አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
‹‹አይ ያማ አይሆንም ..ይሄንን የማደርገው ለአንቺ ብዬ ሳይሆን እራሴ ስለፈለኩ ነው።ጥሩ ነገር ለመስራት ልቤ ሲነሳሳ አንቺ ደግሞ እንቅፋት ስትሆኚብኝ እግዜሩስ ምን ይልሻል?››ይሄንን የመሰለ የታሰበበት ወርቃማ እድል እንዳታበክንብኝ ስለሰጋሁ ቀባጠርኩ፡፡ተሳካልኝና ፈገግ አስባልኳት...ልጇን አቅፋ ከተቀመጠችበት ተነሳችና››እግዜር ይባርክህ...እንዳልከኝ አደርጋለሁ፡፡››ብላኝ እንዳአመጣጧ ሹልክ ብላ  ወጣችና.. በራፉን ዘጋችልኝ።እኔም በረጅሙ የእፎይታ ትንፋሽ ተነፈስኩና በቀጣይ ስለሚሆነው ነገር ማሰብ ጀመርኩ።


ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
21👍17😱3
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ:
እባክሽ አትሂጂ…..
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-ሁለት
///


በሶስተኛው ቀን የሆስፒታሉን ኘሮሰስ ሁሉ ጨርሳ   ባሏን ይዛው ወደቤት ሄደች ።በማግስቱ ከስራ እንደወጣሁ ደወልኩላት።
‹‹ሄሎ ልዕልት ዶ/ር ሳሙኤል ነኝ፡፡››
‹‹አውቄሀለው ዶ/ር ...እንዴት ነህ?››
"ሰላም ነኝ ..ቀጠሮ ነበረን… ለዛ ነው የደወልኩልሽ››
‹‹አዎ ዶክተር.. ስራ በዝቶብህ ምትዘነጋው መስሎኝ ነበር፡፡››
‹‹አይ ፈፅሞ አልዘነጋውም...ያንቺም ጉዳይ ከዋና ስራዎቼ ውስጥ አንዱ  ነው...አሁን ሰፈርሽን ንገሪኝ፡፡››
ደስ በሚል በረጋና ዝም ብሎ ፍስስስ በሚል ድምፅ  የቤቷን አድራሻ በዝርዝር ነገረችኝ...መኪናዬን ወደእዛው አንቀሳቀስኩ…የነገረችኝ ሰፈር እንደተቃረብኩ አንድ ሱፐር ማርኬት ጎራ አልኩና ለትልልቆቹ ልጆቹ ቸኮሌት ለትንሿ ልጅ አሻንጉሊት..ለእናትዬው አዲስ የተቀነጠሰ ትኩስ እንቡጥ ፅጌረዳ አበባ ገዛሁና ጉዞዬን ቀጠልኩ፡፡
እቤቷ አካባቢ ደርሼ ደወልኩላት። ወጥታ ተቀበለችኝ፡፡ መኪናዬን ወደ ጊቢ ውስጥ አስገባሁና አቆምኩ።እቤታቸው ግዙፍ የሚባል የድሮ ቢላ ነው።ጊቢውም ቢያንስ ከ300 ካ.ሜትር በላይ ይሰፋል። ከቢላው ጀርባ አምስት የሚሆኑ  ሰርቢስ ቤቶች ይታዩኛል።ሰው ገባ ወጣ ሰለሚልባቸው ለኪራይ የተዘጋጅ እንደሆነ ገመትኩ።ለልጆቹ የገዛሁትን ቸኮሌትና መጫወቻ አሻንጉሊቱን ከነፔስሉ ይዤ ወረድኩ።በሰላምታ ተቀበለችኝ።አለባበሷ እንደወትሮ ብዙም ያልታሰበበት ቢሆንም ውበቷ ግን ያው እንደተለመደው አስደንጋጭ ነው።
‹‹እንኳን በሰላም መጣህ ዶክተር...ና ግባ፡፡››ብላ ቀድማ ትመራኝ ጀመር..፡፡
በትህትና እየተከተልኳት‹‹እቤታችሁ ግዙፍ ነው..ግቢያችሁም ያምራል አልኳት፡፡››
‹‹ከአያቶቼ የወረስኩት ነው...እነሱ ነበሩ ያሳደጉኝ..አሁን ሁለቱም በህይወት የሉም››አለችኝ፡፡
‹‹አዝናለሁ...ነፍሳቸውን ይማር››አልኳት..በውስጤ እያሰብኩ ያለሁት ግን ጭራሽ ባልሽን በራስሽ የውርስ ቤት እያኖርሽ ነው?ብዬ እያማኋት ነበር፡፡
‹‹አረ ችግር የለም..የቆየ ታሪክ ነው።ግባ ቁጭ በል።››አለች፡፡
ግዙፍ ሳሎን ገብቼ በግራ በኩል ያለው ሶፋ ላይ ልቀመጥ ወይስ በቀኝ ያለው ላይ እያልኩ በመወዛገብ ላይ እያለሁ ሁለቱ ልጆቾ ከውስጠኛው ክፍል እየተሽቀዳደሙ‹‹ዶ/ር መጣ ….ዶ/ር …››እያሉ ሮጠው በመምጣት በግራና በቀኝ ተከፋፍለው ተጠመጠሙብኝ።እኔም እንደጥሩ አጎት ሁለቱንም ግንባራቸውን እያሸሁና ጉንጫቸውን እየሣምኩ አፀፋውን መለስኩ፡፡
‹‹እስቲ ዞር በሉለት ቁጭ ይበል፡፡››ተከላከለችልኝ።ቁጭ ስል በግራና በቀኜ ተቀመጡ...ምን አልባት ይሄ ከልጆቹ ጋር የጀመርኩት መቀራረብ  ትልቅ ውጤታማ እስትራቴጂ ሊሆን ይችላል የሚል ሀሳብ ብልጭ አለልኝ፡፡...በልጆቹ ልብ ውስጥ በጥልቀት ከገባው እዛ ውስጥ የናትዬውንም ልብ ማግኘቴ ስለማይቀር ነገሮችን ያቀልልኝ ይሆናል።
የያዝኩትን ፔስታል ከፈትኩና ሱፐርማርኬት ጎራ በማለት የሸመትኩትን ቸኳሌትና ብስኩት እኩል እኩል አካፈልኳቸው …በደስታ ፈነጠዙ...መጫወቻ አሻንጉሊት አውጥቼ ‹‹ይሄ ደግሞ የሚጡ ነው..የታለች?"
‹‹ተኝታለች፡፡››
‹‹በሉ.. ስትነሳ ስጡልኝ፡፡››
‹‹በሉ አሁን ስጦታቸውን ይዛችሁ ወደክፍላችሁ ሂድ፡፡››እናትዬው ትዕዛዝ አስተላለፈች፡፡
ስጦታቸውን በእቅፋቸው ሰብስበው‹‹ዶ/ር እናመሰግናለን.. ››እያሉ ተከታትለው ወደውስጠኛው ክፍል በመግባት ተሠወሩ።
ከዛ እናትዬው በተቀመጠችበት ትኩረቷን ወደእኔ ሰበሰበችና ‹‹ዶ/ር ለምን እንደዚህ ታደርጋለህ?››ስትል የሀዘኔታ ይሁን የቁጣ ባለየሁት ድምፀት ጠየቀቺኝ፡፡
‹‹ምን አደረኩ..?››
‹‹ይሄ ሁሉ ወጪ..አስፈላጊ አልነበረም እኮ...ለማንኛውም ቡና ላፍላ ወይስ ሻይ?››
‹‹አይ ትኩስ ነገር ላይ እስከዚህም ነኝ.....በቀን አንዴ ብቻ ነው የምጠጣው..››
‹‹ቢራስ...?››
‹‹አይ ካለ ውሀ?››
ወደፍሪጅ ሄደችና አንድ ሊትር የታሸገ ውሀ አምጥታ ፊቴ በማስቀመት ቀድሞ በነበረችበት ቦታ   ተቀመጠች።
‹‹ባለቤትሽ እንዴት ነው?››ጠየቅኳት፡፡
‹‹ያው የተለየ ነገር የለም..አልፎ አልፎ ወደቀልብ እንደመመለስ ይልና መልሶ ደግሞ ጥፍት ይላል።››
‹‹መድሀኒቱስ?››
‹‹መድሀኒቱን ባልከኝ መሰረት እራሴው በሰአቱ እየተከታተልኩ እየሰጠሁት ነው…የተወሰነ ለውጥ እያመጣለት ይመስለኛል፡፡››አለችኝ፡፡
በፈጥረት ታሪክ እንደ ኦክቶፐስ መስዋዕት የምትከፍል ቁርጠኛ የሆነች የእናቶች ተምሳሌት የለችም።አንድ የኦክቶፐስ እናት በአንድ ጊዜ 50 እንቁላል ትጥልና ያለምንም እረፍት ፣ መዘናጋትና እንቅስቃሴ ለ6 ወር ትጠብቃቸዋለች..ከስድስት ወር በኃላ እንቁላሎቹ ሲፈለፈሉ እናት ከጥበቃው ትገላገላለች ።ይሁን እንጂ ለስድስት ወራት ባጋጠማት   መጎዳትና ረሀብ ምክንያት  ህይወቷ ወዲያውኑ  ያልፋል።ይህቺም ፊት ለፊቴ ያለችው ሴት በዚሁ ከቀጠለች በእናትነቷ እና በሚስትነቷ ፍጽም መስዋዕት ሆና ልክ እንደኦክቶፐሷ የመጨረሻ ዕጣዋ መክሰምና መጥፋ እንዳይሆን ፈራለሁ…የእውነት በጣም ፈራለሁ፡፡
እንደምንም ወደ ቀልቤ ተመለስኩና ‹‹አሁን ላየው እችላለሁ?››አልኳት
‹‹ደስ ይለኛል›› ቀድማ ተነሳች፡፡ተከተልኳት፡፡ኮሪደሩን እየሰነጠቅን ብዙ ክፍሎችን  ካለፍን በኃላ አንድ ግዙፍ ክፍል ውስጥ ይዛኝ ገባች።ባልዬው በስርአት በተነጠፈው ግዙፍ አልጋ ላይ ስትር ብሎ ተኝቶል። በቀኝ በኩል ባለ ግድግዳ ላይ የተንጠለጠለ ጉሉኮስ ቱቦ ከክንድ ጋር ተገናኝቷል።ፊቱ ሲታይ ፀጥ ያለ ነው።አይኖቹን እየገላለጥኩና  አንገቱንን እየዳበሰኩ  ተመለከተኩና...‹‹አይ ጥሩ ነው...ዛሬ ዝም ብዬ ሁኔታውን ለማየት ነው የመጣሁት፡፡ነገ ግን መሳሪያ ይዤ መጣና አንዳንድ  ነገሮችን አይቼ  ተጨማሪ መድሀኒትም የሚያስፈልገው ከሆነ አዝለታለሁ።››አልኳት፡፡
‹‹እሺ በቃ ዶ/ር ..በል ና አትቁም፡፡›› አለችና..አይኔ እያየ በድን ሆኖ የተሠተረውን ባሏን ግንባሩን ስማ‹‹የእኔ ጀግና ለእኔ ያድርገው፡፡››በማለት አሁንም ቀድማኝ መኝታ ክፍሉ ለቃ መውጣት ጀመረች ...ተከተልኳት ፡፡ሳሎን ስመለስ የምግብ ጠረጴዛው የቤቱ ሰራተኛ በመሰለችኝ ሴት በምግብ እየተሞላ ነበር።ለመቀመጥ ወደ ሶፋው ስራመድ...‹‹ዶ/ር ወደ ማዕድ ጠረጴዛው ቅረብ››አለችኝ።
‹‹ኸረ ይቅርብኝ››በመሽኮርመም ተግደረደርኩ።
ፍስስ ብሎ ወደውስጥ በሚሰርግ አዚማም ድምፅ‹‹የማይሆነውን...የሚመጥንህ ባይሆንም ያው ለአንተ ብለን የፍቅራችንን ነው የዘጋጀነው።››አለችኝ፡፡
‹‹የፍቅራችንን ›› የምትለዋን ቃል ስሰማ ተንደርድሬ መቀመጫ ያዝኩ።የእጅ ውሀ በተቀመጥኩበት መጣልኝ..ጣፍጦኝ በላሁ።መአድ ተነሳ፡፡ ወደሶፋው ተመልሰን ፊት ለፊት ተቀመጥን።
‹‹ቆንጆ እራት ነበረ ፣አመሠግናለሁ ››አልኳት።
‹‹ስለወደድከው ደስ ብሎኛል...አብዛኛው ግን የሠራተኛዬ ሞያ ነው፡፡››
‹‹እንግዲያው ይህቺን ሰራተኛ እንዳላስኮበልልብሽ ተጠንቀቂ፡፡››አልኳት
‹‹ውይ እንደዛማ አይሆንም..ባይሆን ምግቧን  ሲያምርህ እዚሁ እየመጣህ ብትበላ ይሻላኛል።››
‹‹የወር አስቤዛህን ጭነህ አምጣ እያልሺኝ ነው?››
👍598👎1
ከት ብላ ሳቀች...እንደ እናት ሳይሆን እንደሴት ነው የሳቀችው..እንደሴት መሳቅ ግን እንዴት ነው?
‹‹አይ አስቤዛው እንኳን ከቤቱ ነው፡፡››
‹‹በኃላ ከሰርኩ እንዳትሉ››
‹‹ግድ የለህም...ይልቅ ወደቁም ነገሩ እንመለስ?ምን ያህል ነው ምታስከፍለኝ?››አለችኝ..ፍፁም ያልጠበቅኩት ጥያቄ ነው፡፡ደነገጥኩ...፡፡ምን ለማለት እንደፈለገችም አልገባኝም።
‹‹ለምኑ ነው የምትከፍይኝ?››
‹‹ያው  ተመላልሰህ ለምታይልኝ ነዋ..ጊዜህ አለ…. የመኪና ነዳጅ አለ››ዘረዘረችልኝ፡፡

‹‹እ እሱን ነው...ያው ብዙውን ጊዜ ምመጣው ማታ ከስራ መልስ ነው..እናም በመጣሁ ቁጥር የቅድሙን አይነት እራት እፈልጋለሁ፡፡››
‹‹አትቀልድ ዶ/ር፡፡››
‹‹የቀለድሽው አንቺ ነሽ...እኔ ከአንቺ ክፍያ ምቀበል ከሆነ ከሆስፒታል እንድትወጪ ማድረጌ ምንድነው ጥቅሙ..?እዛው አስተኝተሽ ብትከፍይ አይሻልሽም ነበር?››
‹‹ምን ነካህ ዶ/ር… እቤት በመሆኑ እኮ መአት ነገር ነው የማተርፈው..ቢያንስ ቢያንስ እሱንም ልጆቼንም በተሻለ መንከባከብ እችላለሁ።እና ለአንተ የሚገባህን ከፍዬም ብዙ ነገር አተርፋለሁ፡፡"
ከመቀመጫዬ ተነሳሁ...‹‹በይ አሁን ሸኚኝ...ክፍያ ምትይ ከሆነ ሌላ ሰው መፈለግ ይኖርብሻል…ለእኔ ክፍያ መክፈል ሎጂካል አይደለም››አልኳት..በፈጣሪ አሁን ልክ ያልሆነው እሷ ለእኔ የአገልግሎት ክፍያ መክፈል ነው ወይስ እኔ ከመሬት ተነስቼ በነጻ ካለገለገልኩሽ ማለቴ ነው?
‹‹አስጨነቅከኝ እኮ››
‹‹በቃ እንደወንድምሽ እይኝ...የቤተሠብ አንድ አካል እንደሆንኩ ቁጠሪ...ወይም ደግሞ ጥሩ የድሮ ጓደኛሽ እንደሆንኩ ..ብቻ እንደተመቸሽ ..ግን ልክፈልህ አትበይኝ፡፡››
በዚህን ጊዜ መኪናዬ ጋር ደርሼ ነበር..ከፍቼ ስገባ ወደበሩ ተጓዘችና ከፈተችልኝ። አንቀሳቀስኩና  ከግቢው ወጥቼ ቆምኩ ፡፡መጣችና አጎንብሳ በተከፈተው መስኮት አንገቷን አስግጋ...በፍፅም ፈገግታና በፍፁም ትህትና‹‹በጣም አመሠግናለሁ...ደህና እደር፡፡››አለችኝ፡፡
ተንጠራርተህ የሚንቀሳቀሱ ከንፈሮቾ ላይ ተጣበቅባቸው የሚል ስሜት ተናነቀኝ...እንደምንም እራሴን ተቆጣጥሬ  ‹‹ደህና እደሪልኝ …እነሚጣን ቸው አላልኳቸውም… ሳሚልኝ፡፡››
‹‹እሺ እስምልሀው፡፡››ብላ ቀና አለችና ከመኪናዋ ሁለት እርምጃ ወደኃላ ሸሸት በማለት ቆመች...ሌላ ነገር ቀባጥሬ ሳልዋረድ ብዬ ሞተሩን አስነሳሁና ተንቀሳቀስኩ….  በእስፖኪዬ እያየኋት ነው፡፡ በቆመችበት በፋዘት ሆና ሸኘችኝ...እኔ ደግሞ መላ እሷነቷን በልቤ ተሸክሜ ተሸበለልኩ።ለእሷ ለመስጠት የገዛውት እንቡጥ ፅጌረዳ አበባ አሁንም ኃላ ወንበር እንደተቀመጠ ነው፡፡ምን ብዬ በምን ድፍረት ልሰጣት ነበር የገዛሁት?ማሰቤ እራሱ በጣም አሳፈረኝ።

ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍404
#ትንግርት


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ትንግርት ያታሰረችበት ክፍል ሌሎች አራት ሴቶቸ አብረዋት ታስረዋል፡፡አንድ የ18 ዓመት ወጣት ...ሁለቱ ከ25-30 የሚገመት ዕድሜ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡ከሁለቱ አንደኛዋ ቀጫጫ ቢጤ ስትሆን ስትታይ የቢሮ ሰራተኛ ነገር ትመስላለች.. ሌላኛዋ ግን ደልደል ያለች የተንጨፈረረ ፀጉር ያላት ወንዳወንድ ነገር ነች …አራተኛዋ 4ዐ ዓመት የሚጠጋት ገዘፍ ያለች ሴትዬ ነች፡፡ከእሷና ከልጅ እግሯ ወጣት በስተቀር ሌሎቹ እስር ሲታሰሩ ዛሬ የመጀመሪያቸው እንዳልሆነ ከሁኔታቸው መገንዘብ ይቻላል፡፡

‹‹አቦ አትቆዝሙብን ...እስቲ ወሬ አምጡ ..እናውራ፡፡ ካለዛ የእስር ቤት ተባዬች ደማችንን ሲመጡን በዝምታ ምናዳምጣቸው ከሆነ ስቃዩ ከፍተኛ ነው ሚሆንብን..፡፡ወሬ ግን ማደንዘዣ ነው ..ቀልባችን ወደ ወሬው ከላክን እነሱ ደማችንን ብቻ ነው ሚመጡት፡፡ ካለዛ
ደማችንንም ቀልባቸንንም ምጥጥ ነው የሚያደርጉት፡፡›› ቀጫጫዋ ወጣት ተናገረች

‹‹ተስማምተናል..…እስቲ ከተማሪዋ እንጀምር ..ምን አጥፍተሸ ታሰርሽ?››

‹‹ምንም?›› አለች ፈራ ተባ እያለች፡፡

‹‹ባክሽ አትሽኮርመሚ.. ዝምብለውማ አምጥተው እዚህ አያጉሩሽም... የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነሽ አይደል?››ትልቋ ሴትዬ ጠየቀቻት፡፡

‹‹አዎ... ዋናው ግቢ ነው የምማረው..የሶስተኛ አመት ተማሪ ነኝ፡፡››

‹‹የየት ሀገር ልጅ ነሽ…?››

‹‹የደብረማርቆስ፡፡››

‹‹እሺ ምን ሰርተሸ ታሰርሽ?››

‹‹ፖሊሶቹ ጭፈራ ቤት ለሊት ይዘውኝ፡፡››

‹‹አቦ አትፎግሪ.…ፋራ አረግሺን እንዴ ?››አለቻት ወንዳወንዷ ወጣት፡፡

‹‹እሱማ ዕቃ ይዘውብኝ ነው ፡፡››

‹‹የምን ዕቃ?››

‹‹ሀሽሽ ሚሉትን ዕፅ….፡፡››

‹‹ሀሽሽ !!አይ የዘንድሮ ተማሪ ስትጦዢ ይዘውሽ ነዋ?››

‹‹ወላዲቷን እኔ ነክቼውም አላውቅ ..፡፡ጓደኞቼ ናቸው ቦርሳሽ ውስጥ አስቀምጪልን ፤ የስጦታ ዕቃ ነው አሉኝ፤እውነት መስሎኝ እሺ አልኳቸው፤ከዛ ስንዝናና ስንጠጣ ቆይተን ከሰከርን በኋላ ወደ ጓሮ ይዘውኝ ሄደው ቦርሳዬን ተቀብለው ከውስጡ ያስቀመጡትን ቆንጥረው ወስደው የተቀረውን እዛው በመመለስ የራሴኑ ቦርሳ ለእኔው ካስያዙኝ በኃላ እነሱ እየተቀባበሉ ሲያጬሱ በስካር መንፈስ ናውዤ ቢሆንም በድርጊታቸው ግራ ገብቶኝ ስገረምባቸው ድንገት ከየት እንደፈለቁ
ያላወቅናቸው ፖሊሶች መጥተው ከበቡን..ከዛም አፈሱንና ሲፈትሹን እነሱ ምንም አልተገኘባቸው እኔ ቦርሳ ውስጥ ግን ተገኘ‹‹ካመጣሽበት ጠቁሚ፡፡ ››ተብዬ ይሄው ታስሬያለሁ፡፡

‹‹እና ጓደኞችሽ ምን አሉ?››ትንግርት ጠየቀቻት፡፡

‹‹እንጃላቸው...ምናቀው ነገር የለም መሰለኝ ያሉት..ለዛም መሰለኝ የለቀቋቸው፡፡››

‹‹ታዲያ ምን ይሻልሻል?››

‹‹እንጃልኝ…እቤተሰቦቼ ከሰሙ በቃ ማጣፊያዬ ነው የሚያጥርብኝ... አባቴ ቀጥታ ይገድለኛል..፡፡››

‹‹ቆይ ያልገባኝ ፖሊሶቹ በዛ ሰዓት እንዴት ሊገኙ ቻሉ?›› ትንግርት ነች ግልፅ ስላልሆነላት የጠየቀችው፡፡

‹‹እሱማ ከመካከላችን ሜሪ የሚሏት የዱከም ልጅ በጣም የሚወዳትን ተማሪ ፍቅረኛዋን ችላ ብላ ትልቅ ሀብታም ሰውዬ ጋር ነበር ስትጨፍር ያመሸችው.. ልጁ መጥቶ አብራው ወደ ካምፓስ እንድትመለስ ሲለምናት ነበር..እሷ ግን አልሰማህም ነፍስያዬን ማስደሰት እፈልጋለሁ አለችው፤እያለቀሰና እየፎከረ ነበር ጥሏት የሄደው.....እሱ ይመስለኛል ለፖሊሶች የጠቆመው፡፡››

‹‹እናንተ ፖሊስ እጅ ስትወድቁ ሰውዬው አብሮችሁ ነበር?››

‹‹ነበር ግን ፖሊሶቹ ምንም አላሉትም አልፈተሸትምም..የሚያውት መሰለኝ… ሳስበው ሳስበው ዕፁን እራሱ ለእነሚሪ ያመጣላቸው እሱ ይመስለኛል፡››

‹‹በይ ነገ ይሄንን ሁሉ ለፖሊሶቹ በዝርዝር ንገሪያቸው..ሀሽሽ አለመጠቀምሽንም በምርመራ ማረጋገጥ የሚችሉ ይመስለኛል፡፡››
‹‹እስቲ እግዜር ቢረዳኝ እሞክራለሁ፡፡››ብላ መነፍረቅ ጀመረች፡ሁሉም አባበሏት..ስትረጋጋ ቀጣዩን ባለታሪክ ለማዳመጥ ተዘጋጁ፡፡ቀጣዪ ባለተራ በዕድሜ ከሁሉም አንጋፋ የሆነችው ሴትዬ ነበረች‹‹እሺ ያንቺስ ታሪክ?›› ቀጫጫዋ መጠየቅ ጀመረች፡፡

‹‹የእኔ እንኳን ከበድ ይላል..ከሁለት እስከ አምስት ዓመት ተፈርዶብኝ ወደ ወህኒ መውረዴ አይቀርም፡፡››

‹‹እንዴ !!!እራስሽ ወንጀለኛ እራስሽ ዳኛ ሆነሽ አረፍሺው ?ለማንኛውም እስኪ እንስማው?››

‹‹የባሌን እንትን የማስወገድ ሙከራ አድርጌ ነው፡፡››

‹‹እንትን ምንድነው?››ነገሩ ግራ ገብቷት ጣልቃ በመግባት ሳታስበው ጥያቄ የሰነዘረችው ትንግርት ነበረች፡፡

<< የሚመጠጠው ጀላቲ››አሾፈችባት ወንዳወንዷ፡፡

‹‹አልገባኝም?››

‹‹ባክሽ ሽሮ መብያውን ማለቷ ነው?››ቀጫጫዋ እስረኛ አስረዳቻት፡፡

‹‹በስመአብ ...!!!የባልሽን?››ተማሪዋ ጠየቀች... ሰቅጥጧት፡፡

ትንግርትም...የሴትዬዋ ጭካኔ አንዘርዝሯት‹‹ምነው አንደኛውኑ ብትገይው?››አለቻት፡፡
‹‹ጠላትን ለመበቀል ግድያ የመጨረሻው ቀሺሙ ዘዴ ነው?››መለሰች፡፡

‹‹እንዴት?››ግራ ገብቷት፡፡

‹‹ገደልኩት ማለት እኮ ገላገልኩት ማለት ነው ፤ከሞት በኃላ ፀፀት የለ.... መከራ የለ….ምን ይቀርበታል፡፡ ስለፅድቅና ኩነኔው እንደሆነ ማን እርግጠኛ መሆን ይችላል፡፡እንደውም እኔ ነኝ መከራውን የምቀበለው..እሱን የሰላም ዕንቅልፉ ወደሚያገኝበት ስፍራ ሸኝቼ እራሴን

ለዕድሜ ልክ የእስር ስቃይ አሳልፌ ሰጣለሁ..?ምን በወጣኝ፡፡እኔም እሰቃያለሁ እሱም በቁሙ እየኖረ ይሰቃይ...>>
‹‹ሰማንሽ ...እስቲ ያረግሺውን በዝርዝር አስረጂን?››

‹‹ባሌ ቀለም ቀቢ ነበረ፡፡ ከዛሬ ሁለት አመት
በፊት አንድ ፎቅ ሲቀባ ከሁለተኛ ፎቅ ላይ
መሰላል አንሸራቶት ይፈጠፈጥና የቀኝ እግሩ
ስብርብሩ ይወጣል ይታያችሁ.. እኔ እና ታናሽ
እህቴ በኪራይ ቤት እሱ በሚያመጣው ገቢ
ነበር የምንተዳደረው፡፡እሱ ስብርብሩ ወጥቶ
ቤት ሲቀር የሆነ ነገር ማድረግ የሚጠበቀው
ከእኔ ነው፡፡እራሳችንን መቀለብ ብቻ ሳይሆን
እሱንም አሳክሞ ማዳን የእኔ ኃላፊነት ስለነበር መጣር ጀመርኩ፤ብዙ ነገር ለመስራት ሞከርኩ… ሰው ቤት ፅዳት..ቀን ስራ
ያልሞከርኩት ነገር የለም ፡፡ግን ሁሉም ከልፋት
በስተቀር ለቤተሰቡ የሚበቃ ጠብ የሚል ገንዘብ ሊያስገኝልኝ አልቻለም፡፡ቀለባችንን ችዬ የቤት ኪራይ ከፍዬ ከዛ ተርፎኝ እሱን
ለማሳከም አቅም አነሰኝ…እግሩ ከህክምና እጦት የተነሳ የተነፋፋ ቆሰለ ..ትል ሁሉ ማፍራት ጀመረ፤ምን ላድርግ ?ተሳቀቅኩ፡፡ ሲቸግረኝ ሌላ ዘዴ ቀየስኩ፡፡››

‹‹ምን ዓይነት ዘዴ?››

‹‹የለሊት ስራ ... ፋብሪካ ውስጥ አገኘሁ ብዬ አስወራሁ?››

‹‹ሳታገኚ?››

‹‹ስራውንማ አግኝቼያሁ ...ግን ፋብሪካ ውስጥ አልነበረም፤ ሽርሙጥና ነበር ለመስራት የወሰንኩት፡፡››

ቀጫጫዋ በገረሜታ‹‹ባል እያለሽ?››አለቻት ፡፡

‹‹ባሌማ እኮ ….ዓይኔ እያየ የተሰባበረ እግሩ ከህክምና እጦት የተነሳ መትላት ጀመረ፤ምንበላው አጣን፣የቤት ኪራይ መክፈል አቃተን፣እህቴም ትምህርቷን ልታቋርጥ ጫፍ ደረሰች..እና ምን እንዳደርግ ትጠብቂያለሽ…?

አንዳንዴ ይህቺ አስቀያሚ ህይወት ሁሉንም በራፎች ትከረችምብሽና አዋራጅ እና አስቀያሚ የሆነውን ጭላንጭል የዕድል ቀዳዳ ብቻ ትተውልሻለች፡፡››
‹‹እሺ ቀጥይ ባክሽ፡፡››አለቻት ትንግርት ታሪኳ አጓጉቷት፡፡
👍619👏1😢1
‹‹ከዛ ለሊት ሽርሙጥናዬን እየሰራው ለአንድ አመት ቤቱን ለብቻዬ አስተዳደርኩ፡፡ ባሌንም ከአንድ አመት አስቸጋሪ ህክምና በኃላ እራሱን ችሎ ቆሞ መሄድ ጀመረ፤ትንሽ ሸንከል ቢልም ዳነ ፤ስራ መሞካከር ጀመረ፡፡.እኔም ቀስ በቀስ ሽርሙጥናውን አቆምኩ፡፡በዚህ ጊዜ ሁኔታዎች የተስተካከሉ ሲመስሉ ሌላ ችግር ተከሰተ… እህቴ አረገዘች…፡።

ስጠይቃት ካንድ የትምህርት ቤት ጓደኛዋ ከሆነ ጎረምሳ እንደሆነ እና አሁን ጥሏት እንደጠፋ አረዳቺኝ..፡፡ምን ላድርግ ብቸኛ እህቴ ነች..የእናት እና አባቴ አደራ ነች..አንጀቴ ቢቃጠልም ቻልኩት ፤ጭራሽ እሷን አፅናና
አባብል ጀመር፤ምክንያቱም በብስጭት እራሷ ላይ የሆነ እርምጃ ትወስድና ጉድ ታደርገኛለች ብዬ ሰለሰጋሁ፡፡..በዛ ላይ እኔ ልጅ የለኝም ፡፡ ከዚህ ባለቤቴ ጋር እንኳን ባሳለፍናቸው 5 የትዳር አመታት ልጅ ልወልድለት አልቻልኩም ፡፡መሀን ሳልሆን አልቀርም..ታዲያ እግዚያብሄር በእህቴ በኩል ልጅ ሊሰጠኝ ፈልጐ እንደሆነ ብዬ ሁሉንም በፀጋ ተቀብዬ የመውለጃ ቀኗን በጉጉት እየጠበቅኩ ሳለው ከሶስት ቀን በፊት ጉዴን ሰማሁ፡፡››

‹‹እንዴት?››

<<የሆነ የጓደኛዬ አባት ሞቶ ስለነበር አዳር ብዬ ባለቤቴንም እርጉዟን እህቴንም ተሰናቼ ከቤት ወጣሁ፤ለቅሶ ቤት ስደርስ ግን ጠጠር መጣያ አልነበርም..ድንኳኑ በሰው ተጨናንቋል፡፡በኃላ ሀሳቤን ለወጥኩና አስከ 5 ሰዓት ብቻ አመሻሽቼ ወደ ቤት ተመለስኩ፡፡ስደርስ መብራቱ እንደበራ ነው..ወደ በራፉ ተጠጋሁ… የባሌ እና የታናሽ እህቴ ተንከትካች ድምፅ በጆሮዬ ተሰነቀረ፡፡

‹‹እንዴት እስከ እዚህ ሰዓት ድረስ ሳይተኙ?››በአዕምሮዬ የተሰራጨ ጥያቄ ነበር፡፡ የሆነ ነገር ሸከከኝና ላንኳኳ የዘረጋሁትን እጄን አንከርፍፌ ጆሮዬን አስቀደምኩ፡፡

‹‹የእኔ ቆንጆ ልጃችን መቼ ነው የሚወለደው?››የባሌ ድምፅ ነው፡፡

‹‹አይዞህ ዓይንህን በዓይንህ ለማየት አንድ ወር ብቻ ነው መጠበቅ የሚገባህ፡››

‹‹አቤት አንቺ እኮ ነፍስ ነሽ ....እህትሽ በ5 ዓመት ያልሰጠችኝን ፀጋ አንቺ በአንድ አመት ፍቅር አሻርሺኝ፡፡››ሲላት ሰማሁ፡፡

‹‹አንተ እኮ አሳሳች ሴይጣን ነህ ..እህቴ ላይ ግፍ እንድሰራባት አደረግከኝ፡፡››በ15 ዓመት የምታንሰኝ የታናሽ እህቴ ድምፅ ነው፡፡

