የውብዳር ግራ ገባት…የባለቤቷ ነገረ ስራው አላማራትም፡፡ ከእሷ ጋር አብሮ ለማየት የሚጓጓለት ፊልም ምን አይነት ነው? ስትል በውስጧ አሰላሰለች፡፡ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ይሄንን የመሰለ ግብዣ ከእሱ ቀርቦላት አያውቅም፡፡
‹‹እየቀለድክ ነው?›› አለችው፡፡
በፍፁም በህይወቴ እንደዛሬ አምርሬም አላውቅም፡፡ አንቺ መሪ ተዋናይ ሆነሽ የተወንሽበትን ፊልም አብረን ብናይ ምን አለበት? ምንም ቢሆን እኮ ታማኟና ተወዳጇ ባለቤቴ ነሽ፡፡ >> በማለት ላፕቶፑን ከፈተውና ወደ እሷ አስጠጋላት፡፡በፍራቻና ግራ በመጋባት መመልከት ጀመረች፡፡ከጉሮሮዋ መድረቅ የተነሳ አፏን የምታረጥብበት ምራቅ አጣች፡፡ ሠውነቷ ሲንቀጠቀጥና እየዛለ ሲሄድ ለራሷም ይታወቃታል፡፡ መንቀሳቀስም ሆነ መናገር አልቻለችም፡፡ ከምትመለከተው ፊልም ላይም ፊቷን ዞር ማድረግ አልሆነላትም፡፡ እስኪጠናቀቅ አየች፡፡
ሠሎሞን ማለቁን ሲያይ ዘጋውና ከጐኗ ተነስቶ ፊት ለፊቷ ተቀመጠ፡፡
‹‹እሺ አሁን መነጋገር የምንችል ይመስለኛል፡፡ >>
ለመናገር ከንፈሯን ማላቀቅ አልቻለችም፡፡ በፍራቻ የቀዘቀዙ ዓይኖቿን አንከባለለችበት፡፡
‹‹መልስ ስጪኝ እንጂ?››
<ምን ልበልህ?»
‹‹መነጋገር አለብን እኮ ነው የምልሽ፡፡ >>
<<መቼ?>>
<<ዛሬ አሁን እዚሁ::>>
‹‹አልችልም ነገ፡፡›› እየተጐተተች
ከተቀመጠችበት ለመነሳት ስትሞክር ተንጠራርቶ ክንዷን ጨመቀና መልሶ አስቀመጣት፡፡
መነጋገርማ አለብን‹‹እንዴት ነው ይሄ ጎረምሳሽ….በደንብ አድርጎ ነው አይደል የሚያርስሽ..አዎ! ሁለት ስራ ፈት አውደልዳየች በእኔ በሞኙ ብር በየቤርጎው እየተሸከረከራችው ስትምነሸነሹና አለማችሀ ስትቀጩ ...ወይ ነዶ!›› ተንዘረዘረ.. በጥፊ ሊያላጋትም ፈለገ፡፡መልሶ ተወው፡፡
‹‹እሺ ምን ይሻላል?››
<<ምኑ?>>
‹‹ምኑ ትለኛለች እንዴ?…..ትሰሚያለሽ! እንደውም ካንቺ ጋር መነጋገር አልፈልግም፡ ውሳኔዬን ግን በጥሞና እንድታደምጪኝ እፈልጋለሁ፡፡ ከአሁን ሠዓት ጀምሮ የግል ዕቃዎቼን ብቻ ይዤ ቤቱን ለቅቄልሽ እወጣለሁ፡፡ የምትጠቀሚበትን መኪና አንድ ገዝቼልሻለሁ አሁንም ያንቺው ነው፡፡ ቤቱንም ከጎረምሳሽ ጋር ቅበጪበት... ጨፍሪበት... እንዳሻሽ ሸርሙጪበት፤ ስሙ ባንቺ ስላልሆ ግን የመሸጥ የመለወጥ መብት የለሽም፡፡ ከዛ በተረፈ ከዛሬ ጀምሮ ለልጆቼ ከሚያስፈልገዉ ውጪ በስተቀር ሠባራ ሳንቲም ከእኔ አታገኝም፡፡ ወደ ክስ እሄዳለሁ ብትይ ግን ይሄንን ጉድሽን በአስር ሺ ኮፒ አባዝቼ ፣ለእነዛ ተመፃዳቂና ጉረኛ ዘመዶችሽ በነፍስ ወከፍ አድልልሻለሁ፡፡ በዛም ብቻ አላበቃም በጠበቃዬ በኩል ለፍርድ ቤቱም በማስረጃነት አቀርበዋለሁ፡፡ ከዛ በኋላ ምን አልባት ከእኔ ንብረት መካፈል ብትችይ እንኳን ከዘመዶችሽና ከጎረቤቶችሽ የሚደርስብሽን ውርደት ተቋቁመሽ እዚህ ከተማ ውስጥ መኖር የምትችይ አይመስለኝም፡፡ ለማንኛውም የሚሻልሽን ከውሽማሽ ጋር ተማክረሽ መወሰን ትችያለሽ፡፡›› በማለት ተነስቶ እርምጃ ከጀመረ በኃላ ቆሞ ንግግሩን ቀጠለ፡፡
‹‹...ሌላ አንድ ነገር ይቀረኛል፡፡ በማንኛውም ሠዓት ልጆቼን ማየት ስፈልግ መኪና እልካለሁ ፣ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ትልኪልኛለሽ፡፡ ሳስብሽ ትክክለኛ ሚስት ብቻ ሳይሆን ትክክለኛ እናትም የመሆን ብቃቱ ያለሽ አይመስለኝም ፡።>>
እንባዋን እያረገፈች ፣አንደበት ተሳስሮ ፣ሠውነቷ በድንጋጤና በፀፀት ተኮማትሮ እያያት ያለ ምንም ሀዘኔታ ጥሏት ወደ መኝታ ቤቱ ገባ፡፡ እቃዎቹን ሠብስቦ ቤቱን ጥሎላት ሲወጣ እሱ ከእሷ ውጭ የወሰለተባቸው ከበርካታ አጋጣሚዎች ውስጥ አንዱ እንኳን ትዝ አላለውም፡፡ልክ ዕድሜ ዘመኑን ሙሉ ሌላ ሴት በዓይኑ ቀና ብሎ ሳያይ በታማኝነት የኖረና ድንገት መከዳቱን አውቆ ልቡ የተሰበረ ሰው አይነት ነበር የውሳኔው ቅፅበታዊነት..፡፡
✨ይቀጥላል✨
ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰቦች
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

👍87❤14
የፍቅር 'ርግቦች
ክፍል ሰባት፦ በሰላም ሂድ
©ሃሴድ አጋፔ ፍቅር
“…ቲርርርርርር!…”
“…ቲርርርርርር!…”
“…ቲርርርርርር!…”
የዛን ቀን … ስልኬ በማለዳ ሲጮህ በእንቅልፍና በመንቃት መካከል ሆኜ አየሁት።
ደብዘዝ ያለ ጨለማው ክፍል ውስጥ የሳሌም ስም የስልኬ መስታወት ላይ ሲያበራ ደንግጬ አነሳሁት “…ሄሎ…”
“…ሳዬ…” አለችኝ ሳሌም “…የኔ መልዐክ አሞት ሆስፒታል ነው ያለው ዛሬ ልትመጪ ትቺያለሽ…”
ልቤ በውስጤ ሲደነግጥ ይሰማኛል። ላለፉት አራት ቀናት በራሴ ነገሮች ስዋከብ ጊዜ አጥቼ ዳሪክን ለመጠይቅ አልሄድኩኝም ነበር።
“…ወይ ምን ሆነ? ምን ተፈጠረ? ምን አገኘው?....” ጥያቄን በጥያቄ ላይ አከታተልኩ
“…ትላንት ትንሽ አሞት ሆስፒታል ነው ያደርነው። ብዙም ክፉ አይደለም። ብቻዬን ስልሆንኩኝ ነው። ከቻልሽ ነይልኝ…” የሳሌም ድምጽ ከድካም ወይም ከሃዘን ድክም እንዳለው ያስታውቃል።
“…እሺ! … እሺ!...አሁን እመጣለሁ…” ብዬ ስልኬን ዘጋሁና መዘጋጀት ጀመርኩኝ።
ያ ቀን የጀመረው እንግዲህ እንደዚህ ነው። አንዳንድ ቀን ከእሁድ እስከ ከእሁድ ብቻ አይደለም። አንዳንድ ቀን መንጋትና መምሸት ብቻ አይደለም። አንዳንድ ቀን የጸሐይ በምስራቅ መውጣትና በምዕራብ መጥልቅ ብቻ ሆኖ አይሄድም። አንዳንድ ቀን በሃያ አራት ሰዐት ብቻ አያልቅም ። አንዳንድ ቀን ለየት ያለ ነው። ቀኑ ይዞ የሚመጣው ደስታ፣ ሃዘን፣ ተሰፋ፣ ድል፣ ድካም፣ ብርታት ቀኑን በተለየ በልብ ማህደራችን፣በአእምሮችን የትውስታ ኮሮጆ ውስጥ ለዘመናት እንዲቀመጥ ያደርገዋል።
ይህ ከነዚህ ቀናት አንዱ ነው። ረጅም ቀን ነው።
ሆስፒታሉ ውስጥ ስደርስ ሳሌምና ቀድሞኝ የደረሰው ታዴ ቁጭ ብለዋል።
“…ዳሪክ እንዴት ነው?...” ሁለቱንም ሰላምታ እየሰጠሁኝ ጠይቅኩኝ።
“…ደህና ነው። አሁን የሆነ ምርመራ ይደረግለት ብለው ውስደውታል።…” ሳሌም መለሰች
“…ትገርሚኛለሽ እኮ ሴሊና…” ታዴ ወደ ሳሌም ዞረ “…እውነቱን ብትናገሪ፣ ሃቁን ብትጋፈጪ አይሻልም?...”
“…ማለት? አልገባኝም? የምኑን እውነት?...” ሳሌም ጥያቄውን በጥያቄ መለሰች
“…ዳሪክ ትንሽ አይደለም ያመመው። ታሟል። በጠና ህመም ላይ ነው። እውነቱ ይሄ ነው። ያለበት ሁኔታ ሳያንስው ይሄው ስንት ጣጣ እየበዛበት ስንት ጊዜ ነው ሆስፒታል የሚመላለሰው። እስከ መቼ ነው እውነታውን የምትክጂው የኔ ልጅ?...” ታዴ ኮስተር ብሎ ሳሌም ላይ አፈጠጠባት።
ሳሌም አባቷን አተኩራ እያየች ለመልስ ስትዘጋጅ ከዳሪክ ሃኪሞች አንዱ መጣና ታዴን ማነጋገር እንደሚፈልግ ተናግሮ ይዞት ሄደ።
“…እስክ እዚህ ድረስ የከፋ ነው እንዴ ህመሙ ሴለም?...”
“…እሱ ዝም ብሌ ነው ባክሽ ሳዬ። እነዚህ ሃኪሞች የማይሉት ነገር የለም። እነሱን እየሰማ ነው። ትላንትናና ዛሬማ ከነሱ እግር ስር ነው።…”ሳሌም ግድግዳው ላይ አይኗን ተክላ በሃሳብ ሄደች።
የሁለቱን ሁኔታ ሳይ በአባትና በልጅ መካከል ክፍተት፣ ሰፊ ልዩነት እየመጣ መሰለኝ።
ለደቂቃዎች ሁለታችንም ዝም ብለን ቁጭ አልን።
ከዛም ሳሌም መናገር ጀመረች።
“…አውቃለሁ….”አለች ሳሌም “…አውቃለሁ ብዙዎች በዳሪክ ሁኔታ ተሰፋ ቆርጠዋል። ከሁሉም ሰው አይን ውስጥ የማየው ተስፋ የመቁረጥ ነው። እኔ ግን ተስፋ አልቆርጥም። አለም በሙሉ፣ የሰው ልጆች ሁሉ በአንድ ላይ በዛ በኩል ተሰብስበው ቢቆሙና ተስፋ ቢቆርጡ እኔ ግን ለብቻዬ ከፍቅሬ ጋር ቆሜ ማመኔን እቀጥላለሁ። አምናለሁ። አንድ ቀን አይኖቹ ተከፍተው እንደማይ አምናለሁ።
አይኔንም፣ ልቤንም፣ ጆሮዎቼንም ከፍቼ እየሰማኋት ቀጠለች።
“… ሳዬ ታስታውሺያለሽ የኦፒትሚስት (አውንታዊ ሰው)፣ የፒሲሚስት (አሉታዊ ሰው)ና በብርጭቆ ውስጥ ያለው ግማሽ ውሃ ታሪክ …”
ራሴን ነቀነቀኩ “…አስታውሳለሁ…”
ሳሌም እንደገና ታሪኩም ትነግረኝ ጀመር። “….በጠረጴዛው ላይ ብርጭቅቆ አለ። ብርጭቆው ውስጥ ግማሽ ድረስ ውሃ ሞልቷል።አውንታዊው ሰው መልካሙን አየና ‘…ይህ ብርጭቆ ግማሹ ደረስ ሙሉ ነው..’ አለ። …አሉታዊው ሰው ደሞ ጉድለቱና አየና ‘…ይህ ብርጭቆ ግማሹ ደረስ ጎዶሎ ነው…’ አለ። …ሁላችንም ይህን ታሪክ እዚህ ድረስ እናውቃለን። እኔ ግን ከነዚህ ሁለት ሰዎች በተጨማሪ የእምነት ሰው ቢመጣ ምን ሊል ይችላል? ብርጭቆው ውስጥ ያለው ውሃ እንዴት ይመለከታል? ብዬ አሰብኩኝ። የእምነት ሰው ቢመጣ፣ …ያመነ ሰው ቢመጣ ያን ብርጭቆና ውሃውን አያያም። ይልቅስ የውሃውን ምንጭ ይመለከታል። ያመነ ሰው እንዲህ ይላል ‘…የውሃው ምንጭ ስላማይቋረጥ ይህ ብርጭቆ ሞልቶ ይትረፈረፋል።
ሳሌም ፈገግ ብላ ቀጠለች ….ስለዚህ እኔ አባባሉን እንዲህ አስተካከልኩት
An optimist says “the glass is half full.”
አውንታዊው ሰው ‘…ይህ ብርጭቆ ግማሹ ደረስ ሙሉ ነው..’ ይላል
A pessimist says “the glass is half empty.”
አሉታዊው ሰው ደሞ “…ይህ ብርጭቆ ግማሹ ደረስ ጎዶሎ ነው…” ይላል
A man of faith says “don’t worry guys there is always a refill.”
የእምነት ሰው ደሞ “…አትጨናነቁ ብርጭቆው ሁሌም ሞልቶ ይትረፈረፋል።…” ይላል
..ወደ ኔ ሁኔታ ስመልሰው። ዳሪክን በተመለከተ አሉታዊ ሰዎች ጉድለቱን አይተው ‘…ኦ ዳሪክ እኮ ሙት ነው...’ ብለው ሊያስቡ ይችላሉ። አውንታዊ ሰዎች ደሞ ‘..ኦ ዳሪክ ትንፋሹ አለ፣ ልብ ምቱ ይሰማል ስለዚህ ተሰፋ አለው…’…ሊሉ ይችላሉ። እኔ ግን የእምነት ሰው ነኝ። አማኝ ነኝ። ከዚህ ሁሉ አሻግሬ የህይወትን ምንጭ፣ ጌታን አያለሁ። አምናለሁ። ስለዚህ የኔ መልዐክ ጌታ አዲስ ህይወት ሲሰጠው፣ ሲነቃ፣ ሲነሳ፣ ሲራመድ፣ ሲያወራኝ፣ እጄን ይዞ አብሮኝ ሲጓዝ፣ ‘..የምውድሽ..’ ሲለኝ፣ አይን አይኔን እያየ ሳያቋርጥ ሲስቅ … የኔን መልዐክ ሳገባው፣ አብረን በአንድ ቤት ስንኖር፣ ስንደሰት፣ስንጣላ፣ስንላፋ፣እንደ ልጆች ስንሯሯጥ፣ ደሞ ስንኮራረፍ፣ መልሰን ስንታረቅ፣ አብረን በመንገድ ላይ እጅ ለእጅ ተያይዘን ስንጓዝ፣ የልደት ስጦታ ስንለዋወጥ፣ የመጀመሪያ ልጅ ስንወልድ፣ የህጻኑ ለቅሶ ሌሊት ቁጭ አድርጎ ሲያሳድረን፣ ልጅ ማሳደግ ስንማር፣ ደሞ ሌሎች ልጆች ሲኖሩን፣ ልጆቻችንን ስናሳድግ፣ ልጆቻችን እንዴት እንደተገናኘን ሲጠይቁን፣ የፍቅር ታሪካችንን ስንነግራቸው፣ ደሞ ልጆቻችን ጎርምሰው ሲያስቸግሩ ‘..ምን እናድርግ?..’ ብለን ስንጨነቅ፣ ስንመካከር፣ የህይወትን አቀበት ስንወጣ ቁልቁለቱን ስንወረድ፣ የመኖር ተራራ ላይ ወጥተን የድልን ዜና ስናበስር ፣ደሞ ሸለቆ ውስጥ ስንድረስና አብረን ስንጸልይ፣ አብሮ እድሜያችን ሲጨምር የመጀመረያው ሽበት ጥቅጥቅ ያለው ጸጉሩ ላይ ሲወጣ ‘…ውይ የኔ ፍቅር አረጀህ እኮ ስለው…’…. እሱም መልሶ ‘..አይ አላረጀሁም…’ ብሎ ሲከራከረኝ፣ ስናረጅ፣ ወገባችን ሲጎብጥ፣ ተደጋግፈን የቤታችንን ደረጃ ስንወጣና ስንወርድ ይህ ሁሉ ይታየኛል። አምናለሁ። አየዋለሁ…አምናለሁ…አየዋለሁ። አምኜ አምኜ መልሼ ደሞ አምናለሁ። ያመንኩትን ደሞ አየዋለሁ። ይሄ ለሰዎች ጤናማ ላይመስል ይችላል። ያመመኝ ሊመስላቸው ይችላል። ግን እኔ ምንም አይገደኝም። ሰዎች ምንም ቢያስቡ አይደንቀኝም። እኔ አማኝ ነኝ እንጂ ታማሚ አይደለሁም። በጌታ አምናለሁ። በፍቅር አምናለሁ። ይህ ማመን እንጂ መታመም አይደለም። የምለው ትንሽ ገብቶሻል ሳዬ?....”

