም ነጋዴ ብትሆን?

የሆነችውን ሁሉ አታጠኝም ይለኝ ነበር? አባባ ቢፈቅድልኝና ብመዘገብ ኖሮስን የእውነት ትምህርቱን እወደው ነበር? ሙዚቃ ራሱ እወዳለሁ? ወደ እናቱ መቅረቢያ፣ መሻገሪያ ድልድይ እንጂ መዳረሻዬ ባይሆንስ? ይኼኛው ትንሽ አሳመነኝ፡፡ በራሴ ጸብ ገላጋይ ስሆን ኖሪያለሁና ለራሴ እንደ መፎክር ደገምኩት “አዎ! ሙዚቃ ወደ እናቴ መሻገሪያ ድልድይ እንጂ የእኔ ዕጣ ፋንታ አይደለም!” ስለዚህ ሰው ድልድይ ላይ አይኖርም፣ ወይ መሻገር አልያም መቅረት!" አልኩ፡፡ ብሻገር እናቴ የለችም፣ ብቀር ደግሞ እኔ እራሴ አልኖርም፤ ስለዚህ የራሴን መንገድ ትቼ ለፈጣሪና ለመንግሥት ዕጣፋንታዬን ሰጠሁ፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር እንደ ጉሊት ሽንኩርት እዚያና እዚህ በዘፈቀደ ሲመድበን፣ ንግድ ሥራ ኮሌጅ ላይ ዕጣዬ ወደቀ። አካውንቲንግ ማጥናት ጀመርኩ። እያንጎራጎርኩ መደመርና መቀነሴን ተያያዝኩት። እንትናን ታውቂያታለሽ? አካውንቲንግ ተምራ ነው በኋላ ታዋቂ ዘፋኝ የሆነችው ሲሉ ልቤ እየደነገጠ። ዜማ! እንደወለድኩ ሰሞን፣ የባለቤቴ ቤተሰቦች በየተራ ከአጠገቤ አይጠፉም _ ነበር። ከሆስፒታል ስወጣም የባለቤቴ ቤተሰቦች ቤት ነበር የወሰዱኝ፡፡ለነገሩ ቤታችን ያው አንድ ግቢ ውስጥ ነው፤ እነሱ ወደሚኖሩበት ትልቁ ቤት ነበር የወሰዱኝ፡፡ ስለ ምግብ፣ ስለ ጡት፣ ስለ ልጅ፣ ስለ መልክ፣ ስለ አራስነት ብዙ ያወራሉ። ያ ሁሉ ሰው ከብቦኝ እንኳን “ለልጄ እኔ ብቻ ያለኋትና ምን ማድረግ አለብኝና የለብኝም'' በሚል ሐሳብ እወዛገብ ነበር፤ ዐሥር ጊዜ አያታለሁ፡፡ አንዳንዴ ትንሽ ሸለብ አድርጎኝ ስባንን፣ እዚህ ገንፎ ገንፎ እና ቅቤ ቅቤ የሚሸት ክፍል ውስጥ፣ ያውም በጠራራ ፀሐይ እንደ በሽተኛ አልጋ ላይ የተጋደምኩት ምን እያደረኩ ነው? የሚል ጥያቄ ሽው ይልብኛል፤ ወልደሽ ነው! ልጅ ወልደሽ! እላለሁ ለራሴ፣ ከማን? ብዬ መጮኽ

ያምረኛል፣ በራሴ ጸብ ገላጋይ እሆናለሁ፡፡ ቀስ በቀስ ሁሉም ወደ የግል ሕይወቱ ሄዶ እኔና ይህች ትንሽ ፍጥረት ተፋጠን ቀረን። እንደ እንግዳ ፍጥረት ነበር የማያት፣ እሷም በትንንሽ ዓይኖቿ ታፈጥብኛለች። እርጉዝ ሆኜ ያሰብኩትን ሁሉ እንደቴፕ ሪከርደር ቀርጻ፣ በልቧ ተሸክማው የወጣች ይመስለኛል፡፡ አፍ ብትፈታ እየጮኸች ለሕዝብ የምታወራ፣ ደግሞ ዓይኖቿ ንቃታቼው፤ እጆቿ፣ እግሮቿ፣ ከንፈሯ፣ ሁሉ ነገሯ ትንንሽና ውብ የሆነች ሙዚቃ የምትመስል ነገር፡፡ በዓይን የምትሰማ ሙዚቃ፡፡ ለማንም ባልናገረውም በውስጤ ዜማ ብዬ ስም አወጣሁላት፡፡ ባለቤቴ “የአምላክ ሥራ መባል አለባት'' አለ፡፡ እናቷ ማኅደረሰላም፣ ልጅቱ የአምላክ ሥራ ምንድን ነው ይኼ ሁሉ ሐተታ!? እያልኩ ሳስብ ባለቤቴ ስለ ስያሜው ሰፊ ማብራሪያ ይሰጣል:: “ይገርማችኋል! ወደ ስደት ዓለም ስሄድ ፣ በሱዳን ብዬ፣ በሞሮኮ አድርጌ በረሃው፣ ባሕሩ፣ ጀልባው፣ ጨለማው...
👍325
ለዚህ እበቃለሁ ብዬ አስቤ ነበር? …“ኔቨር”! የአምላክ ሥራ ድንቅ ነው...!" እያለ...እና የሱን የመኳተን ታሪክ እዚህች እንደ ዘፈን ግጥም ምጥንጥን ያለች ዜማ ላይ፣ እንደገና በተንዛዛ ኖታ ሊጽፈው ነው ...? ዜማ ነው የምላት፣ የኔ ዜማ! የማንንም ታሪክ በነፍሷም በስሟም ሳትሸከም የራሷን ሕይወት እንድትኖር ነበር ፍላጎቴ፡፡ መሳም እንደ ሳሙና የሚያሟሟ ቢሆን ኖሮ፣ ከንፈሬ ላይ ሟሙታ ባለቀች ነበር፡፡ ዓይኖቿ፣ ጸጉሯ፣ ጉንጯ፣ አንገቷ (ወይኔ አንገቷ!)፣ እጆቿ፣ እግሮቿ፣ ሁሉ ነገሯ ለመሳም የተሠራ ትንሽ ለስላሳ ፍጥረት፡፡ ለአጭር ጊዜም ቢሆን ውስጤ በዚህች ፍጥረት ተረጋግቶ ነበር፡፡ ያለምክንያት ስንቴ ልብስ ቀዬርኩላት!? ያለምንም ምክንያት አርፋ ከተኛችበት ስንቴ አንስቼ አቀፍኳት!? ደግሞ ዘፈን መዝፈን የወጣልኝ በእርሷ ነበር፡፡ አዳራሽ እንደሞላ ተመልካች እሷ ፊት ያልዘፈንኩት ምን ዘፈን አለ!? ቁልጭ ቁልጭ እያለች እንደ ትልቅ ሰው በጥሞና ስትሰማኝ ዓለም ሁሉ በግርምትና በአድናቆት የሚመለከተኝ እስኪመስለኝ ልቤ በደስታ ይዘል ነበር፡፡ ልጆች አንድ ጥሩ ነገራቼው፣ የምናጫውታቼው አስመስለን _ እስኪወጣልን እንድንጫወት ሰበብ መሆናቼው ነው።

ያ የሚያቅለሸልሽ ጊዜ እንደገና መጣ፡፡ በሌ መዳራት ያምረዋል፤ ዐሥር ጊዜ "ማሬ! አሁንኮ ሰውነትሽ ዝግጁ ነው"ይለኛል፡፡የሴትን ልጅ ሰውነትን ጊዜ አያዘጋጄውም ፍቅር ብቻ ነው የሚያዘጋጀው ብዬ ላምባርቅበት _ እመኛለሁ፡፡ መንፈስ ግን የሰውነት አንዱ ክፍል አይደለም እንዴ? ሰው ሥጋ፣ ነፍስ እና መንፈስ ነው አላሉም? ታዲያ ሥጋ ብቻውን ስላገገመ እንዴት ለመዳራት ዝግጁ ነሽ ይባላል? አብሬው ላለመተኛት የምደረድረው ሰበብ ሁሉ ሲያልቅብኝ፣ እንደተማረከ ወታደር ቅስሜ ተሰብሮ ወደ መኝታ ቤቱ እየተጎተትኩ ገብቼ በጀርባዬ ተኛሁና እግሬን ከፍቼ ዓይኖቼን ጨፈንኩ፡፡ እንደዚህ ሳደርግ፣ ሌላኛዋ ማኅደረ ከመኝታ ቤት ውጭ ቆማ ይችኛዋን ወደ ውስጥ ገፍትራ ያስገባቻት ነው የሚመስለኝ። የተበታተንኩኝ፤ ብዙ የሆንኩኝ ዓይነት። “ፍቅር ከላይ የለበሺውን አታወልቂውም ...?'' ይለኛል፡፡ “ከላይ ምን ጉዳይ አለህ?'' ማለት ያምረኛል፡፡ ዓይኖቼን ጨፍኜ አስባለሁ፣ እነዚህን ወተት ያጋቱ ጡቶች ከልጄ ጋር መሻማት አማረህ?...ሁሉም ነገር ጊዜ አለው...አሁን ጡቶቼ ለወንድ ሐሴት የሚሰጡ ነገሮች አይደሉም፣ የወተት ዕቃዎች ናቸው...በቃ ያንኛው ትውልድ ነኝ...ይኼ ትውልድ የሚያውቀኝ በእናትነት ነው ...እማማ ነኝ!... ባልቴት... የጨረጨስኩ ማሂሰላም ...ማሂ ረብሻ ...ማሂ ማንም! ማሂ ምንም! ሚስትነት ይሁን እናትነት፣ ክብር ይበሉት ወግ፣ ሰው በሕይወት ተገዶ እስከተጫነበት ድረስ _ ምናቼው ያኮራል?! _ አበባም ይሁን ድንጋይ፤ በግድ እስካሸከሙን ድረስ ያው ሸክም ነው!! በዚህም መኻል ደግሞ አእምሮዬ ፊዚክስ የሚመስል ሐሳብ ያሰላስላል፤ለምሳሌ እላለሁ፣ ይኼ ከላዬ ላይ የተከመረብኝ ባለቤቴ፣ ክብደቱ ትንፋሽ ያሳጥረኛል፣ በክብደት ከአብርሃም በጣም ያንሳል፣ ግን አብርሽ አንድም ቀን ክብደቱ ተሰምቶኝ አያውቅም ነበር፣ ያውም አራት ዓመት ተሸክሜው፤ እና... ኦህ...! ዝም ብዬ ነው የምቀባጥረው፣ እናንተ ሸክማችሁ የከበዳችሁ እንደ እኔ ሸክማችሁን ለማቅለል ብላችሁ በገባችሁበት ነገር ሌላ ሸክም ከመጨመር ያድናችሁ!

ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍286
እባክሽ አትሂጂ…..
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አስር


ምግቡን ጨርሼ ገበታው ከፍ ካለ በኃላ ቡናው እየተፈላ ወሬ ጀመርን፡፡በዛ መሀከል.‹‹.ወይ እማዬ እስከአሁን ያመጣሁልሽን እቃ እኮ ሳልሰጥሽ…እንግዳው እኮ ፋታ አልሰጠንም፡፡ ››አለችና ከተቀመጠችበት ተነሳች፡፡
‹‹ጎረቤቶቼ እኮ ደስታዬ አስደስቷቸው ነው…ስጦታው የት ይሄድብኛል? ብለሽ ነው…ደግሞ  የእኔ ስጦታ አንቺ ነሽ››
‹‹ውይ እማዬ ስወድሽ እኮ፡፡ ››ብላ እየከፈተች የነበረውን የሻንጣ ዚፕ  አቋረጠችና ወደእማዬ ተንደርድራ በመሄድ አንገቷ ላይ ተጠምጥማ ጉንጯን አገላብጣ ሳመቻት፡፡ወደሻንጣዋ ተመለሰችና ሙሉ በሙሉ  ከፈተች..ከዛ ሽቶ …ቅባቱ…ቀሚሶች.. ሹራቦች …አይኖቼን ለማየት እስኪደክመኝ እና እኔ በግሌ አስከሚያንገሸገሸኝ ድረስ አንድ በአንድ እያወጣች ለእነማዬ እያሳየችና እያስለካች ቡናው ሁሉ ተጠጥቶ አልቆ ሰዓቱ ሶሰት ሰዓት አለፈ..፡፡
‹‹ወይ ልጄ ይሄ ሁሉ አሁን ለእኔ ምን ያደርግልኛል .?.ገንዘብሽን ከሰከሻ …በይ ከእያንዳንዱ ግማሹን ቀንሺና ለቤተሰቦችሽ ወሰጂላቸው፡፡››
እኔን በጎንዬሽ እይታ እየገረመመቺኝ‹‹ተያ እማዬ…አታበሳጪኝ….ለአንቺ ያመጣሁት ለአንቺ ነው …ሌላ ይቅር አንድ ሽቶ        አንስተሸ ለገዛ ልጅሽ ብትሰጪው እራሱ እበሳጭብሻለሁ››አለቻት፡፡
‹‹ለእሱ እንኳን ለምን ብዬ ሰጠዋለው..?አንቺ ራስሽ ስንት ነገር ታመጪለት የለ?››.
‹‹ውይ እማዬ እኔ ካንቺ ውጭ ለሌላ ለማንም ሰው እቃ አላመጣሁም፡፡ለልጅሽም አንድ ስልክ ብቻ ነው ያመጣሁለት..ቅር እንደማይለውና በአንቺ እንደማይቀና ተስፋ አለኝ፡፡››
የውስጥ ብስጭቴን ላለማሳየት  ብሞክር ሙሉ በሙሉ የተሳካልኝ አይመስለኝም፡፡ያባሳጨኝ ለእኔ ምንም ይዛ አለመምጣቷ ሳይሆን ያንን በገዛ እናቴ ፊት እንደጀግንነት ማውሯቷ ነው፡፡በዚህ ብስጭት ብድግ ብዬ ወደቤቴ መሄድ ሲኖርብኝ እኔ ግን በተቃራኒው ጭራሽ የእናቴን  ቤት ለቆ የመሄዱ ሀሳብን ከአእምሮዬ ሰረዝኩት፡፡
ያንንም ይሄንንም እያወራንና እየተጫወተን እስከ 5 ሰዓት ከቆየን በኃላ እማዬን ከተቀመጠችበት ተነሳችና ‹‹ልጆች..እኔ እንግዲህ አሮጊት ነኝ.. ከዚህ በላይ መቀመጥ አልችልም..ልተኛ፡፡›› ብላ ወደመኝታ ቤቷ በዝግታ መራመድ ስትጀምር እርግበ ‹‹እማዬ›› ስትል ጠራቻት፡፡
‹‹አቤት ልጄ››ቆማ ፊቷን ወደእኛ በማዞር መለሰች፡፡
እኔ የገመተኩት ደህና እደሪ ትላታለች ብዬ ነበር..እርግበ ግን ባልጠበቅኩት ሁኔታ‹‹ካንቺ ጋር ልተኛ?››ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹‹ወይ አፈር በበላሁት…በጣም ደስ ይለኛል..ጫወታሽን ስትጨርሺ ነይ››ብላት ፊቷን አዙራ እርምጃዋን ቀጠለች፡፡
እርግበም ወደእኔ ዞራ በደስታ እየተፍለቀለቀች‹‹ታድዬ››አለች፡፡
ሊፈነዳ የሚንተከተከውን ንዴቴን እንደምንም አፍኜ በመቆጣጠር ዝም አልኳት፡፡የሆነ ነገር ብላት በዚህ እኩለ ለሊት አላስፈላጊ ንትርክ ውስጥ መግባታችን ነው፡፡ለዛ ሚሆን ሞራል ደግሞ የለኝም፡፡
////
ተነስቼ ወደ መኝታዬ ለመሄድ ስንቀሳቀስ..ዘና ብላ ተከተለቺኝ፡፡ ከፍቼ ስገባ  ተከትላኝ ገባች ፡፡ሀሳቧን ቀየረች እንዴ ?ብዬ ደስ የሚል አይነት ስሜት ተሠማኝ።አልጋው ጠርዝ ላይ ስቀመጥ እሷ ከኮመዲኖው የእጅ ቦርሳዋን አነሳችና "የእኔ ፍቅር ደህና እደር"ብላ ጉንጬን ሳመቺኝና ቀጥ ብላ ወጥታ ሄደች።
" ተነሳሁና ከውስጥ በራፍን ዘግቼ  ድንዝዝ ባለ ስሜት ልብሴን አወላልቄ አልጋዬ ላይ ወጣሁና ተኝቼ ማሰላሰል ጀመርኩ፡፡ምናቤ ግን በደቂቃ እርግበን ረስቶ ልዕልት ጋር ነበር የሄደው፡፡.ቅድም እቤቷ የሄድኩ ጊዜ አሪፍ የፍቅር ታሪኳን እየተረከችልኝ ነበር፡፡እርግጥ የእሷን ጣፋጭ የሆነ የፍቅር ታሪክ መስማት ለእኔ መራር ነበር።ቢሆንም ምንም እንኳን ገና ታሪኳን ልትነግረኝ እንደጀመረች  ቤተሠቦቾ በመምጣታቸው ትረካውን ብታ  ቋርጠውም ያቺን ያህል እንኳን ወደአለፈ  ህይወቷ ጠለቅ ብላ ለእኔ ለማውራት  ተነሳሽነት ማሳየቷ በማሀከላችን ያለውን መቀራረብ እድገት እያሳየ እንደሆነ ማሳያ አድርጌ ስለወሰድኩት ከቤቷ ለቅቄ ስወጣ ፍፅም ደስታ እየተሰማኝ ነበር።በቅርብ ደግሞ የጀመረችውን ታሪክ እንድትጨርስልኝ ደግሞ የሆነ ነገር ፈጥሬ የብቻችን የሆነ ሰዓት እንዲኖረን ማድረግ አስቤለው።ስለዝርዝሩ  እስከአሁን  ምንም የመጣልኝም የወሰንኩትም ነገር የለም።
ምን ጊዜ እንቅልፍ እንደወሰደኝ አላውቅም፡፡ብቻ አንዴ እርግበ …ትንሽ ቆይታ ደግሞ ልዕልተ በህልሜ በሆነ ታሪክ ውስጥ እየመጡና እየተቀያየሩ  ከወዲህ ወዲያ ሲያላጉኝ ነው ያደሩት፡፡.ያላሰብኩት የበራፍ መንኳኳት ነበር ከእንቅልፍ ያባነነኝ።ከመቼው ነጋ ብዬ ተነሳሁና ሰዓት ከሞባይሌ ላይ ሳይ ገና 11፡15 ይላል።
በብስጭት "ማነው?" ስል ጠየቅኩ፡፡
‹‹ክፈት እኔ ነኝ፡፡››
ማንነቷን እያወቅኩ እንዳበሸቀቺኝ ላበሽቃት"አንቺ ማን?"ስል ጠየቅኳት።
‹‹እርግበ ነኝ፡፡››
ከመኝታዬ ወጣሁና በፓንት ብቻ እንዳለሁ ከፍቼላት ወደመኝታዬ ተመለስኩ።‹‹የተከፈተውን በራፍ ዘጋችና በዝምታ ወደእኔ መጥታ ከውስጥ ገባችና ተኛች።ነገረ ስራዋ ግራ አጋባኝ።ምነው እማዬ አባረረቺሽ እንዴ?››
‹‹ምን በወጣት ታባርረኛለች...ቅዳሴ ሄዳ ነው.፡፡››
‹‹አሀ ዛሬ ለካ እሁድ ነው፡፡››
‹‹አዎ..፡፡››
‹‹ዝም አልኩና ወደእንቅልፌ የተመለስኩ ማስመሰሌን ቀጠልኩ።ከአስር ደቂቃ በኃላ ተነሳችና ከአልጋው ወረደች።
‹‹ደግሞ ወዴት ልትሄጂ ነው?››
‹‹የትም ...፡፡ሻወር ወስጄ መጣሁ።››ብላ ወደሻወር ቤት አመራች።‹‹አሁን በዚህ ውድቅት ለሊት ሻወር መውሠድ ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው።››በውስጤ ነው ያብሰለሠልኩት።ከ10 ደቂቃ በኃላ ነጭ ፎጣ ከወገቧ በታች አገልድማ ከወገብ በላይ እርቃኗን ሆና መጣች።በተኛሁበት አጨንቁሬ እያየኋት ነው።ከዛ ከአልጋው አንድ ሜትር ርቀት ላይ ፊቷን ወደእኔ ዞራ እንደቆመች ያገለደመችውን ፎጣ መዠርጣ ፈታችና አምላክ እንደፈጠራት እርቃኗን ሆና በመቆም በፎጣው ሰውነቷን ታደራርቅ ጀመር።እኔ ታዲያ ከአመታት በፊት ያንገላታኝን...ምወደውንና የናፈቅኩትን ውብ ገላዋን ዳግመኛ ሳይ ትዝታዎቼ ሁሉ...ብሶቶቼ ሁሉ...ረሀቤና ሰቀቀኔ ሁሉ  ተቀሰቀሰብኝ።በፈጣሪ ውበቷ..የቆዳዋ ጥራትና የሠውነቷ ቅርፅ ይበልጥ ተውቦ...ይበልጥ ተጠርቦ ነው እየታየኝ ያለው። ደግሞ የብልቷን ፀጉር እንዴት ባለ ጥንቃቄ ነው የላጨችው።...ስለብልቷ ሳስብና ሳወራ የገዛ ብልቴ ተገታተረና ያደረኩትን ፓንት ወጣጥሮ ህመም ነገር ተሰማኝ።
ፎጣውን አጠገቧ ያለ ጠረጴዛ ላይ ጣል አደረገችና አንሶላውን ገልጣ ወደ ውስጥ ገብታ ተኛች። በመሀከላችን በቂ ክፍተት የነበረ ቢሆንም እኔ ግን ያንን ክፍተት ጠብቄ ለማቆየት ትዕግስቱ አልነበረኝም።እየተሳብኩ ሄድኩና ተጣበቅኩባት።
‹‹እን...ዳ..ላቀዘ…ቅዝህ፡፡››
‹‹መቀዝቀዙን እኮ ፈልጌው ነው፡፡››ብዬ የቀኝ ክንዴን በአንገቷ ዙሪያ አሽከረከርኩና  አቀፍኳት።
‹‹ይሄን ያህል ሞቀህ ነበር..ማ..ለት ነው?››በልስልስ እና በተዳከመ ንግግሯ ጠየቀቺኝ።
ይበልጥ እየተጣበቅኩባት‹‹የአንቺን እርቃን ገላ  በአይኖቹ  እየተመለከተ በመላ ገላው እሳት የማይንቀለቀልበት ወንድ ይኖራል እንዴ?››
👍47👏21
"እኔ እንጃ ፍ...ቅ...ር  ….. ለእኔ ያለህ ስሜት ጭርሱኑ  የተዳፈነ መስሎኝ ነበር እኮ...››ብላ ሌላ መልስ ከመመለሴ በፊት ከንፈሬ ላይ ተለጠፈችብኝ፡፡ከዛ ምን ልንገራችሁ።ብርድልብሱን ገልቤ ጣልኩና  አላዮ ላይ ተከመርኩባት፡፡ገለበጠቺኝና ከላዬ ተቀመጠች፡፡ቀስ እያለች ወደታች እየተንሸራተተች በእግሮቼ መካከል ገባች።ከዛ በሁለት እጆቾ ፓንቴን ግራና ቀኝ ይዛ ወደታች እየሳበች አወለቀችና ብልቴን ይበልጥ እንዲነቃቃና ይበልጥ እንዲገተር መሰለኝ በስልት ታሸውና ታልበው ጀመር።
ከዛ ምን ልንገራችሁ የእናቴ ቤት መሆኑን እስክዘነጋ ድረስ መቃተትና ሆነ...ሩሄን እንድስት ነው የደረገቺኝ ..፡፡
ከብዙ መፋተግ..ከስንት መቃተትና መወራጨት  በኋላ የሁለት አመት ረሀባችንንና በኩርፊያና መናቆር የተሸፈነ ናፍቆታችንን ተወጥተን ተያይዘን ወደሻወር ገባን። ከዛ በኃላ እቅፍቅፍ ብለን ተመልሰን ተኛን.፡፡አራት ሰዓት አካባቢ እማዬ ከቤተክርስቲያን ተመልሳ ቁርስ ተሰርቶ እስክትቀሰቀሰን ድረስ ሁለታችንም ያለንበትን አናውቅም ነበር።


ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍353😱2
እባክሽ አትሂጂ…..
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አስራአንድ


ወይ ጉዴ አሁን እሺ ምን ላደርግ ነው...?ከጎኔ ካለችው እርግበ ጀርባ የምትታየኝ ልዕልት ነች።ልዕልት ከነሶስት ልጆቾ።ወይ ግራ መጋባት።
ቁርስ በልተን ቡና ተፈልቶ ጨርሰን ካጠናቀቅን በኋላ ‹‹የዛሬ ውሎሽ እንዴት ነው?››ስል በሹክሸክታ እርግበን ጠየቅኳት፡፡
‹‹ማለት?››
‹‹ምትሄጂበት ቦታ አለ?››ይሄን የጠየቅኳት ምን አልባት ቤተሠቦቾ ጋር መሄድ ትፈልጋለች ብዬ ስለገመትኩ ነው።
እሷ ለእኔ መልስ መመለሱን ትታ ወደእማዬ በመዞር‹‹እማዬ››ስትል ተጣራች።
‹‹አቤት የእኔ እርግብ››
‹‹ዛሬ የምትሄጂበት ቦታ አለ እንዴ ?››ስትል ጠየቀቻት።
‹‹አይ ልጄ የትም አልሄድም...ምነው ጠየቅሺኝ?"
‹‹አይ ከተማውን ዞር ዞር እያልን እንድናየው ነው፡፡››
‹‹አዬ ልጄ… አሁን ከእኔ ጋር ምኑን ታይዋለሽ?ከእሱ ጋር አይሻልሽም?››
‹‹አይ ካንቺ ጋር ይሻለኛል፡፡››
‹‹እንደዛ ከሆነ እኔ  የሆነ ጉዳይ ስላለኝ ልሄድ...እንደዋወል››አልኩና ለመሄድ ተነሳሁ።
"ሁለቱም በፈገግታ ሸኙኝ።ወጥቼ መኪና ውስጥ ገብቼ ከግቢው ለቅቄ ወጣሁ፡፡ የምሄድበት ቦታ ስለሌለኝ ወዴት እንደምነዳ ግራ ገባኝ።ዝም ብዬ ወደቤቴ ነዳሁት፡፡ቢያንስ ትንሽ አረፍ ብዬ ልብሴን ቀያይሬ ወጣለሁ፤እስከዛውም ወደየት እንደምሄድ ይገለፅልኝ ይሆናል።እቤት ደርሼ ሶፋዬ ላይ ገደም ብዬ ቻናል በመቀያየር ላይ እያየሁ  ሞባይሌ ተንጫረረ፡፡አነሳሁና አየሁት...የማላውቀው ቁጥር ነው ።ፈራ ተባ እያልኩ አነሳሁት።
‹‹ሄሎ ደ/ር እንዴት አረፈድክ?››ጠንከር ያለ የጎረምሳ የሚመስል ድምፅ።
‹‹ማን ልበል..አላወቅኩህም››
‹‹በቀደም ተገናኝተን ነበር...አቤል እባላለሁ...የልዕልት ወንድም ነኝ››