‹‹ምን ግፍ አለው… ?ድንገት ተፋቀርን በቃ፡፡››

‹‹በመጀመሪያማ ተፋቅረን አይደለም...ምነው እረሳኸው እንዴ..? የጀመርነው አስገድደህ
ደፍረኸኝ ነው፡፡››አለችው፡፡

‹‹ከዛ በኃላ ግን ፈልገሽ ነው?››

‹‹እሱማ ስትደጋግመው ጣመኝ ምን ላድርግ..?እህቴ ብታሳዝነኝም... ማቆም ግን አልቻልኩም፡፡››

‹‹እንደእኔ እንደኔማ ብንጋባ ሁሉ ደስ ይለኛል..አሁን እኮ እንደምታይው ድኜያለሁ ስራም ጀምሬያለሁ፡፡ የእህትሽ እርዳታ አያስፈልገንም..እውነቱን እንንገራት እና የራሳችንን ህይወት እንቀጥል፡፡››ሲላት ቀጥታ በጆሮዎቼ ሰማሁ ፤.መቼስ ጆሮ ማይሰማው የለም፡፡

‹‹ያንንማ…..ፍፅም አታስብ፡፡ ልጅህን እወልድልሀለው… ሶሰት ወር አጠባልሀለው፤ ከዛ ለአንተ እና ለእህቴ አስረክቤ አገር ጥዬ ጠፋለሁ…፡፡ለእህቴ ከዚህ በላይ ክህደት አይገባትም፤ደግሞ እወቅ እህቴም ብቻ ሳትሆን እናቴም ነች፡፡››
በወቅቱ ከዛ በላይ መስማት አቅሙ አልነበረኝም..ወደ ኋላዬ ተመለስኩ…ድሮ ወደ ምሰራበት ሆቴል በመሄድ ስጠጣ አንግቼ እዛው ውዬ ሲመሽ ወደቤት መጣሁ፡፡ሁለቱም የት እንደቆየሁ ቢጠይቁኝም የረባ መልስ አልመለስኩላቸውም፡፡

ከዛ እህቴን ምክንያት ፈጥሬ አንድ ጓደኛዬ ጋር ሄዳ እንድትድር አደረግኩ፤ሥጋ ገዝቼ ችክን ያለች ወጥ ሰራሁና ቆንጆ እራት አበለሁት፡፡ አረቄም ገዝቼ ነበር ...በላይ በላዩ እንዲጠጣ አስገደድኩት፡፡ ሰውነቴን ታጠቤ ሽቶ በላዬ አርከፍክፌ ወደመኝታ ይዤው ሄድኩ፤ልክ እንደተገናኘን ጊዜ እንደነበረው እስኪያለከልክ ድረስ ሰጠሁት..ምክንያቱም የመጨረሻው ስለሆነ ይገባዋል ብዬ ነው እንደዛ ያደረግኩት፡፡ ከዛ በወሲብም በስካርም ተዝለፍለፎ ሲዘረርልኝ...ስዬና ሞርጄ ባዘጋጀሁት ቢላዋ ያንን የቅንዝሩን መሳሪያ ገዘገዝኩለት፡፡››

‹‹ግን ቁርጥ ቁርጥ አደረግሺው?››

‹‹አይ ግማሽ እንደደረስኩ ሆዴ ባባ መሰለኝ ተውኩት..ምንም ቢሆን የበላ አንጀት ሆኖብኝ መሰለኝ፡፡››

‹‹ታዲያ አሁን እንዴት ሆነ?››

‹‹ምን አውቃለሁ በወቅቱ ጮኸ ..አጓራ ..ወሬኛ ጐረቤቶች ተሰበሰቡ እና እሱን ወደ ሀኪም ቤት እኔን ወደእዚህ አምጥተው ወረወሩኝ…..ግን ሙሉ በሙሉ ስላልተለያየ ሊመልሱለት እየሞከሩ ነው አሉ፡፡››

‹‹እንዲህ በማድረግሽ ግን ተበቅዬዋለሁ ብለሽ ታስቢያለሽ?››ትንግርት ጠየቀቻት፡፡

‹‹መቼስ ከመግደል ይሻላል..ማለቴ ብገድለው በቃ ተገላገለ..አሁን ግን የእንትኑን ጠባሳ ወይም ከዛ እየተነሳ የሚጠዘጥዘውን የህመም ስሜት በተሰማው ቁጥር በእኔ ላይ የሰራውም ግፍ አብሮ ይታሰበዋል..ቅጣቱ ለአመታት ህሊናው ሲቆጠቁጠው ይኖራል፡፡ >>
‹‹እኔ ግን እንደዛ አይነት በቀል ውጤታማ አይመስለኝም >>አለች ቀጫጫዋ እስረኛ፡፡

‹‹ታዲያ ንገሪና..… አንቺ ብትሆኚ ምን ታርጊያለሽ?››ወንዳወንዷ ጠየቀቻት፡፡

‹‹እህቴን ከባሌ ጋር አጋባና እኔ ከመካከላቸው እወጣለሁ...ያ ሁለቱንም ከፍተኛ ፀፀት ላይ የሚጥል...ከስህተታቸው እንዲማሩ እና እንዲለወጡ..ቀሪ ህይወታቸውን መልካም ሰው እንዲሆኑ የሚያደርግ እርምጃ ይመስለኛል፡፡አሁን አንቺ ባልሽንም እህትሽንም አጥተሸ እስር ቤት ገባሽ…ባልሽ ዕቃውንም አንቺንም አጣ..እህትሽም እንደዛው ሁለታችሁንም አጣች….አየሽ እነሱ አንድ ስህተት አንቺ ላይ ሰሩ ...አንቺ ደግሞ ሁሉንም ነገር ድብቅልቅ የሚያደርግ አውዳሚ ስህተት ሰራሽ፡፡

ባልሽ ከአሁን ወዲህ መዳን ቢችል እንኳን ጠቅላላ ሴቶች ላይ ምን አይነት ጥላቻ እንደሚያድርበት አስበሽዋል.?.እንኳን እሱ
ቀጥታ ተጠቂው ይቅርና ይህንን ታሪክ የሰማ የአዳም ልጅ ጠቅላላ እንዴት የሴትን ጭካኔ እንደሚያራግብበት አስቢው፡፡እንደእኔ ምልከታ በደል አድርሶብናል ብለን የምናስበውን ሰው በመግደል ወይም እሱና የእሱ የሆኑትን ነገሮች ላይ ጉዳት በማድረስ መበቀል ቀሺምና እርካታ የሌለው ወይም ጥም የማይቆርጥ በቀል ነው፡፡››

‹‹እስቲ እንደአንቺ ጥም ሚቆርጠው በቀል ምን አይነት ነው?››ትንግርት ነች የልጅቷን ፍልስፍና ይበልጥ ለመረዳት የጠየቀቻት፡፡
‹‹እንድሞት አስባ ምግቤን የመረዘችብኝን ጎረቤቴን ..አንድ ቀን ቀን ጥሏት ታማ በህይወት እና በሞት መካከል ወድቃ ባገኘኋት ጊዜ ወደ ህይወት የሚመልሳትን የመጨረሻውን ፈዋሽ መድሀኒት ባለኝ ጥሪት ሁሉ ገዝቼ በመስጠት እንድትድን በማድረግ ነው ልበቀላት የምፈልገው፡፡እንደዛ አይነት በቀል ነው የእኔን ጥም የሚቆርጥልኝ፤ከበዳዬ በልጬ በመገኘት..፡፡››

ሁሉም ፀጥ አለ፡፡ ትንግርትም እሷ በደለችኝ.. ከዳችኝ የምትላት ዶ/ር ሶፊያ ላይ የወሰደችውንና ለመውሰድ ያሰበችውን የበቀል መንገድ ዳግም መከለስ እንዳለባት በድንገት ከእስርቤት ጓደኞቿ በዚህች ጠባብ ክፍል በዚህ ጨለማ ውስጥ የሰማችውን ታሪክ ለአዕምሮዋ መልእክት አስተላለፈላት፡፡‹‹መማር ለፈለገ ለካ ሲዖል ውስጥም ቢሆን ዕውቀት ይገኛል››በማለት አሰበች…፡፡
‹የተቀራችሁትን ታሪክ ነገ እንደበርበታለን… አሁን እንተኛ›› ተባባሉ፡፡ሁሉም በያሉበት አዕምሮአቸውን በሀሳብ ሰውነታቸው በተባዬቹ እየተቦጠቦጠ ቢሆንም ለእንቅልፍ ተመቻቹ፡፡

ይቀጥላል

ቤተሰቦች አረ #subscribe እያደረጋቹ 5 ሰው ብዬ 3ሰው አድርጎ ቆመ እስቲ አሁንም #subscribe እያደረጋቹ

#Share and #subscribe my #YouTube 
👍10117👏3🔥1😁1
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👏14👍1👎1
አትሮኖስ pinned «#ትንግርት ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_ስድስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ትንግርት ያታሰረችበት ክፍል ሌሎች አራት ሴቶቸ አብረዋት ታስረዋል፡፡አንድ የ18 ዓመት ወጣት ...ሁለቱ ከ25-30 የሚገመት ዕድሜ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡ከሁለቱ አንደኛዋ ቀጫጫ ቢጤ ስትሆን ስትታይ የቢሮ ሰራተኛ ነገር ትመስላለች.. ሌላኛዋ ግን ደልደል ያለች የተንጨፈረረ ፀጉር ያላት ወንዳወንድ ነገር ነች …አራተኛዋ 4ዐ ዓመት የሚጠጋት…»
እባክሽ አትሂጂ…..
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-ሶስት

ዋና ስራዬ ስለእሷ ማሰብ ሆነ።ከብዙ ድካም በኃላ ማታ አልጋዬ ላይ ተንጋልዬ በእንቅልፍ እጦት እየተንከባለልኩ  አዲስ አይነት ሰይጣናዊ ሀሳቦች ማሰብ ሁሉ ጀመርኩ።‹‹ሰውዬው ማለት ባሏ ምን አለ ቢሞት፡፡ሞት ማለት…በህይወት ለቆየንባቸው ለእያንዳንዷ ቀን የምንከፍለው ውዝፍ ዕዳ ነው፤ታዲያ እሱስ ብዙ ወለድ ሳይወልድበት ምን አለ ብድሩን አሁኑኑ ቢከፍልና ከህይወትም ከእኔ ፊትም ገለል ቢል?››አሁን እስኪ ከእንደእኔ አይነት ሰውን ለማዳን አመታትን ለፍቶ ከተማረ እና መሀላ ገብቶ ወደስራ ከተሠማራ ዶ/ር የሠውን ሞት ለዛውም እራሱ የሚያክመውን ሰው ሞት መመኘት  የጤንነት ነው?።እርግጥ ሰውዬው ይዋል ይደር እንጂ የመሞት  እድሉ ከሰማንያ ፐርሰንት ዘለግ ያለ ነው።  (ይሄ አባባል  ትክክል አይደለም ፤ለመዳን ያለው ተስፋ 20 ፐርሰንት ነው ተብሎ ቢገለፅ ይሻላል)ምክንያቱም የማንኛውም ሰው የእኔንም ጨምሮ የመሞት እድላችን መቶ ፐርሰንት ነው...ታመምንም አልታመምንም እውነታው ይሄ ነው...ከእሱ ቀድሜ እኔም ልሞት እችላለሁ፡፡ ለማንኛውም ወደ ታማሚው ስመለስ መቼ ነው ሊሞት የሚችለው ?የዛሬ አመት ?የዛሬ ሁለት አመት...?በሁኔታዋች ላይ የሚወሰን ነው?እና እኔ ያን ሁሉ ለመጠበቅ የሚያስችል ትእግስት አለኝ?አይመስለኝም።ከሞተ በኃላስ እሷን የራሴ ለማድረግ ያለኝ እድል ምን ያህል ነው?ምንም ብርሀን አይታየኝ አይደለም ፡፡ቢሆንም ግን ተስፋ የመቁረጥ ምንም አይነት ሀሰብ የለኝም።ሀሳቤን ሳልጨርስ ስልኬ አንቃጨለ  ...በዚህ ሰዓት ማን ነው? ተንጠራራሁና አየሁት...የውጭ ቁጥር ነው። እየተጠራጠርኩ አነሳሁት...፡፡
‹‹አንተ ሰውዬ ለመሆኑ በህይወት አለህ?››
ተንዘርዛሪ ቃጭል ድምፅ...አልተሳሳትኩም እርግበ ነች።እርግበ ማለት የረጅም ጊዜ ጓደኛዬና የሶስት አመት ፍቅረኛዬ የነበረች ሴት ነች።የተዋወቅነው ሁለታችንም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምና ለማጥናት እንደተመደብን ፍሬሽማን ላይ ሆነን ነበር...ለመመረቅ አንድ አመት ሲቀረን ጀምሮ የጠበቀ የጓደኝነት ቀረቤታችንን ወደ ፍቅር ለወጥነው ።አራት አመት በስራ ካሳለፍን በኃላ እኔ አዲስአበባ ሁለተኛ ዲግሪዬን መስራት ስጀምር እሷ ደግሞ የውጭ እድል አግኝታ ሁለተኛ ዲግሪዋን በስነ-ልቦና ልትሰራ ኖሮዌይ ሄደች።እርግጥ ለእኔም ችምር በራሷ ጥረት ተሯሩጣና ተፃፅፋ አብሬያት በመሄድ ውጭ የምማርበትን እድል አመቻችታልኝ ነበር፡፡እኔ ግን ግግም አልኩባት፡፡‹‹እናቴንና አሀገሬን ጥዬ አልሄድም፡፡››የሚል አቋም ያዝኩ፡፡ብትለምነኝ ብታስለምነኝ እሺ አላልኩም፡፡ከዛ የራስህ ጉዳይ ብላ በከፊል ኩርፊያና በከፊል ንዴት ጥላኝ ሄደች፡፡ትምህርቷን እየተማረች ባለችባቸው ለሁለት አመታት ግንኙነታችን በስልክና በቪዲዬ ኮል ቢሆንም   በተስፋ የተሞላና በናፍቆት የታጠረ ነበር፡፡ከተመረቀች በኃላ በገዛ ውሳኔዋ ቆይታዋን ስታራዝም ግን ጭቅጭቆች በመሀከላችን መፈጠረ ጀመሩ...እዛ ካሉ አንዳንድ ጓደኞቼም የምሰማቸው ወሬዋች በወደፊታችን ተስፋ እንዳደርግ የሚያበረታቱ ሆነው አላገኘኋቸውም እና ቀስ በቀስ መደዋወሉን እየቀነስን በቆይታ ማለት ከስድስት ወር በፊት ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በማቋረጥ ከስልኬ ውስጥ ሲሜን አውጥቼ ጣልኩና አዲስ ቁጥር ያዝኩ።
እርግበ ኑግ ታውቃላችሁ? ልክ እንደዛ ወዙ ችፍ ያለ እንደውም  እስፕረይ የተነፋበት የሚመስል የሚያብረቀርቅ አይነት ወዛም መልክ፣  ከዋክብት  የመሰሉ ግዙፍና ጉልህ ተንከባላይ አይኖች ያሏት እንቁላል መሠል ኦቨል የፊት ቅርፅ ከእሱ ጋር በሚቃረን መልኩ ቀጭን ቅንጥስ የምትል የሚመስል ሰንደቅ መሳይ  ቁመት ያላት  ወጣት ነች።የእኔ ብቻ ሳይሆን የብዙ ወንዶች ምኞት ናት።ግን የተረጋጋ መንፈስ የላትም።ሁሌ ተቅበዝባዠና እራሷ ተሸብራ ሌላውን የምታሸብር አይነት ነች።ሁሉንም ነገር በአንዴ የራሷ ለማድረግ የምትጥር መኪናውንም፣ ቤቱንም፣ድርጅቱንም ለምን በአንዴ ላገኝ አልቻልኩም ባይ አግበስባሽ ነገር ነች፡፡ልክ እንደስሟ እርግብ ነች..ሁሌ ለመብረር ዝግጁ ሆና ክንፎቾን ስታማታ ነው የምታገኟት።ወይንም እኔ እንደዛ እንደሆነች ነው የማስበው፡፡እኔ ደግሞ ነገሮች ሂደታቸውን ጠብቀው ተግባራዊ እንዲሆኑ የምመኝ ነኝ። በዚህ ክፍተት የተነሳ በጣም ብወዳትም የግድ መቁረጥ እንዳለብኝ ወሰንኩና አደረኩት...እንግዲህ ግንኙነታችን ሙሉ በሙሉ  ከተቋረጠ ከአምስት ወይም ከስድስት ወራት በኃላ መደወሏ ነው።
‹‹እሺ እርግበ…እንዴት ነሽ?››
‹‹እራስህን ብትሰውርም...አገኘሁህ››ንግግሯ የፉከራ ወዘና ያለው ነው፡፡
‹‹ጎበዝ ነሽ...ግን ስልኬን ከማን አገኘሽ?››
‹‹እናትህ እንደአንተ አይደለችም...ሰላም ልላት ደውዬ ነበር ...ሰጠችኝ፡፡››
‹‹ጥሩ...ሁሉ ነገር ሰላም ነው አይደል?››
‹‹አዎ በጣም ሰላም ነው...ልመጣ መሆኑን ልነግርህ ነው፡፡››
‹‹ልመጣ...መቼ?...እንዴት?››ድንግርግሬ ወጣ፡፡
‹‹አረ ተረጋጋ ..በደስታ ልብህ ቀጥ እንዳትል››መመፃደቋን ቀጠለች።
‹‹ቀልድን ተይና ....ማውራት የፈለግሽውን አውሪ፡፡››
‹‹አትቆጣአ.. አሁን ምን የሚያስቆጣ ነገር ተናገርኩ፡፡ኤኒዌይ ከሶስት ቀን በኃላ ሸገር ነኝ።ኤግዛክት ሰዓቱን በሚሴጅ ልክልሀለው፡፡››
‹‹ምን እንዲያደርግልኝ?››ብልጭ አለብኝና ጠየቅኳት፡፡
‹‹እንዴ ፍቅር...እንድትቀበለኝ ነዋ...ሌላ ለማንም ሰው አልደወልኩም...፡፡››
‹‹አልገባኝም፡፡››
‹‹በቃ ከቻልኩ ነገ ደውልልሀለው...አሁን መሄድ አለብኝ።››ስልኩ ተቋረጠ፡፡
አሁን ምን ላደርግ ነው? የተበጠሰውን ፍቅር  እቀጥላለሁ? ከቀጠልኩ በኃላስ የልዕልተ ጉዳይስ?ለገዛ አእምሮዬ ያቀረብኩለት ጥያቄ ነው።‹‹የልዕልተ ጉዳይ ምን?››አእምሮዬ መልሶ ጠየቀኝ።በህይወቴ እንዲህ ተወዛግቤና ግራ ገብቶኝ አያውቅም። ሁለቱን ሴቶች በምናቤ ጎን ለጎን ሳልኳቸውና ለማወዳደር ሞከርኩ፡፡ ቅንጥስጥስ ያለች ዘናጭ ፤ ጋዋን የለበሰችና ኮንፊደንሶ ሰማይ ላይ የተንጠለጠለው እርግበ..በሌላው ጎን ደግሞ ዙሪያዋን በሶስት ልጆች የተከበበችው አንገቷ ተሰብሮ አይኖቾ አልጋ ላይ የተኛው ባሏ ላይ የተሰካው እና እንደነገሩ የለበሰችውን ልዕልት...፡፡
በፈጣሪ ልቤ ሄዶ እዚች ሚስኪንና ጣጣ-ብዙ የሆነች ሴት ላይ ነው የተጣበቀው.፡፡ታዲያ አሁን እኔ ጤነኛ ነኝ?... አይመስለኝም፡፡ በህክምና የማይድን አይነት በሽታ መጋኛ አይነት ነገር ሳያጠናግረኝ አይቀርም፡፡እንደምንም ሊነጋጋ ሲል እንቅልፌ መጣ።


ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍5410👎1🔥1
#ትንግርት


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ከ8 ሰዓት እራስን የመሳት ሂደት በኃላ ዶ/ር ሶፊያ ስትነቃ ከአንደበቷ ሾልኮ የወጣው የመጀመሪ ቃል <<ትንግርት››የሚል ነበር፡፡ በወቅቱ አጠገቧ የነበረው ታዲዬስ ነበር፡፡ ግንባሯ በቀኝ በኩል በከፊል በፋሻ ተሸፍኗል፡፡ እንደምንም ተረጋግታ ያለችበትን ሁኔታ አጣራችና በደከመ ድምፅ << ታዲ >> ብላ ተጣራች ፡፡

‹‹አቤት…ምን ፈለግሽ?››

‹‹ትን..ግር ትስ?››

‹‹ሰላም ነች..አንቺ እራስሽን አረጋጊ፡።››

‹‹ንገረኝ ..የት ነው ያለችው..?ጥራልኝ በናትህ..ላገኛት እፈልጋለው፡፡››

‹‹አሁን እኮ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ነው..ነገ ታገኚያታለሽ››

‹‹አሁን ነው የምፈልጋት.. ታዲ በፈጠረህ ደውልላት፡፡››

‹‹ሞባይል ቁጥሯ የለኝም፡፡››

‹‹እኔ ሞባይል ውስጥ አለ፡፡››

ሊነግራት ባይፈልግም ስላስጨነቀችው ምንም ማድረግ አልቻለም ‹‹ታስራለች፡፡››አላት ፡፡

‹‹ወይኔ በጌታ ..!!!ማን አሰራ..ት?››አለች... ከተኛችበት ለመነሳት ብትጣጣርም ተራራ በጭንቅላተቷ የተሸከመች ይመስል የገዛ ራሷን ማነቃነቅ እንኳን አልተቻላትም፡፡

‹‹ህግ ነዋ ያሰራት...ልትገልሽ ሁሉ ትችል ነበር.::>>

‹‹ብትገድለኝም ይገባኛል..በፍፅም መታሰር የለባትም፡፡››

‹‹እሱ ያንቺ ፍላጎት ሊሆን ይችላል…ህግ ደግሞ እንደዛ አይልም፡፡››

‹‹ወይኔ ታዲ..አሁን ምን ይሻለናል?››

‹‹ስለምኑ?››

‹‹እንድትታሰር አልፈልግም፡፡››አለችው ደግማ፡፡

‹‹እንግዲ ሲነጋ የሚሆነውን እናያላን..ክስ ልትመሰርቺባት ካልፈለግሽ ምን አልባት በሽምግልና እንጨርሳለን ብለን ልናስፈታት እንችል ይሆናል፤አሁን ግን አንቺ ገና አላገገምሽም አረፍ በይ ፡፡››

‹‹ታዲ ...አንተ ግን ለምን ወደ ቤት ሳትሄድ…? ልጆችህስ?››

‹‹እንዲህ ሆነሽ እንዴት ጥዬሽ እሄዳለሁ…? ለልጆቹም ደውዬ ነግሬያቸዋለው፤ በጣም ነው ያዘኑት ፡፡ቶሎ እንድታገግሚ መልካም ምኞታቸው እንዳደርስላቸው ጠይቀውኛል፡፡ በገዛ እንግዳ እንዲህ በመሆንሽ አዝናለሁ፡፡››

‹‹ፍፅም ማዘን የለብህም...ይሄ የማንም ስህተት አይደለም፤ ለማንኛውም አብረኸኝ
ስለሆንክ ደስ ብሎኛል... አመሰግናለሁ፡፡››አለችውና አይኖቿን በድካም ከደነቻቸው.... እሱም የጀመረውን መጽሀፍ ማንበቡን ቀጠለ፡፡

ከለሊቱ 11 ሰአት ላይ ፎዚያ ተነስታ እየለባበሰች ሳለ ከውጭ የመኪና ጡሩንባ ጩኸት ሰማች... በጣም ነው የደነገጠችው፡፡ ‹‹በዚህን ሰዓት ማን ነው የመጠው..?››ሰውነቷ ሁሉ ተንቀጠቀጠባት፡፡‹‹የምን መርዶ ይዘውብኝ መጡ...?::>>

የመኝታ ቤቷን መስኮት ከፍታ ወደውጩ ስታማትር ዘበኛው የውጩን በር እየከፈተ ነበር፡፡ከዛ መኪናዋ ወደ ውስጥ ዘልቃ ገባች .. የሰሎሞን መኪና ነች፡፡ሮጣ ወደ ውጭ ወጣች፡፡እሱ ሞተሩን አጥፍቶ ከመኪናው ከመውረዱ በፊት እሷ ስሩ ደርሳ ‹‹ምን ተፈጠረ…? ምን ሆንክ..?ኤዲስ ደህና ነች…?››

‹‹አረ ተረጋጊ .…ሁሉም ሰላም ነው፡፡››

‹‹ታዲያ ምነው በዚህን ሰዓት?››

‹‹አብሬሽ ሀዋሳ ልሄድ ነው፡፡››

«ለምን?»

‹‹ለሽርሽር፡፡››አሾፈባት፡፡

‹‹ማለቴ ማን ነገረህ?››

‹‹አንቺ ብትደብቂኝም ሁሴን ደወለልኝ..ይገርማል ሀገር ውስጥ የተሰራ ታሪክ በአሜሪካ ዞሮ ስሰማው››

‹‹እኔ እኮ ኤደን አሟታል ስትለኝ ላስጨንቅህ ስላልፈለኩ ነው፡፡››

‹‹ቢሆንም መስማት ነበረብኝ..አሁን በይ ተዘጋጂና እንሂድ፡፡››

‹‹እሺ ጨርሻለሁ ...አምስት ደቂቃ ብቻ፡፡››አለችውና ወደ ውስጥ ተመልሳ ገባች፡፡

ዝዋይ ሲደርሱ ከጥዋቱ 1፡4ዐ ነበር፡፡‹‹ቁርስ እንሞክር እንዴ?››አላት ሰሎሞን፡፡

‹‹ኧረ ገና ጥዋት ነው… እንቀጥል፡፡›› አለችው..ተስማማና ነዳው፡፡

‹‹ግን ኤደን ታማ እያለ ጥለሀት ስትመጣ አልከፋትም?›› ጠየቀችው... ፎዚያ ፡፡

‹‹ከፍቷታል... ግን ምንም ማድረግ አልችልም፡፡ ሁሴን ሂድና እያት ብሎኝ ምክንያት ፈጥሬ እምቢ ልለው አልችልም፡፡ በዛ ላይ እኔ ኖርኩም አልኖርኩም ለውጥ የለውም፤ቤተሰቦቿ ዙሪያዋን ከበዋታል፡፡››

‹‹ቢሆንም.... ቤተሰብ ሌላ ባለቤት ሌላ፡፡››

‹‹ጉረኛ ...ስለባል ደግሞ ምን ታውቂያለሽ?››

‹‹ለምን አላውቅም፤ ስለባለትዳሮች ለማወቅ እኮ የግድ ባለትዳር መሆን የለብኝም፡፡››

‹‹መስሎሻል.. እኛም ሁለት ጊዜ ያገባነው እንኳን አሁንም ስለትዳር ምንም አልገባንም፡፡››

‹‹ምን ማለት ነው?››

‹‹ባክሽ ሴቶችን ማወቅ በጣም ነው እየከበደኝ ያለው፡፡››

‹‹ይህቺ ነገር..!!!!ምነው ከኤደን ጋር ሰላም አይደላችሁም እንዴ?››

‹‹እኔ እንጃ ባክሽ.. ከባለፉት ሁለት ወራቶች ወዲህ ንጭንጯን ልቋቋመው እየከበደኝ ነው....?»

‹‹መነሻውን አታውቅም? >>

‹‹ውሀ ቀጠነ ነው…ግን ቅዳሜ እና ዕሁድን ከልጆቼ ጋር ማሳለፍ ከጀመርኩ ወዲህ ይመስለኛል ነገሩ የጀመረው፡፡››

‹‹ከልጆቼ ጋር ስትል..ወደ ድሮ ሚስትህ እየሄድክ ማለት ነው?››

‹‹ኖ..ኖ ቅዳሜ እኔ ጋር ይመጣሉ. አብረውኝ አድረው እሁድ ማታ እመልሳቸዋለሁ.. ከእናታቸው ጋር ምንም የሚያገናኘኝ ነገር የለም፡፡››

‹‹ታዲያ እሷን ምኑ ነው የደበራት?››

‹‹እኔም ያልገባኝ እሱ ነው፡፡እንግዲህ መጀመሪያም ልጆች እንዳሉኝ እያወቀች ነው ያገባችኝ...ከሚስቴ ተፋተው እንጂ ከልጆቼ አልተፋታውም፤ ምኑ ቅር እያሰኛት አንደሆነ አልገባኝም፡፡››

‹‹ቆይ ያልገባኝ...ልጆቹን መተው የሚያሳልፉት አብረዋችሁ ቤት አይደል..?››

‹‹በፊት ነበር…በኃላ ግን ቅዳሜና እሁድን መጥተው ከእኛ ጋር ሲያሳልፉ ቅር እያላት ፊቷን እያጠቆረችባቸው ስታሳቅቃቸው ..ነገርኳትና ውጭ ማለቴ ሶደሬ ፤ላንጋኖ ካልተቻለም ደግሞ እዛው አዲስ አበባ ሆቴል አብሬያቸው ማሳለፍ ጀመርኩ፡፡

በነገራችን ላይ በሳምንት ሁለቱን ቀን ከልጆቼ ጋር ማሳለፍ እንዳለብኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳሰበኝ ሁሴን ነው ፤ ከመሄዱ በፊት ሊሰናታቸው ቤት ሄዶ በናፍቆት በጣም ተጎድተውና ተሳቀው ስላገኛቸው እኔም ኤደንም ባለንበት ሁኔታውን በማስረዳት አሳምኖን ሄደ፡፡እኔም ሁኔታውን መለስ ብዬ ሳስበው በጣም ነበር የፀፀተኝ ‹‹እንዴት ልጆቼን ችላ ልል እንደቻልኩ ድንቅ ነበር ያለኝ….በአጠቃላይ ሁኔታው ሁሉ እንደዛ ነው እልሻለው፡፡››

‹‹አይ ቢሆንም ተነጋገሩበት…እሷም ነገሩን መቀበል መቻል አለባት፡፡ ቅሬታም ካላት በግልፅ ትንገርህና መፍትሄ ፈልጉለት፡፡››

‹‹እስቲ እሞክራለሁ....ምን አልባት የራሷን ልጅ ስትወልድ ልጅ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በቅጡ ስለሚገባት ያን ጊዜ ትረዳኛለች ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡››

‹‹እንድትረዳህ እመኝልሀለው...ካለበለዚያ ስታገባ ሰትትፈታ መኖርህ ነው፡፡››ብላ አሾፈችበት፡፡

‹‹እጣ ክፍሌ ከሆነ ምን አደርጋለሁ፡፡››

3 ሰዓት ሀዋሳ ደረሱ፡፡ኤልያስ ሲጠብቃቸው ስለነበረ ወዲያው ወደ ትንግርት ይዞቸው ሄደ፡፡

‹‹ተራማጆቹ ፀሀፊዎች በፖለቲካ በሚታሰሩበት ዘመን አንቺ በፈንካችነት ትቀላቀያቸዋለሽ..? ምነው ምነው?››አላት ሰሎሞን ገና ከፖሊሶቹ ፍቃድ አግኝተው ፊት ለፊት እንደተገናኙ፡፡

‹‹ምን ይደረግ ....ይህቺ ሀገር ፀሀፊ ሳይሆን ጀግና ነው ያጣችው ብዬ ነዋ!!››ብላ መለሰችለት፡፡

የሚነጋገሩት ፖሊሶቹ ጆሮ ይደርሳል... አይደርስም የሚለውን ለማጣራት ግራ ቀኙን ተገለማመጠ

‹‹ምነው ፈራህ እንዴ?››አለችው፡፡

‹‹ልጄ ለምን አልፈራ..በስህተት እንኳን አንድ ቀን እስር ቤት ባድር ፈንድቼ የምሞት ነው የሚመስለኝ፡፡››

‹‹ለመሆኑ እንዴት ነሽ…?ምን አሉሽ?›› አለቻት ፎዚያ በጭንቀትና በሀዘኔታ፡፡
👍829😁4
‹‹ያው ዛሬ እሁድ ነው ....ማንም ምንም አይለኝም፡፡››

‹‹እንዴ ዛሬም እዚህ ልታድሪ?››ፎዚያ ነች፡፡

‹‹እዚሁ ልሰነብትም እኮ እችላለሁ ..አይዞሽ የምታስቢውን ያህል አስፈሪ አይደለም..ለማንኛውም ሁኔታዎች የሚታወቁት ነገ ነው፡፡››

‹‹በቃ እስቲ ተሯሩጠን የሆነ ነገር እናደርጋለን..ልጅቷንም ክስ እንዳትከፍት በሽማግሌ ይዘን ይቅርታ እንድታደርግልሽ እናግባባታለን፡፡›› አለ ሰሎሞን፡፡

‹‹አትሞክሩት፤ እሷን ይቅርታ ከምጠይቅ መቶ አመት በእስር ብበሰብስ ይሻለኛል፡፡››

‹‹ቆይ ግን ይሄን ያህል ያዳረሳችሁ ምንድነው?››ፎዚያ ነች በአእምሮዋ ሲጉላላ ያደረውን ጥያቄ ያቀረበችላት፡፡

‹‹እሱ ሆድ ይፍጀው ነው፤ለመሆኑ አምጪልኝ ያልኩሽን ዲያሪ አመጣሽልኝ?››

‹‹አዎ እኚው፡፡››ብላ ከቦርሳዋ ውስጥ አውጥታ ልታቀብላት ስትል ፡፡

‹‹ለእኔ አይደለም…. ለኤልያስ ስጪው..ሁለቱንም ዲያሪ አንድ ላይ በፖስታ አሽግና ከትንግርት ብለህ ከላይ ፃፍበት እና ስጣት፡፡››

‹‹ለማን? >>

‹‹ለዛች ሰይጣን፡፡››

‹‹ለዶ/ር ሶፊያ ማለትሽ ነው?››

‹‹አዎ… ስሟን ቄስ ይጥራውና፡፡››

‹‹ያመጡላትን ቁርስ በፖሊሱ አማካይነት ከላዩ አንዲቀምሱ ተደረገና አስረከቧት፤ለነገ ሁኔታዎችን ሊያመቻቹ ሶስቱም የፖሊስ ጣቢያውን ግቢ ለቀው ወጡ፡፡

ይቀጥላል


ቤተሰቦች #subscribe እያደረጋቹ

#Share and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍4719
እግዜር ከፋው መሰል
እሺ ነው የሚልልኝ :

ቀንሶ መስጠት አቆመ
ሁሉንም ተወልኝ።

መመላለሴን ወደዋለሁ
አትስጠኝ ጠቅልለህ

:

ቀንስብኛና ልበል ወዴት አለህ?