👍55❤6
" አዎን በደንብ ይገባኛል የኔ ቆንጆ!" እንባዬ አይኔ ውስጥ ግጥም ብሎ አያታለሁ። የሚገርም ነው! …ሳሌም ፍቅሯ፣ እምነቷ የሚገርምና የሚደንቅ ነው።
“የታመምኩኝ ይመስልሻል ሳዬ?”
“አይመስለኝም በጭራሽ ሴለም! በፍጹም እንደዛ አላስብም!...”
ዝም ብላ ብታወራኝ፣ ብትቀጥልልኝ ደስ ባለኝ ነበር። ግን ታዴና ሃኪሙ መጥተው ሳሌምን ማነጋገር እንደሚፍልጉ ነገሩን።
“…እሺ … ነይ ሳዬ እንሂድ…” ስትለኝ ተከትዬ ሄደኩኝ። አንዲት ትንሽ ቢሮ ውስጥ ገብተን ሶስቱም ሲቀመጡ ወንበር ስላልነበር እኔ ጥግ ላይ ቆምኩኝ።
ክፍሉ ለትንሽ ሰከንዶች በጸጥታ ተዋጠ።
ቀጥሎም ሃኪሙ መናገር ጀመረ “…እንግዲህ ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ከ ሚስተር ሃይሉ (ታዴ መሆኑ ነው) ጋር በዳሪክ የጤና ሁኔታ ስንነጋገር ነበር። የዳሪክ የጤና ሁኔታ እየባሰ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። …ኮማ ውስጥ እንዳለ፣ በማሽኖች ርዳታ እየኖረ እንዳለ የታወቀ ነው። አሁን ደሞ ከደረሰበት አደጋና በተለያየ ጊዜ ካጋጠሙት ኢንፌክሽኖች የተነሳ ሁለቱ ኩላሊቶቹ በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድተዋል። አሁን ዳያለሲስ ያስፈልገዋል። በ'ርግጥ እሰክ መጨረሻው ዳያላሲስ ሊያስፈልገውም ላያስፈልገውም ይችላል። ”
“ታዲያ ምን ችግር አለው የሚያስፈልገው ነገር ይደረግለታ …. ሳሌም ነበረች
“ዳያለሲስ ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ ? ” ንግግሯን ሃኪሙ አቋረጣት
“…አላውቅም!...” ሳሌም መለሰች
ሃኪሙ አጠር አድርጎ ኩላሊቶቹ ለተጎዳ ወይም ለማይሰራ ሰው በማሽኖች ደሙ እንደሚጣራ አስረዳንና ቀጠለ “…ጥያቄው ግን። ለዚህ ልጅ እንደገና ሌላ መስመር ሰውነቱ ውስጥ መክተት አለብን ወይ? በሌላ ማሽን የሰውነቱን ስራ መስራት አለብን ወይ? ስቃዩ እጅግ አልበዛበትም ወይ? ከ አደጋው ቡሃላ እንኳን ስንት ጊዜ ለህክምና እኛ ጋር እንደተመላለሰ አስታውሱ። ህይወቱን ለማቆየት ብለን ብዙ ስቃይ አልጨመርንበትምን?.....እነዚህና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ከህግ ተወካዩቹና ሚስተር ሃይሉ ጋር ተነጋግረን ምናልባት ይህን ልጅ በሰላም ከስቃዩ፣ ከህመሙ እንዲለይ፣ እንዲሄድ ብናደርግ የሚለውን ሃሳብ አንስተን ጊዜ ውሰደን ተወያይተን ተስማምተናል። አሁን እዚህ ያለነው ለአንቺ ውሳኔውን ለመናገርና በአካልም በስነ ልቦናም ዝግጁ እንድሆኚ ለማድረግ ነው። …ትክክል ነኝ አይደል?...” ወደ ታዴ ዞረና ጠየቀ።
ታዴ ራሱን በ አውንታ ነቅንቆ አቅርቅሮ ዝም አለ። የሳሌምን አይኖች ለማየት የደፈረ አይመስልም።
ዱብ እዳ ነው። እኔ በድንጋጤ ሰውነቴ ይንዘፈዘፍ ነበር።
ሳሌም አየኋት። በፊቷ ላይ ምንም አይነበብም።
“..በሰላም እንዲሄድ ማለት ምን ማለት ነው?....” ተረጋግታ ጠየቀች።
ሃኪሙ መናገሩን ቀጠለ “…እውነታውን ካየነው ዳሪክ እየተነፈሰ ያለው ሙሉ በሙሉ በማሽን ርዳታ ነው። ማሽኖችን ካቆምናቸው ዳሪክ በሰላም ከዚህ አለም መሄድ ይቻላል። የሚጠበቀው ከሚወዱት ሰዎች ‘…በሰላም ሂድ…’ የሚል ፈቃድ ብቻ ነው… ‘..በሰላም ሂድ!..” ማለት ለኛ፣ በህይወት ላለነው ከባድ ውሳኔ ነው። ግን ደሞ እንደ ዳሪክ ላሉ ታማሚዎች ርፈትና ከስቃይ መገላገል ሊሆን ይችላል።…”
መጀመሪያ የሰማሁትን ማመን አልቻልኩም። “…በሰላም ሂድ!..” ሁለት ቃላቶች። እንዴት ቀላል ሁለት ቃላቶች ናቸው። ይህ ሃኪምስ እንዴት ቅልል አድርጎ ነው የሚያወራው። በሰላም ሂድ ማለት እኮ ይሙት ማለት ነው። በአእምሮዬ ቃላቶቹ ይመላለሱ ጀመር....
በሰላም ሂድ!
በሰላም ሂድ!
በሰላም ሂድ!
በሰላም ሂድ!
አሁንም እንደገና ሳሌም አየኋት።
ሳሌም ቃል አልወጣትም ይልቅስ ሃኪሙን …ደሞ አባቷን …አባቷን እንደገና ደሞ ሃኪሙን በርጋታ እየመላለሰች በነዛ ትላልቅ አይኖቿ አየቻቸው።
የሳሌም አስተያየቷ የሶስትዮሽ ቃላት ውጤት ነው ፦ ሃይል፣ ከፍታና ርጋታ።
አስተያየቷ ሃያል ነው። የሆነ እምቅ ሀይል አለው።
አስተያየቷ ከፍ ያለ ነው። ከሆነ ከፍታ ላይ ሆና በንቀት የምታያቸው ነው የምትመስለው።
አስተያየቷ ጸጥ ያለ ነው። እንደ ሰላማዊ ውቂያኖስ ውሃ ርግት ያለ። እዛ ውሃ ውስጥ ግን ሊፈነዳ ያለ ግዙፍ የሱናሚ ተራራ ያለ ይመስላል።
ምንም ሳትናገር ተነስታ ክፍሉን ለቃ ወጣች።
*
*
ይቀጥላል....
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️

👍56😢15❤7😱3👏1
የፍቅር ‘ርግቦች
ክፍል ስምንት፦ አምስት ጠባሳዎች
©ሃሴድ አጋፔ ፍቅር
“…እንድንነጋገር ትፈልጊያለሽ ሴሊና? እዚህ ውሳኔ ላይ እንዴት እንደደረስን?...” ታዴ ሳሌምን እያየ ይጠይቃል።
ሳሌምን ተከትለን መጥተን ሶስታችንም ዳሪክ የተኛበት የሆስፒታሉ ክፍል ውስጥ ቆመናል። ዳሪክ አሁንም ከሄደበት የምርመራ ክፍል አልተመለሰም።
ሳሌም ምንም ምላሽ አልሰጠችም። ይልቅስ በዛው እርጋታዋ ወደ አልጋው ሄደችና ሌሊት ዳሪክ ተኝቶ ካደረበት አልጋ ፍራሽ ላይ አልጋ ልብሱንና አንሶላውን ማውጣት ጀመረች።
“…እየሰማሽኝ ነው? በዚህ ጉዳይ ላይ እንወያይ?...”
ሳሌም ጸጥ።
ከትራሶቹ ላይ የትራስ ልብሶቹን ታውልቃለች። ቀጥላም ቆሻሻውን አንሶላ፣ አልጋልብስና የትራስ ጨርቆች ክፍሉ ጥግ ላይ ያለው የላውንደሪ ቅርጫት ውስጥ ከተተች።
“..እሺ መልስ ባትሰጪኝም ሃሳቡን ግን እነግርሻለሁ።…” ታዴ ማውራት ጀመረ “… ይህ ልጅ በስቃይ ነው ያለው። ከዛን ርጉም ቀን ጀምሮ ይኸው መከራ ላይ ነው። ስንት ጊዜ ሆስፒታል መጣ? ስንት ጊዜ ታመመ? ሃኪሞቹ በሙሉ ተስፋ እንደሌለው ነግረውኛል። የቀረው እድሜውን በሙሉ በስቃይ ላይ ስቃይ እንደሆነ አስረግጠውልናል። ደሞ ይህን ውሳኔ እኔ በራሴ አይደለም የወሰንኩት። ሃኪሞቹ፣ ዳሪክን እዚህ ሃገር እንዲመጣ ያደረጉት ቤተሰቦችም ተስማምተዋል። እየሰማሽኝ ነው ሴሊና?...”
ሳሌም ዝም።
አሁን ፍራሹ ላይ ንጹህ አንሶላና አልጋ ልብስ እያለበሰች ነው።
ታዴ ቀጠለ “…በዛ ላይ ያንቺስ ህይወት እስከ መቼ ነው እንዲህ የሚቀጥለው? ላለፉት ሰባት ወራት ዳሪክን ሃያ አራት ስትንከባከቢ አለሽ። ትምህርትሽን አቁመሻል። ፈጽሞ ስለ ራስሽ ማሰብ ትተሻል። ሃያ አመት እንኳን ያልሞላሽ ለጋ ልጅ ህልምሽ፣ ህይወትሽ፣ ወደፊትሽ ሁሉ እንደ ጉም ሲበን፣ ሲበተን እንደ አባት ዝም ብዬ ማየት አለብኝ? አለብኝ እስኪ ንገሪኝ?...”
የታዴ አነጋገር ግራ የገባው ሰው ንግግ ር ነው። ለወሰነው ውሳኔ ርግጠኛነት የተሰማው አይመስልም። የድጋፍ ድምጽ ከሁለታችንም የሚፈልግ ነው የሚመስለው።
ሳሌም ክፍሉ ውስጥ ሰው የሌለ ይመስል በፍጹም ዝምታ ያነጠፈችውን አልጋ በጥንቃቄ ታሳምረው ጀመር።
ለጥቂት ሰከንዶች ዝም ብሎ ሳሌምን ሲያያት ቆየ፦ ታዴ።
“..እንደዚህ ነው? አትመልሺልኝም? አታወሪኝም?..” በንዴት ጮኸ
ሳሌም መሬት ሆናለች።
ጸጥ።
ምንም እንዳልተፈጠረ፣ አንዳች ነገር እንዳልሰማች በታላቅ ርጋታ …ትራሶቹን በአዳዲስ የትራስ ሽፋኖች ውስጥ ማስገባት ጀመረች።
ዝምታዋ ሲቀጥል የአባቷ ንዴትም አብሮ ጨመረ። በቁጣና በእልህም ንግግሩን ቀጠለ “..እንግዲህ ምንም አልሽ ምን ውሳኔውን ወስነናል። በጥቂት ቀናት ውስጥ ይተገበራል። ያፈቀረ አንቺ ብቻ አይደለሽም። በስሜት ማስብሽን አቆሚ። በምክንያታዊነት መሰረት ላይ ሆነሽ ለአን ቺም፣ ለዳሪክም የሚጠቅመውን አድርጊ። ከዳሪክ ብትለይ የምትሆኚው ምንድን ነው? ምን ትሆኚያለሽ? እስኪ ተናገሪ ምንድን ነው የሚሆንብሽ? ምንስ ነው የሚመጣብሽ?...”
ሳሌም በርጋታ አንዴ ቀና ብላ አየችውና “…አባቴ!...” አለችው
ቃሉ ከአፏ ሲወጣ ታዴ ንግግሩን አቆመ።
“…አባቴ አይታይህም? የማደረግውን አትመለከትም?...”
ታዴ አንዴ ሳሌምን አንዴ ደግሞ ዙሪያውን ገርሞት ተመለከተ። እኔም ደንቆኝ እያየሁ ነበር፦ በ አካባቢው ላይ ሳሌም እያረገችው ያለ ነገር ካለ ብዬ። የማየው ግን ምንም ነገር አልበረም። እኛው ሶስታችን በአንዲት የሆስፒታል ክፍል ውስጥ ነው ያለነው።
“…ምንድን የምታወሪው? ምን እያደረግሽ ነው?...” ታዴ ጠየቀ
ሳሌም በረጅሙ ተነፈሰች “…የምወደው…የኔ መልዐክ… ከመምጣቱ በፊት አልጋውን እያነጠፍኩ፣ ክፍሉን እያዘጋጀሁለት ነው። አይታይህምን?...ትልቅ ስራ እኮ አለኝ። ስራዬ እሱን ማፍቀር ነው። ስራዬ እርሱን መንከባክብ ነው። ተልዕክዬ ከልቤ ፍቅሬን መውደድ ነው። ከጌታ ቀጥሎ የመጀመሪያ፣ ቅድሚያ የምስጠው ፍቅሬን ነው። ለሌላ ነገር አሁን ጊዜ የለኝም። አቅም አልባ ነኝ። ለክርክር፣ ለጸብ፣ ለጥላቻ ጉልበት የለኝም። እባክህን?....”
ታዴ ንዴት በሚንቦገቦግበት አይኖቹ ለአፍታ ዝም ብሎ ሳሌምን ተመለከታትና ወጥቶ ሄደ።
….ያ ቀን ረጅም ነው። ዘንካታ ረጅም ሳይሆን የሆነ ጠውላጋ የማ ይሄድ፣ የማይገፋ ቀን ነው። ታዴ ወጥቶ ከሄደ ቡሃላ የመጀመሪያዎቹን ሰዐታት ከሳሌም ጋር ምንም አልተነጋገርንም። አላወራንም። በመሃል ዳሪክ ከሄደበት ምርመራ ሲመለስ ሳሌም ሁሌ እንደምታደርገው በጥንቃቄ አጸዳድታ፣ አስውባ አሳመረቸው። ስትጨርስም አልጋው አጠገብ ተቀምጣ አይፓዷን ከሄድ ፖን ጋር አያያዘች። ሄድ ፎኗን ጆሮዋ ላይ ሰካች። በክፍሉ ውስጥ ዳሪክ ላይ ከተሰኩት ማሽኖች ውጪ የሚሰማ ነገር አልነበረም። ጸጥታ።
ጥቂት ረጅም፣ እንደ ዔሊ የሚጎተቱ ሰዐታት አለፉ። አንድ ደቂቃ የሳምንትን ያህል፣ አንድ ሰዐት የሃምሌን ያህል ረዘመ።
ሳሌም የገባችበት ፈተና ክብደት ቢገባኝም፣ አብሪያት መሆን ብፈልግም ምናልባት ከዳሪክ ጋር ብቻዋን መሆን ትፈልግ ይሆን የሚል ሃሳብ ብቅ አለብኝና “..ሴለም ምናልባት ከዳሪክ ጋር ለብቻ ጊዜ ማሳለፍ ትፈልጊ ይሆን?...” ጠይቅኳት
“ ምናልሽ ሳዬ?...” ሄድ ፎኑን ከጆሮዋ ላይ እያወረደች።
ጥያቄውን ደገምኩኝ።
“…ኖ… ኖ…በጭራሽ…” መለሰችልኝ “…እንዲያውም ብትችይ አብረሽኝ ብትሆኚ በጣም ደስ ይለኛል።…”
“….እንደዛ ከሆነ እሺ….” ከተነሳሁበት መልሼ ተቀመጥኩኝ።
“….ሳዬ በጣም አመሰግናለሁ እሺ አለችኝ….” መልሳ ደግሞ
“…ለምኑ?...”
“….በዚህ ሁሉ አብረሽኝ ስለምትሄጂ። ስጠራሽ ዝም ብለሽ ስለምትመጪልኝ። በቃ ብቸኛ እህቴ ስለሆንሽልኝ።…”
በውስጤ፣ ልቤ ስፍስፍ አለላት “….ምንም ችግር የለም የኔ ቆንጆ። እንዳውም እኔ ነኝ ማመስገን የሚገባኝ። አመሰግናለሁ።…”
“…አንቺ ደሞ ለምኑ ነው የምታመሰግኚው ሳዬ?...” ተገርማ
“….በቃ እውነተኛ ፍቅር፣ አምነትና ለሌላ ሰው መኖር ህያው ሆኖ በአንቺ ሲንቀሳቀስ እያየሁኝ ስለሆነ።…”
ሳሌም በ'ምወደው ስስ ፈገግታዋ ፊቷን ሞላችው። ፍቅር፣ አምነት፣ ትህትናና ሰላም በአንድ ላይ በሳሌም ፊት ላይ እዩኝ፣ እዩኝ ይላሉ፦ ስታምር እኮ።
በዛ ረጅም ቀን ያወራነው ይህን ያህል ብቻ ነው። ጸጥ ብለን፣ ዝም ተባብለን ቀኑን ውለን መሸ።
….መሽቶ ከገፋ ቡሃላ እንደገና ታዴ መጣ። መምጣቱ ግን የለወጠው ነገር የለም። ሶስተኛ ሰው የዝምታውን ባህር ውስጥ ከመቀላቀሉ ውጪ። ሶስታችንም ተዝግተን ተቀምጠን የዳሪክ የመተንፈሻ ማሽን ብቻ አየር ሲያስወጣና ሲያስገባ ይሰማል።
ታዴ ከመጣ በግምት ከአንድ ሰዐት ቡሃላ ሳሌም ቀኑን ሙሉ ይዛ የዋለችውን አይ ፓዷን አስቀመጠችና ወደ ታዴ ዞረች....
“…አምስት ናቸው!... ታውቃለህ?...” የተጫነንን የዝምታ ቀንበር ሰበረችው።
“….ምን አልሽኝ? ምኑ?...” ደንግጦ ጠየቃት