ፈዞና ዝሎ የነበረው ሰውነቴ የልዕልትን ስም ሲሰማ በቅፅበት ውስጥ ተነቃቃ‹‹እ አቶ አቤል?እንዴት ነህ?ምነው ልዕልት ሰላም አይደለችም እንዴ?ማለቴ ባለቤቷን አመመው እንዴ?"ጥያቄዬን ደረደርኩ።

‹‹አይ ዶ/ር ሁሉ ነገር ሰላም ነው።ለራሴ ጉዳይ ፈልጌህ ነበር?››

‹‹ነው ጥሩ...ታዲያ መች ይመችሀል?››ዶ/ር ከአንተ ጋር መገናኘት ለእኔ በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ስለሆነ  መቼም ቢሆን ይመቸኛል?...ባይሆን አንተ መች ይመችሀል?››
‹‹እኔ  በሳምንቱ ውስጥ ያለኝ እረፍት ዛሬ ብቻ ነው።››
‹‹እና መገናኘት እንችላለን ዶክተር....እባክህ?››እሺ እንድለው  ተማፀነኝ።
‹‹አሁን የት አካባቢ ነው ያለኸው?››ጠየቅኩት፡፡
‹‹መገናኛ ነኝ››
‹‹በቃ  ወደ22 ጠጋ በል... ከአንድ ሰአት በኃላ  ደውልልሀለው፡፡››
‹‹አመሠግናለው ዶ/ር...እንዳልከው አደርጋለሁ፡፡››
‹‹ስልኩን ዘጋሁና  ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ወደመኝታ ቤቴ አመራሁ...፡፡ ይሄንን  ቀጠሮ እኔም እፈልገዋለሁ...ምክንያቱም የልዕልትን ሰዎች ባገኘሁ ቁጥር ይበልጥ ስለእሷ የማወቅ ዕድል እየኖረኝ ይሄዳል፡፡ያንን አስቤ ነው  የእንገናኝ ግብዣውን በፍጥነት የተቀበልኩት።ቁም ሳጥኑን ከፈትኩና ይመቸኛል  ወይም ያደምቀኛል ብዬ ያሰብኩትን ሙሉ ሰማያዊ ሱፍ ከነጭ ሸሚዝ ጋር መረጥኩና በጥንቃቄ ለብሼና ዘንጬ እቤቱን ለቅቄ ወጣሁ...አቤልን ካገኘሁት በኃላ በዚህ አለባበሴ ወደልዕልት ሄጄ ባገገኛት ጥሩ እንደሆነ አሰብኩና ላደርገው ወሰንኩ...እሷን ስለማግኘት ሳስብ ፊቴ  በፈገግታ ደመቀ...::ልክ 6፡25 ላይ ሀያ ሁለት ተገናኝንና ተያይዘው ክትፎ ቤት ገብተን ጥሩ ምሳ በላን።ከዛ ወጣንና ካፌ ገብተው ትኩስ ነገር እየተጠቀምን ወደተገናኘንበት ጉዳይ ገባን።

‹‹እሺ አቤል በሳላም ነው የፈለከኝ?፡፡››ስል ጠየቅኩት፡፡እውነቱን ለመናገር እሱ ከሚፈልጋኝ በላይ እኔ ፈልጌዋለው…እሱ ከእኔ ለማግኘት ከፈለገው መረጃ በላይ እኔ ከእሱ መረጃ ማግኘት እፈልጋለሁ..እሱ የእህቱ ህይወት ከሚያሳስበው በላይ እኔ ስለእህቱ የነገ ህይወት ያሳስበኛል፡፡እኔ ልዕልተን ለመርዳት ከሚፈልገው በላይ እኔ ልረዳት ፈልጋለሁ፡፡ግን እነዚህ ሁሉ ፍላጎቶቼን በግልፅ ማሳየት አልፈለኩም፡፡እንዴት ብዬ?ስለዚህ እራሴን ተቆጣጥሬ ውይይታችንን በዘዴ ማስኬድ እሞክር ጀመር፡፡
‹‹ዶ/ር  ባሏ ምን ያህል የመዳን እድል አለው፡፡››ፍርጥም ብሎ ፍጥጥ ያለ ጥያቄ ጠየቀኝ፡፡
‹‹ይሄን ለመመለስ አስቸጋሪ ነው፡፡ጥቂት ወራትን ጠብቀን ተጨማሪ ምርመራዎችን ማድረግ አለብን፡፡››
‹‹ቁርጥ ያለ እርግጠኛ መልስ ልትሰጠኝ ባትችልም..የሆነ ግምት ግን ይኖርሀል..እባክህ ዶክተር ማወቅ እፈልጋለሁ፡፡››
‹‹እንግዲያው ንገረኝ ካልክ ተገቢው የህክምና ክትትል ከተደረገለትና የእሱም ሰውነት ተገቢውን ምላሽ መስጠት ሚችል ከሆነ ጥሩ የሚባል የመደና እድል አለው፡፡››
‹‹ጥሩ ሲባል ምን ያህል?››
‹‹አስር ፐርሰንት ፡፡››
‹‹አስር ፐርሰንት..እህቴ ለአስር ፐርሰንት ነው እንዲህ እየተጎሳቆለች ያለችው?አስር ፐርሰንት ዕድል ላለው ሰው ነው እንዲህ ሴት መሆኗን እንኳን የዘነጋችው?ለአስር ፐርሰንት እድል ነው እንዲህ ዘመዶቾን የዘነጋቸው? ወንድሞቾን የረሳችው፤ ከጓደኞቾ ጋር ሁሉ የተቆራረጠችው…?፡፡››
ልመልስለት የማልችለውን ግትልትል በምሬት የታሹ ጥያቄዎችን አዠጎደጎደብኝ፡፡
‹‹ተረጋጋ ..አስር ፐርሰንት እኮ ትልቅ ነው..ሰው አንድ ፐርሰንትስ እድል  ኖሮት እንኳን ያቺን ለመጠቀም የመጨረሻውን ጥረት ይጥር የለ፡፡ባለቤቷ የልጆቾ አባት እኮ ነው፡፡የመጨረሻውን ጥረት ከማድረግ ውጭ ምን ምርጫ ይኖራታል?››
‹‹ዶ/ር እኔ ለምን ታስታምመዋለች አልልኩም፡፡እኔ ከመጀመሪያውም ጀመሮ የሰውዬውን ባልወደውም ለእሷ ግን ባሏ ነው፤የልጆቹ አባት ነው፡፡ያንን ለመካድ ፈልጌ አይደለም፡፡ግን እሷ እየኖረች እሱን ማስታመም ትችላለች እኮ..ነርስ እንቅጠርልሽና ይንከባከቡት አልናት፤አንገቴ ላይ ካራ አስቀምጡ አለች፡፡እሱ እስኪድን ወይም እስኪሞት ምን ያህል ጌዜ ይፈጃል..?እስከዛስ እሷ እንዴት ተሆናለች?ዶ/ር ልዕልተ የቤታችን ብቸኛ ሴት ልጅ ነች፡፡ስምንት ወንዶች መካከል የተወለደች ብቸኛ ሴት ልጅነች፡፡ሁላችንም እንደጣኦት ነው የምናያት፡፡በዛ ላይ አያቴ ስላደሳደጋቻት አብረን አላደግንም፤እናም ስስታችን ነች..በእሷ ሁኔታ እናታችን ቀንና ለሊት በማልቀስ አይኖቾ ሊጠፋ ነው፡፡ለማንኛውም እቤተሰብ ተሰብስቦ አንድ ውሳኔ ወስኗል …ያንን ውሳኔ ለመተግበር ያንተን ትብብር እንፈልጋለን፡፡››
ውሳኔውን ለመስማትና ከእኔ ምን አይነት እርዳታ እንደሚፈልጉ ለማወቅ በጣም ተነቃቃሁ፡፡‹‹መስፍንን ወደውጭ ሄዶ እንዲታከም ወስነናል››
‹‹ጥሩ ነው ግን እኮ ህክምናው ውጭ በሚሰጥበት ጥራትና ብቃት እዚህ ይካሄዳል…ምንም የተለየ ለውጥ አታገኙም፡፡››
‹‹ዶ/ር.. የእኛ ዋና አላማ እሱን ማዳን አይደለም፡፡ እህታችንን ማዳን ነው፡፡አንድ ወንድም አለው እሱን አሳምነን አብረን እንልካቸዋለን.፡፡አብዛኞቹ ወንድሞቼ ውጭ ስለሆኑ እዛ ያለውን ነገር እንሱ ይስተካክሉታል፡፡ከዛ ህክምናውን ይወስዳል..ከዳና መልካም ካልዳነም ችግር የለውም…፡፡››
‹‹ሀሳባችሁ ጥሩ ይመስላል..ግን አብሬው ካልሄድኩ ካለችስ?››ሥል ጠየቅኩት፡፡
‹‹እንዳዛ ልትል ትችላለች፡፡ግን ሶስት ልጆቾን ጥላ መሄድ እንደማትችል ስትረዳ  ሀሳቧን ታስተካክላለች፡፡››
‹‹እሺ እኔ ምንድነው ማደርግላችሁ…?››
‹‹ውጭ ሄዶ ቢታከም የተሻለ እንደሆነ እና ምትችል ከሆነ እንድትልከው ጠቆም አድርጋት..አንተን ስለምታምንህ ወዲያው ነው የምትስማማው….፡፡››
‹‹ያንንን ማድረግ ችላለሁ፡፡››
👍527🤔1
‹‹በጣም ነው የማመሰግነው ዶ/ር…እግዜር ይስጥልኝ፡፡››
ከእሱ እንደተለየሁ መጠጥ ቤት ገባሁ..እስከሁለት ሰዓት ስጠጣ ነበር..ከዛ ወጥቼ ወደቤቴ ልሄድ ካልኩ በኃላ እርግበ እማዬ ቤት እንደሆነች ትዝ ሲለኝ  ሀሳቤን ቀየርኩና ወደእማዬ ቤት አመራሁ፡፡
           …
እቤት እንደገባሁ ሰራተኛዋ ከሶፋው አጠገብ ሲኒዋን ደርድራ በማንደጃ የሚንቀለቀል ከሰል አቀጣጥላ ብናዋን ችስስስ እያደረገችና እየቆላች ነው።
‹‹ውይ መጣህ ጋሼ..ቁጭ በል አለቺኝ።››