ሰጥተህ አትተወኝ
አርገህ አትተወኝ

:

በማግኘት ገረጣሁ በማጣቴ ወዛሁ ከልክለኝ ልጠይቅ እንዳገኝህ በዛው።

🎴ኤልያስ ሽታኹን🎴


ቤተሰቦች #subscribe እያደረጋቹ

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍357🔥3👏2🥰1
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  አስራ አንድ


በገጽ 113 እና 114 መካከል ምን ተደብቋል?

ጓደኛዬ ሃይሚ የማታውቀው ገጣሚና ደራሲ የለም (ገጣሚና ደራሲ ይለያያል ወይስ አንድ ነው? እኔ እንጃ! ብቻ እንደዚያ ነው የሚሉት) እንደ እሷ ድንገት ተነስቶ ግጥም የወደደ ሰው አላጋጠመኝም፡፡ የግጥም ዝግጅት አለ በተባለበት ሁሉ አዲስ ጸበል ፈልቋል እንደተባለ በሽተኛ መሮጥ ነበር ሥራዋ፤ ወደ እንደነዚህ ዓይነት ቦታዎች ስትሄድ የምትዘንጠው አዘናነጥ ሰርግ ቤት ያስንቃል፡፡ አጭር ናት፣ ራሷም እንደምትለው መልክ አላደላትም፤ ውበቷ ዓይኖቿ፣ጥርሷና እግሯ ላይ ያቆማል፤ ሳቋ በግድ ያስቃል፣ ዓይኖቿ አያርፉም፡፡ ሁልጊዜ ነፍሷ የሆነ ነገር እንደፈለገ ነው፡፡ ትውውቃችን ገና ከሕፃንነታችን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነበር፤ አውቃታለሁ እላለሁ፡፡ ብዙ ጊዜ የሥነ-ጽሑፍ ምሽት የሚሉት ጋብዛኝ እዚያው በጸበልሽ ብያታለሁ። ግጥም፣ ልብ-ወለድ የሚሉት ነገር ምኑም አይስበኝም፡፡ ነገሩ ማንበብ ላይ ሰነፍ ሆኜ አልነበረም፤ እንዲያዉም ግለ-ታሪኮችንና በሙያዬ ዙሪያ የተጻፉ መጽሐፍትን፣ አሳድጄ ነበር የማነበው። ልብ-ወለድ፣ በአጋጣሚ እንኳን በሬዲዮ ሲተረክ ከሰማሁ ለወራት _ ከአእምሮዬ_አይወጣም፡፡ ታሪኩን ሳወጣና ሳወርድ፣ በቁም ነገር ሳዝንና ስደሰት እሰነብታለሁ፡፡ እንደ ፈጠራ ሥራ ቀለል አድርጌ ማዬት አልችልም። ያንን ስሜት ደግሞ አልወደውም። ሃይሚም ብትሆን ከእኔ ብዙም አትለይም ነበር፤ እንዲያውም እውነቱን ለመናገር ንባብ ላይ ብዙም አልነበረችም፡፡ ይኼ የግጥም ፍቅሯ ድንገት የሆነ ጊዜ የጀመረ ነበር። ከ “ኤለመንተሪ” እስከ “ሀይስኩል” በኋላም አብረን ኮሌጅ ስንማር ስለ ልብስ እና ጌጣጌጥ እንጂ ስለ ግጥም ስታወራ ሰምቻት አላውቅም ነበር። ታዲያ እንዲህ እንዲህ ያለው ቦታ ጋብዛኝ አልሄድም ስላት “ኋላ ቀር” ትለኛለች፡፡

አንድ ሁለት ጊዜ የሙዚቃ ዝግጅት እንድንሄድ ለምኛት እንቢ ስላለችኝ “ኋላ ቀር እዚያ ሄደሽ የሽማግሌዎች ተረት ስሚ" ብያታለሁ።አንዳንዴ ጓደኝነታችን ይገርመኛል፡፡ በጋራ የምንወደው ነገር “ፒዛ” ብቻ ይመስለኛል፡፡ እኔ ወድጄው ያልጠላችው፣ እሷ ወዳው ያልጠላሁት ነገር የለም። ከሆነ ጊዜ ጀምሮ እቤቷ ከሰበሰበቻቼው መጽሐፎች የሚበዙትን የደራሲያኑ ፊርማ ያለባቼው ስለነበሩ እንደ ቅርስ ነበር የምታያቼው፡፡ ለሰው አታውስም፣ በበኩሌ መጽሐፍ የደራሲው ፊርማ ኖረበት የመጽሐፍ አዟሪው፣ ልዩነቱ አይገባኝም ነበር። ሃይሚ ስለ ማንበብ ጥቅም ብዙ ብዙ ስትለኝ ምን እንዲህ ቀዬራት? እያልኩ በግርምት አያታለሁ፡፡ በተለይ አንድ ሰሞን ወደ ስብከት የሚቀራረብ “ዲስኩር† ነበር _ የምትደሰኩርብኝ፡፡ _ ታዲያ በአንገቴ ገመድ ቢገባ ከቤቴ አይወጡም የምትላቼውን መጽሐፍት፣ ካላነበብሽ እያለች ስትሰጠኝ ጉዱን ልዬው ብዬ ልብ ወለድ ማንበብ ጀማመርኩ። አንዳንዱን በጣት የሚቆጠር ገጽ እንኳን ሳላነብ እመልስላታለሁ፤ አንዳንዶቹን በስንት ትግል ዐሥራ አምስት ቀንም፣ ወርም ወስዶብኝ እጨርሳቼዋለሁ። እንዲህ ስንነታረክ ነበር አንድ መጽሐፍ ያዋሰችኝ፡፡ ያንን መጽሐፍ በጣም ነበር የወደድኩት፤ ታሪኩን ከመውደዴ የተነሳ በሦስት ቀናት ነበር አንብቤ የጨረስኩት። ሃይሚ ያንን መጽሐፍ ስታውሰኝ በጣም እንደወደደችው እና ሁለት ጊዜ እንዳነበበችው አጋና ነግራኝ ነበር፡፡ የመጽሐፉ የመጀመሪያ ገጽ ላይ የደራሲው ፊርማ እና “ከአክብሮት ጋር ለሃይማኖት ዳኛቸው የተሰጠ” የሚል ጽሑፍ በጥቁር እስክርቢቶ ተጽፎበታል፤ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ ስለ አንዲት በአደጋ ምክንያት የማስታወስ ችሎታዋን ስላጣች ሴት ነበር፡፡ ይህቺ ሴት የአምስት ዓመት ልጇንም _ ነበር _ የረሳችው፤ ልጅቱ ሕፃን ናትና ችግሩን አትረዳም፡፡ እናቷን እንደወትሮው ለመቅረብ የማታደርገው ጥረት የለም፡፡ እናት ግን በየቀኑ ትረሳታለች ፤ በዚያ ላይ በጣም ቁጡ እናት ሆና ነበር...መጽሐፉ ሲበዛ አሳዛኝ በመሆኑ ላለማልቀስ እየታገልኩ ነው ያነበብኩት፡፡ እስካሁን ያ ታሪክ ድርሰት

ነው ቢሉኝ አላምንም፤ የሆነ ነፍሴ ውስጥ ተሰንቅሮ ቀርቷል።ያቺ ሕፃን እኔ ነኝ፤ የተረሳሁ፣ የሚገፋኝን፣ የረሱኝን ሁሉ እግራቼው ሥር እየወደቅሁ እንዲወዱኝ የመማጸን፤ እኔ ነኝ። ሰልነግረው የተረዳኝ ሰው ያገኜሁ መሰለኝ፡፡ ደራሲዉ እኔ ራሴ የሆንኩ መሰለኝ፤ የሆነ ተናግሬም፣ አልቅሸም ልገልጸው የማልቾል ነገሬ ላይ ደርሶ ነክቶኛል። መቼም ትንሽ ማወቅ ዕዳ ነው፤ ከዚያ በኋላ ስለ መጽሐፍ በተወራ ቁጥር የማነሳው ያቺን መጽሐፍ ሆነ፡፡ እንድ ነገር ግን ገረመኝ ፣ ስለመጽሐፉ ሳይሆን ስለጓደኛዬ ሃይሚ ... ያዋሰችኝ መጽሐፍ ገጽ 113 እና 114 ከላይ የተጣበቁ ነበሩ፣ ሕትመት ላይ የሚፈጠር ነገር ነው፡፡ ብዙ አዳዲስ “ሪፈረንስ' መጽሐፍት ስገዛ አጋጥሞኝ ያውቅ ስለነበር የገጾቹ መያያዝ አላስገረመኝም፤ የገረመኝ ሃይሚ እንዳለችው ይኽን መጽሐፍ ሁለት ጊዜ ካነበበችው እንዴት ገጾቹን አላላቀቀቻቼውም...?ያላነበበችውን መጽሐፍ ለምን ታደንቃለች....? አራት ጣቶቼን በመኻል አስገብቼ እንደ ክብ ትቦ በተጣበቁት ገጾች መኻል አጨነቆርኩ፤ ምናልባት ሌላ ኮፒ ይኖራት ይሆናል ብዬ በቀስታ በምላጭ አላቅቄ ማንበቤን ቀጠልኩ። ለሃይሚ መጽሐፉን እንደወደድኩት ነገርኳት ስለ ታሪኩ ብዙ አወራኋት “አዎ! አስገራሚ ነው'' ከማለት ውጪ ብዙም ዝርዝር አላወራችኝም። እኔ ግን ማውራቴን ማቆም አልቻልኩም፤ የጥያቄ መዓት አዥጎደጎድኩባት መልስ የለም፡፡ እንዲያውም ለአባቴ ሰጥቼው አንብቦ ወደደው... ብዙ ብዙ አወራንበት፡፡ ለሃይሚ መጽሐፉን ከመለስኩላት በኋላ ሥራዬ ብዬ ሔጄ ለራሴ ገዛሁ፡፡ ልብ-ወለድ መጽሐፍ ስገዛ የመጀመሪያዬ ነበር፤ ምናልባት የመጨረሻዬም!! አንድ ዓርብ ቀን ታዲያ ጓደኛዬ ሃይሚ ደወለችልኝና... “የምትወጂው ደራሲ ነገ ጧት የመጽሐፍ ምረቃ ፕሮግራም ላይ ይመጣል ለምን አንሄድም?'' አለችኝ...

“ኧረ! ባክሽ?'' አልኩ ሰፍ ብዬ... በመሠረቱ ደራሲውን እወደዋለሁ የሚል ቃል ከአፌ አልወጣም ነበር! የት አውቄው? “እውነት! ቶማስ ጋር “ቤስት' ናቸው ያስተዋውቀናል እንዲያውም እኔን ትጠይቂዋለሽ”... ቶማስ ከምታደርቂኝ ስለዚያ መጽሐፍ ያለሽን ጥያቄ ሁሉ የሃይሚ ፍቅረኛ ነበር፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሥነ-ጽሁፍ ተመርቆ እስካሁን አንድ ስንኝ እንኳን ያልጻፈ ነጭናጫ ልጅ፣ በሕሪው ስለሚያስጠላኝ አልወደውም፤ ሃይማ ምኑን እንደወደደችው እስከ ዛሬ ይገርመኛል፡፡ ለወትሮው እንዲህ ዓይነት የሥነ-ጽሑፍ ዝግጅት ይሁን፣ ስብሰባ የሚባል ነገር ባልወድም፣ የዚያን ቀን ግን ደራሲውን ለማዬት ጓጓሁ፤ ምናልባት ውስጤ አድንቆት ይሆናል እንጃ! ብቻ ውስጤ ሊያገኜው ፈለገ፡፡ በቀጣዩ ቀን ቅዳሜ ጧት ከሃይሚ ጋር ተያይዘን ሄድን፡፡ እዚህ ራስ ሆቴል፣ አዳራሹ ካፍ እስከገደፉ በሰው ተሞልቷል። መድረኩ ላይ የባሕል የሙዚቃ ተጫዋጮች የባሕሩ ቃኜን ዘፈን ይጫወታሉ(ይልቅ ይኼ ደስ አለኝ) እንደፈራሁት አልነበረም፡፡ እንዲያውም ደስ የሚል ዝግጅት ነበር፡፡ የተለያዩ ሰዎች መድረክ ላይ እየወጡ ግጥም ያነባሉ፡፡ መጽሐፍ ያሳተመውን ሰውዬ እንኳን ደስ ያለህ ይላሉ፡፡ ፕሮግራሙ ወደማለቁ ሲቃረብ ወጣትና ንጹህ ልብስ የለበሰ፣ በሥርዓት ፂሙን የተስተካከለ ልጅ ወደ መድረክ ሲወጣ ሃይሚ በክንዷ ጎሼም አድርጋኝ “እሱ ነው!!' አለችኝ፡፡ ሰው እንደዚያ አፍጥጨ ዓይቼ አላውቅም፡፡ ትልቅ _ ሰውዬ ነበር የጠበቅሁት፣ መላጣ መነጽር የሚያደርግ ምናምን፡፡ ግጥም አነበበ፣ እውነቱን ለመናገር ግጥሙ አልገባኝም። የአዳራሹ ሰው ሲያጨበጭብ አብሬ
👍355
አጨበጨብኩ። የጓደኛዬ ሃይሚ ፍቅረኛ ቶማስ “አጨብጫቢ ሕዝብ” እያለ ይነጫነጫል፤ ይኼን ነገሩን ነበር የማልወደው ከመተቼትና ከመዝለፍ ውጭ ምንም ሲሠራ አይቼው አላውቅም፡፡ የሆነ የሚያሳፍር ዓይነት ባሕሪ ነበር ያለው፣ እርሜን ባጨበጭብ “አጨብጫቢ ...” ሆሆ!

ዝግጅቱ አልቆ ሰው መውጣት ሲጀምር፣ የአንድ እግር ጫማዬ ወንበሩ ሥር ገብቶ ጠፋኝ፤ አውልቄ ነበር የተቀመጥኩት፤ አልተው ያለኝ ዓመል። አጎንብሽ ለፍለጋ ስንደፋደፍ ሃይሚ “ኤጭ! አሁንም ጫማሽ ጠፋሽ?'' እያለች አብራኝ ማፈላለግ ጀመረች “ምን የአንድ ዓመት ሕፃን ነሽ እንዴ? በዚህ ዕድሜ ጫማሽን በየቦታው መጣል?" ሁልጊዜ የሚያማርራት ይኼ ነገሬ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ እያለን ቶማስ ስሜን ጠርቶ፣ “ተዋወቂው!'' አለኝ፡፡ ቀና ብል ደራሲው አጠገቤ ቆሟል፤ በአንድ እግር ጫማ እንደቆምኩ ተዋወቅን (ተመስገን ይኼ ቶማስ የሚባል ገልቱ ይኽችን እንኳ ጥሩ ነገር ይሥራ ብያለሁ በውስጤ) በሥርዓት ሰላም ብሎኝ ትክ ብሎ እያዬኝ “ምን ጠፍቷችሁ ነው?'' አለ፡፡ “ጫማ!'' አልኩ በእፍረት ወደ አንድ እግሬ እያሳዬሁ፤ እግሬን እያዬ... “እንኳን ጠፋ ይኼን ቆንጆ እግር የማዬት ዕድል ፈጠረልን፡፡ ለማንኛውም ዕቃ መፈለግ አይሆንልኝም ግን እስቲ በፍለጋው ልሳተፍ" አለና ወደ ወንበሩ ሥር ::חחלל “ኸረ! እኛ እንፈልገዋለን”... አልኩ ተሳቅቄ፤ አብሬው ጎንበስ ብዬ ቀና ላደርገው እየሞከርኩ፡፡ ሰዎች ጉልበታቸውን ሊስሙ ያጎነበሱ ሰዎችን ትከሻቼውን ይዘው ቀና እንደሚያደርጓቼው ዓይነት ነበር ሙከራዬ፡፡ “ኸረ! ችግር የለውም!'' አለና፣ ትንሽ ቆይቶ ከተቀመጥኩበት ሦስት መደዳ አልፎ የወደቀ ጫማዬን አገኜው፣ እንደ ዋንጫ ከፍ አድርጎ እዬሳቀ መጣና ጎንበስ ብሎ እግሬ ሥር አስቀመጠልኝ፤ “ሰዎች በእግራቼው እየገፉ ወደዚያ ወስደውት መሆን አለበት አለ!'' በዚያ እየተሳሳቅን ወደ ውጭ ወጥተን እንደቆምን፣ አሁንም ዓይኑን ከእኔ ላይ ሳይነቅል፣

“የሚገርም ጠይምነት!'' አለኝ። አፈርኩ። ብዙ ሰው ከዚያ በፊት እንደዚያ ብሎኛል፤ የእሱ አስተያዬት ግን ለምን የተለዬ እንደመሰለኝ እስከዛሬ አይገባኝም፡፡ ፊቱን በመስተወት ባዬሁ ቁጥር ይኼ አስተያዬቱ ነው የሚያቃጭልብኝ፡፡ ጠይምነቴን ሳስብ፣ እሱ እንደግድግዳ የቀባኝ ይመስል እሱን ነው የማስታውሰው።

“በነገራችን ላይ አልተዋወቅንም፣ አብርሃም'' አለና እጁን ለሰላምታ ዘረጋልኝ፡፡

“ማኅደረ ሰላም'' አልኩ እጁን እየጨበጥኩ፡፡

“ሌላ አስገራሚ ነገር'' ብሎ ሳቀ፡፡

“ምኑ?''አልኩ፡፡

“ስምሽ!"