👍53❤3😁2🥰1
….ምን አልሽኝ? ምኑ?...” ደንግጦ ጠየቃት
በእርጋታዋ ሳሌም መናገር ጀመረች “….አምስት ናቸው!.... በዳሪክ…የኔ መልዐክ ጀርባ ላይ ያሉት ጠበሳዎች። የተበታተኑ አምስት ጠባሳዎች። ሁልጊዜ በየቀኑ አያቸዋለሁ። ማንም ሰው ሳያየኝ እጄን አስገብቼ እዳስሳቸዋለሁ። አምስት ቦታ ነው በጥይት የተበሳሳው። ፍቅሬ ዛሬ መተንፈስ ምጥ የሆነበት፣ ሳንባው አልሰራ ብሎ በዚህ ማሽን የሚተነፍሰው በነዛ አምስት ጥይቶች የተነሳ ነው።…ግን እነዚህ አምስት ጠበሳዎች ከየት መጡ? የመጡት እኔን ካፈጠጠብኝ ሞት ሊታደጉ ነው። እኛ ሁላችን አፍንጫችንን አልፎ ሲገባ የማናስታውሰው የህይወት ስትንፋስ፣ …አየር… ዳሪክ ያጣው ለኔ ነው ….እኔ እንድተነፍስ ነው። እነዚህ አምስት ጠበሳዎች የፍቅሬ ህያው ማህተሞች ናቸው። እነዚህ አምስት ጠባሳዎች ከብዙ መጻህፍት የበለጠ ፍቅርን ይተርኩልኛል። የመውደድን ጥንካሬና ጉልበት ያሳዩኛል። የኔ መልዐክ ሳይሳሳ፣ ሳያቋርጥ፣ከነፍሱ፣ ከልቡ ምን ያህል እንደወደደኝ ያሳዩኛል። ዛሬ ባያወራኝም እንኳን...'የምውደሽ'...ብሎ ባይጠራኝም ነገር ግን ጀርባው ላይ ባሉት ምልክቶች ‘…እወድሻለሁ እኮ!...’ …. ‘…አፈቅርሻለሁ እኮ!... እሳሳልሻለሁ እኮ!...’ …. ‘….የኔ ውድ ነሽ እኮ!...” ይለኛል።….”
ሳሌም እያወራች እኔ እንባዬ በአይኖቼ ውስጥ እየሞላ ነበር።
ጥቂት ዝም አለችና ቀጠለች “…አባቴ እለምንሃለሁ። በታላቅ ትህትና፣ በጌታ ስም እጠይቅሃለሁ።…ፍቅሬን አትውሰድብኝ።… መውደዴን አትንጠቀኝ።… ለአንዲት ልጅህ በሰው አእምሮ የማይታሰብ ዋጋ የከፈለላትን አንድ ልጅ ህይወት ‘ሂድ’ አትበለው? ወረቀት ላይ ለሱ የህግ ተወካይ ስለሆንክ ብቻ በአንዲት ፊርማ ህይወቴን፣ ፍቅሬን፣ መውደዴን፣ መልዐኬን አትቀማኝ?....እባክህን አባቴ፣…እባክህን… እባክህን …አባቴ …ዳሪክን አትቀማኝ….” በሚያሳዝን ሁኔታ ትለምነው ጀመር።
ሳሌም አይን አይኑን በልመና ስታየው ታዴ የጭንቁን ማውራት ጀመር “…ሴሊና እኔ እኮ ብቻ አይደለሁኝም የወሰንኩት ሃኪሞቹም፣ ስፖንሰር ያደረጉት ቤተሰቦችም ሁላችንም ተወያይተን ነው እኮ…።….. ልጄ አንቺ እኮ እየሆነ ያለው ነገር አይታይሽም። ፍቅር በሚባል ስሜት ተሽፍነሻል ። ዳሪክም አንቺም ስቃይ ላይ ናችሁ እኮ። ለሁለታችሁም…”
ሳሌም ግን አቋረጠችውና አሁንም በሚያሳዝን ሁኔታ ልመናዋን ቀጠለች “…ልጅህ ቢሆን ይህን ታደርግ ነበር? እባክህን አባቴ …እለምንሃለሁ? እማጽንሃለሁ?....”
ታዴ የሳሌም ልመና መቋቋም የማይችለው ሁኔታ ላይ ሲደርስበት አሁንም ተነስቶ ክፍሉን ለቆ ወጣ። የታዴ ነገር እኔ ማመን አቅቶኛል። የዛሬ ሰባት ወር ሆስፒታሉ ውስጥ ስለ ሁለቱ ፍቅር ያወራሁት ታዴ አልመስል አለኝ። ለምን እንዲህ ጨከነ? እንዴትስ ለልጁ ርህራሄው ፈጽሞ ጠፋ? ግራ የሚያጋባ፣ መልስ የሌለው ጥያቄ።
ታዴ ወጥቶ ሲሄድ ወደ ሳሌም ዞርኩኝ “…ምንድን ነው ሚሻለን ሴለም?...”
“…አታስቢ ሳዬ…” በእርጋታ መለሰችልኝ “…ጌታ ያለው ይሆናል። አባቴ ሃሳቡን ይቀይራል ብዬ አምናለሁ። አሻግራ ወደ ውጪ በመስኮት እያየች። “…አሁን ስለመሸ ለመኝታ እንዘጋጅ ካለስቸግርኩሽ እዚህ ታድሪያለሽ ሳዬ?...”
እርጋታዋ እንዳለ ቢሆንም ሳሌም ብቻዋን መሆኑ ያስፈራት ትመስል ነበር። እሺ ብዬ የሆስፒታሉን ታጣፊ አልጋ ከዳሪክ አልጋ አጠገብ ዘረጋነውና ለእንቅልፍ ተዘጋጀን።
ረጅሙ፣ ዝምታ የነገሰበት ቀን አልፎ መሽቷል። የዘረጋነው አልጋ ላይ ተጋደምኩ እንጂ እንቅልፍ ግን ለኔ ቅርብ አልነበረም።
ቆይተን “…ሴለም ተኝተሻል?...” አልኳት
“…አልተኛሁም ይሄ ሌሊት እንደ ቀኑ ሳይረዝም አይቀርም….”
“…የሆነ ነገር እንስራ፣ እንጫወት ወይም እናውራ…”
“…ጥሩ ሃሳብ ምን እናድርግ ሳዬ?...”
ለአፍታ አስብኩና “….ለምን ስለ አንቺና ዳሪክ አትነግሪኝም?...”
“….ማለት… ምን ልነግርሽ ሳዬ?...”ወደ እኔ ዞራ በፈገግታ
“…በቃ ሁሉንም ነገር ከጅማሬው ጀምሮ…”
“…መስማት ትፈልጊያለሽ ሳዬ?...”
“….አዎ… ከልቤ… ሁሌም…”
“…እሺ …” ስትለኝ በደስታ ከተኛሁበት ተነስቼ ቁጭ አልኩኝ።
ሳሌም ለሰከንዶች ከየት እንደምትጀምር እያሰበች ይመስል በመስኮቱ አሻግራ ውጪውን ስታይ ቆየች። ጥርት ባለው የክረምት ሰማይ ላይ ግማሽ ጨረቃና፣ ከዋክብት ደምቀዋል። ከሰማዩ በታች የሲያትል ከተማ ረጃጅም ፎቆች ከርቀት ይታያሉ። እነዚህ ጉዕዝ ፎቆች፣ የተሸረፈችው ጨረቃና ከዋክብት ሁሉም ታሪኩን ለመስማት እንደእኔው ያቆበቆቡ፣ የቋመጡ መሰለኝ።
ሳሌም ከዳሪክ አጠገብ ተኝታ በዝግታ የዳሪክን እጆች እየዳሰሰች… አይን አይኑን እያየች.... ጀመረች። የጀመረችውንም.... ቀጠለች። የዛን 'ለት ሌሊት አንዳንዴ እየሳቅኩኝ፣አንዳንዴ እየተከዝኩኝ፣ አንዳንዴ በደስታ እንባዬ እየመጣ ከሳሌም አፍ የሚፈሰውን የሁለቱን 'ርግቦች የፍቅር ታሪክ ሳዳምጥ አደርኩኝ።….ያ ሌሊት ምናልባትም ሶስታችን አንድ ላይ ያሳልፍነው የመጨረሻ የደስታ ሌሊት ሳይሆን አይቀርም።
…..ከ72 ሰዐታት ቡሃላ ....ዳሪክን ለማይቀረው ጉዞው እያሰናዳነው ነበር፦ ሳሌምና እኔ።

👍51❤10😁2👏1
#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አንድ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ለሁለት ወራት ድምፅዋን አልሠማም፡፡ አልደወለችለትም፡፡ ምንም አይነት አዲስ ጽሁፍም አላከችለትም፡፡ እሷ ልታገኘው ካልፈለገች እሱ ሊያገኛት የሚችልበት ምንም መንገድ የለውም፡፡ ይሄ ሁኔታ ሁሴንን እጅግ ሲያስጨንቀውና ሲያበሳጨው ነው የከረመው፡፡ ዛሬ ግን በሀሳብ የሚያባክነው ጊዜ አላገኘም፤ውጥረት ላይ ነው ያለው፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ በዋቤ ሸበሌ ሆቴል የሚስጥር የግጥምና የአጫጭር ልብ ወለድ መጽሐፍ ይመረቃል፡፡
ሁሴን፣ሠሎሞን እና ትዕንግርት ነገሮችን ሁሉ በታቀደላቸው ዕቅድ መሠረት እየተከናወኑ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ከወዲህ ወዲያ ይሯሯጣሉ፡፡
‹‹አሁን ምን ቀረ?›› ሠሎሞን ነው የጠየቀው፡፡
‹‹ምንም ... የእንግዶቹ መምጣት ብቻ..፡፡›› ሁሴን መለሰ፡፡
‹‹የሚዲያ ሠዎችስ .. ያረፍዱ ይሆን?›
‹‹ኧረ ደርሰዋል...ሆቴል ሻይ ቡና እያሉ ናቸው፡፡››
‹‹በትክክልም መድረስ አለባቸው፡፡ ይሄን የመሠለ ግራ የገባው ታሪክ ለመዘገብ የማይጓጓ የወሬ ሠው የት ይገኛል ብለህ ነው?››ሰሎሞን ነው ተናጋሪው፡፡
‹‹እስቲ ዛሬ እንኳን ስድብህን ዋጠው፡፡›› አለው ሁሴን እንደመበሳጨት ብሎ
<እንዴ ቁጭ ብላችሁ ታወራላችሁ እንዴ......? እንግዶች እኮ መምጣት ጀምረዋል፡፡ ውጭ ናቸው›› ትንግርት ነች በሩን ከፍታ ወደ ውስጥ እየገባች የምታወራው፡፡
‹‹በቃ የቀረን ነገር የለም ... ዝግጅታችንን አጠናቀናል፡፡ ዘና የሚያደርጉን ሙዚቃኞች ከነ ሙዚቃ መሳሪያቸው መጥተዋል፡፡ ዝግጅቱን በንግግር የሚከፍቱልን የክብር እንግዳችን የደራሲን ማህበር ፕሬዘዳንትም በሠዓቱ እንደሚገኙ ማረጋገጫ ሠጥተውናል፡፡
ለእድምተኞች ከመጽሐፍ በመቀንጨብ የሚያነቡ ሠዎችም ተመድበዋል፡፡ ያው እንደተነጋገርነው በመጀመሪያ አንቺ ታነቢያለሽ ሌላውን እኔ ጨምራለሁ፡፡ ይሄ ቀፈታም
ኢንጂነር እንደሆነ አይኖቹ ብር ላይ የሚገኝ ቁጥር እንጂ ፊደል ማንበብ ካቆሙ ዘመናት አልፈዋል፡፡ ስለዚህ የእሱ ኃላፊነት እንግዶች በስርዓት መስተናገዳቸውን መቆጣጠር ነው፡፡›› ንግግሩን ገታ አደረገና አይኖቹን ሠሎሞን ላይ ተክሎ ንግግሩን ቀጠለ ‹‹ደግሞ ዛሬ እንዴት ነው አለባበስህ? ሚስትህን ጥለህ ከቤት ስትኮበልል ወጣት የሆንክ መሰለህ
እንዴ?>>
‹‹ሰውዬ እንደውም ዛሬ ከዕድምተኞቹ ውስጥ አንዷን ምርጥ ካገኘሁ መጥበሴ አይቀርም፡፡›› አለው ሠሎሞን፡፡
‹‹ምን አልባት ከአስተናጋጆቹ መካከል ከሆነ እስማማለሁ፡፡ ዝግጅቱን ለመታደም ከሚመጡት ውስጥ ግን ላንተ ነፍስ የምትስማማ የምትኖር አይመስለኝም፡፡ ደራሲ ወይም ገጣሚ አፍቅረህ ልታብድ ነው...እስቲ በእኔ ይብቃ››ተሳሳቁ!!
‹‹ግን ዛሬም አትመጣም ማለት ነው?! >> ትንግርት ነበረች ጠያቂዋ፡፡ መልሱን ከሁሴን አንደበት ለመስማት በጉጉት ስሜት አይኖቿን እያቁለጨለጨች፡፡
‹‹በቃ ስለ እሷ እያወራችሁ ስሜቴን አታደፍርሱት፡፡ እንዲያውም ሠዓቱ ደርሷል በራፉን ክፈቱና እንግዶችን ወደ ውስጥ አስገቧቸው፡፡››
ሠሎሞን ተንደርድሮ በሩን ከፈተና ውጭ የተጠራቀሙትን እንግዶች ወደ ውስጥ እንዲገቡ ይጋብዛቸው ጀመር፡፡ ጋዜጠኞችም ከካሜራ ባለሞያቸው ጋር እየተንጋጉ ገቡ፡፡ በ3ዐ ደቂቃ ውስጥ ከተጠሩት ሠዎች
አብዛኞቹ ስለተገኙ ፕሮግራሙን ለማስጀመር ሁሴን ወደ መድረኩ ማይኩን በቀኝ እጁ የተወሰኑ ወረቀቶችንና በእለቱ ለምረቃ የተዘጋጀውን መጽሐፍ አንድ ቅጂ በግራ እጁ ይዞ ወጣ፡፡መድረኩ ፊት ለፊት ግድግዳ ላይ ከሩቅ እንዲነበብ ታስቦ በባነር ላይ የተጻፈ ፅሁፍ ተለጥፏል፡፡ እንዲህ ይነበባል፡፡
የመፅሀፍ ምረቃ በዓል
የመፅሀፍ አይነት፦ የግጥምና አጫጭር ልቦለድ መድብል
ርዕስ፦ የጨረቃ ፍካት
ደራሲ፦ ምስጢር በለጠ
አሳታሚ፦ ፍካት ማተሚያ ቤት
የታተመበት ቀን፦ ሠኔ 2ዐ ቀን 2007 ዓ.ም.
ሁሴን ከአትሮኖሱ ጀርባ ቆሞ ጉሮሮውን ጠራረገና ንግግሩን ጀመረ፡፡ ከተለያዩ መጽሔት፣ ጋዜጣ፣ ሬዲዬና ቴሌቪዥን ጣቢያ የመጡ ጋዜጠኞች ካሜራቸውንና መቅረፀ ድምጻቸውን በዙሪያው ቀሠሩ፡፡
‹‹ክቡራንና ክብርት የጥበብ አፍቃሪዎች
በመጀመሪያ ጥሪያችንን አክብራችሁ ከጥበብ ማዕዱ ለመቋደስና የደስታችን ተካፋይ
ለመሆን እዚህ ስለተገኛችሁ በደራሲዋ እና በራሴ ስም የከበረ ምስጋናዬን ለማቅረብ እፈልጋለሁ፡፡በማስከተልም ስለደራሲዋ
አንዳንድ ያልተለመዱ ነገሮች መናገር እፈልጋለሁ›› መጽሀፉን አነሳና ወደ ታዳሚው
በማሳየት ንግግሩን ቀጠለ፡፡
‹‹ይሄ መጽሐፍ
ሠባት አጫጭር ልብ ወለድ እና ሠላሳ የተመረጡ ግጥሞች የተካተቱበት ባለ ሁለት መቶ ሃያ ገጽ መጽሐፍ ነው፡፡ ከነዚህም መካከል አራቱ አጭር ልብ ወለዶች እና ሃያ የሚሆኑት ግጥሞች በተለያየ ጊዜ በፍኖተ ጥበብ ጋዜጣ ላይ ለህትመት የበቁና በአንባቢ
ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኙ ናቸው፡፡ለዚህም
የጋዜጣው አንባቢ የሆናችሁ መመስከር ትችላላችሁ፡፡ ሌሎቹ ግን በደራሲዋ የቀረቡ ከዚህ በፊት ያልተነቡ አዳዲሶች ናቸው፡፡
የመሸጫ ዋጋው ሰላሳ ሁለት ብር ነው፡፡ ዋጋው ካለው የወረቀት ውድነትና ይሄን ተከትሎ አሳታሚ ድርጅቶች ከሚጠይቁት ዋጋ አንፃር ተሠልቶ የተተመነ ስለሆነ ተመጣጣኝ ነው ብለን እናስባለን፤ ስለ መጽሐፉ ይሄን ያህል ካልኩ ስለ ደራሲዋ ደግሞ ጥቂት ነገር ማለት ያለብኝ ይመስለኛል፡፡ደራሲዋ አሁን በመሀከላችን... >> ንግግሩን አቋረጠና ወደ ውስጡ ትንፋሹን ደጋግሞ ሳበ፡፡ እንደ ማሳል አለና በተንቀረፈፈ ሁኔታ ንግግሩን ቀጠለ ፡፡
‹‹...አሁን በመሀከላችን የለችም፡፡ ማለቴ እዚህ ዝግጅት ላይ እንድትታደምና የድካሞን ውጤት፤ የዘራችውን ዘር ፍሬ እንድታጣጥም ማድረግ አልቻልኩም፡፡ ምክንያቱም በአካል አላውቃትም፤ መኖሪያ ቤቷን፣ ስልኳን፣ ፖስታ ሳጥን ቁጥሯን አላውቅም፡፡ ላውቅ ያልቻልኩትም እኔ ማወቅ ስላልፈለግኩ ሳይሆን እሷ እንዳውቅ ስላልፈለገች ነው፡፡››
ከእድምተኞች አካባቢ ጉምጉምታ በዛ፣ የጋዜጠኞች ጆሮ ይበልጥ ተቀሠረ፣ካሜራዎቻቸውን ከወዲያ ወዲህ በፍጥነት ማሽከርከር ቀጠሉ፡፡ ብዛት ያላቸው ሠዎች በተንቀሳቃሽ ሞባይል ስልካቸው ሳይቀር ንግግሩንም ሆነ የዝግጅቱን ድባብ በተቻላቸው መጠን በመቅረፅ ላይ ናቸው፡፡‹‹... ያው እንዳልኳችሁ ምስጢር ከሁለት ዓመት ለበለጠ ጊዜ የፍኖት ጥበብ ጋዜጣ ቋሚ አምደኛ ነች፡፡ ጽሁፎችን የምትልከው በፖስታ ቤት በኩል ሲሆን አድራሻዋን ግን አትፅፍም፡፡ ጽሁፎቿ በጣም ማራኪ ብስለት ያልተለያቸውና ዘና የማድረግ ደረጃቸው ከፍ ያሉ በመሆናቸው ዛሬም ድረስ የእሷ አድናቂ እንድሆን ተገድጄያለሁ፡፡ በነገራችን ላይ በግል ስልኬም ትደውልልኛለች፤ እውነቴን ነው የምላችሁ መፃፍ ብቻም ሳይሆን ማውራትም ትችልበታለች፡፡ የምትጠቀመው ስልክ የሕዝብ ነው አንድ ቀን ከልደታ፣ በሌላ ሳምንት
ከመገናኛ፣ ሲያሰኛት ከሳሪስ አካባቢ ባለ የሕዝብ ስልክ ነው የምትደውልልኝ፡፡ ከምታስቡት በላይ ግራ አጋቢ የሆነች ፍጡር ነች፡፡ በተደጋጋሚ ጊዜ ላገኛት እንደምፈልግ ነግሬያት ብማፀናትም ጥያቄዬን ልትቀበል አልቻለችም፡፡
በመጨረሻ እሷን ከተደበቀችበት ጉድጓድ እንዴት አድርጌ ለማውጣት እችላለሁ? ብዬ ሳስብ የፃፈቻቸውን ፅሁፎች የማሳተም ሃሳብ በአዕምሮዬ ተሠነቀረና አማከርኳት፤ ነገሩ ግን እንደገመትኩት አልሆነም፡፡ ጽሁፎቿን የማሳተም ፍላጎት እንደሌላትና እኔ ማሳተም ከፈለኩ ግን እንደማትቃወመኝ እናም ውክልናውንም እንደምትሠጠኝ ነግራኝ ከዛ አልፎ ግን ከእኔ ጋር ለመገናኘት ለጊዜው ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላት አረዳችኝ፡፡ እንዳለችውም ውክልናውን በፖስታ ቤት ላከችልኝ..

👍87❤10🥰1👏1
በዚህም መሠረት መጽሐፍ በእኔ አማካይነት እና በጓደኞቼም እገዛ ታትሞ እንሆ ዛሬ ለምረቃ በቃ ፡፡ እኔም ጋዜጠኛ እንደመሆኔ
መጠን እዚህ ያላችሁ ጋዜጠኞች መዓት ጥያቄ
በአዕምሮአችሁ እየተጉላላ መሆኑ ቢገባኝም አሁን ወደ ዝግጅቱ በቀጥታ እንድንገባ እየጠየቅኩ በስተመጨረሻ ላይ ግን በተቻለ መጠን ለጥያቄያችሁ መልስ ልሠጣችሁ እንደምሞክር ቃል እገባለው፡፡ በመቀጠል የእለቱን የክብር እንግዳ የሆኑት የደራሲያን ማህበር ፕሬዘዳንት በንግግር እንዲከፍቱልን በክብር እጠይቃለሁ›› በማለት መድረኩን ለፕሬዘዳንቱ አስረከበ፡፡
ፕሬዘዳንቱም ንግራቸውን በመገረም ጀምረው በመደነቅ ጨረሱና መድረኩን መልሠው ለሁሴን አስረከቡ፡፡
ሁሴን ንግግሩን ቀጠለ ‹‹በመቀጠል የደራሲዋ አድናቂዎች ከመጽሐፉ የተወሠነ ጽሁፍ በመቀነጫጨብ ለዕድምተኞቻችን ያቀርቡልናል፡፡ የመጀመሪያዋ አቅራቢ ትንግርት ትሆናለች፡፡ ትንግርት ወደ መድረኩ ብትመጪልን፡፡ በነገራችን ላይ ትንግርት በሞያዋ ሠዓሊ ነች፡፡ በሚቀጥለው ሳምንት በአልያንስፍራንስ የመጀመሪያ የሥዕል
ኤግዚብሽኗን ታቀርባለች፡፡
ጋዜጠኞች ይህቺን ልጅ ብትከታተሏት ድንቅ ታሪክ ከጀርባዋ እንደምታገኙ በምስጢር ሹክ ልላችሁ እወዳለሁ፡፡›› በማለት ነጭ የአበሻ ቀሚሷን ለብሳ በቄንጠኛ እርምጃ ወደ መድረኩ ለተቃረበችው ትዕንግርት መድረኩን ለቀቀላት፡፡
እሷም ያለምንም የመግቢያ ንግግር ቀጥታ መጽሐፉን ገልጣ ወደ ማንበብ ነበር የገባችው፡፡ ‹እናቴ› በሚል ርዕስ የተፃፈውን አጭር ልቦለድ ነበር የምታነበው፡፡ አዳራሹ በፀጥታ ተሸበበ፤ ጋዜጠኞች ሳይቀሩ መቁነጥነጣቸውን አቁመው በተመስጦ በማዳመጥ ላይ ናቸው፡፡ የታሪኩ ፍሠትና የቃላቶቹ ውበት ብቻ አልነበረም እንዲመሠጡ ያስገደዳቸው፡፡ የተራኪዋም ድንቅ ችሎታ አፍ ያስከፍታል፡፡ የምታነበው ድርሠት በሦስት ገፀ ባሕርያት የተዋቀረ ነው፡፡ አንድ ወጣት ሴት፣ አንድ አዛውንት እናት እና ጎረምሳ ወንድ፡፡ የሦስቱንም ንግግር
በተለያየ የድምፅ ቅላፄ ሳታምታታ እየቀያየረች ስታቀርብ ቀድሞውንም ሕይወት ላለው ድርሠት ድርብ ሕይወት ዘራችበት፡፡ በዚህም ችሎታዋ እድምተኛውም ሆነ ጋዜጠኞች በሙሉ በእጅጉን ተደነቁባት፡፡ ሠሎሞንና ሁሴንም በመገረም ፈዘው ነበር፡፡
የሙዚቃ እረፍት ከተደረገ በኋላ ሌሎች ሦስት
አንባቢዎች ፎዚያንም ጨምሮ የመረጡትን
በንባብ አሠሙ፡፡በአጠቃላይ የመጽሀፍ ምረቃ በዓሉ ከተለመደው የተለየ ብዙ አስገራሚ
ነገሮች የታመቁበት ነበር፡፡ እያንዳንዱ ጋዜጠኛ
ያገኟቸውን መረጃዎች በቅደም ተከተል አጠናቅሮ በየሚሠሩበት ሚዲያ ላይ
ለማቅረብ ከፍተኛ ጉጉትና መቻኮል ይታይባቸው ነበር፡፡ሁሴንም እንዲህ ያሠፈሠፈውን እያንዳንዱን ጋዜጠኛ ነገሮችን በምንም መልኩ እንደተረዱት እና በምን መልኩም ለሕዝብ ለማስተጋባት እንደወሠኑ
ለማወቅ ጓጓ፡፡ መጽሀፉም በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኛል? ወይስ አንባቢ አጥቶ በየመጽሃፍ መሸጫ መደብሩ የብል ሲሳይ ሆኖ
ይቀራል? የሚለውን ጥያቄ ሌላ ያስጨነቀው ጉዳይ ነበር የሆነበት፡፡ መልሶቹን ለማግኘት ግን የተወሠኑ የጊዜ ሽክርክሮችን በትዕግስት መጠበቅ እንዳለበት አልጠፋውም፡:
ግን የተወሰኑ የጊዜ ሽክርክሮችን በትግስት መጠበቅ እንዳለበት አልጠፋውም።