‹‹እማዬስ?››

‹‹እናትህ መአድ ቤት እራት እየሠሩ ነው?››

እርግበስ ብዬ ልጠይቃት አልኩና ለምን እንደሆነ አላውቅም ከምላሴ ላይ መለስኩት...እና ቀጥ ብዬ ወደመአድ ቤት አመራሁ።ከእማዬ ጎን ትኖራለች ብዬ ጠብቄ ነበር።ስደርስ እማዬና የምትሰራው የምግብ ሽታ ብቻ ነበር የተቀበለኝ።

‹‹ውይ ልጄ መጣህ?››

‹‹አዎ እማዬ...እንዴት ነሽ?››

‹‹ደህና ነኝ...ምነው አትስመኝም እንዴ?››

‹‹ስራ ላይ አይደለሽ ..ለዛ ነው።››
‹‹ትኩር ብላ አየችኝና ...ቀማምሰሀል ማለት ነው...?ደግሞ ምን ሆንክ?››

እናት የልጇን አሁናዊ ሁኔታ የምታነብበትና የምትተነትንበት ብቃት ያስገርመኛል...የእኔ እናት ብቻ ነች ወይስ የሁሉም እናቶች ተመሳሳይ ናቸው?ይሄው አይኔን ብቻ አይታ መጠጣቴን ብቻ ሳይሆን ለምን እንደጠጣሁ ሳይቀር መገመት ትችላለች።ዝም አልኳት።

‹‹እራት ደርሶል ሂድና እርግበን ጥራት››

‹‹አለች እንዴ?መኝታ ቤት ተኝታ ነው?››

‹‹አይ እቤቷ ነች፡፡››

የእማዬ መልስ ግራ አጋባኝ‹‹እቤቷ ማለት?››

‹‹የጀርባውን ቤት ገብታበታለች፡፡››

‹‹ምን ማለት ነው?››
‹‹እንዴት ምን ማለት  ነው… አንተ ነቃ ብለህ እቤትህ ወስደህ ካላኖርካት ታዲያ በረንዳ ትደር?››

‹‹እማዬ ደግሞ ምን እያልሽ ነው?ለመሆኑ  የተከራዩት ሰዎችስ?ለቀው ነው?››

‹‹አይ ...ልጄ ቤት አስፈልጓታል ብዬ አስወጣኋቸው...መቼስ የእኔ የእናቷ ቤት እያለ ቤት ፍለጋ አትንከራተትም፡፡››

ከዛ በላይ ከእማዬ ጋር መነታረኩ እርባን ያለው ሆኖ ስላላገኘሁት እግሬን አንቀሳቀስኩና ጀርባ ወዳለው ቤት ሄድኩ ።እቤቱ ቤተሰብ ያላቸው ሰዎች እንዲከራዩት ታስቦ የተሠራ ባለአንድ መኝታ ክፍል የራሱ የሆነ ሻወር ቤትና ኪችን ያለው ዘመናዊ ቤት ነው።ደረስኩና አንኳኳሁ።ተከፈተልኝ።
ከስር አጭር ጅንስ ቁምጣ አድርጋ ከላይ ብጣቂ ጨርቅ እላዮ ላይ ጣል አድርጋለች።
‹‹መግባት ይቻላል?››ንዴቴን እንደምንም በውስጤ አፍኜ   ጠየቅኳት።

‹‹ግባ..ግባ››በራፉን በደንብ ከፈተችልኝና ዞር ብላ መግቢያውን ለቀቀችልኝ።


ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍404
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  አስራ አምስት

አደባባይ!

በአንድ የጷግሜ ማለዳ ስርቅርቅ የሚል የሴት አባውዴ ድምፅ ከእንቅልፌ አነቃች፡፡ በዚያ ውብ ድምፅ የባለቤቴን እናት እያሞገሰች ነበር።

ጓዳሽ ለሁሉ ክፍት እንዳ'ደባባይ፣ ደግነትሸ መብራት ባለም የሚታይ፣
ፊትሽ የማይጠቁር የመጣው ቢመጣ፣ ቸርነትሽ አይነጥፍ ቢወጣ ቢወጣ፣..."

ከዚያች የአባውዴ ግጥም በላይ የባለቤቴን እናት የሚገልጽ ምንም ነገር የለም። ያ ግጥም የባለቤቴ እናት ፎቶ ነበር፡፡ ከባሌ ዮናስ ቤተሰቦች ቤት እንደ አደባባይ ሰው አይጠፋም፡፡ የአክስትና አጎቶቹ፣ የሩቅና የቅርብ ዘመዶቹ ብዛት ለጉድ ነበር፡፡ ጭር አለ ከተባለ በሳምንት ሁለት እና ሦስት እንግዳ መምጣቱ አይቀርም፡፡ ታዲያ ባለቤቴ “በተቸገርንበት ሰዓት አንድኛቼውም አልነበሩም'' ይለኛል:: ወልጄ አንድ ዓመት አልፎኝ እንኳን፣ የአራስ ጥዬቃ እያሉ የሚንጋጉት ዘመዶቻቼው ብዛት ይገርመኝም ይጨንቀኝም ነበር፡፡ ለይቶለት እንግዳ ተብሎ የሚመጣው ይቅርና “በዚህ ሳልፍ ሰላም ልበላችሁ ብዬ ..." ብሎ ጎራ ካለ በኋላ ግማሽ ቀን ቆይቶ የሚሄደው ሰው ብዙ ነበር፡፡ እናቲቱም እንግዳ ይወዳሉ። እንግዳ በመጣ ቁጥር አንድ ቀን ፊታቼው ላይ ቅሬታ ዓይቼ አላውቅም። ለእሳቼው ሁሉም ሰው የመድኃኒዓለም እንግዳ ነው። እህቶቹም በእናታቸው ወጥተው ነው መሰል ሽር ጉድ ብለው እንግዳ ማስተናገድ ይችሉበታል፡፡ የሚገርም ትህትና ያላቼው ሁለት እህቶች አሉት፡፡ እናታችንን ትተን አንሄድም ብለው እስከአሁን ያላገቡ፤ ታዲያ እናቲቱ “ግቢው ሰፊ፣ ባትሄዱ እንኳን እዚህ አምጧቼው እና ኑሩ፤ አንቺ በዚያ በኩል ቤት ብትሠሪ አንቺኛይቱ በዚህ