“ረዘመ?”

“አዎ! ግን በጣም ነው ደስ የሚለው!”

“...የአባቴን ቀንሼልህ ነው፡፡'' ተሳሳቅን፡፡ ለሁሉም ሰው የምለው ነበር፡፡

ሃይሚ በወሪያችን መኻል ጣልቃ ገብታ “መጽሐፍህን አንብባ የአገር ጥያቄ ስታዘንብብኝ፣ ራሱን ጠይቂው ብዬ አመጠኋት፤ በጣም ነው የወደደችው" አለችው፡፡

“እና ዛሬ ችሎት መቅረቤ ነዋ? ...ለምን በእኔ ግብዣ ቡና እየጠጣን አናወራም ታዲያ?'' ብሎ ሁላችንም ተያይዘን እዚያው አካባቢ ያለ ካፌ ገባን፡፡ በግርምት አዬዋለሁ፤ ቡና አዘዘ፣ ልክ እንደመጣለት በሚገርም ፍጥነት መጠጣት ጀመረ። እያወራን ሌላ ቡና አዘዘ ...እና ሦስተኛ ቡና ሲያዝ፣ ሳላስበው ቀና ብዬ አዬሁት! እሱም ቀና ብሎ አዬኝ፡፡ ዓይኖቻችን ሲገጣጠሙ የማደርገው ነገር ጠፋኝ። የእፍረቴን “ቡናው አልበዛም?'' አልኩት፡፡ እየሳቀ ወደ አስተናጋጁ ዞረና “በቃ ውሃ

አምጣልኝ ቡናውን ተወው” አለ፡፡ እያንዳንዱን ቅጽበት አልረሳውም፡፡ የዚያን ቀን በሕይወቴ ደራሲ የሚባል ፍጥረት ጋር ተዋወቅሁ ... ያው ሰው ናቸው፤ ከዬት ነው የሚያመጡት ታሪኩን!?... ለምንድን ነው ብዙ ቡና የሚጠጣው!? ... ሲጋራ ያጨስ ይሆን!? እያልኩ አዬዋለሁ፡፡ አልፎ አልፎ ዓይኖቻችን ይጋጫሉ፤ ሃይሚ፣ ቶማስ እና እሱ ስለ _ ግጥም ምናምን ሲያወሩ በየመኻሉ ተጫዋች ይለኛል፡፡ ስለ መጽሐፉ አላነሳንም። ቆይቶ...

“እና ምን ትሠሪያለሽ ልገምት ?'' አለ፡፡

“ገምት፣”

"ነርስ?"

“አይይይ!”

“ሥራ አጥ ነርስ?'”

“እንዴዴዴ፣'” ተሳሳቅን “አካውንታት.. ኦዲተር ...ነኝ'' አልኩት፡፡

“ኦ! ግምት ላይ ቀሽም ነኝ፣''

“አዬሁህ'ኮ!” ረዘም ያለ ሳቅ።

“በቃ! ለስሕተቴ ቅጣት...ቅዳሜ የግጥም ምሽት አለ፤ በእኔ ወጭ ልጋብዝሽ''አለኝ፡፡

“ግጥም _ አልወድም!'” አልኩት፡፡ ሊሰጠኝ፣ ከሆነ መጽሐፍ ውስጥ ያወጣውን የመግቢያ ትኬት ለሃይሚ አቀበላትና ሌላ ትኬት አውጥቶ ባትወጂም ነይ ብሎ ሰጠኝ ተሳሳቅን፡፡ ስትደርሽ ደውይልኝ ብሎ ትኬቱ ላይ ስልኩን ጻፈልኝ፡፡ ለምን እንደሆነ እንጃ፣ እንደ ሕፃን ነበር “ትሪት' የሚያደርገኝ፡፡ አላስታውስም ሰዎች እንዲህ ያናገሩብኝን ጊዜ፤ እንደዚያ ተዋወቅን፡፡በዚያው ሰበብ መደዋወል እና መገናኜት ጀመርን፡፡

የዚያች ካፌ የቡና ጠረን፣ የሰዎች ጫጫታ፣ በነጭ ድንክ የቡና ስኒ ቡና አጠጣጡ፣ አስተያዬቱ፣ እያንዳንዷ ድርጊት፣ ድምፅ እና ዝምታ ጭምር ነፍሴ ውስጥ ታትሞ ቀርቷል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ተቀጣጥረን የተገናኜን ጊዜ ጨንቆኝ ነበር፡፡ ወንድ ጋር ከሥራ ጉዳይ ውጭ ስቀጣጠር የመጀመሪያዬ ነበር፡፡ ቀድሜው ደረስኩ፤ እንደ ደረሰ ሰላም ብሎኝ ተቀመጠና ካዘዝኩት ለስላሳ የእኔን ብርጭቆ አንስቶ ተጎነጨ፡፡ ከዚያ ቡና አዘዘ፤ ይኼ ድርጊቱ ውስጤ የነበረውን መጨናነቅ ቀንሶ በጓደኝነት ስሜት አንድናወራ አድርጎኝ ነበር፡፡ አብርሃም ጋር እንዲህ ነበር ትውውቃችን፡፡ አልዋሽም ጥሩ ልጅ ነበር፡፡ ነገሮች የት ላይና ለምን እንደተበላሹ እስከዛሬ አይገባኝም፡፡ በብዙ ነገር ከተረባባሼ ሕይወቴ የማርፈው እሱ ጋር ስሆን ብቻ ነበር፡፡ ለምንድን ነው ግን ሕይወቴ እኔ ባልፈጠርኩት ረብሻ የተከበበ የሚሆነው? ደግሞ ክፋቱ ሁሉም ረብሻዎች በፍቅር፣ በደግነት፣ በትህትናና በበጎነት የተጠቀለሉ መሆናቼው ነበር፡፡ አቤት ያለፍኩባቼው ረብሻዎች መዓት....!

ረብሻ አንድ!

ጋራዡ ስም የለውም፣ በቃ ጋራዡ ነው የሚባለው፡፡ ከቤታችን መቶ ሜትር ያኽል ቢርቅ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ እዚህ ጋራዥ ሊጠገኑ የሚመጡ መኪናዎች የጋራዡ ጠባብ ግቢ ስለማይበቃቼው ቤታችን መስኮት ጥግ ድረስ ይሰለፋሉ፡፡ ከእነዚህ መኪናዎች የሚንጠባጠብ ዘይት፣ ግራሶና ነዳጅ ባጠቆረው ወዛም ቆሻሻ ሰፈር መኖር ቢለመድም፣ የሚያስመርር ነገር ነበረው፡፡ የተለመደ ምሬት። ከዚህም በላይ ከጧት እስከ ማታ የከባድና ቀላል መኪና ሞተር ሲያጓራ፣ እንደ ማዕድቤት ጭስ የጠቆረ፣ እንደ ደመና የነጣ፣ የመኪና ጭስ አየሩን ሲሞላው፣ የተሰረጎደ የመኪና አካል እንዲቃና በመዶሻ ሲቀጠቀጥ፣ የብረት መበዬጃና መቁረጫ ሲንጫረርና ሰፈሩ በሊድ ሽታ ሲቀረና፣ የማያቋርጥ የመበዬጃ ጨረር በርና መስኮት ተዘግቶ እንኳን በሆነ ቀዳዳ አልፎ እንደ ካሜራ ፍለሽ ሲንቦገቦግ፣ በዚህ ሁሉ መኻል ነው ያደግሁት...ለምጄዋለሁ ግን ያስመርረኛል፤ ወይም

አብሬው እኖራለሁ ግን አለመድኩትም፡፡ እኔ እንጃ! በሕይወቴ ብዙ ምኞት አልነበረኝም ቢያንስ ሰላምና ሙዚቃ ያለባት አንዲት ክፍል ቤት ነበር ምኞቴ። ከዚሀቹ ምኞት ብሶ እንደ ሰማይ ስትርቅብኝ አይገርምም? በለ ጋራዡ አንዳንዴ ክፉኛ ይሟዘዛል እንጂ የተመሰከረለት ጥሩ ሰው ነው፡፡ ክፍሌ ይባላል፤ ኤርትራዊ ነው። ሰው ታመመ ከተባለ መኪናው ከአንቡላንስ ቀድሞ ሆስፒታል የሚያደርስ፣ ሰርግ _ ከተባለ እንኳን የራሱን ሊሰሩ ጋራዡ የቆሙ መኪኖቹን አሰልፎ የሚያደምቅ፣ የሰፈር ሰው ሁሉ የሚወደው ሰው ነው። በየዓመቱ ጥምቀት ሲከበር የሰፈራችን ታቦት የሚያልፍበትን መንገድ ከፍሎ
👍3210
የሚያስጸዳውም (የሚበዛው ቆሻሻ የራሱ ቢሆንም)ይኼው ክፍሌ ነበር፡፡ ታዲያ እኔም ጋር ጥሩ የእህትና ወንድማዊ ቅርርብ ነበረን፣ እንደ እናትሽ ጠይም ሰይጣን ይለኛል። ደፍሬ ሰው ቀና ብዬ ማዬት የምፈራ እኔ... ክፍሌ ጋር ምላሴን የማረዝመው ነገር አለ፤ እንዲሁ እወደው ነበር፡፡ አለ አይደል ንጹህ ልብ ያለው የሥራ ሰው እንደዚያ ነው፡፡ በዚያ ላይ አባቴን ሲወደው ለጉድ ነው፡፡ታዲያ በየዓመቱ የኦዲት ሪፖርት የምሠራለት እኔ ነበርኩ “እነዚህ ገቢዎች ሲኦል ያስገባቼውና..." እያለ የደረሰኝ መዓት ፊቴ ይከምርልኛል፡፡ የምወደውን “ፒዛ” ልጅ ልኮ ያስመጣል፤ እንደ ታላቅ ወንድም ነበር የምቀርበው፤ ሚስጢረኛዬ ነበር፡፡ “መኪና ከገዛሽ ለጥገናው የዕድሜ ልክ ዋስትና በእኔ ጣይው'' ይለኛል .... ከልቡ ነው ደግሞ። “አንተ ቤት የሚጠገን መኪናማ አልገዛም...” “መናቅሽ ነው ...ዶሮ የሌላት ላም አማረረች አሉ!'' “አህያ የሌላት በቅሎ ታማርራለች ነው የሚባለው!" “የዛሬ ልጆች ሥራ አትወዱም እንጂ፣ የተረት ቡለን ፍቱ ...” ይላል፡፡

“...እና ደንበኞችህ በሙሉ ሰካራሞች ናቸው ... እየተጋጩ ነው የሚመጡት ... የከተማዋን አጥርና ምሰሶ የጨረሱት የአንተ ደንበኞች ናቸው።'' “ምናለ ታዲያ.ወንድ ልጅ ካልጠጣ፣ ካልተጋጨ ምኑን ወንድ ሆነ ...? ከመቼ ነው አንቺ እንዲህ ምላሳም የሆንሽው!?”... ታዲያ አብርሃም ጋር የተጣላን _ ሰሞን ጸብም ባይባል ወደ መጨረሻው አካባቢ፣ በጭንቀት ልፈነዳ ስደርስ ፍቅር እንደ መኪና ጋራዥ ይጠገን ይመስል፣ የሆንኩትን ሁሉ ነገርኩት ... አሰበ አሰበና፣ “እናስደብድበው ይሆን!?'' አለኝ ሳቄ አመለጠኝ፡፡ “ምን ያስቅሻል? ጥርሳም... ይኼ ሸርሙጣ ... መቅመስ አለበት! ለመሆኑ ምንድን ነው ሥራው?'' “ደራሲ!”

“ያው “ሸርሙጣ” ማለት'ኮ ነው! አንቺ ስንት ሰው እያለ ምን አልከሰከሰሽ? እኔ ወርቅ እጅ ያለው ሜካኒክ እድርሽ አልነበር? እውነቴን'ኮ ነው በዚህ ስታልፊ ስንት ሠራተኞቼ ናቸው አንችን እያዩ አአአአአአ ብለው ሥራ የሚፈቱት የነበር ... !? ሴቶች ስትባሉ ሕዝብ መኻል ካለ ንብ፣ መድረክ ላይ የሚዘል ዝንብ ትወዳላችሁ.... ሚስቴም ጥላኝ የሄደችው እዚያ ከበሮ የሚደልቅ ዘፋኝ ወዳ ነው ... “ሸርሙጠ'' ሆና እንጂ ከበሮ ምኑ ይወደዳል? ደግሞ ደራሲ ትላለች ...ሁለተኛ አጠገቡ እንዳትደርሺ ....ሆሆ'' በብስጭት የሚይዝ የሚጨብጠውን አጣ፡፡ ግን ምክሩን አልሰማሁም፡፡ እዚህ ድረስ እየወደድኩት፣ እየቀረብኩት ሰፈሬን ያስጠላኝ ረብሻ ግን ከዚህ ሰው ጋራዥ ነበር የሚመነጨው፡፡ ዕድሌ ይሆን ፍቅርና ረብሻ አንድ ላይ የሚሰጠኝ፡፡

ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍351
እባክሽ አትሂጂ…..
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አራት