👍77❤26
የፍቅር 'ርግቦች
ክፍል ዘጠኝ፦ 4 አይኖች 2 ልቦች
©ሃሴድ አጋፔ ፍቅር
ከሰባ ሁለት ሰዐታት ቡሃላ …
ይዘንባል፦ዝናቡ። ዝግ ብሎ፣ ችፍ ችፍ እያለ፣ በዛፎቹ፣ በሜዳው ሳሩ ላይ ልስልስ ብሎ ይወርዳል። በማለዳ ከእንቅልፌ ተነስቼ፣ በሆስፒታሉ ክፍል መስኮት መስኮት አሻግሬ የዝናቡን አወራርድ እያየሁ ነው። የዝናቡ ግልገል ጠብታዎች በመሬት ላይ ተከታትለው ሲያርፉ የሚሰሩት ክበቦች ሃሳብን ይሰርቃል። ቀኑ ዝናባማ ነው። ይህን ቀን ላለማየት ጸሀይ ራሱ የተደበቀች ነው የምትመስለው።
ዞር ብዬ ሳሌምን አየኋት። በ'ርጋታዋ የዳሪክን እጅ ይዛ እየጸለየች ነው። በልብዋ የምትለውን፣ ለጌታ የምትናገረውን ለአፍታ መስማት ብችል ብዬ ተመኘሁ። (((ባለፉት ሰባ ምናምን ሰዐታት ብዙ አዲስ ነገር ሆኗል። በህይወቴ ባይኔ አየዋለሁ ብዬ የማላውቀውን፣ የክፋት ሁሉ ምንጭ የሆነ ሰው ትላንት አይቻለሁ። ይህን ሰውም ሳሌም ፍቅርና ይቅርታ ከልቧ ስታፈስለት በአይኖቼ አይቼ መጥቻለሁ። ይህን ታሪክ ሌላ ጊዜ እጽፋለሁ ...))))
ጸሎቱን ስትጨርስ በዝምታ ዳሪክን ማዘጋጀት ጀመርን፦ ሳሌምና እኔ። የለበሰውን አረንጓዴ ጋውን አውለቅን። ሌላ ሙሉ ለሙሉ ነጭ የሆስፒታሉን ልብስ ማልበስ ጀመርን። ወደ ጎን ስናዞረው ባለፈው ሳሌም ስታወራለት የነበረውን አምስት ጠባሳዎች አየኋቸው። አምስት የዳኑ፣ የደረቁ ጠባሳዎች ግን ደሞ ብዙ ነገር የሚናገሩ፣ የሚተርኩ የተበታተኑ ጠባሳዎች። አልቻልኩም። የዳሪክ ለሞት መታጨት …ሌሊቱን ሙሉ ሲጨንቀኝ፣ ሆዴን ባር ባር ሲለኝ፣ ሲያሳዝነኝ…ከእንባዬ ጋር ስታገል ነው ያደርኩት። በቃ አሁን ግን አልቻልኩም። እንባዬ ከአይኔ ፈንቅሎ ይወርድ ጀመር። ራሴን መቆጣጠር አቃተኝ። ማዘጋጀቱን ትቼ፣ አልጋው አጠገብ ካለው ወንበር ላይ ቁጭ አልኩኝና አጎንብሼ ስቅስቅ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩኝ።
ሳሌም መጥታ አቀፈችኝ “…ሳዬ…ሳዬ… አሁን የምናልቅስበት ጊዜ አይደለም። አሁን ፍቅሬን የምናዘጋጅበት ጊዜ ነው። ወደፊት አትቅደሚ። የወደፊቱን የሚያውቀው ጌታ ብቻ ነው። እኛ የሚጠበቅብን አሁንን መኖር ነው። አሁን የኔ መልዐክ በህይወት አለ። ለወደፊቱ ደግሞ ጌታ ያለው ይሆናል።…”
ለቅሶዬ በውስጤ እያንቀጠቀጠኝ፣ ሰውነቴን እያረገበገበው እንደምንም ጸጥ አልኩኝ። ሳሌም ቀና ብዬ ሳያት…ያው ናት። ጸጥ፣ርግት ያለች ሳሌም። የማትነቃነቅ ጽኑ ተራራ። የመከራ ንፋስ የማያናውጣት ውብ ሰማያዊ ባህር። ምን አይነት ልጅ ናት? ምን ጉድ ናት? እንደገና ደግሞ መልሼ በራሴ አፈርኩኝ። እሷ ልታዝን፣ ልታለቅስ እኔ ደግሞ ላጽናናት ሲገባ በተቃራኒው መሆኑ አሳፈረኝ።
…..እንደገና አየኋት። በ'ርጋታ በትላልቅ ውብ አይኖቿ፣ ስስ ፈገግታዋን አጅባ ታየኛለች። እነዚህ ትላልቅ ውብ ሁለት አይኖች፣ ከአመታት በፊት ዳሪክ ያዩ አይኖች፣ ከአመታት በፊት የዳሪክ ልብ የወሰዱት 'ርግት ያሉ አይኖች...
*
*
*
ከሰባ ሁለት ወራት በፊት…
አዲስ አበባ፦ወሎ ሰፈር፣ አንዲት ትንሽ ቸርች ግቢ ውስጥ… ቅዳሜ ነው። ግቢ ….ሜዳ፣ ጥግ ላይ በቆርቆሮ የተሰራ አዳራሽ፣ ከአዳራሹ አጠገብ ትናንሽ ክፍሎች። ሜዳው ላይ አዋራው ይጨሳል፦ ዳሪክና ጎዳኞቹ ከሚጫወቱት የእግር ኳስ የተነሳ። በቸርቹ ድጋፍ የሚደርግላቸው ልጆች ቅዳሜ ኳስ ይጫወታሉ ግቢው ውስጥ። ዳሪክ አንዱ ነው። ጨዋታው ሲሞቅ ከተዋጫዋቾቹ አንዱ ያጎናት ኳስ አቅጣጫዋን ስታ በግቢው ውስጥ ጥግ ወዳሉ አነስተኛ ክፍሎች አመራች። ዳሪክ ኳሷን ለማምጣት ተከትሎ ሄደ። ያች ድቡልቡል ኳስ፣ ቀስ እያለች ትሄድ ጀመር…. ክብልል፣…. ክብልል፣… ክብልል ….የምትሄድበትን ታውቅ ይመስል… ክብልል ክብልል… “..ና…. እያለችው …ክብልል … ያቺ ኳስ ታዳጊው ዳሪክ ምናልባትም የህይወቱን አቅጣጫ በሚገርም ሁኔታ ወደ ሚቀይረው ሌላ ታዳጊ ልጅ ጋር፣ ፍቅሩ ጋር እየሄደች መሆኑን ፈጽሞ አላወቀም። ክብልል፣ አሁንም ክብልል ….በመጨረሻም … ያቺ ኳስ ...በስፍራና ጊዜ ኡደት ውስጥ የሚፈለገው ስፍራና ጊዜ ላይ ሄዳ ቀጥ አለች። ቆመች። …ዳሪክ ኳሷ ጋር ሲደርስ ያየው ነገር ሙሉ በሙሉ አይኑን ቀማው፣ የሰማው ነገር ልቡን ወሰደው። አንዲት ክፍል …. በትንሹ ገርበብ ብሎ የተከፈተ በር….አንዲት ታዳጊ…. ለስላሳ ሙዚቃ ከፊቷ ካለው ኦርጋን ላይ በ‘ርጋታ ትጫወታለች። ዳሪክ ከምንም በፊት ያየው ጣቶች ነው። አለንጋ የሳሌም አስር ጣቶች በነጭና በጥቁር የፒያኖ ቁልፎች ላይ ከወድያ ወዲህ እንደ ውብ ዳንሰኞች ይስግራሉ፣ በዝግታ ይጓዛሉ። ሙዚቃው በ'ርጋታ ይፈሳል። ….ያማሩ ውብ የጥፍር ዘውዶች ከደፉት አለንጋ ጣቶች ቀጥሎ ደሞ ያየው ፊቷን ነው። … ብቅ ልትል እንደተዘጋጀች የማለዳ ጸሀይ በረጅም ጽጉሯ በክፊል ተሸፍኗል። … ‘ርግት ያለው ፊቷ የጣቶቿ ደቀ መዝሙር ነው። ፊቷ ጣቶቿን ይከተላል። ጣቶቿ በፒያኖው ላይ ወደ እዚህ ጥግ ሲመጡ፣ ፊቷ አብሮ ዘንበል ይላል። ወደ ዛኛው ጥግ ሲሄዱም እንዲሁ። መዝሙሩን ተከትላ አንዳንዴ አይኗን ጨፈን ደግሞ አንዴ ከፈት … ሰበር ሰካ የሚሉ ቆንጆ ጣቶች፣'ርግት ያለ ቆንጆ ሽራፊ ፊት ፣ዝግ ካለው የሙዚቃው ስልት ጋር የሚንቀሳቀሰው ጸጉሯ የተዘናፈለበት የሳሌም ትከሻ…ውብ ትዕይንት ነው። የዳሪክ ጊዜ ቆመ። ህዋሳቶቹ ባሉበት ዝም አሉ። የልብ ትርታው ረገበ። ‘ስትንፋሱ በሳንባው ውስጥ ተረጋጋ። ሁሉም ስሜቶቹ ወደ ሳሌም ሄዱ። ዳሪክ ኳሷን ትቶ …ቀጥ፣ ቆም፣ ድርቅ …. በቃ ሳሌምን እያያት …ፍዝዝ አለ።
በዚያው ቅጽበት ሳሌም የሆነ ሃይል የነገራት ይመስል ዞር ብላ ወደ ዳሪክ ተመለከተች። ሁለት የሳሌም ትላልቅ አይኖች፣ ሁለት የዳሪክ አይኖች ተገናኙ። ለመጀመርያ ጊዜ ተያዩ። አይኖቿን ሲያይ የሆነ ነገር ወረረው። ከውስጧ፣ ከነፍሷ የሆነ ነገር፣ የሳሌም ቁራጭ የተላለፈበት፣ የመጣበት መሰለው። ምንድን ነው? እንዴት ያለ ስሜት ነው? እኔ አላውቅም። ይህን ማንም ሊያስረዳው ወይም ሊጽፈው አይችልም።
አሁን የዳሪክ የረገበ የልብ ትርታ ጨመረ። አሁንም ግን ፍዝዝ እንዳለ ነው። አልተነቃነቀም። አልሄደም። ዝም ብሎ ሳሌምን ያያል። ሳሌም የዳሪክ ሁኔታ ገርሟት ፈገግ አለች ፦ ያ የሁልጊዜ ስስ ፈገግታ በከናፍርቶቿ መሃል ብልጭ፣ ብቅ አለ። ያ ፈገግታ ዳሪክን አጠናቀቀው። ሳሌም ፦ በአይኗ ጀመረችው። ሳሌም፦ በፈገግታዋ ጨረሰቸው። ይህ ሁሉ የሆነው ምናልባትም በሲሶ ደቂቃ ነው። በነዚያ አርባ ምናምን ሰከንዶች ዳሪክ ፍቅር በሚባለው ጎዳና ዘጠና ዲግሪ ዞሮ መንገድ … ሳሌም ሊወድ “…ሀ…” ብሎ ጀመረ። ይህ የፍቅሩ አልፋ ነው። የመውደዱ መነሻ ነው።
ከፍቅሩ አልፋ ቀን ጀምሮ ዳሪክ ሳሌምን ማየት ርሃቡ ሆነ።
ሳታየው ያያታል።
ተደብቆ ያያታል።
ስትሄድ ያያታል።
ከሩቅ ያያታል።
ማየት፣ማየት፣ ማየት ደሞ ማየትና ማየት። ዝም ብሎ ሲያያት ቀናትና ሳምንታት አለፉ።
በዚህ አለም ቋንቋ የሁለት አለማት ልጆች ናቸው፦ ዳሪክና ሳሌም። ሃብታምና ድሃ ተብሎ በተራራቀ ሰው ሰራሽ መደብ ላይ የተቀመጡ ታዳጊዎች።
ዳሪክ ፦ ብቻውን ነው። ከጥቂት አመታት በፊት ወላጆቹ ተከታትለው ሞተዋል። ወላጆቹ ሞቱ፣ ተቀበሩ። ከዛን ቀን ጀምሮ ዳሪክን ሊያይ የመጣ የቅርብም፣ የሩቅም ዘመድ የለም። ዳሪክ ወሎ ሰፈር ውስጥ ካሉት ችግረኛ ጎረቤቶቹና የሰፈር ሰዎች በቀር ማንንም አያውቅም። ብቸኛ ነው።ዳሪክ መንግስት ት/ቤት ይማራል። ጎበዝ ተማሪ ነው። ታግሎ ይሰራል። በሳምንቱ መጨረሻ የታክሲ ረዳት ነው። በሳምንቱ የስራ ቀናት ደሞ ይማራል። ከ'ርዳታ ድርጅቱ ከሚያገኘው ጋር ተዳምሮ በቂው ነው።