እንዳለሁላችሁ ወለድ ወለድ አድርጉ!” ይላሉ። ታዲያ ይኼን፣ ይኼን ሳይ፣ ወደ ኋላ ተመልሼ የራሴን ሕይወት እታዘባለሁ። እኛ ቤት እንግዳ ተብሎ ሰው የመጣበት ጊዜ ትዝ አይለኝም፡፡ በጣም አልፎ አልፎ የሠራተኛችን የጽጌ አባት ይመጡ ነበር። እሳቼውም አይቆዩም፣ ወይ ከገጠር ለሕክምና አልያም ለሆነ ጉዳይ ከተማ ብቅ ሲሉ፣ እግረ መንገዳቼውን ነበር ልጃቼውን ለማዬት እቤታችን ጎራ የሚሉት። ተሸማቀው በር ሥር ያለች ወንበር ላይ እንደተቀመጡ፤ የሚበሉም ከሆነ በልተው፣ ቡናም _ ከተፈላላቼው ጠጥተው፣ ይሄዳሉ። ከፍ ስል የሰው ናፍቆቴን ለመወጣት እንደሆነም እንጃ በጣም ብዙ ጓደኞች ነበሩኝ። ደመወዜ የሚያልቀው _ በሰርግ፣ በልደትና በክርስትና ስጦታ በየጓደኞቼ ቤት ስዞር ነበር፡፡ ቆይቼ የተረዳሁት ነገር፣ ጓደኞቼን በስጦታ ልገዛቼው እየታገልኩ እንደነበር ነው፡፡ ዛሬ ላይ አንዳቼውም የሉም፣ ዛሬ እዚህ አደባባይ ላይ :: ታዲያ አሁን ላይ የባሌ ቤተሰቦች፣ ዘመድ አዝማድ ነን የሚሉ በዙሪያዬ የሚያንዣብቡ እናቶች ያስጠሉኛል፤ ያው''አንችም እናት እኛም እናት''በሚል ሒሳብ ስለጡጦ፣ ስለዳይፐር፣ ስለምናምን ሊያወሩኝ ሲጀምሩ ሰበብ ፈጥሬ ከወሬያቼው ርቃለሁ፡፡ በጣም ጥልቅ ቢሆንም ለራሴ ብቻ የገባኝ አንድ ነገር፣ አንዳንድ ሴቶች ስለ ልጅ ጸጋነት ከሚያወሩት በላይ በመውለድ አደገኛ መቀዣበር ውስጥ ይገባሉ፡፡ እና ወጣት ሴቶች ቶሎ ወልደው ወደዚህ የመቀዣበር ዓለም እንዲዘፈቁ ሳያሰልሱ ይመክራሉ “ውለጅ እንጂ!'' ሲሉ እኔ “ያዬሁትን ደስታ እይ'' ማለት ብቻ አይደለም፣ “የቀመስኩትን ፍዳ አንችም ቅመሽ'' የሚል ምቀኝነትም ውስጡ ያለ ይመስለኛል፡፡ እና ስለወለድኩ ብቻ ጓደኛቼው ሊያደርጉኝ ይፈልጋሉ፣ ወሪያቼው ይደክመኛል፡፡ አንድኛቼውም ስለ ድሮ ፍቅረኛቼው አያወሩም፤ ከእናታቼው ማሕፀን ሲወጡ ባሎቻቼው በማቀፊያ እየተቀበሉ _ ወደየቤታቼው የወሰዷቼው ይመስል... ስለ ትላንት፣ ስላለፉበት ሕይወት ቢሞቱ አያወሩም፡፡

እኔ ስለ ትዳር፣ ስለ ላጅ ልቤ አርፎ ማውራት አልቾልም :: ገና ነኝ፣ ያልተዘጋ የሕይወት ሒሳብ በልቡ አልነነ ታት ለመንገድ መሳሳም፣ በየጢሻው መጓተት፣ በ Rot ቤቱ ጨለማ መጎነታተል ልቤ ይሸል፡፡ ገና ነኝ ሥጋዬ እንጂ፣ ነፍሴ ለእናትነት አልተዘጋጀችም፤ ጨዋ ሚስት አይደለሁም፡፡ ምናለ ዳይፐርና ምናምናችሁን ይዛችሁ ወደዚያ ብትሄዱልኝ፡፡ የሚሰትር ነገር ይሰትራቼውና “እንዲህ በወጣትነት በትዳር መሰተር መባረክ ነው!” ይሉኛል፡፡ ነፍሶብኛል፣ውስጤ አውሎ ነፋስ አለ፣ እንደ ፊኛ ውስጤን ሞልቶ አቅልሎኛል፣ ወደነፈሰበት እንድንሳፈፍ አድርጎኛል፣ ይኼ ባል የሚባለው ሰውዬ የነፋስ ጣት ላይ ነው ቀለበቱን ያጠለቀው፡፡ አንዳንዴ ልጄን ለሆነ ሰው መስጠት ያምረኛል፣ ወይም ልጄን ለባሌ እናት ሰጥቼ፣ በዚያው ፍርድቤት ጎራ ብዬ የፍች ወረቀት ማስጻፍና በሰው ልኬለት ወደዚህ ቤት አለመመለስ። ሐሳቤ ያስደነግጠኝና ዜማን እንስቼ ጥብቅ አድርጌ አቅፋታለሁ፤ ሁልጊዜም ውስጤ ይቅርታ ይጠይቃታል፡፡ ይቅርታ ስላት አባባ ትዝ ይለኛል:: ላገባ ሁለት _ ሳምንት ሲቀረኝ አባባ አድርጎት የማያውቀውን «እስኪ ዛሬ ራት ልጋብዝሸ!» አለኝ፡፡ ደስ ብሎኝ ተያይዘን ወጣን፡፡ ራት በልተን፣ ስናወራ “ማኅደሬ መቼም ላንችም፣ ለወንድሞችሽም ያለፈው ጊዜ ቀላል አልነበረም፤ ከዚያች ሴት ስለወለድኳችሁ ይቅርታ አድርጊልኝ፡፡ ሰው ነኝና ወድጃት ነበር፤ ግን ሁኔታዋን ከጅምሩ እያዬሁ፣ እናተንም መውለዴ ራስ ወዳድነቴ ጭፍን ቢያደርገኝ ነው"አለኝ፡፡ እኔም ገና ካሁኑ ከባለቤቴ ስለወለድኳት ሳይሆን፣ በዚህ መወዛገብ ውስጥ ሆኜ ስለወለድኳት ይቅርታ ይላል ውስጤ፡፡ በእግሮች መካከል... ፈጣሪ ሴትን ልጅ ድንግል አድርጎ የፈጠራት ለምንድን ነው? ምናልባት ከምታገባው ወንድ ውጭ ሄዳ እንዲህ ዓይነት መዘበራረቅ ውስጥ እንዳትገባ ልዩ የተፈጥሮ ማስጠንቀቂያ ይሆን!? ድንግልና ከልባችን እና ከአእምሯችን ጋር የተያያዘ

የሴትነታችን ማዕከል ይሆን? ወይስ ዙሪያችንን እንደ መንፈስ የከበበን የማይታይ ስስ መስተዋት? ለምን ሴቶች ብቻ ተለይተን እንደዚያ ተፈጠርን? 'ኦዲተር' ነበርኩና አንድ ነገር አውቃለሁ፤ የከበረ ነገር የተቀመጠበት ካዝና ምንጊዜም በጥብቅ ማኅተም የታሸገ ነው፡፡ ምን ችግር አለው ማንስ ቢከፍተው? ይሉት አጉል ፈሊጥ ከዬት የመጣ ጅል ሐሳብ ነው?! ከጋብቻ በፊት ወሲብ ምንም ችግር የለውም ያሉኝ አሁን የት ናቸው!? እውነት ነው የፈሰሰ ውሃ አይታፈስም፤ ግን ስንደናበር የደፋነውን ውሃ መደፋቱ ልክ ነበር ማለት የጅል ሙግት፣ መራርም ቀልድ ነው፡፡ በተለይ የሚያሳዝነው እንደፈለገ የሚረግጥ ወንድ እግር ሥር ብርጭቋችንን ከከበረ መደርደሪያው አውርደን _ ማስቀመጣችን፤ ጎንበስ ብሎ እንኳን ምን ተሰበረ? ምንስ ተደፋ ለማይል ደንታ ቢስ- ሂያጅ! ከጋብቻ በፊት ወሲብ፣ ከጋብቻ በፊት ዕልል ያልተባለለት ጋብቻ መሆኑን እንዴት አልነገሩኝም!? ጉዳዩ የአምስት ደቂቃ ያበደ የሥጋ ፍላጎት ብቻ ነው እንዴ!? የሚተኛን ወንድ በእግራችን መኻል አልፎ የሚሄድ መንገደኛ ነው? የሴት ልጅ እግሮች የከተማ መግቢያ ላይ እንደተተከለ የእንኳን ደህና መጣችሁ 'ቅስት' ናቸው፤ በዚያ አልፎ ወደልባችን ከተማ የሚገባ ጸጉረ ልውጥ መቼ እንደሚወጣ ማን ያውቃል ?...
👍385👏1
እንደ ሁኔታው የከተማችን ነዋሪ ሆኖ ከመኖር አልፎ አንዳንዱ እንዲያውም የከተማችን ከንቲባ ሆኖ ቁጭ ሊል ይችላል፡፡ አንድ ከተማ ስንት ከንቲባ ይኖራታል ታዲያ!? አልፎ መሄድ የሚባል ነገር የለም፣ ደመቀም ደበዘዘም፣ ሁሉም ትላንታችን፣ ውስጣችን ተቀማጭ ነው፡፡ ያውም ዛሬያችንን ጋር እየተጋፋ። ከገጠር እስከ ከተማ፣ ከተማሩት ፊደል አጠገብ ዝር እስካላሉት ድረስ የሴት ልጅ የዕድሜ ልክ ችግር እንደ ባቡር እየተጎተተ የሚያልፈው በእግሮቿ መኻል ነው። እያንዳንዷ ሴት በፍቅርም ይሁን በሌላ መንገድ እግሯን ከከፈተችባት ቅጽበት ጀምሮ በሥጋ፣ በነፍስ፣ በመንፈስ ዕድሜ ልክ የሚከፈል ዕዳ ከሕይወት ግምዣ ቤት ትበደራለች፡፡ ይመስለናል... ስላገባን ዕዳችን የሚከፈል፤ ይመስለናል... ስለወለድን ነፃ የምንወጣ፤ ይመስለናል... በሐብት እና ስኬት ማማ ላይ ስለቆምን ትላንታችን የሚፋቅ፡፡