ባሏን አይቼላት …መመርመር  የሚገባኝን ሁሉ መርምሬ ከሚወስዳቸው መድሀነቶች መካከል አንድን  ቀንሼ ሌላ አንድ ተጨማሪ መድሀኒት በቅያሬ አዝዤ አሁን እየሸኘችኝ ነው፡፡ቆይቼ እራት እንድበላ ብትጠይቀኝም አልተስማማሁም፡፡ሳልፈልግ ቀርቼ ሳይሆን ትናንት ከኖሮዌይ በደወለችልኝ የቀድሞዋ እጮኛዬ እርግበ ምክንያት ጠቅላላ መንፈሴ እርብሽብሽ ብሎ ስለዋለና አሁንም ያ ስሜት አብሮኝ ስላለ ድብርቴን ወደ እሷ ላጋባባት ስላልፈለኩ ነው፡፡
‹‹ደ/ር  ግን ቢያንስ አንድ ሲኒ ብና ሳትጠጣ ቅር አሰኝተሀኛል፡፡››
‹‹ምን ነካሽ እቤቴ እኮ ነው…ብፈልግ እራሴ ጠይቄ አፍይልኝ እልሽ ነበር..ስለቸኮልኩ ነው፡፡››
‹‹ይሁን….››አለቺኝ፡፡
እኔ ወደ መኪናዋ ሳመራ እሷ የውጩን  በራፍ ልትከፍትልኝ ሄደች፡፡መኪናዬን በማሰነሳት ከግቢው ወጣሁና ዳር አሲዤ  አቆምኩ፡፡መኪናዋን  ሳላቆም እጄን በማውለብለብ ተሰናብቼያት መቀጠል እችል ነበር..አሁን  ማቆሜ ግን  ነይና ቀርበሽ ሰላም በይኝ የሚል ምልክታዊ መልዕክት ማስተላለፌ እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡፡ ..አላሳፈረችኝም ወደ መኪናው ቀረበችና ጎንበስ አለች….
‹‹በይ እንግዴ ..ከነገ ወዲያ እንገናኝ….ችግር ካለ በማንኛውም ሰዓት ደውይልኝ››
‹‹እሺ ዶክተር…ደውልለሀላሁ…››በማለት አረጋገጠችልኝና ቀና አለች፡፡››
‹‹ ቆይ አንዴ››አልኩና ወደኃላ ዞሬ ከኃላ መቀመጫ ወዳለው እቃ ተንጠራራሁ…ቀዩን እንቡጥ ፅጌረዳ ተውኩና በካርቶን ያለውን ቸኮሌት አንስቼ ሰጠኋት››
‹‹ምንድነው?››
‹‹ላንቺ አይደለም…ለነዳኒ ስጪልኝ››
‹‹ኸረ ዶክተር ተው..፡፡››
‹‹በይ ደህና ሁኚ…››ሌላ መልስ ከእሷ ሳልጠብቅ መኪናዬን አንቀሳቀስኩ…፡፡የሰጣኋትን አነስተኛ ካርቶን እንደያዘች ወደ ውስጥ ገባች፡፡ በእስፖኪያ ወደ ኃላ ወንበሬ እያየሁ ነዳሁት፡፡ፅጌረዳ አበባዋ ዛሬም ለሁለተኛ ጊዜ መባከኗ ነው፡፡ ቅድም ስገዛው ከቸኮሌቱ ጋር አብሬ እንደምሰጣት ባለ ሙሉ ወኔ ነበርኩ፡፡አሁን የእውነቱ ሰዓት መጥቶ ከእሷ ጋር ስፋጠጥ ግን ወኔዬ ተሰለበ፡፡ደግሞም ይሄንን ለማድረግ በጣም ፈጥኜያለሁ፡፡ከዚህ ማለቴ አበባ ከመስጠት በፊት የሚቀድሙ ገና ብዙ ሂደቶች አሉ፡፡እንዴ ቢያንስ አንድ ቀን ካፌ ቁጭ ብለን ማኪያቶ በመጠጣት የግል ወሬ አውርተን አናውቅም…ለእኔ ጭላንጭል እንኳን የሆነ ፍላጎት ይኑራት አይኑራት አላውቅም፡፡ብዙ ብዙ ነገር አላውቅም፡፡ስለዚህ ነገሮች ድብልቅልቃቸው ወጥተው የቤቷን በራፍ ዘግታብኝ ከቤቷም ከባሏም አካባቢ ልታርቀኝ ትችላለች፡፡፡ እንደዚህ አይነት ሪስክ መውሰድ አልፈለኩም.. ለዛነው ይዤ የመጣሁትን እንቡጥ ፅጌረዳ መልሼ ይዤ እየሄድኩ ያለሁት፡፡
ቀጥታ ወደ መጠጥ ቤት ነው ያመራሁት፡፡ይህ የዘወትር ባህሪዬ አይደለም.. ግን ዛሬ መጠጣት እና ውስጤና ማረስረስ አምሮኛል፡፡ሰዓቱ ገና 12፡15 ቢሆንም ግድ አልሰጠኝም፡፡.አልፎ አልፎ ጎራ የምልበት ከሰፈሬ ቀረብ ያለ አንድ ሆቴል ገባሁና ሰወርና ነጠል ያለ ቦታ መርጬ በመቀመጥ ቀዝቃዛ ቢራዬን አዘዤ ከትካዜ ጋር መማግ ጀመርኩ፡፡
አእምሮ ግን ምን አይነት እረፍት አልባ ተፈጥሮአዊ ማሽን ነው?እንኳን ላስብ ብለው አስበውበት ይቅርና እንዲሁም ሀሰሱንም ገሰሱንም ጨምሮ በቀን ከ60 ሺ በላይ ቁርጥራጭ ሀሳቦችን እንደሚያስብ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ይታያችሁ 60 ሺ ሀሳብ፡፡ ከዛ ውስጥ ጎጂው ስንት ነው…? ጠቃሚውስ… ?አስደሳቹ ምን ያህል ነው…? ሀዘን ላይ የሚጥለንስ የትኛው ነው…? ሰው አስተሳሰብን በምን ያህል መጠን መቆጣጠር ይችላል? ከመቀባዠሬ ሳልወጣ  ስልኬ ቨይብሬት ስታደርግ በኪሴ ውስጥ ስለተሰማኝ አውጥቼ አየሁት፡፡ወይ እየሸሸሁት ከነበረ ሰው የተላከ መልእክት ነው፡፡
‹‹ነገ ማክሰኞ በኢትዬጵያ ሰዓት
አቆጣጠር ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ ቦሌ እንደርሳለን
ያንተው ፍቅር እርግበ ነኝ፡፡››ይላል፡፡
በንዴት ግማሽ የነበረውን የቢራ ጠርሙስ አነሳሁና ተጋትኩት፡፡ሙሉ በሙሉ አጋብቼ አስቀመጥኩት፡፡አስተናጋጁን ጠራሁና ጅን እንዲቀይርልኝ ነገርኩት፡፡አመጣልኝ፡፡
አዎ ከበሰበሱ አይቀር መብከት ይሻላል፡፡ሁለት ሰዓት ሲሆን በደንብ ግዬ ነበር፡፡ሳልዋረድ እንደምንም እራሴ ገሰፅኩና ሂሳቤን ከፍዬ መኪናዬን በዝግታ እየነዳሁ ወደ ቤቴ ገባሁ፡፡የምኖረው አፓርታማ ላይ ተከራይቼ ስለሆነ መኪናዬን ፓርክ አደረኩና እንደምንም እግሮቼን እየጎተትኩ ሁለተኛ ወለል ላይ ወደ ሚገኘው ባለሁለት መኝታ ክፍል ቤቴ አመራሁ፡፡ከፍቼ እንደገባሁ የቤቱ ስልክ ሲጠራ እኩል ሆነ፡፡ እየተንገዳገድኩ ሄድኩና በመነጫነጭ አነሳሁት፡፡
‹‹ሄሎ ..ማን ልበል?››
‹‹ሳምዬ ምነው? ስልክህ እኮ አይሰራም፡፡››
‹‹እንዴ እማዬ፡፡አረ ይሰራል፡፡››ስልኬን አውጥቼ ሳየው ዘግቷል፡፡
‹‹ወይ እማዬ ቻርጅ ዘግቷል.. አላየሁትም ነበር፡፡››
‹‹ምንድነው?  ሰላም አይደለህም እንዴ?››
‹‹ኸረ ሰላም ነኝ? ምን ሆንኩ፡፡››
‹‹ኸረ ወዲያ…. አፍህ ተሳስሮ የለእንዴ?
‹‹እኔ ትንሽ ከጓደኞቼ  ጋ ቆይቼ አንድ ሁለት ቢራ ጠጥቼ ነው፡፡››
‹‹በል ..ነገ እርግበን መቀበሉን እንዳትረሳ፡፡››ትዕዛዛዊ የሆነ ጠንከር ያለ አረፍተ ነገር ነው፡፡
‹‹እርግበን….እኔ ጋር እኮ አይደለም ሀገሯ ነው የምትመጣው፡፡››
‹‹እና ሀገሯ ሄዳ ትቀበላት እያልከኝ ነው?››እማዬ እያሽሞጠጠቺኝ ነው እንዴ?፡፡
‹‹እኔ እንጃ?››
‹‹በል አትጨማለቅ፡፡ሄደህ በስነስርአት  ተቀበላት፡፡ቅሬታም ካለህ ውላ ካደረች በኃላ ትነጋገራላችሁ፡፡ልጄን ገና ከመምጣቷ እንድታስቀይምብኝ አልፈልግም፡፡››
እርግበን በተመለከተ ከእማዬ ጋር ተከራክሬ ላሳምት እንደማልችል ስለማውቅ ነገሩን ማንዛዛት አልፈለኩም፡፡ እማዬ እርግበ ከእኔ ጋር ተጋብታ ምራቷ እንደምትሆን በእርግጠኝነት ለዘመድ  ወዳጁ ሁሉ አዋጅ በሚመስል  ሁኔታ ዜናውን ነዝተዋለች፡፡እርግበም የእማዬን እንዴት አንጀት መብላትና ማስደሰት እንደሚቻል ገብቷታል….፡፡
‹‹እማዬ..እሺ እንዳልሽ፡፡ስራ ከሌለኝ እቀበላታለሁ፡፡››
‹‹አይ እንግዲህ ..ስራ ካለኝ ምናምን አይሰራም፡፡ማትችል ከሆነ ከአሁኑ ንገረኝ፡፡››
‹‹ብነግርሽ ምን ልታደርጊ ነው?››
‹‹እንዴ ልጄንማ አላሳቅቃትም፡፡በከዘራ እያነከስኩ ቢሆንም ሄጄ እቀበላታለሁ፡፡››
‹‹እንዴ….አንቺ?››
‹‹ጅሎ …ታዲያ አንተ ከፈዘዝክ ምን ላድርግ?››
‹‹እሺ በቃ እማዬ እኔ እቀበላታለሁ፡፡.በይ ደህና እደሪ፡፡››
‹‹ደህና እደር….››ስልኩ ተዘጋ፡፡ወደ ኃላ ተመለስኩና በራፉን ቆልፌ ቀጥታ ወደ መኝታ ቤቴ በመሄድ ከነልብሴ ተዘረርኩ፡፡


ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍579👎2👏1
ለቅሶ ቤት ሄድኩና…

እንባዬ ደርቆብኝ ፡ ለማልቀስ ስቸገር

በድንገት ትዝ አለኝ ፡ ያደረግሺኝ ነገር

ትውስ ያለኝ ጊዜ : የሰራሺኝ ስራ

ሚፈሰው እንባዬ : እንደምን ያባራ

አልቅሼ አላቀስኩኝ : ሳላዝን በሟቹ

ድሮም ያንቺ ፍቅር ፡ ለሀዘን ነው ምቹ

🎴 እንደልቡ🎴


ቤተሰቦች #subscribe እያደረጋቹ

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍31😁102🔥1👏1
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  አስራ ሁለት


ረብሻ ሁለት!

ከሰርጋችን በኋላ ባለቤቴ ረፍቱን ጨርሶ ወደ አሜሪካ ሲመለስ ቤተሰቦቹ ቤት ነበር አስቀምጦኝ የሄደው። የሚያምር ትልቅ ግቢ፣ በአበቦች የተዋበ፣ ከዋናው “ሺላ ነጠል ብሎ በሰርቪስ ስም የተሠራ ሌላ ባለ ሦስት ክፍል 'ቪላ' ውስጥ ለብቻዬ ነው የምኖረው፡፡ ቤተሰቦቹ (እናቱና ሁለት እህቶቹ) ሲበዛ ጥሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ዋና ሥራቼው እኔን መንከባከብ እስኪመስለኝ አፈር አይንካሽ ብለው ነበር የያዙኝ። ከገባሁ በኋላ ሥራ አቁሜ ስለነበር ውሎዬ ቤት ነው። “ምን ጎድሎ በየገጠሩ ትንከራተቻለሽ?'' ብሎ ነበረ ባሌ ሥራ ያስቆመኝ፡፡ በዚያ ላይ ወደ አሜሪካ ለመሄድ ወዲያው “ፕሮሰስ'' እንደሚጀምርልኝ ስለነገረኝ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሥራ ማቆሜ አይቀርም በሚል የቤት እመቤት ሆንኩ። እውነቱን ለመናገር እኔም ወደ ውጭ መውጣት፣ ሰው ጋር መገናኜት በራሴ ምክንያት ጠልቼ ነበርና ሥራዬን ማቆሜ አላስከፋኝም። ታዲያ በሰበብ አስባቡ (እነሱ በፍጹም ቅንነት ብቼኝነት እንዳይሰማኝ በማሰብ) እሀቶቹ፣ አልያም እናቱ ከአጠገቤ አይጠፉም ነበር፡፡ በጭራሽ ብቻዬን መሆን አልቻልኩም፡፡ እሱም ባልከፋ፤ ሰብሰብ ሲሉ በአንድም በሌላም መንገድ “የሴት ልጅ ሙያ'' ስለሚሉት ነገር ሳያነሱ ያልፋሉ ማለት ዘበት ነበር። ስለ ጠላ መጥመቅ፣ ስለ ዶሮ ወጥ ጣዕም፣ ስለ እንጀራ ዓይን፣ ስለ ዳቦ ኩፍ ማለት፣ ስለ በርበሬ መቀንጠስ፣ ስለምናምን መደለዝ ይኼ ትንሽ ሳያማርረኝ አልቀረም፡፡ በተለይ የባለቤቴ እናት! ከሃያ ዓመት በፊት ሰው ቤት ሄደው ስለቀመሱት የማይረባ ዶሮ ወጥ ሳይቀር አንስተው ያማርራሉ «ሴት ልጅ እንዴት የግዜር ዶሮ ወጥ መሥራት ያቅታታል? አሁን ማን ይሙት ዶሮ እንደዚያ ይበለታል?» ይላሉ በግርምት። ጉድዎትን አልሰሙ፣ እላለሁ በውስጤ! ይህች ጥሩ ሴትዮ እንጀራ መጋገር አላውቅበትም ብላቼው ራሳቼውን ስተው የሚወድቁ ነው የሚመስለኝ፤ እጄን ታጥቤ ሲቀርብልኝ ከመብላት ባለፈ ዶሮ ይገንጠል፣ ይፈጭ ግድ አይሰጠኝም ብላቼው ደግሞ በቀጣዩ ቀን ቀብር የምንውል ይመስለኛል።

እውነቴን ነው፤ እኛ ቤት ምግብ በሕይወት ለመሰንበት ከመበላቱ ውጭ እንዲሀ ትልቅ ርዕስ ሆኖ አያውቅም። ሠራተኛችን ጽጌም ብትሆን ከእናቴ ብትሻልም ምግብ ላይ ያን ያኽል የምትደነቅ አልነበረችም። ምስኪን የገጠር ሴት ናት። ከተማ እንደገባች እኛ ቤት ተቀጠረች፤ የከተማ ምግብ የሚባለውን ሙያ እናቴ ናት እንግዲህ ያሰለጠነቻት። ይኼን ሳስብ ሳቅ ይቀድመኛል። ጓደኛዬ ሃይሚ እግር ጥሏት ስበላ ከደረሰች አንዴ ጎርሳ ትተወውና “ከእናንተስ ቤት ምግብ የእኛ ቤት ርሃብ ይሻላል'' ትለኛለች። በተለይ በሠራተኛችን ጽጌ እንጀራ እንደቀለደች ነው “ጽጌ እኮ እንጀራ ሆኖባት ነው እንጀራ የምትጋግረው'' ትልና እንስቃለን። የሆነ ሆኖ የባሌ ቤተሰቦች ከዬት እንዳገኟት እንጃ በደግ ቀን የቀጠሩልኝ ሠራተኛ በዚህ ባለሙያ ቤተሰብ መኻል ከመዋረድ አድናኛለች። ይኼንንም ችዬ ታዲያ በጣም ያማረረኝ ሲበዛ ሃይማኖተኞች መሆናቼው ነበር። ጧት ማታ ቤተክርስቲያን እንሂድ ንዝናዚያቼው ማቆሚያ የለውም፡፡መጀመሪያ እማማ (የባለቤቴ እናት)... “ያይኔ አበባ!” ይሉኛል (እንደዚያ ነው ሲጠሩኝ፣ አቤት ይኼ ስም ሲያስጠላኝ! የሆነ ሰው አምጥቶ እዚህ ግቢያቼው ውስጥ የተከለኝ፣ ከትንሽ ጊዜ በኋላ የምጠወልግና ጠርገው የሚጥሉኝ የሆነ ከንቱ አበባ የሆንኩ መስሎ ነው የሚሰማኝ፡፡) “ነገ የዓመቱ ሚካኤል ነው በጧት ይቀሰቅሱሻል ልጆቹ፤ ቤተስኪያን እንሄዳለን" “አይ! እኔ አልሄድም እማማ'' ደንገጥ ብለው አዩኝ፡፡ አደነጋገጣቼው ጾታዬ'ኮ ወንድ ነው ያልኳቸው ዓይነት ነበር ፡፡ “ምነው! ያውም ለክብረ በዓሉ ከቤተስኪያን የሚያስቀር ...?'' ድንገት የመጣልኝን ሰበብ ወረወርኩ “ፔሬድ ላይ ነኝ'' አልገባቼውም፡፡ ትልቋ ልጃቼው እየሳቀች “ንጹሀ አይደለሁም! ማለቷ ነው" አለች፡፡ የዚያን ቀን በዚህ አለፍኩ፡፡ ከዚያ በኋላ የነበረው የዬቀን ጥያቄ ግን ማቆሚያ አልነበረውም፡፡

ቤታቼው ውስጥ መንፈሳዊ መዝሙር ካልሆነ ምንም ዓይነት ዘፈን አይከፈትም፡፡ ሬዲዮ እንኳን ሲከፍቱ ሰምቼ አላውቅም፡፡ ታዲያ አፍ አውጥተው ባይናገሩትም እኔ ዘፈን ስከፍት ፊታቼው ላይ የማዬው ግራ መጋባት ይረብሸኝ ነበር፡፡ የሆነ መብረቅ ላስመታቼው የተላክሁ ዓይነት ዓይናቼው ማረፊያ ያጣል፡፡ ቀስ በቀስ የራሴን ፍላጎት ቶቼ፣ የእነሱን ለማክበር ከሙዚቃ እየራቅሁ፣ ከመዝሙሩም ሳልቀረብ ዝምታ ውስጥ እየተነከርኩ መጣሁ። ይኼ ደግሞ ድብርቴን አባብሶት ግቢው እስር ቤት እስኪመስለኝ በጭንቀት ልሞት ደረስኩ፡፡ አንዳንዴ አባቴ ጋር ሄጄ አድር ነበር፡፡ በተለይ የባሌ እናት ይኼ ነገር ፈጽሞ ደስ አይላቼውም፡፡ ምንድን ነው ይኼ ሁሉ ነገር? እላለሁ ለራሴ... ምን ውስጥ ነው የገባሁት? ታዲያ አባቴ ቤት ስሄድ እዚያ ሜክሲኮ “ላፍቶ ላፍቶ” የሚል የታክሲ ረዳት ጥሪ “ማኅደረ ሰላም'' ከሚለው ስሜ እኩል ይጎትተኛል፡፡ አምላኬ ርዳኝ ስንቴ አልኩ!