👍44❤3👏1
ሳሌም፦ ሰፊና ብዙ ናት።
የምትኖረው ሃብታም አያቶቿ ቤት ነው። በአመት ሲበዛም በሁለት አመት እየመጣ የሚያያት አባቷ ለብዙ አመታት አሜሪካ የኖረ ዲያስፖራ ነው። ሳሌምን እጅግ ይወዳል። ከምትጽፍበት እርሳስ ጀምሮ እስከ ላፕቶፕ ድረስ ተጭኖ ይመጣላታል፦ ከሃገረ አሜሪካ። እናቷን አታውቃትም። በልጅነቷ እንደሞተች ነው ። እንግዲህ ሳሌም ትኖራለች፦ ቦሌ። ትመጣለች፦ በሹፌርና መኪና። ትሄዳለች ፦ በሌላ መኪና። ይኸው ነው።
ዳሪክ ሳሌምን ከማየት ውጪ እድልም ተሰፋም አልነበረውም።
ሁለቱን ያስተያያችው ጌታ ግን የበለጠ አላማ ነበረው። ዩኒቨርስን፣ ሁኔታዎችን አመቻችቶ እንዲገናኙ ...
አንድ ቀን …
ሳሌም ሙዚቃ መጫወት ስትጀምር ትመሰጣለች። ትሄዳለች። አትሰማም። አታይም። በሙዚቃው ትሰፍፋለች። ሰዐት ይረሳል። የዛን ለት ተመስጣ እየተጫወተች፣ የሚወስዳትን መኪና ስትጠብቅ ጊዜው መምሸቱን አላስተዋለችም። በመሃል ስልኳ ላይ ዛሬ መኪና እንዳትጠብቅ በታክሲ ወደ ቤት እንድትመጣ መልዕክት ገብቷል። አላየቸውም። ቆይቶ ደሞ ባትሪ የጨረሰው ስልክ ላይበራ ተኝቷል።
ሳሌም መምሸቱን ስታውቅ ተጣድፋ ተነሳችና ወደ በሩ አመራች። የቸርቹ ግቢ ጭር ብሏል። ሰው የለም።
“…ውይ ልጄ እስካሁን እዚህ ነሽ እንዴ?....” በሩን የሚጠብቁት ዘበኛ ነበሩ። ሰው መኖሩንም ያወቁ አይመስሉም።
“…ይቅርታ አባባ ስልኬ ባትሪ ጨርሷል። የሚወስደኝ ሹፌር ደሞ ቀረ። ስልክ ካሎት ልዋስና ልደውል?...” በትህትና ጠየቀች
“….የቸርቹን ስልክ መጠቀም እንችላለን ብለው በሩ ላይ ካለችው ትንሽ ክፍል ውስጥ የመስመር ስልክ አወጡ።….”
“…አመሰግናለሁ!...” ብላ የስልኩን እጀታ አነሳች። ማሰብ ጀመረች። ሌላ ጣጣ። ቁጥሮቹን ከየት ታምጣቸው? የሹፌሩን፣ የቤተሰቧን ስልክ አታውቅም። ሁሉም ያለው የሞባይል ስልኳ ላይ ነው። አሰበች። አሰበች። ምንም ነገር ሊመጣላት አልቻለም። ስልኩን በቦታው መለሰችና ለመሄድ ተነሳች።
ሳሌም ወደ በሩ ስታመራ “…ምነው ልጄ?...”አሏት ዘበኛው “….ማግኘት አልቻልሽም የመሂናውን ነጂ…”
“….አይ በቃ በእግሬ እሄዳለሁ አባባ….” ሳሌም የማንንም ቁጥር እንደማትውቅ መናገሩ አሳፍሯት ነበር።
“….ልጄ ተጠንቀቂ መጥፎ ሰፈር ነው….” አሉ ዘበኛው ሳሌም ከኋላዋ እያዩ “….ጌታ ከ አንቺ ጋር ይሁን።….”
ሳሌም ፈሪ አይደለችም። ግን የዛንለት የምትሄድበት መንገድና ጨለማው እያስፈራት እየተደነቃቀፈች መጓዝ ጀመረች። በኮረንኮንቹ ለደቂቃዎች ሄዳ ወደ ግራ ስትታጠፍ ከየት መጡ ሳይባሉ ሶስት ጎረምሶች ከየጥጋ ጥጉ ወጥተው ከፊት ለፊቷ ተደረደሩ።
ሳሌም ልቧ ደረቷን አልፎ ይወጣ ይመስል እንደ ታንቡር ይጮህ ጀመር። ጨለማ ነው ባ‘ካባቢው ሰው የሚባል አይታይም።
“…ም…ን … ም.. ንን ፈልጋችሁ?” ሳሌም ራሷን ለመቆጣጠር እየፈለገች
ጠቆር ያለው አንዱ ቀደሞ መናገር ጀመረ “…የቸርች በግ? የቅባት ልጅ ምነው ዛሬ ብቻሽን?...”
“…እ.. እ…” ሳሌም በፍርሃት መርበትበት ጀመረች።
“…ተረጋጊ እኛ ጀለሶችሽ ነን። መጀመሪያ እንተዋወቅ እኔ ቦዲ እባላለሁ…” እጁን ዘረጋና የሳሌምን ቀኝ ጨበጠ።
“…ካቹ…” አለ ሌላኛው
“…ዲናሬ…” አለ ሶስተኛው
“….ምንም አናረግሽም። የምፍለገው ነገር ያለሽን ነው። ያለሽን ጩባ፣ ኮይን ምናምን እጄ ላይ ዱቅ ታደርጊያለሽ። ከዛ ቀጥ ብለሽ ትከተይናለሽ። ወስደን ድፍን መሆንሽን በየተራ….” ቦዲ እጇን በትልቅ ሻካራ እጆቹ ጥብቅ አድርጎ ሲያወራ ሳሌም የሚለው ባይገባትም አደጋ ከፊቷ እንዳለ ገብቷታል።
“…እያረፍሽው ነው ያልኩትን ነገር?...” ጸጉሯን ሊነካ ሲጀመር
ብፈራም ለመታገል መሞከር አለብኝ ብላ አሰበች። “…ጫፌን እንዳትነካኝ…” እጁን ከጸጉሯ ላይ ስተገፈትረው ሁለተኛውንም እጇን ያዘው። ሁለቱን እጇን በአንድ እጁ ግጥም አድርጎ ሲይዝ መፈናፈኛ አጣች።
“…እጮሃለሁ…” ሳሌም የሞት ሞቷን እየታገለች
“…እንደዛማ አታደርጊም…” ትልቅ ሲንጢ አወጣ። “….ብትጮሂም ማንም አይደርስልሽም።….”
ሳሌም ተሰፋ ቆረጠች። ድቅድቅ ጨለማ፣ የማትውቀው ሰፈር በሶስት ጉልበተኞች ፊት ናት። ጌታ ሆይ እባክህን። ጌታ ራሱ እንዲወርድ ወይም ከመላዕክቶቹ አንዱን እንዲልክ በልቧ አጥብቃ ተመኘች።
“….ፒስ ነው ጀለሶች?...” ድንገት ከኋላዋ ድምጽ ሰማች
ሳሌም ዞር ስትል አንድ ጠይም፣ ረዘም ያለ፣ ከርዳዳ ጸጉር ያለው ልጅ ከኋላዋ እየመጣ ነው። መጣ። ቀረበና ቆመ። “…ሰላም ነው ጀለሶች?...”
“…ሰላም ነው አቡቲ? እንዴት ነሽ?...” ሁሉም እየተቀለሰልሱ ሰላም አሉት።
“…ምን እያረጋችሁ ነው ፍሬንዴን?...” በሳሌምና በሶስቱ መካከል ቆመ
“…ታውቃታለህ እንዴ ቺኳን?...” ቦዲ ጠየቀ
“…አዎ…” ጠይሙ ልጅ መለሰ “…ከባድ ጀለሴ ናት!...”
“…አላወቅንም አቡቲ ይመችሽ …በቃ እንሸበለላለን….” ብለው ሶስቱም ወደፊት መንገዳቸውን ቀጠሉ።
ሳሌም የተነጋገሩት ምንም ባይገባትም ከደቂቃዎች በፊት አውሬ የነበሩት ሶስቱ ባለጋራዎቿ በጠይሙ ልጅ ፊት እንደ ለማዳ የሳሎን ውሻ ሹክክ ብለው መንገዳቸው ሲቀጥሉ ግን የሆነ ተዐምር መስሏት ፈዘዛ ታያለች።
ሳሌም የሆነውን ማመን አቃታት። አየችው፦ ጠይሙን ልጅ። እንደ መልዐክ ሳታስበው ብቅ ያለው፣ በሷና በአጥፊዎቿ መካከል የተገኘው ፦ ጠይም ከርዳዳ ጸጉር ያለው ልጅ።
“…አመሰግናለሁ…” አይን አይኑን እያየች “….አመሰግናለሁ …”
“…ችግር የለውም…እዚህ ሰፈር ብቻሽን፣ በምሽት መሄድ የለብሽም። አደገኛ ነው።…”
“…እሺ.. ሁለተኛ አላደርገውም…” ባለችበት ደርቃ ቆማ
“…ልሸኝሽ?...” ልጁ ጠየቃት
ሳሌም አላቅማማችም “…እሺ…”
መሄድ ሲጀምሩ ሳሌም ሳታስበው በእጇ ክንዱን ይዛው ነበር። ከፍርሃቷ፣ ከድንጋጤዋ፣ ከመሸበሯ። ዋናው አስፋልት ድረስ እስኪወጡ ድረስ አልለቀቀችውም።
በአስፋልቱ እግረኛ መንገድ ላይ እየሄዱ መነጋገር ጀመሩ።
“…ቸርች አውቅሻለሁ ኦርጋን ስትጫወቺ… ስምሽን ግን አላውቀውም…”
“…ሳሌም ያንተስ?...”
“…ዳሪክ….”
ጥቂት ዝም ተባባሉ። “…እኔ ግን ቸርች አይቼህ አላውቅም?...”
“…በቸርቹ ከሚረዱት ልጆች አንዱ ነኝ። እኔም እኮ ሙዚቃ እወዳለሁ።…በትርፍ ጊዜ በ'ርዳታ ድርጅቱ ጊታር እየተማርኩ ነው።…”
“…እውነት። እኔም ጊታር እሞክራለሁ…” ሳሌም መለሰች
“…ትቺያለሽ?... እኔ በጣም ጀማሪ ነኝ።…”
“…አዎ ከፈለግክ አንዳንድ ኪዎች ላሳይህ እችላለሁ።…”
ዳሪክ ፊቱ በደስታ ተፍልቀለቀ “…በጣም ደስ ይለኛል ካልስቸገርኩሽ?...”
“….አልቸገርም።…”
ለሚቀጥለው ሳምንት ቅዳሜ ተቀጣጠሩ፦ ቸርች።
በተቀጣጠሩበት ቀን ሲገናኙ ከጥናታችው ይልቅ ያሳለፉት ሲያወሩ ነው።ዳሪክ ሲጠቀለል ሁለት ነገር ነው። ዳሪክ ደስታና ሳቅ ነው። ሳቁ ደግሞ ተላላፊ ነው።
ሳቁን ማስተላለፍ ካልቻለ ደግሞ ቀልድ ያመጣል። አንዴ ሰፈሩ የሰማውን፣ አንዴ እንደ ክበበው ገዳ (ሸምሱ) እየሆነ … “..መቶ ብር አማረኝ…” እያለ ሳሌምን ሲያስቃት፣ ሲያፍነከንካት ቆዩ። በሚቀጥለውም ቀንም፣ ከዛም፣ ቀጥሎም እንዲሁ። ዳሪክ ሳሌም ልብ ውስጥ የገባው በሳቆች ሰረገላ፣ በደስታ ፈረሶች ላይ ሆኖ ነው። ብዙ ጊዜ እንደምታውቀው ጓደኛዋ “..ዲ..” ብላ አቆላምጣ ልትጠራው ስትጀምር ጊዜ አልፈጀባትም።
አንዳንዴ አርፍዶ ይመጣል። ብዙ ጊዜ የሚያረፍደው ለዕለት ጉርሱ…ለስራው ሲሮጥ ነው። ሳሌም ግን ይህን አታውቅም።
አርፍዶ ሲደርስ “…አንተ ዲ ምን ሆነህ ነው?...” ሳሌም ትጠይቃለች።

👍34❤6🔥1😁1
“…ባክሽ ዛሬ …እንኳን በረሮች ናቸው…”
"የምን በረሮ?...” ሳሌም ቀልድ እንደሚጀምር ይገባታል
“…የኛ ቤት በረሮች ናቸዋ። በቃ ዛሬማ ጥለኸን አትሄድም ብለው የመጨረሻ እግሬን ይዘው አትሄድም ብለውኝ ግማሹ እያለቀሱ በቃ እነሱን ሳረጋጋ…”
እየሳቀ ሲነግራት ሳሌም መሳቅ ትጀምራለች “…ለመሆኑ ፍሊት ምናምን የለህም ለበረሮዎቹ?...”
“…ለኛ ቤት በረሮዎች? ትቀልጂያለሽ?....” ኮስተር ብሎ
“…ምነው?...”
“…ህም የወሎ ሰፈር በረሮ አታውቂያቸውም። ምንም በትነፊባቸው አፍንጫቸውን እንዲዚህ ይዘው ነው ላሽ…. የሚሉት...."አፍንጫውን በጣቶቹ ግጥም አርጎ ይዞ ያሳያታል።
ሳሌም ትስቃለች። ትስቃለች።
ስትስቅ ይቀጥላል። ከዛ ምድረ በረሮ አባበዬ ስወጣ ደሞ ጎረቤታችን እማማ ዘነቡ የዝክር ጌሾ እያስወቀጡ ነው። ቀስ ብዬ ላመልጥ ስል ‘…ና እንጂ አቡቲ …አንድ ሁለት በልና ሂድ…’ (ድምጹን እንደ አሮጊት አድርጎ ይቀይራል) ሲሉኝ “ …ኸረ እማማ ዘነቡ ጊታር ክላስ እየሄድኩኝ…” ነው ስላቸው
“…ምናልክ አቡቲ ደሞ ምንድን እሱ እስኪ አብራራ አይሉኝም። ካስር ደቂቃ የጥያቄና የማብራራት ቡሃላ ‘…ይሄ ፈርንጆቹ ትከሻቸው አንግበው የሚደበድቡትን ነው የምትለው…’ አሉኝ
‘..አዎ...’ ስላቸው
‘….እሱንማ አወቀዋለሁ እና እሱን እየተማርህ ነው?...’ አሉ …
እኔም ደስ ብሎኝ ‘..አዎ..’ ስላቸው
‘…በል ሂድ… እሺ ሂድማ… ‘ያ ላንድ ጥርስ የላት በዘነዘና ትነቀስ’… አሉ በል ሂድ ሽቦህን ወጥር።…”ብለው አበረታቱኝ እልሻለሁ።
ሳሌም አወራሩን፣ አገላለጹን እያየች ዝም ብላ ትስቃለች። እንባዋ ሲኪወርድ በሳቅ ትንከተከታለች።
እንዲህ እያለ የዳሪክ ሳቅ ለሳሌም ሳቅ ሆነ። ሳሌም ለመደችው። ሳሌም ወደደችው። አንዳንድ ቀን ዳሪክ ዝም ብሎ ይናፍቃት ጀመር። የሳምንቱ መጨረሻ ደርሶ እስክታየው አብራው እስክትስቅ ራሱ መታገስ አልችል አለች።
ከሶስት ወራት ቡሃላ አንድ ዕለት አብረው መዝሙር እየተጫወቱ ነው።
“..ዲ...” አለችው
“…አቤት ሳሌም…”
“…ለምንድን ነው ግን ሁሌ ሳሌም የምትለኝ የቁልምጫ ስም አትሰጠኝም?... ለምሳሌ ሴሊ፣ ሴሊና…” ሳሌም ቀልድ ፈልጋ ነበር።
ዳሪክ ግን የዛን ‘ለት ቀልድ አላመጣም። ዝም ብሎ ያያት ጀመር። ዝም ሲላት ሳሌም ከኦርጋኑ ላይ ቀና አለችና ዳሪክን ስታየው ዝም ብሎ እያያት ነው።
“….ታውቂያለሽ ሳስብ ነበር ምን ብዬ ልጥራሽ ብዬ። ምን ብዬ እንደምጠራሽ ታውቂያለሽ?...”
“…ምን?...” ሳሌም በጉጉት
“….የምወድሽ!...” ብዬ ነው የምጠራሽ “….የምወድሽ!…” ደገመው።
ሳሌም በትላልቅ አይኖቿ ታየው ጀመር። ዳሪክም መልሶ እንዲሁ።
አራት ንጹህ አይኖች ይተያያሉ። ሁለት የዋህ ልቦች ይሳሳባሉ፦ እንደዚህ።

👍43❤8🥰3
#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ሁሴንና ሰሎሞን ለመዝናናት ተያይዘው ወጥተዋል፡፡ቦታው ሃያ ሁለት አካባቢ ነው፡፡ ሠዓቱ ከምሽቱ 4፡45 ሆኗል፡፡ ያሉበት ጭፈራ ቤት በጠጪዎችና በቡና ቤት ሴቶች ተሞልቷል፡፡ በዲጄው ፍላጎት በሚለቀቁ ሙዚቃዎች የተወሠኑ ሠዎች ይውረገረጋሉ፡፡ ሠሎሞንና ሁሴን አንድ ጥግ ይዘው መጠጣቸውን ከጨዋታ ጋር እያወራረዱት ነው፡፡
‹‹ቆይ አንተ ጨክነህ እንደ እኔ ወንደላጤ ሆንክ ማለት ነው?›› ሁሴን ነበር ጠያቂው፡
‹‹ኧረ !!ትቀልዳለህ እንዴ! እስከዛሬም የተጃጃልኩት ለልጆቼ ስል ነበር፡፡››
‹‹ቆይ በቤተክርስቲያን ስርዓት አይደል እንዴ ያገባሀት? እና ዝም ብሎ መፋታት ይቻላል…?
ከምትፈራውስ ከፈጣሪ ጋርስ አያቀያይምህም?››
‹‹ዝም ብለህ አትበለኝ፤ዝም ብዬ አይደለም የፈታኋት፡፡ በእኛ ሀይማኖት ፍቺ የሚፈቀዱባቸው ሦስት መሰረታዊ ሁኔታዎች አሉ፡፡ አንደኛው ከተጋቢዎቹ አንዱ ሲሞት፣ ሁለተኛ ከሁለት አንዱ በዝሙት ኃጥያት ከወደቀ ሲሆን ሦስተኛው ደግሞ የማይድን የአዕምሮ በሽተኛ ሲኮን ነው፡፡››
ሁሴን ከአፉ ተቀበለው፡፡ ‹‹ገባኝ... ገባኝ... ታዲያ እኔ እስከማውቀው ድረስ ያንተዋ አልሞተች ወይም የአዕምሮ ህመምተኛ አልሆነችም የቀረው ዝሙት ያልከው ጉዳይ ደግሞ አንተም እየተንቦራጨክበት ነው፡፡ >>
‹‹ቢሆንም እኮ እኔ ወንድ ነኝ፡፡››
‹‹መፅሀፉ ለወንዶች ልዩ ፍቃድ ይሰጣል ማለት ነው?>>
‹‹ባክህ ነገር አታጣም፡፡ ያው እንደምታውቀው እኔ ሆነ ብዬ ሳይሆን አንዳንዴ ስጠጣና ስበሳጭ የምፈፅመው ስህተት ነው፡፡ ለዛውም ከቡና ቤት ሴቶች ጋር ነው፡፡ አንዴ ያወጣኋትን ሴት መልሼ እንደማልደግማት ታውቃለህ፡፡ ይሄንን የማደርገው ደግሞ ከማንም ከሌላ ሴት ጋር ፍቅር እንዳይዘኝ ስለምፈራ ነው፡፡ እሷ ግን ሥጋዋንም ልቧንም ጠቅላላ እሷነቷንም ነው ያስረከበችው፡፡ ስለዚህ ለእኔ ምን ይተርፈኛል? ምንም … ፡፡ባዶ በድን ገላና የተራቆተ ልብ...
በቃ፡፡››
‹‹እኔ በበኩሌ ለውሳኔህ ያቀረብከው ምክንያት አላሳመነኝም፡፡ የሀይማኖቱን አላውቅም፡፡ በሞራል በኩል ግን ኢፍትሃዊነት ይመስለኛል፡፡››
ሠሎሞን ተበሳጨ <<አቦ በቃ ጨዋታ ቀይር፤ልዝናና ነው የመጣሁት፤በደስታ ልጠጣበት ፡፡››
ሁለቱም ፊት ለፊታቸው ያለውን የቢራ ጠርሙስ አነሱና ወደ ጉሮሮአቸው ካንቆረቆሩለት በኃላ መልሰው አስቀመጡ፡፡ አዲስ የጨዋታ ርዕስ ለማምጣት የቀደመው አሁንም ሠሎሞን ነበር፡፡
<<ለመሆኑ የመጽሀፉ ሽያጭ እንዴት እየሆነ ነው?>>
‹‹አትጠይቀን ባክህ ... የተአምር ያህል ነው፡፡ በቅርብ ሁለተኛ ዕትም ማሳተማችን የግድ ነው፡፡ በየጋዜጣውና የየሬዲዮ ጣቢያው መነጋገሪያ ርዕስም ሆኗል፡፡ የድርሰቱ ምርጥነት ብቻም ሳይሆን የደራሲዋ ማንነት አለመታወቅ ያልተለመደ ክስተት በመሆኑ መነጋገሪያ እንዲሆን የራሱን አስተዋጽኦ ሳያደርግ አይቀርም፡፡››
‹‹ቆይ ደውላልህ አታውቅም?››
<<ማ? >>
‹‹ጣኦትህ ነቻ...ደራሲዋ?››
‹‹መፅሀፉ ከታተመ ወዲህ አንዴ ደውላልኝ ነበር፡፡ በጣም የሚገርመው ስሜት የለሽ ሆና ነበር ያናገረችኝ፡፡ መቼም አንድ ጤነኛ ሠው የመጀመሪያ ልጁን ሲወልድ እንደሚፈነጥዝ ሁሉ አንድም ደራሲ የመጀመሪያ መፅሐፉ ሲታተምለት በደስታ መፍነክነኩ የሚጠበቅ ነው፡፡ እሷ ግን ደንታም የሠጣት አይመስለኝም፡፡ ስለ ሌላ ነገር ነበር የምታወራልኝ፡፡››
‹‹አሁንም ልታገኝህ አትፈልግም ማለት ነው?››
‹‹እሷን ለማግኘት አንድ አማራጭ ብቻ እንዳለ ነግራኛለች፡፡››
‹‹ምንድነው .. እንዴት አይነት አማራጭ?››
‹‹አልነገረችኝም...ትንሽ ታገስ አለችኝ፡፡››
‹‹አሁንስ አበዛችው…ቆይ እሷ እንደኛው ሠው አይደለችም እንዴ? ነው ወይስ የመላዕክት ዝርያ አለባት ይሆን?... ብቻ እኔን ለማየት አርባ ቀንና ለሊት ፁምእንዳትልህ!››
‹‹ምን ችግር አለው…እጾማለኋ፡፡ ጣኦቴ አይደለች? ሠው ለጣኦቱ ነፍሱንስ ለመስዋዕትነት ይለግስ የለ?››
‹‹ወይ ጉድ!! በሕወቴ ማየት እፈልግ የነበረው አንድ ነገር ያንተን በሴት ፍቅር ተንበርክከህ ስትንገላወድ ማየት ነበር፡፡ አንድ ቀን እንደሚሆን እምነቴ ቢሆንም እንዲህ መላ ቅጡ በጠፋ መልኩ ይሆናል ብዬ ግን ፍፁም ግምቱ አልነበረኝም፡፡ በነገራችን ላይ ይህቺ ደራሲህን ሳስብ አንድ ነገር ትዝ አለኝ፡፡ የመጽሐፍ ምረቃው ቀን ፎዚያን በጣም ስከታተላት ነበር፤ ስታነብ ታሪኩ የራሷ ይመስል ተመስጣ ነበር፡፡››
‹‹አዋ እኔም ያንን ታዝቤለሁ፡፡››
‹‹ቆይ የሥነ ጽሁፍ ችሎታ አላት እንዴ?››
‹‹እኔ እስከማውቀው ድረስ የላትም፤አንባቢ እንደሆነች ግን አውቃለው….ግን ምነው ጠየቅከኝ?››
‹‹አይ የሆነ ጥርጣሬ ነገር በውስጤ ተጭሮ ነው፡፡ >>
ሁሴን ተንከትክቶ ሳቀ፡፡ ‹‹ደራሲዋ ፎዚያ ነች ልትል ነው?››
‹‹ነች አላልኩም፤ ተጠራጠርኩ እንጂ፡፡ አንዳንዴ በዚህ ዓለም ላይ ሊሆን አይችልም የምትለው ነገር ሆኖ ታገኘዋለህ…።››
‹‹እሱ ትክክል ነህ፡፡ ጥርጣሬህ ግን መሰረተ ቢስ ነው …፡፡›ንግግሩን ሳይጨርስ በዙሪያቸው ስትሽከረከር የቆየች አንዲት የ18 ዓመት ውብ ወጣት እጎናቸው ባለው ባዶ ወንበር ላይ ሳታስፈቅድ ተቀመጠች፡፡ እርግጥ ለመቀመጥ እንድትደፍር ያደረጋት የሰሎሞን ዓይኖች ለተደጋጋሚ ጊዜ መላ አካሏቷ ላይ ሲሽከረከር ደጋግማ ስለያዘችው ነው፡፡
በመኮሳተር ንግግሯን ጀመረች፡፡‹‹ቆይ እናንተ የመጣችሁት ልትዝናኑ ነው ወይስ የፓርላማ ውይይት ልታካሂዱ?›› ሁለቱም በአግራሞት አፍጥጠው ቢመለከቷትም መልስ ለመስጠት የቀደመው ግን ሲያፈጥባት የቆየው ሠሎሞን ነՈԸ::
‹‹እስከ አሁን ስትሰልይን ነበር እንዴ?››
‹‹ምን እሰልላችኋለሁ... ገርማችሁኝ እንጂ ፡፡ አሁንም እስቲ በደረቁ አታናዙኝ…ጋብዙኝ፡፡››
‹‹እዘዢ›› ሁሴን ነበር የፈቀደላት፡፡ አስተናጋጁን ጠርታ ቢራ አዘዘች፡፡
ሠሎሞን‹‹ቆንጆ ነሽ፡፡›› አላት ፡፡
ትላልቅ አይኖቿን አንከባለለችበትና ፈገግ ብላ ‹‹ሊበሏት ያሠቧትን ወፍ ጅግራ ነሽ ይሏታል፡፡›› አለ ያገሬ ሠው ስትል›› ተረተች
‹‹እንዴት ማለት?›› አላት ሠሎሞን፡፡
‹‹አይገባህም... ቅኔ አልተማርክም እንዴ?››
‹‹ተይው እሱ ስለ ስሚንቶና ድንጋይ ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡›› የሁሴን ንግግር ነበር፡፡
‹‹ግምበኛ ነው እንዴ?›› ከቢራዋ እየተጎነጨች በፈገግታ ጠየቀች፡፡
‹‹ትክክል ነሽ..…የግንበኞች ሀለቃ ነው››
‹‹እሺ አንተስ?››
ሠሎሞን ብድሩን ለመመለስ ተሽቀዳደመ፡፡ ‹‹እሱማ ያው ወሬ ለቃቃሚ ነው ... ወሬ ይገዛል፤ ይሸጣል፡፡››
‹‹ኧረ... እኔ ጋር ብዙ ወሬ አለ፤ ለምን አትገዛኝም.. ? ግን ደስ የምትሉ ጓደኛሞች ናችሁ፤ተረባችሁ ደስ ይላል፡፡››
ሠሎሞን እጁን አንስቶ ጭኗ ላይ በማስቀመጥ ጨመቅ እያደረጋት ወሬውን ቀጠለ ‹‹ተረብ እኮ አይደለም ...እውነቴን ነው የወሬ ነጋዴ ነው ...እሱና መሰሎቹ ግን ለራሳቸው ቆንጆ ስም ሠይመዋል፡፡ ስራችሁ ምንድነው ? ሲባሉ ደረታቸውን ነፍተው ጋዜጠኛ ይላሉ… ።››
ሁሴን ተቀበለው፡፡ ‹‹ልክ እናንተም ስትጠየቁ ኢንጅነር እንደምትሉት ሁሉ፡፡››
‹‹በቃ ይበቃችኋል እኔ ስለማንነታችሁ በቂ መረጃ አግኝቼያለሁ፡፡››
‹‹ኮሚሽን እፈልጋለሁ፡፡›› አላት ሁሴን፡፡
<<ለምኑ?>>
‹‹አያያዙን ሳየው የሚለቅሽ አይመስለኝም፤ ታዲያ ስትደራደሩ ምን ያህል መክፈል እንደሚችል እንድታውቂ መረጃ ሠጥቼሻለሁ፡፡››
‹‹ባክህ ስንት ቀብቃባ ኢንጅነር አይተናል መሰለህ!!>>