ድንግልና ይኼን የዕድሜ ልክ ብድር ከመውሰዳችን በፊት፣ ብድሩን ምን ላይ እንደምናውለው ቀድመን እንድናስብ የተቀመጠ የተፈጥሮ ማስጠንቀቂያ ነው። ስለ ሥጋ ድንግልና ብቻ ማለቴ አይደለም፤ መንፈሳችን ምን ጊዜም ድንግል ነው፤ ማንም ጋር ከመጋደማችን በፊት ኅሊናችን ይኼ ሰው ማነው? ሲለን ያቺ ጥያቄ፣ ያቺ ከፍላጎትና ስሜታችን ጋር እየታገለች ወደ ኋላ ልትጎትተን የምትሞክረው የውስጥ ጩኸት፤ እሷ የመንፈሳችን ድንግልና ናት። ያቺ ድንግልና ቦታዋ ኅሊና ነውና ጾታ የላትም፤ ወንድም ሴትም ላይ አለች፡፡ ለባለቤቴ ዮናስ እንዳረገዝኩ የነገርኩት ቀን በደስታ ምድር ጠበበችው፤ ምሳ ውጭ ካልጋበዝኩሽ አለ፡፡ የአዲሳበባን ውድ ሆቴሎችና ሬስቶራንቶች ስም ሲያነሳ ሲጥል፣ ሁልጊዜ አብርሃም ጋር እንገናኝበት የነበረ ሜክሲኮ አካባቢ ያለ ሬስቶራንት እንዲወስደኝ ነገርኩት፤ ነፍሴ ናፍቃ ነበር፡፡ ሰው ብቻ አልነበረም፣ የበፊት ፍቅረኛዬን ብቻ አልነበረም የናፈቅሁት...ደረጃዎቹ ናፍቀውኝ ነበር፣... ወንበሮቹ ናፍቀውኝ ነበር፣... የዚያ ቤት ሙዚቃ ናፍቆኝ ነበር...ሁሉም ነገር ናፍቆኝ ነበር፡፡ በቃ አረገዝኩ፣ በቃ አለቀ ልክ እንሚወዱት ሰው መቃብር እርሜን ላወጣ ነበር የሄድኩት፣ባሌን እየጎተትኩ፡፡ ወደ ለቅሶ ቤት ሲወስዷቼው ሃይሎጋ እያሉ የሚሄዱ ምስኪኖች ምንኛ ያሳዝናሉ!? ባሌ እንደዚያ ነበር፡፡ ምሳ በልተን ዮናስ የባጥ የቆጡን ሲያወራ (ስለፈረደባት አሜሪካ) ፊት ለፊት አብርሃም ሲገባ አዬሁት፡፡ ልክ የዓመት ቀጠሮ እንደያዘ ሰው፤ ከዚያ በፊት ለዓመት በአካል አላዬሁትም ነበር። ልቤ ተመንጥቃ ልትወጣ ምንም አልቀራትም፣ ትንፋሼን ዋጥ አድርጌ ያላዬሁት ለመምሰል _ ሞከርኩ፡፡ አይቶኛል፣ ተያይተናል በጣም የሚያሳዝነው ነገር ትንሽ እንኳን አልደነገጠም፡፡ ፍቅረኛውን ወንድሟ ጋር ተቀምጣ ያያት ወንድ እንኳን ከዚህ የተሻለ ይደናበራል፤ ተረጋግቶ አንድ ሦስት ጠረጴዛ ያኽል ርቆ ፊት ለፊቴ ተቀመጠ - ፊት ለፊቴ፡፡ ሌላ ቦታ አልነበረም? ነበር፤ ትዕቢቱ ነው! ሌላ ወንድ ጋር ስላዬሁሽ አልቀናሁም የራስሽ ጉዳይ ነው።

ወደ ጠረጴዛው ሳቀረቅር አንዳች ኃይል ጸጉሬን ይዞ ወደ ኋላ የሚጎትተኝ ይመስል፤ ቀጥ ብዬ የማዬት ፍላጎቴ እያሸነፈኝ ዐሥር ጊዜ አዬዋለሁ፣ አምሮበታል፡፡ እንደ ሁልጊዜው እጅጌው ክንዱ ላይ የተጠቀለለ ሰማያዊ ሸሚዝ ለብሷል፡፡ አስተናጋጁ ሊታዘዘው ሲሄድ እንደሚቆይ _ ነገረው፣ ተቃጠልኩ፤ አለማዘዙን ያወቅሁት አስተናጋጁ ትሪውን እንደያዘ ሄዶ አንዱ ጥግ ሲቆም ነው፡፡ ሴት እንደቀጠረ እርግጠኛ ነበርኩ፤ ነግሮኛል...አሳይቶኛል፣ ሴት ሲቀጥር ሁልጊዜ ቀድሞ ከተገኜ የቀጠራት ሴት እስክትመጣ ምንም አያ'ዝም፡፡ የቀጠራት ሴት ነች ...ሴት ነች አውቂያለሁ፡፡ ውስጤ ባሕር በሚያኽል ዕንባ ሲሞላ ታወቀኝ፤ ያውም የፈላ የሚንተከተክ ዕንባ! እርግጠኛ ነኝ ሴት ነች፣ ስለ እኔ ምንም አይላትም እንደ ሌሎቹ ሁሉ ያለፍኩና ያለፈብኝ አንዲት ልጅ ነኝ፡፡ ባለቅስ የሬስቶራንቱን ሰሃንና ማንኪያ ሁሉ የሚያንሳፈፍ ውሃ ቤቱን የሚሞላው እስኪመስለኝ ዕንባ ብቻ ነበር ውስጤ፡፡ አምላኬ ሆይ ዕንባዬ ድንገት እንዳይዘረገፍ እርዳኝ! _ እያልኩ የምትመጣውን ሴት ለማዬት ነፍሴ ተስገበገበች፤ ...ምን ታደርግልኛለች!? ብልም፡፡ እዚህ ባሌ ያወራል፣ ምን እንደሚያወራ እንጃ! ለደቂቃ እንኳን ዝም ቢል ምን ይሆናል? እዚያ አሜሪካ የሰው ያለኽ ብሎ ነው እንዴ የመጣው!? ዓይኞቼ በባሌ ትከሻ ላይ አሻግረው፣ ባሌ እንዲሆን የምመኜውን ሰው ይመለከታሉ፤ በግዴለሽ ዓይኖቹ አካባቢውን ይቃኛል፡፡ ሄደሽ እቀፊው- እቀፊው ይለኛል፣ ሳሚው-ሳሚው፣ እዚሁ ልብስሽን አወላልቀሽ ...ባልጊ ይለኛል፡፡ ደግሞም ፊቴ በቀረበው ሰሃን ብርጭቆ ምናምን አናቱን በይው የሚለኝም ክፉ ሐሳብም አለ፡፡አሁን መታጠቢያ ቤት ደርሼ ብመለስ ወንበሬን ስቼ እሱ አጠገብ የምቀመጥ ይመስለኛል፡፡ ምንድን ነው አሁን ይኼ የተረገመ ልጅ ኖሮት ያገባሁት ሰው የሌለው?...ምን...? ባሌ ለመሄድ ሲዘጋጅ (እንሂድ እያልኩ ሳጣድፈው የነበርኩት ራሴ ነኝ) ቡና እንደምፈልግ ነገርኩት(ሱሰኛ ሆነሺልኛል ብሎ ፈገግ አለ)ለቀልዱ ትንሽ ሳንቲሞች ቲፕ እንደመወርወር ዓይነት ፈገግ አልኩለት፤ ይኼ ፈገግታዬ ያቁነጠንጠዋል፤ እዚያ ጋ ለተቀመጠው ፍጥረት ግን ሠላሳ ሁለት ጥርሴን አገር እስኪያዬው ብገለፍጥ ግድ