ረብሻ ሦስት!

የስልክ ሰው አይደለሁም፡፡ ሰው በስልክ ዐሥር ደቂቃ ከሚያወራኝ፣ በአካል ሙሉ ቀን ቢያወራኝ እመርጣለሁ፡፡ባለቤቴ፣ በየቀኑ አንዳንዴም በቀን ሁለትና ሦስት ጊዜ ከአሜሪካ ይደውልና ረዢም ሰዓት ሊያወራኝ ይሞክራል... ቀን፣ ሌሊት፣ ጧት፣ ማታ አይልም፤ ይገባኛል...ሚስቱ ነኝ፣ ሌላ የሚያገኝብኝ አማራጭ የለውም፣ ይናፍቅ ይሆናል፣ ግን ሁሉም ነገር ዞረብኝ፤ ስልክ አልወድም።ይኼን ባህሪዬን የሚያውቁኝ ሁሉ ያውቃሉ፣ “ውይ እሷና ስልክ'' ነው የሚባለው፡፡ ሌሊት ከእንቅልፌ መንቃት አልወድም፣ አባቴ እንኳን እኔ ከተኛሁ እንዳይቀሰቅሰኝ ቤት ውስጥ በጥፍሩ ነበር የሚራመደው፣ ረዘመ ከተባለ ያውም የሥራ ጉዳይ ከሆነ ዐሥር ደቂቃ ካወራኹ ራስ ምታት ይጀምረኛል፡፡ ጓደኛቼ “ቴክስት" ቢልኩልኝ እመርጣለሁ፡፡ የሆነ ጊዜ ባለቤቴ አንድ ሰዓት ሙሉ ያወራኝ ቀን ሲዘጋው አለቀስኩ፤ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ። ፊቴን የጋለ ጆርዬን በቀዝቃዛ ፎጣ ሸፍኜ አለቀስኩ ጩኺ! ጩኺ! አለኝ፣ ርግማን ነው ይኼ! ምንም ምንም በነፍስም በሥጋም የሚቀራረብ ነገር የሌለን ሰዎች ምን ዓይነት ነገር ነው ያገናኜን? ባሕሪው ጥሩ ይሁን አይሁን የራሱ ጉዳይ።

ለምሳ ወጥቼ ነው ብሎ በደረቅ ሌሊት ይደውላል፤ አእምሮዬ ሌሊት ነውና ስለምሰ ማሰብ አይችልም። ባሌ በሌሊት ምሳ የሚበላ ፍጥረት ነው? አይ! አሜሪካ የምለ ሰዓት ነው እላለሁ ለራሴ፣ ይሁና በዚህ ሰዓት የሆነ ነገር እያላመጠ የሚያወራ ሰው በእንቅልፍ ልብ መስማት ያቅለሸልሻል፡፡ ስልኬን ከዘጋሁ በቤት ስልክ ዋናው ቤት ደውሎ ደህና አይደለችም እንዴ? ይላል እየተንጋጉ መጥተው በደረቅ ሌሊት በሬን ያንጓጓሉ፡፡ የሩቅ ትዳር ርግማን ነው፣ ዝም ብሎ ሲያወራ ሬዲዮ ይመስለኛል፡፡ ስሜን የሚጠራ የሆነ ዜና አንባቢ…“ማሂዬ የኔ ማር!” አጠራሩ ይዘጋኛል፡፡ የAND3 መራራቅ በወሬ ሊሞሉ መጣር፤ እንዲያውም ሌላ ነገር ያምረዋል፣ በስልክ ስለ ሴክስ ማውራት ምናምን፤ በራሴ አዝናለሁ በምርጫዬ ድድብና ራሴን ረግመዋለሁ። አዲስ አበባ የተቀመጠ የከሰል _ ፍም፣ _ አሜሪካ በረዶ ላይ ተቀምጦ ሊሞቅ እንደሚታገል ሰው ምን ምስኪን አለ? እንዲህ ዓይነት ሕይወት...
👍353
የእሱ ችግር አይደለም ድድብናዬ ነው። ከአንድ አብርሃም ለመሸሽ አሜሪካ ድረስ መሮጥ ምንድን ነው? ፈረስ ጭኖ፣ ጦር አሰልፎ አሳደደኝ? ቆይ ባላገባስ?...እዚህ መሥሪያ ቤቴ ስንት የሚመኙኝ ወንዶች ነበሩ፣ አንድ ወንድ ስለገፋኝ ስንት ሚሊዮን ሕዝብ የሚኖርባት አገሬን፣ ሥራዬን፣ ፀሐዬን፣ ሰፈሬ ሜክሲኮን፣ አዲስ አበባዬን ትቼ መፈርጠጥ አልተጋነነም? ምን ዓይነት ፈሪ ብሆን ነው? አስባለሁ...ስለ አብርሽ አስባለሁ፤ ከፍተኛ በስልክ ያወራብኝ ያውም ረጅሙ አሞኝ ሊጠይቀኝ የደወለ ጊዜ ነበር፡፡ አምስት ደቂቃ ቢሆን ነው፡፡ ከፊልድ ስመለስ ታመምኩ፣ በአጋጣሚ ሲደውል መታመሜን ነገርኩት።

“ሆስፒታል ሄድሽ?''

“አልሄድኩም::''

“ተዘጋጅና ጠብቂኝ መጣሁ እንሄዳለን” በቃ ትዕዛዝ ነበር።

ሆስፒታል የማልወደው ልጅ ተዘጋጅቼ ጠበቅሁት አብሬው መሄዴ ነበር ያስደሰተኝ። በኮንትራት ታክሲ መጣ እና ወሰደኝ፡፡ እንደዚያን ቀን ተደስቼ አላውቅም። ሁልጊዜ

በታመምኩ ብዬ እስከምመኝ። ከእኔም የባሰ ስልክ የማይወድ ሰው ነበር፤ ለምንድን ነው ግን ያላገባኝ? ወይስ የምፈልገውን ለማግኜት እንዴት መዋጋት እንደነበረብኝ አላወቅሁም...?

ሰላም ውልብ ሲል!

መቼም ሁሉም ሰው ለአፍታም ቢሆን ከዚህ ዓለም ሁካታ ራሱን የሚደበቅበት ቦታ ይኖረዋል።ይኼ ደግሞ _ ከሕፃንነታችን የሚጀምር የነፃነት ፍላጎት ሳይሆን አይቀርም። ለዚያ ሳይሆን ይቀራል ሕፃናት በዬአልጋና ጠረንጴዛ ሥሩ የራሳቼውን ዓለም ፈጥረው ቁጭ የሚሉት? ባለቤቴ ዮናስ ከማያቋርጥ የወሬ ጎርፉ በአንዱ ስለ መርካቶ አውርቶኝ ነበር። አባቱ ሳይሞቱ በፊት መርካቶ የጣቃ መሸጫ ሱቅ ነበራቸው። እና በዚያ የመርካቶ ሁካታ መኻል በእነዚያ የጣቃ ጨርቆች መጋረጃ ነገር ሠርቶ ውስጡ ይደበቅ ነበር። ሰላም ይሰማኝ የነበረው በእነዚያ ግርዶሾች ውስጥ ነበር ይላል። ነገሩ የልጅ ዕቃ-ዕቃ ጨዋታ ይምሰል እንጂ ስሜቱ ይገባኛል። እነዚያ የጣቃ ግርዶሾች የኮንክሪት ግድግዳ አልነበሩም፣ዕድሚያቼው አጭር ነበር ወይ ይሸጣሉ አልያም ተጠቅልለው ይደረደራሉ። ግን ለቅጽበት የሰጡት ሰላም እስከአሁን ትዝታው ሆኗል። የአብርሽ ቤት ለእኔ እንደነዚያ የጣቃ ግርዶሾች ነበር። ለጊዜው እራሴን የጋረድኩበት ትዝታው የቀረ ግርዶሽ። አብሮነታችን ከምን እንደተሠራ ስላልገባኝ ነበር ዘላለማዊ ካልሆነ ብዬ ችክ ያልኩት፤ ወይ እሱ በእኔ ውስጥ ተደብቆ ነበር፣ አልያም እኔ በእሱ ውስጥ ተደብቄ ነበር። ዕቃ-ዕቃው ፈረሰ ሲባል የኔ ነፍስ የዕቃ-ዕቃውን ሕግ ጥሳ ተነጫነጨች፤ ፍቅር እፍርታም አደረገኝ። በዚህ ሁሉ የሕይወቴ ረብሻ መካከል በጣት የሚቆጠር የሰላም ጊዜ የነበረኝ እሱ ጋር እዚያ ቤት ነበርና ዛሬም ቢሆን በራሴ አልፈርድም። ለምንድን ነው ማንም በቀላሉ ሊያደርገው የሚችለውን ቀላል ነገር ሁሉ እሱ ሲያደርገው እንደ ትልቅ ተአምር፣ እንደ ትልቅ ታሪክ ነፍሴ ውስጥ ታትሞ የሚቀረው? በእነዚያ አራት ዓመታት የማይረሱኝ እስከ አሁን ሳስባቼው ልዩ ስሜት የሚሰጡኝ ጊዜያት ነበሩ። ጥቂት

ናቸው በጣም ጥቂት። የሆነ ቀን ሲደውልልኝ ፔሬድ ላይ መሆኔን ነገርኩት፤ ፔሬድ ላይ ስሆን በተለይ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት ስቃይ ነበሩ። እሱ ቤት ከሄድኩ የግድ አብረን መተኛት እንዳለብን አእምሮዬ አምኖ ነበርና ፔሬድ ላይ ከሆንሽማ ሌላ ጊዜ እንገናኛለን እንደሚለኝ ነበር ያሰብኩት። “እና መምጣት አትችይም?'” አለ ግራ ገብቶት። “መምጠትማ እችላለሁ ግን . . ." ሳቀና “ችግር የለም ! ነይና እዚህ አርፈሽ፣ ተጫውተሽ ትሄጃለሽ፤ አሪፍ ምሳ ሰርቻለሁ _እንደምታውቂው ሙዚቃም አለ" አለኝ የዚያን ቀን ለምን እንደዚያ ተለማመጠኝ እላለሁ። ምናልባት የሆነ ብቸንነት ተሰምቶት ይሆን? አላውቅም:: እቤቱ እንደደረስኩ ሻወር ወስጄ በቦርሳዬ የያዝኩትን ፒጃማ ለብሼ ጋደም አልኩ። የሚስትነት ስሜት እስከሚሰማኝ ተንከባከበኝ። ምሳ በላን፣ሻይ አፈላልኝ፤ ከዚያ በፊት ሕመሜ ጋር ከመታገል ውጭ ምንም ዓይነት ማስታገሻ መድኃኒት ወስጄ አላውቅም _ ነበር። ሄዶ “አይቦፕሮፊን' የሚባል የሕመም ማስታገሻ መድኃኒት ገዝቶልኝ መጣ። አጠገቤ ቁጭ ብሎ ስለ ጽሁፎቹ አዲስ እዬጻፈ ስለነበረው መጽሐፍ አወራኝ። እንደዚያን ቀን ረዘም ላለ ጊዜ አውርቶኝ አያውቅም። ከምሳ ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሸቱ አንድ ሰዓት አካባቢ ከአጠገቤ አልራቀም። የተሰማኝ ምቾትና ሰላም እስከ አሁን ውስጤ አለ። እንዴት ውብ ስሜት ነበር!! የዚያን ቀን እሱ ጋር ማደር ፈለግሁ። ሁል ጊዜ ቤቱ ማደር እፈልግ ነበር። እሱ ደግሞ በግልጽ “ማሂ ሰላም! አብረሽኝ ብታድሪ በጣም ነው ደስ የሚለኝ፤ ግን ያላገባሽው ሰው ቤት በጭራሸ ማደር የለብሽም''ይለኛል፡፡ “ምንድን ነው ፍልስፍና ነው?'' እለዋለሁ፡፡ “ልትይው ትችያለሽ፤ እንዲሁ የግል እምነቴ ነው። ለአንዳንድ ነገሮች ቦታ መተው አለብን። ለምሳሌ ለትዳር፣ አብሮ ማደር ለትዳር መተው ያለበት ነገር ነው የሚል

ጽኑ እምነት አለኝ። ቢያንስ ስለ ትዳር ስናስብ ልንጓጓለት የሚገባ የሆነ ነገር መተው አለብን. . . ስናገባ ለመጀመሪያ ጊዜ አደረግነው የምንለው ነገር ... ቀላቀል ሐሳብ ይመስላል፣ ግን ለምን እንደሆነ እንጃ ማደር የሚባለውን ነገር በቀላሉ ማዬት እልችልም' ይለኛል። እኔ ግን ቀን አብረን ስንውል ካደረግነው ነገር የተለዬ ሌሊት የሚፈጠር ምን ተአምር ይኖራል እያልኩ ውስጤ በቅሬታ ይሞላል፤እሱ ጋር ማደር እፈልግ ነበር። የዚያን ቀን እንደዚያ በሰላም ውዬ በኮንትራት ታክሲ ወደ ረብሻዬ ተመለስኩ። በአራት ዓመታት ቆይታችን አንድም ቀን አብረን አድረን አናውቅም። ታዲያ ባለቤቴ ዮናስ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ሀዋሳ አብረን ስናድር (ያኔ ገና አልተጋባንም) በነገሮች ብረባበሽም እንደ ትልቅ ተአምር ነበር ያየሁት። እሱ ጋር ማደሬን ሳይሆን ወንድ ጋር ማደሬን። እንደዚህ የመሳሳሉ የሰላም _ ውልብታዎች እንደ ትልቅ ትዝታ በዬቀኑ እእምሮን ይሞሉታል፤ እንደ ጣቃ እየተተረተሩ የሚያልቁ ግርዶሾች።

***።*።

አረገዝኩ! ሕይወት ቀልድ አታውቅም፤ የባልዬው ሲገርመኝ ነፍስ አልባ ሥጋዬ ውስጥ ሌላ ነፍስ አደረ፡፡ ካገባሁ ከዓመት በኋላ ነበር ያረገዝኩት፣ ያገባሁት ከሆነ ሰው ለመሸሽ እንደሆነው ሁሉ ያረገዝኩትም ይኼን ሸሽቴን ሙሉ ያደርገዋል በሚል ስሌት ነበር፡፡ ባለቤቴ ከአሜሪካ ተመልሶ መጥቶ እኛ ጋር ወዲያ ወዲህ እያለ ሰርግና ምላሽ ሆኖለታል፤ በጣም ደስ ብሎት ስለነበር የሚይዝ የሚጨብጠውን አያውቅም፤ እኔ ግን __ ብዥዥ እያለብኝ ነበር፡፡ እንደ ሴቶቹ ጧት አላስመለሰኝም፣ ምግብ አልዘጋኝም፡፡ እንዲያውም በሕይወቴ እንደዚያን ሰሞን በልቼ አላውቅም፡፡ በቃ ቁጭ ብዬ ያገኜሁትን ወደ አፌ መላክ ሆነ። እርግዝና _ ከሚለው ቀጥሎ አእምሮዬ ውስጥ የሚያቃጭለው ማስወረድ የሚል ቃል ነበር፡፡ ያስጠላኝ ብቼኛ ነገር ባሌ እና የቡና ሺታ ብቻ ነበር፡፡ ሳወራ ይደክመኛል በሚል ሰበብ ባሌ ጋር ለዛ ቢስ ማስመሰል የሞላው ወሬ ከማውራት ዳንኩ፡፡

እርግዝናው ምቾት አልሰጠኝም በሚል ሰበብ አልጋ ለዬሁ፡፡ ለብቻዬ ሰፊ አልጋዬ ላይ ተኝቼ ያለመሳቀቅ ስለማፈቅረው ሰው ማሰብ፣ የማፈቅረውን ሰው መርገም አንዳንዴም በሹክሹክታ ለብቻዬ _ ማውራት _ ጀመርኩ፡ ደግሞ የክፋቱ ክፋት በመጀመሪያወቹ የእርግዝናዬ ወራቶች መልሼ ለማሰብ እንኳን እስኪከብደኝ የማልቋቋመው የወሲብ ስሜት ይሰማኝ ነበር፡፡ ቤተሰብ የተረገዘው ልጅ ወንድ ነው ሴት? እያለ ይነታረካል፡፡ አባቱን ይመስላል እናቱን እያለ ይተነብያል (ሲወለድ ሊያዩት ምን ሥራ አስፈታቼው?) ወንድ ይሁን ሴት፣ እኔን ይምሰል ይኼን አብሬ
👍334