👍102❤8😱3👏1
እንዲህ እንዲህ እየተጫወቱ የሚበቃቸውን ያህል ከጠጡና የሚበቃቸውን ያህል ካመሹ በኋላ ሁለት ሆነው የገቡበትን ቤት ሦስት ሆነው ለቀቁ፡፡ሠሎሞን ወጣቷን ሸጉጦ በራሱ መኪና ገብቶ ሁሴንን ተሠናበተና ተፈተለከ፡፡
ሁሴንም የራሱን መኪና አስነስቶ ጉዞ ጀመረ፡፡ ብቸኝነት ተሠማው፡፡ ተንቀሳቃሽ ስልኩን አንስቶ ደወለ፡፡ ትንግርት ጋር ነው እየደወለ ያለው፡፡በጣም ናፍቃዋለች፤እንዲህ ሆድ ሲብሰው ሁሌ እሷ ነች የምታሰኘው፤ከአራት ጥሪ በኋላ ተነሳ፡፡
« ምነው ጋሼ?>>
‹‹እንዴት ምነው?››
‹‹እኩለ ለሊት እኮ ተቃርቧል፡፡››
‹‹ተኝተሸ ነበር እንዴ?››
‹‹ነገሩ እንኳን አልተኛሁም ... ለመሆኑ የት ነህ? መኪና እየነዳህ መሠለኝ፡፡››
‹‹አዎ ከዛ ቦርጫም ጋር ዘና ብዬ ወደ ቤት እየገባሁ ነው፡፡››
‹‹ጥሩ ነዋ …፡፡››
‹‹አሁን የደወልኩት ላገኝሽ ስለፈለኩ ነው፡፡››
<<ምን??>>
‹‹ምነው ደነገጥሽ ..?››
‹‹አሁን እኮ እንደበፊቱ ሸርሙጣ አይደለሁም፡፡ በፈለክ ሠዓት ገንዘብህን ከፍለህ ልታገኘኝ አትችልም፡፡›› በማለት ጆሮው ላይ ጠረቀመችበት…ግር አለው፡፡ሲደውልላት እሷ ባሰበችው መልኩ ፈፅሞ አስቦት አልነበረም፡፡ ስለናፈቀችው ነበር ላግኝሽ ያላት፡፡ በዚህ በዚ መልክ ሆደ ባሻና ቁጡ ስትሆን አይቷት አያውቅም፡፡.....
✨ይቀጥላል✨
ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰቦች
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
ሁሴንም የራሱን መኪና አስነስቶ ጉዞ ጀመረ፡፡ ብቸኝነት ተሠማው፡፡ ተንቀሳቃሽ ስልኩን አንስቶ ደወለ፡፡ ትንግርት ጋር ነው እየደወለ ያለው፡፡በጣም ናፍቃዋለች፤እንዲህ ሆድ ሲብሰው ሁሌ እሷ ነች የምታሰኘው፤ከአራት ጥሪ በኋላ ተነሳ፡፡
« ምነው ጋሼ?>>
‹‹እንዴት ምነው?››
‹‹እኩለ ለሊት እኮ ተቃርቧል፡፡››
‹‹ተኝተሸ ነበር እንዴ?››
‹‹ነገሩ እንኳን አልተኛሁም ... ለመሆኑ የት ነህ? መኪና እየነዳህ መሠለኝ፡፡››
‹‹አዎ ከዛ ቦርጫም ጋር ዘና ብዬ ወደ ቤት እየገባሁ ነው፡፡››
‹‹ጥሩ ነዋ …፡፡››
‹‹አሁን የደወልኩት ላገኝሽ ስለፈለኩ ነው፡፡››
<<ምን??>>
‹‹ምነው ደነገጥሽ ..?››
‹‹አሁን እኮ እንደበፊቱ ሸርሙጣ አይደለሁም፡፡ በፈለክ ሠዓት ገንዘብህን ከፍለህ ልታገኘኝ አትችልም፡፡›› በማለት ጆሮው ላይ ጠረቀመችበት…ግር አለው፡፡ሲደውልላት እሷ ባሰበችው መልኩ ፈፅሞ አስቦት አልነበረም፡፡ ስለናፈቀችው ነበር ላግኝሽ ያላት፡፡ በዚህ በዚ መልክ ሆደ ባሻና ቁጡ ስትሆን አይቷት አያውቅም፡፡.....
✨ይቀጥላል✨
ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰቦች
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
❤57👍29
የፍቅር ‘ርግቦች
ክፍል አስር፦ ‘የምወድሽ አትውረጂ’
©ሃሴድ አጋፔ ፍቅር
‘..የምወድሽ…’ እያለ ሲጠራት ጥቂት ሳምንታት ቆዩ።
ባንዱ ቅዳሜ…
“…ለምንድን ነው የምትወደኝ ግን?...” ሳሌም ኮስተር ብላ ፊት ለፊት አይኑን እያየችው ጠየቀቸው፦ ዳሪክን
ሳሌም የዋህ ብትሆንም ብልህ ናት። ወደድኩሽ ያላትን ሁሉ እንዲሁ ቃሉን አምና የምትቀበል ልጅ አይደለችም። ዳሪክ ወደድኩሽ ስላላት፣ ‘..የምወድሽ..’ ብሎ ስለ ጠራት ብቻ ልቧን ሙሉ ለሙሉ አሳልፋ መስጠት ሞኝነት መሆኑን ታምናለች። ከዚህ በፊት ወደድኩሽ ላሏት ጥቂት ወንዶች ይህን ጥያቄ አቅርባለች። ብልህነቷ ደሞ ጥያቄውን የምታቀርበው አሳቻ ሰዐት ላይ ሳይታሰብ ነው። ያልተዘጋጁ አፍላ የስሜት አፍቅሪዎች የሚሉት ጠፍቷቸው ሲደናበሩ ወይም ለምን ተጠይኩኝ ብለው ሲቆጡ ሳሌም በስስ ፈገግታዋ ታያቸዋለች። ከዛም በልቧ ታስባለች '...እውነተኛ ፍቅር እኮ አይደናበርም።አይደነግጥም። አይቆጣም። ፍቅር ትሁትና የተረጋጋ ነው። ፍቅር መልስ አለው። ለምን እንደወደዱኝ ሳያውቁ ወደድኩሽ ለማለት እንዴት ይደፍራሉ?...' ደፋሮች!!!.... በቃ ወደድኩሽ ያሏት ወንዶች ሁሉ ይቺን ጥይቄ ማለፍ ሳይችሉ ተሰነካክለው ወደቁ።
ዛሬ የዳሪክ ተራ ነው። ዳሪክ ጥያቄውን ከሰማ ቡሃላ መልስ አልመለሰም። ዝም ብሎ አይን አይኗን ሲያይ ጥቂት ጊዜ ቆየ።
“…ለምን ዝም ብለህ ታየኛለህ ዲ?... ጥይቄውን መልስ እንጂ?...”
ዳሪክ በዛው መረጋጋት ከኪሱ በልብ ቅርጽ የተጣጠፈች ወረቀት አወጣ “…የምወድሽ…”
“..አቤት..”
“….ይህን ጥያቄ ስለጠይቅሽኝ በጣም ደስ ብሎኛል። በየቀኑ ይህን በጠየቀሽኝ ብዬ ከልቤ ስመኘው ነበር። መልሱን እዚህ ወረቀት ላይ ተጽፎ ታገኚዋለሽ።…”
ሳሌም ተገርማ ዳሪክ የሰጣትን የልብ ቅርጽ ወረቀት ተመለከተች። ዳሪክ አንድ ርምጃ ቀድሟታል። ከሷ ወደፊት ሄዷል። ተዘጋጅቷል።ፍቅሩ መልስ አለው።
የሰጣትን ወረቀት ከፍታ ለማንበብ ስትጣደፍ ዳሪክ እጇን ያዘው “…የምወድሽ እዚህ አይደለም የምትከፍቺው። ….ይህን የምትከፍቺው፣ የምታነቢው ቤት ስትደርሺ ነው እሺ…..” በትህትና ነገራት
“…እሺ…”
ሲጫወቱ፣ ሲስቁና ደሞ ትንሽ ሙዚቃውን ሲሰሩ ቆዩና ተለያዩ። ሳሌም ቤት እንደደረሰች ወረቀቱን ከፍታ ማንበብ ጀመረች።
ግጥም ነው። በራሱ በዳሪክ እጆች የተጻፈ።እንዲህ ይላል፦
ገጣሚው ሲገጥም - ለፍቅሩ - ስንኝ ሲደረድር
“…ያደምቀኛል ብለሽ ያሰብሺውን ሁላ
እግዜር ከኔ ወስዶ ከሰጠሽ ቡሃላ
ያስቀርልኝ አይኔን
አንቺን ማየት ብቻ ያኖረኛል እኔን ….” ብሎ ጽፎ ነበር
ውዴ..
ለኔ ግን የተቃራኒ ነው- አንቺን ሳይሆን ማየት
አንቺ እኔን ስታዪኝ- ‘ሚደምቅልኝ ህይወት
ውዴ..
አይኖችሽ ሳያዩኝ ህይወቴ አንዲህ ነበር፦ ክረምት!
እዛ ክረምት ውስጥ….
የዶፍ ጠብታዎች፣ ጭጋግ ጉሞችና ነጓድጓድ አሉበት!
(…እኔ ሳይህስ ብትይኝ?...)
ስታዪኝ…
ከዶፍ ጠብታዎች- ደረጃ ገንብቼ - ከዳመናት በላይ - ከፍ ብዬ ወጣለሁ
(…ከፍታው ላይ ሆኜ ….ከዛስ?...)
ከዛ- ከነጫጭ ጉሞች - እልፍኝ ሰርቼ - የጸሀይን ጥልቀት - ቁጭ ብዬ አያለሁ
(….ቀጥሎስ?...)
ከነጎድጓዱ ድምጽ - ሙዚቃ ቃኝቼ - ለጌታ አዜማለሁ
ስታዪኝ …
ድም!... ድው! … (ብዙ ሰከንዶች)…ድም!... ድው..
…ታንቡር እንዳይመስልሽ የልቤ ድምጽ ነው
ስታዪኝ …
በደረቴ ይረግባል - የልቤ ትር-ርርታ
እ..ፎፎፎፎፎፎፎፎይ - በሳንባዬ ይረጋ -ጋል- የስትንፋሴ እፍታ
በሰርክ ላይ ጠሎት - ጥሞና እንደገባች
ነፍሴ ስጋዬ ውስጥ - ጸጥ ረጭ ትላለች
ስታዪኝ …
በብርሃን ፍጥነት - ይዛኝ ትሄዳለች -
የቆምኩባት ምድር
ሰማይ ፈለኮችን - የጸሐይ ጭፍሮችን - አልፋ - ወደ አዲስ ጠፈር!
ምድር ስትሄድ
ሲያሮችን አልፋ….
ዓለማትን አልፋ…
ከዋክብቶችን አልፋ…
(…አቤት ሲያምር…)
ስትሄድ
ስትሄድ
ስትሄድ
ስትሄድ
ሄዳ ሄዳ ስትቆም-
አዲስ ህዋ ደርሳ - ባ'ዲስ ም'ዋር አርፋ- አዲስ ምድር ስትሆን - አይኖቼ ያያሉ
በዛ አዲስ ምድር ፦ ሶስት ጸሐዮችና-ሰባት ጨረቃዎች- ውስጤን ያደምቃሉ
ኮረብቶች በፍቅር ዳንኪራ ይመታሉ
ፏፏቴዎች ከሰማይ - ሿዋዋዋዋዋዋ- ወደ ታች ይፈሳሉ
በፏፏቴው ዙሪያ
የሰማይ አእዋፍ - ‘ ፍቅር የሁሉም ስር..’-
ብለው ያዜማሉ
ከፏፏቴው ስርም - አናብስትና ጎሽ-
ተቃቅፈው ይስቃሉ!
የምወድሽ፦ እኔ የወደድኩሽ
ስታዪኝ ባይኖችሽ
ደሞ..
ባይኖችሽ ስታዪኝ
ከላይ እንደፃፍኩት- እንዲህ ነው የሚያረገኝ
የምወድሽ፦ እባክሽን ….እባክሽን …እ…ዪ…ኝ!
ሳሌም ይህን ስዕላዊ ግጥም/ስድ ንባብ የመሰለ ጹህፍ አነበበችው። ደግማ አነበበችው። የአማርኛ መዝገበ ቃላት አውጥታ ሲገባት፣ ስክትረዳው ድረስ አነበበችው። መኝታዋ ላይ ሆና ልትሸመድደው ትንሽ ስኪቀራት ድረስ አነበበችው። አንብባ ስትጨርስም ዳሪክን ልትወደው፣ ከልቧ ልታፈቅረው በውስጧ የሆነ የፍቅር ትንሽ ብቅለት ሲበቅል ተሰማት። ያቺ የበቀለች የፍቅር ዘር ደስ ደስ የሚል፣ በውስጧ ሳቅ፣ ሳቅ የሚል ስሜት ይዞ መጣ። ከዛ የደስታ ስሜት ጎን ለጎንም ሳሌም የማታውቀው የፍቅር አለም ውስጥ ልትገባ መሆኑን ስታውቅ ፍርሃት፣ ፍርሃት አላት። ሳሌም ፈራች። ያስፈራት የማታውቀው አዲሱ የፍቅር አለም ነው። ያስፈራት ከጨዋታውና ሳቁ በስተቀር ብዙም የማታውቀውን ዳሪክን ለማፍቀር መጀመሯ ነው። አሰበች አሰበችና ለራሷ ወሰነች፦ ይህን ልጅ ልርቀው ይገባል። ከዚህ ቡሃላ ከሱ ጋር አልገናኝም። ቅዳሜ፣ ቅዳሜ ቸርች አልሄድም። ውሳኔውን ተገበረችው። ሁለት ቅዳሜዎች ቀረች።
በዛው ሰሞንም ሳሌም በባህሪዋ ከሷ ለየት ከሚሉ የት/ቤት ጓደኞች ጋር ወዳጀነት መሰረተች። አለ አይደል …. ፓርቲ፣ መዝናናት፣ መጨፈር ከሚወዱ ወጣት ሴቶች ጋር።ሳሌም ይህን ለማድረግ የተነሳችውም ዳሪክ በልቧ ውስጥ የጫረውን ፍቅር የሚያስቆም ጊዚያዊ መፍትሄ፣ ጊዜዋን የሚገል ነገር ፍለጋ ነው።
በሶስተኛው ሳምንት አርብ ቀን ቦሌ መንገድ ላይ ካሉ አንዱ ጭፈራ ቤት ለመግባት ቆማለች፦ ከነዚህ አዲስ ጓደኞቿ ጋር።
ድንገት ከኋላዋ ድምጽ ሰማች “…የምወድሽ…”
ሳሌም ዞር ስትል ዳሪክ ቆሟል። ዳሪክ የታክሲ ረዳት ነው። ከሚሰራበት ታክሲ ላይ ተሳፋሪዎች ሲጠራ ነው ድንገት ሳሌም ቆማ ያያት።
ሳሌም በድንጋጤ የምትለው ጠፍቷት ስታየው “…የምወድሽ እዚህ ምን ታደርጊያለሽ?...” ተኮሳትሮ ጠየቃት። አጠያየቁ እንደ ታላቅ ወንድም፣ እንደ ጠባቂዋ ...በስልጣን ነበር።
ሳሌም አሁንም በድንጋጤ ትንሽ ሃፍረትም ተሰምቷት ዝም ብላለች። አብረዋት ያሉት ሁለት አዲስ ጓደኞችም በእጁ ሳንቲምና ብር የያዘውን ጠይም ልጅና ሳሌምን ይመለከቱ ጀመር።
“…አንድ ጊዜ ለብቻሽ ላነጋግርሽ?...”
“…እ…” ሳሌም ጓደኞቿ እያየች ስታንገራግር ዳሪክ ቀስ ብሎ እጇን ይዞ ሳብ አደረጋት። “…አይዞሽ ብዙ ጊዜ አልወስድም። ትንሽ ላነጋግርሽ።…” ሳሌም የ‘ፍረቷን ተከተለችው።
“….የምወድሽ ምን እያደረግሽ ነው እዚህ? እዚህ ጭፈራ ቤት ልገባ ነው እንዳትይኝ ብቻ?...”
“…አይደለም…” ሳሌም ለመዋሸት ጀመረችና እንደማያዋጣ ስታውቅ “…ቢሆንስ ምን ችግር አለው ከጓደኞቼ ….”