አይሰጠውም!... መናቅ ዕልኽ አጋብቶኝ ይሆን የወደድኩት!?... ወይስ መውደዴ ይሆን ይኼን መናቄን በጸጋ እንድቀበል ያደረገኝ!? በዚያች ቅጽበት አብርሃም ስልክ ሲያወራ ነበር፡፡ የሚለውን ለመስማት ጆሮዬን በቆምም፣ እንዲሁ ከድምፅ በስተቀር መልዕክቱ አልተሰማኝም፡፡ ድንገት ተነስቶ ወጣ፣ ወዴት ነው!? ብዬ ለመጮኽ ቃጥቶኝ ነበር፡፡ ያዘዝኩት ቡና ሲመጣ፣ ውስጤ ተገለባበጠ ሊያስመልሰኝ ይታገለኝ ጀመር፡፡ ተነስቼ ወደመታጠቢያ ቤት ሮጥኩ፣ አስመለሰኝ፣ ተቃጠልኩ! የት አባቱ ሊያገኛት ይሆን? ድፍን የአዲስ አበባ ሬስቶራንቶች፣ ካፍቴሪያዎች ባንዴ ብዙ ሺሀ ሆኜ መገኜት አማረኝ፤ በዚህ ሰዓት ለእኔ፣ ይኼ ሰው የቀጠራትን ሴት ማዬት ምንም ነገር ከማዬት በላይ ጉጉቴ ነበር፡፡ ሴት ናት አውቂያለሁ፣ ቦታ ቀይሮ እንደቀጠራት አውቂያለሁ፡፡ እንደወጣ የመጣልኝን ቡና ሳልቀምሰው ቦርሳዬን አነሳሁና እንሂድ አልኩት፡፡ ባሌ ግራ ተጋብቶ፣ አንዴ እኔን አንዴ ቡናውን ሲመለከት፣ እቤት ሄደን አሪፍ ቡና አፈላለሁ አልኩት...ተፍነከነከ፣ ጅል! መቼም ቡናዬ አሪፍ ሆኖ አያውቅም፤ ይኼን እንዴት ይረሳል!? ማን ናት!?...ረዥም የሚያማምሩ እግሮች ያላት ቀይ ሴት(እግር ይወዳል እንደውሻ) ጠይም፤ ዳሌዋ ሰፊ የኮሌጅ ተማሪ ወጣት፣ ግጥም ምናምን አደንቃለሁ የምትል ቀልቃላ የ19 ዓመት ልጅ፣ የሆነች ገና 26 ዓመቴ ነው የምትል ኑሮ የተመቻት የ37 ዓመት ሴትዮ...ማናት!?... የማላውቃት ሴት ጋር፣ የማውቀው ቤት፣ የማውቀው አልጋ ላይ፣ የማውቀው ሰውነቱን ማዬት ራሴን አዞረው፡፡ ስልኬን አውጥቼ መልሼ ወደ ቦርሳዬ አስገባሁት፣ ባሌ ጎን ሆኜ ልደውልለት ምንም አልቀረኝም፤ ባሌ ያወራል፣ በእርግዝና ወቅት ቡና መጠጣት ጥሩ እንዳልሆነ በሰፊው እያብራራ ነበር መላ ሰውነቴ ሚጥሚጣ እንደተነሰነሰበት ሁሉ ተንገበገበ፡፡ ባሌ ጋር ሲያዬኝ ለምን አልቀናም? አውቃለሁ አይቀናም... ለእኔ ግድ እንደሌለው አውቃለሁ ...በሽተኛ ነው!... አንዱ መንገደኛ ይቅርታ አንዴ ስልክህን ልደውልበት ቢለው እንደሚሰጠው ሁሉ፣...ይቅርታ አንዴ ፍቅረኛሀን እዚያ መንገዱን ተሻግሮ
👍32🔥21
ያለው አልቤርጎ ወስጄ _ ልተኛት ቢለው ወደ ሰውዬው ገፋ አድርጎኝ፣ እስክመለስ ግጥም እየጻፈ የሚጠብቅ ዓይነት ሰው ነው። ምን ዓይነት ወንድነት ነው ይኼ? ሌላው ሁሉ ነገር ይቅር፣ ለምን ሰራሱ ክብር አይኖረውም? "ሸርሙጣ!'' አለ ክፍሌ፣ ሰው ወዶ አይደለም ለካ የሚባልገው፡፡ ለምን ከዚያ ሁሉ ነገር በኋላ ተወኝ? አውቃለሁ “በቃን'' የሚል ቃል ከአፉ ስላልወm ራስሽ ተውሽኝ እንጂ እኔ አልተውኩሽም እንደሚል፣ ሰምቻለሁ ከአሜሪካ የመm ሰው ለማግባት ተወችው እንደተባለ፡፡ የተወኝ ግን እሱ ነው፣ እያለሁ ሰውነት ብቻ ያደረገኝ፡፡ ለምን ተወኝ? የወተት ጥርስ እንደሚባለው የወተት ፍቅረኛ አለ? ጊዜው ሲደርስ ከልባቼው ድድ ላይ ነቅለው ጥለው ዋናውን ፍቅር የሚያበቅሉበት? በልጅነት እንዳልደመቁበት? የፈገግታ ሀ ሁ... እንዳልተማሩበት? እኔ ለእሱ የወተት ጥርስ ነበርኩ፤ የፍቅር ፈገግታ በሆንኩበት የሕይወት ድዱ በቅዬ የተነቀልኩ፣ ገና መነቃነቅ ስጀምር ከሥር ሌላ ሕይወት እየበቀለ መሆኑ ገብቶኛል፡፡ ገና ሊነቅሉን ሲያነቃንቁን አይሆንም እንዳንል “የመጀመሪያ ፍቅረኛ ጋር ጋብቻ አይሰምርም'' በሚሉት ፈሊጥ አለማምደውናል፡፡ ዘፈን ሁሉ አላቼው...! “ምን ያለው አሞራ ከዛፍ ይሟገታል፣ ከወደዱት ጋራ ማን ሲኖር አይቶታል" ... የእውነት ግን እፎይ ብዬ ያረፍኩበት ዛፍ ነበር'ኮ አብርሽ ለእኔ፡፡ ብሟገት ለምን እወቀሳለሁ? ማን ነው ለርስቱ የማይሟገት? ሰዎች እንኳን ለሕይወት፣ ለሰባራ ሳንቲም እንዴት እንደሚሆኑ ጠንቅቄ የማውቅ አካውንታንት ነኝ፤ ለምን ይኼን ይኼን ያቃልሉታል...!? ሌላው ሌላው፣ ይቅር ከዛፍ የሚሟገተው አሞራ፣ ክንፍ እያለው፣ መብረር እየቻለ፣ ከግንድ ምን አሟገተው አይሉም? መብረር የማይችሉ ሰዎች ለምን አይበርም? እያሉ ሲዘባበቱ፣ ለመብረር ክንፍ ብቻ በቂ መስሏቼው ነው መቼስ፤ ለሌሎች በማይታይ ቋጠሮ ክንፋችን ሲታሠር _ ከመካሪው በላይ የምናውቃት መብረር ሩቅ ትሆንብናለች፡፡

አንዳንድ ያልታደሉ ወንዶች አሉ፣ ባንወዳቼውም ሁሉን ነገር ስንጨርስ፣ አልያም ከሕይወት ተሸንፈን ስንባረር፣ በትዳር ስም አንደ ሬሳ ሳጥን የምንከተትባቼው፡። ትዳር ለአንዱ የሕይወት ጅማሬ ለሌላው ፍጻሜ ሲሆን ደስ አይልም፡፡ ሁሉን ነገር ጨራርሶ የፍቅር ቅራሪው እንኳ ተለቅልቆ የተደፋ ባዶ ሰውነትን በቬሎ ገንዞ፣በል የሚሉት የሬሳ ሳጥን ውስጥ ሲጥሉ፣ ሰርግ እልል የሚባልበት ለቅሶ ነው፡፡ ለልጆች በሉ የተራረፈውን ብሉ፣ ተብሎ እንደሚሰጠው ዓይነት የተራረፈ መንፈስና ሥጋ የሚቀርብላቼው ርሃብተኛ ናቸው፤ እና ረሃቡ መለስ እስከሚልላቼው የትራፊ ጠዓም አይገባቼውም፡፡ ባል ብዬ ያገባሁት ሚስኪን እንደዚያ ነበር፤ ከመሬት ተነስቼ ሳዬው እበሳጫለሁ፣ ነገረ ሥራው ሁሉ ደሜን ያፈላዋል፣ ማታ ሲገባ ቀንሽ እንዴት ነበር? ብሎ ከንፈሬን ሲስመኝ በቃሪያ ጥፊ ባጠናግረው ደስታዬ ...ምናገባው ስለቀኔ? የቱ ቀን ነው? ቀን መቁጠሪያ ዓይቼ እንደ ትልቅ ቀመር ቀንሸና ደምሬ ካልሆነ ቀኑ ሰኞ ይሁን ዓርብ አላውቅም፣ የምወዳት ቅዳሜ እንኳን ዞራ ስትመጠ የምሰማው ከሌሎች ነው “ዛሬ ቅዳሜ ነው'' ሲሉ፡፡ እቤት ስንደርስ ቃል የገባሁለትን ቡና ላፈላ ይቅርና አንድ ቃል አላወራሁም፣ መኝታ ቤቴ ገብቼ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ። የማይወዱትን ሰው አግብቶ መኖርና፣ የማይወዱትን ሰው አግብተው እየኖሩ የሚወዱትን መናፈቅ፣ ሌላ ነገር ነው፡፡ ከሁለት መጥፎ አንዱን ምረጭ ብባል፣ የመጀመሪያው ይሻላል፡፡ ምስኪን የአገሬ ልጅ ነው በድህነት ተጠብሶ፣ በስደት በሰው አገር ተንከራቶ፣ ላብና ጉልበቱን ገብሮ፣ እዚህ የደረሰ፤ እንደ ሰው ሚስት አግብቶ፣ ልጅ ወልዶ፣ ከብዶ የመኖር ጤነኛ ምኞት ያለው ምስኪን ወንድ... ምን አጠፋ ምን በደለኝ? ቢያንስ ደፋር ነው፣ ማግባትን አልፈራም፡፡ እኔ ነኝ ራስ ወዳዷ፣ ሳላፈቅረው የማስመስለው... እስኪወጣልኝ ተነፋረቅሁ፡፡ግን ምንም የወጣልኝ ነገር አልነበረም፡፡ ደግሞ ሌላ ሰበብ ዓይኔ አባብጦ ስወጣ “ምነው አለቀሽ እንዴ? ...ይገባኛል እርግዝና ሆርሞኑ ምናምን...''ሰው ለሚወደው ሰው እንዴት ነው እንዲህ ድፍንፍን የሚለው!?

ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍4111🥰2🔥1