👍37❤9🥰1👏1😁1
“…ምን ችግር አለው?...” አቋረጣት “…ይህን ቤት በዝና ሰምቼዋለሁ ስንት አይነት ድራግ መጠጥ ውስጥ እየተጨመረ ብዙ ክፋት የሚደረግበት ቤት ነው። ብዙ ችግር አለው የምወድሽ…”
ሳሌም አጎንብሳ አንገቷን ሰብራ ዝም አለች።
ዳሪክ ቀጠለ “…እመኚኝ የምወድሽ ይህ ስፍራ አንቺን አይመጥንሽም! ... ደሞ እኮ አንቺ ራስሽ እዚ ጭፈራ ቤት ለመግባት አትፈልጊም። ከልብሽ፣ ከውስጥሽ አትፈልጊም። ይህን እንዴት እንዳወቅኩ ልንገርሽ?..”
ዳሪክ የሚለው እውነቱን ነው። ሳሌም የመጣችው በግፊት ነው…. በአዲስ ጓደኞቿ ግፊት።
“…ተናገር እስኪ በምን አወቅክ?...” ሳሌም እንዳጎነበሰች።
“…አየሽ ጓደኞችሽ ሁለቱም ከራቁት መለስ ያለ ልብስ ነው የለበሱት። አንቺ ግን ጤናማ አለባበስ ነው የለበስሸው። ውስጥ ገብተሽ የምትለውጪውን ሚኒ ስከርት ወይም ቁምጣ በቦርሳሽ ደብቀሽ ነው የመጣሽው።" በጀርባዋ ያነገበችውን ቦርሳ እያመለከተ " እንደዚህ የማታምኚበትን፣ የማትፈልጊውን ነገር አታድርጊ፣ የምውድሽ ካለሽበት ከፍታ ላይ አትውርጂ።….ለጓደኞችሽ ….”
“….ለጓደኞቼ አይደለም….” ሳሌም ተቃወመች “….ደሞ ምን ታውቃለህ?... እነዚህን ጓደኞቼን ጌታ እኔን ተጠቅሞ ሊቀይራቸው ይችላል።…”
“..ከምርሽ ነው? …” ዳሪክ ተገርሞ
“….አዎ በእኔ ሊቀይራቸው ይችላል….” ሳሌም የመጨረሻ መከላከያዋ የምትለውን ሃሳበ ወረወረች።
“…የምወድሽ ..እኔ ግን ሳየው እነሱ አንቺን እየቀየሩ ነው የሚመስለው። ከከፍታሽ ላይ እየተንከባላልሽ ነው የሚመስለው…”
“…ከፍታ… ከፍታ… የምን ከፍታ ነው የምታወራው?...” ሳሌም ግራ ተጋብታ
“…አልገባሽም ?...”
“…አልገባኝም…”
“….ይቅርታ የምወድሽ….” ዳሪክ የሆነ ነገር የሚፈልግ ይመስል ዙሪያውን መመልከት ጀመረ። በስተቀኛችው ሰው የሌለበት የሆነ የህንጻ ደረጃ ሲመለከት ደስ አለው። “…ነይ እዛ ደረጃ ጋር እንሂድና ስለ ከፍታና መውረድ አሳይሻለሁ።…”
ሳሌም በገረሜታ እያየችው ተከተለችው። ተከታትለው ሲሄዱ ዳሪክ ከሚሰራበት ሚኒ ባስ መስኮት ቢጠራው ቢጠራው አልሰማ ስላለው ሹፌሩ ወርዶ መጣ።
“…አንተ አቡቲ ስራህን ትተህ የት ነው የምትዞረው?... ናና ጥራ እንጂ…” ዳሪክ ላይ አፈጠጠበት።
“…ሳንቾ ይቅርታ መስራት አልችልም ከምወድሽ ጋር የማወራው ነገር አለ…”
“ ከማን ጋር?.. ማናት ወደድኩሽ?...” ሹፌሩ ፊቱን አኮሳትሮ
“…ሳንች ረጅም ታሪክ ነው። ይኸው እንካ የቀረው ሂሳብ …ጆርናታው ይብራብኝ ዛሬ።….” ዳሪክ በእጁ ያለውንና ሌሎች ብሮችን ከኪሱ አውጥቶ ለሾፌሩ ሲሰጠው ሹፌሩ ባለማመን ተመለከተው። መጀመሪያ እውነት አልመሰለውም። ዳሪክ የምሩን መሆኑን ሲያውቅ ግን የተለያየ አይነትና ጥራት ያላቸው የስድብ ዝናብ አዝንቦበት ወደ መኪናው ሄደ። ዳሪክ ግን የሚሰማበት ጆሮ አልነበረውም።
ወደ ደረጃው እየሄዱ “…ታክሲ ላይ እንደዚህ እንደምትሰራ አልነገርከኝም?...” ሳሌም ነበረች
“..የምወድሽ አልጠይቅሽኝም እኮ። ብትጠይቂኝ ስለ እኔ ብዙ የምነግርሽ ነገር አለ…” በፈገግታ “…አሁን ግን ወደ ከፍታው ምሳሌ…”
ደረጃው ጋር ደረሱ።
ዳሪክ ጀመረ። “…ከከፍታ ስለመውረድ በምሳሌ ላስረዳሽ።ምሳሌው መሰራት ያለበት አንዳችን ጠረጴዛ ላይ ቆመን ሌላችን ደሞ መሬት ሆነን ነበር። ቢሆንም ደረጃ ላይም ይሰራል። …የምወድሽ ደረጃው ላይ ውጪ…”
ሳሌም ምን እንደሚያደርግ ለማየት አንድ ደረጃ ወጣች።
"...ትንሽ ወደላይ እስከ ሶስት ወይም አራት ደረጃዎች ውጪ።..."
ሳሌም ሶስተኛው ደረጃ ላይ ወጥታ ቆመች።
“…አሁን እጅሽን ስጪኝ ። ..."
እጇን ስትሰጠው ዳሪክ ጨብጦ ያዛት።
"...አሁን እኔ ወደ ታች እስብሻለሁ፣ አንቺን ለማውረድ .. አንቺ ደግሞ ላይ ደረጃው ላይ ለመቅረት ሞክሪ።..."
ተስማማች።
ዳሪክ ገና ሳብ ሲያደረጋት ሳሌም ወረደች።
"... አሁን ቦታ እንቀያየርና ሞክሪ።..."
ተቀያየሩ። ሳሌም ዳሪክን በቀላሉ ስባ አወረደችው።
“….አሁን ገባሽ?...” ዳሪክ በፈገግታ እያያት።
“…ምንም አልገባኝም?...”
እሺ ላብራራልሽ…” ዳሪክ ጀመረ “….አየሽ ከፍታ ላይ ያለን ሰው ወደ ታች ለማውረድ ቀላል ነው። ታች ያለን ሰው ደሞ ወደ ላይ ለማውጣት ይከብዳል። አሁን አንቺ ከፍታ ላይ ነሽ። አሁን እየሄድሽ ባልሽበት መንገድ ወደ ታች የመውረድ እድልሽ ከፍተኛ ነው። እዚህ ስፍራ በመምጣት ጓደኞችሽን አትለውጪያቸውም። ይልቅስ እነሱ እየለወጡሽ ነው። ከከፍታሽ ላይ ስበው እያወረዱሽ ነው። የምወድሽ ስሚኝ ...አጋጣሚ ቢመስልም፣ ጌታ ዛሬ እኔን አንቺ ጋር ያመጣው ከጥፋት ሊያተርፍሽ ነው። ስለዚህ ጭፈራ ቤት የሰፈር ልጆች ብዙ ነገር ሲያወሩ ሰምቼያለሁ። …የምወድሽ ከከፍታሽ ላይ አትውረጂ፣ እባክሽን… ‘..የምወድሽ አትውረጂ!...’ ከዚህ አስቀያሚ ስፍራ ወደ ቤት ሂጂ…”ዳሪክ ሳሌምን ይለምናት ጀመር።
ዳሪክ እየለመናት የሳሌም ጓደኛ ካደረገቸው ጥብቆና ሂል ጫማ ጋር እየታገለች መጣች።
“…አንቺ ሴሊ ልጆች ሁሉ እየገቡ ነው ነይ እንጂ?...”
ሳሌም አንዴ ጓደኛዋን አንዴ ዳሪክን ማየት ጀመረች፦ ለምርጫ። ልሂድ፣ አልሂድ? ልግባ፣ አልግባ?
“…አንቺ ሴሊ…”ጓደኛዋ
“…አልገባም በቃ….” ሳሌም መለሰች “…ሃሳቤን ቀይሬያለሁ። ወደ ቤት ልሄድ ነው።…”
“…ምን?...” ልጅቷ ተኮሳትራ “…ለዚ ወያላ ብለሽ ነው?...”
ሳሌም የሰማችውን ባለማመን አፏንም ትላልቅ አይኖቿንም ከፍታ አፈጠጠችባት “…ምን አልሽ አንቺ?...” የምትለው ጠፍቷት ከንፈሯ ተንቀጠቀጠ። “…የምወደው ጓደኛዬ ነው። ስሙ ዳሪክ ነው። ካንቺ በጣም የተሻለ መልካም ልጅ ነው።…”
“….የምወደው?... ኢ…ው?.... ይሄንን?...” ፊቷን የሚመር ነገር የጠጣች አስመስላ ወደ ዳሪክ ደግማ ተመለከተች። ሳሌምን ጥላት ሄደች።
ሳሌም ንዴቱ እያንቀጠቀጣት ደረጃው ላይ ቁጭ አለች። የሁለቱን ንግግር በዝምታ ሲመለከት የነበረውና የተሰደበው ዳሪክ ራሱ የሷን ያህል አልተናደደም። ዳሪክ አጠገቧ ተቀመጠ። ጥቂት ዝም ተባባሉ።
“…የምወድሽ ጥሩ ውሳኔ ነው የወሰንሽው….”
ሳሌም መልስ አልመለስችም።
“…የምወድሽ…ደሞ ሁለት ቅዳሜዎች ቀረሽ። አንቺ ባትመጪም እኔ ግን ሁሌም ቅዳሜ ቀን በምናገናኝበት ሰዐት እመጣለሁ።…”
ሳሌም አሁንም ዝም።
“…የምወድሽ… ወደ ቤት….”
“…ፕሊስ….” ሳሌም አቋረጠችው።“…ማውራት አልፈልግም…” ንዴቷ ቀጠለ።ለምን እንደተናደደች ሳሌምም አልገባትም። ዳሪክ ስለተሰደበ? ጓደኛዋ ስላሾፈችባት? ዳሪክን መውደዿን ባደባባይ ፊት ለፊት ስለተናገረች? .. አይታወቅም። ሳሌም ግን ተናዳለች። በቃ ይኸው ነው።
“…የምወድሽ እኔ እኮ…”
“…በፈጠረህ... የምወድሽ!... የምወድሽ!.... አትበለኝ.. ስሜ ሳሌም ነው!.... ደሞ እንደ ታላቅ ወንድም፣ እንደ መካር መሆንህን አቁም።። እንደ ጠባቂ መልዐክ ዙሪያዬ ሆነህ ይሄ ጥፋት ነው፣ ይሄ መልካም ነው… ይሄ ከፍታ ነው፣… ይሄ ዝቅታ ነው እያልክ አትፈላሰፍብኝ።…ይህን ሁሉ ፍልስፍና በዚህ እድሜህ እንደ ሼባ ከየት እንደምታመጣው ራሱ?...”
ዳሪክ ፈገግ አለ “…ምናልባት ጠባቂ መልዐክሽ ልሆን እችላለሁ…”
ፈገግታው እየቀለደ መስሏት የበለጠ ተናደደች። “….አሁን የሚወስደኝ መኪና ስኪመጣ ዝም በለኝ… አታናግረኝ። ከፈልግክም መሄድ ትችላለህ።….” ስልኳን አወጣችና መደወል ጀመረች:- ወደ ሹፌሯ።
“…ብቻሽን ጥዬሽ አልሄድም የምወድሽ…”

👍33❤3👏1
“…መቀመጥ ትችላለህ…” ትከሻዋን እየሰበቀች። መኪናው መጥቶ ስኪወስዳት ዝም ተባብለው ቆዩ።
መኪናው መጣ። ወደ ቤት ሄደች።
ሳሌም እቤት ደረሳ፣ሰዐታት አልፈው … አልፎላት…ስታርፍ ግን ወደ ኋላ ተመልሳ ማሰብ ጀመረች። የዋህ ልቧ ለምን ዳሪክ ላይ ተናደድሽበት? ብሎ ሊጠይቃት ሲጀምር መልስ አልነበራትም። ከራሷ ጋር መነጋገር ጀመረች፦ በሃሳቧ። ምን አደረገኝ? ምን ክፉት ወጣው? ያለው ሁሉ እውነት ነው። ደሞ... ዳሪክ ሁሌም እሷን ከማሳቅ፣ ከመውደድ፣ ከክፋት ከመጠበቅ ውጪ ያደረገው ነገር የለም። የጮኸችበትን ሁኔታ ስታስበው አፍረት ተሰማት። እንደገና ደሞ ቅድም ባደባባይ ለጓደኛዋ ‘…የምወደው ጓደኛዬ…’ ብላ ስትከራከርለት በሃሳቧ መጣ። አሁን ስታስበው እንደዛ መናገሯ በውስጧ የሆነ ደስታን ነው የሰጣት። አላፈረችም። ደስ ነው ያላት።
ዝም ብላ…ዳሪክን ስለመውደድ፣ ስለ ፍቅር ማሰብ ጀመረች። ስታስብ ደስ ይላት ጀመር። ያኔ ከሳምንታት በፊት ግጥሙን ስታነብ የበቀለው የፍቅር ዘር፣ አሁን በሳሌም ልብ አድጎ ጠንካራ ችግኝ ሆኗል። ስለ ፍቅሩ ማስበ ስትጀመር ችግኙ መነቃነቅ ጀመረ። ንቅናቄውን ተከትሎም ….ደስ፣ ደስ የሚለው የፍቅር ፍሰት በውስጧ ያድግ፣ ይሰፋ ጀመር። በፍቅሩ ፍሰት ውስጥም ዳሪክ እየዋኘ ብቅ አለ፦ በልቧ ውስጥ። ። በጀርባዋ ተኝታ፣ አይኖቿን ጨፍና ሃሳቡ ዝም ብሎ እንዲፈስ ተወችው።
ዳሪክ፦ የመጀመሪያው ቀን በሷና በዱርዬዎቹ መሃከል ብቅ ሲል።
ዻሪክ፦ ቀልዶቹን ይዞ፣…ሲያስቃት …ሲያፍነከንካት።
ዳሪክ ፦ ደሞ ‘…የምወድሽ…’ ሲላት
ዻሪክ ፦ የፍቅር ግጥሙን ይዞ…
ስታዩኝ … ከዶፍ ጠብታዎች ደረጃ ገንብቼ
ስታዩኝ …ድም… ድው .. በደረቴ ይረግባል
ስታዪኝ … በብርሃን ፍጥነት
ዳሪክ ደሞ ዛሬ ፦ ‘…የምወድሽ አትውረጂ!...’ ሲላት
ዳሪክ! ….ዳሪክ! …..ዳሪክ!….ዳሪክ!....
በፍቅር ያልተነካው የሳሌም የዋህ ልቧ ዝግጁ ሆነ ፦ ለዳሪክ።
*
*
ይቀጥላል

👍27❤24🔥1
የፍቅር ‘ርግቦች
ክፍል አስራ አንድ ፦ ብቸኛ ቅርንጫፍ
©ሃሴድ አጋፔ ፍቅር
በማግስቱ ቅዳሜ በዓል ነበር። ሳሌምና ዳሪክ አልተገናኙም። ሳሌም መጠበቅ ነበረባት። ሰባት ቀናት ፦ እስከሚቀጥለው ቅዳሜ ድረስ። በ‘ነዚህ ሰባት ቀናት በሳሌም ልብ ውስጥ በቅሎ ያደገው ፍቅር ሌላ ፍሬ አፈራ ፦ ናፍቆት። ፍቅር መናፈቅ የሚባል ልጁን ወለደ፦ ሳሌም ልብ ውስጥ። ሳሌም ዳሪክን አብዝታ፣ ከውስጧ ናፈቀችው። ት/ቤት ቀኑን ፍዝዝ ብላ ታሳልፋለች፦ የምታስበው ዳሪክን ነው። ቤት ስትመጣ፣ ሰዎች ሲያወሯት ንጭንጭ ትላለች። የምትፈልገው ዝምታ ነው። በጸጥታው ውስጥ ደሞ የምታስበው አንድ ነገር ነው፦ ዳሪክን። ሌሊት ጥቂት ሰዐታት ትተኛና ትነቃለች። የመኝታ ቤቷን ኮርኒስ እያየች ማሰቧን ትቀጥላለች፦ ስለ ዳሪክ። ዳሪክ በሳቁ፣ ዳሪክ በጨዋታው፣ ዳሪክ በፍቅርት ጥሪው፣ ዳሪክ በትህትናው፣ ዳሪክ በመልካምነቱ …. በነዚህ ሁሉ የናፍቆት ሃሳቦች መናፈቅን ናፈቃት።
አይደርስ የለ የሚገናኙበት ቅዳሜ ደረሰ። ሳሌም ማልዳ ተነሳች። የተነሳችው የቤት ስራ ልትሰራ አይደለም። ወይም የምታደርገው አስቸኳይ ነገር አልነበራትም። ሳሌም የተነሳቸው ፍቅሯን ዳሪክ ከልቧ ስለናፈቀችው ነው። ዳሪክን የምታይበትን ሰዐት ጎትታ የምታመጣው ይመስል ነው፦ በጠዋት መነሳቷ። ደቂቃውን ስትቆጥር፣ የምትለብሰውን አንዱን አንስታ አንዱን ስትጥል፣ እንዲሁ ደስ ደስ፣ ዝም ብሎ ሳቅ ሳቅ ሲላት ሰዐቱ ደርሶ ወደ ቸርች ሄደች።
ዳሪክ ጊታር፣ ሳሌም ኪ -ቦርድ የሚለማመዱበት ክፍል ውስጥ ገብታ ተቀመጠች። እርጋታዋ ጠፍቶ፣ ልቧ በፍጥነት ይመታ ጀመር። ጣቶቿ ዝም ብለው በኪ-ቦርዱ ላይ እየሄዱ ቅኝት የሌለው መዝሙር ይጫወታሉ። ሃሳቧ የለም። ልቧ ውጪ ነው። አይኗ በሩ ላይ ነው። ዳሪክን ለማየት እጅግ በጣም ናፍቃለች። ልታየው ከልክ በላይ ጏጉታለች።
ልቧ አብዝቶ እየናፈቀው አስራ አምስት ደቂቃ አለፈ፦ ዳሪክ አልመጣም።
አይኖቿ በር በሩን እያዩ ግማሽ ሰዐት አለፈ፦ ዳሪክ የለም።
አንድ ሰዐት ፦ ዳሪክን የውሃ ሽታ ሆነ።
ሁለት ሰዐታት፦ ዳሪክ ብቅም አላለ።
ሶስት …አራት… ሰዐታት ዳሪክ ምናልባትም ለመጀመሪያ ጊዜ ያን ቅዳሜ አልመጣም። ዳሪክ ቀረ።
ወደ ቤት ስትሄድ ሳሌም ሌላ ሳሌም ነበረች። ክፍት ብሏታል። ስብር ብላለች። ማልቀስ ፈልጋለች። አዝናለች።
ቤት ደርሳ አልጋዋ ላይ ተዘረጋች። ማሰብ ጀመረች። አእምሮዋ ጦር ሜዳ ሆነ፦የሃሳቦች ‘ርስ ‘በርስ ውጊያ የሚካሄድበት የጦር አውድማ። መጀመሪያ ንዴትና እልህ መጣባት። እንደወደድኩት አውቆ ነው። እንዳፈቀርኩት ገብቶት ነው። አሳየዋለሁ። ልክ አስገባዋለሁ። በእልህ ዛተች።
ሰዐታት ሲያልፉ…ንዴቱ አለፍ ሲልላት ደሞ ረጋ ያለው ልቧ ሃሳቡን ያጫውታት ጀመር። ዳሪክ በፍቅርሽ ላይ የሚተብት ልጅ አይደለም። የፍቅርሽን አንድ የፈተና ጥያቄ (ለምንድን ነው የምትወደኝ?) ብለሽ ስትጠይቂው በከፍተኛ ብቃት ያለፈ ልጅ ነው።እንደወደደሽ፣ እንዳፈቀረሽ በትህትና የነገረሽ ልጅ ነው። '...የምወድሽ...' ብሎ አቆላምጦ የሚጠራሽ ዳሪክ ነው። መውደድሽን እንዴት ያውቃል? እንዳፈቀረሽው በምን ይረዳል? አልነገርሽውም እኮ። እንዳፈቀረሽ እንጂ እንዳፈቀርሽው አያውቅ? እንዴት ብሎ ይተብታል?
ሰክና ስታስበው ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ አልነበራትም።
ታዲያ ለምን ቀረ? ..ቆይታ ደሞ ሌላ ሃሳብ መጣባት። የመጨረሻው ቀን ስለ ተጣላሁት ነው። ስላኮረፍኩት አዝኖ ነው። ሳሌም ራሷን መውቀስ ጀመረች። ምን አደረገኝ? ምን አይነት መጥፎ ልጅ ነኝ?....እሱ እኔን ለማስደሰት፣ ከክፉ ለመመለስ ጥረት ባደረገና ዋጋ በከፈለ ልናደድበት አይገባኝም ነበር። ሳሌም ከራሷ ጋር እያወራች፣ ያጠፋች መሆኗን ውስጧ እያመነ ሲመጣ ዳሪክን ይቅርታ ለመጠየቅ ከልቧ ፈለገች። እንዴት አግኝቼው ነው ይቅርታ የምጠይቀው ብላ ስታስብ ደግሞ ሌላ ትልቅ ፈተና ሆነ። ሳሌም ዳሪክን ብዙ አታውቀውም። በአንድ የሴልፎን ክሊክ የምታገኘው፣ የምትደውልለት የት/ቤት ጓደኛዋ አይደለም። ስልክ የለውም። ቤቱ የት እንደሆነ መረጃ የላትም። ሌላው ቢቀር የአባቱን ስም እንኳን አታውቀውም። እስከ ዛሬ ዳሪክን የምታገኘው እሱ ራሱ ስለሚመጣ ነው። እሱ እሷ ያለችበትን ቤትና የምትገኝበትን ቦታ ያውቃል እንጂ እሷ አታውቅም። ከፈለገ ዳሪክ መጥፋት ይችላል። '...ከዛሬ ጀምሮ አልመጣም፣ሳሌምን ማየት አልፈልግም..' ብሎ ከወሰነ ሳሌም ዳሪክን ለማግኘት የምትችልበት መንገድ አልታይ አላት። ስታስበው ሃሳቡ ራሱ ፍርሃትን ለቀቀባት። በህይወቷ ለመጀመሪያ ጊዜ ልቧን ያሸነፈው ወጣት፣ ያፈቀረችው ልጅ እልም ብሎ ሲጠፋባት ማሰቡ ራሱ በጣም አስፈራት። ….ናፍቆቱ በዚህ በኩል…ዳሪክን የማጣት ፍርሃት በሌላ በኩል…ሁለት ሃሳቦች ሲያንገላቷት፣ ከዚህ ወደ ዚያ ሲቀባበሏት የሌሊቱ አብዛኛው ክፍል አለፈ። በሃሳቦቹ ማዕበል ውስጥ አንድ ሃሳብ ለልቧ ሹክ አላት። ዳሪክ ያለበት ድረስ ሄዳ ማግኘት።
“…ማግኘት አለብኝ!.. ዳሪክን ማየት አለብኝ!...” ለራሷ በራሷ አወራች። ስለ ዳሪክ የምታውቀው አንድ ነገር ሰፈሩን ነው። ነገ ሰፈሩ ድረስ ሄጄ አገኘዋለሁ። አየዋለሁ። ወሰነች። ከወሰነች ቡሃላ ተረጋግታ ተኛች። እንቅልፍ ወሰዳት።
በማግስቱ ከቸርች በፊት ሳሌም እግሯ ወደ መራት፣….ወሎ ሰፈር ከዳሪክ ከሰማችው …የዳሪክ ሰፈር ነው ብላ በምታምንበት መንገድ መጓዝ ጀመረች። ወደ ውስጥ ጥቂት እንደሄደች የማታውቀው ሰፈር ሁኔታው፣ የምታያቸው ልጆች፣ የሚለክፏት መጨመራቸው ትንሽ ቢያስፈራትም ዝም ብላ መሄዷን ቀጠለች…ወደፊት። በአንድ ሱቅ ጋር ሰብስብ ብለው በተሰበሰቡ ወጣቶች አጠገብ ስታልፍ “…ቆንጆ…” አንዱ ጠራት።
ሳሌም ሌላ ለካፊ ነው ብላ ልታልፍ ስትል “…የአቡቲ ጀለስ፣ ቺኳ…”
ሳሌም የዳሪክን የሰፈር ስም ስትሰማ ቆመችና ዞር ብላ የሚጠራትን ልጅ ስታይ እየሮጠ ወደሷ መጣ።
“…አረፍሽኝ እሙ?...”
“…ምን? ምን አልከኝ?...”
“…አወቅሽኝ ማለቴ ነው?...”
ሳሌም አይታው አታውቅም። ወይም ረስታዋለች። “…ይቅርታ አላወቅኩህም…”
“…ቦዲ ነኝ እኮ… አንድ ቀን ምሽት ላይ…መንገድ ላይ…..”
ሳሌም ትዝ ሲላት በድንጋጤ ወደ ኋላ አፈገፈገች።
“..አይዞሽ ቀሽት አልነካሽም። የአቡቲ ጀለስ ስልሆንሽ እዚ ሰፈር ማንም የሚነካሽ የለም።ያኔም ስላላወቅን ነው። እኛ የሰፈር ልጆች አንነካም። ሌላውንም ቢሆን ሲቸግረን ነው እንጂ የምናስፈራራው.... ግን ማንንም አንጎዳም።…” ቦዲ ልስልስ ብሎ
ሳሌም በጥቂቱ ተረጋግታ ስትሰማው ቦዲ ቀጠለ “…ለማንኛውም ምን ፈለገሽ መሀል ወሎ ሰፈር ከች አልሽ? አቡቲን ፈልገሽው ነው?....”
ሳሌም የጥያቄዋ መልስ ፊት ለፊቷ ሲመጣ ድንጋጤው ለቀቃትና “…አዎ ዳሪክን በጣም ላገኘው ፈልጌ ነው። ቤቱን ታውቀዋለህ?...”
“…ታውቀዋለህ?...” ፈገግ አለ።ቦዲ ፈገግ ሲል ሸራፋ ጥርሱ ወጣ። “…ጎረቤት ነን እኮ አቡቲ ማለት …”
“…ታሳየኛለህ?.. ሳሌም አቋረጠችው
“…ሰፈራችን እኮ ታች ነው…ትንሽ ይርቃል። ... አሁን እንኳን የጀበና ልል ነበር…” ቦዲ እየተጠራጠረ
“…በጌታ? ባ'ክህን አሳየኝ?...” ሳሌም በልመና አይን
ቦዲ ሲያመነታ ሳሌም አጥብቃ ልመናዋን ቀጠለች።
ልመናዋ ሲበረታና ሲያዝን...ቦዲ ወደ ጓደኞቹ ዞረ። “…ጠብቁኝ አንዴ አቡቲ ጋር አድርሺያት መጣሁ።…”
“… እሺ እሙዬ እንሂድ …” ቦዲ መሄድ ሲጀምር ሳሌም ተከተለችው።
እየሄዱ ቦዲ ወሬ ጀመረ። ሳሌም ዙሪያዋን እያየች ትሰማለች …በግማሽ ልብ።

👍43❤5
“…አቡቲ ሰፈሩ በሙሉ የሚያከብረው ልጅ ነው።…ሜጋ… ማለቴ ጎበዝ ተማሪ ነው…” በአንድ መስጊድ አጠገብ እያለፉ
“…ከአንድ እስከ አሰረኛ ክፍል አንደኛ እየገጨ እየተሸለመ አስረኛ ፈተናን ሰቅሎ ያለፈ ልጅ ነው…” በቤቶች መሃል በተሰጡ ልብሶች ስር ሲሄዱ።
“…በቃ ምን ልበልሽ የሰፈራችን ተስፋ ነው። ይሰራል፣ ይማራል፣ ልጆችን ሰብስቦ ያስጠናል። የኔ ትንሽ ወንድም ራሱ የመጨረሻ ጎበዝ ተማሪ ሆኗል…አቡቲ እያስጠናው።…” ተጠባብቀው በተሰሩ ትንናሽ ቤቶች ባለ ቀጭን መንገድ ከፊትና ከኋላ እየሄዱ
ጎማ ደርድረው ላዩ ባለ ፕላስቲክ ማጠቢያ ልብስ በሚያጥቡ ሴቶች መሃል፣ ኳስ በሚራገጡ ትናንሽ ህጽናትን ከፍለው፣ ቁልቁለት ሲወረዱ፣ ቦዲ ከሚያወራው ግማሹን እንኳን የሰማችው አትመስልም፦ ሳሌም። ዙሪያውን፣ ሰፈሩን የምታልፍበትን መንገድ፣ ሰውን እያየች ነበር።
“…ሰማሽኝ እሙ?...” ቦዲ እየጠየቃት ነበር
“….ምን አልከኝ?... ይቅርታ አልሰማሁም…”
“….አቡቲን ልትጠይቂው ነው አይደል የመጣሽው? ሰለ ታመመ?...”
“…ምን?....” ሳሌም ባለችበት በድንጋጤ ቆመች “…ዳሪክ ታሟል። መቼ ነው የታመመው? ምን ሆኖ ነው?....”
“…አንድ ሳምንት ነገር ሆኖታል። አሞት ተኝቷል ሲሉ ነው የሰማሁት። እኔ ራሴ አልጠየኩትም። ያወቅሽ መስሎኝ ነው እሙ…”
ሳሌም ድንጋጤዋ አለፍ ሲልላት ጉዟቸውን ቀጠሉ። አሁን ገና ለምን ዳሪክ ትላንት እንደቀረ ገባት።
በዝምታ...መጨረሻ ላይ አንዲት ትንሽ ያዘዘመች የአፈር ቤት ጋር ደርሰው፣ ደገፍ ተደርጎ የተዘጋን የሚንፏቀቅ፣ በጣውላ ተገጣጥሞ የተሰራን በር ከፍተው እስኪገቡ ድረስ አልተነጋገሩም።
ሳሌም እዛ የተጎሳቆለ ቤት ውስጥ ስትገባ አይኗ ያረፈው በቀኝ በኩል ግድግዳው ጥግ መሬት የተነጠፈ ፍራሽ ላይ የተኛው ዳሪክ ነው። አጠገቡ ሄዳ በርከክ አለችና "...ዳሪክ..."ጠራችው
ዳሪክ በሩ መከፈቱን ሲያይ ቀና ብሎ የገባውን ሰው ለማየት እየተጋለ ነው። ፊቱ ጭው ከማለቱ በሙሉ በላብ ተጠምቋል። እንደገናም ሰውነቱ ይንቀጠቀጣል። ለመነሳት ራሱ አቅም አጥቶ፣ መሬቱን ተደግፎ፣ ጥርሱን ነክሶ ሲታገል ቦዲ ደግፈው። ፍርሹ ላይ ሆኖ፣ በግማሽ የፈራረሰውን ግድግዳው ተደግፎ ቁጭ አለና ሳሌምን ያያት ጀመር።
“…የምወድሽ?...” እጁን ዘረጋ።
እጁን ጨበጠችው። ሰውነቱ እሳት ነው። “..አቤት..”
“…ይቅርታ ዛሬ ሰለቀረሁ። ለመምጣት ሞከርኩ ዛ…ሬ….” ዳሪክ ቃላት የጠፉበት ይመስል ዙሪያውን ያይ ጀመር።
ዳሪክ ትላንት ማለቱ ነው። ቀኑ ተምታቶበታል። ትኩሳቱ ከፍ ብሎ በመንቃትና ቅዥት አለም ውስጥ ነው።
ሳሌም ነፍሷ ተንሰፈሰፈ። “….ምን ያህል ጊዜ ሆነው እንዲህ ከታመመ?...” ወደ ቦዲ ዞረች
“…እኔ አላውቅም። ሳምንት ይሆነዋል። የሰፈር ሰዎች ሲያወሩ ነው የሰማሁት።…”ቦዲ ራሱ የዳሪክ ሁኔታ አስደንግጦታል።
እነሱ ሲያወሩ ዳሪክ በሰመመን ቁጭ ባለበት እንደ ማሸለብ አደረገው።ስላልቻለ ፍራሹ ላይ ተመልሶ ተኛ።
….ዳሪክ …ዳሪክ ….ዳሪክ ….” ብትጠራውም አይኑን እየከፈተ መልሶ ከማሸለብ በስተቀር ሊመልስላት አልቻለም።
“…አሞታል። በጣም ታሟል። አሁኑኑ ሃኪም ጋር ልንወስደው ይገባል።….” ሳሌም ነበረች “… ቤተሰቦቹን መጥራት አለብን…”
“…አታርፊም እንዴ? …” ቦዲ ተገርሞ
“…ማለቴ አታውቂም እንዴ?...”ሳሌም ስታፈጥበት ጥያቄውን አስተካከለ።
“…ምኑን?....”
ለሰከንዶች ዝም ብሎ ተመለከታት። “…የአቡቲ ወላጆች ሞተዋል። ቆይተዋል።…”
ሳሌም ሌላ ድንጋጤ ሰውነቷን ወረረው። “…አላወቅኩም …ወንድም?... እህት… የለውም?...” ጠየቀች።
“…የለውም…” ቦዲ በሀዘኔታ “…አንድ ራሱ ብቻውን ነው የሚኖረው…”
ዝም ብሎ የሚስቀው ዳሪክ፣ ሁሌም ደስታ ፊቱ ላይ የሚፈስበት ዳሪክ ብቸኛ ነው። ማንም የለውም። ብቻውን እዚች ትንሽ ቤት ውስጥ ይኖራል።
ሳሌም ወደ ዳሪክ እያየች እንባዋ በአይኗ ሞላ።
እንባ በሞላው አይኗ ቀና ብላ ቦዲን አየችው “…ታክሲ ጥራልኝ…” ከቦርሳዋ ውስጥ ለማንኛውም ብላ ከምትይዘው ብር አወጣችና ሰጠችው “…ሃኪም ጋር አሁኑኑ እንወስደዋለን።…”
ቦዲ ተስማምቶ ተጣድፎ ወጣ።
ታክሲው እስኪመጣ ድረስ ሳሌም ዳሪክ ያለበትን ቤት ዙሪያ ማየት ጀምረች። መሬቱ ሙሉ ለሙሉ አፈር ነው። ዳሪክ ከተኛበት በስተቀኝ በኩል ሁለት ወንበሮችና አንድ ጠረጴዛ አለ፦ ሁሉም ያረጁ ናቸው። በጠረጴዛው ላይና ዙሪያውን የተለያዩ የትምህርትና ሌሎች መጻህፍቶች ተደርድረዋል። ግድግዳው ላይ ዳሪክ እየሳቀ ከወላጆቹ ጋር በልጅነቱ የተነሳው ፎቶ ባንድ በኩል አለ። በሌላ በኩል የሁለት መሃከለኛ እድሜ ላይ የሚገኙ ፈረንጆች ተቃቅፈው የተነሱት አነስተኛ ፎቶ ይታያል። የቤቱ አንድ ጥግ በያቅጣጫው በተቦጫጨቀ መጋረጃ ተከልሏል። ከመጋረጃው ጀርባ ያረጀ መሶብ ተቀምጦ ዙሪያውን በተለያዩ የማብሰያ እቃዎች ታጅቧል። የጠቆረው ጣሪያ ደግፎ በያዙት እንጨቶች ላይ የተንጠለጠለ ፍሎረሰንት በኤሌክትሪክ ገመድ ከማብሪያና ማጥፊያው ጋር ተያይዞ ይታያል። በእርጅና የተበሳሳው ግድግዳ በተለያዩ ጋዤጦች ተለጣጥፏል። ይህ የዳሪክ ቤት ነው። ዳሪክ ብቻውን የሚኖርበት ትንሽዬ ክፍል።
ታክሲው መጥቶ ቦዲና ጓደኞቹ ደግፈው ሲጭኑት ራሱ ዳሪክ ከትኩሳቱ፣ አቅም ከማጣቱ የተነሳ በድካምና በ’ንቅልፍ መሃል ነበር። በየመሃሉ ብቻ ከንቅልፉ ወጣ እያለና ሳሌም እያየ ‘…የምወድሽ…’ ይላል።
ሃኪም ቤት ደርሶ ሲታከም ዳሪክ የያዘው ቀላል ኢንፌክሽን ነው። ነገር ግን ህክምና በጊዜ ባለማግኘቱ ብቻ ደሙ ድረስ ተበክሎ ነበር። ጸረ-ባክቴሪያ መድሃኒቶችና በተለምዶ ጉልኮስ የሚባለው ፈሳሽ ሲሰጠው ትኩሳቱ እየቀነሰ ማምሻውን ደህና መሆን ጀመረ።
ዳሪክ ብዙ ድካም ላይ ስለነበረ እዛውም ማደር ስለነበረበት…ሳሌም አምሽታ ወደ ቤት ሄደች።
በማግስቱ ከት/ቤት መልስ ልታየው ስትሄድ ዳሪክ ተመልሶ ዳሪክን ሆኗል። ሳቅ በሳቅ ሆኖ ጠበቃት። እንደለመደው…እንደ ሁልጊዜው እየቀለደ፣ እያሾፈ ሁለቱም ሲስቁ አመሹ።
ሳሌም ወደ ቤት ልትሄድ አካባቢ አጠገቡ ቁጭ ብላ “..ዲ…”
“…አቤት የምወድሽ…”
“…ብቻህን ነው ግን የምትኖረው? ቤትህ ውስጥ?...”
ዳሪክ ትክ ብሎ አያትና “…አዎ ብቻዬን ነው።…”
"..ወላጆችህ እንደሞቱ ነገሩኝ። ወንድም፣ እህት ዘመድ ምናምን የለህም?...”
ዳሪክ መልስ ሳይመልስ ዝም ብሎ ሲያያት ቆየ። በመቀጠልም ራሱን ግራና ቀኝ አወዛወዘና ወደ ግድግዳው ዞረ።
ሳሌም ከተቀመጠችበት ተንጠራርታ ስታየው እንባው አይኑ ውስጥ ሞልቷል።
“…ይቅርታ!.. በቃ ሌላ ወሬ እናውራ እሺ…. ይቅርብን ይሄን ነገር ማውራት….” ሳሌም በጸጸት
“…ችግር የለውም የምወድሽ ላንቺ የውስጤን ማውራት እፈልጋለሁ።….” ዳሪክ እንባውን ጠራረገና ማውራት ጀመረ።
“….የምወድሽ…. አዎ እኔ ብቻዬን ነኝ። ወንድም፣ እህት የለኝም። ወላጆቼ ሞተዋል። የመጡት ከገጠር ነው። የመጡበትን አካባቢውን እንኳን አላውቀውም። ያስተዋወቁኝ አንድ የማውቀው ዘመድ የለም። ካያቴ ስም በላይ አላውቅም። ተከታትለው ሲሞቱም የነገሩኝ ነገር የለም። ከነሱ የቀረልኝ ሁለት ነገር ነው፦ አቡቲና ዳሪክ። አቡት እናቴ የምትጠራኝ ስም ነው። ዳሪክ ደሞ አባቴ። በቃ የቀሩኝ እነዚህ ስሞች ናቸው።ብቻዬን ነኝ። ብቻዬን እኖራለሁ። ብቻዬን ህይወትን እታገላለሁ።….”

👍33❤7👎1